Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም፡፡
*************************************
ምስጋና ለአላህ ነው፤ ሁለት የመደሰቻ በአላትን የደነገገ፡፡ አሁንም ምስጋና ይገባው ይህንን ሸሪዓ ከመበረዝ እጠብቀዋለሁ ብሎ ቃል የገባው አላህ፤ የሃይማኖት ድንጋጊን ሁላ ለራሱ ብቻ ያደረገ፤ በዚህም ላይ ታላቅ ጥበቡን ያሳየ፡፡ እንደሌሎቸ ሀይማኖቶች፤ ቀሳውስት እንደበረዙት (እንደጨመሩበት እና እንደቀነሱበት) እንዳይሆን በግልፅ ሸሪዓዊ ድንጋጌን ለራሱ ብቸኛ አውጪ ያደረገ፡፡
ሱና ፆም ፆመን ዝም ብሎ ማለፍ እንጂ ከአላህ የተደነገገ በዓል የለም፡፡ ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር ከነብያችንም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፤ ከሰሃባዎቻቸው (ሪድዋኑላሂ አለይሂም)፤ ከ3 ምርጥ ትውልድ፤ ከ4 አኢማዎች አላገኘንም፡፡ ታድያ ለምንድን ነው እኛ ያልታዘዝነውን የምንሰራው???
ሰኞ እና ሀሙስ ፆመን ምንም በአል ከሌለ፤ 13፣14፣15 ፆመን ምንም በአል ከሌለ፤ የሸዋል 6 ከየት መጣ??? አላህን እንፍራ፡፡
አንዳንድ ቦታ ያውም ከዋናው ኢድ በላይ ይህን ቀን ያከብሩታል፡፡
እወቅ የአላህ ባሪያ ከሽርክ ቀጥሎ ሸይጧን ዘንድ የተወደደው ወንጀል ቢድዓ ነው፡፡ ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ ለእሳት ነው፡፡
አላህ በደነገገልን 2 ኢዶች፤ ከዛ በጁምዓ ብቻ እንብቃቃ፡፡ ሁሉ ነገር የሌለው ይቀላውጣል፡፡ አላህ ግን ይህን ዲን ሞልቶታል፤ ታድያ እንደ አህለል ኪታብ መጨማመሩ ምን አስፈለገ፤ የአላህን ቁጣ ለመውረስ ካልሆነ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም፡፡ ተጠንቀቁ አስጠንቅቁ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት እና ሩሱሎች ኢማም ላይ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አመቱን ሙሉ እንደፆመ መሆኑ አይፈልጉምን?
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
“ረመዳንን የፆመ ከዛም ከሸዋል (ወር) ስድስት ቀናትን (በመፆም) ያስከተለ፣ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ነው::”
ይህን በፍላጎት የሚፆም ፆም እንፁም እና ከምንዳው እንካፈል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የአላህ ችሮታ
በእስልምና አንድ አመት 12 ወራቶች አሉት፡፡
ረመዳን እንደ 10 ወር ሲቆጠር፣ ስድስቱ የሸዋል ቀኖች እንደ ሁለት ወር ይቆጠራሉ፡፡
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
“ረመዳንን የፆመ ከዛም ከሸዋል (ወር) ስድስት ቀናትን (በመፆም) ያስከተለ፣ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ነው::”
ምክንያቱም ቸሩ አላህ መልካም ስራን በአስር አባዝቶ ስለሚቀበል፡፡
የሚገርመው መሃሪው አላህ ረመዳንን በሁለት ረመዳኖች ውስጥ የተሰራውን ወንጀል ማስማሪያ ሰበብ አድርጎታል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ሸይኽ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ
“(ረመዳን) ወሩ በማለቁ አንደሰትም፡፡ ነገር ግን የምንደሰተው ወሩን አላህን በመገዛት ስለጨረስን ነው፡፡”
አላህ የነብያት ወራሾች የሆኑትን አዋቂዎች ይጠብቅልን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሁል አእማል
ሲሉ ሰምታ ዶሮ ታንቃ ሞተች!!

ኮሚቴ ተብየው የሆነ ሆቴል ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ ተብሎ ፎቶም ተለቋል፡፡ የሚገርመው ሀገራችን ብዙ ቦታዎች ላይ በአላህ ላይ ሲጋራ፣ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ሲወድም እና ቢድኣ ሲስፋፋ፣ ዘረኝነት ኡመተል ኢስላምን ጎራ ይዞ ገዳይ “አላሁ አክበር” ተገዳይ “ላኢላሃ ኢለላህ” እያለ ሲጫረስ፣ ጫት ሙስሊሙን እና ትውልዱን ብሎም ሀገር ሲያወድም ዝም ያሉት ኮሚቴዎች ዛሬ የመጅሊስ ስልጣን እና ሌሎች ሀገሪቱ ላይ ያሉ የስልጣን ወንበሮች ላይ ጉብ ለማለት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡
እኛ ፖለቲካ ውስጥ ለምን ገቡ አንልም። ኢስላምን መንጠላጠያ መሰላል ሲያደርጉት ግን ያመናል።
የእውነት የሙስሊሙ ጉዳይ የሚያስጨንቃቸው ከሆነ ግን
- ሀገራችን ላይ በሁሉም አቅጣጫ አዲስ አበባን ጨምሮ የሚሰራውን ከአላህ ውጭ አምልኮ ወገባቸውን ታጥቀው ሊዋጉት ይገባል፣
- መውሊድ እየተባለ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና የሚናድበትን፣ በነብዩ ውዴታ ስም የአላህ መብት ተቆርሶ ለነብዩ የሚሰጥበትን፣ ሸሆች የሚመለኩበትን፣ የሙስሊሙ ገንዘብ የሚበዘበዝበትን፣ ይህ አደንዛዥ ቅጠቅ የሚታኘክበትን በግልፅ እንዲህ መግለጫ እየሰጡ በአደባባይ በኢስላም የሌለ መሆኑን መናገርና ሲሰራም መቃወም አለባቸው፡፡ እነሱ እስከዛሬ ሲናገሩ የሰማናቸው “መውሊድ አይለያየንም፣ አይከፋፍለንም” ነው። ከዚህም አልፎ የነሱ አስተማሪ ሀሰን ታጁ “መውሊድ” የሚባል መፀሀፍ ፅፎ ኡማውን ወደ እሳት መርቷል፡፡ እነሱ ግን ከሱ ጋር እጅና ጓንት ናቸው።
- ሙስሊሙን ሲቀጥል ሀገራችንን እያወደመ ያለውን ጫት “ቀንሱ” እያል ማሽሞንሞን ሳይሆን ለሙስሊሙና ለሀገር ከታሰበ በግልፅ በየመስጂዱ ትምህርት ሊሰጥበት እናንተም በዚህ ጉዳይ ከመግለጫው በፊት ቢዚ ልትሆኑ ይገባ ነበር፡፡ አሳዛኙ ግን እናንተ አንድ ነን ከምትሏቸው ውስጥ ሙፍቲ የሚባለው “ጫት መስፈርቱ ተጠብቆ ስላማይቃም እንጂ ኡለማዎቻችን ጫት ቅመው ዝናብ ያዘንቡ ነበር” እያለ መስጂድ ውስጥ በማይክሮፎን መለፈፉ ነው፡፡ እስኪ ከናንየ ውስጥ ማነው ይህን ጥፋት መጋፈጥ የሚችል ጀግና?
ገርሞ ከሚገርመኝ “አኽላቃችሁ” ውስጥ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ከትክክለኛው ተውሒድ ወደ ክህደት በመንዙማ ስንኛቸው የሚመሩትን የመንዙማ ጨፋሪዎች አይደለም ልትቆጧቸው፣ አይደለም ሙስሊሙ እንዲጠነቀቃቸው ልታደርጉ ቀርቶ “ቲቢ አፍሪካ” ላይ ማቅረባችሁ ነው፡፡ የኢድ እንግዳችን የሚል ስምም ትሰጧቸዋላችሁ፡፡ እንደው ያ አያያዙ የበረታውን አላህ አትፈሩትም፡፡ እስከመቼ ሸውዳችሁ ትኖራላችሁ?
እስቲ ሌሎች ፖለቲከኞችስ ስራቸው ሌላ ነው፡፡ እናንተ በየመስጂዱ የሙስሊሙ ጉዳይ ይመለከተናል የምትሉ ሰዎች ሙስሊሞችን የሚገድላቸው እና የሚያጋድላቸው ጉዳይ ከምንም በላይ እስቲ ስሩበት፡፡ እኛ ሙስሊሞች ከኢኮኖሚም፣ ከማህበራዊም ችግራችን በላይ አብዛኛው ህዝቡ በሺርክ፣ በቢድኣ፣ በዘረኝነት፣ በጫት በመጥፎ ህይወት ውስጥ እየዋዠቀ ነው፡፡
ይህን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ የመጅሊስን ስልጣን መቆናጠጥም ይሁን፣ የፓርላማ ወንበርን መያዝ አይጠይቅም፡፡ ዳእዋን አርአያችን፣ አስተማሪያችን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቅድሚያ እምነትን የማስተካከል ተውሒድን የማስቀደም ስራ እንደሰሩት መስራት ነው፡፡ ያኔ ለውጥ ይመጣል፡፡
እስቲ ቃሉን የማያፈርሰው ጌታችን አላህ ምን እንዳለ ልብ እንበል
[Q 24:55] وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمْ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَيَسْتَخْلِفَنَّهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ كَمَا ٱسْتَخْلَفَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَلَيُمَكِّنَنَّ لَهُمْ دِينَهُمُ ٱلَّذِى ٱرْتَضَىٰ لَهُمْ وَلَيُبَدِّلَنَّهُم مِّنۢ بَعْدِ خَوْفِهِمْ أَمْنًا ۚ يَعْبُدُونَنِى لَا يُشْرِكُونَ بِى شَيْـًٔا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ
አላህ እነዚያን ከእናንተ ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን እነዚያን ከእነሱ በፊት የነበሩትን እንደተካ በምድር ለይ በእርግጥ ሊተካቸው፣ ለእነሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፣ ከፍርሃታቸውም በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል፡፡ በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ይግገዙኛል፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡
መልካም የተባሉ ነገሮችን ለማግኘት፣ የሙስሊሙን ችግር ለመቅረፍ፣ ይሄው አላህ እንዳለው “በእኔ ምንንም የማያጋሩ ሆነው ይግገዙኛል፡፡” እውነታው ግን የተገላቢጦሽ ነው፡፡
እናንተ አንድነት የመሰረታችሁት በአላህ ላይ ከሚያጋሩት፣ የነብዩን ሱና በቢድኣ ከሚያበላሹት ሰዎች ጋር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሆይ! ጉዳያችሁ ይመለከተኛል ያለ ሁሉ የናንተ ጉዳይ የእውነት ያስጨንቀዋል ማለት አይደለም፡፡ ሁሉን ነገር በኢስላም ሚዛን እንመዝነው፡፡
አላህ ሆይ! ሐቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡

https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from ABU MUSLIM A-DUROOS
*"የኔ ግጥም ጭንቅላት ነው የሚመታው!!"*

የሆነ ጊዜ አንድ ልጅ ግጥም እገጥማለሁ ብሎ ተነሳ። ግጥሞቹ ግን የመጀመሪያው ስንኝ ከሁለተኛው ጋር አይተዋወቁም። ይህን ያዩ ሰዎች "ያባትህ ግጥም ቤት ይመታል። ያንተ ግን አይመታምሳ?" ሲሉት ምን ቢላቸው ጥሩ ነው?
"የኔ ጭንቅላት ነው የሚመታው!!" አለ። አይ ቢጠግብ! ለካስ ቤት መምታት ምን እንደሆነ አልገባውም።
።።።።
አሁን ይህን ያስታወሰኝ የያሲን ኑሩ ግጥም ነው። ይሄውና እንዲህ ሲል ቅኔውን ዘርፎታል:–
――――
"ደመቀ " አሉኝ ሰማይ
"ለማ" አሉኝ ምድሩ
·
·
"ገዱ" እንዲቀናነ እነዲያምር ነገሩ
እንዲህ መደመር ነው "አብይ" ሚስጥሩ
____________
ከዚያም ከስር እንዲህ ተብሎበታል:–
"ገጣሚ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ"
――――――――――
ቆማጣ ቤት አንድ ጣት ብርቅ ነው!! እነ እንቶኔ ቤት ሁለት ስንኝ የገጠመ ሰው – ያውም በዚህ መልኩ ― "ገጣሚ" የሚል ማእረግ ያሸልማል። ትንሽ ቢቀጥል ሎሬት ይሉት ይሆናል። ስለ ትራፕ ሲያወራ "የፖለቲካ ተንታኝ"፣ ትንሽ ታሪክ ሲደሰኮር የታሪክ ምሁር፣…። የስም ግንባታ ገበያው የጦፈ ነው።
ይህስ ይሁን። ግጥሙ ውስጥ ይህን ስንኝ አይታችሁታል?
―――
"ገዱ" እንዲቀናነ እነዲያምር ነገሩ
――――
ሰምና ወርቅ መሆኑ ነው። ወርቁ ገዱ አንዳርጋቸው መሆኑ ነው።
ሰሙስ?? ሰሙማ ግልፅ ነው!! "ገጣሚው" ገድ እንዲቀናቸው፣ ጥሩ እንዲገጥማቸው እየተመኘ ነው። "ገጣሚው" በኢስላም ይሄ የገድ እምነት (ጢየራ) ከሺርክ እንደሚመደብ አልተረዳም። ይሄ ነው እንግዲህ ስለተውሒድ መፅሀፍ የፃፈው። "የሌለው አይሰጥም" ይላሉ ዐረቦች። የራሱን የተውሒድ ግንዛቤ ሳያስተካክል የህዝብ ዐቂዳ ሊያርም ይነሳል።
ኢብኑ ሙነወር

📌 *ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ*

🌐 t.me/AbumuslimAlarsi
Forwarded from ABU MUSLIM A-DUROOS
🖋 *ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁሏህ*

ከሰልፉ ላይ መገኘት ዋጂብ (ግዴታ) ነው እያሉ የሚቀሰቅሱ ሰዎች እንዳሉ ሰማሁ። ስለዚህ ሰልፉ ላይ ያልተገኘ ሰው ወንጀለኛ ነው ማለት ነው። ሰልፉ ላይ በሆነ አደጋ የሞተ ሰው ደግሞ ሸሂድ ነው እንደሚሉ ይጠበቃል፣ ልክ ሸይኻቸው አልቀርዷዊ እንዳለው። እበት ትል ይወልዳል ይሏል እንዲህ ነው!!!

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ

🌐 t.me/AbumuslimAlarsi
"ሰላማዊ ሰልፍ"
ሰላማዊ ሰልፍ የሚባለው ቃል ሰላማዊ ላለመሆኑ የሰው ህይወት እንደሚጠፋበት፣ ሰዎች እንደሚገረፉበት፣ እንደሚታሰሩበት፣ ክብራቸው እንደሚጎድፍ፣ አላህ የከለከለው ሴት እና ወንድ እንደሚቀላቀሉበት የእውቀት ባለቤቶች ነግረውን ነበር።
አብዛኛው ሰው አልሰማ በማለት ነፍሱን ሲያመልክ፣ ስሜት አምላኪዎችን ሲከተል፣ ይሀው በተጨባጭ የተመከረውን እያገኘው ነው።
እስቲ ሀገራችን ላይ አሁን ያለውን የፖለቲካ ውጥረት ያየ፣ ለሙስሊሞች የእውነት ያሰበ እንዲህ አይነት የእልቂት ሰልፎችን ሙስሊሙ እንዲወጣ "ዋጂብ (ግዴታ)" ነው እያለ ይቀሰቀሳል?
ለነገሩ የእሱ ሚስት እና የእሱ ልጆች አይደል አደጋ ሲደርስም የሚደርስባቸው።
አረ ሙስሊሞች ሆይ! አላህ እንፍራ።
ቆይ የዛሬው አሳዛኝ አደጋ አሁን ከደረሰው በላይ በሺዎች ቢሞቱበትና ነገ አላህ ፊት ምን ስትሰሩ ሞታችሁ? ተብሎ ቢጠየቅ መልሳችን ምን ይሆናል።
መሪ መልካም ሲሆን እኮ አላህ ነው የሚመሰገነው። አደባባይ ላይ ተወጥቶ ዘፈን እየተዘፈነ፣ ሴት እና ወንድ ተደባልቃችሁ አመስግኑ የሚል ነገር ሙሉ የሆነው እስልምና ውስጥ እናገኛለንን?
በፍፁም። እባካችሁ አላህን እንፍራ።
እንዲህ አይነት ቦታ ሄዳችሁ እራሳችሁ ለአደጋ የምትማግዱ ሰዎች አላህ ለምን እንደፈጠረን፣ እናት ዘጠኝ ወር በሆዷ እንደተሸከመችን፣ ቤተሰቦች ስንት ለፍተው እንዳሳደጉን እንወቅ።
ጨርሻለሁ። እንደተለመደው ነፍሴንም እናንተንም እመክራለሁ። ከፊሎች እንደምትሳደቡም አውቃለሁ።
አላህ ልብ ይስጠን። በነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዲን ከሚመከሩት ያድርገን።
የአላህ ሰላትና ሰላም በሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።
https://t.me/SadatTextPosts
ማን ነው ‹‹ሸሂድ (ሰመዓት)፣RIP (Rest in Peace)›› የሚባለው?
አንዳንድ ወንድምና እህቶች በአላህና በመልክተኛው መታመን ባለበት ሁሉ የማያምኑ ካፊሮችን ‹‹ሸሂድ (ሰመዓት)፣ RIP (Rest in Peace)›› ብለው ሲፅፉና ሲናገሩ ይሰማል፡፡ ይሄ ከባድ ስህተት ነው፣ እርምት ይሻል፡፡
አደለም በአላህ፣ በመልክተኛው መታመን ባለበት ሁሉ ያላመነን ካፊር፣ ሙስሊም የሆነን ሰው እንኳን አላህና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከመሰከሩለት ሰው ውጭ እኛ ከመሬት ተነስተን ‹‹ሸሂድ (ሰመዓት)›› አንለውም፡፡
ኢማም አል-ቡኻሪ በሰሂሀል-ቡኻሪ ‹‹እገሌ (እንትና) ሸሂድ (ሰመዓት) አይባልም›› ብለው አርስት አዘጋጅተው የሚከተለውን ሀዲስ ዘግበውልናል
ሰህል ኢብን ሰዓድ አሳኢድይ (ረድየላሁ አንህ) ‹‹የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እና ሙሽሪኮች ፊት ለፊት ጦር ተጋጥመው ነበር፡፡ የአላህ መልክተኛም (ﷺ) ሙሽሪኮችም ወደ ካምፓቸው ሲመለሱ፣ ስለ አንድ ብቻውን ያገኘውን ሙሽሪክ ሁሉ በሰይፉ ስለሚገድል ባልደረባቸው አንድ ሰው አወራ፡፡ እንዲህም አለ ‹‹ዛሬ እንደዛ ሰው በትክክል ስራውን (ውጊያውን) የሰራ የለም››
የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ግን ‹‹ይህ ሰው ከእሳት ሰዎች ነው፡፡›› አሉ፡፡
ከሰዎች አንዱ ይህን ሰው መከታተል አለብኝ አለ (የአላህ መልክተኛ (ﷺ) የእሳት ነው ያሉትን ሰው ማለት ነው)
አብሮትም ሆነ ሲቆም ይቆማል፣ ሲሮጥ ይሮጣል፡፡ (ጀግና) የተባለው ሰውየም ቆሰለ ሞቱንም ማፍጠን ፈለገ፡፡ የሰይፉን መያዣ መሬት ላይ ቀበረውና ሁሉቱ ደረቶቹ መሃል ላይ አድርጎ ሰይፉ ላይ ተኛበት በዛውም ሞተ፡፡
ሌላኛው ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ዘንድ መጥቶ ‹‹የአላህ መልክተኛ መሆኖትን እመሰክራለሁ›› አላቸው፡፡ አል-ቡኻሪ 2898 ……………….
ከዚህ የምንረዳው የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ከመሰከሩለት ሰው ውጭ እኛ አንድን ሰው ሸሂድ ነው፣ ለዲን ሲል ነው የሚታገለው ማለት አንችልም፡፡ ምክንያቱም ለአላህ ብሎ የሚታገለውን አላህ ብቻ እንደሚያውቀው አቡሁረይራ ባስተላለፉት
وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَنْ يُجَاهِدُ فِي سَبِيلِهِ
‹‹አላህ የበለጠ ያውቃል ማን በእሱ መንገድ ላይ እንደሚታገል›› ሀዲስ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ነግረውናል ሰሂሀል አል-ቡኻሪ 2787፡፡

RIP (Rest in Peace) በሰላም እረፍ እንደማለት ነው፡፡ ይህን አባባል ከሙስሊም ውጭ ለሆነ ሰው መጠቀም በፍፁም አይገባም፡፡ ምክንያቱም የሚቀጥለው አለም ጌታ አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላን በትክክለኛ እምነት፣ በንፁህ ልብ፣ በነብዩ (ﷺ) ሱና፣ መታመን ባለበት ሁሉ አምኖ ለሄደ ብቻ ነው ሰላም ያለው፡፡ ከዛ ውጭ ግን ከባድ አደጋ ነው፡፡ አላህ የሚቀጥለው አለም ለነማን እንደሆነ ሰላም ያለው እንዲህ ሲል ይናገራል
ውዱ የአላህ ባርያ ነብየላህ ኢብራሂም (አለይሂ ሰላም) እንዲህ አለ
وَلَا تُخْزِنِى يَوْمَ يُبْعَثُونَ
በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፡፡
يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ
ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡
إِلَّا مَنْ أَتَى ٱللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»
ይህ ነው እንግዲህ ተጨባጩ ሁኔታና እውነታ፡፡ ዛሬ ሙስሊም ያልሆነ ዘፋኝ፣ አርቲስትና የመሳሰለው ሲሞት RIP (Rest in Peace) እያሉ የሚፅፉ ስንቶች ናቸው፡፡ አላህ እውቀትን ይስጠንና፡፡
ማጠቃለያ፡-
1) ለካፊር ሰመዓት (ሸሂድ) አይባልም፣
2) ለሙስሊምም በጥቅሉ በአላህ መንገድ ላይ የሞተ ሸሂድ ነው እንላለን እንጂ እከሌ ብለን አንድን ሰው ነጥለን ሸሂድ ነው አንልም፡፡ ምክንያቱም መለኮታዊ ራእይ የማይለያቸው ነብዩ (ﷺ) ብቻ ናቸው እንዲህ ብለው ሊናገሩ የሚችሉት፡፡ እሳቸው ደግሞ ሞተዋል፡፡ በሳቸው ሞት ደግሞ መለኮታዊ ራእይ ተቋርጧል፡፡ ከሳቸው ባኋላ ማንም ይህን መናገር አይችልም፡፡ ኢንሻ አላህ ሸሂድ ይሆናል ብለን ግን መመኘትና ዱዐ ማድረግ ችግር የለውም፣
3) ለካፊር RIP (Rest in Peace) አይባልም፣
4) ሙስሊም የሆነ ሰው ሲሞት እንዲያውም ዱዓ እናደርግለታለን፡፡ አላህ ይዘንልህ/ሽ፣ ይማርህ/ሽ፣ ቀብርህን/ሽን ያስፋልህ/ልሽ እያልን፡፡

አላህ ሸሪዐችንን ጠንቅቀን የምናውቅ፣ የምንሰራበትም፣ የምንፀናበትም ያድርገን፡፡ ከአላህ ውጭ ሃይልም ጥበብም ብልሃትም የለም፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው፣ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
Channel photo updated
ጥያቄ፡- “ፌስ ቡክ ላይ ተውሒድ ተውሒድ ትላላችሁ፡፡ ለምን ክፍለ ሀገር አትሄዱም?”
መልስ፡- ክፍለ ሀገር ሄደን ዳእዋ ስናደርግ ፎቶ ተነስተን መልቀቅ የለብንም፡፡ እውነታው ደግሞ አብዛኛዎቹ በፌስቡክ የሚለቀቁ ዳእዋዎች ክፍለ ሀገር ተደርገው የተቀዱ ናቸው፡፡ በአላህ ፍቃድም በሜሞሪ መብራት የሌለባቸው፣ በሶላር የሚሰሩ፣ ከተማ ቻርጅ ተደርገው የሚመጡ ስልኮች ላይ ሁሉ ይህን የተውሒድ ጥሪ አላህ በፍቃዱ አሰራጭቶልናል፡፡ በጣም ገጠር የሚባለው ቦታ ላይ ሁሉ በአላህ እገዛ ገበሬዎች ሁሉ ጭምር እንደሚሰሙት ተረጋግጧል፡፡
ይልቁንስ አብዛኛው ህዝብ በሺርክ፣ በቢድኣ፣ በጫት ተዘፍቆ እያለ የማይመለከታቸው ፖለቲካ ውስጥ ገብተው፣ የተወለዱበት ክፍለ ሀገር ውስጥ ስንት ሺርክ እያለ ዩሮፕ እና አረብ ሀገራት ላይ የሚመላለሱትን ፖለቲከኞች “ለምን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቅድሚያ የሰጡትን ተውሒድ ቅድሚያ አትሰጡም” ብለው አይጠይቀዋቻም?”
በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ሶሺያል ሚድያን ተጠቅመን ከአዲስ አበባ እስከ ክፍለ ሀገር ብሎም አለም ላይ ሐቅ ይሰራጫል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
“ዝናቡ እኝኝ አለ፡፡ ዉይ አሰለቸን እኮ”
አንዳንድ ግለሰቦች ክረምት ላይ የሚዘንበው ዝናብ አመቱን ሙሉ የሚጠጣ ውሃ ብለን የምንጠጣው እንደሆነ አይገነዘቡም፡፡ አላህ በእዝነቱ ዝናብ አዝንቦልን ሲያበቃ እኛ “ኡፍ፣ ኤጭ“ ምናምን እያልን መበሳጨታችን፣ የእኛን አላዋቂነት፣ የአላህን እዝነት እና ጥበብ አለመረዳታችንን ነው የሚያስይዘው፡፡
ይልቁንስ ዱኣ ተቀባይነት ከሚያገኝባቸው ወቅቶች ውስጥ ዝናብ ሲዘንብ ነውና፣ ይህ የአላህ እዝነት በሚወርድበት ወቅት ከመበሳጨት ይልቅ አላህን እናመስግን ዱኣም እናድርግ፡፡
እኛ ሰዎች አብዛኛዎቻችን አስቸጋሪዎች ነው፡፡ ሲቸግረን እንነጫነጫለን፣ የአላህ ፀጋ ሲሰጠን እናስተባብላለን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ሐጅ ዘንድሮም ግዴታ ነው፡፡
አላህ ግዴታ ያደረገውን ማንም ሊሽረው አይችልም፡፡ “መንገዱ ሰላም አይደለም” የሚል ውሸት እየሰማን ነው፡፡ የመን ጦርነት ቢኖር በጅቡቲ በኩል ነው አውሮፕላን እየበረረ ያለው፡፡ ሳውዲ ውስጥም ጦርነት የለም፡፡ ስለዚህ “መንገዱ ሰላም አይደለም” የሚለው ውሸት ከማንም ቢመጣ እንዳትቀበሉ፡፡
“ህገ ወጡ መጅሊስ ዘራፊ ነው፡፡ እነሱ ከስልጣን ካልወረዱ ዘንድሮ ሐጅ ግዴታ አይደለም” የሚላችሁን እንዲህ በሉት

- አምናም ይህ ህገወጥ መጅሊስ ይዘርፍ ነበር “ለምን ሐጅ አደረግን”፣
- ከአህባሹ በፊት የነበረው ሌላኛው ዘራፊ የሱፊያ መልጂስም ሙስሊሙን ከላይ እስከ ታች ሲዘርፈው ነበር፣ ሀጅ ላይም ሲያሰቃየው ነበር ታድያ ለምን ይህን ነገር መቀስቀስና ይህኛውን ዘራፊ ብቻ መናገር አስፈለገ?

ሙስሊሞች ሆይ! ንቁ፡፡ ሐጅን በህይወት አንድ ጊዜ፣ በቻለ ሰው ላይ አላህ ግዴታ አድርጎታል፡፡ አላህ ግዴታ ያደረገውን ማንም ሊሽረው አይችልም፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ሙስሊሞች ከነዚህም ተጠንቀቁ፡፡
የፔንጤን ተንኮል ተጠንቀቁ፣ የአሕባሽን ተንኮል ተጠንቀቁ ተብሎ በማስረጃ ሲነገር የጀዛከላህ መኣት የምታዘንቡ ሙስሞች ሆይ! በሺርክ መንዙማቸው ወደ ክህደት የሚጣሩትን፣ በቢድኣቸው፣ ከኢስላም ባፈነገጡ ትምህርቶቻቸው ሙስሊሙን ጠመው የሚያጠሙ ሁሉ ስማቸውም በማስረጃ ተጠንቀቋቸው ሲባል ይህንንም ልንቀበል ይገባናል፡፡ አለበለዚያ ፔንጤውን እና አህባሹን ምን ይዘው ስለመጡ ነበር የተቃወምናቸው የሚለው ለነፍሳችን ከባድ ጥያቄ ይሆናል፡፡
ሙሐመድ አወል ሐምዛ እና ሌሎች ጓደኞቹ ኡመተል ኢስላምን ከተውሒድ ወደ ክህደት በአደባባይ ሲጣሩ መልስ ሲሰጥባቸው የከፋው ካለ መጀመሪያውንም ሰውን የሚወደውም የሚጠላውም ለአላህ ሲል አይደለምና እራሱን ይመርምር፡፡
እኛ ከብቸኛዋ፣ ከቀጥተኛዋ አንድ መንገድ ውጭ ያሉትን ማንኛውንም የጥመት መንገድ ይዞ የመጣን ቡድንም ይሁን ግለሰብ ልንቃወም ብሎም ሙስሊሞችን ልናስጠነቅቅ ይገባናል፡፡ አህባሽን ብቻ ተቃውሞ ሱፍያን፣ አሽአሪያ፣ ኢሕዋንን፣ ተብሊግን…. የተለያዩ የጥመት ቡድኖች ዝም ማለት፣ ብሎም አትንኳቸው ማለት የጥመት ምልክት ነው፡፡ ይህ ነው ኡማውን ከቀጥተኛው መንገድ ለያይቶ ሰዎችን በተለያየ የጥመት መንገድ ላይ ወደ እሳት እንዲጓዙ ማመቻቸት፡፡
በነገራችን ላይ ማንም የተደራጀውን ያህል ቢደራጅ፣ ያቀደውን ያክል ቢያቅድ፣ ያወጣውን ያህል ገንዘብ ቢያወጣ ሐቅ አንድ እና አንድ ብቻ ናት፡፡ እሷም የጥንት የጠዋቷ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ባልደረባዎቻቸው እነሱን በበጎ የተከተሉ ያሉባት መንገድ፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉት የለፉትን ያህል ቢለፉ ሺርክን ተውሒድ አድርገው ለማቅረብ ቢሞክሩ፣ ቢድኣን ሱና አድርጎው ለማቅረብ ቢሞክሩ፣ ዘረኝነትን የተቀደሰ አድርገው ለማቅረብ ቢሞክሩ፣ ይህን አደንዛዥ ቅጠል ጫት የኢስላም አካል አድርገው ለማቅረብ ቢሞክሩም አላህ እያንዳንዷን ነገር ተመልካች ስለሆነ አያሳካላቸውም፡፡ ከዚህ በፊት እንደቀመሱት ውርደትን ቢቀምሱ እንጂ ሌላን አያመጡም፡፡
ከእኛ የሚጠበቀው ከማንም ይምጣ ከማን ጥመትን ማጋለጥ፡፡
አላህ ሆይ! ሐቅን በሐቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያችን፣ በሰሃባዎቻቸው፣ በባለቤቶቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts