ከጠዋቱ ለ 12 ሰዓት 5 ጉዳይ የሚሰገደውን ፈጅር ሰላት መስጂድ ሄዶ የማይሰግድ በየጫት ቤቱ፣ በየ እስታድየሙ፣ በየ ፊልም እና ቲያትር ቤት የማይጠፋው የሙስሊም ወጣት ሶሻል ሚድያ ላይ መጥቶ “ተበደልን፣ ጥያቂያችን አልተመለሰም…..” ይላል፡፡
መልሱ በጣም አጭር ነው፡፡ አላህ ያዘዘንን ስንተገብር አላህ የሚያስፈልገንን ሁሉ ይለግሰናል፡፡
ሰው የዘራውን ያጭዳል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts

ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ውርደት እና ክብረቢስነት ትእዛዜን በጣሰ ላይ ሆነች” ብለዋል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማርያም ወዳጅ እንጂ ጠላት አይደለንም!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ሰሞኑን #እስቴ ላይ መስጂዶች የተቃጠሉት በአንድ የሙስሊም ሰርግ ላይ ለዲኮርነት በተበተነ ወረቀት ላይ "የማርያም ምስል" መገኘቱ ነው። በርግጥ ወረቀቱ ባህርዳር ከተማ ውስጥ ከሚገኝ ማተሚያ ቤት የተገዛ ሲሆን በተበተነው ወረቀት ውስጥ የተገኘው ዘግይቶ ከሰአት በኋላ ነው። ሆን ተብሎ አልተፈፀም ማለት ነው።
·
በርግጠኝነት ይሄ ወረቀት የተገኘው ከአንድ ክርስቲያን ሰርግ ላይ ቢሆን የአራት የአምስት ሰዎች አጀንዳ እንኳን መሆን አይችልም ነበር። ስለዚህ ጉዳዩ ያ ሁሉ ጥፋት የተከተለው አጀንዳ የሆነው ከሙስሊም ቤት መገኘቱ ነው። ሙስሊሞች ሆነ ብለው ለትንኮሳ አድርገውታል ብሎ ከማሰብ ወይም ለማርያም ክብር የላቸውም ከሚል እሳቤ የመነጨ ይመስለኛል።
በርግጥ እኛ እንደ ሙስሊም የማንም ምስል ቢሆን ለስእል ክብር የለንም። የእየሱስም ተባለ የሙሐመድ፣ የማርያምም ተባለ የዓኢሻ ለኛ ልዩነት የለውም። ነገር ግን ይህንን አቋማችንን
ለትንኮሳና ለብጥብጥ አናውለውም።
·
ስለ ማርያም ያለን እምነት ግን በአክብሮት የተሞላ ነው። አክብሮታችንም ከቁርኣንና ከነብያችን (የአላህ ሶላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) አስተምህሮት የተቀዳ ነው። ለምሳሌ ያክል ጥቂት ብናይ:–
① ማርያም በአምላካዊ እንክብካቤ ስር በሥርዓት ተኮትኩታ ያደገች እንደሆነች ቁርኣን ይመሰክራል
(وَأَنْبَتَهَا نَبَاتًا حَسَنًا)
"(ጌታዋም) በመልካም አስተዳደግ አሳደጋት፡፡" [ኣሉ ዒምራን: 37]
② ማርያም ጌታዋን ፈሪ፣ ህጉን አክባሪ፣ የተሟላ ስብእና ባለቤት ነች ይላል የፈጠራት ጌታ
(وَإِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاكِ وَطَهَّرَكِ وَاصْطَفَاكِ عَلَى نِسَاءِ الْعَالَمِينَ * يَا مَرْيَمُ اقْنُتِي لِرَبِّكِ وَاسْجُدِي وَارْكَعِي مَعَ الرَّاكِعِينَ )
"መላእክትም ያሉትን (አውሳ)፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነፃሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡» «መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ፡፡ ስገጂም፡፡ ከአጎንባሾቹም ጋር አጎንብሺ፡፡» [ኣሉ ዒምራን: 42–43]
ስለዚህ ማርያም የከበረች ሙስሊም ነች። ሙስሊም ማለት ለፈጣሪ እጅ የሰጠ፣ ለትእዛዙ ያደረ ማለት ነው። ማርያም ደግሞ በሚገባ ለጌታዋ እጅ የሰጠች ነበረች።
③ ማርያም ከሃዲዎች ከወነጀሏት የዝሙት ፍፁም የራቀች፣ ይልቁንም በአምላክ ፈቃድ በተአምር ፀንሳ የወለደች ናት። አላህ በቁርአን እንዲህ ይላል:–
(إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ )
"መላእክት ያሉትን (አውሳ)፡- ‘መርየም ሆይ! አላህ ከርሱ በሆነው ቃል ስሙ መሲሑ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በሆነ (ልጅ) ያበስርሻል፡፡’ " [ኣሉ ዒምራን: 45]
④ ልጇም የዝሙት ልጅ ሳይሆን ከታላላቅ የፈጣሪ መልእክተኞች እንደሆነ በቁርአን ተመስክሯል።
( إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّهِ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَى مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِنْهُ )
"መሲሑ የመርየም ልጅ ዒሳ የአላህ መልክተኛ፣ ወደ መርየም የጣላት ‘የሁን’ ቃሉ እና ከእርሱ የሆነ መንፈስም ነው፡፡" [አንኒሳእ: 171]
⑤ ማርያም የእውነተኞች ተምሳሌት ናት። ፈጣሪ እንዲህ ይገልፃታል:–
(مَا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِنْ قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ كَانَا يَأْكُلَانِ الطَّعَامَ)
"መሲሑ የመርየም ልጅ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡" [አልማኢዳህ: 75]
⑥ ባጠቃላይ ማርያም የጌታ ተአምር ነች ማለት ይቻላል። በቁርአን እንዲህ ተገልፃለች: –
(وَجَعَلْنَا ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ آيَةً )
"የመርየምን ልጅና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው፡፡" [አልሙእሚኑን: 50]
⑦ መርየም ከታላላቅ የጀነት (ገነት) ሴቶች ውስጥ እንደሆነች ነብያችን መስክረዋል ። [ሙስነድ አሕመድ: 2668]
·
ይሄ እምነታችን ከቁርኣን የወሰድነው፣ ከቀደምቶቻችን የወረስነው ነው። ይሄ ሐቅ ሙስሊሞች በጣም ጥቂትና ደካሞች በነበሩበት የመካ ዘመን ጀምሮ ሃገር እስከመሰረቱበት የመዲና ዘመን ድረስ የፀና ነው። በአንድ ወቅት የቁረይሽ ዐረቦችን እንግልት ሸሽተው ወደ ሐበሻ ተሰደው ይኖሩ የነበሩ ሙስሊሞችን የኢትዮጵያው ንጉስ ስለ ዒሳ (እየሱስ) ሊጠይቃቸው ፈልጎ ሰው ላከባቸው። ንጉሱ በጊዜው አልሰለመም ነበርና ምን ብለው ሊመልሱለት እንደሚገባ ለመመካከር ተሰባሰቡ። ስለ ዒሳ ከጠየቃችሁ ምንድነው መልሳችሁ?" ተባባሉ።
"ወላሂ! በዚህ ጉዳይ ላይ የፈለገ አካል ቢመጣ ስለሱ አላህ የተናገረውን ፣ ነብያችን ያደረሱንን ነው የምንናገረው!!" ተባባሉ።
ንጉሱ ዘንድ እንደገቡም "የማርያም ልጅ ስለሆነው እየሱስ ምን ትላላችሁ?" የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። እየመራቸው የገባው የነብዩ የአጎት ልጅ የሆነው ጀዕፈር እንዲህ አለ:–
"ስለሱ ነብያችን ያመጣልንን ነው የምንለው። እሱ (ዒሳ) የአላህ ባሪያና መልእክተኛ ነው። እርሱ ከፈጠራቸው ነፍሶች ውስጥና ወደ ድንግሏ መርየም የጣለው የሁን ቃሉም ነው።"
ንጉሱ በዚህን ጊዜ በእጁ መሬቱን መታና እንጨት አንስቶ የመርየም ልጅ ዒሳ ከተናገርከው እቺን እንጨት የምታክል አላለፈም" አለ። [ሙስነድ አሕመድ: 1742]
·
ይህ ነው ስለ ማርያም ያለን እምነት። ድንበር ማለፍ የሌለበት፣ አሷን ወደ ማምለክና ወደ መማፀን የማይሻገር ፍፁም አክብሮት። ይሄ ስለሷ ብቻ ሳይሆን ስለሌሎችም ፃድቃን ያለን እምነት ነው።
በእርግጥ "የማርያም ምስል" ተብሎ አሁን ክርስቲያኖች ዘንድ የሚገኘውን ስእል በተመለከተ እሷን ለመምሰሉ ማንም ማረጋገጫ ሊያቀርብበት አይችልም። ምክንያቱ ለማንም አይሰወርም።
·
በነገራችን ላይ ስእሎችን ማክበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የለውም። ለምሳሌ ያክል ጥቂት ጥቅሶችን እንይ:–
"በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር #የማናቸውንም_ምሳሌ፥ #የተቀረጸውንም_ምስል ለአንተ አታድርግ።"
(ኦሪት ዘጸአት 20:4)
" እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ #የተቀረጸም_ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።"
(ኦሪት ዘሌዋውያን 26:1)
"እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥ "
(ኦሪት ዘዳግም 4:16)
"አምላካችሁም እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የተማማለውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፥ አምላክህም እግዚአብሔር የከለከለውን #በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።" (ኦሪት ዘዳግም 4:23)
"በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር #የማናቸውንም_ምሳሌ #የተቀረጸውንም_ምስል ለአንተ አታድርግ፤"

(ኦሪት ዘዳግም 5:8)
" #ለተቀረጸ_ምስል የሚሰግዱ #ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ መላእክቱ ሁሉ፥ ስገዱለት።" (መዝሙረ ዳዊት 97:7)
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 28/2011)

ሙስሊም በሙስሊም ላይ አምስት መብት አላቸው
1) ሰላምታን መመለስ (አሰላሙ አለይኩም ሲባል ወአለይኩም ሰላም ብሎ መመለስ)፣
2) በሽተኛን መጠየቅ (ሲታመም መጠየቅ)፣
3) ሲሞት ሪሳውን (ጀናዛውን) መሸኘት (መቅበር)፣
4) ጥሪን ማክበር (ጥሪ ሲጠራህ ጥሪውን ተቀብለህ መሄድ)፣
5) ሲያነጥስ (አልሐምዱሊላህ ሲል) የርሀሙከላህ (አላህ ይዘንልህ) ብሎ መልስ መስጠት
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
https://t.me/SadatTextPosts
1) ሰላምታን መመለስ (አሰላሙ አለይኩም ሲባል ወአለይኩም ሰላም ብሎ መመለስ)፣
2) በሽተኛን መጠየቅ (ሲታመም መጠየቅ)፣
3) ሲሞት ሪሳውን (ጀናዛውን) መሸኘት (መቅበር)፣
4) ጥሪን ማክበር (ጥሪ ሲጠራህ ጥሪውን ተቀብለህ መሄድ)፣
5) ሲያነጥስ (አልሐምዱሊላህ ሲል) የርሀሙከላህ (አላህ ይዘንልህ) ብሎ መልስ መስጠት
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
https://t.me/SadatTextPosts
የኢትዬጵያ ሚድያዎች?
ሙስሊሞች ሆይ! እንደሚታወቀው ዛሬ በሚድያ ብዙ ነገሮች ይደረጋሉ፡፡ ሙስሊሞችም ዘፋኝ፣ ፖለቲከኛ፣ ኳስ ተጫዋች፣ የፖለቲካ ሚድያ፣ ኢቢሲ፣ ፋና፣ ኢቢሴስ፣ ሸገር፣ ኤልቲቪ፣ ጄቲቪ፣ ኢሳት፣ ኦኤምኤን፣ አማራ ቲቪ እና ሌሎችም ጣቢያዎች አይቀራቸው በሰፊው ይከታተላሉ፡፡ ፊስቡክ እና ዩቲውብ ገፃቸውንም ላይክ ያደርጋል፡፡
ሁሉም ሚድያዎች ማለት ይቻላል ፍትሀዊ አይደሉም፡፡ ወገንተኞችም ናቸው፡፡ ለዚህ ታላቁ መድሃኒቱ እነዚህን ሚድያዎች እርግፍ አድርጎ መተው ነው፡፡ ምንም አይነት ግንኙነት ከነሱ ጋር አለማድረግ ነው፡፡ ተመልካች ባይኖራቸው ሐቁን ለማቅረብ ይገደዳሉ፡፡
እውነተኝነት ቢኖር ኖሮ ሀገራችን የት በደረሰች ነበር፡፡ ነገር ግን በምላስ ስለ እውነት፣ ስለ ሀገር ፍቅር፣ የሰዎችን እምነት ስለማክበር፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዘሩ ከማንም በላይ ከማንም በታች ሳይሆን ተከብሮ ይኖራል እየተባለ ይወራል፡፡ በተጨባጭ ግን ከፊል ሀይማኖቶችን የማንገስ ከፊሎቹን የማፍረስ፣ ከፊሉን ዘር ከፍ የማድረግ ከፊሉን የማግለል ተንኮል በደንም ይፈፀማል፡፡
እውነተኛው አምላክ ደግሞ ከሰባት ሰማይ በላይ ሆኖ ይህንን የውሸት ክምችት ስለሚመለከት ካለንበት መከራ መውጣት አቅቶናል፡፡
ሀገር በእውነት ላይ ካልተገነባች የሁሉ ፈጣሪ አላህ ካለችበት መከራ አያወጣትም፡፡
ሀገራችን ላይ ሚድያዎች እና ፖለቲከኞች ሙስሊሞች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚያደርሱት ጫናዎች ከባዶች ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ዋናው
“መቻቻል” የሚባለው ቃል ነው፡፡
መቻቻል ቃሉ መልካም የሚመስል ውስጡ እና ተግባሩ መርዝ የሆነ አካሄድ ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ ሙስሊም የክርስትና እምነት መገለጫ የሆነውን የጥምቀት በአል አብሮ ወጥቶ ታቦት ካልሸኘ “ሀገራችን ላይ ኢስላማዊ አክራሪዎች እየተስፋፉ ነው፡፡” ይባላል፡፡
አንድ ክርስትያን ግን “የኢድ ስግደት ላይ እስታዲዬም አልገኝም፡፡”፣ ወይንም “እሬቻ በአል ከኦርቶዶክስ ጋር አይሄድም” ቢል፣ “ሃይማኖት የግል ነው ሀገር የጋራ ነው” ተዉት ሁሉም ሃይማኖቱን ይከተል ይባላል፡፡
በሌላ ጎኑ አንድ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ “ጥምቀት በአል ላይ አልገኝም፣ ታቦት አልሸኝም፡፡” ቢል ማንም አይናገረውም፡፡
እኛ ሙስሊሞች ታቦት መሸኘትም ይሁን፣ እሬቻ፣ አሸንዳ ላይ መሳተፍ ሃይማኖታችን አይፈቅድልንም፡፡ ሃይማኖታችን የማይፈቅዳቸውን ነገሮች ደግሞ ለምን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጫና ይፈጠርብናል?
ከወራት በፊት እራሱ በመቻቻል ስም “የማስመሰል” ተግባር ተፈፅሟል፡፡ አላህ የሁሉ ፈጣሪ ደግሞ አስመሳይነትን አይወድም፡፡ አስመሳይነት የተጣላ ባህሪ ነው፡፡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዬች ሃይማኖታቸው የማያዛቸውን አንዋር መስጊድ መጥተው አፀዱ፡፡ የእስልምና እምነት ተከታዬች ነን የሚሉትም አማኑኤል ቤተክርስትያንን ሄደው የማያምኑበትን መስቀል ቲሸርታቸው ላይ አሳትመው ለብሰው አፀዱ፡፡ ይሄ በፍፁም መቻቻል አይደለም፡፡ ይሄ ማስመሰል ነው፡፡ አስገራሚው ኡስታዝ ተብየዎች ይህንን ተግባር የተወደደ እና የተወደሰ ነው ሲሉ በኢቲቪ ቀርበው ተናግረዋል፡፡ አላህ ከአስመሳይነት ይጠብቀን፡፡
መቻቻል ማለት አንድ ክርስትያን ሲቸገር፣ ሲታመም፣ ሲታረዝ ሙስሊም የሆኑ ሰዎች ይረዱታል፡፡ እምነቱን ግን አብረውት ያከብራሉ ማለት አይደለም፡፡ ልክ እንደዚሁ አንድ ሙስሊም ሲቸገር፣ ሲታመም፣ ሲታረዝ ክርስትያኖች ይረዱታል፡፡ አብረናችሁ ረመዳንን እንፁም ወይንም በኢስላም አመኑ ማለት አይደለም፡፡ ሀገራችን ላይ በለቅሶ፣ በድርቅ በተለያዩ መከራ እና ደስታዎች ሁሉም የእራሱን እርድ አርዶ በጋራ ተኑሯል፡፡ ይሄ ትክክለኛ መቻቻል ነው፡፡
ሙስሊሞች የበዙበት አካባቢ ክርስትያኖቹን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለመስጂድ መስሪያ አዋጡ ሊባሉ አይገባቸውም፡፡ ወይንም ክርስትያኖች የበዙበት አካባቢ መስጂዶችን ማቃጠል ወይንም የሙስሊሞችን ሱቅ መዝረፍ ይቻላል ማለት አይደለም፡፡ ይሄ መቻቻል አይደለም፡፡
ቤተክርስትያን ሲቃጠል ያውም ከጀርባው ድብን ያለ የፖለቲካ ትርፍ የሚተረፍበት ብሎም በሙስሊሙ እና በክርስትያኑ መካከል ጠብ እንዲነሳ የሚፈለግበትን ተግባር፣ የኢትዬጵያ ሚድያዎች ሞቅ አድርገው ደጋግመው ይዘግባሉ፡፡ በተገላቢጦሹ ሙስሊሞች መስጊዳቸው ሲቃጠልባቸው በጆሮ ዳባ ልበስ ይታለፋል፡፡ ለምን የሙስሊሞች መስጊድ መቃጠል አልተዘገበም ማለት ቤተክርስትያን መቃጠሉን መደገፍ ማለት አይደለም፡፡ ቤተክርስትያኖቹን ማን እንዳቃጠላቸው፣ አቃጣዬቹን ማን እንደላካቸው በደንብ ማጣራትም ይበጃል፡፡ ዛሬ ሀገሪቱን ለማፍረስ የተለያዩ አላማ ያላቸው ፖለቲከኞች የበዙባት ሀገር ናት፡፡ አላህ ፍትህን እና ሰላም ያስፍን፡፡
ፍትህ ማለት በምላስ የምትነገር ቃል ብቻ አይደለችም፡፡ በተግባር የምትሰራም ጭምር ብትሆን እንጂ፡፡
አላህ ሀገራችንን ከገባችበት መከራ ያውጣት፡፡

ለሙስሊሙ ብቸኛው መፍትሄ ወደ አላህ በተውበት በመመለስ፣ ከሺርክ፣ ከቢድኣ፣ ከዘረኝነት፣ ከተለያዩ ሱሶች በመራቅ ተውሒድን፣ ሱናን እውነተኛ ወንድማማችነትን አንግቦ መንቀሳቀስ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ “ኮሚቴው መግለጫቸው ላይ ይህን ጠብቀን ነበር፣ ምርጫው መቼ ነው የሚካሄደው፣ አህባሽ መጅሊስ መቼ ነው የሚለቀው፣ ተበደልን……” እያሉ የሚፅፉ ሰዎች በጣም ይገርሙኛል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن تَنصُرُوا۟ ٱللَّهَ يَنصُرْكُمْ وَيُثَبِّتْ أَقْدَامَكُمْ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የአላህን ህግጋት ብትፈፅሙ፤ (አላህ) ይረዳችኋል፡፡ ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል፡፡
መስፈርቱን ሳናሟላ፣ መስፈርቱን ላሟሉ ሰዎች የተቀመጠውን ሽልማት ስንመኝ እንኖራለን፡፡ በጣም በሚገርም ሁኔታ አሁን ከምንም ጊዜ በበለጠ ወጥረን የምንሰራበት ጊዜ ነው፡፡ እውቀትን መገብየት የምናውቀውን አሉ በሚባሉ መንገዶች ሁሉ ማስራጨት፡፡ የላኢላሃኢለላህን ትርጉም ጠንቅቆ የማያውቅ ብዙ ማህበረሰብ ባለበት ሀገር ላይ “ጴንጤ ሙስሊሙን እያከፈረ ነው” ብሎ መፎከሩ የትም አያደርስም፡፡ ጠንክሮ ተውሒድን ሱናን ሌሎች ኢስላማዊ እውቀቶችን በሰፊው ለኡማው ማሰራጨት ነው፡፡
እስቲ ልብ በሉ
1) ከአህባሽ ጋር “የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት….ኮንፍረንስ” ብሎ የተደበለ ለሙስሊሙ ምን ያመጣል?
2) 300 “ኡለማዎች” ተሰብስበዋል በተባለበት ስብሰባ ላይ “እድሉ መጥቶልናል፡፡ ወላሂ ወቢላሂ ከአሁን በኋላ ሙሳም ቢመጡ ኢሳም ቢመጡ ነብዩና ሙሐመድም ቢመጡ ከዚህ የበለጠ እድል…” ሲል አደም ካሚል ሌሎቹ “አላሁ አክበር” እያሉ የገዛ ዲናችንን እየናዱ ከነዚህ ሰዎች ምን እንጠብቃለን? ለሙስሊም ምንስ ያመጣሉ?
3) የሺርክ መነሃሪያ የሆነውን “መውሊድ” የሚያንቆለፓፕስ ቴሌቭዥን ላይ ቀርበው የሚያጭበረብሩ ለኡማው ምን ያመጣል?
4) ሙስሊም ነኝ እያለ በጥንቆላ መፀሀፍ በሸህ ሁሴን ጂብሪል የሚያምን “መብቴ ተነካ፣ ተበደልኩ” ቢል ምን ያመጣል?
5) እውቀት አላቸው የሚባሉ ሰዎች ሐቅን ሳይናገሩ ብሎም ሐቅን እየደበቁ …. ለሙስሊሙ ምን ያመጣሉ?
6) አብዛኛው በዘረኝነት ተወሮ ላኢላሃ ኢለላህ ያለ ወንድሙን እህቱን የሚገድል፣ የሚዘርፍ፣ ክብራቸውን የሚያጎድፍ፣ ዲን ያውቃሉ የሚባሉት አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ ይህንን እያዩ እየሰሙ ዝም ብለው ለኡማው ምን ያመጣል?
7) እስታድዬም ሄደው ጉሮሯቸው እስኪሰነጠቅ ሲጮሁ ይውሉና፣ ፊልም ሲያዩ ያመሹና አላህ ግዴታ ያለውን የፈጅር ሰላት ከነጋ እና ፀሃይ ከወጣ በኋላ እየሰገዱ “መብት፣ መብት” ቢሉ ምን ያመጣሉ?
8) ሴቷ ከጉልበቷ በታች፣ ከቁርጭምጭሚቷ በላይ እየለበሰች፣ ደረቷን እያሳየች፣ ሜክ አፕ እና ሽቶ ተቀብታ እየዞረች…. ምን ታመጣለች?
9) ሙስሊም ነኝ እያለ………..
ብቻ አላህን እንፍራ፡፡ ሐቅ ካልያዝን፣ በሐቅ ላይ ካልተሰባሰብን፣ በሐቅ ላይ ካልፀናን መሬት ብንቧጥጥ ምንም ጠብ አይልልንም፡፡
ሙስሊሞች ሆይ! የአላህን ህግጋት ስንተገብር አላህ በዱንያም በአኸይራም የገባልንን ቃል ይሞላልናል፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

👆🏻አላህን ማወቅ
አጠር ያለች መፀሀፍ
ዝግጅት ዶክተር ሷሊህ አል-ሷሊህ (ረሂመሁላህ)
አጠር ያ ማብራሪያዎች በሳዳት ከማል
ይህንን ሶፍት ኮፒ ከሚከተሉት የቴሌግራም ቻናል ሊንኮች ማውረድ ይችላሉ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/1630
https://t.me/SadatTextPosts/401
https://t.me/Kitaboch/38

Telegram
SadatKemal Abu Meryem
የሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ጆይን በማለት ተቀርተው ያለቁ ሙሉ የኪታብ ኦዲዬዎችን ዳውን ሎድ ያድርጉ
https://t.me/Kitaboch
አርባኢን (40 ሀዲሶች)
አቂደቱል ዋሲጥያ (በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ)
አል-ዋጂባት
ኹዝ አቂደተክ
አል-ኡሱል አስ-ሰላሳ
አል-ቀዋኢዱል አል-አርበኣ
በተጨማሪ ከ300 በላይ ሙሃደራዎች ለማግኘት የሚከተለውን ቴሌግራም ቻናል ጆይን ይበሉ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ የአላህ ባሪያዎች ሆይ!
አጀሩምያህ ሙሉው ደርስ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሃያ ሶስት
በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር ግደይ
የሚከተለውን ሊንክ ጆይን በማለት ማግኘት ይችላሉ
https://t.me/Kitaboch
አጀሩምያህ ሙሉው ደርስ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሃያ ሶስት
በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር ግደይ
የሚከተለውን ሊንክ ጆይን በማለት ማግኘት ይችላሉ
https://t.me/Kitaboch
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ የአላህ ባሪያዎች ሆይ!
ኩን ሰለፊየን አለል ጃዳህ ሙሉው ደርስ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሃያ አምስት
በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር ግደይ
የሚከተለውን ሊንክ ጆይን በማለት ማግኘት ይችላሉ
https://t.me/Kitaboch
ኩን ሰለፊየን አለል ጃዳህ ሙሉው ደርስ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሃያ አምስት
በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር ግደይ
የሚከተለውን ሊንክ ጆይን በማለት ማግኘት ይችላሉ
https://t.me/Kitaboch
እውነት ኢትዮጵያ የአህለ ሱና ሀገር ናትን?
★★★★★★★★★★★★
ኢትዮጵያ ሀገራችን የአህለ ሱና ሀገር ብትሆን ምንኛ ደስ ባለን ነበር። ነገር ግን ሺርክ፣ ቢድአ፣ መሀይምነት፣ ዘረኝነት፣ አመፀኝነት በሰፊው የተንሰራፋባት ሀገር ናት።
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደረባዎቻቸውን ወደ ሀበሻ ሁለት ጊዜ ስደት እንዲሄዱ ነበር ያዘዙት።
ተውሒድን ከማንም በላይ ይፋ ማድረግና ከሺርክ መራቅ ሲገባን፣ አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ አብዛኛው ሺርክ እና ቢድአ በማጨማለቅ ላይ ነው።
"ሀገራችን የአህለ ሱና ሀገር ነው። ሁሉም አህለ ሱና ነው።" ብለው የሚዋሹ ሰዎች ስላሉ፣ ሀገራችን የአህለሱና ሀገር እንዳልሆነችና ሁሉም አህለ ሱና እንዳልሆነ በተጨባጭ ማስረጃ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ
ሺርክ ማለት ለብቸኛው ፈጣሪ አላህ የሚገባውን አምልኮ ለፍጡራን (መላኢካ፣ ነብይ፣ ጂን፣ ሷሊህ፣ ወልይ፣ ዛፍ፣ ዲንጋይ …) መስጠት ነው።
እውነት ሀገራችን የአህለ ሱና ሀገር ናት ወይንስ ሺርክ እና ቢድአ የተንሰራፋባት የሚለውን ለማየት የሚከተሉት ሀገራችን ላይ በየአቅጣጫው በሰፊው የሚሰሩ በአድ አምልኮዎችና፣ ኢስላም ላይ የተጨመሩ ቢድአዎች በከፊሉ እዘረዝራለሁ
1) በጎንደር "ጌታው ሸህ አሊ ግንደር፣ ሸህ አብድል ባሲጥ፣ ሸህ አባድር፣ ፈቂህ አሊ ሙዝ …" እየተባለ ለነዚህ ከአላህ ውጭ ላሉ ፍጡሮች ለአላህ ብቻ የሚገባው አምልኮ ይሰጣቸዋል፣
2) አሁንም በጎንደር "የእሽት ዶሮ" እየተባለ ዶሮ ለእርኩስ መንፈስ ይሰጣል፣
3) ጎጃም አዴት የሚባል ቦታ ለሞተ ውሻ እላዩ ላይ ቀብር ተሰርቶለት ይመለካል፣
4) ወሎ ደግዬ፣ ዳና ፣ እና እና ሌሎች ቦታዎችም ላይ ባአድ አምልኮ ይፈፀማል፣
5) አንበሶ፣ አዳል ሞቴ፣ ራሂሎ እና የመሳሰሉትን እየተባለ ለጂኖች "ሙወከል" እየተባለ ለሰይጣን ዶሮ ይታረድለታል፣
6) አዲስ አበባ የድሮ እስላም መቃብር የሸህ ሀሰን በቱል ቀብር ይመለካል፣ "ዱአ አድራጊ ናቸው" በሚል ስም ብዙ ጠንቋዮች ይመለካሉ፣
7) ጉራጊ አብሬት፣ ቃጥባሬ ከአላህ ውጭ ይመለካሉ፣
8) ስልጤ አልከሶ፣ ኑርሁሴን ከአላህ ውጭ ይመለካሉ፣
9) ካእባ ላይ ብቻ መደረግ ያለበትን ጠዋፍ ኦሮሚያ ባሌ ኑር ሁሴን ቀብር ላይ ጠዋፍ ይደረጋል፣
10) "የሸህ ሁሴን ትንቢት" እየተባለ በጥንቆላ ይታመናል፣
11) ምስራቅ ኢትዮጵያ ለጅብ ገንፎ በማገንፋት ባእድ አምልኮ ይፈፅማሉ፣
12) አላህ ያላዘዘው፣ ነብዩ ያልሰሩት ያላዘዙት "መውሊድ (የነብዩ ልደት)" ብለው በክህደት ስንኞች፣ በመጨፈር፣ በማፏጨት፣ ጫት በመቃም፣ ሴት እና ወንድ በመቀላቀል ያሳልፉታል፣
13) የአላህን ስም እና መገለጫዎች የሚያጣሙ ብሎም የማይቀበሉ አህባሽን ይመስል የጥመት ቡድኖች አሉ፣
14) ሀገራችን ላይ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደረባዎች የሚሰደቡበት ኪታብ ይሸጣል፣ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይከፋፈላል፣
15) አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተማዎችም ላይ ሀሙስ ማታ ከመግሪብ እስከ ኢሻ ብለው በሰለዋት ስም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይመጣሉ ብለው ከተቀመጡበት "መርሃባ ነቢ" ብለው ይነሱላቸዋል፣
አረ ስንቱ……
ታድያ ይህችን ሀገራችንን ነው "ሀገራችን የአህለ ሱና ሀገር ነው። ሁሉም አህለ ሱና ነው።" እየተባለ የውሸት ምስክርነት የሚሰጣት?
አላህ ለምን አይፈራም።
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በአላህ ስም ምዮ የምናገረው ተውሒድን እና ሱናን የተፃረረ ብሎም ሺርክ እና ቢድአን የሚያጨማልቅ አህለ ሱና አይባልም።
አህለ ሱናዎች ማለት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው የነበሩባትን መንገድ የሚከተሉ ናቸው።
ነብዩ እና ሰሀባዎቻቸው ደግሞ ከላይ ከተጠቀሱት እርጉም እና እርኩስ የጥፋት መንገዶች የራቁ ናቸው።
የአህለ ሱናዎችን መንገድ የተቃረኑ ሰዎች የጮሁትን ያህል ቢጮሁ፣ የዋሹትን ያህል ቢዋሹ አላህ አያሳካላቸውም።
ይሀው ሀገራችን ላይ በትክክለኛው እምነት መሰባሰብ አቅቷቸው አላህ ውርደት ያቀመሳቸውን የጥፋት ቡድኖች እና ግለሰቦች እያየን ነው።
አላህ ባዘዘው መንገድ ያልተሰባሰቡ ተበታተኑ እንጂ አንድ ሆኑ አይባልም።
መፍትሄው የውሸት መስካሪዎችን፣ አውቆ አጥፊዎችን በጭፍን መከተል ሳይሆን ቁርአን እና ሀዲስ በሰሀባዎች መንገድ መረዳት ነው።
ሙስሊም ወንድም እና እህቶቼ ሆይ! አላህ ከፊትና ይጠብቀን። ከሁሉም የጥመት ቡድኖች ይጠብቀን። ብቸኛዋን የሐቅ ጎዳና ይምራን።

አቂዳ አንድ ያላደረጋቸውን የበሬ አጥንት አንድ አያደርጋቸውም፡፡
★★★★★★★★★★★★
በአቂዳ ተለያይተው አንድነት እና ሰደቃ እያሉ በሬ አርደው በመብላት አንድ እንሆናለን ብለው ያሰቡትን ሰዎች መጨረሻ ተመለከታችሁን?
በኒ መስጂድ እና አየር ጤና ላይ ጥግ ጥጋቸውን ይዘው መደስኮራቸውን ይዘዋል፡፡
አቂዳ አንድ ያላደረጋቸውን በሬ አርዶ መብላት እና አብሮ ፎቶ መነሳት አንድ አያደርጋቸውም፡፡
በጥመት ላይ የተሰባሰቡ ሰዎች መጨረሻቸው ይህ ነው፡፡ አብዛኛውን ምስኪን ቢሸውዱትም አላህ ሁሉን ተመልካች ነውና አያሳካላቸውም፡፡ በኪታብ እና በሱና አንድ መሆን አቅቷቸው፣ በል እንዲያውም ወደ ተውሒድ እና ሱና የሚጣሩ ወንድሞችን “የኡማው ጠላቶች” እያሉ ከሺርክ እና ቢድኣ ሰዎች ጋር አብረው ሄደው ሲዶልቱ እና ሲተሻሹ የነበሩ ሰዎች ይሀው ውርደታቸውን ቀመሱ፡፡ ከተቋም በፊት በእምነት አንድ መሆን ይጠበቃል፡፡አላህም በእምነት ገመድ አንድ ሁሉ ሲል ነው ያዘዘው፡፡ ሱናን መፃረር ለውርደት ይዳርጋል፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! በኪታብ እና በሱና አላህ አንድ ያድርገን፡፡ አሽአሪ፣ ማትሩዲ፣ አህባሽ፣ ሱፊ፣ ኢኽዋን….. ከሚባሉ የጥመት ቡድኖች ሁሉ አላህ ይጠብቀን፡፡ ብቸኛዋን የጥንት የጠዋቷን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው የነበሩባትን የሰለፉነ ሷሊሂን መንገድ ይምራን፡፡

ኢኽዋንንም ይሁን ሌሎች የቢድኣ ቡድኖችን ማጋለጥ ለሙስሊሞች ከማዘን እና ከማሰብ ነው፡፡
★★★★★★★★★★★★
ከሺርክ እና ከባለቤቶቹ፣ ከቢድ እና ከባለቤቶች ማስጠንቀቅ ለሙስሊሞች ከማዘን እና ለእነሱ ከመቆርቆር ነው፡፡
ለሙስሊሞች ማዘን ማለት እንደ ኢኽዋን፣ ኸዋሪጅ፣ እና ሌሎችም ሙስሊሞችን ለችግር የሚዳርጉ ቡድኖችን እና ሚድያዎቻቸውን ማጋለጥ ነው፡፡ ሙስሊሞችን ለተለያዩ ችግሮች የዳረጉት ኢኽዋኖች ናቸው፡፡ ይህንን ደግሞ አይደለም ኢልም አለኝ የሚል ሰው እራሳቸው ኢኽዋኖች ክስረት እንዳመጡ እራሳቸው ላይ እየመሰከሩ ነው፡፡ለምሳሌ አረብ ሀገራት (ቱኒስያ፣ ግብፅ፣ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊብያ….) ሀገራችንም ላይ ተገለባባጭ እና ተለዋዋጭ የሆኑት ኢኽዋኖች ለፖለቲካ ጥቅማቸው ሲሉ በኢስላም ስም ሙስሊሞችን መከራ ላይ የዳረጉት፡፡
ሙስሊሙ በድጋሚ በነዚህ ሰዎች እንዳይሸወድ፣ እዚህ ከባድ መከራ ውስጥ ሙስሊሙን የከተቱት ኢኽዋኖች ናቸው ማለት ለሙስሊሙ አለማዘን አይደለም፡፡ እንዲያውም ከዚህ አደገኛ ቡድንም ይሁን ከሌሎች ቡድኖች ኡማውን ማስጠንቀቅ ለኡማው በጣም ከማዘን እና ከመጨነቅ ነው፡፡
በተገላቢጦሹ አንዳንድ የእውቀት ባለቤት ነን እያሉ ኡማው በነዚህ ተኩላዎች ሲሸወደ እያዩ ዝምታን የመረጡ ሰዎች አላህን አይፈሩትምን
አላህ እንዲህ ይላል
وَإِذْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ لَتُبَيِّنُنَّهُۥ لِلنَّاسِ وَلَا تَكْتُمُونَهُۥ فَنَبَذُوهُ وَرَآءَ ظُهُورِهِمْ وَٱشْتَرَوْا۟ بِهِۦ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ فَبِئْسَ مَا يَشْتَرُونَ
አላህ የነዚያን መጽሐፉን የተሰጡትን ቃል ኪዳን ለሰዎች በእርግጥ ታብራሩታላችሁ አትደብቁትምም በማለት የያዘባቸውን (አስታውሱ)፡፡ በጀርባዎቻቸውም ኋላ ጣሉት፡፡ በርሱም ጥቂትን ዋጋ ገዙ፡፡ የሚገዙትም ነገር ከፋ!
ይህ አንቀፅ አላህ እውቀት ሰጥቷቸው በእውቀታቸው የማይሰሩትን፣ እውነቱን ለሰዎች የማያብራሩትን እና የሚደብቁትን የሚወቅስበት ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ለቀላቢያቸው አልታመን ብለዋል፡፡ ሐቁን ደብቀዋል፡፡ ብሎም ለባጢል ጥብቅና ቆመዋል፡፡
ኢኽዋን የከሰረ የጥመት ቡድን ነው፡፡ ኢኽዋን ከእለት እለት ኪሳራው በግልፅ በወጣ ቁጥር ኢኽዋንን አናስነካም ብለው፣ ለኢኽዋን ጥብቅና የቆሙ፣ ማስረጃን ሲጠመዝዙ የነበሩ በጠቅላላ ከኢኽዋን በላይ የከሰሩ መሆናቸውን እያየን ነው፡፡
አላህ በሐቅ ላይ ይሰብስበን፡፡ ሐቅን በሐቅነቱ ያሳያን የምንቀበለውም ያድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ ያሳየን የምንርቀውም ያድርገን፡፡

አንድ ሙስሊም በአደባባይ ቢድኣ ሲሰራ፣ ዲን ሲፈርስ፣ የባጢል ሰዎች ቢድአቸውን ሲረጩ ካየ ከቁርኣን፣ ከሀዲስ፣ ከሰለፎች ወይንም ከኡለማዎች ንግግር ጠቅሶ መልስ መስጠት ይችላል ብቻ ሳይሆን ተገቢም ነው፡፡ ቢድአ እና ጥፋትን ለማስጠንቀቅ ከየትኛውም ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ ዲግሪ፣ ማስተርስ፣ ዶክትሬት ብሎም የየትኛውም መርከዝም ይሁን ግለሰብ ፍቃድ አያስፈልገውም፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
https://t.me/SadatTextPosts
በእስልምና ወሮች 12 ናቸው እነሱም
1) ሙሐረም፣
2) ሰፈር፣
3) ረቢእ አል-አወል፣
4) ረቢእ አስ-ሳኒ፣
5) ጀማዳ አል-አወል፣
6) ጀማዳ አስ-ሳኒ፣
7) ረጀብ፣
8) ሻእባን፣
9) ረመዳን፣
10) ሸዋል፣
11) ዙል ቃኢዳ፣
12) ዙል ሂጃህ ናቸው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
1) ሙሐረም፣
2) ሰፈር፣
3) ረቢእ አል-አወል፣
4) ረቢእ አስ-ሳኒ፣
5) ጀማዳ አል-አወል፣
6) ጀማዳ አስ-ሳኒ፣
7) ረጀብ፣
8) ሻእባን፣
9) ረመዳን፣
10) ሸዋል፣
11) ዙል ቃኢዳ፣
12) ዙል ሂጃህ ናቸው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የሀገራችን ጉዳይ ወሬ ሳይሆን ዱኣ ይፈልጋል፡፡ በየ ሶሻል ሚድያው፣ በየ ካፌው የማይጠቅም ወሬ ከማውራት፣ አንዱ የሌላውን ዘር ከማጥላላት አምርሮ ዱአ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ ምክንያቱም አላህን ለማምለክ እንኳን ሰላም አስፈላጊ ነው፡፡
አላህ ሀገራችን ላይ ፍትህ እና ሰላም ያስፍን፡፡ እሱም ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ ነው፡፡