Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
ከ 200 በላይ የድምፅ ዳእዋ ፋይሎች ከሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ያግኙ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
Rabbi siif haa kennu
ውንድሜ ፉአድ ሙሐመድ (አላህ ይጠብቅህ) በኦሮሚኛ ስለ ነሺዳ ባስተማርከው ትምህርት አላህ ይቀበለህ፡፡ ባስተማርክበት ቋንቋ Rabbi siif haa kennu፡፡ ኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪ እና አዳማጭ የሆናችሁ የተከበራችሁ ወንድም እና እህቶቼ እንስቲ ይህን በኦሮሚኛ ተናጋሪ ወንድሞቻችን የተከፈተ ቴሌ ግራም ቻናል ጆይን ብላችሁ ከሚሰጡት ትምህርት ተጠቀሙ፡፡
https://t.me/daawaa_fi_barnoota
ወንድማችን ስለ ነሺዳ ያስተማረበትን ሙሐደራ ለማዳመጥ የሚከተለውን ሊንክ ክሊክ አድርጉ
https://t.me/daawaa_fi_barnoota/184
አልሐምዱሊላህ ሰው እንደዚህ ሲለወጥ ደስ ይላል፡፡
ከሺርክ እና ከቢድኣ በአላህ ፍቃድ ሰዎች እንደተለወጡት ሁሉ አሁን ደግሞ ስለ ነሺዳና መንዙማ ከቁርዓን አዘናጊነት ትምህርት ከተለቀቀ በኋላ አንድ የዩቲዩብ ተጠቃሚ እንዲህ ሲል ኮሜንት ፅፏል

"ውይ እኔ ነሺዳ ማዳመጥ አንድ ቁጥር ነኝ ቁርዓኑ ግን አንድ ሁለት ሱራ እደቀራሁ እንቅልፍ ይደፍኛል ……ከዛሬ ጀምሬ ስልኬ ላይ ነሺዳ ሚባል ሁላ አዎጣለሁ"

አልሐምዱሊላህ ገና ይቀጥላል ሙስሊሙ ኡማ ከጫትም ከሌሎችም መጥፎ ነገሮች በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ይለወጣል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አላህ ሁሉን ሰሚ ነው፡፡
ዱኣ (ፀሎት) በአረብኛ ማድረግ በላጭ ነው፡፡ አረብኛውን ለማይችሉ በአማርኛ፣ በኦሮሚኛ፣በስልጢኛ፣ በጉራጊኛ፣ በትግሪኛ፣ በሀደሪኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ…. በማንኛውም ቋንቋ አላህን መለመን ይቻላል፡፡ ዱኣ ታላቅ አምልኮ ነው ትርጉሙን ተምረን አላህን እንለምነው፡፡ ዱኣን ትርጉሙን ካላወቅን ብዙም ጥፍጥናውን አናውቀውም፡፡ አላህ እውቀት ይጨምርልን፡፡ https://t.me/SadatTextPosts
ረመዳን ገና አላለቀም፣ እኛም ገና አልሞትንም፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ረመዳን ሲገባ አልሐምዱሊላህ መስጂዶች ሰው በደንብ አስተናግደው ነበር፡፡ አሁን ገና ረመዳኑ ሳያልቅ ትንሽ መቀነስ ይታያል፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩ አመታት ላይ እንደሚታየው ረመዳን ሲወጣ አብዛኛው ሰው ከመስጂድ ይርቃል፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ባረከላሁ ፊኩም ረመዳን ገና አላለቀም፡፡ ረመዳን አለቀ ቢባል እንኳን አንድ በበለጠ ሁኔታ ኸይር የሚሰራበት ወር አለቀ እንጂ ሌሎች አላህ የሚመለኩባቸው እና መልካሞች የሚሰሩበት እና ከመጥፎ የሚራቁባቸው ወራት እንደቀጠሉ ነው፡፡ ረመዳን ውስጥ በተለይ የተከበሩት የመጨረሻዎቹ ለይለቱል ቀድር ይገኝበታል ተብሎ የሚገመቱት አስር ቀናት አሉ፡፡ እባካችሁ ነቃ እንበል፡፡ እኛን አላህ የፈጠረን እስከለተ ሞታችን ድረስ እሱን በብቸኝነት እንድንገዛው ነው፡፡ አላህ ለሰው ልጆች ሁሉ ፈርጥ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አላቸው
[15:99] وَٱعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ ٱلْيَقِينُ
እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡
እሳቸውም የጌታቸውን ትዕዛዝ በመፈፀም እስከለተ ሞታቸው ድረስ የማይሞተውን ህያው አምላክ አላህ አመለኩት፡፡ ከዚህ አለም ሲለዩም የመጨረሻ ንግግራቸው
“አላህ ሆይ! ከላይኛው የጀነት ጓዶች አድርገኝ” የሚል ነበር፡፡
ታድያ ያለፈውንም የሚመጣውን ሁሉ አላህ የማራቸው የሰው ልጆች ሁሉ ፈርጥ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይህን ያህል ከለፉ እኛስ የሚል ጥያቄ ነፍሴንም እናንተም እየጥቃለሁ፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለሙኣዝ ኢብን ጀበል ሰላትን ከማጠናቀቁ በፊት “አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት ላይ፣ በማመስገን ላይ እና ያማረን አምልኮ ላንተ በመፈፀም ላይ አግዘኝ” እንዲል ጠቁመውታል፡፡
እኛም አላህን እንለምነው፡፡
አላህ ፅናት ይስጠን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በረመዳን ተውበት አድርገው በተመለሱ ወንድም እና እህቶች ላይ አታሹፍባቸው ምክንያቱም ይህ የመለወጫ ሰበባቸው ይሆናልና ኢንሻ አላህ ልክ አንተ/ቺ ከለታት በአንድ ቀን ውስጥ እንደተመለስከው/ሺው፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ከማንኛውም ወንጀል ተውበት በማናችንም ላይ ግዴታ ነው፡፡ ከወንጀል የተመለሱ ወንድም እና እህቶችን በማበረታታት እና መጥፎ ጓደኛዎቻቸውን እንዲርቁ በመምከር በሀቅ ላይ ይፀኑ ዘንድ ማበረታታት ይገባል፡፡
አላህ ሁላችንንም ንፁህ ተውበት ይለግሰን፣ በሃቅ ላይም ያፅናን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
ከሌሊቶች ሁሉ በላጭ የሆነችው ሌሊት በጀመርናቸዉ 10 የረመዳን መጨረሻ ሌሊቶች ውስጥ ትገኛለች — በርካታ ኡለሞቻችን እንደሚሉት ።
በርካታ ኸይሮች ያለባትን ይችን የተከበረች ሌሊት አትርፎባት ማለፍ የፈለገ አማኝ ከወዲሁ ጀምሮ ወገቡን ማጥበቅ ይጠበቅበታል — الله ለሚወዳቸው ስራዎች!!
ነብዩ እነዚህን ውድ ሌሊቶች ሽርጣቸውን ጠበቅ በማድረግ ( ከሚስቶቻቸው በመራቅና ኢባዳን በማብዛት) ፣ፈጣሪያቸውን በብርቱ በማምለክ ሳይተኙ ያሳልፏቸው ነበር!!

በተረፈ በነዚህ የተከበሩ ሌሊቶች ውስጥ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ከአገርና ከቤቶቻቸው የተፈናቀሉ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን እናስታውስ!! ዱዓ እናርግላቸው።
ወንድሞችና እህቶች አላህን እንፍራ!
ዱባዬች ተጠንቀቁ
ማንን ?
ካላችሁ
በየአመቱ ኢድ እና አረፋ በመጣ ቁጥር ሴት እና ወንዶችን አዳራሽ ላይ በመደባለቅ ከአዲስ አበባ ከመጡት "ሙነሺዶች" ጋር በመሆን በአሉን እናክብር በማለት ብራችሁን ከሚበዘብዙት እና አላህ የጠላውን* "ኢኽቲላጥ" (ሴት እና ወንድን መደበላለቅ) ከሚፈፅሙት የዲን ደጋዴዎች።

አላህ በሚመሰገንበት ቀን አላህን ስታምፁ እንድትውሉ እነዚህ ተሳስተው አሳሳቾች ይጠሯችኀል፣ ይጎተጉቷችኀል አትስሟቸው ራቋቸው።

ተጠንቀቋቸው ከነሱም አስጠንቅቁ።
https://t.me/SadatTextPosts
የእኛም ህይወት
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ረመዳኑ ቀኑ መፍጠኑ ብዙዎቻችንን አስደነገጠን፡፡ እንዲህ ሲፈጥን ሁሉም የአቅሙን መልካም በመስራት እንደው በዚህ የተከበረ ወቅት ልጠቀምበት በሚል መልካሞችን በአቅሙ ልክ እያበዛ ነው፡፡ ታድያ የአላህ ባሪያዎች የእኛንም ህይወት ከተመለከትነው እውነታው ይህ ነው፡፡ አንድ ቀን ባደርን ቁጥር አንድ ቀን ወደ ሞት እየተጠጋን ነው፡፡ ከሞት በኋላ ደግሞ ለሰራነው ስራ ውጤት ማግኘት እንጂ ስራ መስራት አይቻልም፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አንድ ቀን ባነጋን ቁጥር ወደ ማይቀረው የተቀጠርንለት ሞት እየቀረብን ነውና ለሚቀጥለው አለም ስንቃችንን እናዘጋጅ፡፡ አላህን ሁሌ እናምልከው፡፡ ከስንቆች ሁሉ በላጭ አላህን መፍራት ነውና አላህን እንፍራ፡፡
አላህ ሆይ! አንተን መፍራትን አላብሰን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም፡፡
*************************************
ምስጋና ለአላህ ነው፤ ሁለት የመደሰቻ በአላትን የደነገገ፡፡ አሁንም ምስጋና ይገባው ይህንን ሸሪዓ ከመበረዝ እጠብቀዋለሁ ብሎ ቃል የገባው አላህ፤ የሃይማኖት ድንጋጊን ሁላ ለራሱ ብቻ ያደረገ፤ በዚህም ላይ ታላቅ ጥበቡን ያሳየ፡፡ እንደሌሎቸ ሀይማኖቶች፤ ቀሳውስት እንደበረዙት (እንደጨመሩበት እና እንደቀነሱበት) እንዳይሆን በግልፅ ሸሪዓዊ ድንጋጌን ለራሱ ብቸኛ አውጪ ያደረገ፡፡
ሱና ፆም ፆመን ዝም ብሎ ማለፍ እንጂ ከአላህ የተደነገገ በዓል የለም፡፡ ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር ከነብያችንም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፤ ከሰሃባዎቻቸው (ሪድዋኑላሂ አለይሂም)፤ ከ3 ምርጥ ትውልድ፤ ከ4 አኢማዎች አላገኘንም፡፡ ታድያ ለምንድን ነው እኛ ያልታዘዝነውን የምንሰራው???
ሰኞ እና ሀሙስ ፆመን ምንም በአል ከሌለ፤ 13፣14፣15 ፆመን ምንም በአል ከሌለ፤ የሸዋል 6 ከየት መጣ??? አላህን እንፍራ፡፡
አንዳንድ ቦታ ያውም ከዋናው ኢድ በላይ ይህን ቀን ያከብሩታል፡፡
እወቅ የአላህ ባሪያ ከሽርክ ቀጥሎ ሸይጧን ዘንድ የተወደደው ወንጀል ቢድዓ ነው፡፡ ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ ለእሳት ነው፡፡
አላህ በደነገገልን 2 ኢዶች፤ ከዛ በጁምዓ ብቻ እንብቃቃ፡፡ ሁሉ ነገር የሌለው ይቀላውጣል፡፡ አላህ ግን ይህን ዲን ሞልቶታል፤ ታድያ እንደ አህለል ኪታብ መጨማመሩ ምን አስፈለገ፤ የአላህን ቁጣ ለመውረስ ካልሆነ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም፡፡ ተጠንቀቁ አስጠንቅቁ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት እና ሩሱሎች ኢማም ላይ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አመቱን ሙሉ እንደፆመ መሆኑ አይፈልጉምን?
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
“ረመዳንን የፆመ ከዛም ከሸዋል (ወር) ስድስት ቀናትን (በመፆም) ያስከተለ፣ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ነው::”
ይህን በፍላጎት የሚፆም ፆም እንፁም እና ከምንዳው እንካፈል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የአላህ ችሮታ
በእስልምና አንድ አመት 12 ወራቶች አሉት፡፡
ረመዳን እንደ 10 ወር ሲቆጠር፣ ስድስቱ የሸዋል ቀኖች እንደ ሁለት ወር ይቆጠራሉ፡፡
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
“ረመዳንን የፆመ ከዛም ከሸዋል (ወር) ስድስት ቀናትን (በመፆም) ያስከተለ፣ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ነው::”
ምክንያቱም ቸሩ አላህ መልካም ስራን በአስር አባዝቶ ስለሚቀበል፡፡
የሚገርመው መሃሪው አላህ ረመዳንን በሁለት ረመዳኖች ውስጥ የተሰራውን ወንጀል ማስማሪያ ሰበብ አድርጎታል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ሸይኽ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ
“(ረመዳን) ወሩ በማለቁ አንደሰትም፡፡ ነገር ግን የምንደሰተው ወሩን አላህን በመገዛት ስለጨረስን ነው፡፡”
አላህ የነብያት ወራሾች የሆኑትን አዋቂዎች ይጠብቅልን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሁል አእማል