Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
መውሊድ?

ነብዩ ከሞቱ ከ1400 አመት በላይ ተቆጥሯል፡፡
ሰው ከሞተም በኋላ የልደት በአሉ ይከበርለታልን?
እንደ ውቡ፣ ሙሉው እስልምና ከሆነ፣ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተወለዱበትን ቀን አመት ጠብቀው በህይወት በነበሩበት ጊዜ እንኳን አንድም ጊዜ የራሳቸውንም ይሁን የሌሎች ነብያት ወይንም የሌላን ግለሰብ አላከበሩም፡፡ አይደለም ሰው ሞቶ ልደቱ ሊከበር ቀርቶ፡፡
ግን አሳዛኙ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተወለዱበት ቀን በቁርጥ ባይታወቅም፣ የሞቱበት ቀን ግን አሁን ሰዎች ረቢአል አወል 12 እያሉ የሚጨፍሩበት ቀን ነው፡፡ ሰይጣን ይህን ያህን የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ዲን ነብዩን እንወዳለን በሚል ስም ሲንዱት ተግባራቸውን አሳምሮ አቀረበላቸው፡፡

አላህ በሱና ከሚብቃቁት ያድርገን፡፡ የነብዩን ሱና በቢድኣ ከመናድ ይጠብቀን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ የአላህ ባሪያዎች ሆይ!
አል-ቀዋኢዱል አርበኣ ሙሉው ደርስ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አራት ከሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ማውረድ ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/Kitaboch
ከዚሁ የተመሳሳይ ቻናል
1) አቂደቱል ዋሲጥያ ሙሉ ደርስ፣
2) ኡሱሉ ሰላሳ ሙሉ ደርስ፣
3) ኹዝ አቂደተክ እምነትህም ከቁርኣን እና ከሀዲስ ያዝ ሙሉ ደርስ፣
4) አል-ዋጂባት ሙሉ ደርስ ማግኘት ትችላላችሁ
ላልደረሳቸውም አድርሱት
ከ200 መቶ በላይ ለሚሆኑ የድምፅ ፋይሎች ከሚከተሉት የቴሌግራም ቻናል ማውረድ ትችላላችሁ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
አላህ ይቀበለን፡፡
"የአላህን ህግጋቶች ብትከተሉ አላህ ይረዳችሇል"

አላህ እና መልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እያመፁ ኢስላምን መርዳት ይቻላልን ወይንም ኢስላም እርዳታ ማግኘት ይችላልን???
======================

1) ሽርክ ፈጦ እየታየ፣
2) የሽርክ እና የጭፈራ መንዙማዎች በየመንገዱ በትልቅ ስፒከር እየተደመጡ፣
3) ቢድዓ በአይነታው ተንሰራፍቶ፣
4) የወላጆች ሃቅ ተጓድሎ
5) በስሜት እና መሃይምነት መመራት፣
6) ዲን ምን ይላል ሳይሆን ኢንተርኔት ላይ ያለን ማንነቱ የማይታወቅን ካፊር ይሁን ሙስሊም አለ ብሎ መከተል፣
7) ፊልም፣ ድራማ፣ አርት እያሉ ወንድ እና ሴት መጨባበጥ፣ የአጅነቢዮችን ምስል አላህ ቤት ላይ ለጥፎ መስጂዶችን ማቆሸሽ፣
8) ኢስላም ውሸትን ከልክሎ ሲያበቃ፣ በቻናል ላይ የሌለን የውሸት ታሪክ ድራማ ብሎ ከካፊር ተመሳስሎ ሰዎችን ከቁርዓን ማዘናጋት፣
9) ሴት ልጆች አላህ እና መልክተኛው የረገሙትን "ቅንድብ ማስቀንደብ እና መቀንደብ፣ ዊግ መቀጠል እና ማስቀጠል፣ ንቅሳት መንቀስ እና ማስነቀስ"፣ መጥፎ አለባበስ እየለበሱ፣
10) ወንዶች ኳስ፣ ጫት እያሉ ጀመዓ ሰላትን ትተው (በወንድ ላይ ግዴታ ነው ጀመአ ሰላት)፣ ጭራሽ የማይሰግድም ብዙ አለ፣
11) ነጋዴዎች ዘካን በስነስርአት ሳያወጡ፣
12) ዝሙት ተንሰራፍቶ፣ ኒካህ ላይ የጣጣ መዓት ተደርድሮበት፣
እና የመሳሰሉት ሁሉ ችግሮች እያሉ ከፈተና መውጣት ይቻላል???

በፍፁም፣ አይታሰብም ጭራሽ ፈተናው ቢብስ እንጂ።

የሀዲስ ሊቅ የሆኑት ሸይቭ አልባኒ (ረሂመሁላህ) "ኢንተንሱሩላህ የንሱርኩም" የሚለውን አንቀፅ ሲያብራሩ "የአላህን ህግጋቶች ብትከተሉ አላህ ይረዳችሇል" ብለዋል።

እስቲ ግዜ ሳንሰጥ ዛሬውን በጣም አሳሳቢ የሆነውን አገራችን ላይ የተስፋፋውን እና የተንሰራፋውን ሽርክ ከምንም ነገር በማስቀደም አስከፊነቱን እራሳችን አውቀን፣ ለማህበረሰቡ አዝነን ማስተማር እንጀምር።

አላህ በጣም አዛኝ ነው ባርያዎቹ እሱን ብቻ አምልከው 2 አገር ነጃ እንዲወጡ ነብያትን ላከ፣ መፀሃፍትን አወረደ፣ በዋነኝነት የእዝነት መገለጫ የሆነውን የሰው ልጆችን ከጨለማ የሚያወጣውን ተውሂድ አስቀደሙ መልክተኞች ሁሉ።

ታድያ መልክተኞች የሄዱበትን ተቃርኖ የሚሄድ እውነት ለማህበረሰቡ ያዝናል??? በፍፁም።

የተውሂድ እና ሱና ትልቅነት፣ የሽርክ እና ቢድአ አስከፊነት አውቀን እናሳውቅ። በነዚህ ጉዳዮች ላይ ቸልተኛ የሆነ ሰው፣ የለፋውን ቢለፋ ጠብም አይልለትን።

ከምንም በፊት ቅድሚያ ለተውሂድ እና ሱና።

አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንከተለውም አድርገን፣ ባጢልን በባጢልበቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን።
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በሰሃባዎቻቸው፣ ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።
https://t.me/SadatTextPosts
ያለ ማስረጃ የሚነገረንን ሁሉ አሜን ብለን ብንቀበል ኖሮ ዲናችንን አፍርሰን ነበር፡፡
አንዳንድ ሰዎች “አሊም፣ ሙፍቲ” ናቸው እየተባለ የሚከተለውን አይነት ማስረጃ ሰንሰለት የሌለው ንግግር፣ ተሰምቶ የማያውቅ ወደ ኢስላም አስጠግተው ቢድኣ የሆነውን መውሊድ የዲን አካል አድርገው ሊያቀርቡልን አህባሾች ሬድዬ ላይ ቀርበው ነበር
“…እንዲሁም ከሰሃባዎች ውስጥ ከቶም አንዱ ሰሃባ ዝግጅት አዘጋጅቶ እንዲሁ ደግሶ ለነብያችን መላክ መወለድ ደስታ ዝግጅት አድርጎ ሰብስቦ አብልቷል….”

ታድያ ይህንን ከላይ ያለውን ንግግር የሚናገርን እና በኢስላም የሌለን ነገር ሊደነግግ የሚሞክርን ሰው “ሙፍቲ” ቢባል እንኳን ልንቀበለው ነው ወይ?
እነዛ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ከነፍሳቸው በላይ ይወዱ የነበሩ ሰሃባዎች ይህንን ተግባር (መውሊድን) አያውቁትም፡፡ እነሱ ላይ መዋሸት ደግሞ በአደራ ያስተላላፉልንን ንፁህ ዲን እንደመናድ ነው የሚቆጠረው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ለሙስሊሙ ብሎም ለሀገራችን ያሰበ “ጫት ሸርጡ ተጠብቆ ስላልተቃመ እንጂ መሻኢሆቻችን ጫት ቅመው ዝናብ ያዘንቡ ነበር” እያለ ባልዋሸና ባልሰበከ ነበር፡፡
የሚያሳዝነው እንዲህ አይነቱ ሀይማኖት እና ሀገር አፍራሽ ግለሰብ የሀይማኖት ሰው ተደርጎ መወሰዱ ነው፡፡
ጫት ሙስሊሙን ያሽመደመደ፣ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ያስቀረ አደገኘ መርዘኛ አደንዛዥ ቅጠል ነው፡፡
አላህ ለሙስሊሙም ለሀገርም የሚጨነቁ እውነተኛ የሀይማኖት አባቶች ይለግሰን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ከ 7 ሰማይ በላይ…..
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ማንኛውንም ስራ ስንሰራ ከ7 ሰማያት በላይ ያለውን ሁሉን አዋቂ፣ ተመልካች፣ ሰሚ አላህ አስበን፣ ፈርተን እንስራ፡፡
ምክንያቱም የሰራናት ስራ እሱ ዘንድ ተቀባይነት ካለት የእድለኞች ሁሉ እድለኞች እንሆናለን፡፡ እሱ ከተቆጣብንም የከሳሪዎች ሁሉ ከሳሪ እንሆናለን፡፡
ስለዚህ ለአላህ ብቻ አጥርተን እንስራ፡፡ ወንጀል ስንሰራ ወዲያውኑ በንሰሀ ወደ እሱ እንመለስ፡፡
የምንናገረው እና የምንሰራው መልካም መሆኑን እናረጋግጥ አላህ ዘንድ ይደርስልን ዘንድ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል

إِلَيْهِ يَصْعَدُ ٱلْكَلِمُ ٱلطَّيِّبُ وَٱلْعَمَلُ ٱلصَّٰلِحُ يَرْفَعُهُۥ ۚ
መልካም ንግግር ወደርሱ (ወደ አላህ) ይወጣል፡፡ በጎ ሥራም ከፍ ያደርገዋል፡፡
[ 35:10]
አላህ ለእርሱ ብቻ ስራቸውን ከሚያጠሩት፣ እሱን ብቻ ከሚፈሩት፣ ሲሳሳቱ ወደ እሱ ከሚመለሱት ባሪያዎች ያድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የሐጅ ጉዟችሁ በመጅሊስ በኩል ያልሆናችሁ ሰዎች አደራችሁን በሚናም ሆነ በዐረፋ የመጅሊሱን ድንኳን (ኸይማ) እንዳትጠቀሙ። በመጅሊስ በኩል ገንዘባቸውን ከስክሰው የሄዱ ወገኖች ድንኳን እየሞላባቸው በዚያ ከባድ ፀሐይ እየተለበለቡ፣ ለድንኳኑ ያልከፈላችሁ ሰዎች ድንኳኑን በማጨናነቅ የሌሎችን ሐቅ ልትጋፉ አይገባም። ይሄ ቀላል ጥፋት አይደለም። ሴቶችና አቅመ ደካሞች ድንኳኑ ዘንድ ለመድረስ ጊዜ ይፈጅባቸዋል። እንዳቅማቸው ተጉዘው እቦታው ሲደርሱ በወጣቶች፣ በተለይም ሳዑዲ ኗሪ በሆኑት ተስሪሕ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ወንድሞች ድንኳኑ ሞልቶ ይጠብቃቸዋል። በዚህም ሳቢያ ለዚያ ፈፅሞ ለማያውቁት ከባድ የፀሐይ ቃጠሎ (በተለይም ዐረፋ ላይ) ይጋለጣሉ። መቋቋም አቅቷቸው ነስር በነስር የሚሆኑ አሉ። በርግጠኝነት እነዚያ ያለ ሐቃቸው ቀድመው ኸይማውን የሚሞሉ ወጣቶች ይህን የደካሞችን እንግልት ከውጭ ሆነው ቢያዩ በጥፋታቸው ይሸማቀቃሉ። ይህ እንዳይሆን ዘንድ ያልከፈልንበትን አገልግሎት ለማግኘት ከመጋፋት ልንቆጠብ ይገባል። ደካሞችን ከተጨማሪ እንግልት፣ ሌሎቹን ደግሞ የሰው ሐቅ ከመጋፋት ለማትረፍ ሰበብ እንሆን ዘንድ መልእክቱን በማሰራጨት ተባበሩኝ። (ወንድማችሁ ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 24/ 2010)
አቂዳ አንድ ያላደረገውን የበሬ አጥንት አንድ አያደርገውም፡፡
**********************************
በአቂዳ (በእምነት) እና በሱና አንድ ሳይሆኑ እጅ ለእጅ ተያይዞ ፎቶ በመነሳት፣ በሬ አርዶ ስጋ በመብላት አንድ መሆን አይቻልም፡፡
እምነት ያልሰበሰበውን አጥንት መጋጥ እና እጅ ለእጅ ተያይዞ ፎቶ መነሳት አንድ አያደርገውም፡፡
ፎቶ መነሳቱ፣ ሆቴል ተከራይቶ መደስኮሩ፣ እጅ ለእጅ ተያይዞ አንድ ነን ማለቱ አንድ ቢያደርግ ኖሮ ስንት የፖለቲካ ፓርቲዎችን አንድ ባደረገ ነበር፡፡
እባካችሁ የአላህና መልክተኛውን አማና አትብሉ፡፡ ነፍሳችሁን እንጂ ማንንም አታታሉም፡፡
አቂዳ አንድ ያላደረገውን የበሬ አጥንት አንድ አያደርገውም፡፡ ቅድሚያ ለእውነተኛ አንድነት፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አላህ ሲያዝንልን እንወቅበት፡፡
ዙል-ሒጃ አስር ቀናትን ይመስል አዛኙ ለእኛ ሊያዝን ትንሹን ስራ ትልቅ አድርጎ ሊቀበለን፣ ወንጀላችንን ሊምረን በነዚህ እና በመሳሰሉት ቀናት ተጠቀሙባቸው ብሎ ቻንስ ሲሰጠን እንወቅባቸው፣ በአግባቡ እንጠቀምባቸው፡፡
መልካም ስራዎች ብዙ ናቸው፡፡ መፆም፣ ቁርኣን መቅራት፣ ሰደቃ መስጠት፣ አላህን ማውሳት እና ማወደስ፣ ዘመድ መጠየቅ……..
አላህ ወንጀላቸውን ከሚማሩ፣ ስራቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎ ከሚቀበላቸው ያድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አናሳ ብሄር፣ ትልቅ ብሄር አይባልም፡፡ ሰውን ትልቅ እና ትንሽ ያደረገው ከጌታው ጋር ያለው መልካም እና መጥፎ ግንኙነት ብቻ ነው፡፡ የትኛውም ዘር ከየትኛውም ዘር አይበልጥም አያንስምም፡፡ አናሳ እና ትልቅ ብሎ ብሄርን መከፋፈል አደለም ተምረናል ከሚሉና አልተማሩም ከሚባሉትም አይጠበቅም፡፡
የሁሉ ፈጣሪ አንድ አምላክ አላህ እንዲህ ይላል
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡
አላህ እሱን ከሚፈሩት ያድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ለአረፋ ቤተሰብ ዚያራ ለምትሄዱ
የሚከተሉትን ሶስት የተውሒድ ፓምፍሌቶች ከሚከተሉት ሊንኮች ብትወስዱ ወሳኝ መልክት አላቸው፡፡

1) አቂዳን ለሙስሊም ልጆች ማስተማር
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/1463
2) ወሳኝና አንገብጋቢ ነጥቦች በጥያቄና መልስ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/1465
3) የእምነት መሰረቶችን ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ ማስገንዘብ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/1467
ሌሎች ከ200 በላይ ሙሃደራ እና ደርሶችን በድምፅ ለማረድ የሚከተለውን ሊንክ ተጠቀሙ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
ሐጅ ላይ ላልሆናችሁ የአላህ ባሪያዎች
ሰኞ ዙል-ሂጃ 9 መፆም እንዳንረሳ፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ያለፈውን አመት እና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል” ብለዋል፡፡ ኢማሙ ሙስሊም 1162 ዘግበውታል
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ ለእኛ ለማዘን ብዙ ሰበቦችን አስቀምጦልናል፡፡ እኛም እንወቅበት፡፡ ሰኞ 9ኛው የዙል ሒጃ ቀንን በመፆም በአላህ ፍቃድ የሁለት አመት ወንጀላችንን እናስምር፡፡ ላልሰሙ ሙስሊሞች ሁሉ አድርሱት፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ወደ መልካም ያመላከተ እራሱ እንደሰራው ነው” ብለዋል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ቢላዋን በደንብ መሳል
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ስታርዱ አስተራረዳችሁን አሳምሩ፣ አንዳችሁ ቢላዋውን በድንብ ይሳል፣ የሚታረደውን ይገላግለው፡፡” ሙስሊም ዘግበውታል
https://t.me/SadatTextPosts
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
ተውሒድ
ተቀባይነት ያለው ዱኣ፣ ከዱኣ ሁሉ በላጭ ….

- የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ከዱኣ ሁሉ በላጭ የአረፋ ቀን ዱኣ ነው፡፡ ከምላቸው (ዱኣዎች ውስጥ) ምርጡ ዱኣ እኔና ከእኔ በፊት የነበሩ ነብዩች ያሉት [ላ ኢላሃ ኢለላህ ዋህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሀምድ ወሁወ ኣላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር] (ትርጉሙም ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ የለም፡፡ በብቸኝነት፣ ለእርሱም አጋር የለውም፣ ንግስና በጠቅላላ የእሱ ነው፣ ምስጋናም በጠቅላላ የእሱ ነው፣ እሱም ሁሉን ነገር በማድረግ ላይ ቻይ ነው፡፡”
የምንወስዳቸው ቁምነገሮች
- የዛሬው ቀን ወሳኝ የዱኣ ቀን እንደሆነ፡፡ ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ከዱኣ ሁሉ በላጭ የአረፋ ቀን ዱኣ ነው” ብለዋልና፡፡
- የተውሒድ ቃል “ላ ኢላሃ ኢለላህ ዋህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሀምድ ወሁወ ኣላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር” የነብዩ ሙሐመድም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሆነ የሌሎች ነብያት የሚጋሩት እና የተላኩበት መልክት እንደሆነ፡፡
- የሰው ልጅ ከእሳት ተጠብቆ ጀነት የሚገባው ይህችን ውድ የተውሒድ ቃል ሳያፈርሳት በውስጡ አምኖባት፣ በምላሱ እየተናገረ፣ በሰውነቱ ሲሰራባት ነው፡፡ ይህን ማድረግ ከቻለ አላህ በእዝነቱ ታላቁን ሽልማት ጀነት ይለግሰዋል፡፡ ከታላቁ ቅጣት ጀሀነም ይጠብቀዋል፡፡
- በዚህ ቀን ይህን ዱኣ ማብዛት፡፡ በነገራችን ላይ በሌላ ዘገባ በቀን 100“ላ ኢላሃ ኢለላህ ዋህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሀምድ ወሁወ ኣላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር” ያለ ሰው የቀኑ ኸይር ሰራተኛ ነው ከእሱ በላይ ያለ ሲቀር ብለው አዛኙ ነብይ ነግረውናል፡፡
- ዱኣ በሁለት ይከፈላል
o የጥየቃ ዱኣ፡- አላህ ሆይ! ጤና ስጠኝ፡፡ አላህ ሆይ! ልጅ ስጠኝ፡፡ አላህ ሆይ! ሚስት ስጠኝ፡፡
o የአምልኮ ዱኣ፡- አላህን ማምለክ በጠቅላላ እዚህ ውስጥ ይገባል፡፡ ለምሳሌ የአምልኮዎች ሁሉ ታላቁ አምልኮ የሆነውን ከላይ የተጠቀሰውን የተውሒድ ቃል አምኖበት ላለው ሰው ከዱኣ ሁሉ በላጭ የአረፋ ቀን የሚደረግ ነው፡፡ እኔም ከእኔ በፊት የነበሩ ነብያት ያሉት ሲሉ አዛኙ ነብይ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ነግረውናል፡፡ ከአላህ ጋር ያለን እውነተኛ የአምልኮ ትስስር ተውሒድ ሲያምር በተውሒድ ሰበብ ከጠፊዋ ዱንያ በላይ ያሉትን የእሱን ፊት ማየት፣ ጀነትን እና ፀጋዎቿን ይለግሰናል፡፡
አላህ በተውሒድ ኖረው በዛው መንገድ ላይ ከሚሞቱት ያድርገን፡፡ እኛንም ዝርያዎቻችንንም ከሺርክ ይጠብቀን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በሙሐመድ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተሉ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts