ቢላዋን በደንብ መሳል
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ስታርዱ አስተራረዳችሁን አሳምሩ፣ አንዳችሁ ቢላዋውን በድንብ ይሳል፣ የሚታረደውን ይገላግለው፡፡” ሙስሊም ዘግበውታል
https://t.me/SadatTextPosts
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

ተውሒድ
ተቀባይነት ያለው ዱኣ፣ ከዱኣ ሁሉ በላጭ ….
- የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ከዱኣ ሁሉ በላጭ የአረፋ ቀን ዱኣ ነው፡፡ ከምላቸው (ዱኣዎች ውስጥ) ምርጡ ዱኣ እኔና ከእኔ በፊት የነበሩ ነብዩች ያሉት [ላ ኢላሃ ኢለላህ ዋህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሀምድ ወሁወ ኣላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር] (ትርጉሙም ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ የለም፡፡ በብቸኝነት፣ ለእርሱም አጋር የለውም፣ ንግስና በጠቅላላ የእሱ ነው፣ ምስጋናም በጠቅላላ የእሱ ነው፣ እሱም ሁሉን ነገር በማድረግ ላይ ቻይ ነው፡፡”
የምንወስዳቸው ቁምነገሮች
- የዛሬው ቀን ወሳኝ የዱኣ ቀን እንደሆነ፡፡ ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ከዱኣ ሁሉ በላጭ የአረፋ ቀን ዱኣ ነው” ብለዋልና፡፡
- የተውሒድ ቃል “ላ ኢላሃ ኢለላህ ዋህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሀምድ ወሁወ ኣላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር” የነብዩ ሙሐመድም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሆነ የሌሎች ነብያት የሚጋሩት እና የተላኩበት መልክት እንደሆነ፡፡
- የሰው ልጅ ከእሳት ተጠብቆ ጀነት የሚገባው ይህችን ውድ የተውሒድ ቃል ሳያፈርሳት በውስጡ አምኖባት፣ በምላሱ እየተናገረ፣ በሰውነቱ ሲሰራባት ነው፡፡ ይህን ማድረግ ከቻለ አላህ በእዝነቱ ታላቁን ሽልማት ጀነት ይለግሰዋል፡፡ ከታላቁ ቅጣት ጀሀነም ይጠብቀዋል፡፡
- በዚህ ቀን ይህን ዱኣ ማብዛት፡፡ በነገራችን ላይ በሌላ ዘገባ በቀን 100“ላ ኢላሃ ኢለላህ ዋህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሀምድ ወሁወ ኣላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር” ያለ ሰው የቀኑ ኸይር ሰራተኛ ነው ከእሱ በላይ ያለ ሲቀር ብለው አዛኙ ነብይ ነግረውናል፡፡
- ዱኣ በሁለት ይከፈላል
o የጥየቃ ዱኣ፡- አላህ ሆይ! ጤና ስጠኝ፡፡ አላህ ሆይ! ልጅ ስጠኝ፡፡ አላህ ሆይ! ሚስት ስጠኝ፡፡
o የአምልኮ ዱኣ፡- አላህን ማምለክ በጠቅላላ እዚህ ውስጥ ይገባል፡፡ ለምሳሌ የአምልኮዎች ሁሉ ታላቁ አምልኮ የሆነውን ከላይ የተጠቀሰውን የተውሒድ ቃል አምኖበት ላለው ሰው ከዱኣ ሁሉ በላጭ የአረፋ ቀን የሚደረግ ነው፡፡ እኔም ከእኔ በፊት የነበሩ ነብያት ያሉት ሲሉ አዛኙ ነብይ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ነግረውናል፡፡ ከአላህ ጋር ያለን እውነተኛ የአምልኮ ትስስር ተውሒድ ሲያምር በተውሒድ ሰበብ ከጠፊዋ ዱንያ በላይ ያሉትን የእሱን ፊት ማየት፣ ጀነትን እና ፀጋዎቿን ይለግሰናል፡፡
አላህ በተውሒድ ኖረው በዛው መንገድ ላይ ከሚሞቱት ያድርገን፡፡ እኛንም ዝርያዎቻችንንም ከሺርክ ይጠብቀን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በሙሐመድ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተሉ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

አላሁ (ሱብሃነሁ ወተአላ) እንዲህ ይላል።
وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ مَاذَا تَكْسِبُ غَدًا ۖ وَمَا تَدْرِي نَفْسٌ بِأَيِّ أَرْضٍ تَمُوتُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِير
ማንኛይቱ ነፍስም ነገ ምን እንደምትሰራ አታውቅም።
ማንኛይቱ ነፍስም የት እንደምትሞት አታውቅም።
አላህ አዋቂ ውስጥ አዋቂ ነው።
*************************
ሰው የት እንደሚሞት፣ መቼ እንደሚሞት ካላወቅ፣ በማንኛውም ቦታ እና ወቅት ለ ፍጡራን የማይቀረው ሞት ሳይቀድመው አላህን ሊፈራ ይገባዋል።
አላህ ሆይ! አንተን ከሚፈሩት ባሪያዎችህ አድርገን።

በ Mohammed Ibrahim Ali
August 25 at 2:27 PM
#ዋቄፈና/Waaqeffannaa
.
.
ዋቄፈና በሀገራችን ከሚገኙ ዘልማዳዊ እምነቶች አንዱ ነው። በማእከላዊና ደቡባዊ ኢትዮጵያ ጥቂት የማይባሉ ተከታዮች የቀሩት እምነት ነው።
.
ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን የብሄር ፓለቲካውን መነሳሳትን ተከትሎ ይህን ከጊዜ ጊዜ እየተመናመነ የሄደ ዘልማዳዊ እምነት መልሶ ለማንሳት የሚታትሩ ሰዎችን እያየን ነው።
.
.
#ዋቄፈና ምንድን ነው?
.
.
ስለዋቄፈና እምነት የሚገልፅ የእምነቱ መመሪያ መፅሀፍ የለም። እንዳውም ያለፈ ታሪኩን እንኳ የሚገልፅ ጥንታዊ ሰነድ አይገኝም። እንደ ተከታዮቹ ግንዛቤ በአንደበት ከሚተላለፈው እሳቤ በዘለለ የተጨበጠ እና አንድ አይነት ምልከታን የሚያስይዝ የጋራ ስምምነት የለውም። ለዛም ነው ዋቄፈና 'ዘልማዳዊ እምነት' የምንለው።
.
ዋቄፈና - ዋቃ/Waaqaa ከሚለው ቃል ተወስዶ ለእምነቱ መጠሪያነት እያገለገለ የሚገኝ ስያሜ ነው። ዋቃ በኦሮሚያ አካባቢ በሚገኙ አማኞቹ ዘንድ እንደ አምላክ የሚታሰብ አንዳንዶች ታላቅ ግኝ/Supreme being/ እንደሆነ ሌሎች ደግሞ ፈጣሪ እንደሆነ የሚያምኑበት ነው። 8
.
እምነቱ በከፊል ሰርጎ በገባባቸው እንደ አማራ ክልል ባሉ ቦታዎች 'ውቃቢ' እየተባለ ሲጠራ የሚሰጠው ባህሪ ግን ዋቄፈናዎች ዘንድ ካለው ፍፁም የተለየ ነው።
.
ወንድ የእምነቱ ተከታይ ዋቄፈታ/Waaqeffataa/ ሲባል ዋቄፈቱ/Waaqeffattuu/ ደግሞ ለሴት የእምነቱ ተከታይ የሚሰጥ መጠሪያ ነው፡፡
.
.
#የዋቄፈና እምነቶች
.
.
(እምነቱ የተፃፈ የወል መመሪያ ስለሌለው ከቦታ ቦታ ሊለያይ ይችላል)
.
.
* ዋቄፈናዎች 'ዋቃ' ድሮ ከሰዎች ጋር ይኖር ነበር ይላሉ፤ ሰዎች መጥፎ መስራት ሲጀምሩ ከነሱ ተለይቷል ብለው ያምናሉ።
.
* ዋቃ (አምላክ በነሱ እሳቤ) ጥቁር ነው ብለው ያምናሉ፤ በፀሎታቸውም ጥቁር አምላክ/Waaqaa gurracha ሲሉ ይጠሩታል።
.
* ዋቃን በሰማይ ይመስላሉ፤ መሬትም የዋቃ ሚስት ነች ብለው ያስባሉ። ይህንንም በምርቃትና እርግማኖቻቸው ይገልፁታል።
.
* ዋቃን ለመለማመን ወደ ተራሮች ይወጣሉ፤ እሱም በጥቁር ደመና ተመስሎ ይቀርበናል ብለው ያስባሉ።
.
* ለኦዳ/ዛፍ የተለየ ቦታ ይሰጣሉ። የተለያዩ እምነቶችንም በሱ ላይ ያሳድራሉ፤ ለመሬት መስዋእት ለማቅረብ በኦዳ/ዛፍ ስር ያርዳሉ። (አንዳንዶች የኦዳ ዛፍን እንደ እምነቱ ምልክት በመቁጠር ቅርፁን አንገታቸው ላይ ያስሩታል)
.
* ለምስጋና በሚል በዛፎች፣ በሀይቆችና ተራሮች ላይ የኢሬቻን በዓልን ያከብራሉ። ለዋቃ እርጥብ ሳርን በቁርባን መልክ ውሀ ላይ ይበትናሉ።
.
* 'ቃሉ' በመባል የሚጠሩ የዋቃን መልእክት ለህዝቡ የሚያደርሱ፣ የህዝቡንም ፀሎት ለዋቃ የሚያስተላልፉ ሰዎች አሉ ብለው ያምናሉ። (ቃሉዎች ልክ እንደ ጠንቋዮች ከጅኖች ጋር ቁርኝት እንዳላቸው ይገመታል)
.
[ እምነቱ በከፊል በሰረገባቸው ሌሎች ቦታዎች ጠንቋዮች 'ቃሉ/ቃልቻ' በመባል ይጠራሉ - ሆኖም 'ቃልቻ' የሚለውን ቃል ለሸሆች እንደተለዋጭ ስም የሚጠቀሙም እንዳሉ ልብ ይሏል]
.
* 'አያና' የሚባል የሞቱ ሰዎች መንፈስ አለ ብለው ያምናሉ። ያ መንፈስ በሰዎች ላይ እንደሚያድርም ያስባሉ። መንፈሱ አድሮባቸዋል የሚሏቸውንም ሰዎች አያና/አያንቱ ወይም ቃሉ/ቃሊቲ ብለው ይጠራሉ።
.
* አድባር እና አቴቴ የሚባሉ አማልክት በተለያየ በዓል እና ድግስ መልክ ምስጋናና ልመና ይቀርብላቸዋል።
[ይህ እምነቱ በከፊል በሰረገባቸው ማህበረሰቦችም ዘንድ ይታያል]
.
* የዋቄፈና እምነት ከአስተዳደራዊ የአባገዳ ስርአት ጋር ታሪካዊም መንፈሳዊም ቁርኝት አለው። (ይህንን መካድ የአፄዎቹ ስርዓት ከኦርቶዶክስ ክርስትና ጋር ቁርኝት አልነበረውም ብሎ እንደመሞገት ነው)
.
* ዋቄፈናዎች ከቀብር በኋላ ስላለው ህይወት ጥርት ያለ ምልከታ የላቸውም። በዚህና በሌሎችም አንዳንድ ነጥቦች ላይ ከሌሎች ሰማያዊ ሀይማኖቶች የተኮረጁ እምነቶችን ይቀላቅላሉ።
.
.
ይህ ከላይ የሰፈረው እንግዲህ ስለዋቄፈና እምነት በወፍ-በረር ጥቆማ ይሰጣል። እምነቱ ዘልማዳዊ እንደመሆኑ ያልደረጀ እና በተከታዮቹም ዘንድ ወጥ የሆነ ምልከታ የሌለው ነው።
.
ዋቄፈና ያልተብራሩ እምነቶችን ከመያዙም ጋር ከሌሎች ሃይማኖቶች በተኮረጁ ገለፃዎችም የተጠጋገነ ነው።
.
አንድ የሚያስማማን ነገር ግን እምነቱ በመሰረቱ ከአይሁድ፣ ከክርስትናም ሆነ እስልምና የተለየ መንገድን የሚከተል ግና ከዚህም ከዚያም እየኮረጀ በሁለት እግሩ ለመቆም የሚውተረተር መሆኑ ነው።
.
.
#ዋቄፈና ሌሎች ዘንድ...
.
.
ዋቄፈናን ሰዎች እንዴት እንደሚመለከቱት ስናስተውል ሶስት አይነት ሰዎችን እናገኛለን።
.
1. የመጀመሪያዎቹ ስለ እምነቱ የማያውቁ ሰዎች ሲሆኑ እይታቸው ከቃላቱ በመነሳት በተለይም 'ዋቃ' የሚለውን በመመልከት ብቻ ይህ ቃል የአምላክ የአፋን ኦሮሞ ስም እንደሆነ የሚገምቱና ከዚህ ያለፈ ግንዛቤ የሌላቸው ናቸው።
.
2. ሁለተኛዎቹ ስለእምነቱ ጥቂትም ቢሆን ግንዛቤ ያላቸው እና እምነቱን እንደባዕድ አምልኮ የሚቆጥሩ ናቸው።
.
3. ሶስተኛዎቹ ግን ስለእምነቱ ጥልቅ ግንዛቤ ያላቸው (ምናልባትም የሚያምኑበት) ሆኖም እምነቱን ከኦሮሞ ብሄርተኝነት ጋር በማቆራኘት ለማስፋፋት የሚጥሩና ይህም እንዳይታወቅባቸው በማድበስበስ የተጠመዱ ናቸው።
[እዚህ ጋር ግን ጥልቅ እውቀት ሳይኖራቸው በወገንተኝነት ብቻ ዋቄፈናን ከፍ ከፍ ለማድረግ የሚደክሙም እንዳሉ ልብ ይሏል]
.
የሶስተኛዎቹ ሰዎች ምልከታ ምናልባትም እምነቱን ከመክሰም በመታደግና ዘመናዊ ቁመና በማልበስ ወደ ገበያ ለመመለስ የሚፍጨረጨሩ እንዳሉ ያሳያል።
.
እነዚህ ሰዎች እምነቱ በሌሎች ሀይማኖቶች ዘንድ ጥርጣሬ እንዳያስነሳ ዋቄፈናን ከየሀይማኖቱ ለማመሳሰል ወይም የቃላት ትርጉም እንጂ ልዩነት እንደሌለ ለማሳመን ሲጥሩ ይስተዋላል።
.
በሌላ በኩል ደግሞ ዋቄፈና የኦሪት መሰረት ያለውና እስልምናንም ሆነ ክርስትናን የቀደመ እምነት እንደሆነ ሲደሰኩሩ ይሰማል። አያይዘውም የራሱ መርሆ እና ቀኖና እንዳለው ይሰብካሉ።
.
በግላጭ የሚታዩ የባዕድ አምልኮ ተግባራትን በመካድም ምንም አይነት ባዕድ አምልኮ እንደሌለ እንዳውም እምነቱ አሀዳዊ እንደሆነ ለመግለፅ ይሞክራሉ።
.
.
እኛስ ...
.
.
ከላይ በሶስተኝነት የተጠቀሱት አካላት ሰሞነኛ የፓለቲካ ትኩሳትን ተጠቅመው የተዘነጋውን ዘልማዳዊ እምነት ወደ ፊት ለማምጣት እየተሯሯጡ ነው። ይህን እያዩ ማለፍ ነገ ዋጋ ሊያስከፍል ስለሚችል እንደሙስሊም የምንችለውን ማድረግ ይኖርብናል።
.
እንደሚታወቀው እኛ ሙስሊሞች ሙሉ የሆነ እና ለየትኛውም ዘመን እና ህዝብ የሚመጥን ሀይማኖት ከጌታችን ተሰጥቶናል። ይህም በቁርአንና በነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሱና በበቂ ሁኔታ ተብራርቷል። በዓሊሞቻችን ትግልም ሳይበረዝ እኛ ዘንድ ደርሷል።
.
الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا
.
"ዛሬ ሐይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ ፀጋዬንም በናንተ ላይ ፈፀምኩ፤ ከሐይማኖትም እስልምናን መረጥኩላችሁ" አል-ማኢዳ 3
.
ከዚህ ሀይማኖት ውጪ የሚሻ ወይም የሌላን አመለካከት ማስረግ የሚፈልግ ከቀጥተኛው ጎዳና እንደሚወጣና ራሱንም ለጥፋት እንደሚያጋልጥ በማስጠንቀቂያ ተናግሯል።

وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا
.
"ቀናው መንገድ ከተገለጠለት በኋላ መልእክተኛውን የሚፃረር እና ከምእመናን መንገድ ሌላን የሚከተል በተሾመበት (ጥመት ላይ) እንሾመዋለን፣ ጀሀነምም እንዶለዋለን፣ መመለሻይቱም ከፋች" አ'ኒሳዕ 115
.
ስለሆነም የህይወት መመሪያችን የሆነውን እስልምና አጥብቀን በትክክለኛው ጎዳና እንዘልቅ ዘንድ ከእንዲህ አይነት የባህል ካባ የደረቡ እምነቶች ሙሉ በሙሉ ከመዘፈቅም ሆነ ጥቂቱን ከመቀበል ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል።.
.
ከዚህም ባሻገር አላዋቂ ወንድሞቻችን ተሳስተው ወደ ጥፋት እንዳይገቡ ልንታደጋቸው ይገባል። እንዲሁም እምነቱ እንደ ክርስትናና አይሁድ እምነት እንደማይቆጠር የነርሱንም ሑክም/ብያኔ እንደማያገኝ ልብ ማለት ያስፈልጋል።
.
ነገር ግን ስለዋቄፈና ስንናገር ጉዳዩን ከብሄር ጋር በማቆራኘት ከመቃወምም ሆነ ከመከላከል ልንቆጠብ ይገባል። ሁለቱም አካሄድ የማንፈልገውን ያመጣልና።
.
በመጨረሻም ጉዳዩ የተለየ ትኩረት ተሰጥቶት ዓሊሞችና ዱዓቶች ህዝቡ በሚረዳው ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጡ ማስታወስ ያስፈልጋል።
.
.
አላህ በቀናው መንገድ ላይ ያፅናን!

የጭንቅ ጊዜ ዱአ
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የጭንቅ ጊዜ ዱኣ የሚከተለው እንደሆነ አስተምረውናል
"ላኢላሃ ኢለላሁል አዚሙል ሀሊም። ላኢላሃ ኢለላሁ ረቡል አርሺል አዚም። ላኢላሃ ኢለላሁ ረቡ ሰማዋቲ ወረቡል አርዲ ወረቡል አርሺል ከሪም።"
ይህንን ዱኣ እናብዛ። ሀገራችን ፊትና ላይ ናት።
አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ። ሰላምም ካንተ ነው። ሀገራችንን ሰላም አድርግልን።

አላህ እንዲህ ይላል
وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِنْ شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ وَلَئِنْ
كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِي لَشَدِيدٌ
ጌታችሁም «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋለሁ) ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡

SadatKemal Abu Meryem:
ኢትዮጵያ፣ የገጠር ልጅ፣ የከተማ ልጅ ዘረኝነት፣ ፖለቲከኞች፣ አንድ አምላክ አላህ።
– ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካ ውስጥ የምትገኝ ሀገር ናት፣
– በውስጧ 80 የሚጠጉ ብሄር ብሄረሰቦች አሉ፣
– ሀገሪቱ ላይ መጥፎም ጥሩም ታሪኮች አልፏል፣
መናናቅ፣ አንዱ እራሱን የበላይ ማድረጉ ሌላውን የበታች ማድረጉ ለማንም አይበጅም።
እዚህች ሀገር ላይ ያሉ ብሄር ብሄረሰቦች በንግድ፣ በጋብቻ ተሳስረዋል።
አንዱ አንዱን አልፈልግም ወይንም አይፈልጉኝም ሊል አይገባም።
ሁሉም በዚህች ሀገር ላይ የየራሱ ድርሻ አለው።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አብዛኛው ቀለባቸው ከክፍለ ሀገራት ነው የሚመጣው።
የክፍለ ሀገር ሰዎች መድሀኒቶች ሌሎች የእለት ከለት መገልገያ ቁሶች ከዋናው ከተማ ነው የሚደርሳቸው (በአውሮፕላን የሚገባው)።
ስለዚህ የአዲስ አበባ ሰው ከተማይቱ ብትሰለጥን በአስተሳሰብ ከፍ ያለ ቢመስለውና የክፍለ ሀገር ሰው በአስተሳሰቡ ደካማ ቢመስለው ከባድ ስህተትን እየፈፀመ ያለው የከተማ ሰው ነኝ ባዩ ነው።
የገጠር ቤተሰቦች መሰረተ ልማት ሳይሟላላቸው በከባድ መከራ ልጆች ያሳድጋሉ። የቋንቋ፣ የ exposure ክፍተት እና ጉድለት አለ። በዚህ ሁኔታ አንድ አንዱን መናቅ ሳይሆን መተዛዘን እና መከባበር ነው ያለብን።
ፖለቲከኞች ሆይ! ሆደ ሰፊ እና አስተዋይ ሁኑ። አንድ ሀገር ላይ የመጠፋፋት፣ የመናናቅ ፖሊሲ የትም አያደርስም።
በንግድና በጋብቻ የተሳሰረ ዜጋ አንዱ የአንዱን ቋንቋ እና ባህል እያከበረ እና ሳይንቅ ሊኖር ይገባዋል።
ሀገሪቱ ትልቅ ችግር ውስጥ ገብታለች። ይህ ችግር አንዱን ዘር ወይንም አንዱን ክልል አለየም። ሁሉም የችግሩ ተጠቂ ነው። ስለዚህ ችግሮቻችንን በጋራ ለመፍታት ሁሉም በጋራ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በመሳተፍ ሁሉን (ገጠሬውንም ከተሜውንም) ተጠቃሚ ያደረገ መፍትሄ እንድናገኝ አንድ አምላክ፣ ብቸኛው ፈጣሪ አላህን እንለምነው።
ይህች ሀገርም ይሁን ሌሎች ሀገሮች ሀይል አለን፣ ብቃት አለን ብለው ፈጣሪን በረሱ ቁጥር ለውድቀት እና ለእርስ በእርስ ችግር ይዳረጋሉ።
የፖለቲከኞችን ስም እና ገድል አላህ ለእኛ ከዋለው ውለታ እና ውዳሴ በላይ ስናወሳቸው ዝቅጠት ውስጥ እንወድቃለን።
ሃይልም ጥበብም የአላህ ነው። ሀገራችን ላይ ብዙ ጊዜ ከእናት በላይ አዛኝ የሆነው አላህ ብዙ ደም አፋሳሽ ጉዳዮችን ሲያሳልፍልን አይተናል። እኛ ግን ውለታውን ከማመስገን ይልቅ በዘፈን መደለቅ፣ መጮህ ብሎም የፖለቲካ ሰዎችን ከአላህ በላይ ማወደስ ላይ ተውጠናል።
ዘረኝነት እየተባለ አንዱ አንዱን ሲከስ ይታያል። ዘረኝነት የጥቂቶች መገለጫ አይደለም። ዘረኝነት ማለት የራስን ዘር ከፍ ማድረግና የሌላን ዘር መናቅ ነው። ይህ በሽታ ሁሉ ያለበት ዘረኛ ነው። ይህ በሽታ አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ አብዛኛው ተለክፎበታል። አንድ ሰው በራሱ ቋንቋ ስላወራ ዘረኛ አይባልም። ይህ ማንነቱ ነው። ቋንቋ መግባቢያ ነው። እንዲያውም ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ጠንካራ ሀገር ስላልሆነች እንጂ ትምህርት "በእንግሊዘኛ" የሚሰጥባት፣ እንደ ቻይና ጀርመን ያሉ ሀገራት በራሳቸው ቋንቋ ነው ዶክትሬት ድረስ የሚማሩት። የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሌላ የሀገሩን ቋንቋ ቢያውቅ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ አይሆንም። አሳዛኙ ሰዎችን በዘረኝነት የሚፈርጀውን ሰው እራሱ ሙልጭ ያለ ዘረኛ ሆኖ ታገኘዋለህ። ዘረኝነት ማለት የራስን ዘር ከፍ ማድረግ ወይንም የሌላን ዘር መናቅ ነውና ይህ በሽታ ከሌለብህ ብቻ ዘረኛ አይደለሁም በል እንጂ ከዚህ ውጭ አንተም ከምትኮንነው ነገር አልጠራህም።
ስጨርስ ኢትዮጵያዊያን ሆይ! በመከባበር፣ ባለመናናቅ የዚህችን በጣም ብዙ resource ያላት ሀገር ለማናችንም በቂ ሆና እናገኛታለን። በመናናቅ በመተቻቸት እነዚህን ሁሉ ማንም ሳይጠቀምባቸው ከስረው ይቀራሉ።
አላህ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን። መሪንም ተመሪንም ያስተካክለን። እውነተኛ መከባበር፣ መቻቻል ያለባት ሀገር ያድርግልን።

ሰላምን ምንም አይተካትም።
አላህ ሰላም ይስጠን። የአላህ ባሪያዎች ሆይ! መጥፎና አሳዛኝ ነገሮች ሀገራችን ላይ እየተከሰቱ ነው።
ታድያ ይህንን ሁሉ ነገሮች እያየን ወደ አላህ መመለስ አይሻልምን?
እኛ ወሬውን በየጓዳው ብናወራው ምንም አናመጣም። ባለስልጣናቱና የፖለቲካ አክቲቪስቶች ነገሩን ማብረድ አቅቷቸዋል።
ከአሳዛኞች ሁሉ አሳዛኙ ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን ማረጋጋት እና ሰላም ማምጣት የሚችለውን አላህ መለመን ትተን ሌላ ወሬ ውስጥ የተዘፈቁትን ማየታችን ነው።
መቼም በደለኛ በድሎ አይቀርም። ለማንም የማያዳላው አላህ፣ እውነተኛ ፍርድ ይሰጣል።
ሰዎች ሆይ! መበደል አደጋ አለው። አላህ አያያዙ የበረታ ነው። አላህ ሲታገስ የለም ማለት አይደለም።
ሙስሊሞች ሆይ! ለሰላም ዱኣ እናድርግ። ሰላም በመቃወሱ ምክንያት ታላላቅ የሆኑት አምልኮዎችን በጀመኣ መፈፀም ሁሉ አስቸጋሪ እየሆነ ነው።
አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ። ሀገራችንን ሰላም አድርግልን።

ሙስሊም አይዋሽም። ሸይኽ፣ ኡስታዝ ተብሎ ሲዋሽ ብሎም ውሸቱ የሱና ሰዎች ላይ ሲሆን የከፋ እና የከረፋ ነው። ውሸት ወደ ምን እንደሚመራ ኡስታዝ የሚባሉ ውሸታሞች ሳያውቁት ቀርተው ነው? ወይንስ ውሸት ለእነሱ የተፈቀደ ነገር ሁኖ ነው?
ሰዎች ሲዋሽባቸው ዝም ካሉ ወይ ከታገሱ ውሸታሙ እውነት ተናግሯል ማለት አይደለም። ይልቁንም ትንሽ እና ውሸታም መሆኑም እያሳየ ነው።
አላህ ከዚህ አደገኘ ወንጀል ይጠብቀን።
https://t.me/SadatTextPosts
ሰዎች ሲዋሽባቸው ዝም ካሉ ወይ ከታገሱ ውሸታሙ እውነት ተናግሯል ማለት አይደለም። ይልቁንም ትንሽ እና ውሸታም መሆኑም እያሳየ ነው።
አላህ ከዚህ አደገኘ ወንጀል ይጠብቀን።
https://t.me/SadatTextPosts
ሰሀባዎች ለድል የበቁት ተውሒድን ይዘው፣ ሺርክን ርቀው፣ ሱናን ይዘው ቢድአን ርቀው ነው።
ታቢእዮች፣ አትባኡ ታቢኢን ለድል የበቁት ተውሒድን ይዘው፣ ሺርክን ርቀው፣ ሱናን ይዘው ቢድአን ርቀው፣ የሰሀባዎችን አረዳድ ይዘው የነ ኸዋሪጅን፣ የነ ቀደርያን፣ የነ ሺአን እርጉም አረዳድ ትተው ብሎም ተዋግተው ነው።
ዛሬም ድልን የፈለገ ተውሒድን ሊይዝ፣ ሺርክን ከነባለቤቶቹ ሊርቅና ሊጠላ፣ ሱናን ሊይዝ ቢድአን ከነባለቤቶቹ ሊጠላና ሊርቅ፣ የሰሀባዎቹን እና የሰለፉነ ሷሊሂንን አረዳድ ሊይዝ እርጉም የሆኑትን የኸዋሪጅ፣ የራፊዳ ሺአ፣ የቀደሪያ፣ የሙእተዚላ፣ የማትሩድያ፣ የጀህሚያ፣ የአሽአሪያ፣ የኩላቢያ፣ የሱፊያ ከነ ጡሩቆቻቸው •••••• የአህባሽ፣ የኢኽዋን፣ የተብሊግ፣ የሂዝቢያ (የጎጠኝነት)•••• መንገዶች በጠቅላላ እርግፍ አድርገን ሊርቅ እና ሊጠላ ብሎም ህዝቡን በነሱ ወጥመድ እንዳይያዝ ሊያስጠነቅቅ ግድ ይለዋል።
የሐቅ መስመር አንድ እና አንድ ብቻ ናት። እሷም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሀባዎቻቸው የነበሩባት መንገድ ናት።

ነጃሺና ቱሪዝምን ምን አገናኛቸው?
"መውሊድ" የተባለውን ኢስላም የማያውቀው መጥፎ ሰዎች የጨመሩትን ጭማሪ "በደርግ ጊዜ እኮ ነው ከስንት በደሎች በኀላ እንደ ሀገር አቀፍ ብሄራዊ በአል እንዲከበር የተፈቀደው
•••••" የሚሉ አሉ።
አሁን ደግሞ
ነጃሺ ላይ የሚፈፀመውን ቀብር አምልኮ "የቱሪስት መስህብ" በሚል ስም ኢስላምን አፍራሽ የሆነ ተግባር የሚሰራበትን ቦታ ጉዞ እንዲደረግበት የሚቀሰቅሱ አሉ።
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከሶስት መስጂዶች ውጭ ጓዝ ጠቅልሎ ለኢባዳ ወዴትም መስጂድ መሄድ እንደማይቻል ተናግረዋል። ሶስቱ መሄድ የሚቻልባቸው መስጂዶችም መካ ላይ ያለው ሀረም፣ መዲና የሚገኘው የነብዩ መስጂድ፣ ቁድስ የሚገኘው መስጂደል አቅሳ ናቸው።
ነብዩ የከለከሉትን ክልከላ ቱሪዝም፣ ደርግ፣ ••••• ምናምን አያሉ የሚዳፈሩ እርጉም ሰዎች እንደማየት ምን የሚያሳምም ነገር አለ?
ስንቶች አሉ ገንዘባቸው፣ ዘራቸው እና ክብራቸው ሲነካ ኡ ኡ ኡ ብለው የሚጮሁ። ነገር ግን እንዲህ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ክልከላ ሲጣስ ዝም የሚሉ፣ ከዚህም አልፎ አጥፊዎች ላይ መልስ ሲሰጥ ለአጥፊዎች ጥብቅና የሚቆሙ።
ሀገራችን ላይ ነጃሺ፣ አሊ ጎንደር፣ ዳንግላ፣ ዳና፣ ጫሌ፣ ገታ፣ ቦረና፣ አብሬት፣ ቃጥባሪ፣ አናጂና ኑር ሁሴን፣ አባድር ሀረር••••• የመሳሰሉት ቦታዎች ላይ ከባባድ ከኢስላም የሚያስወጡ ሺርኮች ይፈፀማሉ።
ታድያ የአላህ መብት ሲጓደል፣ የነብዩ ትእዛዝ ሲጣስ ዝምታን የሚመርጡ ብሎም ለአጥፊዎች ጥብቅና የሚቆሙ እንዴት መብታቸው እንዲከበርላቸው ይከጅላሉ?
የአላህን ህግጋት ስንፈፅም የእኛም መብት ይሟላል።

ሙስሊም ወንዶች አላህን እንፍራ።
መቼም አላህን እንፍራ የሚያስብሉ ጉዳዮች ብዙ ቢሆኑም ለዛሬ ላስታውሳችሁ የምፈልገው ጊዜን በአግባብ በመጠቀም ላይ ነው።
መቼም ለአማኞች ከነፍሳቸው በላይ አዛኝ የሆኑት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአደም ልጅ የውመል ቂያማ ስለ አራት ነገር ሳይጠየቅ ታፋውን እንደማያንቀሳቅስ ነግረውናል። ከዛም ውስጥ ጊዜውን በምን እንዳጠፋ ይገኝበታል።
ዛሬ ዛሬ አሳዛኝ በሆነ እውነታ ኢትዮጵያ ላይ ከመግሪብ እስከ ኢሻ ያለውን ጊዜ አላህ ካዘነላቸው ውጭ ከፊሎች ያለ አግባብ ካፌዎች፣ ፑልና ከረንቡላ ቤቶች እና መጥፎ ቦታዎች ላይ ጊዜያቸውን ሲያጠፉ ይስተዋላል።
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህን እንፍራ። ከሞት በኀላ ያለው ጉዞ በጣም ስንቅ ይፈልጋል። ትንሽ ስንቅ ይዘን በራሳችን ላይ ከምንቀልድ ጊዜያችን በአግባቡ እንጠቀም።
ለዛሬ ውዱ ነብይ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) "አራህማን (አዛኙ አላህ) ዘንድ በጣም ተወዳጅ፣ ለምላስ በጣም ቀላል፣ ሚዛን ላይ በጣም ከባድ" ብለው ይህቺን ዚክር ነግረውናል
"ሱብሐነላህ ወቢሐምዲሂ፣ ሱብሐነላሂል አዚም"
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ ወንጀላችንን እና ቸልተኝነታችንን ይማረም። እሱን አብዝተው መሀርታ ከሚለምኑት፣ እሱን አብዝተው ከሚያወሱት፣ ሲሰጣቸው ከሚያመሰግኑት፣ መከራ ሲያጋጥማቸው ከሚታገሱት፣ ጊዜያቸውን በአግባብ ከሚጠቀሙት ያድርገን።

አላህ ያስረዳን።
አዛኙ አላህ እንዲህ ብሏል
هُوَ الَّذِي أَنْزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً ۖ لَكُمْ مِنْهُ شَرَابٌ وَمِنْهُ شَجَرٌ فِيهِ تُسِيمُونَ
– እርሱ (አላህ) ያ ከሰማይ (ከዳመና) ውሃን ያወረደ ነው፡፡
– ከእርሱ (ከውሃው) ለእናንተ መጠጥ አላችሁ፡፡
– ከእርሱም (እንስሳዎችን) በእርሱ የምታሰማሩበት ዛፍ (ይበቅልበታል)፡፡
يُنْبِتُ لَكُمْ بِهِ الزَّرْعَ وَالزَّيْتُونَ وَالنَّخِيلَ وَالْأَعْنَابَ وَمِنْ كُلِّ الثَّمَرَاتِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
– በእርሱ ለእናንተ አዝመራን፣
– (የዘይት) ወይራንም፣
– ዘምባባዎችንም (ተምርን)፣
– ወይኖችንም፣
– ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል፡፡
– በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡
وَسَخَّرَ لَكُمُ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ وَالنُّجُومُ مُسَخَّرَاتٌ بِأَمْرِهِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ
– ለእናንተም ሌሊትንና ቀንን፣
– ፀሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ፡፡
– ከዋክብትም በፈቃዱ የተገሩ ናቸው፡፡
– በዚህ ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምራቶች አልሉ፡፡
ልብ ብንል ብናስተውል እና ብንመለከት የአላህን ውለታዎችና ፀጋዎች ቆጥረንም አንጨርሳቸውም።
ከአላህ ውጭ በውሸት የሚመለኩት መለአክት፣ ነብያት፣ ጂኖች በጠቅላላ ፍጡሮች ከላይ ከተዘረዘሩት አንድንድም ማድረግ አይችሉም።
ተውሒድ እና ሱና ከምንም አርእስት በፊት ሲቀደሙ ኡማውን ጌታውን እና መልክተኛን በአግባቡ ማወቅ ይችላል። ይህ ከተሳካ በአላህ ፍቃድ ሁለት ሀገር ስኬት በስኬት ይኮናል።
አላህ ሆይ! አንተን በብቸኝነት ከሚያመልኩት፣ አንተንም ከሚያመሰግኑት አድርገን።

በቅዱሳኖቹ ካልተቻለ በሌሎቹ ይባስ አይቻልም።
ተውሒድን ጠንቅቆ ማወቅ በአላህ ፈቃድ ከሁለት ሀገር ክስረት ይጠብቃል።
አላህ ከእርሱ ውጭ ያሉትን ማንንም ይሁን ማን አምልኮ እንደማይገባቸው፣ ከአላህ ውጭ ላለ ማንኛውም አካል አምልኮ ቢፈፀምለት ይህ አምልኮ የታላቆች ሁሉ ታላቅ ወንጀል ሺርክ እንደሆነም ነገሮናል።
አላህ ሺርክን እየሰራ ለሞተ ሰው ዘላለም የጀሀነም እሳት ነዋሪ እንደሚያደርገው እና ጀነት በአጋሪዎች ላይ እርም መሆኗን ነግሮናል።
አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይህንን ታላቅ እውነታ በሚገባ አብራርተውታል።
እስቲ ጥቂት ምሳሌዎች
– የመላኢካዎች አለቃ ጅብሪል፣ የሰው ልጆች አለቃ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም፣ ታላቁ ኢሳ አለይሂ ሰላም፣ ጥብቋን መርየም ፍጡራን ናቸው አምልኮ በፍፁም አይገባቸውም።
እነዚህ ፃድቅ መሆናቸው አላህ ዘንድ የተመሰከረላቸው ታላላቅ ፍጡሮች ናቸው። አምልኮ የሚገባው ለብቸኛው ፈጣሪ አላህ ብቻ ነው።
ስለዚህ ይህ ማለት እነ ጅብሪልን፣ ሚካኢልን፣ መርየምን፣ ኢሳን፣ ሙሐመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ማምለክ ክልክል ከሆነ እና ተግባሩ ሺርክ ከሆነ እነ አብሬትን፣ ቃጥባሪን፣ ኑር ሁሴንን፣ ጀይላኔን፣ ከድርን፣ የቦረናውን፣ አሊ ጎንደርን፣ሰይፉ ጨንገሬን፣ አዳል ሞቴን፣ ዛፍን °°°°°° ሌሎችንም ማምለክ ይበልጥ ክልክል ይሆናል።
አላህ በእሱ ላይ አንድንም (ማንንም ምንንም) እንዳናጋራበት ነው ያዘዘው። ዛሬ ግን ካእባን መለመን ሺርክ እንደሆነው ሁሉ በሰፈሩ ወይንም በሀገሩ ላይ ያለን ዛፍ ማምለክ ሺርክ እማይመስለው እና የማያውቅ ስንት አለ።
ጠፊዋ ዱንያ ላይ ለመኖር እውቀት ካስፈለገ፣ እንዴት ነው የማይጠፋ የሆነውን አኸይር ከማወቅ እና አስፈላጊውን ዝግጅት ከማድረግ የተዘናጋነው?
አላህ ከመሀይምነት ያውጣን። ዙርያችንን ብንፈትሽ በሺርክ ተወረናል። ታላቁን አደጋ አቅፈን ስለ ሌሎች አርእስቶች ማቡካት የአደጋ ሁሉ ከባድ አደጋ ነው።
ቅድሚያ ለተውሒድ።

አልሐምዱሊላህ
ወንድም እና እህቶቼ ሆይ! ትንሽ በህክምና ጉዳይ ጠፋ ብዮ ነበር። አዛኙ አላህ ህክምናውን ሰበብ አድርጎልኝ ለውጥ አግኝቼያለሁ።
ስትጠይቁኝ፣ በዱአችሁ ስታስቡኝ የነበራችሁ ወንድም እና እህቶቼ ሆይ አላህ መልካሙን ሁሉ ይመንዳችሁ።
አላህ ሁለት ሀገር ከመከራ ይጠብቀን።
ወንድማችሁ ሳዳት ከማል አቡ መርየም።

ዘሬን ከሀይማኖቴ አላስበልጥም፣ እኩልም አላደርግም፡፡
ሙስሊሞች ሁሉ ከኔ ዘር ቢሆንም ባይሆንም ወንድሜ እና እህቴ ናቸው፡፡
ኢስላም አላህ የሚቀበለው ብቸኛው የነብያት ሁሉ ሃይማኖት ነው፡፡
ኢስላም
- ከአሳማሚው የጀሀነም እሳት ይጠብቃል፣
- ሲራጥን ያሻግራል፣
- ብቸኛው የአለም ሙስሊሞች መተሳሰሪያ ገመድ ነው፣
- ያቺን ውድ ሀገር ጀነት ያስወርሳል………፡፡
ዘር
- አንድ ሰው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘር እንኳን ቢሆን እምነቱን ካላስተካከለ ከእሳት አይጠበቅም (ምሳሌ አጎታቸው አረቡ አቡ ለሃብ)፣
- ጀነትም አያስገባም፣
- ሲራጥንም አያሻግር፣
- የሙስሊሞችን አንድነት በዘረኝነት አማካኝነት ሲበታትን በተጨባጭ ታይቷል……
ዘር ከሀይማኖት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም፡፡ የሰውን ልጅ ሰው ያደረገው ዘሩ ሳይሆን ከጌታው ጋር ያለው ግንኙነት (እምነቱ፣ እስልምናው) ነው፡፡
አላህ እሱን መፍራት እንጂ ዘርን የሰው ልጆች መበላለጫ አላደረገውም
[49:13] يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
- እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡
- እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡
- አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡
- አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡
አንድ ሰው ሰው ነኝ እስካለ ድረስ አባቱ አደም ነው፡፡ አደም ደግሞ ከአፈር ነው የተፈጠረው፡፡ ከአንድ አባት የተገኙ ልጆች ደግሞ አንዱ በአንድ ላይ የበላይ ነኝ ሊል አይገባውም፡፡ ማን ከማን በላይ ነው የሚለው መስፈርቱ ተቀምጧም
አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡
ሰው ከሃይማኖቱ በላይ ዘሩን ካስቀደመ ከባድ ክስረት ውስጥ ወድቋል፡፡
ሙስሊሞች ሁሉ ከኔ ዘር ቢሆንም ባይሆንም ወንድሜ እና እህቴ ናቸው፡፡ ከኢስላም እና ከሱና ውጭ ሰዎችን የምወድበት እና የምጠላበት መስፈርት የለኝም፡፡
የእኔ ዘር ከማንም ዘር አይበልጥም፣ ከማንም ዘርም አያንስም፡፡
አላህን እንፍራ ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም፣ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአላህ መልክተኛ ናቸው ብሎ የመሰከሩ ሰዎችን የእኛ ዘር ስላልሆኑ ብቻ ደማቸውን ከማፍሰስ፣ ገንዘባቸውን ከመዝረፍ፣ ክብራቸውን ከማጉደፍ እንጠንቀቅ እንቆጠብ፡፡ አለበዘለዚያ ዛሬ እዚህ ምድር ላይ ለሰራናት ትንሽም ትልቅም ስራ የአለማቱ ጌታ አሸናፊ አላህ ዘንድ ቀርበን ከባድ ምርመራ፣ ከዛም ቅጣት ይጠብቀናል፡፡
ሙስሊሞች ሆይ! አላህን እንፍራ የእኛ ብቸኛው መተሳሰሪያ ገመዳችን ኢስላም እና ሱና ነው፡፡ ኢስላም እና ሱናን የያዘ ወንድም እና እህታችን ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ዘረኝነትን በመካከላችን እናጥፋ ማለት አንድ ሰው ዘሩን እና ቋንቋውን ይካድ ማለት አይደለም፡፡ አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፡፡ አላህ የሰላም ባለቤት ነው፡፡ ሰላምን የፈለገ የሰላሙን ባለቤት በብቸኝነት ይለምን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡