Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
700 መቶ እንጀራ?
አላህ ለደነገገው ኢድ እና አራፋ የማያደርጉትን አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ላለዘዙት ቢድኣው መውሊድ ሀገራችን ላይ የሚከተለውን ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡

“40 በርሚል ቡሆ ይቦካል፡፡
ከዚያ ሲቀጠን ከ50-60 ይደርሳል፡፡
አንዱ በርሚል እስከ 700 መቶ እንጀራ ይሆናል፡፡
700 እንጀራ ይመጣል አንዱ በርሚል ብቻ፡፡”
ኢቢሲ ላይ ቀርበው የሰጡት ቃለ ምልልስ

ቢድኣ ለዚህ ኡማ ምንም አስተዋፅኦ የለውም፣ ዲንን መናድ እንጂ፡፡ ይሉ ይሆናል “በመውሊድ ይህን ያህል አውጥተን ድሀ ብናበላ ምኑ ላይ ነው ችግሩ?”
መልሱም
- አላህ ያላዘዘውን በኣል እኛ መደንገግ አንችልም፣
- ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው (አላህ አይቀበለውም)” ብለዋል፡፡ ልደቴን አመት ጠብቃችሁ አክብሩልኝ፣ አርዳችሁ አብሉልኝ ብለው አላዘዙም፡፡ ኢስላም ያላዘዘውን የሰራ ሰው ደግሞ ወደ አላህ መቃረብ ሳይሆን ከአላህ ይርቃል፣
- ድሃን ለማብላት አመት መጠበቅ አያስፈልግም… እውነተኛ ለደሃ ተጨናቂ ከአመት እስከ አመት ማብላት ይችላል፡፡
አላህ ሆይ! ህዝቡክ ከዚህ አደገኛ ቢድኣ አንቃልን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ልብ ሲታወር አደጋ ነው፡፡
አንዳንድ መውሊድ አክባሪ አህባሾችና ሱፍዬች የሚከተለውን ልባቸውን የታወሩበትን ግጥም ይገጥማሉ
“ሱናቸውን ይዘን ነቢን ተከትለን፣
ያስያዙንን ይዘን ያዘዙትን ወደን፣
የከለከሉትን እኛም ተከልክለን፣
የዊላዳውን ቀን እናከብረዋለን!!”

እስቲ እነ ሸህ ደፋሩ ልባቸው ታውሮ የሚያቀነቅኑትን ስንኝ መስመር በመስመር እንየው
1) “ሱናቸውን ይዘን ነቢን ተከትለን”
የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና ማለት እንግዲህ
- በቃል ያዘዙት፣
- በተግባር የሰሩት፣
- ሰሃባዎቻቸው ሲሰሩ አይተው ዝም ያሉት ነው፡፡
መውሊድ እንግዲህ በቃላቸውም አላዘዙበትም፣ በተግባራቸውም አልሰሩትም፣ እነዛ ስለስርዓት ያላቸው ሰሃባዎችም አልሰሩትም….. ታድያ እንዴት “ሱናቸው ይዘን ነቢን ተከትለን” ይላሉ?
እንዲያውም “ሱናቸውን ትተው ቢድዐን እና ሸይጧንን ተከትለው” የሚለው ነው እነሱ የሚፈፅሙትን የሚገልፀው፡፡
2) “ያስያዙንን ይዘን ያዘዙትን ወደን”
እዚህም ጋር መውሊድን ለማንም አላስያዙትም፡፡ ብሎም ያዘዙትን ወደን ካሉ እሳቸው ያዘዙት ሱናቸውን እንድንይዝ፣ ቢድዐን እንድንርቅ ነው፡፡ ይሀው እነሱ በተገላቢጦሽ ሸይጧን ጥፋታቸውን አሳምሮላቸዋል፡፡
3) “የከለከሉትን እኛም ተከልክለን”
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቢድዐ በዲን ላይ የሚደረግን ፈጠራ ራቁ ብለው አዘው እነዚህ ሰዎች አያፍሩም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ታላላቅ ከከለከሏቸው ነገሮች ውስጥ ቢድዐን ሆኖ ሳለ “የከለከሉትን እኛም ተከልክለን” ብለው ይዋሻሉ፡፡
ላይ ላዩን ቢዋሹ አላህ ውስጥ አዋቂ ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) እያመፁ እሳቸውን መከተል የለም፡፡
4) “የዊላዳውን ቀን እናከብረዋለን!!”
ኩራተኛ ሰው እንዲህ ድርቅ ብሎ ሃቅን አልቀበል ብሎ የጀሀነም መንገድ የሆነውን ቢድዐ ዲን አድርጎ ይይዛል፡፡ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ግን ለ23 አመት ነብይ በነበሩበት ጊዜ አንድም ቀን አላከበሩትም፡፡ ታድያ ከዚህ በላይ ጥመት ምን አለ?

ሌላኛው ደፋራቸው ደግሞ እንዲህ ሲል ፃፈ
5) “የነቢ አሽክር እንደመሆን ምን መታደል አለ?”
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እራሱ የማን ባርያ ናቸው?
መልሱም የአላህ ናቸው፡፡
ታድያ እኛን እሳቸው “የአላህ ባርያዎች ሁኑ” እያሉ እንዳላስተማሩን ዛሬ “የነቢ አሽክር እንደመሆን ምን መታደል አለ?”
አንድ ሰው ተነስቶ “የኢሳ አሽክር እንደመሆን ምን መታደል አለ?” ቢል ይጠየፉታል፡፡ ለኢሳ ሲሆን እኛ ለአላህ፣ ለብቸኛው ፈጣሪ ብቻ ነው አሽከር ልንሆን የሚገባን አይነት መልስ ይሰጣሉ፡፡
ታድያ አላህ እኮ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምንም) ይሁን ኢሳን (አለይሂ ሰላም) የፈጠረ ብቸኛው አምላክ፣ ለእሱ ብቻ ባርያ ልንሆን የሚገባን ነን ሲባሉ፡፡
“ወሃብዬች” ብለው ፍየል ወድያ ቅዝምዝም ወዲህ ይሆኑብናል፡፡

አደለም እኛ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንኳን የአላህ ባርያ ናቸው፡፡ እሳቸው ያስተማሩን እሳቸውን በማወደስ ድንበር እንዳናልፍ እና ስለ እሳቸው ስንናገር “የአላህ ባርያውና መልክተኛው ነው” ብለን እንድንመሰክርልቸው ብቻ ነው ያስተማሩን፡፡ እኛም በአላህ ፍቃድ አደበኞች በመሆን ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መልክተኛውና ባርያው ናቸው እንላለን፡፡

የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤታቸው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
Bedegami Post yetederege
https://t.me/SadatTextPosts
Channel photo updated
ኢትዬጵያዊው ሺአ

ይህ ግለሰብ ሺኣን በኢትዬጵያ ለማስፋፋት ከሚሞክሩ ግለሰቦች ውስጥ ነው፡፡ ፒያሳ አወልያ እሁድ እሁድ ኢኽዋኖች ከሚመለምሏቸው ተማሪዎች ውስጥ ነበር፡፡ ፒያሳ አካባቢ የሚገኘው ፑሽኪን አዳራሽ ላይ “ኡመር” የሚል ድራማ ቢጤ ሰርቶ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ትላንት ኡመር ባለበት አፉ የኡመርን ጠላቶች ይሀው ተቀላቅሎ ኢትዬጵያ ውስጥ ሺኣን ሊያስፋፋ ነው፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! ሺኣዎች ማለት የአላህ፣ የመልክተኛው ﷺ፣ የሰሃባዎች እና የአማኞች ጠላቶች ናቸው እንጠንቀቃቸው፡፡ ሙስሙን ማህበረሰብ ትክክለኛውን ተውሒድ በማስተማር፣ ከሺርክ እና ከሺአዎች የክህደት እምነቶች እንዲቆጠብ በሰፊው በማስተማር ሙስሊሙን ወደ ጀሀነም እንዳይነዱት ተግተን እንስራ፡፡ እኛ እጃችንን አጣጥፈን ብንቀመጥ የሰሃባዎች ጠላት የሆኑትን ሺአዎች አላህ እራሱ ይበቀላቸዋል፡፡ ግን እኛ የአቅማችንን ብንጥር አላህ በሁሉም ጠላቶቻችን ላይ ድልን ያጎናጥፈናል፡፡ ሺአዎች አቅም ስላላቸው በሀገሪቱ ላይ በገንዘብ ሀይል ተጠቅመው ኡማውን እንዳይሸውዱት ትክክለኛውን የሰሃባዎች እምነት እና ውድቅ የሆነውን የሺአዎች ክህደት ማስተማር አለብን፡፡ አላህ ሆይ! እኛ ደካማዎች ነን እርዳታህን ለግሰን፡፡ https://t.me/SadatTextPosts
የሺአ ሰባኪ ህዝቡን አላህን ትተው ሁሴንን እንዲያመልኩ እንዲህ ሲል የክህደት ንግግርን ያስተምራል
“ካንተ ውጭ እኮ ማንም የለንም፡፡ ጨሎታችንን ስማን አንተ የአብደላህ አባት ሁሴን ሆይ! ዱንያችን እና አኸይራችን ነህ፡፡ ችግር ባጋጠመህ ጊዜ ወደ ሁሴን ተመልከት፣ ለምነው፡፡ ሁሴን ወዳንተ በእርግጥ መጥቶ ጉዳይህን ይፈፅምልሀል፡፡ ሁሴን ያንተን ጥሪ ለመስማት አገናኝ አማላጅ አይፈልግም፡፡”

ተመልከቱ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! የብቸኛው ፈጣሪን አላህ መብት ሙሉ በሙሉ አንስተው ለፍጡር ሲሰጡት፡፡ ይሄ ነው ሺርክ ማለት፡፡ ሺርክ ማለት እየሰራው ለሞተ ዘላለም አለሙን ከጀሀነም እሳት አይወጣም፡፡ ጀነት በእርሱ ላይ እርም ናት፡፡
የኢትዬጵያ ሙስሊሞች ሆይ! ሺአዎች በጣም አደገኛ የጥመት ቡድኖች ናቸው፡፡ ኡማውን ስለነሱ ማስጠንቀቅ እና በእውቀት ማነፅ አለብን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ሱዳንን አላህ ይጠብቃት፡፡

ሱዳን ላይ የዳቦ ዋጋ ተወደድ ብለው ተቃውሞ ሰልፍ መንግስታቸው ላይ ወጥተዋል፡፡ የሚገርመው የሶርያ ስደተኞች ሰላም አጥተው የሚበሉት አጥተው ሱዳን ውስጥ ይለምናሉ፡፡ የሱዳን ሰልፈኞች ይህንን እንኳን እያዩ እንዴት አይማሩም፡፡

ሱዳን ላይ ስንት እና ስንት ሺርክ (በአላህ ላይ ማጋራት፣ በአድ አምልኮ)፣ ቢድኣ (በሀይማኖት ላይ ጭማሪ)፣ ወንጀል አለ፡፡ ይህን ሁሉ ዝም ብለው፣ አብዛኛዎቹ እራሳቸው በነዚህ ወንጀሎች ተዘፍቀውበት ዳቦ ዋጋው ተወደድ ብለው ሀገራቸውን ለማፍረስ ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ አላህ ልብ ይስጣቸው፡፡ ብልጥ ማለት ከሌሎች የሚማር ነው ተብሏል፡፡ እነ ቱኒስያ፣ ግብፅ፣ ሊቢያ፣ የመን፣ ሶሪያ ላይ ሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍ ብለው ሀገራቸውን ያፈረሱ ሰዎች አሁን ተፀፅተዋል፡፡ ነገር ግን ዋጋ የለውም፡፡

ችግር የሚመጣብን በራሳችን ጥፋት እንደሆነ አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል
[Q 16:112] وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا قَرْيَةً كَانَتْ ءَامِنَةً مُّطْمَئِنَّةً يَأْتِيهَا رِزْقُهَا رَغَدًا مِّن كُلِّ مَكَانٍ فَكَفَرَتْ بِأَنْعُمِ ٱللَّهِ فَأَذَٰقَهَا ٱللَّهُ لِبَاسَ ٱلْجُوعِ وَٱلْخَوْفِ بِمَا كَانُوا۟ يَصْنَعُونَ
አላህ ጸጥተኛ፣ የረካች፣ ሲሳይዋ ሰፊ ኾኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢኣት የረኃብንና የፍርሃትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ (መካን) ምሳሌ አደረገ፡፡

[Q 42:30] وَمَآ أَصَٰبَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍ
ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት (ኃጢኣት) ምክንያት ነው፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡

እስቲግፋር (አላህን ማረን) እያልን ለሰራነው ወንጀል አላህን ማህርታውን መጠየቅ ሲገባን፣ ሱዳኖቹ ይሀው አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያዘዙትን ትተው የጥፋት ተጣሪዎችን ተቀብለው ሀገራቸውን ሊያፈርሱ ነው፡፡
አላህ ሱዳንን ከመፍረስ ይጠብቃት፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
*የዱንያ ነገር!!*
~~~~~~~~~~~~~~~
ዐልይ ኢብኑል ሀይሠም እንዲህ ይላሉ:–
"አምሳያ ያላየሁለት የዘመን መገለባበጥ፣ የጊዜ መለዋወጥ አይቻለሁ።
★ የአልፈድል ኢብኑ ረቢዕ ንብረት በአንድ ሺህ ግመል ተጭኖ አይቻለሁ። ሌላ ጊዜ ግን ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተደብቄ አይቻለሁ። በውስጧ መድሃኒቶቹ ተጨምረው።

★ አልሐሰን ኢብኑ ሰህልን ደግሞ ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተመልክቻለሁ። ከዚያ ግን ንብረቱ በአንድ ሺ ግመል ላይ ተጭኖ አይቸዋለሁ።"

||

ዱንያ እንዲህ ነች። መርጋት የማታውቅ ወላዋይ!!
ሃያላን ይዋረዳሉ። ደካሞች ይነግሳሉ።
ሀብታሞች ጎዳና ላይ ይወድቃሉ። ምንዱባን በሰማይ ጠቀስ ህንፃ ይንፈላሰሳሉ።
ሳር ቅጠሉን የተፀየፈው ጨፍጫፊ አረመኔ አለም ጠባው ከአይጥ ጎሬ ሲያደፍጥ ታየዋለህ። የትላንቱ ተሳዳጅ ተራውን ሲያሳድድ ትመለከታለህ።

® ይሄው ነች ዱንያ!! ብልጭ ብላ ድርግም፣ ቦግ ብላ እልም የምትል። ሁሌ ሳቅ የለም! ሁሌ ድል የለም።
|
በድር ላይ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገሩ፣ ጥጋብ ያስከራቸው ቁረይሾች፣ 70 መኳንንቶቻቸው ትላንት ሲያሳድዷቸው በነበሩ ሶሐቦች ሰይፍ ተበልተው፣ ሌላ 70 ደግሞ በምርኮ አስረክበው የሐዘን ማቅ ለብሰዋል። መካ በዋይታ ተንጣለች።
|
ኡሑድ ሌላ ቀን ነው። ሌላ ተራ!! አጋሪዎች የፈነደቁበት፣ እነ ሐምዛን፣ እነ ሙስዐብን ጨምሮ ከ70 በላይ ታላላቅ ጀግኖች ወድቀው ሌላ 70 የቆሰሉበት፣ አሳዝኝ ክስተት እውን የሆነበት ቀን። ሶሐቦች አካላቸው በስለት፣ ልባቸው በሐዘን ቢቆስል ጊዜ አላህ እንዲህ ሲል አሳሰባቸው: –

(إِنْ يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ الْقَوْمَ قَرْحٌ مِثْلُهُ ۚ وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسَ)

"ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ እናም እነዚህን ቀናት በሰዎች መካከል (በመልካምና በሌላ) እናቀያይራቸዋለን፡፡" [ኣሉ ዒምራን: 140]

|||

ዱንያ አመሏ ነው። ዛሬም እንዲሁ ናት።
ግን ማነው የሚማረው? ግን ማነው የሚመረምረው? ግን ማነው የዱንያን ከንቱነት ተገንዝቦ ለዘላለም ቤቱ ከልብ የሚጨነቀው?
እስከ መቼ ነው የምናንቀላፋው?
እስከ መቼ ነው የምንዘናጋው?
እስከ መቼ ነው በከንቱ የምንባዝነው?
ኢንና ሊላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን!!
ኢላሂ ልብ ስጠን!!
ሀገራችን አሁንም ዱኣ ያስፈልጋታል፡፡ አብዛኛዎቹ ሰዎች በፖለቲካ፣ በዘረኝነት እና በሌላም ነገር ተወጥረው አላህን የረሱ አሉ፡፡ ይሀው ሀገራችን ግን በተለያዩ አቅጣጫዎች ደም ይፈስባታል፡፡ አላህን ማረን፣ እዘንልን፣ ይቅር በለን፣ ሀገራችንን ሰላም አድርግልን ብለን መለመን ከመቼውም ጊዜ በላይ ያስፈልገናል፡፡
ወንዶች ሆይ! አደራ ጀመአ ሰላትን በአላህ ቤቶች ላይ እንስገድ፡፡ ሰሞኑን እንዲያውም ፈጅር እየተሰገደ ያለው ለ 12 አስር ጉዳይ አካባቢ ነው፡፡ አላህ ያዘዘንን ትተን እንዴት ነው በምድር ላይ መመቻቸትን የምንከጅለው?
አላህን እንፍራ፡፡ አላህ ከሺርክ፣ ከቢድኣ፣ ከዘረኝነት የጠራ አንድነት ይስጠን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
የነብዩ ባልደረቦች በብዙ ችግርና ፈተና ውስጥ አለፉ ።
ለናሙና ያህል ፣
ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር ያደገው የተቀማጠለ ኑሮን ከተላመደች ሃብታም እናቱ ዘንድ ነበር ።
የነብዩን ጥሪ በተቀበለ ማግስት እናቱ ጦር ሰበቀችበት ። ወደኔው እምነት ካልተመለስክ አይንህን ላፈር አለቸው! ! የተውሒዱ ጥሪ ልቡ ውስጥ ጠልቋልና አልሰማትም !! ለዛቻዋ ቁብ አልነበረውም ። ከእናቱ ጋር ተቆራረጠ!!
እናም መከራና ችግር ተፈራረቀበት!! በምቾት ያደገ ገላው ተጎሳቆለ! ቆዳው ተሸልቅቆ እስኪረግፍ ድረስ በብርቱ ተንገላታ! ሙስዐብ ዱንያን በአኺራው ለውጧልና የሆዱ ነገር አላሳሰበውም ነበር ! ! አቀማጥላ ከሳደገቸው እናቱ ይልቅ ወደ ኢስላምና ወደ ተውሒድ የጠሩትን ታላቅ ነብይ አስበለጠ! !

መጨረሻም ከሃዲያንን ሲታገል በህይወት እያለ ችላ በማለት የተሰናበታትን ዱንያ በሞት ተሰናበተ ። ቀብር ከመግባቱ በፊት ገላው ሊከፈን ይገባው ነበር ። ነገር ግን ከራሱ እስከ እግሩ ድረስ የሚሸፍን ጨርቅ አልተወም ነበርና ገላውን በከፈን ማዳረስ አልተቻለም ። በነብዩ ትእዛዝ እግሩ ላይ ሳር ብጤ ተደርጎና ሌላው አካሉ በጨርቅ ተከፍኖ ተቀበረ — ያ ጀግና! !
ኢማን ይሏችሇል ይሄ ነው
ምን ሆነናል እኛ ?! ኧረ እናስተውል ጎበዝ! !! ለዱንያ ስንል ሐራምን መዳፈር ፣ ለሆድ አቋምን መለዋወጥና መደበቅ! ....... ግዚያዊና እንስሳዊ ለሆነ ደስታ ወደ ሓራም መመልከት .... ኧረ ስንቱ ከንቱ ነገር ውስጥ ተነክረናል ጎበዝ !! ወደ አላህ እንመለስ! ! አላህ ይመልሰን! !!
ስለ ሰሞኑን ከባድ ብርድ እስልምና ምን ይላል፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ
ኢስላም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሀይለኛ ሙቀት እና በሀይለኛ ብርድ ሰው ተቸግሯል፡፡ ይህም ከመሆኑ ጋር ለአላህ ካጠፋነው ጥፋቶች ንሰሀ ከመግባት ይልቅ በየዜና አውታሩ “የአለም በረዶ ስለቀለጠ ነው፣ ዛፎች በመቆረጣቸው ነው፣ ኦዞን በመሳሳቱ ነው…..” እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች ናቸው እየተባለ ይለፈፋል፡፡
እስቲ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምን እንደሚሉ እንይ
አቡ ሁረይራ (ረድየላሁ አንሁ) ባስተላለፉት፣ ኡማሙ አል-ቡኻሪ በዘገቡት ትክክለኛ ሀዲስ ላይ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
“ጀሀነም (እሳት) ወደ ጌታዋ ስሞታ አቀረበች፡፡ ከፊሌ ከፊሌን በላው አለች፡፡ አላህ ሁለት ጊዜ እስትንፋስን ፈቀደላት፡፡ አንደኛው በቀዝቃዜ ወራት ሌላኛው ጊዜ በሙቀት ወራት፡፡ በሙቀት ጊዜ የምታገኙት ከባድ ሙቀት እና በቅዝቃዜ ጊዜ የምታገኙት ከባድ ውርጭ (ቅዝቃዜ፣ ቀቅ) (ናቸው)፡፡”
حَدَّثَنَا أَبُو الْيَمَانِ، أَخْبَرَنَا شُعَيْبٌ، عَنِ الزُّهْرِيِّ، قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو سَلَمَةَ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ، أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا، فَقَالَتْ رَبِّ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا، فَأَذِنَ لَهَا بِنَفَسَيْنِ نَفَسٍ فِي الشِّتَاءِ وَنَفَسٍ فِي الصَّيْفِ، فَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ فِي الْحَرِّ، وَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الزَّمْهَرِيرِ ‏"‌‏.‏
ልብ እንበል ከባዱም ሙቀት እና ከባዱም ብርድ የአዋቂዎች ሁሉ አዋቂ፣ የአላህን ፈሪዎች ሁሉ ፈሪ፣ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ እንደነገሩን የጀሃነም እሳት የምትተነፍሰው ሁለት ትንፋሽ ምክንያት ነው፡፡
ሌላው መገንዘብ ያለብን ነገር እስልምና ሙሉ መሆኑን ለማንኛውም አለም ላይ ላለ ክስተት በል እንዲያውም ለሚቀጥለው አለም ጉዳዩች፣ የሚቀጥለው አለም ላይ ምን እንደሚከሰት በዝርዝር እና በጥቅል የተናገር ዉድ፣ ልዩ፣ የማይበረዝ፣ የማይሰረዝ፣ የማይደለዝ፣ ዘመን የማያልፍበት ሀይማኖት ነውና አጥብቀን እንያዘው፡፡ ይሀው ተመልከቱ አለም “Economic Crises” ኢኮኖሚክ ክራይስስ ብለው ሲያወሩ አላህ ጥንትም የወለድ መጨረሻው ይህ መሆኑን ነግሮን ነበር፡፡
ትዳር እንዲመሰረት እና ከዝሙት እንድንታቀብ ከጥንትም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት መክሮ ነበር፡፡ ግን ይህን አልሰማ ብለው አሁን አለም ላለችበት ከባባድ በሽታዎች ተዳርገዋል፡፡
በሁሉም የህይወት ዘርፍ ላይ የጥንት የጠዋቱ ኢስላም (ሰለፍያ) በሄደበት መንገድ መሄድ ብቻና ብቻ ነው ዋስትናው፡፡ ሁለት ሃቅ የለም፡፡ ሁሉም ሙስሊም ከጥመት ቡድኖች እርቆ ወደ ብቸኛዋ አማራጭ እና ሁለተኛ ወደሌላት ሃቅ ጎዳና፣ ሰለፉነ ሷሊሂን የተጓዙባት ጎዳና መመለስ ግድ ይለዋል፡፡ አለበለዚያ በሙስሊሙ አለም ላይ እንዳየነው አሁንም ከባድ ኪሳራ ይከሰታል፡፡
ታድያ ምን ይበጀን?
አማኞች ወደ ጌታቸው በንሰሃ ሊመለሱ፣ ያችን “ጭማሪ አለን?” ብላ የምትጠይቀውን ጀሀነም ከሷ ጌታችን እንዲጠብቀን እሱን ዘውትር መለመን ግድ ይለናል፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ፡፡ አላህ እነዚህን ሁሉ ተዓምራት የሚያሳየን በሰጠን አእምሮ የሱን ጌትነት፣ በቸኛ ተመላኪነት አውቀን ወደሱ እንድንመለስ ነው፡፡
አላህ ሆይ! ሁሌ ወዳንተ በጸጸት ከሚመለሱት አድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
Siyaasa addaa addaaf jecha dhiiga muslimaa tokko rakasa gochuun gamnummaa miti

Namni dhuguma muslimootaaf cinqamu ibidda jahannamaa irraa waan isaan ittiin baqatan barsiisu qaba malee ituu isaan shirkiifi wanjaloota guguddaa keessaa hin ba'in waan biraa dhaa isaaniin biizii gochuun isaaniin ganuu dha

Ummatni keenya akkuma beeknu diinii irraa fagaachaa jira sababa addaa addatiin kun kan baduu ykn hirrachuu danda'u sirritti qur'aanaafi hadiisa xuquu dhaan nama geeddaruu yaaluu dhaani dha malee waan isaan jaallatan qofa itti himaa kolfisiisaa gowwomsuu dhaan miti , haqqii itti himtee isa qacheelchuu keetu faayidaa qaba .

Kun hin ta'u taanaan nuti karaa ergamaa rabbii عليه السلام irra jiraachuu keenya deebinee sirritti haa mirkaneefannu !

Fuad Mohammed
https://t.me/dawwaa
هل تريد أن تعرف الإخواني من أول نظرة ؟ فهاك إذن صفاته اللازمة !
Mallattoolee ikhwaaniyyootaa irraatii...
1 -Gara tawhiida rabbiitti waamuu dhiisuu ykn haala xiqqoo ta'een waamuu fii mata dureelee biroo irraatti xiyyeefannaa cimaa dhaan hojjechu kan akka siyaasaafii k.k.f .
2 - Mata jajjaboon ikhwaaniyyoota waan ittiin adda ba.an qabu isaan keessaatti Areeda haaduu ykn gabaabsuufii suurree isaanii gabaabsuu dhiisuun mallattoo isaanii isa cimaa keessaatii isa tokko.
3 -dhiiraaf dhalaa walitti makanii barsiisuu
4 - salafiyyootatti hamma danda'aniin warana jaba banuu kan akka maqaa balleessuutiin .
5 - Gariin isaanii gariin Sobaan wal faarsuu .
6 - tokkoon isaanii yoo bida'aafii shirkiyyata addaa addaa keessa lixee wal gorsuu dhiisuufii walii dhoksuu nama waan kana dhowwuuf yaaluu immoo jibbuufii jibbisiisuu
7 - Firqaa kami wajjiin iyyuu yoo ta'e wal gargaaruu , selefiyyoota waliin irraan kan hafe
8 -Akka gaararraa hundaaf bifa isaaf maluun itti dhiyaachuu yaaluu.
9 -dhiiga muslimootaa dhaan daldaluu .
10 - hiriira nagaa jechuun maqaa waan itti baasaniin biyyoota arabaa daakuu gochuu.

Fuad Mohammed
https://t.me/dawwaa
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
ታላቅ ለውጥ ከአማራ ክልል፡፡
ሌሎች የኢትዬጵያ ክልሎችም ላይ ይህን መርዝ ጫት ከሀገራችን መሬት በማስወገድ ትውልዱን ከክስረት እንጠብቅ፡፡
………..

የባሕር ዳር አርሶ አደሮች ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ
***********************************
በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጎርደማ አካባቢ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ለዓመታት ሲያለሙት የነበረውን ጫት ከማሳቸው ማስወገድ ጀመሩ፡፡
አርሶ አደሮቹ ጫት እያስከተለ ያለውን ማኅበራዊ ጉዳት በመረዳት ነው ከማሳቸው በማስወገድ በሌላ ጠቃሚ ሰብልና የጓሮ አትክልት ለመተካት እንቅስቃሴ የጀመሩት፡፡
ዛሬ በአንድ ሄክታር ማሳ ላይ ያለሙትን ጫት ማስወገድ የጀመሩት አቶ ምስጦፋ ታደሰ የተባሉ የጎርደማ አካባቢ ነዋሪ ናቸው፤ ሌሎችም የእርሳቸውን አርዓያነት እንደሚከተሉ ይጠበቃል፡፡
ጫት በባሕር ዳር አካባቢ ማኅበራዊ ችግር እየሆነ መምጣቱን በመጥቀስ በርካቶች መፍትሔ እንዲሰጠው ሲጠይቁ መኖራቸውን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ፤ የአማራ ብዙሃን መገናኛ
https://t.me/SadatTextPosts