Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
👆🏻አላህን ማወቅ
አጠር ያለች መፀሀፍ
ዝግጅት ዶክተር ሷሊህ አል-ሷሊህ (ረሂመሁላህ)
አጠር ያ ማብራሪያዎች በሳዳት ከማል
ይህንን ሶፍት ኮፒ ከሚከተሉት የቴሌግራም ቻናል ሊንኮች ማውረድ ይችላሉ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/1630
https://t.me/SadatTextPosts/401
https://t.me/Kitaboch/38
የሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ጆይን በማለት ተቀርተው ያለቁ ሙሉ የኪታብ ኦዲዬዎችን ዳውን ሎድ ያድርጉ
https://t.me/Kitaboch
አርባኢን (40 ሀዲሶች)
አቂደቱል ዋሲጥያ (በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ)
አል-ዋጂባት
ኹዝ አቂደተክ
አል-ኡሱል አስ-ሰላሳ
አል-ቀዋኢዱል አል-አርበኣ
በተጨማሪ ከ300 በላይ ሙሃደራዎች ለማግኘት የሚከተለውን ቴሌግራም ቻናል ጆይን ይበሉ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ የአላህ ባሪያዎች ሆይ!
አጀሩምያህ ሙሉው ደርስ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሃያ ሶስት
በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር ግደይ
የሚከተለውን ሊንክ ጆይን በማለት ማግኘት ይችላሉ
https://t.me/Kitaboch
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ የአላህ ባሪያዎች ሆይ!
ኩን ሰለፊየን አለል ጃዳህ ሙሉው ደርስ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሃያ አምስት
በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር ግደይ
የሚከተለውን ሊንክ ጆይን በማለት ማግኘት ይችላሉ
https://t.me/Kitaboch
እውነት ኢትዮጵያ የአህለ ሱና ሀገር ናትን?
★★★★★★★★★★★★

ኢትዮጵያ ሀገራችን የአህለ ሱና ሀገር ብትሆን ምንኛ ደስ ባለን ነበር። ነገር ግን ሺርክ፣ ቢድአ፣ መሀይምነት፣ ዘረኝነት፣ አመፀኝነት በሰፊው የተንሰራፋባት ሀገር ናት።

የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደረባዎቻቸውን ወደ ሀበሻ ሁለት ጊዜ ስደት እንዲሄዱ ነበር ያዘዙት።

ተውሒድን ከማንም በላይ ይፋ ማድረግና ከሺርክ መራቅ ሲገባን፣ አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ አብዛኛው ሺርክ እና ቢድአ በማጨማለቅ ላይ ነው።

"ሀገራችን የአህለ ሱና ሀገር ነው። ሁሉም አህለ ሱና ነው።" ብለው የሚዋሹ ሰዎች ስላሉ፣ ሀገራችን የአህለሱና ሀገር እንዳልሆነችና ሁሉም አህለ ሱና እንዳልሆነ በተጨባጭ ማስረጃ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ

ሺርክ ማለት ለብቸኛው ፈጣሪ አላህ የሚገባውን አምልኮ ለፍጡራን (መላኢካ፣ ነብይ፣ ጂን፣ ሷሊህ፣ ወልይ፣ ዛፍ፣ ዲንጋይ …) መስጠት ነው።

እውነት ሀገራችን የአህለ ሱና ሀገር ናት ወይንስ ሺርክ እና ቢድአ የተንሰራፋባት የሚለውን ለማየት የሚከተሉት ሀገራችን ላይ በየአቅጣጫው በሰፊው የሚሰሩ በአድ አምልኮዎችና፣ ኢስላም ላይ የተጨመሩ ቢድአዎች በከፊሉ እዘረዝራለሁ

1) በጎንደር "ጌታው ሸህ አሊ ግንደር፣ ሸህ አብድል ባሲጥ፣ ሸህ አባድር፣ ፈቂህ አሊ ሙዝ …" እየተባለ ለነዚህ ከአላህ ውጭ ላሉ ፍጡሮች ለአላህ ብቻ የሚገባው አምልኮ ይሰጣቸዋል፣
2) አሁንም በጎንደር "የእሽት ዶሮ" እየተባለ ዶሮ ለእርኩስ መንፈስ ይሰጣል፣
3) ጎጃም አዴት የሚባል ቦታ ለሞተ ውሻ እላዩ ላይ ቀብር ተሰርቶለት ይመለካል፣
4) ወሎ ደግዬ፣ ዳና ፣ እና እና ሌሎች ቦታዎችም ላይ ባአድ አምልኮ ይፈፀማል፣
5) አንበሶ፣ አዳል ሞቴ፣ ራሂሎ እና የመሳሰሉትን እየተባለ ለጂኖች "ሙወከል" እየተባለ ለሰይጣን ዶሮ ይታረድለታል፣
6) አዲስ አበባ የድሮ እስላም መቃብር የሸህ ሀሰን በቱል ቀብር ይመለካል፣ "ዱአ አድራጊ ናቸው" በሚል ስም ብዙ ጠንቋዮች ይመለካሉ፣
7) ጉራጊ አብሬት፣ ቃጥባሬ ከአላህ ውጭ ይመለካሉ፣
8) ስልጤ አልከሶ፣ ኑርሁሴን ከአላህ ውጭ ይመለካሉ፣
9) ካእባ ላይ ብቻ መደረግ ያለበትን ጠዋፍ ኦሮሚያ ባሌ ኑር ሁሴን ቀብር ላይ ጠዋፍ ይደረጋል፣
10) "የሸህ ሁሴን ትንቢት" እየተባለ በጥንቆላ ይታመናል፣
11) ምስራቅ ኢትዮጵያ ለጅብ ገንፎ በማገንፋት ባእድ አምልኮ ይፈፅማሉ፣
12) አላህ ያላዘዘው፣ ነብዩ ያልሰሩት ያላዘዙት "መውሊድ (የነብዩ ልደት)" ብለው በክህደት ስንኞች፣ በመጨፈር፣ በማፏጨት፣ ጫት በመቃም፣ ሴት እና ወንድ በመቀላቀል ያሳልፉታል፣
13) የአላህን ስም እና መገለጫዎች የሚያጣሙ ብሎም የማይቀበሉ አህባሽን ይመስል የጥመት ቡድኖች አሉ፣
14) ሀገራችን ላይ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደረባዎች የሚሰደቡበት ኪታብ ይሸጣል፣ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይከፋፈላል፣
15) አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተማዎችም ላይ ሀሙስ ማታ ከመግሪብ እስከ ኢሻ ብለው በሰለዋት ስም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይመጣሉ ብለው ከተቀመጡበት "መርሃባ ነቢ" ብለው ይነሱላቸዋል፣

አረ ስንቱ……
ታድያ ይህችን ሀገራችንን ነው "ሀገራችን የአህለ ሱና ሀገር ነው። ሁሉም አህለ ሱና ነው።" እየተባለ የውሸት ምስክርነት የሚሰጣት?
አላህ ለምን አይፈራም።
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በአላህ ስም ምዮ የምናገረው ተውሒድን እና ሱናን የተፃረረ ብሎም ሺርክ እና ቢድአን የሚያጨማልቅ አህለ ሱና አይባልም።
አህለ ሱናዎች ማለት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው የነበሩባትን መንገድ የሚከተሉ ናቸው።

ነብዩ እና ሰሀባዎቻቸው ደግሞ ከላይ ከተጠቀሱት እርጉም እና እርኩስ የጥፋት መንገዶች የራቁ ናቸው።

የአህለ ሱናዎችን መንገድ የተቃረኑ ሰዎች የጮሁትን ያህል ቢጮሁ፣ የዋሹትን ያህል ቢዋሹ አላህ አያሳካላቸውም።
ይሀው ሀገራችን ላይ በትክክለኛው እምነት መሰባሰብ አቅቷቸው አላህ ውርደት ያቀመሳቸውን የጥፋት ቡድኖች እና ግለሰቦች እያየን ነው።
አላህ ባዘዘው መንገድ ያልተሰባሰቡ ተበታተኑ እንጂ አንድ ሆኑ አይባልም።

መፍትሄው የውሸት መስካሪዎችን፣ አውቆ አጥፊዎችን በጭፍን መከተል ሳይሆን ቁርአን እና ሀዲስ በሰሀባዎች መንገድ መረዳት ነው።
ሙስሊም ወንድም እና እህቶቼ ሆይ! አላህ ከፊትና ይጠብቀን። ከሁሉም የጥመት ቡድኖች ይጠብቀን። ብቸኛዋን የሐቅ ጎዳና ይምራን።
https://t.me/SadatTextPosts
አቂዳ አንድ ያላደረጋቸውን የበሬ አጥንት አንድ አያደርጋቸውም፡፡
★★★★★★★★★★★★
በአቂዳ ተለያይተው አንድነት እና ሰደቃ እያሉ በሬ አርደው በመብላት አንድ እንሆናለን ብለው ያሰቡትን ሰዎች መጨረሻ ተመለከታችሁን?
በኒ መስጂድ እና አየር ጤና ላይ ጥግ ጥጋቸውን ይዘው መደስኮራቸውን ይዘዋል፡፡
አቂዳ አንድ ያላደረጋቸውን በሬ አርዶ መብላት እና አብሮ ፎቶ መነሳት አንድ አያደርጋቸውም፡፡
በጥመት ላይ የተሰባሰቡ ሰዎች መጨረሻቸው ይህ ነው፡፡ አብዛኛውን ምስኪን ቢሸውዱትም አላህ ሁሉን ተመልካች ነውና አያሳካላቸውም፡፡ በኪታብ እና በሱና አንድ መሆን አቅቷቸው፣ በል እንዲያውም ወደ ተውሒድ እና ሱና የሚጣሩ ወንድሞችን “የኡማው ጠላቶች” እያሉ ከሺርክ እና ቢድኣ ሰዎች ጋር አብረው ሄደው ሲዶልቱ እና ሲተሻሹ የነበሩ ሰዎች ይሀው ውርደታቸውን ቀመሱ፡፡ ከተቋም በፊት በእምነት አንድ መሆን ይጠበቃል፡፡አላህም በእምነት ገመድ አንድ ሁሉ ሲል ነው ያዘዘው፡፡ ሱናን መፃረር ለውርደት ይዳርጋል፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! በኪታብ እና በሱና አላህ አንድ ያድርገን፡፡ አሽአሪ፣ ማትሩዲ፣ አህባሽ፣ ሱፊ፣ ኢኽዋን….. ከሚባሉ የጥመት ቡድኖች ሁሉ አላህ ይጠብቀን፡፡ ብቸኛዋን የጥንት የጠዋቷን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው የነበሩባትን የሰለፉነ ሷሊሂን መንገድ ይምራን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ኢኽዋንንም ይሁን ሌሎች የቢድኣ ቡድኖችን ማጋለጥ ለሙስሊሞች ከማዘን እና ከማሰብ ነው፡፡
★★★★★★★★★★★★
ከሺርክ እና ከባለቤቶቹ፣ ከቢድ እና ከባለቤቶች ማስጠንቀቅ ለሙስሊሞች ከማዘን እና ለእነሱ ከመቆርቆር ነው፡፡

ለሙስሊሞች ማዘን ማለት እንደ ኢኽዋን፣ ኸዋሪጅ፣ እና ሌሎችም ሙስሊሞችን ለችግር የሚዳርጉ ቡድኖችን እና ሚድያዎቻቸውን ማጋለጥ ነው፡፡ ሙስሊሞችን ለተለያዩ ችግሮች የዳረጉት ኢኽዋኖች ናቸው፡፡ ይህንን ደግሞ አይደለም ኢልም አለኝ የሚል ሰው እራሳቸው ኢኽዋኖች ክስረት እንዳመጡ እራሳቸው ላይ እየመሰከሩ ነው፡፡ለምሳሌ አረብ ሀገራት (ቱኒስያ፣ ግብፅ፣ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊብያ….) ሀገራችንም ላይ ተገለባባጭ እና ተለዋዋጭ የሆኑት ኢኽዋኖች ለፖለቲካ ጥቅማቸው ሲሉ በኢስላም ስም ሙስሊሞችን መከራ ላይ የዳረጉት፡፡
ሙስሊሙ በድጋሚ በነዚህ ሰዎች እንዳይሸወድ፣ እዚህ ከባድ መከራ ውስጥ ሙስሊሙን የከተቱት ኢኽዋኖች ናቸው ማለት ለሙስሊሙ አለማዘን አይደለም፡፡ እንዲያውም ከዚህ አደገኛ ቡድንም ይሁን ከሌሎች ቡድኖች ኡማውን ማስጠንቀቅ ለኡማው በጣም ከማዘን እና ከመጨነቅ ነው፡፡
በተገላቢጦሹ አንዳንድ የእውቀት ባለቤት ነን እያሉ ኡማው በነዚህ ተኩላዎች ሲሸወደ እያዩ ዝምታን የመረጡ ሰዎች አላህን አይፈሩትምን
አላህ እንዲህ ይላል
وَإِذْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ لَتُبَيِّنُنَّهُۥ لِلنَّاسِ وَلَا تَكْتُمُونَهُۥ فَنَبَذُوهُ وَرَآءَ ظُهُورِهِمْ وَٱشْتَرَوْا۟ بِهِۦ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ فَبِئْسَ مَا يَشْتَرُونَ
አላህ የነዚያን መጽሐፉን የተሰጡትን ቃል ኪዳን ለሰዎች በእርግጥ ታብራሩታላችሁ አትደብቁትምም በማለት የያዘባቸውን (አስታውሱ)፡፡ በጀርባዎቻቸውም ኋላ ጣሉት፡፡ በርሱም ጥቂትን ዋጋ ገዙ፡፡ የሚገዙትም ነገር ከፋ!

ይህ አንቀፅ አላህ እውቀት ሰጥቷቸው በእውቀታቸው የማይሰሩትን፣ እውነቱን ለሰዎች የማያብራሩትን እና የሚደብቁትን የሚወቅስበት ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ለቀላቢያቸው አልታመን ብለዋል፡፡ ሐቁን ደብቀዋል፡፡ ብሎም ለባጢል ጥብቅና ቆመዋል፡፡
ኢኽዋን የከሰረ የጥመት ቡድን ነው፡፡ ኢኽዋን ከእለት እለት ኪሳራው በግልፅ በወጣ ቁጥር ኢኽዋንን አናስነካም ብለው፣ ለኢኽዋን ጥብቅና የቆሙ፣ ማስረጃን ሲጠመዝዙ የነበሩ በጠቅላላ ከኢኽዋን በላይ የከሰሩ መሆናቸውን እያየን ነው፡፡
አላህ በሐቅ ላይ ይሰብስበን፡፡ ሐቅን በሐቅነቱ ያሳያን የምንቀበለውም ያድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ ያሳየን የምንርቀውም ያድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አንድ ሙስሊም በአደባባይ ቢድኣ ሲሰራ፣ ዲን ሲፈርስ፣ የባጢል ሰዎች ቢድአቸውን ሲረጩ ካየ ከቁርኣን፣ ከሀዲስ፣ ከሰለፎች ወይንም ከኡለማዎች ንግግር ጠቅሶ መልስ መስጠት ይችላል ብቻ ሳይሆን ተገቢም ነው፡፡ ቢድአ እና ጥፋትን ለማስጠንቀቅ ከየትኛውም ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ ዲግሪ፣ ማስተርስ፣ ዶክትሬት ብሎም የየትኛውም መርከዝም ይሁን ግለሰብ ፍቃድ አያስፈልገውም፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በእስልምና ወሮች 12 ናቸው እነሱም
1) ሙሐረም፣
2) ሰፈር፣
3) ረቢእ አል-አወል፣
4) ረቢእ አስ-ሳኒ፣
5) ጀማዳ አል-አወል፣
6) ጀማዳ አስ-ሳኒ፣
7) ረጀብ፣
8) ሻእባን፣
9) ረመዳን፣
10) ሸዋል፣
11) ዙል ቃኢዳ፣
12) ዙል ሂጃህ ናቸው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የሀገራችን ጉዳይ ወሬ ሳይሆን ዱኣ ይፈልጋል፡፡ በየ ሶሻል ሚድያው፣ በየ ካፌው የማይጠቅም ወሬ ከማውራት፣ አንዱ የሌላውን ዘር ከማጥላላት አምርሮ ዱአ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ ምክንያቱም አላህን ለማምለክ እንኳን ሰላም አስፈላጊ ነው፡፡
አላህ ሀገራችን ላይ ፍትህ እና ሰላም ያስፍን፡፡ እሱም ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ ነው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
መፅሀፋ በገበያ ላይ ዋለ !!
አዲስ አበባ ባሉ ኪታብ ቤቶች ማግኘት ይችላሉ ክፍለ ሀገርም ያሉ ነጋዴዎች ጋር እየተዳረሰ በመሆኑ አቅራቢያችሁ በሚገኝ ኪታብ ቤት በመጠየቅ እንዲያስመጡላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ

ከሀገር ውጪ ያላችሁ ብዛት የምትፈልጉ በዚህ ቁጥር አናግሩት ይልክላችኋል
¶ 0925504315 ሙሀመድ ሰዒድ
አስደሳች ዜና

ማንኛውንም የተውሂድ ፣ የሱና ፣ ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋቶችን እና የሰለፎችን ታሪክ የሚዳስሱ መፅሀፎችን ውጪ ሀገር ለምትኖሩ ወንድምና እህቶች በብዛት መላክ ጀምረናል።

ዱባይ፣ኩየት፣ሳኡድአረቢያ፣ኳታር፣
አሜሪካ፣እንግሊዝ እንዲሁም በሌሎች ሀገሮችም ጭምር እንልካለን።

ጀመአ ጀመአ በመሆን አንድን ሰው በመወከል ይዘዙን ባሉበት ቦታ እንልካለን።

በዚህ ስልክ ቁጥር ያናግሩን
በዋትስአፕም በቴሌግራምም
በኢሞም ያገኙናል
👇👇👇👇
+251925504315
+251925504315
ሙሐመድ ሰኢድ
መውሊድን ስንቴ ነው የሚያከብሩት?
የአፊንጮ በሩ አል-አቅሳ መስጊድ?

እንደሚታወቀው በኢስላም ሁለት አመታዊ በዓል ተደንግገውልናል፡፡ እነሱም ኢድ አል-ፊጥር እና ኢድ አል-አድሃ ናቸው፡፡ በኢስላም ላይ አላህ እና ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላዘዙበት፡፡ ሰሃባዎች፣ አራቱ አኢማዎች፣ ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ቲርሚዚ፣ ኢብን ማጃ እና ሌሎችም ሙሐዲሱች የማያውቁት እና ያልሰሩት፡፡ ከአራት መቶ አመት በኋላ ሺአዎች የጀመሩትን “መውሊድ (ነብዩ ሙሐመድ የተወለዱበትን ቀን ረቢአል አወል 12 ብለው ማክበር)” ተጀመረ፡፡ ይህ ፅሁፍ ኢስላም የማያውቀውን መውሊድን ስንቴ ነው የሚያከብሩት? የሚል ይሆናል፡፡ የሚገርመው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተወለዱበት ቀን በኡለማዎች መሃል ልዩነት አለ፡፡ የሞቱበት ግን በቁርጥ ረቢአል አወል 12 ነው፡፡

እነዚህ ሰዎች የሚያከብሩት የሞቱበትን ወይንስ የተወለዱበትን?
ያሳለፍነው እሁድ አዲስ አበባ አፊንጮ በር አካባቢ የሚገኘው አል-አቅሳ መስጂድ መውሊድ ተከበረበት፡፡ 17 ረጀብ 1440 ሒጅራ አቆጣጠር ማለት ነው፡፡ ጥያቄው እነሱ ዘንድ “መውሊድ” የሚሉት በአል በወቅት የተገደበ አይደለምን? በአመት ስንት ጊዜ ነው የሚከበረው? ለምን ይሆን ከአምስት ወር በኋላ ደግመው ያከበሩት?

ሁለቱ በኢስላም የተደነገጉት ኢዶች (ኢድ እና አረፋ) በቀናቸው ነው የሚከበሩት፡፡ ይሀው ኢስላም የማያውቀው፣ የሺርክ መነሀሪያ፣ የጭፈራ እና የመደለቂያ ፈጠራ (ልደት ማክበር) ከመጣ በኋላ በተለይ በሀገራችን ይህን ሁሉ ውዥንብር እያየን ነው፡፡ ረቢአል አወል አስራ ሁለትን አልፈው ከአምስት ወር በኋላም ጭፈራ፣ መብላት መጠጣታቸውን ለመወጣት ያከብሩታል፡፡ መቼም የቢድኣ (ዲንን የማፍረስ) አባዚ የተጠናወተው በአንድ ቢድኣ ላይ አይቆምም፡፡ ይሀው አንዷ ቢድኣ ቀን አልበቃቸው ብላ ያችኑ ቢድኣ በተለያየ ቀን ያጨማልቋታል፡፡

በሀገራችን የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደት የሚሉትን ብቻ አይደለም የሚያከብሩት፡፡ ይልቁንም የአብሬት መውሊድ፣ የቃጥባሬ መውሊድ፣ የዳንግላው መውሊድ….. የመሳሰለውን እየተባለ በተለያየ ቀናት አመቱን ሙሉ የሺርክ እና ክህደት ስንኞች ይዜማሉ፣ ሴት እና ወንድ ተደብልቀው ይጨፈራል፣ ይህ መርዝ አደገኛ ቅጠል ጫት ይታኘካል፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት የለውም)” ብለዋል፡፡ መውሊድ አላህም መልክተኛውም አላዘዙበትም፡፡

ከሁሉ የሚገርመው እዚሁ መስጂድ ላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ቂርኣት መቅራት ጀምረው ነበር፡፡ ግን ተከለከሉ፡፡ አህባሽን መስጂድ ውስጥ የሚያስጨፍር፣ ተማሪዎችን ቂርኣት የሚከለክል ኡለማ፣ ባለሃብት እና ኮሚቴ ነገ አላህ ፊት ምን ይሆን መልሱ?

ያሳዝናል መስጂዱ በስንት መከራ እና መስዋትነት እንደተሰራ የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ዛሬ ግን ቂርኣት ተከልክሎ መውሊድ የሚደለቁበት መስጂድ ሆኗል፡፡ አላህ ተውሒድ እና ሱና የበላይ የሚሆንበትን፣ ሺርክ እና ቢድኣ የሚዋረድበትን ወቅት ያቅርብልን፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ዘረኝነት?
ማንም ከማንም አይበልጥም፣ ማንም ከማንም አያንስም አላህን በመፍራት ቢሆን እንጂ፡፡

ነብዩ (ﷺ) ከመሞታቸው በፊት ስለ ዘረኝነት አስከፊነት መክረውን ነበር፡፡

“አረብ እኮ አረብ ባልሆኑት ላይ ብልጫ የለውም፣
አረብ ያልሆነውም በአረብ ላይ ብልጫ የለውም፡፡
ነጭ (ፈረንጅ) በጥቁር ላይ ብልጫ የለውም፣
ጥቁርም በነጭ ላይ ብልጫ የለውም
አላህን በመፍራት ቢሆን እንጂ፡፡”

የአላህ ውድ፣ ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) እንዲህ በሽታችንን ሁሉ ግልፅልፅ አድርገው ነግረውናል፡፡ መድሃኒቱንም ነግረውናል፡፡
ለሚመከር ከነፍሱ በላይ የሆኑ መካሪ ናቸው፡፡ አላህ ጀነት ላይ የእኝህ ውድ መካሪያችን ጎረቤት ያድርገን፡፡

አላህ ሀገራችንን ከዘረኝነት የፀዳች፣ አላህን በመፍራት ላይ የተገነባች ያድርጋት፡፡
https://t.me/SadatTextPosts