Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
መፅሀፋ በገበያ ላይ ዋለ !!
አዲስ አበባ ባሉ ኪታብ ቤቶች ማግኘት ይችላሉ ክፍለ ሀገርም ያሉ ነጋዴዎች ጋር እየተዳረሰ በመሆኑ አቅራቢያችሁ በሚገኝ ኪታብ ቤት በመጠየቅ እንዲያስመጡላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ

ከሀገር ውጪ ያላችሁ ብዛት የምትፈልጉ በዚህ ቁጥር አናግሩት ይልክላችኋል
¶ 0925504315 ሙሀመድ ሰዒድ
አስደሳች ዜና

ማንኛውንም የተውሂድ ፣ የሱና ፣ ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋቶችን እና የሰለፎችን ታሪክ የሚዳስሱ መፅሀፎችን ውጪ ሀገር ለምትኖሩ ወንድምና እህቶች በብዛት መላክ ጀምረናል።

ዱባይ፣ኩየት፣ሳኡድአረቢያ፣ኳታር፣
አሜሪካ፣እንግሊዝ እንዲሁም በሌሎች ሀገሮችም ጭምር እንልካለን።

ጀመአ ጀመአ በመሆን አንድን ሰው በመወከል ይዘዙን ባሉበት ቦታ እንልካለን።

በዚህ ስልክ ቁጥር ያናግሩን
በዋትስአፕም በቴሌግራምም
በኢሞም ያገኙናል
👇👇👇👇
+251925504315
+251925504315
ሙሐመድ ሰኢድ
መውሊድን ስንቴ ነው የሚያከብሩት?
የአፊንጮ በሩ አል-አቅሳ መስጊድ?

እንደሚታወቀው በኢስላም ሁለት አመታዊ በዓል ተደንግገውልናል፡፡ እነሱም ኢድ አል-ፊጥር እና ኢድ አል-አድሃ ናቸው፡፡ በኢስላም ላይ አላህ እና ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላዘዙበት፡፡ ሰሃባዎች፣ አራቱ አኢማዎች፣ ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ቲርሚዚ፣ ኢብን ማጃ እና ሌሎችም ሙሐዲሱች የማያውቁት እና ያልሰሩት፡፡ ከአራት መቶ አመት በኋላ ሺአዎች የጀመሩትን “መውሊድ (ነብዩ ሙሐመድ የተወለዱበትን ቀን ረቢአል አወል 12 ብለው ማክበር)” ተጀመረ፡፡ ይህ ፅሁፍ ኢስላም የማያውቀውን መውሊድን ስንቴ ነው የሚያከብሩት? የሚል ይሆናል፡፡ የሚገርመው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተወለዱበት ቀን በኡለማዎች መሃል ልዩነት አለ፡፡ የሞቱበት ግን በቁርጥ ረቢአል አወል 12 ነው፡፡

እነዚህ ሰዎች የሚያከብሩት የሞቱበትን ወይንስ የተወለዱበትን?
ያሳለፍነው እሁድ አዲስ አበባ አፊንጮ በር አካባቢ የሚገኘው አል-አቅሳ መስጂድ መውሊድ ተከበረበት፡፡ 17 ረጀብ 1440 ሒጅራ አቆጣጠር ማለት ነው፡፡ ጥያቄው እነሱ ዘንድ “መውሊድ” የሚሉት በአል በወቅት የተገደበ አይደለምን? በአመት ስንት ጊዜ ነው የሚከበረው? ለምን ይሆን ከአምስት ወር በኋላ ደግመው ያከበሩት?

ሁለቱ በኢስላም የተደነገጉት ኢዶች (ኢድ እና አረፋ) በቀናቸው ነው የሚከበሩት፡፡ ይሀው ኢስላም የማያውቀው፣ የሺርክ መነሀሪያ፣ የጭፈራ እና የመደለቂያ ፈጠራ (ልደት ማክበር) ከመጣ በኋላ በተለይ በሀገራችን ይህን ሁሉ ውዥንብር እያየን ነው፡፡ ረቢአል አወል አስራ ሁለትን አልፈው ከአምስት ወር በኋላም ጭፈራ፣ መብላት መጠጣታቸውን ለመወጣት ያከብሩታል፡፡ መቼም የቢድኣ (ዲንን የማፍረስ) አባዚ የተጠናወተው በአንድ ቢድኣ ላይ አይቆምም፡፡ ይሀው አንዷ ቢድኣ ቀን አልበቃቸው ብላ ያችኑ ቢድኣ በተለያየ ቀን ያጨማልቋታል፡፡

በሀገራችን የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደት የሚሉትን ብቻ አይደለም የሚያከብሩት፡፡ ይልቁንም የአብሬት መውሊድ፣ የቃጥባሬ መውሊድ፣ የዳንግላው መውሊድ….. የመሳሰለውን እየተባለ በተለያየ ቀናት አመቱን ሙሉ የሺርክ እና ክህደት ስንኞች ይዜማሉ፣ ሴት እና ወንድ ተደብልቀው ይጨፈራል፣ ይህ መርዝ አደገኛ ቅጠል ጫት ይታኘካል፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት የለውም)” ብለዋል፡፡ መውሊድ አላህም መልክተኛውም አላዘዙበትም፡፡

ከሁሉ የሚገርመው እዚሁ መስጂድ ላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ቂርኣት መቅራት ጀምረው ነበር፡፡ ግን ተከለከሉ፡፡ አህባሽን መስጂድ ውስጥ የሚያስጨፍር፣ ተማሪዎችን ቂርኣት የሚከለክል ኡለማ፣ ባለሃብት እና ኮሚቴ ነገ አላህ ፊት ምን ይሆን መልሱ?

ያሳዝናል መስጂዱ በስንት መከራ እና መስዋትነት እንደተሰራ የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ዛሬ ግን ቂርኣት ተከልክሎ መውሊድ የሚደለቁበት መስጂድ ሆኗል፡፡ አላህ ተውሒድ እና ሱና የበላይ የሚሆንበትን፣ ሺርክ እና ቢድኣ የሚዋረድበትን ወቅት ያቅርብልን፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ዘረኝነት?
ማንም ከማንም አይበልጥም፣ ማንም ከማንም አያንስም አላህን በመፍራት ቢሆን እንጂ፡፡

ነብዩ (ﷺ) ከመሞታቸው በፊት ስለ ዘረኝነት አስከፊነት መክረውን ነበር፡፡

“አረብ እኮ አረብ ባልሆኑት ላይ ብልጫ የለውም፣
አረብ ያልሆነውም በአረብ ላይ ብልጫ የለውም፡፡
ነጭ (ፈረንጅ) በጥቁር ላይ ብልጫ የለውም፣
ጥቁርም በነጭ ላይ ብልጫ የለውም
አላህን በመፍራት ቢሆን እንጂ፡፡”

የአላህ ውድ፣ ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) እንዲህ በሽታችንን ሁሉ ግልፅልፅ አድርገው ነግረውናል፡፡ መድሃኒቱንም ነግረውናል፡፡
ለሚመከር ከነፍሱ በላይ የሆኑ መካሪ ናቸው፡፡ አላህ ጀነት ላይ የእኝህ ውድ መካሪያችን ጎረቤት ያድርገን፡፡

አላህ ሀገራችንን ከዘረኝነት የፀዳች፣ አላህን በመፍራት ላይ የተገነባች ያድርጋት፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
122 ሀዲሶች ለመሀፈዝ
رَوْضَةُ الْبَادِئِينَ
محمد بن على بن حزام البعداني
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በሙሐመድ፣ በባልደረባዎቻቸው፣ በባለቤቶቻቸው እና ሐቅን በተከተሉ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ ነብዩ (ﷺ) “አላህ መልካም የሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል” ብለዋል፡፡ ይህችን አጭር ኪታብ “የጀማሪዎች ጨፌ” በመባል ትታወቃለች፡፡ በአምስት ታላላቅ አርእስቶች የተከፋፈለች ናት፡፡ አርእስቶቹም በስራቸው ከያዟቸው ሀዲሶች ጋር እንደሚከተሉት ናቸው፡፡ ከአቂዳ ጋር የተያያዙ ሃያ አምስት ሀዲሶች፣ ከፊቅህ ጋር የተያያዙ ሃያ ሀዲሶች፣ ከከባባድ ወንጀሎች እና ከሀራም ጋር የተያያዙ ሃያ ስድስት ሀዲስች፣ ከስነ-ስርዓት ጋር የተያያዙ ሰላሳ አራት ሀዲሶች፣ ከዚክር እና ከዱኣ ጋር የተያያዙ አስራ ሰባት ሀዲሶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ አንድ መቶ ሃያ ሁለት የነብዩ (ﷺ) ሀዲሶች የያዘች መፀሀፍ ናት፡፡ ለመሸምደድም፣ ለመማር ማስተማርም በጣም ጠቃሚ ሆና አግኝቻታለሁ፡፡ ስለዚህም በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ለህትመት በቅታለች፡፡ ውድ ኡስታዞች ሆይ! ተማሪዎቻችሁን እንዲሸመድዷት ገፋፉ፣ ትርጉሟንም በየቋንቋው ለማህበረሰባችን በደንብ አብራሩ፡፡ በየመርከዙ እና በየመድረሳው በትምህርትነት ብትሰጥ በአላህ ፍቃድ በጣም ጠቃሚ ትሆናለች፡፡ ይህ ህዝብ የዱንያውም ይሁን የአኸይራው ጉዳይ የሚስተካከለው ስለ ኢስላም ጠንቅቆ ሲማር ነው፡፡ አላህ እውቀትን ይጨምርልን፣ ዲኑን ያስገንዝበን፣ መሀይምነትን ያንሳልን፣ መጨረሻችንን ያሳምርልን፣ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፡፡ አሚን፡፡
ኪታቡን ከሚከተሉት ሊንኮች ያውርዱ እና ለሌችም ሼር ያድርጉት
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/1705
https://t.me/Kitaboch/198
ሱዳን ላይ ከዳቦ መወደድ እና ከሺርኩ የቱ ይብሳል?

ሱዳኖቹ ዳቦ ተወደደ ብለው ህይወታችውን አደጋ ላይ ሲጥሉ፣ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ምን ብለው ነበር?

قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مَنْ أَصْبَحَ مِنْكُمْ آمِنًا فِي سِرْبِهِ مُعَافًى فِي جَسَدِهِ عِنْدَهُ قُوتُ يَوْمِهِ فَكَأَنَّمَا حِيزَتْ لَهُ الدُّنْيَا
የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ አሉ “ከእናንተ ውስጥ በመኖሪያ ቤቱ (አካባቢው፣ ቤተሰቡ….) ሰላም ሆኖ፣ ሰውነቱ (አካሉ) ጤነኛ ሆኖ፣ የእለት ቀለቡ ያለው ሆኖ ያነጋ (ያደረ) ሰው፣ (ይህ ሰው) ለእርሱ ዱንያ እንደተሰበሰበችለት (የእሱ እንደሆነችለት) ነው፡፡” ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሀሰን ብለውታል 2346

ተመልከቱ በመላው አረብ ሀገራት ላይ “ኑሮ ተወደደ” እያሉ የተከበረውን ጁምዓ ቀን ለነሱ ከኢስላም ጋር ምንም ግንኙነት ለሌለው ፖለቲካዊ ሰልፍ ይጠቀሙበታል፡፡ እርጉሙ አልጀዚራ ያቀጣጥልላቸዋል፡፡ አስገራሚው ግን የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ከላይ እንዳየነው አንድ ሰው ምን ሲሟላለት ዱንያ ለእሱ የተሰበሰበችለት እንደሆነ ጠቀሱ
- ሰላም ሆኖ በመኖሪያው ያነጋ፣
- ሰውነቱ ጤነኛ ሆኖ ያነጋ፣
- የእለት ቀለቡ ያነጋ ሰው
* ዱንያ ለእሱ እንደተሰበሰበችለት ነው ብለው ተናገረው ሲያበቁ ፖለቲከኞቹ ሰልፍ ወጪዎች አንሰማም “ዳቦ ተወደደብን” በሚል ህይወት ለመጥፋት ሰበብ የሆኑ ሰልፎች ተካሄዱ፡፡
አስገራሚው ሱዳን ላይ ከዳቦው ጉዳይ በላይ በአላህ ላይ የሚያጋሯቸው ስንት እና ስንት ቀብሮች አሉ፣ ስንት እና ስንት ጠንቋይ እና ድግምተኞች አሉ፡፡ ይህ ሁሉ “ዳቦ ተወደደ” ለሚሉት ፖለቲከኞች ደንታቸው አይደለም፡፡
አላህ ደግሞ እኛ እራሳችንን እስካልቀየርን ድረስ ምንም እንደማይቀይርልን ነገሮናል፡፡
አላህ በቁርዓን እና በነብዩ አስተምህሮት ከሚመከሩት ያድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
"አረብ ስፕሪንግ" ከእስልምና ሀይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።

በየ አረብ ሀገራቱ ከፍጡራን መብት በላይ የአላህ መብት ተገፎ
– ከአላህ ውጭ ለፍጡራን ይሰገዳል፣ ፍጡራን ይለመናሉ፣ ለፍጡራን እርድ አምልኮ ይፈፀማል፣ በፍጡራን ላይ ይመካሉ፣ የፍጡራንን ቀብር ይጠውፋሉ፣ የቀብር አፈር ይቅማሉ በጥብጠው ይጠጣሉ፣ በፍጡራን ይምላሉ …
– የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ትተው መውሊድ፣ ረጀብ፣ ሸእባን … እያሉ ዲኑን ከውስጥ ሆነው ይንዳሉ፣
– ሴቶች አላህ የተረገመበትን ቅንድብ ይቀነደባሉ። አለባበሳቸውም ከእለት እለት ከዲን ያፈነገጠ ሆኖዋል፣
– ወንዶች በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ወድቀዋል፣
ይህ ሁሉ በደል እራሳቸው እየፈፀሙ "መሪ በደለን" ብለው ወንድ እና ሴት ተደባልቀው አደባባይ ወጡ። በዚህም ምክንያት
– ሀገራቸውን አወደሙ፣ አፈረሱ፣
– የሰው ህይወት ጠፋ፣
– ስደት ተስፋፋ፣
– ሴቶች ተደፈሩ፣
– ህፃናት ከአቅማቸው በላይ የሆነ ከባድ እንግልት ደረሰባቸው፣

ምንም እንኳን ጁምኣ ቀንን ለፖለቲካ አላማቸው ቢጠቀሙ፣ መፈክሮቻቸው ላይ "አላሁ አክበር፣ ላ ኢላሃ ኢለ አሏህ… …" ስላሉ፣ እዛው አደባባይ ላይ ሰላት ስለሰገዱ በፍፁም ሀይማኖታዊ ሊሆን አይችልም። እውነት ለኢስላም እና ለሙስሊሞች ቢሆን ኖሮ ትግላቸው ነብያት እንደለፉት ሰዎችን ዘላለም ጀሀነም እሳት ውስጥ የሚያከርመውን በአላህ ላይ ማጋራት ከምንም ነገር በፊት ቀድመው ይዋጉት ነበር።

ለዚህ ሁሉ ደም መፍሰስ፣ ስደት፣ ሀገር መፍረስ ይህንን የፖለቲካ አካሄድ ሀይማኖታዊ ቅብ እየቀቡ ወጣቱን ሲያነሳሱ የነበሩ የጠመጠሙ የሰው ሰይጣናት፣ አልጀዚራ የተባለው የቴሌቭዥን ጣቢያ ባለቤቶች፣ አሰራጮች አላህ ዘንድ ተጠያቂ ይሆናሉ። አላህም አያያዙ የበረታ ነው።

አብዛኛው ሰው በተለይ አላዋቂዎች "አላሁ አክበር" በተባለ ቁጥር ሁሉ ነገር ኢስላማዊ እና ለኢስላም የሚመስላቸው ስንት ምስኪኖች አሉ። አረብ ሀገራቱ ላይ "አ ሻእብ ዩሪድ… " ሲባል የነበረው ምንም የሀይማኖታዊ ሽፋን ሊሰጠው ቢሞክርም ከሀይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ፖለቲካ ነው።

ለእኛ አዛኝ የሆኑት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሙስሊም መሪዎችን አስመልክቶ "ገንዘባችሁን ቢቀሟችሁ፣ ቢደበድቧችሁ… ሰላትን እስከሰገዱ ድረስ ስሟቸው ታዘዟቸው።" ብለው በጥብቅ አዘው ነበር። ምክንያቱም ሙስሊም መሪን አለመታዘዝ ምን ያህ አደጋ እንደሚያስከትል ወህይ (መለኮታዊ ራእይ) የማይለያቸው ታላቁ ነብይ በግልፅ ነግረው ነበር። ነገር ግን የሰው ሰይጣናት ይህን ግልፅ የሀዲስ መልክት በማዛባት የሙስሊሙን ኡማ ጌታውን አላህ እንዲያምፅ፣ የነብዩን ሱና እንዲቃረን በመልፋት አብዛኛው ሰው አጠመሙ።
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሸሪአዊ እውቀትን ማካበት በሰው ሰይጣናት ወጥመድ ውስጥ ከመግባት ለመጠበቅ ትልቅ ሰበብ ነው። የነብዩን ሀዲስ እንማረው ለቢድአ ሰዎች ታላቁ እራስ ምታት የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሀዲስ ነው። እንማረው፣ እንስራበት፣ እናስተምረው።

አላህ ሁላችንንም ለሱና እጃቸውን ከሚሰጡት ያድርገን።
https://t.me/SadatTextPosts
ለፆመኛ የሚወደዱ ነገሮች፡-
1. ሰሑር መመገብ፡- ነብዩ ﷺ “በኛና በመፅሐፉ ሰዎች መካከል ያለው ጾም መበላለጫው የሱሑር ምግብ ነው” ብለዋል፡፡ [ሙስሊም፡ 1096]
2. ሰሑርን ተምር ማድረግ፡- ነብዩ ﷺ “ተምር ምን ያማረ የሙእሚን ሰሑር ነው” ብለዋል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 562]
3. ሰሑርን ማዘግየት፡- ነብዩ ﷺ “ሶስት ነገሮች ከነብያዊ ተግባራት ናቸው፡፡ ፊጥራን ማፋጠን፣ ሰሑርን ማዘግየት እና በሶላት ላይ ቀኝ እጅን ግራ ላይ ማድረግ ናቸው፡፡” [አልጃሚዑ አስሶጊር፡ 5349]
4. ፊጥራን ማፋጠን፡- ነብዩ ﷺ “ሰዎች ፊጥራን እስካቻኮሉ ድረስ ከኸይር አይወገዱም” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
5. ሰሑርና ፊጥራን በልክ ማድረግ፣
6. በእሸት ተምሮች ማፍጠር፣ ካልተገኘ በበሰሉ ተምሮች፣ ከሌለ ውሃ መጎንጨት፡- “ነብዩ ﷺ ከመስገዳቸው በፊት በእሸት ተምሮች ያፈጥሩ ነበር፡፡ እሸቶች ከሌሉ በተምሮች፣ እነሱም ከሌሉ ውሃ ይጎነጩ ነበር፡፡” [አስሶሒሐህ፡ 2056]
7. ከፊጥራ በኋላ የሚከተለውን ዱዓእ ማድረግ፡- “ዘሀበ’ዝዞመኡ፣ ወብተልለቲል ዑሩቁ፣ ወሰበተል አጅሩ ኢንሻአላህ፡፡” አልባኒ “ሐሰን” ብለውታል፡፡ [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 4678] ትርጉሙም፡- “ጥሙ ተወገደ፤ ደም ስሮች ረጠቡ፤ በአላህ ፈቃድ ምንዳውም ተረጋገጠ፡፡”
8. ላስፈጠረህ ዱዓእ ማድረግ፣
9. ፆመኛ ማስፈጠርን ማብዛት፡- ነብዩ ﷺ “ፆመኛን ያሰፈጠረ ሰው ልክ የሱን (የፆመኛውን) አምሳያ ምንዳ አለው፡፡ ባይሆን የፆመኛው ምንዳ ምንም አይቀንስም” ብለዋል፡፡ [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 6415]
10. ተራዊሕን ኢማሙ እስከሚያጠናቅቅ አብሮ መስገድ፣
11. በመልካም ስራዎች ላይ ከወትሮው በተለየ መበርታት፡- ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ነብዩ ﷺ ከማንም በላይ ቸር ነበሩ፡፡ ይበልጥ ቸር የሚሆኑት ደግሞ በረመዳን ነበር፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም] ስለዚህ ለቤተሰብ፣ ለዘመድ፣ ለጎረቤት፣ ለችግረኞች ከወትሮው በተለየ ማሰብና መደጎም፡፡ ዚክር፣ ዱዓእ፣ ቁርኣን መቅራት፣ ሱና ሶላቶችን መስገድ፣ በሽተኛን መጠየቅ፣ ቀብር መዘየር፣ ደዕዋ ማድረግ፣ መፋቂያ መጠቀም፣ ሰላምታ፣ ፈገግታ፣ መልካም ንግግር፣… ማብዛት፣
12. በመጨረሻው አስሩ የወሩ ቀናት በተለይም ሌሊቱ ላይ ይበልጥ ለዒባዳ መነሳሳት፡- “የአላህ መልእክተኛ ﷺ በመጨረሻዎቹ አስሮች ላይ - በሌሎቹ ከሚበራቱት በተለየ - ይበልጥ ይበራቱ ነበር፡፡” [ሙስሊም፡ 1175]
13. በሱሑር ሰዓት ኢስቲግፋር ማብዛት፣
14. ለሚሳደብ ሰው “እኔ ፆመኛ ነኝ” ብሎ መመለስ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
15. ልጆችን ፆም ማለማመድ፣
16. ለቻለ ዑምራ ማድረግ፣
17. ኢዕቲካፍ ማድረግ፣…
ረመዳን አልደረሰምን….?
ጠለሃ ኢብን ኡበይዳህ (ረድየላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት
ሁለት ሰዎች ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጥተው በእኩል ወቅት እስልምናን ተቀበሉ፡፡ አንደኛው ከሌላኛው በላይ ጂሀድ ላይ ይሳተፍ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ጀሀድ ተሳትፎ ሰመኣት ሆነ፡፡ ሌላኛው ከዚህኛው አንድ አመት ያህል ቆይቶ ከዛም ሞተ፡፡
ጠለሀ እንዲህ አለ
“በህልሜ የጀነት በር ላይ ሆኜ አየሁ፡፡ ከሁለቱም ጋር ነበርኩ፡፡ አንድ ሰው ከጀነት ውስጥ መጥቶ ዘግይቶ የሞተውን ቀድሞ እንዲገባ አደረገው፡፡ ከዛም ድጋሚ መጥቶ ሰመኣቱን እንዲገባ አደረገው፡፡ ከዛም ተመልሶ መጣና አንተ ተመለስ ጊዜህ አልደረሰም አለኝ፡፡”
ጠለሀ (ከእንቅልፉ) ከነቃ በኋላ ለሰዎች ስለ ሁኔታው ተናገረ፡፡ ሁሉም ተገረሙ፡፡ ይህ ጉዳይ መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጋር ደረሰ፡፡ ለመልክተኛውም ጉዳዩ ሲነገራቸው
እሳቸውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
من أي ذلك تعجبون؟ قالوا: يا رسول اللهّ هذا كان أشد الرجلين اجتهاداً ثم استشهد ودخل هذا الآخر الجنة قبله فقال رسول الله (صلى الله عليه وسلم) : أليس قد مكث هذا بعده سنة؟ قالوا: بلى. قال: أدرك رمضان فصام وصلى كذا وكذا من سجدة في السنة؟ قالوا: بلى. قال رسول الله (صلى الله عليه وسلم): فما بينهما أبعد مما بين السماء والأرض
“ምንድን ነው የሚገርማችሁ?”
እነሱም አሉ
“የ አላህ መልክተኛ ሆይ! ከሁለቱም ይህኛው በጣም ታግሏል (በጂሃድ) ሰመኣትም ሆነ፡፡ ነገር ግን ይህኛው ቀድሞት ጀነት ገባ፡፡”
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ከሱ በኋላ አንድ አመት ወደ ኋላ አልቀረምን?” አሉ
እነሱም “አዎ ቀርቷል” አሉ
እሳቸውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ረመዳን አልደረሰምን፣ አልፆመምን፣ ይህን ይህን ያህል ሱጁዶች በዚህ አመት አልሰገደምን?” አሉ
እነሱም “አዎን (ደርሷል)” አሉ
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “በሁለቱ መሃል ያለው ልዩነት በሰማይ እና ምድር ካለው ልዩነት ይበልጣል” አሉ
ኢብን ማጃህ የዘገቡት ትክክለኛ ዘገባ (2/345 346) እና አልባኒ አስ-ሲልሲላህ አስ-ሰሂሃ
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ረመዳንን በአግባቡ እንጠቀምበት፡፡ ይህን ያህል ታላቅ ምንዳ አለው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ለአቡበክር አሕመድ በሚድያ ለተሰራጨ የተሳሳተ ንግግር የተሰጠ እርማት፡፡

ከሰማይ የወረደው እስልምና ሃይማኖት ብቻ ነው፡፡
እየሱስ እንደሌሎች ነብያት ተውሒድ እና ፍቅርን ያስተማረ ነብይ እንጂ ጌታ አይደለም፡፡

አቡበክር አሕመድ ከላይ ቪድዬ ላይ እንደምትሰሙት እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡
“ሁሉም ሰማያዊ እምነቶች እኮ ስለ ፍቅር ነው የሚሰብኩት አይደለም? ክርስትና እንግዲህ እየሱስ ፍቅርን ያስተማረ ጌታ ነው፡፡”

ይህ ንግግር ስህተት ስለሆነ ከኢስላም አንፃር እንደሚከተለው መልሶች ይሰጥበታል፡፡
አንድ ሊታወቅ የሚገባው ሰዎች በሐቅ ይለካሉ፡፡ ሐቅ በሰዎች አትለካም፡፡ ስለዚህ ማንም ይሳሳት ማን ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከአጥፊዎች፣ ከተሳሳቾች ለመታደግ ሲባል መልስ ይሰጥበታል፡፡ ይህም ኡማውን ለመከፋፈል፣ ለኡማው ካለማዘን፣ ጭቅጭቅ ለመፍጠር ሳይሆን ህዘበ ሙስሊሙ ሐቅን ከባጢል እንዲለይ፣ ሰዎችን በጭፍን ተከትሎ ገደል እንዳይገባ፣ ለሙስሊሙ ከማዘን የሚሰጥ መልስ ነው፡፡ አላህ ኢኽላስ ይሰጠን፡፡
አቡበክር የተናገራቸውን ንግግሮች ይሀው እንደሚከተለው በተራ ቁጥር ማረሚያው መልሶች ይሰጡታል
1) ከሰማይ የወረደው ሃይማኖት አንድ ብቻ ነው፡፡ እሱም የነብያት ሁሉ ሃይማኖት የሆነው እስልምና ነው፡፡ ለእኛም የመረጠልን፣ ፀጋውን የሞላበት፣ የወደደልን ኢስላምን ብቻ ነው፡፡ እስልምና ብቻ ነው አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው፡፡
ኢስላም የነብያት ሁሉ ሃይማኖት፣ ከሰማይም የወረደው ኢስላም ብቻ ነው ስንል የሚከተሉትን ማስረጃዎች ይዘን ነው
[3:19] إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ ۗ
አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡
[3:85] وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ ٱلْإِسْلَٰمِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى ٱلْءَاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡
[5:3] ٱلْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَٰمَ دِينًا ۚ ٌ
ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡
ነብየላህ ኑሕ (አለይሂ ሰላም) የመጀመሪያው መልክተኛ እንዲህ አለ
[10:72] فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَمَا سَأَلْتُكُم مِّنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ
«ብትሸሹም (አትጎዱኝም)፡፡ ከምንዳ ምንንም አልለምናችሁምና፡፡ ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ፡፡»
ነብየላህ ሙሳ (አለይሂ ሰላም) ደግሞ እንዲህ አሉ
[10:84] وَقَالَ مُوسَىٰ يَٰقَوْمِ إِن كُنتُمْ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُوٓا۟ إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ
ሙሳም አለ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ ሙስሊሞች (ታዛዦች) እንደ ሆናችሁ (በአላህ ላይ ትመካላችሁ)፡፡»
ሴቷ ንግስት ቢልቂስ ከሱለይማን ጋር ምን እንዳለች አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል
[27:44] قَالَتْ رَبِّ إِنِّى ظَلَمْتُ نَفْسِى وَأَسْلَمْتُ مَعَ سُلَيْمَٰنَ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
«ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩ (ሰልሜያለሁ)» አለች፡፡
ከነብየላህ ሙሳም፣ ከነብየላህ ኢሳም በፊት የነበረው ኢብራሂም፣ ነገር ግን የሁዳዎችም ነሷራዎችም እንከተለዋለን የሚሉት ነብየላህ ኢብራሂም የሁዳም ነሷራም እንዳልሆነ ብሎም ጥርት ያለ ሙስሊም እንደሆነ አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል
[3:65] يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تُحَآجُّونَ فِىٓ إِبْرَٰهِيمَ وَمَآ أُنزِلَتِ ٱلتَّوْرَىٰةُ وَٱلْإِنجِيلُ إِلَّا مِنۢ بَعْدِهِۦٓ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በኢብራሂም ለምን ትከራከራላችሁ? ተውራትና ኢንጂልም ከርሱ በኋላ እንጅ አልተወረዱም፡፡ ልብ አታደርጉምን? በላቸው፡፡
[3:67] مَا كَانَ إِبْرَٰهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ
ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡
ስናጠቃልል ሰማያዊ ሃይማኖት የሚባል የለም፡፡ ዛሬ አቡበክር አሕመድ ሰመያዊ ሃይማኖት እያለ የጠራቸው በነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ነብይነት ብሎም በነብየላህ ኢሳ ነብይነት የማያምኑትን ጭምር ነው፡፡ የሁዳዎች የነብዩላህ ኢሳን እና የነብዩ ሙሐመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ነብይነት አይቀበሉም፡፡ ክርስትያኖች ደግሞ የነብዩ ሙሐመድ ነብይነትን አይቀበሉም፡፡ መልክተኞች ሁሉ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ሁሉም መልክተኛ ተቀብሏቸዋል፡፡ በእርሳቸው ዘመን ቢደርሱ እሳቸውን ሊያምኑባቸው እና ሊያግዟቸው ቃል ገብተዋል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
[3:81] وَإِذْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلنَّبِيِّۦنَ لَمَآ ءَاتَيْتُكُم مِّن كِتَٰبٍ وَحِكْمَةٍ ثُمَّ جَآءَكُمْ رَسُولٌ مُّصَدِّقٌ لِّمَا مَعَكُمْ لَتُؤْمِنُنَّ بِهِۦ وَلَتَنصُرُنَّهُۥ ۚ قَالَ ءَأَقْرَرْتُمْ وَأَخَذْتُمْ عَلَىٰ ذَٰلِكُمْ إِصْرِى ۖ قَالُوٓا۟ أَقْرَرْنَا ۚ قَالَ فَٱشْهَدُوا۟ وَأَنَا۠ مَعَكُم مِّنَ ٱلشَّٰهِدِينَ
አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን ከመጽሐፍና ከጥበብ ሰጥቻችሁ ከዚያም «ከእናንተ ጋር ላለው (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ መልክተኛ (ነብዩ ሙሐመድ) ቢመጣላችሁ በርሱ በእርግጥ እንደምታምኑበት በእርግጥም እንድትረዱት ሲል በያዘ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ አረጋገጣችሁን? በዚህም ላይ ኪዳኔን ያዛችሁምን?» አላቸው፡፡ «አረጋገጥን» አሉ፡፡ «እንግዲያስ መስክሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ» አላቸው፡፡

የሁዳዎች የነብየላህ ሙሳን (አለይሂ ሰላም) ዲን ቀይረዋል፡፡ ነሷራዎች የነብየላህ ኢሳን (አለይሂ ሰላም) ዲን ቀይረዋል፡፡ ስለዚህ ከሰማይ የመጣው አንድ ሃይማኖት ብቻ ነው፡፡

2) እየሱስ ነብይ እንጂ ጌታ አይደለም
ለዚህም ከቁርኣን የሚከተሉት ማስረጃዎችን እንደሚከተሉት ይቀርባሉ
እንደሚታወቀው ጌታ በመባል የሚጠራው የሚፈጥር ነው፡፡ ብቸኛው ፈጣሪ ደግሞ አላህ ነው፡፡ ነብየላህ ኢሳም (አለይሂ ሰላም) ሆነ እናቱ ቅድስት መርየም ፍጡሮች ናቸው፡፡
[16:17] أَفَمَن يَخْلُقُ كَمَن لَّا يَخْلُقُ ۗ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
የሚፈጥር እንደማይፈጥር ነውን? (ኢሳን ጌታ ስትሉ) አትገሰጹምን?
[6:14] قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ ۗ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ
«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?» በላቸው፡፡ «እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን (ተብያለሁ)» በላቸው፡፡
ነብየላህ ኢሳ (አለይሂ ሰላም) የአላህ ባሪያ ናቸው፡፡
[4:172] لَّن يَسْتَنكِفَ ٱلْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ وَلَا ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ ٱلْمُقَرَّبُونَ ۚ وَمَن يَسْتَنكِفْ عَنْ عِبَادَتِهِۦ وَيَسْتَكْبِرْ فَسَيَحْشُرُهُمْ إِلَيْهِ جَمِيعًا
አልመሲሕ (ኢየሱስ) ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክትም (አይጠየፉም)፡፡ እርሱን ከመገዛት የሚጠየፍና የሚኮራም ሰው (አላህ) ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል፡፡

ነብየላህ ኢሳ ለየሁዳዎች ምን አላቸው
[5:72] لَقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ ٱلْمَسِيحُ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ
እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡
ይህን የመሰሉ በጣም ብዙ ማስረጃዎችን ኢሳ (አለይሂ ሰላም) የአላህ መልክተኛ ለመሆናቸው እና በፍፁም ጌታም፣ የአላህ ልጅም ላለመሆናቸው ማምጣት ይቻላል፡፡
አቡበክር አሕመድ ለነፍስህ እዘንላት ከፖለቲካ ውጣ ቁጭ ብለህ ለሚቀጥለው አለም የሚበጅህን እስልምና ከኡለማዎች ስር ተማር፡፡ ግድ የለህም ይበጅሃል ተመለስ፡፡ እየሄድክበት ያለው አካሄድ ወደ ከባድ ስህተት እየከተተህ ነው፡፡
አላህ አንተንም እኛንም ይምራን፡፡
አላህ ሆይ! ሐቅን በሐቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያቶች መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
https://t.me/SadatTextPosts/428
አቡበክር አሕመድ ወዴት እየሄደ ነው?
“ሁላችንም የፈጣሪ ልጆች ነን፡፡…..” ብሏል፡፡
በአደባባይ ለተሳሳተው በአደባባይ እዛው ሚድያ ወይንም ሌላ ሚድያ ላይ ቀርቦ ስህተቱን ማረም አለበት፡፡

አላህ ሚስትም፣ ወንድ ልጆችም፣ ሴት ልጆችም የሉትም፡፡ አላህ ክህደት ከሚላቸው ነገሮች ቁጥር አንዱ አላህን ሚስት እና ልጆች አሉ የሚለው እምነት ነው፡፡ ከክርስትና እና ከየሁዳ እምነት ጋር ከሚለያዩን ታላቅ አርእስቶች ውስጥ አላህ ልጅ አለው የለውም የሚለው ነው፡፡ እኛ ሙስሊሞች ለአላህ ልጅም፣ ሚስትም የለውም እንላለን፡፡ የሁዳና ክርስትያኖች “እኛም የአላህ ልጆች ነን፣ እዝራም የአላህ ልጅ ነው፣ ኢየሱስም የአላህ ልጅ ነው፡፡” ይላሉ፡፡ አላህ ከየሁዳዎችም፣ ከክርስትያኖችም፣ ከመካ አጋሪያንም ይህን አባባል ውድቅ አድርጓል
1) የሁዳዎች እዝራ የአላህ ልጅ ነው አሉ፡፡
[9:30] وَقَالَتِ ٱلْيَهُودُ عُزَيْرٌ ٱبْنُ ٱللَّهِ
አይሁድ ዑዘይር የአላህ ልጅ ነው አለች፡፡
2) ክርስትያኖች ኢሳ የአላህ ልጅ ነው አሉ
[9:30] وَقَالَتِ ٱلنَّصَٰرَى ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ ٱللَّهِ ۖ
ክርስቲያኖችም አልመሲሕ የአላህ ልጅ ነው አሉ፡፡
3) የመካ አጋሪያን መላእቶች የአላህ ሴት ልጆች ናቸው አሉ
[21:26] وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحْمَٰنُ وَلَدًا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۚ بَلْ عِبَادٌ مُّكْرَمُونَ
«(አዛኙ አላህ) አልረሕማንም (ከመላእክት) ልጅን ያዘ» አሉ፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም (መላእክት) የተከበሩ ባሮች ናቸው፡፡

የሁዳና ነሷና “እኛ የአላህ ልጆች ነን” ቢሉም አላህ ውድቅ አደረገባቸው፡፡ አላህ ሚስትም ልጅም የለውም፡፡
ማስረጃዎቹም እንደሚከተሉት ናቸው
ጂኖች ምን እንዳሉ አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል
[72:3] وَأَنَّهُۥ تَعَٰلَىٰ جَدُّ رَبِّنَا مَا ٱتَّخَذَ صَٰحِبَةً وَلَا وَلَدًا
‹እነሆም የጌታችን ክብር ላቀ፡፡ ሚስትንም ልጅንም አልያዘም፡፡›
- ሱረቱል ኢኽላስ በመባል የምትታወቀው ሱራ ላይ አላህ እንዲህ ይለናል
[112:1] قُلْ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ
በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡
[112:2] ٱللَّهُ ٱلصَّمَدُ
«አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡
[112:3] لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
«አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡
[112:4] وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ
«ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡»

- አላህ ልጅ አለው ስላሉ ብቻ አላህ ምን ያህል እንደተቆጣ እንዲህ ይለናል
[19:88] وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحْمَٰنُ وَلَدًا
«አልረሕማንም ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡
[19:89] لَّقَدْ جِئْتُمْ شَيْـًٔا إِدًّا
ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፡፡
[19:90] تَكَادُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ يَتَفَطَّرْنَ مِنْهُ وَتَنشَقُّ ٱلْأَرْضُ وَتَخِرُّ ٱلْجِبَالُ هَدًّا
ከእርሱ (ከንግግራቸው) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡
[19:91] أَن دَعَوْا۟ لِلرَّحْمَٰنِ وَلَدًا
ለአልረሕማን ልጅ አልለው ስለአሉ፡፡
[19:92] وَمَا يَنۢبَغِى لِلرَّحْمَٰنِ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا
(ለአላህ) ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡

አቡበክር አሕመድ እባክህ ለነፍስህ እዘንላት ፖለቲካ ይቅርብህ፡፡ ይሀው በጥፋት ላይ ጥፋት እየፈፀምክ ነው፡፡ እናንተ ትላንት ሙስሊሙን ከነ አቡበክር እና ጓደኞቹ ስናስጠነቅቅ “አርፋችሁ ቁጭ በሉ፣ እናንተ ለዚህ የተገባችሁ አይደላችሁም፣ ኡማውን አትበታትኑ፣ ታዋቂ ለመሆን ፈልጋችሁ ነው እያላችሁ ንያችንን ስትፈትሹ የነበራችሁ፣ ቅናት ነው ስትሉ የነበራችሁ፣ ትንሽ እውቀት ይዛችሁ አታውሩ፣ …..” ስትሉን የነበራችሁ እና ለነዚህ ሰዎች ጥብቅና ስትቆሙ የነበራችሁ ሁሉ አሁንስ ተረዳችሁት ጥፋታችሁን እና ጥብቅና የቆማችሁላቸውን ሰዎች ጥፋት?

እኛ በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ድሮ የነበርንበት አቋም ላይ ነው ያለነው፡፡ እንዲህ አይነትን ጥፋት አይተን ዝም አንልም፡፡ ለአንዷ ብቸኛ ሐቅ እንጂ ለማንም ቡድን ጥብቅና አንቆምም፡፡ አሕባሽን ተቃውመን ኢኽዋንን ዝም አንልም፡፡ ምስጋና ሁሉ ለአላህ ነው፡፡ ባጢል ባጢል ነው ከአህባሽ ይምጣ፣ ከኢኽዋን፡፡

የአቡበክር አሕመድን ንግግር ቆርጣችሁበት ነው ለምትሉ ይሀው “ሁላችንም የፈጣሪ ልጆች ነን” ካለው ንግግሩ በፊትና በኋላ ያሉ ንግግሮቹንም አስቀምጫለሁ፡፡
አላህ ሐቅን በሐቅነቱ ያሳየን የምንቀበለውም ያድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብዩ ሙሐመድ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
https://t.me/SadatTextPosts/431
By Ibnu Munewor
የአሕባሽ ፅንሰ ሐሳብ አንዳንዶች ዘንድ ልክ እንደ ጭራቅ ነው። ጭራቅ ምናባዊ ማስፈራሪያ እንጂ እውነታ የለውም። ልክ እንዲሁ ከሚያልሙት ቦታ መድረስ ሲያቅታቸው እንቅፋት የሆናቸውን አካል ሰው እንዲፀየፈው፣ አጃቢ እንዲቀለው አሕባሽ ወይም የአሕባሽ ተባባሪ አድርገው ይፈርጁታል።
★ በዚህን ጊዜ አሕባሽ ማለት አይሁዳዊ ተልእኮ አንግቦ ኢስላምን ለማጥፋት የሚንቀሳቀስ እጅግ አደገኛ ቡድን ነው።
★ በዚህን ጊዜ አሕባሽ ማለት ታጥቦ የማይጠራ የአሳማ ስጋ ነው።
★ በዚህን ጊዜ አሕባሽንና ሰዎቹን ማብጠልጠል እንደ መከፋፈል፣ እንደ ሃሜት የሚቆጠር አፍራሽ ምግባር ሳይሆን ህይወት እና ንብረት እንኳን ቢጠፋበት የማይበዛበት ጂሃድ ነው።
★ በዚህን ጊዜ በተካሄደ "ትግል" ህይወት ጠፍቷል፤ አካል ጎድሏል፤ ክብር ጎድፏል፤ ንብረት ወድሟል፤ ህዝብ ታፍሷል፤ በርካታ አገር ጥሎ ተሰዷል፤ መስጂድ ተደፍሯል።

ግና አሕባሽ ማታገያ ጭራቅ እንጂ ይህ ሁሉ መስዋዕትነት ሊከፈልለት የሚገባ፣ ህልውና ያለው ጠላት አይደለም– ከ "ትግሉ" ዘዋሪዎች ዘንድ። ስለሆነም ወደ ህልማቸው እንደተጠጉ ሲሰማቸው የትላንቱ ጭራቅ በጠላትነት ያስወረፈው ሁለ ነገሩ እንዳለ ቢሆንም እንደ ወዳጅ፣ እንደ አጋር ይቆጠርና እጅ ለእጅ ተያይዞ ይዘመራል። ፍትጊያው በተራ የኳስ ጨዋታ ተመስሎ ጨዋታው ይደመደማል። ነፋስ ገብቶባቸው እንጂ መሰረታዊ ልዩነት እንደሌላቸው በጋራ ያውጃሉ። እዚህ ላይ ያ ዲን የሚያጠፋ ጠላት መጣ ተብሎት ህይወቱን ንብረቱን አሳልፎ የሰጠው ምስኪን ሸፍጥ እንደተፈፀመበት ይገባሀል። ቤተሰብ ምን ይሰማው ይሆን? ለካስ ጠላት በሌለበት ኖሯል ያ ሁሉ መስዋዕትነት!!
ቢሆንም
ቢሆንም
ዛሬም አልረፈደም። ይህ የቁማራቸው መጨረሻ አይደለም። ነገ አዲስ ጭራቅ ፈጥረው፣ ካልሆነም የሞተውን ቀስቅሰው አይናቸውን በጨው አጥበው ይመጣሉ። ከትላንቱ አልማር ብለህ ነገም እንደ ትላንቱ "ትግሉ ለዐቂዳ ነው" እንዳትል እፈራለሁ። ለነገሩ ድግምት የማይሰራው የለም።
https://t.me/SadatTextPosts/433
ህዝቡ አልገባውም እንጂ ነገሩ ሁሉ ጨዋታ ነው፡፡
ፀቡ በግለሰቦች መሀል ከነበረ መጀመሪያውንም የኢስላም ሽፋን ሊሰጠው አይገባም ነበር፡፡ (አህባሽ…….. ሊባል አይገባም ነበር፡፡)
ፀቡ የዲን ከነበር ወደ ትክክለኛው ዲን እስኪመጣ ድረስ ምንም አይነት መተቃቀፍ፣ መፎጋገር፣ መላቀስ አይገባም ነበር፡፡ ይሄ መሸዋወድ ነው፡፡
ነገር ግን ፀቡ የወንበር ስለነበር “አህባሽን የምንቃወመው ለፖለቲካል አጀንዳው ብቻ ነው፡፡” ያሉ ስለነበሩ አሁን ወንበሩ በአህባሽ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ይካፈል ሲባል፣ ኢኽዋኖችም ጠበቃዎቻቸውም ትላንት “አህባሽ ዲን አፍራሽ” እያሉ ኡማውን ከስቅሰው ካስጨረሱት በኋላ አሁን ደግሞ “አልሀምዱሊላህ፣ ሸይጧን ተሸነፈ ኢስላም አሸነፍ፣ ላለፈው ሁሉ አውፍ እንባባል……” ብለው አጭበረበሩ፡፡
ሰውን ቢያታሉ አላህን ማታለል አይቻልም፡፡ የወንበሩን ጥያቄ በዲን ስም ሲፋተጉበት የነበረውን ሀሰን ታጁ እንዲህ ሲል ይጠቅሰዋል
“ላለፉት 9 ወራት የነበረውን ከነሱም ጋር የነበረ ፍትጊያ አለ፡፡ እንደ ኳስ ጨዋታ ነው የማየው እኔ፡፡ ማለት ነገሩ ቁም ነገር ቢሆንም፣ ሰዎች እስፖርት ላይ ኳስ ላይ፣ ይገፋፋሉ ይጠራረባሉ፣ ይወድቃሉ መጨረሻ ላይ ግን ውጤቱ ላይ ሲሆን ይተቃቀፋሉ፡፡”
ጉድ ነው፡፡ ህዝቡ እንደመሩት ነው፡፡ ቁጭ በል ሲሉት ቁጭ፣ ቁም ሲሉት መቆም፡፡ ትላንት አህባሽ ናቸው፣ ተከትለናቸው አንሰግድም ሲባሉ የነበሩት ሰዎች ሁላ ተውበት ሳያደርጉ፣ ከያዙት አቋም ሳይመለሱ አሁን ደግሞ “መተቃቀፍ፣ እንባ መራጨት…. አውፍ ተባብለናል” መባባሉ ማጭበርበር ለመሆኑ ወይንም መጀመሪያውንም የዲን ጉዳይ እንዳልነበር ያሳያል፡፡ ስልጣን አላጋራም ያሉትን አካላት የአቂዳ (የእምነት) ችግር አለባቸው ብሎ ሲከስ ቆይቶ ወንበር ሲያጋሩት የአቂዳ ችግራቸውን ጭጭ ካለ መጀመሪያውንም የአቂዳ ችግር አለባቸው ሲል የነበረው መቀስቀሻ እንጂ እውነት እንዳልነበር ማስረጃ ነው፡፡
ሙስሊሙ ከምንም ጊዜ በላይ በፖለቲከኞች ቁማር ላለመበላት ኢስላምን መማር ግድ ይለዋል፡፡
አላህ ሆይ! እውነተኛ አንድነትን ስጠን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
የተከበረውን የረመዳንን ወር በባዶ ወይም በጎደለ ቤት ላለመቀበል ሽር ጉዱ ከወዲሁ ተጀምሯል። ቁሳዊ ዝግጅቱ አንዳንዴም መጠኑን ያለፈ እንዳይሆን ያሰጋል።
ባንፃሩ ለዚሀ የተከበረ ወር ያለን መንፈሳዊ ዝግጁነት ግን በእጅጉ የወረደ ነው— የብዙዎቻችን! እናም ይህን ጣፋጭና ተናፋቂ ወር በተራቆተ ልቦና እንዳንቀበለው እንጠንቀቅና የቀልቡንም ስንቅ እንዳንዘነጋ አደራ እላለሁ — ደካማዋ ነፍሴንና ወዳጆቼን ።
الله
እንዲህ ብሏል:
ۗ وَتَزَوَّدُوا۟ فَإِنَّ خَيْرَ ٱلزَّادِ ٱلتَّقْوَىٰ ۚ وَٱتَّقُونِ يَٰٓأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ
" ተሰነቁም( ስንቅን አዘጋጁ)፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው፡፡ የአእምሮዎችም ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ፡፡ "
ቅድሚያው ለቀልብ ስንቅ ይሁን!!
በዚህ የቁርአን ወር ላይ ደጋግመን ቁርአን በመቅራትና በማድመጥ ፋንታ በነሺዳና በመንዙማ ተወጥረን የማይመለሰውን ግዜ በከንቱና ባልተደነገገ ዒባዳ አናባክን።
ባጠቃላይ አላህን እንፍራ!! ወደ አላህ እንመለስ! ያለፈው ጥፋትና ከንቱ ስራ ከበቂ በላይ ነውና ጥፋቶችንነ አንዳጋግም !
አላህ ይምራን!!