አልሐምዱሊላህ
ወንድም እና እህቶቼ ሆይ! ትንሽ በህክምና ጉዳይ ጠፋ ብዮ ነበር። አዛኙ አላህ ህክምናውን ሰበብ አድርጎልኝ ለውጥ አግኝቼያለሁ።
ስትጠይቁኝ፣ በዱአችሁ ስታስቡኝ የነበራችሁ ወንድም እና እህቶቼ ሆይ አላህ መልካሙን ሁሉ ይመንዳችሁ።
አላህ ሁለት ሀገር ከመከራ ይጠብቀን።
ወንድማችሁ ሳዳት ከማል አቡ መርየም።

ዘሬን ከሀይማኖቴ አላስበልጥም፣ እኩልም አላደርግም፡፡
ሙስሊሞች ሁሉ ከኔ ዘር ቢሆንም ባይሆንም ወንድሜ እና እህቴ ናቸው፡፡
ኢስላም አላህ የሚቀበለው ብቸኛው የነብያት ሁሉ ሃይማኖት ነው፡፡
ኢስላም
- ከአሳማሚው የጀሀነም እሳት ይጠብቃል፣
- ሲራጥን ያሻግራል፣
- ብቸኛው የአለም ሙስሊሞች መተሳሰሪያ ገመድ ነው፣
- ያቺን ውድ ሀገር ጀነት ያስወርሳል………፡፡
ዘር
- አንድ ሰው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘር እንኳን ቢሆን እምነቱን ካላስተካከለ ከእሳት አይጠበቅም (ምሳሌ አጎታቸው አረቡ አቡ ለሃብ)፣
- ጀነትም አያስገባም፣
- ሲራጥንም አያሻግር፣
- የሙስሊሞችን አንድነት በዘረኝነት አማካኝነት ሲበታትን በተጨባጭ ታይቷል……
ዘር ከሀይማኖት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም፡፡ የሰውን ልጅ ሰው ያደረገው ዘሩ ሳይሆን ከጌታው ጋር ያለው ግንኙነት (እምነቱ፣ እስልምናው) ነው፡፡
አላህ እሱን መፍራት እንጂ ዘርን የሰው ልጆች መበላለጫ አላደረገውም
[49:13] يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
- እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡
- እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡
- አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡
- አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡
አንድ ሰው ሰው ነኝ እስካለ ድረስ አባቱ አደም ነው፡፡ አደም ደግሞ ከአፈር ነው የተፈጠረው፡፡ ከአንድ አባት የተገኙ ልጆች ደግሞ አንዱ በአንድ ላይ የበላይ ነኝ ሊል አይገባውም፡፡ ማን ከማን በላይ ነው የሚለው መስፈርቱ ተቀምጧም
አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡
ሰው ከሃይማኖቱ በላይ ዘሩን ካስቀደመ ከባድ ክስረት ውስጥ ወድቋል፡፡
ሙስሊሞች ሁሉ ከኔ ዘር ቢሆንም ባይሆንም ወንድሜ እና እህቴ ናቸው፡፡ ከኢስላም እና ከሱና ውጭ ሰዎችን የምወድበት እና የምጠላበት መስፈርት የለኝም፡፡
የእኔ ዘር ከማንም ዘር አይበልጥም፣ ከማንም ዘርም አያንስም፡፡
አላህን እንፍራ ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም፣ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአላህ መልክተኛ ናቸው ብሎ የመሰከሩ ሰዎችን የእኛ ዘር ስላልሆኑ ብቻ ደማቸውን ከማፍሰስ፣ ገንዘባቸውን ከመዝረፍ፣ ክብራቸውን ከማጉደፍ እንጠንቀቅ እንቆጠብ፡፡ አለበዘለዚያ ዛሬ እዚህ ምድር ላይ ለሰራናት ትንሽም ትልቅም ስራ የአለማቱ ጌታ አሸናፊ አላህ ዘንድ ቀርበን ከባድ ምርመራ፣ ከዛም ቅጣት ይጠብቀናል፡፡
ሙስሊሞች ሆይ! አላህን እንፍራ የእኛ ብቸኛው መተሳሰሪያ ገመዳችን ኢስላም እና ሱና ነው፡፡ ኢስላም እና ሱናን የያዘ ወንድም እና እህታችን ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ዘረኝነትን በመካከላችን እናጥፋ ማለት አንድ ሰው ዘሩን እና ቋንቋውን ይካድ ማለት አይደለም፡፡ አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፡፡ አላህ የሰላም ባለቤት ነው፡፡ ሰላምን የፈለገ የሰላሙን ባለቤት በብቸኝነት ይለምን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts

እንግሊዝ ሀገር የሚገኘው አልጄሪያዊው ወንድማችን ሸምሲ ለአንድ ሰው ዳእዋ ሲያደርግለት እንዲህ ሲል አስተማረው
If you want to worship your creator, you should worship him the way he loves, not the way you love. Because he knows what is the correct way.
“ፈጣሪህን ማምለክ ከፈለግክ፣ አንተ በወደድከው መንገድ ሳይሆን እሱ (አላህ) በሚወደው (በሚፈልገው) መንገድ ልታመልከው ይገባል፡፡ ምክንያቱም እሱ (አላህ) ትክክለኛ መንገድ የቱ እንደሆነ ያውቃልና፡፡”
የሱና ሰዎች የትም አለም ይኑሩ መርሆዋቸው አንድ ነው፡፡ የቀዱት ከአንድ ምንጭ ነውና፡፡

አላህ ሀገራችንን ስንት ጊዜ ከከባባድ ፈተናዎች ጠብቋታል።
በእኛ ሀይልና ጥበብ ሳይሆን በእሱ እዝነት ከስንት መከራ አውጥቶናል።
አሁንም ዱአ እናብዛ። አላህ የሰላም ባለቤት ነው። ሰላም የሚጠየቀው ከእሱ ነው። አላህ ሀገራችንን፣ አለምን በጠቅላላ ሰላም ያድርግልን።
ሀይልም ጥበብም የአላህ ብቻ ነው።
አሸናፊው፣ ጥበበኛው አላህ የእሱን ፀጋ እና እዝነት ተረድተው ለእሱ ከሚተናነሱት፣ እሱን ከሚያውቁት፣ እሱንም ከሚያመሰግኑት ባሪያዎቹ ያድርገን።
አላህ እንዲህ ይላል
"ብታመሰግኑ እጨምርላችኀለሁ፣ ብትክዱም ቅጣቴ የበረታ ነው።"
አላህ ለዋለልን ውለታዎች በጠቅላላ አመስጋኝ ያድርገን።

ሺርክ እና ሽንት?
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ
ሙስሊሙ ማህበረሰብ በየመስጂዱ፣ በየመድረሳው ሽንት በሚሸናበት ወቅት እንዳይፈናረትበት የሃይማኖት አስተማሪዎች አጥበቀው ስለነገሩት ለምን መሃል ከተማ አይሆንም ሽንቱን ሲሸና ሱሪውን አጥፎ እግሩን በልቀጥ አድርጎ፣ ከዛም እንጥብጣቢ እንዳይኖር እጁን ሱሪው ውስጥ ከሶፍት ጋር ከቶ ሲያዳርቅ ይታያል፡፡ ተቸግሮ ካልሆነ በስተቀር ቆሞ የማይሸናም ስንት አለ፡፡
ለምን ቢባል አንድ ሰው ሽንቱን ሲሸና ልብሱ ላይ ካንጠባጠበ የቀብር ቅጣት እንዳለው የሀይማኖት አስተማሪ የሚባሉት ደጋግመው ስለ ነገሩት፡፡
በሌላ ጎኑ በምድራዊ ህይወት፣ በቀብር ውስጥም ይሁን በሚቀጥለው አለም ጀሀነም እሳት ውስጥ የሚያስገባውን ሺርክ፣ ብሎም ጀነት የማያስገባውን ሺርክ (በአላህ ላይ ማጋራት) በየመስጂዱ፣ በየመድረሳው አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ አብዛኛው የሃይማኖት አስተማሪ ተብዬ ችግሩ እንደሌለ አድርገው አድበስብሰውት ስለሚያልፉ፣ አልፎም የሃይማኖቱ ዋና አካል ተደርጎ እንዲታይ በማድረጋቸው፣ የሺርክ አቀንቃኞቹን የኢስላም ባለውለታዎች አድርገው ቻናሎች ላይ ሁሉ ስለሚያቀርቧቸው ይህንን አደገኛ ሺርክ አብዛኛው ሰው እግሩን አጣምሮና አጣጥፎ፣ እጣን እያጨሰ፣ ወደ ግራ ወደ ቀኝ እየተወዛወዘ፣ እያለቀሰ፣ እያጨበጨበ እንዲሰማው ሆኗል፡፡
የሃይማኖት አስተማሪዎች ሆይ! አላህን አትፈሩም ታላቁን ወንጀል ለምን ከሱ በጣም ባነሱ ወንጀሎች ትሸፋፍኗቸዋላችሁ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
وَإِذْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ لَتُبَيِّنُنَّهُۥ لِلنَّاسِ وَلَا تَكْتُمُونَهُۥ فَنَبَذُوهُ وَرَآءَ ظُهُورِهِمْ وَٱشْتَرَوْا۟ بِهِۦ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ فَبِئْسَ مَا يَشْتَرُونَ
አላህ የነዚያን መጽሐፉን የተሰጡትን (አህለል ኪታቦችን) ቃል ኪዳን ለሰዎች በእርግጥ ታብራሩታላችሁ አትደብቁትምም በማለት የያዘባቸውን (አስታውሱ)፡፡
በጀርባዎቻቸውም ኋላ ጣሉት፡፡
በርሱም ጥቂትን ዋጋ ገዙ፡፡
የሚገዙትም ነገር ከፋ!
ልብ በሉ አላህ መፀሃፍቱን ከተሰጡት ውስጥ የእውቀት ባለቤቶች (የሃይማኖት አባቶች) ለህዝባቸው ሀቁን እንዲያብራሩ እና እንዳይደብቁ ታዘው ነበር፡፡ እነሱ ግን ታላቁን ሀቅ አላብራሩም፣ ደበቁት፡፡ በጀርባቸው ወደ ኋላም ጣሉት፡፡ ዱንያዊ ጥቅማጥቅምን ፈለጉበት፡፡ አላህ የሚገዙት ነገር ከፋ ሲል ወቀሳቸው፡፡
ከዚህም ኡማ አላህ እውቀት ሰጥቶት ሲያበቃ ይህን ታላቅ አምልኮ የሆነውን ተውሒድ፣ የበደሎች ሁሉ በደል ታላቅ ወንጀል የሆነውን ሺርክ (በአላህ ላይ ማጋራት) የማያብራራ፣ የሚደብቅ እና የሚያድበሰብስ ይሀው ዛቻ ያገኘዋል፡፡
ሀገራችን ላይ ሺርክ የሚሰሩ ወደ በአድ አምልኮ የሚጣሩ ታላላቅ አጥማሚ ሰዎችን ኡማው እንዲጠነቀቃቸው ከማድረግ ይልቅ እነዚህን ሰዎች የኢድ እንግዳ እየተደረጉ ቻናሎች ላይ ሁሉ ይቀርባሉ፡፡ ብሎም “አንድ ነን እኛ ማንም አይለየን” እያሉ ክህደት እና ትክክለኛውን እምነት አንድ ሊያደርጉ የሚታገሉ የጥመት አራማጆች አሉ፡፡ አላህ ግን ሁሌም እንዳዋረዳቸው ነው፡፡
ህዝባችን ቀን ከፋፍሎ ከአላህ ውጭ ፍጡራንን፣ ጠንቋይን፣ ጂኖችን፣ ዛፍን፣ …… ሌላንም ያመልካል፡፡ ይሄ ደግሞ የወንጀሎች ሁሉ ታላቁ ወንጀል ነው፡፡ ታድያ ለምን ይሆን ይህ ታላቅ የአላህ መብት ሲናድ አላህ ካዘነላቸው ጥቂት እውነተኛ የሃይማኖት አስተማሪዎች ውጭ አብዛኛው በሃይማኖት አስተማሪነት የሚታወቀው ዝም የሚለው?
እውነት ለህዝቡ አስበው ነው? በፍፆም፡፡
ምክንያቱም ለህዝበ ሙስሊሙ ያሰበ ሙስሊሙን ሁለት ሀገር ከሚያከስረው ሺርክ ነብያት እንዳደረጉት ዘውትር ከምንም አርእስት በፊት ያስጠነቅቃል፡፡ ኡማውንም በአንድ አምላክ አላህ አምልኮ (ተውሒድ) ላይ ዘውትር ይኮተኩታል፡፡
እኛ ከነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በላይ አዛኝ አይደለንም፡፡ እሳቸው ከተውሒድ ጀመሩ፣ ከሺርክ አስጠነቀቁ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሺርክን ችላ ብለው ስለ ሽንት ነጃሳነት አላስተማሩም፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስለ ሺርክ አደገኝነት ካስተማሩት በላይ ቦታ ሰጥተው ስለ ሽንት ነጃሳነት አላስተማሩም፡፡ ለሁሉም የተሰጠውን ክብደት በተሰጠው ክብደት ያህል እናስቀምጠው፡፡ እኛ ተከታዬች እንጂ አዲስ ነገር አምጪዎች አይደለንም፡፡
ከሽንት በላይ የሆነውን ሺርክ ለህዝባችን በደንብ አብራርተን እናስተምረው፡፡ እኛም ህዝባችንም ከሁለት ሀገር ክስረት እንጠበቅ ዘንድ፡፡
አንድ ሰው የፈለገ ከሽንት ነጃሳ እራሱን ቢያፀዳ በአላህ ላይ እያጋራ ቢሞት ዘላለም አለሙን የእሳት ነው፡፡ ጀነትም በእሱ ላይ እርም ናት፡፡ ታድያ ይህንን ከባድ አደጋ ያየ የሺርክን አስከፊነት ዝም ይላልን? ያውም የሃይማኖት አስተማሪ ተብሎ፡፡ አረ አላህን እንፈረው፣ እንፍራውም፡፡
ዱንያዊ ጥቅምን ፍለጋ የአላህን ሃቆች ህዝብ እንዳይረዳቸው መደበቅ የትም አያደርስም፡፡ ሲሳያችን ከሰማይ ነው፡፡ የአላህን መብት አጥብቀን እንወቅ፣ እናሳውቅ፡፡ ለሁሉም ነገር የተቀመጠለትን ደረጃ ለህዝቦች እናሳውቅ፡፡
አላህ እኛንም ዝርያዎቻችንንም ከሺርክ ይጠብቀን፡፡ በተውሒድ ላይ ይግደለን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

ላሰው / ላሺው
የፈለገ ደረጃ ቢኖርህ/ሽ፤ የፈለግከውን ብትለብስ/ሽ
አትፈር / አትፈሪ
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ አንድ የኢስላምን ውበት ያላወቀ ሰው የተናገረውን ይዤ ነው፡፡ እርሱም እንዲህ ሲል ተናገረ
‹‹የእኛ ሰው ነው ያልሰለጠነው፡፡ ሸራተን ገብቶ ጣቱን ይልሳል››፡፡ ይህ በጣም ከባድ ንግግር ነው፡፡ ይህ ሰው የኢስላምን እውቀት አለማወቁ እንጂ ዛሬ ሳይንቲስቶች በእጅ መብላት፤ ጣትን መላስ ያለውን ጥቅም ደርሰውበት ኢስላምን እየተከተሉ ነው፡፡
የአላህ ባሪያ ሆይ! ዶክተር ብትሆን፤ ባለስልጣን ብትሆን፤ ሃብታም ብትሆን፤ በማህበረሰቡ የተከበርክ ሰው ብትሆን፤ የእውነተኛ የአንድ ሰው ትልቅነት የሚለካው የነብዩ ((ﷺ)) ሱና የትም ቦታ ላይ ሳያፍርበት ሲተገብረው ነው፡፡
መርሳት የሌለብን ነብዩ ሙሃመድ ((ﷺ)) ማለት የአላህ መልክተኛ ናቸው፡፡ የአላህ መልክተኛ ብቻ መሆናቸው ይበቃናል፡፡ አላህ ማለት ያ የፈጠረን፤ አምልኮ ለእርሱ ብቻ የሚገባው፤ ስም እና ባህሪያት ያሉት፤ የሚጠቅመንን እና የሚጎዳንን የደነገገ እና የከለከለ፤ በመልክተኛው አማካኝነት አብራርቶ ያሳየ ነው፡፡
አንዳንዶች ደግሞ ምግብ እየበሉ በግራ እጃቸው መጠጥን ይጠጣሉ፡፡ በቀኝህ ጠጣ ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ ሲል ወይንም ስትል መልስ ትሰጣለች ‹‹ብርጭቆው ከሚቆሽሽ ብዬ ነው››፡፡ ሸይኽ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ሲሉ መለሱ ‹‹የአላህ ዲን ከሚቆሽሽ ብርጭቆው ይቆሽሽ››፡፡ የሚገርመው ግን አብዛኛው ሰው ‹‹ሰው በጠጣበት አልጠጣም››፤ ‹‹ንፁህ ብርጭቆ ስጡኝ›› ይላል፡፡ ታድያ ለምን ይሆን የነብያችንን ((ﷺ))ሱና ትቶ፤ ነብያችን ((ﷺ))እንዳሉት ‹‹ሸጥጧን በግራው ይበላል ይጠጣል›› ለምን ሸይጧንን ይመሳሰለል?????
ኢስላም ባስቀመጣቸው ህግጋቶች፤ መንገዶች፤ እና ተግባሮች እያፈሩ ዘመናዊነት እና ስልጣኔ አለን???
ካሃዲያን ሃይማኖታችንን ተቹብን እያሉ ሁሌ ከመጮህ መጀመሪያ እራሳችን ሃያማኖታችን ላይ ባሉ ህግጋቶች ወደን ተቀብለናልን???
መጀመሪያ እራሳችንን ይህን ጥያቄ እንጠይቅ፡፡
በአላህ ጌትነት፤ በኢስላም ሃይማኖትነት፤ በሙሃመድ ነብይ እና መልክተኝነት ወደድኩ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኛው፤ በቤተሰቦቻችው፤ በባልደረቦቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

“መውሊድ”፣ “ክሪስማርስ”፣ አሹራ….?
*******************************************
ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው በላይ አውቀው ነው ወይ?
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ነብይ ተደርገው በተላኩ ጊዜ ነሷራዎችም (ክርስትያኖች) ይሁዳዎችም ነበሩ፡፡ ነሷራዎች የኢሳንም ልደት ሲያከብሩ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የወንድማቸውን ኢሳ ልደት አንድም ቀን አክብረው አያውቁም፡፡ ምክንያቱም በአላህ አልታዘዙምና፡፡ የነብይም ይሁን የሌላ ግለሰብ የልደት በዓል ማክበር የነብያቶች እምነት እስልምና በፍፁም የሚያውቀው አይደለም፡፡ ልደት ማክበር የእስልምና አካልም አይደለም፡፡በሌላ በኩል ሌላኛው ወንድማቸው ነብየላህ ሙሳን (አለይሂ ሰላም) አስመልክቶ የሁዳዎች አሹራን ሲፆሙ አዩ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሁዳዎችን ለምን እንደሚፆሙ ጠየቁ “አላህ ሙሳን እና የእስራኢል ልጆችን ከፊርዐውን ነፃ ያወጣበት ቀን ነው” ሲሉ መለሱላቸው፡፡ ነብዩም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “እኛ በሙሳ ጉዳይ ከናንተ የበለጠ የተገባን ነን” ብለው አሹራን ፆሙ እንዲፆምም አዘዙ፡፡ እንዲያውም ረመዳን ከመደንገጉ በፊት አሹራ በሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነበር፡፡ ከረመዳን በኋላ ይሀው እኛም የሳቸውን ፈለግ በመከተል እንፆመዋለን፡፡ ልክ እንደዚሁ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ሰኞ ለምን እንደሚፆሙ” ሲጠየቁ “የተወለድኩበት ቀን ስለሆነ እና ቁርዐን እኔ ላይ የወረደበት ቀን ስለሆነ ነው” ብለዋል፡፡ ታድያ ግዴታ ያልሆነ የሱና ፆም አሹራን በአመት አንዴ እንድንፆመው፣ እሳቸው የተወለዱበትን ቀን እና ቁርዓን የወረደበትን ቀን ሰኞ እንዲሁ በሳምንትን አንዴ ሱና ፆም እንድንፆም ነግረውናል፡፡ የሚያሳዝነው አብዛኛው “መውሊድን” አከብራለሁ የሚል ሰው የታዘዘውን በየሳምንቱ የሚፆመውን ሱና ሲፆም አይታይም፡፡ ይልቁንስ ለምሳሌ “የኢስነይን ሰዎች ነን” እያሉ ሰኞ ሰኞ ጉንጫቸውን በአንደንዛዡ ቅጠል ጫት ወጥረው ሲቅሙ እና ሲጨፍሩ የሚውሉ ሸይጧን የተጫወተባቸው አሉ፡፡ በአመት አንዴ ግን ያልታዘዙትን “መውሊድ” ብለው በማክበር “የኢሳ ልደት” ብለው ከሚያከብሩት ሰዎች ጋር ተመሳስለዋል፡፡ የታዘዙትን ትተው ያልታዘዙትን በመስራት ወደ አላህ እዝነት ሳይሆን ቁጣውን ወደሚያከናንባቸው የሰይጣን መንገድ የሚንደረደሩ ሰዎች ምን አለ ቆም ብለው ቢያስቡ?
አላህ እኮ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) በመከተል እንጂ ውዴታውን እና ምህረቱን ቃል የገባልን ያላዘዙትን በመስራት አይደለም፡፡ ሸይጧን ደግሞ እንዲህ አሳቢ መስሎ ነው ከጥንት እስከዛሬ ሰዎችን ሲያጠም የነበረው፡፡ አላህ ከተንኮሉ ይጠብቀን፡፡
ሌላው ሰሃባዎች አላህ አማኝ፣ እውነተኞች፣ ወድጃቸዋለሁ እያለ ያወደሳቸው….. ከነሱ መንገድ ውጭ ያለን የሚከተል መንገድ የሳተ፣ ጀሀነምም እንደሚገባ አላህ እና መልክተኛው ነግረውን ሲያበቁ፡፡ ለምን ይሆን መውሊድንም ይሁን ሌሎች ተግባራትን በተመለከተ ሰሃባዎች የቆሙበት ቦታ የማንቆመው?
ሰሃባዎች ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በህይወት በነበሩ ግዜም ይሁን ሞተው አንድም ቀን የማንንም ነብይ ይሁን የረሱልን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደት አክብረው አያውቁም፡፡
ታድያ እኛ ማን ሆነን ነው ሰሃባዎች ያልሰሩትን የምንሰራው? የአላህን ዲን፣ ንፁሁን የነብዩ ሱና በቢድዐ ለማቆሸሽ፣ የሰይጣንን ተልኮ “ነብዩን መውደድ” በሚል ስም ለማሳካት ደፋ ቀና የሚባለው?
እውነት ሰሃባዎች ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሳይወዱ ቀርተው ነው የነብዩን መውሊድ ያላከበሩት?
ወይንስ እነሱ ለነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላቸው ውዴታ ሸሪዐ በደነገገው መልኩ በገንዘብ፣ በህይወት መስዋትነት እና በሌላም ስለገለፁ ነው?
እውነታው እነሱ ስለስርዐት አላቸው፡፡ ይህንን ከሰማይ የወረደ ዲን “እኔ እንደሚመስለኝ” እያሉ ሳይዳፈሩ ያንን ንፁህ ምንም ጭማሪ የማይፈልግ ዲን ለእኛ በሰላም አድርሰዋል፡፡ አላህም ወዷቸዋል፡፡ ዛሬ አላህ ዘንድ ገና ፍርድ ያልተሰጠባቸው ሰዎች ይህን ዲን መጥተው በፈለጉ ጊዜ በቀያየሩት ቁጥር እኛ አብረን የምንቀያየረው አላህን ነው የምናመልከው ወይንስ እነዚህ አላህ ያልደነገገውን የሚደነግጉ ዲን አፍራሾች?
መውሊድ የሸሮች ሁሉ መጠራቀሚያ፣ የሙስሊሞችን አንድነት ማፍረሻ፣ የድሆችብ ንብረት መብያ….. እርኩስ ተግባር ነው፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! ራቁት፡፡
አይ ሸይጧን በየዘመኑ መጥፎውን ነገር ጥሩ አስመስሎ ስም እየቀያየረ የአደም ልጆችን ያጠማቸዋል፡፡ ወደ እሳትም ይመራቸዋል፡፡ ተመልከቱ አደም እና ሀዋን ያቺን ዛፍ ስሟን አሳምሮ እንዳትበሉ የተባሉትን አስበላቸው ከዛም ስህተት ውስጥ ጣላቸው፡፡ የኑሕን (አለይሂ ሰላም) ህዝቦች በሞቱት 5 ደጋግ ሰዎች ያዘነ መስሎ መቀማመጫቸው ላይ ሀውልት አሰርቶ ገደል ከተታቸው፡፡ የጠፉበትን እርኩስ ተግባር ሽርክ ውስጥ ዘፈቃቸው፡፡ አሁንም ይህን ኡመት “ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላችሁን ውዴት ልደቱን አክብሩለት” የሚመስል የሰይጣን ሹክታ እዚህ ኡማ ላይ ተሰራጭቶ የሽርክ መነሃርያ የሆነውን መውሊድ እያከበሩ ወደ እሳት ሲነዱ ይታያሉ፡፡ መውሊድ ላይ ከባባድ የሽርክ ቃላትን ከእስልምና አስፈንጥረው የሚያስወጡ የሽርክ ተግባራት ይታያሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ አላህን ትቶ ፍጡራንን መለመን፣ እነሱን ድረሱልን ብሎ መጣራት፣ አላህን ትቶ ለፍጡራን ስለት መግባት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
አሳዛኙ ደግሞ ጥመቱን እንደሃቅ፣ ሃቁን እንደ ጥመት ቆጥረው “ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ሰሀባዎቻቸው፣ ታቢኢኖች፣ አትባኡታቢኢን፣ 4 አኢማዎች፣ ሙሐዲሶች፣ 3 ምርጥ ክፍለ ዘመን እና ትውልድ አላከበረውም” ሲባሉ ሃቁን ከመቀበል ይልቅ ያልታዘዝነውን አንሰራም ያሉትን “ነብዩን የማይወዱ፣ የነብዩ ጠላቶች፣ ወሃብዬች እና ሌላም” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡
ከድጡ ወደ ማጡ ይሉሃል ይህ ነው፡፡ ሸይጧን ግን ዛሬ ጥፋታቸውን እያሸበረቀላቸው ዲንን በዲን ስም እንዲንዱ እየገፋፋቸው ነው፡፡
ነሷራችን በነብየላህ ኢሳ (አለይሂ ወሰለም) ላይ ድንበር አልፈው “የአላህ ልጅ ነው” እንዲሉ ያደረጋቸው የሰው እና የጂን ሰይጣናት ናቸው፡፡ ነሷራች ኢሳን ድንበር ያለፉበት ጠልተውት ሳይሆን ወደውት ነው፡፡ ግን ድንበር አለፉ፡፡ ከልክ በላይ ከፍ ከፍ አደረጉት፣ ያላታዘዙትን ልደቱን አከበሩለት፡፡ ከዚህም ኡማ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመውደድ ስም ሸይጧን መንገድ አስቷቸው ልክ እንደነሷራች ያልታዘዙትን ልደት ማክበር፣ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “መጣ ያለፈው ወንጀላችንን ማረ”፣ “የሁሉ ቀላቢ”፣ “ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ” እና የመሳሰሉትን የብቸኛ ፈጣሪና ተመላኪ አላህ መብት አሳልፈው ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመስጠት ታላቁን ማጋራት እና ቢድዐ ሲሰሩ ይታያል፡፡
ሸይጧን መቼም ለሰው ልጎች ከባድ ጠላታቸው ነው፡፡ አላህ ድንበር ከማለፍ፣ ከሽርክ፣ ከቢድዐ እና አላህ ከጠላው ሁሉ ይጠብቀን፡፡ አላህ ወደ ተውሒድ፣ ሱና፣ የሰለፉነ ሷሊሂን አረዳድ፣ እሱ መልካም ወዳለው ሁሉ ይምራን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

በ Ibnu Munewor
ሰልፍ እና ሸይኽ ዑሠይሚን
**********
መግቢያ አንድ:–
ለምን በአሁኑ ሰዓት ስለ ሰልፍ መፃፍ አስፈለገ?
መቼስ ቢፃፍ ምን ችግር አለው ወንድሜ?! ደግሞስ በሃገራችን ሰልፍ እንደ አሸን የፈላበት ወቅት ላይ አይደለን?! ስለዚህ የዑለማዎችን ፈትዋዎች ከራሳቸው ቁንፅል አስተሳሰብ በማስቀደም ለሚጓዙ ሰው ማስታወስ አይከፋም።
መግቢያ ሁለት:–
"እንደ ኢብኑ ባዝ፣ አልባኒ፣ ሙቅቢል፣ ፈውዛን፣ ወዘተ ያሉ የሱንና ዑለማዎች እንደማይፈቅዱት እየታወቀ ለምን ዑሠይሚንን ለይተህ መጥቀስ አስፈለገህ?" ከተባለ
ምክንያቱ በሳቸው ስም የሚነግዱ ሰዎች ስላሉ ብዥታ ለመግፈፍ ነው የሚል ነው።
።።።።።።።።
አዎ ሰልፍ ማካሄድ ከሱንና ዑለማዎች ዘንድ በጥብቅ የሚኮነን ነው። ዑሠይሚንም በዚህ ላይ የተለየ አቋም የላቸውም።
ነገር ግን አንዳንዶች "ሰልፍ የሚከለከለው በሙስሊም ሃገራት/ መሪዎች ላይ ሲሆን ነው። በካፊር ሃገራት ሲሆን ግን ይፈቀዳል" ይላሉ።
"መነሻችሁስ?" ስትሏቸው "ሸይኽ ዑሠይሚን በካፊር ሃገር ሲሆን ፈቅደዋል" ይላሉ።
እነዚህ አታላዮች በደፈናው በዚህ መልኩ ከመናገር ውጭ የሸይኹን ፈትዋ ቃል በቃል አይጠቅሱም። የሚያቀርቡትም ከብዙ ሸፍጥ ጋር ነው።
|||
ሰዎቹ የሚንጠለጠሉበትን የሸይኽ ዑሠይሚን ፈትዋ እንመልከት:–
✳️ ጥያቄ:– "በሃገራችን ጥፋቶችን ለመቃወም ሲባል ሰልፎችን ማካሄድ በሚፈቅዱ ሰዎች ተፈትነናል። የሆነን ጥፋት ባዩ ጊዜ ሰልፍ ያካሂዳሉ። መሪው እነዚህን ነገሮች ይፈቅዳል ሲሉ ይሞግታሉ።"
♻️ መልስ:– ሰልፍ ያለጥርጥር አይጠቅምም። ይልቁንም የሸርና የሁከት በር መክፈት ነው።
👉🏽 እነዚህ መንጋዎች በሱቆችና በተለያዩ የሚሰረቁ ነገሮች በኩል ሲያልፉ ሊሰርቁ ይችላሉ።
👉🏽 በለጋ ወጣቶችና ጎልማሶች መካከል ቅልቅል ሊኖርባቸው ይችላል።
👉🏽 አንዳንዴ ሴቶችም ሊኖሩበት ይችላል።
ስለዚህ እራሱ (ሰልፉ) ኸይር የሌለበት ጥፋት ነው።
👂🏼 ነገር ግን አንዳንድ ክርስቲያናዊ የምእራብ ሃገራት በሰልፍ ካልሆነ በስተቀር መብትን ማግኘት እንደማይቻል ሰዎች ጠቅሰውልኛል። ምእራባውያን ክርስቲያኖች በአከራካሪ ጉዳዮች ላይ መርታት ሲፈልጉ ሰልፍ ያካሂዳሉ።
➡️ በነዚህ የከሃዲዎች ሃገራት የተለመደ ከሆነና
➡️ በክፉ ካላዩት፣
➡️ እንዲሁም አንድ ሙስሊም ወይም ሙስሊሞች በዚህ እንጂ ወደ ሐቃቸው መድረስ ካልቻሉ ችግር እንደማይኖርበት ተስፋ አደርጋለሁ።
🚫 በሙስሊም ሃገራት ግን ክልክልና ያልተፈቀደ እንደሆነ ነው የማምነው።
📌 በአንዳንድ መሪዎች ሁኔታ ግን እደነቃለሁ። በውስጡ ሁከት ከመኖሩ ጋር እውነት አንተ እንዳልከው (ሰልፉን) የሚፈቅደው ከሆነ ምንድን ነው የሚገኝበት ትርፍ⁉️አዎ! ምናልባት አንዳንዱ መሪ ለምሳሌ የሆነን ነገር ይፈልግና ቢፈፅመው ምእራቡ አለም የሚተቸው ይሆናል። እሱ ምእራቡን ይመሳሰላል። እናም ምእራባውያኑን "ተመልከቱ! ህዝቡ እንዲህ ፈልጎ፣ ወይም ተቃውሞ ተሰለፈ" ለማለት ህዝቡ ሰልፍ እንዲወጣ ይፈቅዳል። ይሄ ምናልባት ለሌላ ሰበብ ሊሆን ይችላልና የሚታይ ይሆናል። ጥቅሞቹ ይበዛሉ ወይስ ጉዳቶቹ?
✳️ ጠያቂ:– እንዲሁ ጥፋት ደረሰና ሰልፍ ተካሂዶ ጠቅሟል።
♻️ ሸይኽ ዑሠይሚን:–
ነገር ግን ይበልጥ ይጎዳል። በዚህኛው ጊዜ ቢጠቅም እንኳን በሁለተኛው ጊዜ ይጎዳል።"
[ሊቃኡል ባቢል መፍቱሕ: 203/29]
📌መጠነኛ ዳሰሳ!!📌
።።።።።።።።።
1️⃣ ከፈትዋቸው ሸይኹ ሰልፍን በጥብቅ እንደሚቃወሙ እንረዳለን። የጠቀሷቸው በሰልፍ ሰበብ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጥፋቶች በሃገራችንም በብዛት ያጋጥማሉ።
👉🏽 በሰልፍ ላይ ያለው ቅልቅል በተጨባጭ ያለ ነው።
👉🏽 በሰልፍ ሰበብ የሰልፈኞች ሞባይል፣ ገንዘብ፣ ጌጣጌጥ፣… ተዘርፈዋል።
👉🏽 በሰልፈኞችና ወሮበሎች መጓጓዣዎች፣ ሱቆችና ንብረቶች ላይ ጥፋት ሲደርስ ያጋጥማል።
👉🏽 በርካታ ሰልፈኛ ታፍሶ ታስሯል፣ ተደብድቧል፣ አኳሉ ጎድሏል፣ ተገድሏል፣ አገር ጥሎም ተሰዷል። ይሄ የሙስሊሞች ሰልፍ ላይ በሰፊው ያጋጠመ ነው። ባለፉት አምስት ወራት መዲናዋ ላይ በተደረጉ ፖለቲካዊ ሰልፎችም ቢያንስ ሰባት ሰው የሞተ ሰው ከ150 በላይ ሰው ተጎድቷል።
👉🏽 መስጂዶች ሰልፈኞችን በሚያሳድዱ ወታደሮች/ፖሊሶች ተደፍረዋል።
👉🏽 ከሰልፍ የታፈሱ ሴቶች መደፈር፣ ልብስን አስወልቆ ራቁት መባረር፣ በከሃዲዎች መዘባበት ተፈፅሞባቸዋል። ሌላም ሌላም።
2️⃣ ሁለተኛ ሸይኹ በጠባብ ሁኔታ ብቻ ሰልፍን ፈቅደዋል። እሱም:–
📌 በካፊር ሀገር ከሆነ፣
📌 ፈቃድ ካለውና
📌 መብት የሚከበርበት ብቸኛ መንገድ ከሆነ ነው።
አንዳንድ አታላዮች ግን ሌሎቹን መስፈርቶች ቆርጠው በማውጣት "ሸይኹ በካፊር ሃገር ከሆነ ፈቅደዋል" እያሉ ያራግባሉ። ይሄ ግን በሸይኹም ላይ ጭምር ሸፍጥ መፈፀም ነው። ወደው አይደለም "እኔማ የሚዋሽብኝ ብዛቱ!" ማለታቸው፣ ረሒመሁላህ!!
👂🏼የሸይኹን ቅድመ ሁኔታዎች ከሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር ስናነፃፅራቸው ፈትዋቸው በሁለት ምክንያት የቀደመውን የሃገራችንን ሰልፍ አይፈቅድም።
1️⃣:– ሰልፉ የሙስሊሞችን ጉዳይ በሚመለከት መንግስታዊ ፈቃድ አልነበረውም። ፈቃድ ከሌለው ደግሞ ሸይኹ እንዲህ አይነቱን ሰልፍ አልፈቀዱም።
የስሜት ተከታዮች ግን "በሃገራችን እየደረስብን ያለውን ሃይማኖታዊ በደል የምንቃወመው መንግስት በሚፈቅደው ሰልፍ ነው" እያሉ ሳዑዲ ድረስ ሄደው የታላላቅ ዑለማዎችን በር ሲያንኳኩ ነበር። ምኞታቸው አልተሳካላቸውም እንጂ። እውነታውን እየደበቁ አሽሞንሙኖ በማቅረብ የሚፈልጉትን ፈትዋ ለማግኘት መጣር አሳፋሪ የሆነ የስሜት ተከታዮች መታወቂያ ነው። እዚህም ላይ "ሰልፉን መንግስት ይፈቅደው ነበር" ማለት አይን ያወጣ ውሸት ነው። ተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የሃገሪቱ ህግ ይፈቅዳል ማለት ስልጣን ላይ ያለው መሪ ይፈቅደዋል ማለት አይደለም። እውነት እንደምትሉት መንግስት ሰልፉን ከፈቀደላችሁ:
👉🏽 ለምን ሰልፈኞችን በጭስ ቦምብ ይበትናል?
👉🏽 ለምን ሰልፈኞች ላይ ጥይት ይተኩሳል?
👉🏽 ለምን ሰልፈኞችን ይደበድባል?
👉🏽 ለምን አፈሳ ይፈፅማል?
👉🏽 ሰልፈኞች ላይ ዘረፋ፣ አስገድዶ መድፈር፣ እርቃን አድርጎ ማባረር የፈፀመውስ ማን ያሰማራው ፖሊስ ነው?
👉🏽 ሰልፍ ከተፈቀደ ለምን ሰልፍ ሲያስተባብሩ የነበሩ ወጣቶች ሀገር ጥለው ሸሹ?!
2️⃣:– ሌላኛው የዑሠይሚን ቅድመ ሁኔታ በሰልፍ ካልሆነ በስተቀር መብት የማይከበር ከሆነ ነው ሰልፍን የፈቀዱት።
እኛ ዘንድ ግን በሰልፉ ጥያቄ ሊመለስ ቀርቶ ዱላ ነው የቀረበው። ብዙ ጥፋት ነው የደረሰው።
♻️ ስለዚህ ከዚህ በኩልም ስንመለከተው እስካሁን ባለው ዘመን የሸይኹ ፈትዋ በሃገራችን ሰልፍን የሚፈቅድበት ሁኔታ የለውም።
በመጨረሻም አንድ ኢስላማዊ ባልሆነ ስርኣት ውስጥ የሚገኝ መሪ ፈቃድ እየሰጠ ሰዎች ሰልፍ ያካሂዳሉ። በሚነቀፉ ጊዜም መሪው እንደሚፈቅድላቸው ያመካኛሉና ስለዚህ ምን ይላሉ ተብለው ተጠይቀው የሰጡትን ምላሽ በማንሳት እቋጫለሁ።

"ሰለፎችን በመከተል ላይ አደራህን። ሰለፎች ዘንድ ከነበረ መልካም ነው። ካልነበረ ግን መጥፎ ነው። ያለጥርጥር ሰልፍ መጥፎ ነው። #ከሰልፈኞቹም ሆነ #ከሌሎች በኩል ወደ ሁከት ነውና የሚወስደው። በሰዎች ክብር ወይም በገንዘብ ወይም በአካል ላይ ወሰን መተላለፍ ሊከሰትበት ይችላል። ምክንያቱም በዚህ የነውጥ ባህር ላይ ሰው የሚናገረውንና የሚፈፅመውን እስከማያውቅ ድረስ እንደ ሰካራም ሊሆን ይችላልና።
👂🏼ስለዚህ ሰልፎች መሪው ፈቀደም አልፈቀደም ሁላቸውም መጥፎ ናቸው።
የአንዳንድ መሪ መፍቀድም ፕሮፓጋንዳ ብቻ ነው። እንጂ ወደ ልቡ ብትመለስ በፅኑ ይጠላዋል። ነገር ግን ‘ዲሞክራት ነው’፣ ‘ለሰዎች የነፃነትን በር ከፍቷል’ ይባል ዘንድ ያስመስላል። ይሄ የሰለፎች መንገድ አይደለም።"
[ሊቃኡ ባቢል መፍቱሕ: 179/19]
የሌሎች #የሱንና ዑለማዎች ፈትዋዎችን፣ በርእሱ ላይ የሚነሱ ብዥታዎችንና ምላሾቻቸውን በዝርዝር መመልከት የፈለገ በርእሱ ላይ የተፃፉ ኪታቦችን መመልከት ይችላል።

መውሊድ
=====
ከአላህ እና ከመልክተኛው (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ውጭ ሸሪዓን መደንገግ የሚችል አለን? አላሁ (ሱብሀነሁ ወተዓላ) ሃይማኖቱን ሞልቶታል፡፡ ይህ ታላቅ እውነታ ሊረሳ አይገባውም፡፡ በእስልምና ሀይማኖት የአላህ መልክተኛ በተግባር ሰርተው ያሳዩት እና ያዘዙበት ሁለቱን ኢዶች ብቻ ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ ከመልክታቸው የደበቁት ነገር አለን? አላህን ከመልክተኛው ቀጥሎ አላህ ላይ ያመኑ፤ የወደዱት፤ ሀብት ንብረታቸውን ለአላህ ዲን የሰጡት ሰሃባዎች፤ ከማናችንም በላይ የአላህን መልክተኛ ይወዱ ነበር፡፡ የታዘዙትንም ይፈፅሙ ነበር፡፡ ይህንን የሚጠራጠር አለን?
አላህም ሙሃጂርና አንሳርን የተከተለን ሰው እንደሚወድ ተናግራል፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንመልስ
ነብያችን ሰርተውበታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
አቡበክር አሲዲቅ ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
ኡመር ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
ኡስማን ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
አልይ ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
ሙሃጂሮችና አንሳሮች ሰርተውታልን?
ታቢእዮች፤ አትባ ታቢኢን፤ አቡ ሀኒፋ፤ ኢማሙ ማሊክ፤ ኢማሙ ሻፊእ፤ ኢማሙ አህመድ፤፤፤፤፤ ሰርተውታልን?
መውሊድ ከዚህ ሁሉ አመታት በሃላ ዲን ላይ መጨመሩ ብቻ የጥፋት መንገድ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ አይሆንምን?
አላህ መውሊድ በመስራቴ ይቀጣኛልን? ብሎ አንድ ሰው ቢጠይቅ፡፡ የሰይድ ሙሰየብ ንግግር መልስ ይሆናል፡፡ አንድ ሰው ከሱቢህ በሃላ ደጋግሞ ሰላት ሲሰግድ አዩት፤ ከዛም እሳቸው ተው ሲሉት እሱም እንዲህ አለ ‹‹አላህ ሰላት በመስገዴ ይቀጣኛልን?›› እሳቸውም እንዲህ ብለው መለሱለት ‹‹ሰላት በመስገድህ ሳይሆን መልክተኛውን በመቃረንህ ነው››
ይህ ከሆነ እውነታ፡፡ መውሊድን ለማክበር ችግር የለውም የሚሉ ሰዎች የአላህን ቅጣት አይፈሩምን?
የአላህ ባርያዎች ሆይ! መውሊድ እንደማይቻል መናገር አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት የሙስሊሙን አንድነት የሚበታትን አይደለም፤ እንዲያውም እውነተኛ ወንድማማችነትን፤ ታማኝ መካሪነትን የሚያሳይ ነው፡፡ በአላህ ስም ወንድምና እህቶቼን የምመክረው አላህና መላክተኛው ያዘዙንን በአቅማችን እንስራ፤ ከዛ በተረፈ ያልታዘዝነውን ከመስራት አላህን እንፍራ፡፡ አንድነት ይበታተናል እየተባለ ቢድዓ ዝም ማለት የአላህ ቅጣት ሲመጣ ሁላችንን ነው የሚነካን፡፡ አላህ የሃቅን መንገድ ሁላችንንም ይምራን፡፡ አሚን፡፡

ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል-ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ስለ መውሊድ
“ልደትን ማክበር የተወለደውን በማላቅ ከቢድኣ ይካተታል (ይቆጠራል)፡፡ ከነብዩም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሆነ ከሰሃባዎች አልተገኘም (ያልተገኘ ነው)፡፡ (ልደቱ) የነብዩም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይሁን ወይንም የሌሎች እንደ ኡለማዎች ያሉ ወይንም የደጋጎችም ቢሆን (ማክበሩ ቢድኣ ነው)፡፡ (ለዚህም) ማስረጃው በጣም ቀላል ነው፡፡ የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደት ማክበር ቢድኣ መሆኑን የሚጠቁም (ከሚጠቁሙት ውስጥ)”
- “እናንተ መውሊድን አክባሪዎች ሆይ! ከሰሃባዎች የበለጠ ነብዩን ትወዳላችሁ ወይ?” (እንላቸዋለን)
- (እነሱም) “ሰሃባዎች ይበልጣሉ ካሉ”
- (እኛም) “ይህን የምታደርጉት ለነብዩ ውዴታ ነውን? እንላቸዋለን”
- (እነሱም) “አዎ ለነብዩ ውዴታ ነው ካሉን”
- (እኛም) “ታድያ ከናንተ የበለጠ ነብዩን የሚወዱት (ሰሃባዎች) ለምን አላደረጉትም (አላከበሩትም)? እንላቸዋለን”
- “(ሰሃባዎች) ዘንግተውት? ወይንስ ችላ ብለውት ነውን? ወይንስ ሳያውቁት ቀርተው?”
- “ሁሉም ልክ አይደለም፡፡”
- (እነሱም) “ይህን የምናደርገው ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለማስታወስ ነው ካሉ”
- (እኛም) “ሱብሃነላህ (ለአላህ ጥራቻ ይገባው) እንላለን፡፡ እስልምና ያልደረሰበትን ደረሳችሁበትን?” (እንላቸዋለን)
- (እነሱም) “አዎን ካሉ፡፡ ጉዳዩ በጣም አደገኛ ነው፡፡”
- (ይህ አባባላቸው) “ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁ፡፡ የሚለው የአላህ ቃል ልክ አይደለም እንደ ማለት ነው፡፡”
- “ምክንያቱም (እነሱ) እስልምና ላይ የሚጨመር አገኙ (ማለት ነው)፡፡”
- (እነሱ) “እስልምና ላይ አንጨምርም ካሉ”
- (እኛም) “እስልምና በደነገገው ልክ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ማስታወስ በቂ ነው እንላቸዋለን”
የሸይኽ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ንግግር እዚህ ላይ አለቀ፡፡

ከአላህ ውጭ በነብያችን መመካት ይቻላልን???
አላህ ከሽርክ ይጠብቀን
============
በዚህ አመት ረመዳን የህፃናት መንዙማ ተብሎ የወጣው ላይ የሚከተለው የሽርክ ንግግር ይገኝበታል፡፡ አላህ ከሽርክ ይጠብቀን እና፡፡
ያቀመረል መካ አሰላሙ አለይካ
ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ
‹‹ምዕመናን እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ተመኩ››
‹‹በአላህም ላይ የሚጠጋ(የሚመካ) ሰው እርሱ (አላህ)በቂው ነው››
አላህ ያዘዝን በእርሱ ብቻ እንድንመካ ነው፡፡ እንዲህም ሲል
በማይሞተው ህያው አምላክ (አላህ) ላይ ተመካ፡፡ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ባሪያ ናቸው እሳቸውም አላህ ላይ ነበር ሲመኩ የነበረው እኛንም ያዘዙን እሱ ላይ ብቻ እንድንመካ ነው፡፡
ኢብራሂምም አለይሂ ሰላም ሆነ ሁሉም አማኞች በአንድ አላህ ላይ ባቻ ነው የተመኩት፡፡
ቅድሚያ ለተውሂድ፡፡
ይህንን መንዙማ እንጠንቀቅ ሰዎችን እናስጠንቅቅ፡፡ አንድ ስራ ሽርክ ከተደባለቀበት ስራን ሁሉ ያበላሻል፡፡

በልደት ቀናቸው ቢፆሞ ኖሮ ታድያ ለምንድን ነው አመት ጠብቀው ያቺ የተወለዱባትን ቀን ያልፆሙት?????
================================
የተለመደው የሱፍዬች እና የአህባሾች ማምታቻ መውሊድን በተመለከተ ሲጋለጥ
እንዲህም ይላሉ ‹‹ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰኞን በመፆም የተወለዱበትን ቀን አክብረዋል››
ይሄ በመውሊድ ወቅት ሰው ዘንድ የተሰራጨ ብዥታቸው ነው ‹‹መውሊድ ማክበር ችግር የለውም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እራሳቸው ሰኞን በመፆም ስላከበሩት፡፡›› ነገር ግን ይሄ ቅጥፈት ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ ላይ ውሸትን የሚቀጥፍ ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡
ሀዲሱ እንዲህ ነው የሚለው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰኞን ስለመፆማቸው ተጠየቁ እሳቸውም ‹‹በዛ (ቀን) ተወለድኩ እናም በዛው ቀን ወህይ (መለኮታዊ ራዕይ) ወረደልኝ›› ሰሂህ ሙስሊም (1162)
እውነታው የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደታቸውን አላከበሩም፡፡ የተወለዱበትን ቀን ሰኞ ፆሙ እንጂ በልደት ቀናቸው አልፆሙም፡፡ በሁለቱ መሃል በጣም ሰፊ ልዩነት አለ ድጋሚ አንብቡት ወንድም እና እህቶች፡፡
‹የፆሙት በተወለዱበት (ሰኞ) ቀን እንጂ አመት ተጠብቆ የምትመጣዋን የልደት በዓልዋ ቀን አይደለም›
የተወለዱበት ቀን በሚለው ላይ በኡለማዎች መሃል ልዩነት አለ፡፡ ለምሳሌ ረቢዑል አወል 12, 9 እና የመሳሰሉትን) የሞቱበት ቀን ግን በቁርጥ ረቢዑል አወል 12 ነው፡፡
ጥያቄዎች
=====
የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰኞን ፆመዋል፡፡ በልደት ቀናቸው ቢፆሞ ኖሮ ታድያ ለምንድን ነው አመት ጠብቀው ያቺ የተወለዱባትን ቀን ያልፆሙት?????
ይልቁንስ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ብዙ ሰኞዎችን ፆመዋል፡፡ በሱፍዬች እና በአህባሾች ሎጂክ መሰረት ‹‹በአመት ውስጥ በተለያየ ግዜ ነው የተወለዱት›› ማለት ነው?????
ማጠቃለያ
======
ሰኞ ቀናቶችን የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና በመከተል እንፆማለን እንጂ ስሜታችንን ለመከተል ሀዲስ አናጣምም፡፡
መውሊድ ውስጡ ሽርክ ያቀፈ ቢድዓ ነው፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! እንሽሸው፡፡ ከሃቅ ባኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

መውሊድ?
ማስረጃ የሚጠየቀው ማን ነው?
አንድ ግለሰብ ፌስቡክ ኮሜንት ላይ እንዲህ ሲል ጠየቀ/ች
“መውልድን አታክብሩ የሚል ደሊል ከቁርአንና ከሀድስ መልስ እፈልጋለሁ? ???????”
ትክክለኛው ጥያቄ
“መውሊድን አክብሩ የሚል ከቁርአን እና ከሀዲስ መልስ እፈልጋለሁ” ነበር፡፡
ምክንያቱም ማንኛውም አምልኮ በቁርአን እና ሀዲስ ካልታዘዝን እኛ በደመ ነፍስ ተነስተን ልንፈፅመው አንችልም፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ
“የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ወደራሱ ተመላሽ ነው” ትክክለኛ ሀዲስ
በዚህ ሀዲስ መሰረት በቁርኣን እና ሀዲስ መውሊድ አውጡ የሚል ታዟልን?
በፍፁም፡፡ ስለዚህ ማስረጃ የሚጠየቀው በዲን ላይ የሌለን ነገር የሚሰራው እንጂ፣ በዲን ላይ የሌለን ነገር የሚቃወመው አይደለም፡፡
የአላህ መልክተኛ እንድንታገላቸው ካዘዙን ሰዎች ውስጥ “ያልታዘዙትን የሚሰሩ፣ የማይሰሩትን የሚናገሩ” ናቸው፡፡
የነብይም፣ የአገርም፣ የልጅም፣ የእናትም ብሎም የማንንም ልደት ባእል አመት ጠብቀን እንድናከብር ኢስላም አላዘዘንም፡፡ ስለዚህ እንርቀዋለን፡፡
ለምሳሌ ሁለቱ ኢዶች በሸሪአ ተደንግገዋል ስለዚህ የአላህ መልክተኛ፣ ሰሃባዎች፣ ፉቀሃዎች፣ ሙሀዲሶች እና የነሱን መንገድ የተከተሉ ሁሉ ይሀው እስከዛሬ ያከብሩታል፡፡ በተገላቢጦሹ መውሊድ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ሰሃባዎች፣ ፉቀሃዎች፣ ሙሀዲሶችና የነሱን መንገድ የተከተሉ ሁሉ አልሰሩትም፡፡
ታድያ ማን ነው ማስረጃ ከቁርኣን እና ሀዲስ ማቅረብ ያለበት?
አላህን እንፍራ ያልታዘዙትን መስራት ከአላህ ቢያርቅ እንጂ አያቃርብም፡፡ ሸይጧን ዘንድ ደግሞ ቢድኣ (በዲን ላይ የሚደረግ ጭማሪ) ከወንጀል በላይ ተወዳጅ ነው፡፡
አላህ ውብ የሆነውን የሱና ጎዳና ይምራን፡፡

የመውሊድ ውድድር
ፈተና አንድ
1) ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስንት ጊዜ ነው መውሊድ በኣል ላይ የተሳተፉት?
___________________
2) የትኛው ከተማ ላይ ነበር መውሊድ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሃባዎች የተከበረው?
_____________________________________
3) ሰሃባዎች የትኛውን አይነት የመውሊድ አወጣጥ ነበር ለታቢኢኖች ያስተማሩት?
________________________________________________________
4) ምን አይነት ምግብ ነበር በመውሊድ ወቅት ሲመገቡት የነበረው?

5) መውሊድ ላይ በሰሃባዎች ሲዜሙ ከነበሩ ዘፈኖች ውስጥ ዋናዋናዎቹን ጥቀስ
___________________________________
___________________________________
• አስታውሱ ሁሉም መልሶች ከሚከተሉት መሰረታዊ ምንጮች ነው መሆን ያለባቸው፡
1. ከቁርኣን፣
2. ከሀዲስ፣
3. ከሰሃባዎች ንግግር
በደንብ አስባችሁ፣ ጊዜያችሁን ውሰዱና ቁርኣንን ፈትሹ፣ ቡኻሪ ሙስሊም እና ሌሎች የሀዲስ መዛግብትን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡
የተተረጎመ

ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከሰሃባዎች ጋር አዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት መጥተዋልን?
http://bit.ly/2DAlFv8
http://bit.ly/2ROcgCS
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/1524

ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
- ሞተዋል፣
- የተቀበሩትም የምእመናን እናት አኢሻ (ረድየላሁ አንሃ) ቤት ውስጥ ሳውዲ አረቢያ ላይ መዲና ከተማ ውስጥ ነው፣
- ሞተው ከተቀበሩ በኋላ ሰሃባዎች ለማየት እንኳን ከቀብራቸው አልወጡም፡፡
- እሳቸው ወደ እኛ አይመጡም፡፡
- እኛ ካለንበት ሆነን እሳቸው ላይ የምናወርደው ሰለዋት ቀብራቸው ውስጥ ሆነው ይደርሳቸዋል፡፡
ሸሪአተል ኢስላም ላይ በመዋሸት ከሚታወቁት አንዱ ሙሐመድ አወል (የሺርክ መንዙማ አቀንቃኙ) አዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት ላይ ለተሰበሰቡ ሰዎች እንዲህ ብሏቸዋል
“አይዟችሁ ተደሱ (ተደሰቱ)፣
መውሊድ የመጣችሁ፣
እስተ አስሀቦቹ (እስከነ ሰሃቦቹ)፣
ነቢ መጡላችሁ”
ሲል ይዋሻል፡፡

የትኛውን መውሊድ?
እንደሚታወቀው በኢስላም የታዘዙት ሁለት አመታዊ በኣላት፣ ኢድ አል-ፊጥር እና ኢድ አል-አድሃ ናቸው፡፡ ኢድ አል-ፊጥር አንድ ቀን ብቻ ሲሆን፣ ኢድ አል አድሃ ደግሞ 4 የበኣል ቀናቶች ናቸው፡፡ ታድያ በሀገራችን ተጨባጭ አላህ 4 ቀን እንዲከበር ያዘዘውን አንድ ቀን ብቻ እያከበርን ያልታዘዝነውን መውሊድ ግን ከአንድ ቀን በላይ በተለያዩ ሰዎች ስም ሲከበር ይታያል፡፡
ለምሳሌ ሀገራችን ላይ በተለያየ ቀናት ከሚከበሩ የመውሊድ አይነቶች ውስጥ
1) የነብዩ መውሊድ፣
2) የአሊ ጎንደር መውሊድ፣
3) የአባድር መውሊድ፣
4) የዳንግላው መውሊድ፣
5) የአብሬት መውሊድ፣
6) የቃጥባሬ መውሊድ፣
7) የአልከሶ መውሊድ፣
8) እና ስፍር ቁጥር የሌላቸው መውሊዶች……
ለምን ይሆን በኢስላም የታዘዝነውን ትተን ያልታዘዝነውን የምንሰራው?
እውነት ይህ ነው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ውዴታ?
በፍፁም፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “አደራችሁን አዳዲስ ነገሮችን (በዲን ላይ ከመጨመር) ተጠንቀቁ፡፡ ሁሉም አዲስ ነገር ጥመት ነው፡፡” ብለው ሲያበቁ
አሁንም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው (ተቀባይነት አያገኝም፣ ውድቅ ነው)” ብለው ሳለ
ዛሬ እሳቸው ያዘዙትን ትተው ያላዘዙትን የሳቸውንም ይሁን ሌሎች ጥሩ ሰዎች ናቸው ብለው የሚገምቷቸውን የአሊ ጎንደር መውሊድ፣ የአባድር መውሊድ፣ የዳንግላው መውሊድ፣ የአብሬት መውሊድ፣ የቃጥባሬ መውሊድ፣ የአልከሶ መውሊድ እና የመሳሰሉትን እያሉ በውዱ ሃይማኖታችን ላይ ቅጥፈትን ይቀጥፋሉ፣ የክህደት ንግግሮችን መውሊዶች ላይ ይናገራሉ፣ ይጨፍራሉ፣ ይህን አደንዛዥ ቅጠል ያላምጣሉ፡፡
ሱብሃነላህ ይህ በፍፁም ነብዩን መውደድ አይሆንም፡፡ ነብዩን ከማንም በላይ የሚወዱት ሰሃባዎች የነብዩን ፈለግ ህይወታቸው ላይ ተላበሱ እንጂ እንዲህ ልደት እናክብር አላሉም፡፡
ለሙስሊሙ ከታሰብ መውሊድ ብሎ በሺርክ፣ በቢድኣ፣ በጭፈራ እና አደንዛዥ ቅጠል ጫትን መቃም እና ማስቃም ሳይሆን፣ መስጂዶችን ማስፋፋት፣ መድረሳዎች መገንባት፣ እውነተኛውን የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አስተምህሮት ማሰራጨት፣ ከሱስ የፀዳ ሃይማኖቱን እና ሀገሩን የሚጠቅም ትውልድ ማነፅ ይጠበቅብናል፡፡
ይሄ እውነተኛ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ውዴታ የሚገለፀበት ተግባር ነው፡፡
አላህ ሱናቸውን ከሚከተሉት ከቢድኣ ከሚርቁት ትውልዶች ያድርገን፡፡