Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
ኡማው ረመዳንን ለመቀበል ቁርኣንን ለመቅራት … ደፋ ቀና ይላል ደፋሮቹ ኡማውን ከቁርኣን ለማዘናጋት
“30 FFAA EEBBA NASHIIDAA” “30ኛ የነሺዳ ምርቃት” ብለው ዘንድሮም እንደለመዱት ለረመዳን ብቅ አሉ፡፡ አስገራሚው ካፊሮች፣ ፖለቲከኞችም ጭምር የነሺዳው ምርቃት ላይ መሳተፋቸው ነው፡፡ ይህ ስራቸው ከሀይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ይሀው ተግባራቸው እራሱ ያሳያል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው በዲን ሽፋን የሚነግዱበት ህዝብ ነው፡፡ በአላህ ፍቃድ ህዝቡ እያወቃቸው ነው፡፡ በአላህ እገዛ እኛም እነሱ እንዲህ ዲን ሲያበላሹ እያየን ዝም አንላቸውም፡፡
አላህ ከነዚህ ሰዎች ተንኮል ይጠብቀን፡፡
ቁርኣን በ አንድ ሀርፍ አስር ሀሰና እንዳለው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ነግረውናል፡፡
መንዙማ እና ነሺዳ ያውም ሺርክ፣ የሙዚቃ መሳሪያ፣ ፉጨት፣ ጭፈራ የተደባለቀባቸው ምን ምንዳ ይኖራቸዋል?
አደለም ምንዳ ሊያስገኙ ያስቀጣሉ፡፡
ቁርኣንን አደለም መቅራቱ ፀጥ ብሎ መስማቱ የአላህን እዝነት እንደሚያስገኝ አላህ ነግሮናል፡፡
ታድያ ለምን ይሆን የኪሳራ መንገድ የሆነውን መንዙማ እና ነሺዳ በሚጮህ ስፒከር ታክሲ ላይ ተጭኖ ከተማ እየዞሩ ህዝቡን የሚረብሹት?
ታድያ ለምን ይሆን በዚህ በተከበረ የረመዳን ወር ሙስሊሙ የአላህን ቃል ቀርቶ በአንድ ሀርፍ አስር ሀሰና እንዳያገኝ የሚያዘናጉት?
አላህ ሆይ! ቀጥተኛውን መንገድ እኛንም እነሱንም ምራን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የሚለፉለትን ነገር ይወቁ።
ስራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኘው ለአላህ ብቻ ተብሎ የተሰራና በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና መሰረት ሊሆን ግድ ይለዋል። አለበለዚያ ትርፉ አመድ አፋሽ መሆን ነው። በአላህ ፍቃድ ዋና ለዛሬ ማንሳት የፈለግኩት ረመዳን ላይ በዲን ስም ስለሚሰሩ ቢድአ (በዲን መሰረት የሌላቸው) ፈጠራዎች ነው።
ዚክርን የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደነገጉት መንገድ እና ሁኔታ መፈፀም እራሱ ስራውን አላህ ዘንድ ውድቅ ያደርገዋል። ለዚህም ማስረጃው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ ነው
"የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው (ውድቅ ነው)"።
ታድያ አንተ/ቺ የአላህ ባርያ ሆይ! በአንዳንድ መስጂዶች በጀመአ ኢማሙ እያወጣ መእሙሙ እየተቀበሉ
1) አሽሀዱ አን ላ ኢላሃ ኢለላህ፣ አስተግፊሩላህ፣
2) ነስአሉከል ጀነተ ወናኡዙ ቢከ ሚነናር፣
3) አስተግፊሩላህ 100 ጊዜ
እና የመሳሰሉትን።
ልብ በሉ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ከላይ ያሉት ትክክለኛ ዚክሮች ሽርክ የሌለባቸው የተውሂድ ቃላቶች ከመሆናቸውም ጋር ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲፆሙ እነዚህን ዚክሮች አገራችን ላይ እንደምናየው አይሉዋቸውም ነበር።
"የእኛ ትእዛዝ የሌለበት ስራ የሰራ ሰው ስራው ውድቅ ነው" ባሉት መሰረት እነዚህ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው ያልሰሩትን በመስራት ወደ አላህ እቃረባለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ በነፍሱ ላይ እየፈረደ ነውና ሳይመሽበት ይቶብት።

ፆምና ሌሎች ኢባዳዎችን አጥፊ የሆነው ደግሞ አንዳንድ መስጂዶች ላይ
1) "አጊስና ያረሱለላህ" (አጠጡን አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ)
2) "ኹዝ ቢየዲ ያረሱለላህ" (አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! እጄን ያዙኝ)
እንግዲግ እነዚ 2 ስንኞች እና መሰሎቻቸው ለብቸኛው ፈጣሪ አላህ ብቻ የሚገባውን ፀሎት ፍጡር ለሆኑት ነብዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚሰጡ ናቸው።

ሽርክ ማለት ደግሞ አላህንም እያመለኩ ሌሎች አካላትን (መላእክት፣ ነብይ፣ ሰሃባ፣ ሷሊሆችን፣ ጂን —-----) አብሮ ማምለክ ነው።
በአላህ ላይ እያጋራ የሞተ ሰው የእሳት ነው። በአላህ ላይ ለሚያጋራ ሰው ፆምም፣ ሀጅም አይጠቅመውም። ስለዚህ የሽርክን አደገኝነት ተገንዝበን ማህበረሰቡን እንደ ሰበብ እናንቃ።
ዲናችን ሀብታችን ነውና ስራችንን በኢኽላስና በሱና በማስጌጥ፣ ከሽርክና ቢድአ ከነባለቤቶቻቸው በመረቅ ለነፍሳችን እንዘን።
ሽርክና ቢድአ አደጋቸው ከባድ ነው።
https://t.me/SadatTextPosts
የጫት እርሻዎች በእህል እርሻ ከተቀየሩ ህዝቡ ከረሀብ ወጥቶ በምግብ እራስን ለመቻል እና እንደነ ዳቦ ያሉ የስንዴ ውጤቶች ለድሀው ህዝብ ቅናሽ ዋጋ ለመቅረብ ሰብብ ይሆናል፡፡
አላህ ይህንን እርኩስ ትውልድን የገደለ ቅጠል ከምድረ ገፅ ያጥፋው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ዘሬን ከሃይማኖቴ አላስበልጥምም፣ እኩልም አላደርግም፡፡
አላህ እውቀት ይስጠን፡፡
እንዴት ነው አንድ ሰው ኢስላምን ከዘሩና ከሀገሩ እኩል የሚቆጥረው?
ኢስላም አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ብቸኛ ሃይማኖት ነው፡፡ ኢስላምን የያዘ ሰው ከአሳማሚ እሳት ተጠብቆ፣ ያችን ታላቅ ሀገር ጀነት በአላህ ፍቃድ ይወርሳል፡፡ አንድ ሰው እምነቱ ካልተሰተካከል አይደለም ዘሩ፣ ዘር ማንዘሩ ቢሰበሰብ ከጀሀነም እሳት መውጣት አይችልም፣ ያችን ውድ ሀገር ጀነትንም አይወርስም፡፡
ሰው ስሜቱን ማምለክ ሲጀምር እንዲህ አይነት ከባድ እምነቱን የሚነካ አደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ስራው (ከጀነት) ያስቀረውን ዘሩ አያስቀድመውም፡፡” ብለዋል፡፡
ሀገር እና ብሄር ከሃይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም፡፡ አንድ ሰው ሙስሊም ሆኖ ከዛም በተጨማሪ ቁረይሽ እና አረብ ብሎም ሳውዲያዊ ቢሆን ሳውዲያዊ፣ አረብ፣ ቁረይሽ መሆኑ ምንም አይጨምርለትም፡፡ ልክ እንደዚሁ አንድ ሀገራችን ላይ ያለ ግለሰብ የሆነ ብሄር ቢሆን እስልምናውን አጥብቆ መያዝ ብቻ እንጂ አላህ ዘንድ ከእሳት ተጠብቆ ጀነት እንዲገባ የሚያደርገው ብሄሩ ወይም ኢትዬጵያዊነቱ ከእስልምና ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ይህን ታላቅ የነብያቶች ሁሉ ሃይማኖት ከብሄር እና ሀገር እኩል አድርጎ ማቅረብ የመሃይምነት ጥግን የሚያሳይ ነው፡፡ እንጠንቀቅ፡፡
አልሐምዱሊላህ እኔ ሃይማኖቴን ከዘሬም ከሀገሬም አላስቀድምም፣ እኩልም አላደርግም፡፡ የእኔ ሰውነት ከእንስሳ በላይነት የተረጋገጠው በእስልምናዬ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ታላቁ ሰሃባ ቢላል (ረድየላሁ አንሁ) እራሳቸውን አረቦች የነብየላህ ኢስማኢል (አለይሂ ሰላም) ዘሮች ነን የሚሉት ሰዎች ዘንድ እንደ ባሪያ ነበር የሚታየው፡፡ እሱ ግን አላህ ዘንድ ታላቅ ሆነና ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ መሰከሩለት “ጀነት ላይ የእግርህን ኮቴ ሰማሁት”፡፡
ቢላል (ረድየላሁ አለንሁ) በሀበሻነቱም፣ በጥቁርነቱም አልነበረም ጀነት ላይ ኮቴው የተሰማው፡፡ ነገር ግን በእስልምናው ብቻና ብቻ እንጂ፡፡
አላህ ሆይ! እኛንም ዝርያዎቻችንንም ከዘረኝነት በሽታ አፅዳን፡፡ አላህ ሆይ! የመሃይምነት ዘመን መገለጫ ከሆነው ዘረኝነትም በአንተ እንጠበቃለን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ፖለቲካ አልናፈቀንም፡፡
ሙስሊሞችን በኢስላም ሽፋን ማታለል ይቁም፡፡
ይገርማል?
መልክተኞች ሁሉ የተላኩት በሽርክ ጨለማዎች ውስጥ የተዘፈቁትን ህዝቦች ወደ ተውሒድ ብርሃን በአላህ ፍቃድ ለመምራት ነበር፡፡ መልክተኞችን የተከተሉ የእውቀት ባለቤቶችም በዚሁ በመልክተኞች ፋና ላይ ነበር የተጓዙት፡፡
ዛሬ በተገላቢጦሹ አላህ ካዘነላቸው ጥቂት የነብያት ተከታዬች ውጭ፣ የነብያትን ፈለግ ተቃርነው የሚከተሉት ከባባድ ሽርክ ጨለማዎች እና ተግባሮች አገራችንም ላይ ይሁን አለም ላይ እያሉ እነሱ ወደ ሌላ አርስት የሚጣሩ በጣም ብዙ አሉ፡፡ ገርሞ የሚገርመው ሀገራችን በሺርክና ቢድኣ ተወራ ስታበቃ “የናፈቀን ፖለቲካ ነው፡፡” ብለው የሚደሰኩሩ ጠሞ አጥማሚዎችን ማስማታችን ነው፡፡ መስጂድ ውስጥ እንዲህ አይነት እርኩስ ንግግሮችን መናገር ደግሞ አደጋውን ያከፋዋል፡፡
ፖለቲካ የጠማው ካለ ሙስሊሞችን ለቀቅ አድርጎ፣ ኢስላምን ለፖለቲካው አላማ ሳያውል እዛው እራሱን ወክሎ ይደስኩር፡፡ እኛ ሙስሊሞች የአላህ መልክተኛ በሄዱበት መንገድ በመሄድ ኡመተል ኢስላምን ከምንም በፊት ከጌታው ጋር በማስተዋወቅ፣ ሺርክና ቢድኣ የተባሉትን ዋና ነቀርሳዎች በአላህ ፍቃድ ከኡመቱ ላይ በመፈንቀል ወደ ተሻለው መንገድ እንጓዛለን፡፡

እስቲ ምን ይሆኑ እነዚህ ሽርኮች፡፡ በአላህ ፍቃድ አገራችን ላይ ካለው ሽርክ ዘልዬ አልወጣም፡፡
- ነጃሺ ቀብር ላይ የሚሰራው አስፀያፊ ሽርክ፣
- ጎንደር ላይ የሚመለከው “የአሊ ጎንደር” ቀብር፣ አባድር…..
- ጎጃም ላይ “እኔ ኢንቨስተር እንጂ ሸህ አደለሁም” ያለውን ሸህ ማምለክ፣
- ጎጃም አዴት “ለውሻ” የሚፈፀመው አመታዊ እርድ፣
- ጎጃም ዳንግላ…..
- ጎጃም ቲጃኒያ….
- ወሎ “የቦረናው ደግዬ እርዱኝ አባብዬ”፣
- ወሎ ሌሎች ብዙ ቦታዎች ላይ ሽርክ…...፣
- ቡሬ የቲጃንዩ ሸህ……
- “የሸህ ሁሴን ጂብሪል ትንቢት” የሚባለው ጥንቆላ
- የጅማ አባጅፋር መውሊድ፣
- አዲስ አበባ ጉለሌ እስላም መቃብር….፣
- አዲስ አበባ ብዙ ጠንቋይ ቤቶች…..
- በጉራጌ “ቃጥባሬ”፣ “አብሬት”….
- በስልጤ “አልከሶ”…
- ድሬ ባሌ ኑር ሁሴን….
- ለጅብ ገንፎ አግንፍቶ ማቀዋደስ፣
- አንበሶ፣ ሰይፉ ጨንገሪ፣ አዳል ሞቴ፣ ወሰን፣ ሮመዲ፣ ዘባንያ እና የመሳሰሉት እርድ የሚፈፀምላቸው ሰይጣናት….
- አባድር በሃረር…. “አባድር ፆም አያሳድር” የሚባል የክህደት ንግግር፣
እና የመሳሰሉትን፡፡ እዚህ ጋር የጠቀስኳቸው ቀብራቸው ላይ ጠዋፍ የሚደረግ፣ ከአላህ ውጭ ድረሱልን እየተባሉ የሚጠሩ፣ ስለት የሚገባላቸው፣ መውሊድ እየተባለ ባወጡት ቀን የሚከበርላቸው እና የመሳሰለውን ነው፡፡
አሳዛኙ ብዙ ዱዐቶች እነዚህ ሁሉ ሽርክ ከሚሰሩባቸው ክፍለ ሀገራት ነው ተወልደው ያደጉት፡፡ የመጀመርያ ጥሪያቸውም ተውሒድ ነበር መሆን የነበረበት፡፡ ግን እነሱ አደራቸውን በልተው ተውሒድ ካልተስተካከል ምንም ጥቅም የሌላቸውን አርስቶች ሲደጋግሙ ይታያሉ፡፡
መንዙማ እየተባለ
- “ያቀመረል መካ አሰላሙ አለይካ ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ”፣
- “ሀቢቢ ሀቢቢ ሀቢቢ መዲና ና ይበሉኝ”፣
አረ ስንት ማለት ይቻላል፡፡ እነዚህ ለምሳሌ በቂ ናቸው፡፡ አንዱ ሽርክ ስራዎችን ሁሉ አፈር ከድሜ ለማስገባት በቂ ነው፡፡ ተመልከቱ ህያው አላህን ትተው በሞቱት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲመኩ፡፡
አላህ ግን እንዲህ ብሎን ሲያበቃ
وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱلْحَىِّ ٱلَّذِى لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِۦ ۚ وَكَفَىٰ بِهِۦ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرًا
በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ (አላህ) ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡
ሌላው ይህን ምድር በብቸኝነት የሚያስተናብረው አላህ ሆኖ ሳለ አላህን ትተው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) “መዲና ና ይበሉኝ” ብለው ይጠይቃሉ፡፡
አሳዛኙ ግን አብዛኛዎቹ ዱዐት የተባሉት ሰዎች አይደለም ይህን ሽርክ ሊቃወሙና፣ የእንደዚህ አይነት ሽርክ አቀንቃኞችን ቻናላቸው ላይ የኢድ ባዕል “እንግዳ” አድርገው ያቀርባሉ፡፡
ሱብሃነላህ፡፡ አላህ እኛንም እነሱንም ይምራን፡፡
ታድያ ይህ ሁሉ ሽርክ የሚፈፀምበት አገር ላይ ተቀምጦ ተውሒድን ማስተማር ሲገባ ከዚህ አርስት ውጭ ሌላን አርስት መተንፈሱን ምን አመጣው?
እውነት ለኡማው ታስቦ ነውን?
ለኡማው እማ ከአላህ እና ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የበለጠ ያዘነለት የለም፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሽርክን አስጠንቅቀው ወደ ተውሒድ ተጣርተው ነበር ዳእዋቸውን የከፈቱት፣ በዛም ላይ የሞቱት፡፡
አሳዛኙ የነብዩላህ ኑሕ (አለይሂ ሰላም) ህዝቦች የጠፉት በሽርክ ሰበብ ነበር፡፡ ዛሬ አብዛኛው ዘንድ ይህን ሁሉ ሽርክ፣ ቢድዐ፣ ፍልስፍና እና ወንጀሎች ተሸክሞ “ድል ናፈቀን” እና የመሳሰለውን ቃል ከአፋቸው ሲያወጡ፣ እነዚህ ሰዎች አእምሮዋቸው ይሰራል ወይ? ያስብላል፡፡ ምክንያቱም መጀመርያ ይህን የሚያክል ሽርክ ፊት ለፊታችን አፍጥጦ ተቀምጦ እሱን ከመዋጋት ይልቅ አድበስብሰው እያለፉ ከዛም “ነስሩ ቅርብ ነው” እያለ በየሶሻል ሚድያው እና በየመድረኩ የሚደሰኩር ሳይ ግርም ይለኝል፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለ “ድል” አያውቁም ወይ?
ከሽርክ እና ከቢድዐ ፀድቶ በተውሒድ እና ሱና ላይ ከመኖር የበለጠ ምን ድል አለ?
እስቲ ይህችን ነጥብ ልብ እንበል፡፡ አላህ እዝነቱ ካፊሩንም አማኙንም፣ ሙናፊቁንም ሙኽሊሱንም፣ ሱንዩንም ሙብተዲውንም፣ እንስሳውንም ያጠቃለለ ነው፡፡ ድልን ግን ከሸርጥ ጋር ነው ያደረገው፡፡ ተውሒዳቸውን አሟልተው የኖሩ ሰዎች በዱንያ ላይ መመራት አላቸው፣ በአኸይራ ላይ ደህንነት አለላቸው፡፡ ከእሳት ተጠብቀው ጀነት ይገባሉ፡፡ አላህ ከነሱ ያድርገን፡፡
ሽርክ እና ቢድዐን አዝሎ ሌላ ነገር ማውራት እብደት፣ ድንቁርና፣ መሃይምነት ነው፡፡
አላህ መመልከቻ ልቦና ይስጠን፡፡
እነዚሁ ፖለቲካ ተጠምተናል የሚሉ ግለሰቦች እንዲህ የያዙት መንገድ ልክ እንዳልሆነ ሲጋለጡ “በኢስላም ፖለቲካ የለም ልትሉን ነውን?” ይላሉ፡፡ እኛም እንዲህ የሚል መልስ እንሰጣቸዋለን እውነተኞች ሁኑ አታጭበርብሩ፡፡ በኢስላም ያለው ፖለቲካ በሁሉ ጉዳይ አላህ እና መልክተኛውን ፈራጅ ማድረግ እንጂ ዛሬ እናንተ ልታቦኩት የተዘጋጃችሁት እና የቋመጣችሁለት ሰው ሰራሽ ህግ አይደለም፡፡
እውነተኞች እንደሆናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ከ 200 በላይ የድምፅ ዳእዋ ፋይሎች ከሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ያግኙ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
Rabbi siif haa kennu
ውንድሜ ፉአድ ሙሐመድ (አላህ ይጠብቅህ) በኦሮሚኛ ስለ ነሺዳ ባስተማርከው ትምህርት አላህ ይቀበለህ፡፡ ባስተማርክበት ቋንቋ Rabbi siif haa kennu፡፡ ኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪ እና አዳማጭ የሆናችሁ የተከበራችሁ ወንድም እና እህቶቼ እንስቲ ይህን በኦሮሚኛ ተናጋሪ ወንድሞቻችን የተከፈተ ቴሌ ግራም ቻናል ጆይን ብላችሁ ከሚሰጡት ትምህርት ተጠቀሙ፡፡
https://t.me/daawaa_fi_barnoota
ወንድማችን ስለ ነሺዳ ያስተማረበትን ሙሐደራ ለማዳመጥ የሚከተለውን ሊንክ ክሊክ አድርጉ
https://t.me/daawaa_fi_barnoota/184
አልሐምዱሊላህ ሰው እንደዚህ ሲለወጥ ደስ ይላል፡፡
ከሺርክ እና ከቢድኣ በአላህ ፍቃድ ሰዎች እንደተለወጡት ሁሉ አሁን ደግሞ ስለ ነሺዳና መንዙማ ከቁርዓን አዘናጊነት ትምህርት ከተለቀቀ በኋላ አንድ የዩቲዩብ ተጠቃሚ እንዲህ ሲል ኮሜንት ፅፏል

"ውይ እኔ ነሺዳ ማዳመጥ አንድ ቁጥር ነኝ ቁርዓኑ ግን አንድ ሁለት ሱራ እደቀራሁ እንቅልፍ ይደፍኛል ……ከዛሬ ጀምሬ ስልኬ ላይ ነሺዳ ሚባል ሁላ አዎጣለሁ"

አልሐምዱሊላህ ገና ይቀጥላል ሙስሊሙ ኡማ ከጫትም ከሌሎችም መጥፎ ነገሮች በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ይለወጣል፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አላህ ሁሉን ሰሚ ነው፡፡
ዱኣ (ፀሎት) በአረብኛ ማድረግ በላጭ ነው፡፡ አረብኛውን ለማይችሉ በአማርኛ፣ በኦሮሚኛ፣በስልጢኛ፣ በጉራጊኛ፣ በትግሪኛ፣ በሀደሪኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ…. በማንኛውም ቋንቋ አላህን መለመን ይቻላል፡፡ ዱኣ ታላቅ አምልኮ ነው ትርጉሙን ተምረን አላህን እንለምነው፡፡ ዱኣን ትርጉሙን ካላወቅን ብዙም ጥፍጥናውን አናውቀውም፡፡ አላህ እውቀት ይጨምርልን፡፡ https://t.me/SadatTextPosts
ረመዳን ገና አላለቀም፣ እኛም ገና አልሞትንም፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ረመዳን ሲገባ አልሐምዱሊላህ መስጂዶች ሰው በደንብ አስተናግደው ነበር፡፡ አሁን ገና ረመዳኑ ሳያልቅ ትንሽ መቀነስ ይታያል፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩ አመታት ላይ እንደሚታየው ረመዳን ሲወጣ አብዛኛው ሰው ከመስጂድ ይርቃል፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ባረከላሁ ፊኩም ረመዳን ገና አላለቀም፡፡ ረመዳን አለቀ ቢባል እንኳን አንድ በበለጠ ሁኔታ ኸይር የሚሰራበት ወር አለቀ እንጂ ሌሎች አላህ የሚመለኩባቸው እና መልካሞች የሚሰሩበት እና ከመጥፎ የሚራቁባቸው ወራት እንደቀጠሉ ነው፡፡ ረመዳን ውስጥ በተለይ የተከበሩት የመጨረሻዎቹ ለይለቱል ቀድር ይገኝበታል ተብሎ የሚገመቱት አስር ቀናት አሉ፡፡ እባካችሁ ነቃ እንበል፡፡ እኛን አላህ የፈጠረን እስከለተ ሞታችን ድረስ እሱን በብቸኝነት እንድንገዛው ነው፡፡ አላህ ለሰው ልጆች ሁሉ ፈርጥ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አላቸው
[15:99] وَٱعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ ٱلْيَقِينُ
እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡
እሳቸውም የጌታቸውን ትዕዛዝ በመፈፀም እስከለተ ሞታቸው ድረስ የማይሞተውን ህያው አምላክ አላህ አመለኩት፡፡ ከዚህ አለም ሲለዩም የመጨረሻ ንግግራቸው
“አላህ ሆይ! ከላይኛው የጀነት ጓዶች አድርገኝ” የሚል ነበር፡፡
ታድያ ያለፈውንም የሚመጣውን ሁሉ አላህ የማራቸው የሰው ልጆች ሁሉ ፈርጥ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይህን ያህል ከለፉ እኛስ የሚል ጥያቄ ነፍሴንም እናንተም እየጥቃለሁ፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለሙኣዝ ኢብን ጀበል ሰላትን ከማጠናቀቁ በፊት “አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት ላይ፣ በማመስገን ላይ እና ያማረን አምልኮ ላንተ በመፈፀም ላይ አግዘኝ” እንዲል ጠቁመውታል፡፡
እኛም አላህን እንለምነው፡፡
አላህ ፅናት ይስጠን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በረመዳን ተውበት አድርገው በተመለሱ ወንድም እና እህቶች ላይ አታሹፍባቸው ምክንያቱም ይህ የመለወጫ ሰበባቸው ይሆናልና ኢንሻ አላህ ልክ አንተ/ቺ ከለታት በአንድ ቀን ውስጥ እንደተመለስከው/ሺው፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ከማንኛውም ወንጀል ተውበት በማናችንም ላይ ግዴታ ነው፡፡ ከወንጀል የተመለሱ ወንድም እና እህቶችን በማበረታታት እና መጥፎ ጓደኛዎቻቸውን እንዲርቁ በመምከር በሀቅ ላይ ይፀኑ ዘንድ ማበረታታት ይገባል፡፡
አላህ ሁላችንንም ንፁህ ተውበት ይለግሰን፣ በሃቅ ላይም ያፅናን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
ከሌሊቶች ሁሉ በላጭ የሆነችው ሌሊት በጀመርናቸዉ 10 የረመዳን መጨረሻ ሌሊቶች ውስጥ ትገኛለች — በርካታ ኡለሞቻችን እንደሚሉት ።
በርካታ ኸይሮች ያለባትን ይችን የተከበረች ሌሊት አትርፎባት ማለፍ የፈለገ አማኝ ከወዲሁ ጀምሮ ወገቡን ማጥበቅ ይጠበቅበታል — الله ለሚወዳቸው ስራዎች!!
ነብዩ እነዚህን ውድ ሌሊቶች ሽርጣቸውን ጠበቅ በማድረግ ( ከሚስቶቻቸው በመራቅና ኢባዳን በማብዛት) ፣ፈጣሪያቸውን በብርቱ በማምለክ ሳይተኙ ያሳልፏቸው ነበር!!

በተረፈ በነዚህ የተከበሩ ሌሊቶች ውስጥ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ከአገርና ከቤቶቻቸው የተፈናቀሉ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን እናስታውስ!! ዱዓ እናርግላቸው።
ወንድሞችና እህቶች አላህን እንፍራ!
ዱባዬች ተጠንቀቁ
ማንን ?
ካላችሁ
በየአመቱ ኢድ እና አረፋ በመጣ ቁጥር ሴት እና ወንዶችን አዳራሽ ላይ በመደባለቅ ከአዲስ አበባ ከመጡት "ሙነሺዶች" ጋር በመሆን በአሉን እናክብር በማለት ብራችሁን ከሚበዘብዙት እና አላህ የጠላውን* "ኢኽቲላጥ" (ሴት እና ወንድን መደበላለቅ) ከሚፈፅሙት የዲን ደጋዴዎች።

አላህ በሚመሰገንበት ቀን አላህን ስታምፁ እንድትውሉ እነዚህ ተሳስተው አሳሳቾች ይጠሯችኀል፣ ይጎተጉቷችኀል አትስሟቸው ራቋቸው።

ተጠንቀቋቸው ከነሱም አስጠንቅቁ።
https://t.me/SadatTextPosts