ቤተመንግስት ውስጥ ሰላት መስገድ?
ምድር ሁሉ የአላህ ናት፡፡ አንድ ሙስሊም ሰላት ወቅቱ ሲደርስበት አውሮፕላን ላይም፣ መርከብ ላይ የትም ይሁን የት ይሰግደዋል፡፡ ዱርዬ የሚባለው ሙስሊም እንኳን ሰላት ሲሰግድ ፎቶ አይነሳም፡፡ ዛሬ ዛሬ እነ ጋሽ ብርቂ ግን ቤተመንግስት ውስጥ መስገድ እንደ ትልቅ ጀብዱ ይቆጥሩታል፡፡ እሱንም በፎቶ ተነስተው “ቤተመንግስት ውስጥ ያለማንም ፍራቻ በሚገርም ሁኔታ ሰላቱን ሰገደ” ይባልላቸዋል፡፡ እውነት ቤተመንግስት ውስጥ ሰላት ለመስገድ እነሱ የመጀመሪያው ናቸው እንዴ? ወይንስ ከነሱ በፊት የሰገዱት እና ፎቶ ያልተነሱት ለጣኦት ነበር የሰገዱት? ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡
- አንድ ሰው እናቱን ቢስም እና ቢንከባከብ አላህ ስላዘዘው ነው፡፡ እሱ ብቻም አይደለም እናቱን የሚወደው፡፡ እነ ጋሽ ብርቄ እናታቸውን ለመዘየር ሲሄዱ ካሜራ ማኖቻቸው አሉ፡፡ የእናታቸው ጉልበት ሲስሙ ካሜራ ማኖቻቸው ቀጭ አድርገው ያነሷቸዋል፡፡ እነሱም አይከለክሉም፣ ከዛም ያቺ ፎቶ “አሚራችን እናቱን ሲስም፡፡ ጀነት በእናት እግር ስር ናት” የሚባል መለወሻ ተጨምሮባት ትለቀቃለች፡፡
- እነ ጋሽ ብርቄ መስጊድ ውስጥ ገብተው ህፃናትን ከኋላቸው አድርገው እራሳቸውን ሰልፊ ያነሳሉ፡፡ ከዛም ሶሺያል ሚድያ ላይ ይለቁታል፡፡
- እነ ጋሽ ብርቂ አረብ ሀገር ካሉ ሴቶች ተሰብስቦ የመጣውን ብር ለደሃ ሲሰጡ ልክ ፖለቲከኞች እርዳታ ሲሰጡ ፎቶ እንደሚነሱት እነሱን ይነሳሉ፡፡
- እነ ጋሽ ብርቄ የውሃ ቦቴ ትልቅ መኪና ውስጥ በካሜራ ለማንሳት አልታይ ሲላቸው በሹፊሩ በኩል ያለውን በር ከፍተው ይነሳሉ፡፡ የሚያሳዝነው ካሜራ ማኖቻቸው መሰላል ላይ ቢወጡም መስታዎቱ ስለሚከልላቸው የሹፊሩን በኩል በር ከፍተው አጅሬ የከባድ መኪና መሪ ይዞ ፎቶ ይነሳል፡፡
- ከሁሉ የሚገርመው እነ ጋሽ ብርቄ ለድሆች የሚሰጥ እህል ተሸክመው ፎቶ ለመነሳት ያለ አቅማቸው ሁለት ሰው የሚሸከመውን ለብቻቸው እሸከማለሁ ሲሉ ወደቀባቸው፡፡ ይህም በቪድዬ ተቀርፆ ፌስ ቡክ ላይ ተለቀቀ፡፡
ከነሱ ሌላ ለድሃ የሚረዳ እንደሌለ፣ ከነሱ ሌላ ለዲኑ የሚለፋ እንደሌለ፣ ከነሱ ሌላ በሽተኛ የሚጠይቅ እንደሌለ በፎቶ እና ቪድዬ ፕሮፖጋንዳ ልክ እንደ ፖለቲከኞች ህዝቡ ላይ ሊደግሙበት ይፈልጋሉ፡፡
ማንን አስበው ይሆን ስራን የሚሰሩት ቤተመንግስት፣ ሀረም፣ ዋይት ሀውስ፣ ባህርም ላይ፣ ሰማይም ላይ አላህ ይመለካል፡፡ አንድ ሰው ደግሞ አላህን የሚያመልከው ለእራሱ ሲል እንጂ ለሰዎች ሲል አይደለም፡፡ አንድ ሰው ቤተመንግስትም ይሁን ዩናይትድ ኔሽን ላይ የሚሰግደው ለነፍሱ ሲል ነው፡፡ ጀብዱም አይደለም ግዴታ እንጂ፡፡
ይልቁንስ ትላትን “የተቃውሞ ሰልፉን የሚቃወሙ የመንግስት ቅጥረኛ ናቸው፡፡” ሲሉ እንዳልነበር ዛሬ ቤተመንግስት ድረስ ግብዣ ተደርጎላቸው ገብተዋል፡፡
የሱና ኡለማዎችን “የቤተመንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች” ሲሉ ነበር፡፡
እነ ጋሽ ብርቂ ቤተመንግስት ሲገቡም ተከታዬቻቸው ጥያቄ እንዳያነሱ “ለኢስላም ነው፡፡” የሚል ቅብ ይቀቡላቸዋል፡፡ ከመንግስት ጋር ሲጣሉም “ተው እንጂ ከመንግስት ጋር ጓደኛ አይደላችሁ እንዴ?” ሲባሉ “ኢስላም አደጋ ላይ ስለወደቀ ነው” የሚል ቅብ ይቀቡታል፡፡
አላህ ግን ምስጋና ይገባው እነዚህ ሰዎች የያዙትን ይፋ እያደረጉ አላህም እያጋለጣቸው ሙስሊሙ ቀስ በቀስ እያጋለጣቸው ነው፡፡
ትላንት ሀሰን ታጁ አብሯቸው ነበር፡፡ መሃል ላይ የተለያዩ መሰሉ፡፡ ዛሬ ደግሞ አብረው ቤተ መንግስት ገቡ፡፡
ቤተመንግስት መግባት ለነሱ ሲሆን ………..?
አላህ ሆይ! ኡመተል ኢስላምን ከማታለል ባንተ እንጠበቃለን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts

የረመዳን ቱሩፋቶች
1) የጀነት በሮች ይከፈታሉ፣ የጀሃነም በሮች ይዘጋሉ፣ ሰይጣናት ይጠፈራሉ፣
2) አምኖ እና ሂሳቤን አላህ ይከፍለኛል ብሎ ለፆመው ወንጀል ያስምራል፣
3) ትክክለኛ ፆም አላህን መፍራት ያላብሳል፣
4) ከ 1000 ወራት የምትበልጠዋ ልዩ ለሊት በረመዳን ውስጥ ትገኛለች፣
5) በረመዳን ወር ኡምራ ማድረግ ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር ሀጅ እንደማድረግ ይቆጠራል፣
6) ፆም የቸርነት ወር ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቸር ነበሩ፣ ይብልጥ ደግሞ በረመዳን ቸር ነበሩ፣
7) ፆም ጋሻ ነው፣
8) ፆመኛ ሰው ሁለት ደስታ አለው አንድ ሲያፈጥር ሁለት ጌታውን ሲገናኝ፣
9) ፆም ያማልዳል፣
10) ረመዳን የአንድነት ወር ነው እና ሌሎችም፡፡
አላህ ረመዳን ደርሰው ከሚጠቀሙበት ያድርገን፡፡

ረመዳን አልደረሰምን….?
ጠለሃ ኢብን ኡበይዳህ (ረድየላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት
ሁለት ሰዎች ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጥተው በእኩል ወቅት እስልምናን ተቀበሉ፡፡ አንደኛው ከሌላኛው በላይ ጂሀድ ላይ ይሳተፍ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ጀሀድ ተሳትፎ ሰመኣት ሆነ፡፡ ሌላኛው ከዚህኛው አንድ አመት ያህል ቆይቶ ከዛም ሞተ፡፡
ጠለሀ እንዲህ አለ
“በህልሜ የጀነት በር ላይ ሆኜ አየሁ፡፡ ከሁለቱም ጋር ነበርኩ፡፡ አንድ ሰው ከጀነት ውስጥ መጥቶ ዘግይቶ የሞተውን ቀድሞ እንዲገባ አደረገው፡፡ ከዛም ድጋሚ መጥቶ ሰመኣቱን እንዲገባ አደረገው፡፡ ከዛም ተመልሶ መጣና አንተ ተመለስ ጊዜህ አልደረሰም አለኝ፡፡”
ጠለሀ (ከእንቅልፉ) ከነቃ በኋላ ለሰዎች ስለ ሁኔታው ተናገረ፡፡ ሁሉም ተገረሙ፡፡ ይህ ጉዳይ መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጋር ደረሰ፡፡ ለመልክተኛውም ጉዳዩ ሲነገራቸው
እሳቸውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
من أي ذلك تعجبون؟ قالوا: يا رسول اللهّ هذا كان أشد الرجلين اجتهاداً ثم استشهد ودخل هذا الآخر الجنة قبله فقال رسول الله (صلى الله عليه وسلم) : أليس قد مكث هذا بعده سنة؟ قالوا: بلى. قال: أدرك رمضان فصام وصلى كذا وكذا من سجدة في السنة؟ قالوا: بلى. قال رسول الله (صلى الله عليه وسلم): فما بينهما أبعد مما بين السماء والأرض
“ምንድን ነው የሚገርማችሁ?”
እነሱም አሉ
“የ አላህ መልክተኛ ሆይ! ከሁለቱም ይህኛው በጣም ታግሏል (በጂሃድ) ሰመኣትም ሆነ፡፡ ነገር ግን ይህኛው ቀድሞት ጀነት ገባ፡፡”
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ከሱ በኋላ አንድ አመት ወደ ኋላ አልቀረምን?” አሉ
እነሱም “አዎ ቀርቷል” አሉ
እሳቸውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ረመዳን አልደረሰምን፣ አልፆመምን፣ ይህን ይህን ያህል ሱጁዶች በዚህ አመት አልሰገደምን?” አሉ
እነሱም “አዎን (ደርሷል)” አሉ
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “በሁለቱ መሃል ያለው ልዩነት በሰማይ እና ምድር ካለው ልዩነት ይበልጣል” አሉ
ኢብን ማጃህ የዘገቡት ትክክለኛ ዘገባ (2/345 346) እና አልባኒ አስ-ሲልሲላህ አስ-ሰሂሃ
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ረመዳንን በአግባቡ እንጠቀምበት፡፡ ይህን ያህል ታላቅ ምንዳ አለው፡፡

ሙነሺዶቹና ፊልም ሰሪዎች ለምን ረመዳንን ይመርጣሉ?
እነሱ የፈለገ መልካም አስበን ነው ቢሉም ሙስሊሙን ከረመዳን ወር እያዘናጉት ነው፡፡
ውዴታ በተግባር ይገለፃል፡፡
ረመዳን ቁርዓን የወረደበት፣ ሰይጣን የሚታሰርበት፣ የጀነት በሮች የሚከፈቱበት፣ የእሳት በሮች የሚዘጉበት፣ ቁርዓን በብዛት የሚቀራበት፣ ተራዊህ የሚሰገድበት፣ ሰደቃ የሚበዛበት ታላቁ የአምልኮ ወር ነው፡፡
ሰይጣን እና ሰራዊቶቹ “ከአላህ ጋር ልናጣላችሁ ነው” ብለው በግልፅ ቢመጡ ማንም አይቀበላቸውም፡፡ እነሱ ግን ይህን አይደለም የሚያደርጉት ይልቁንስ ከዚህ በተገላቢጦሹ አዛኝ፣ መካሪና ተቆርቋሪ መስለው ነው እራሳቸውን የሚያቀርቡት፡፡ ሰይጣን አደም እና ሀዋን አላህ የከለከላቸውን ፍሪ እንዲበሉ ሲጎተጉት እንዲህ ነበር ያላቸው
وَقَاسَمَهُمَآ إِنِّى لَكُمَا لَمِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ
“እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ” ሲልም አማለላቸው፡፡
ተመልከቱ “እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ” ሲል ሽነገላቸው፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ እስቲ ተመልከቱ በዚህ በተከበረ ወር ሰዎች ቁርኣንን እንዳይቀሩ ለማዘናጋት “ኢስላማዊ ፊልም፣ ኢስላማዊ ነሺዳ፣ ኢስላማዊ ድራማ” እየተባለ ሰዉን ያዘናጉታል፡፡
አስገራሚው በአላህ ፍቃድ ከዘፈን የተመለሰው ሙሐመድ አወል ሳላህ ዛሬ ፂሙን ላጭቶ “ዉዴታ እስከ ጀነት” ሲል ይሰብካል፡፡ ሙኣዝ የተባለው ደግሞ ፀጉሩን ፓንክ ተቆርጦ “እኔን” ይላል፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ፂማችሁን ልቀቁት፣ ቀድሞ ቀመሳችሁን (ከንፈር ላይ ያለውን) ቁረጡት” ሲሉ ያውም ዛሬ እንደ ሙሐመድ አወል ሳላህ ያሉት ኢስላማዊ ሙነሺድ ተብለው የነብዩን ትዕዛዝ ተቃርኖ ፂሙን ይላጫል ሱሪውንም ይለቃል፡፡ ሙኣዝም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ፀጉራችሁን ስትቆረጡ አንዱን ካንዱ አታበላልጡት” የሚለውን የነብዩ ትዕዛዝ ጥሶ “ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ” ሲል ይቀጣጥፋል፡፡ አሳዛኙ የአላህ መስጂድ ቤቶች በሮቻቸው በእንዲህ አይነት ግለሰቦች ፎቶ ተበላሽተዋል፡፡ የአላህ ቤቶች ከማንኛውም ምስል መፅዳት ሲገባቸው፡፡
እንደሚታወቀው ረመዳን ሲወጣ ብዙ ሰዎች ከመስጂድ እና ከመልካም ነገሮች ይርቃሉ፡፡ እንዲህ አይነት በሽታዎችን በአላህ ፍቃድ የሚያሽረው የጌታችን የአላህ ቃል ቁርኣን ነው፡፡ እነዚህ መንዙማ፣ ነሺዳ ባዬች፣ ፊልም አክተሮች ከመስጂድ ርቆ የነበረውን ሙስሊም የአላህን ቃል እንዳይቀራ፣ እንዳያዳምጥ ጋሬጣ ሆነውበታል፡፡
ቁርኣን ፀጥ ብሎ ላዳመጠው የአላህን እዝነት ያስገኛል፡፡ ከቀራው በእያንዳንዱ ሀርፍ 10 ያስከፍላል፡፡ ፊልም የሚሉት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ አይመልከት፣ ሴት ልጅ ወንድ ልጅን አትመልከት” ያሉትን ነብያዊ ትእዛዝ ተቃርኖ በውሸት ገፀ ባህሪ ሙስሊሙን ያጠማል፡፡ አጅር አይገኝበትም፡፡ ሙነሺድ ተብየዎቹም በሸሪኣ የተቀመጠው ግጥም ሆኖ ሳለ ይዘፍናሉ፣ ያዜማሉ….. የመሳሰለውን፡፡ ይህም ለሙስሊሙ ምንም አይፈይድም፡፡ ምክንያቱም አንድ አምልኮ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ኢኽላስ እና ሙታበኣን (የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና ገጥሞ መገኘት አለበት) ሊኖረው ግድ ይላል፡፡
ከማንም በላይ አላህን እና መልክተኛውን በተግባር ወደው ያሳዩን ሰሃባዎች በረመዳንም ይሁን ከረመዳን ውጭ ፊልምና ድራማ እየሰሩ ሱሙንም “ኢስላማዊ” እያሉ አልነበረም፡፡ ኢስላማዊ ነሺዳ ብለውም የእራሳቸውንም ከነሱ በኋላ የመጡትን ጊዜ አላባከኑም ነበር፡፡
ፊልም፣ ነሺዳ፣ መፀሀፍ ምርቃት እያሉ ቲያትር ቤት ሰዎችን ጠርተው ወንድ እና ሴቶችን ያለ መጋረጃ ሳይለዩ በተለያየ ረድፍ አስቀምጠው ለፈተና መዳረግ መሰልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው፡፡
አላህን እንፍራ፡፡
ዉዴታ በተግባር ይገለፃል፡፡ ሰሃባዎች ከእኛ በላይ አላህን እና መልክተኛውን ይወዳሉ፡፡ እነሱ ረመዳናቸውን በቁርኣን፣ በተራዊህ በሰደቃ እንዳሳለፉት እኛም እናሳልፍ፡፡
መልካም ሁሉ ሰለፉነ ሷሊሂንን በመከተል ላይ ነው፡፡ መጥፎ ሁሉ መጤ መንገዶች እና አስተሳሰቦችን በመከተል ላይ ነው፡፡

ኡማው ረመዳንን ለመቀበል ቁርኣንን ለመቅራት … ደፋ ቀና ይላል ደፋሮቹ ኡማውን ከቁርኣን ለማዘናጋት
“30 FFAA EEBBA NASHIIDAA” “30ኛ የነሺዳ ምርቃት” ብለው ዘንድሮም እንደለመዱት ለረመዳን ብቅ አሉ፡፡ አስገራሚው ካፊሮች፣ ፖለቲከኞችም ጭምር የነሺዳው ምርቃት ላይ መሳተፋቸው ነው፡፡ ይህ ስራቸው ከሀይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ይሀው ተግባራቸው እራሱ ያሳያል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው በዲን ሽፋን የሚነግዱበት ህዝብ ነው፡፡ በአላህ ፍቃድ ህዝቡ እያወቃቸው ነው፡፡ በአላህ እገዛ እኛም እነሱ እንዲህ ዲን ሲያበላሹ እያየን ዝም አንላቸውም፡፡
አላህ ከነዚህ ሰዎች ተንኮል ይጠብቀን፡፡

ቁርኣን በ አንድ ሀርፍ አስር ሀሰና እንዳለው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ነግረውናል፡፡
መንዙማ እና ነሺዳ ያውም ሺርክ፣ የሙዚቃ መሳሪያ፣ ፉጨት፣ ጭፈራ የተደባለቀባቸው ምን ምንዳ ይኖራቸዋል?
አደለም ምንዳ ሊያስገኙ ያስቀጣሉ፡፡
ቁርኣንን አደለም መቅራቱ ፀጥ ብሎ መስማቱ የአላህን እዝነት እንደሚያስገኝ አላህ ነግሮናል፡፡
ታድያ ለምን ይሆን የኪሳራ መንገድ የሆነውን መንዙማ እና ነሺዳ በሚጮህ ስፒከር ታክሲ ላይ ተጭኖ ከተማ እየዞሩ ህዝቡን የሚረብሹት?
ታድያ ለምን ይሆን በዚህ በተከበረ የረመዳን ወር ሙስሊሙ የአላህን ቃል ቀርቶ በአንድ ሀርፍ አስር ሀሰና እንዳያገኝ የሚያዘናጉት?
አላህ ሆይ! ቀጥተኛውን መንገድ እኛንም እነሱንም ምራን፡፡

የሚለፉለትን ነገር ይወቁ።
ስራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኘው ለአላህ ብቻ ተብሎ የተሰራና በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና መሰረት ሊሆን ግድ ይለዋል። አለበለዚያ ትርፉ አመድ አፋሽ መሆን ነው። በአላህ ፍቃድ ዋና ለዛሬ ማንሳት የፈለግኩት ረመዳን ላይ በዲን ስም ስለሚሰሩ ቢድአ (በዲን መሰረት የሌላቸው) ፈጠራዎች ነው።
ዚክርን የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደነገጉት መንገድ እና ሁኔታ መፈፀም እራሱ ስራውን አላህ ዘንድ ውድቅ ያደርገዋል። ለዚህም ማስረጃው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ ነው
"የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው (ውድቅ ነው)"።
ታድያ አንተ/ቺ የአላህ ባርያ ሆይ! በአንዳንድ መስጂዶች በጀመአ ኢማሙ እያወጣ መእሙሙ እየተቀበሉ
1) አሽሀዱ አን ላ ኢላሃ ኢለላህ፣ አስተግፊሩላህ፣
2) ነስአሉከል ጀነተ ወናኡዙ ቢከ ሚነናር፣
3) አስተግፊሩላህ 100 ጊዜ
እና የመሳሰሉትን።
ልብ በሉ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ከላይ ያሉት ትክክለኛ ዚክሮች ሽርክ የሌለባቸው የተውሂድ ቃላቶች ከመሆናቸውም ጋር ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲፆሙ እነዚህን ዚክሮች አገራችን ላይ እንደምናየው አይሉዋቸውም ነበር።
"የእኛ ትእዛዝ የሌለበት ስራ የሰራ ሰው ስራው ውድቅ ነው" ባሉት መሰረት እነዚህ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው ያልሰሩትን በመስራት ወደ አላህ እቃረባለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ በነፍሱ ላይ እየፈረደ ነውና ሳይመሽበት ይቶብት።
ፆምና ሌሎች ኢባዳዎችን አጥፊ የሆነው ደግሞ አንዳንድ መስጂዶች ላይ
1) "አጊስና ያረሱለላህ" (አጠጡን አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ)
2) "ኹዝ ቢየዲ ያረሱለላህ" (አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! እጄን ያዙኝ)
እንግዲግ እነዚ 2 ስንኞች እና መሰሎቻቸው ለብቸኛው ፈጣሪ አላህ ብቻ የሚገባውን ፀሎት ፍጡር ለሆኑት ነብዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚሰጡ ናቸው።
ሽርክ ማለት ደግሞ አላህንም እያመለኩ ሌሎች አካላትን (መላእክት፣ ነብይ፣ ሰሃባ፣ ሷሊሆችን፣ ጂን —-----) አብሮ ማምለክ ነው።
በአላህ ላይ እያጋራ የሞተ ሰው የእሳት ነው። በአላህ ላይ ለሚያጋራ ሰው ፆምም፣ ሀጅም አይጠቅመውም። ስለዚህ የሽርክን አደገኝነት ተገንዝበን ማህበረሰቡን እንደ ሰበብ እናንቃ።
ዲናችን ሀብታችን ነውና ስራችንን በኢኽላስና በሱና በማስጌጥ፣ ከሽርክና ቢድአ ከነባለቤቶቻቸው በመረቅ ለነፍሳችን እንዘን።
ሽርክና ቢድአ አደጋቸው ከባድ ነው።

የጫት እርሻዎች በእህል እርሻ ከተቀየሩ ህዝቡ ከረሀብ ወጥቶ በምግብ እራስን ለመቻል እና እንደነ ዳቦ ያሉ የስንዴ ውጤቶች ለድሀው ህዝብ ቅናሽ ዋጋ ለመቅረብ ሰብብ ይሆናል፡፡
አላህ ይህንን እርኩስ ትውልድን የገደለ ቅጠል ከምድረ ገፅ ያጥፋው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አላህ ይህንን እርኩስ ትውልድን የገደለ ቅጠል ከምድረ ገፅ ያጥፋው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ዘሬን ከሃይማኖቴ አላስበልጥምም፣ እኩልም አላደርግም፡፡
አላህ እውቀት ይስጠን፡፡
እንዴት ነው አንድ ሰው ኢስላምን ከዘሩና ከሀገሩ እኩል የሚቆጥረው?
ኢስላም አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ብቸኛ ሃይማኖት ነው፡፡ ኢስላምን የያዘ ሰው ከአሳማሚ እሳት ተጠብቆ፣ ያችን ታላቅ ሀገር ጀነት በአላህ ፍቃድ ይወርሳል፡፡ አንድ ሰው እምነቱ ካልተሰተካከል አይደለም ዘሩ፣ ዘር ማንዘሩ ቢሰበሰብ ከጀሀነም እሳት መውጣት አይችልም፣ ያችን ውድ ሀገር ጀነትንም አይወርስም፡፡
ሰው ስሜቱን ማምለክ ሲጀምር እንዲህ አይነት ከባድ እምነቱን የሚነካ አደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ስራው (ከጀነት) ያስቀረውን ዘሩ አያስቀድመውም፡፡” ብለዋል፡፡
ሀገር እና ብሄር ከሃይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም፡፡ አንድ ሰው ሙስሊም ሆኖ ከዛም በተጨማሪ ቁረይሽ እና አረብ ብሎም ሳውዲያዊ ቢሆን ሳውዲያዊ፣ አረብ፣ ቁረይሽ መሆኑ ምንም አይጨምርለትም፡፡ ልክ እንደዚሁ አንድ ሀገራችን ላይ ያለ ግለሰብ የሆነ ብሄር ቢሆን እስልምናውን አጥብቆ መያዝ ብቻ እንጂ አላህ ዘንድ ከእሳት ተጠብቆ ጀነት እንዲገባ የሚያደርገው ብሄሩ ወይም ኢትዬጵያዊነቱ ከእስልምና ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ይህን ታላቅ የነብያቶች ሁሉ ሃይማኖት ከብሄር እና ሀገር እኩል አድርጎ ማቅረብ የመሃይምነት ጥግን የሚያሳይ ነው፡፡ እንጠንቀቅ፡፡
አልሐምዱሊላህ እኔ ሃይማኖቴን ከዘሬም ከሀገሬም አላስቀድምም፣ እኩልም አላደርግም፡፡ የእኔ ሰውነት ከእንስሳ በላይነት የተረጋገጠው በእስልምናዬ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ታላቁ ሰሃባ ቢላል (ረድየላሁ አንሁ) እራሳቸውን አረቦች የነብየላህ ኢስማኢል (አለይሂ ሰላም) ዘሮች ነን የሚሉት ሰዎች ዘንድ እንደ ባሪያ ነበር የሚታየው፡፡ እሱ ግን አላህ ዘንድ ታላቅ ሆነና ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ መሰከሩለት “ጀነት ላይ የእግርህን ኮቴ ሰማሁት”፡፡
ቢላል (ረድየላሁ አለንሁ) በሀበሻነቱም፣ በጥቁርነቱም አልነበረም ጀነት ላይ ኮቴው የተሰማው፡፡ ነገር ግን በእስልምናው ብቻና ብቻ እንጂ፡፡
አላህ ሆይ! እኛንም ዝርያዎቻችንንም ከዘረኝነት በሽታ አፅዳን፡፡ አላህ ሆይ! የመሃይምነት ዘመን መገለጫ ከሆነው ዘረኝነትም በአንተ እንጠበቃለን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

ፖለቲካ አልናፈቀንም፡፡
ሙስሊሞችን በኢስላም ሽፋን ማታለል ይቁም፡፡
ይገርማል?
መልክተኞች ሁሉ የተላኩት በሽርክ ጨለማዎች ውስጥ የተዘፈቁትን ህዝቦች ወደ ተውሒድ ብርሃን በአላህ ፍቃድ ለመምራት ነበር፡፡ መልክተኞችን የተከተሉ የእውቀት ባለቤቶችም በዚሁ በመልክተኞች ፋና ላይ ነበር የተጓዙት፡፡
ዛሬ በተገላቢጦሹ አላህ ካዘነላቸው ጥቂት የነብያት ተከታዬች ውጭ፣ የነብያትን ፈለግ ተቃርነው የሚከተሉት ከባባድ ሽርክ ጨለማዎች እና ተግባሮች አገራችንም ላይ ይሁን አለም ላይ እያሉ እነሱ ወደ ሌላ አርስት የሚጣሩ በጣም ብዙ አሉ፡፡ ገርሞ የሚገርመው ሀገራችን በሺርክና ቢድኣ ተወራ ስታበቃ “የናፈቀን ፖለቲካ ነው፡፡” ብለው የሚደሰኩሩ ጠሞ አጥማሚዎችን ማስማታችን ነው፡፡ መስጂድ ውስጥ እንዲህ አይነት እርኩስ ንግግሮችን መናገር ደግሞ አደጋውን ያከፋዋል፡፡
ፖለቲካ የጠማው ካለ ሙስሊሞችን ለቀቅ አድርጎ፣ ኢስላምን ለፖለቲካው አላማ ሳያውል እዛው እራሱን ወክሎ ይደስኩር፡፡ እኛ ሙስሊሞች የአላህ መልክተኛ በሄዱበት መንገድ በመሄድ ኡመተል ኢስላምን ከምንም በፊት ከጌታው ጋር በማስተዋወቅ፣ ሺርክና ቢድኣ የተባሉትን ዋና ነቀርሳዎች በአላህ ፍቃድ ከኡመቱ ላይ በመፈንቀል ወደ ተሻለው መንገድ እንጓዛለን፡፡
እስቲ ምን ይሆኑ እነዚህ ሽርኮች፡፡ በአላህ ፍቃድ አገራችን ላይ ካለው ሽርክ ዘልዬ አልወጣም፡፡
- ነጃሺ ቀብር ላይ የሚሰራው አስፀያፊ ሽርክ፣
- ጎንደር ላይ የሚመለከው “የአሊ ጎንደር” ቀብር፣ አባድር…..
- ጎጃም ላይ “እኔ ኢንቨስተር እንጂ ሸህ አደለሁም” ያለውን ሸህ ማምለክ፣
- ጎጃም አዴት “ለውሻ” የሚፈፀመው አመታዊ እርድ፣
- ጎጃም ዳንግላ…..
- ጎጃም ቲጃኒያ….
- ወሎ “የቦረናው ደግዬ እርዱኝ አባብዬ”፣
- ወሎ ሌሎች ብዙ ቦታዎች ላይ ሽርክ…...፣
- ቡሬ የቲጃንዩ ሸህ……
- “የሸህ ሁሴን ጂብሪል ትንቢት” የሚባለው ጥንቆላ
- የጅማ አባጅፋር መውሊድ፣
- አዲስ አበባ ጉለሌ እስላም መቃብር….፣
- አዲስ አበባ ብዙ ጠንቋይ ቤቶች…..
- በጉራጌ “ቃጥባሬ”፣ “አብሬት”….
- በስልጤ “አልከሶ”…
- ድሬ ባሌ ኑር ሁሴን….
- ለጅብ ገንፎ አግንፍቶ ማቀዋደስ፣
- አንበሶ፣ ሰይፉ ጨንገሪ፣ አዳል ሞቴ፣ ወሰን፣ ሮመዲ፣ ዘባንያ እና የመሳሰሉት እርድ የሚፈፀምላቸው ሰይጣናት….
- አባድር በሃረር…. “አባድር ፆም አያሳድር” የሚባል የክህደት ንግግር፣
እና የመሳሰሉትን፡፡ እዚህ ጋር የጠቀስኳቸው ቀብራቸው ላይ ጠዋፍ የሚደረግ፣ ከአላህ ውጭ ድረሱልን እየተባሉ የሚጠሩ፣ ስለት የሚገባላቸው፣ መውሊድ እየተባለ ባወጡት ቀን የሚከበርላቸው እና የመሳሰለውን ነው፡፡
አሳዛኙ ብዙ ዱዐቶች እነዚህ ሁሉ ሽርክ ከሚሰሩባቸው ክፍለ ሀገራት ነው ተወልደው ያደጉት፡፡ የመጀመርያ ጥሪያቸውም ተውሒድ ነበር መሆን የነበረበት፡፡ ግን እነሱ አደራቸውን በልተው ተውሒድ ካልተስተካከል ምንም ጥቅም የሌላቸውን አርስቶች ሲደጋግሙ ይታያሉ፡፡
መንዙማ እየተባለ
- “ያቀመረል መካ አሰላሙ አለይካ ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ”፣
- “ሀቢቢ ሀቢቢ ሀቢቢ መዲና ና ይበሉኝ”፣
አረ ስንት ማለት ይቻላል፡፡ እነዚህ ለምሳሌ በቂ ናቸው፡፡ አንዱ ሽርክ ስራዎችን ሁሉ አፈር ከድሜ ለማስገባት በቂ ነው፡፡ ተመልከቱ ህያው አላህን ትተው በሞቱት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲመኩ፡፡
አላህ ግን እንዲህ ብሎን ሲያበቃ
وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱلْحَىِّ ٱلَّذِى لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِۦ ۚ وَكَفَىٰ بِهِۦ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرًا
በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ (አላህ) ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡
ሌላው ይህን ምድር በብቸኝነት የሚያስተናብረው አላህ ሆኖ ሳለ አላህን ትተው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) “መዲና ና ይበሉኝ” ብለው ይጠይቃሉ፡፡
አሳዛኙ ግን አብዛኛዎቹ ዱዐት የተባሉት ሰዎች አይደለም ይህን ሽርክ ሊቃወሙና፣ የእንደዚህ አይነት ሽርክ አቀንቃኞችን ቻናላቸው ላይ የኢድ ባዕል “እንግዳ” አድርገው ያቀርባሉ፡፡
ሱብሃነላህ፡፡ አላህ እኛንም እነሱንም ይምራን፡፡
ታድያ ይህ ሁሉ ሽርክ የሚፈፀምበት አገር ላይ ተቀምጦ ተውሒድን ማስተማር ሲገባ ከዚህ አርስት ውጭ ሌላን አርስት መተንፈሱን ምን አመጣው?
እውነት ለኡማው ታስቦ ነውን?
ለኡማው እማ ከአላህ እና ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የበለጠ ያዘነለት የለም፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሽርክን አስጠንቅቀው ወደ ተውሒድ ተጣርተው ነበር ዳእዋቸውን የከፈቱት፣ በዛም ላይ የሞቱት፡፡
አሳዛኙ የነብዩላህ ኑሕ (አለይሂ ሰላም) ህዝቦች የጠፉት በሽርክ ሰበብ ነበር፡፡ ዛሬ አብዛኛው ዘንድ ይህን ሁሉ ሽርክ፣ ቢድዐ፣ ፍልስፍና እና ወንጀሎች ተሸክሞ “ድል ናፈቀን” እና የመሳሰለውን ቃል ከአፋቸው ሲያወጡ፣ እነዚህ ሰዎች አእምሮዋቸው ይሰራል ወይ? ያስብላል፡፡ ምክንያቱም መጀመርያ ይህን የሚያክል ሽርክ ፊት ለፊታችን አፍጥጦ ተቀምጦ እሱን ከመዋጋት ይልቅ አድበስብሰው እያለፉ ከዛም “ነስሩ ቅርብ ነው” እያለ በየሶሻል ሚድያው እና በየመድረኩ የሚደሰኩር ሳይ ግርም ይለኝል፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለ “ድል” አያውቁም ወይ?
ከሽርክ እና ከቢድዐ ፀድቶ በተውሒድ እና ሱና ላይ ከመኖር የበለጠ ምን ድል አለ?
እስቲ ይህችን ነጥብ ልብ እንበል፡፡ አላህ እዝነቱ ካፊሩንም አማኙንም፣ ሙናፊቁንም ሙኽሊሱንም፣ ሱንዩንም ሙብተዲውንም፣ እንስሳውንም ያጠቃለለ ነው፡፡ ድልን ግን ከሸርጥ ጋር ነው ያደረገው፡፡ ተውሒዳቸውን አሟልተው የኖሩ ሰዎች በዱንያ ላይ መመራት አላቸው፣ በአኸይራ ላይ ደህንነት አለላቸው፡፡ ከእሳት ተጠብቀው ጀነት ይገባሉ፡፡ አላህ ከነሱ ያድርገን፡፡
ሽርክ እና ቢድዐን አዝሎ ሌላ ነገር ማውራት እብደት፣ ድንቁርና፣ መሃይምነት ነው፡፡
አላህ መመልከቻ ልቦና ይስጠን፡፡
እነዚሁ ፖለቲካ ተጠምተናል የሚሉ ግለሰቦች እንዲህ የያዙት መንገድ ልክ እንዳልሆነ ሲጋለጡ “በኢስላም ፖለቲካ የለም ልትሉን ነውን?” ይላሉ፡፡ እኛም እንዲህ የሚል መልስ እንሰጣቸዋለን እውነተኞች ሁኑ አታጭበርብሩ፡፡ በኢስላም ያለው ፖለቲካ በሁሉ ጉዳይ አላህ እና መልክተኛውን ፈራጅ ማድረግ እንጂ ዛሬ እናንተ ልታቦኩት የተዘጋጃችሁት እና የቋመጣችሁለት ሰው ሰራሽ ህግ አይደለም፡፡
እውነተኞች እንደሆናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ፡፡

ከ 200 በላይ የድምፅ ዳእዋ ፋይሎች ከሚከተለው የቴሌግራም ቻናል ያግኙ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
Rabbi siif haa kennu
ውንድሜ ፉአድ ሙሐመድ (አላህ ይጠብቅህ) በኦሮሚኛ ስለ ነሺዳ ባስተማርከው ትምህርት አላህ ይቀበለህ፡፡ ባስተማርክበት ቋንቋ Rabbi siif haa kennu፡፡ ኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪ እና አዳማጭ የሆናችሁ የተከበራችሁ ወንድም እና እህቶቼ እንስቲ ይህን በኦሮሚኛ ተናጋሪ ወንድሞቻችን የተከፈተ ቴሌ ግራም ቻናል ጆይን ብላችሁ ከሚሰጡት ትምህርት ተጠቀሙ፡፡
https://t.me/daawaa_fi_barnoota
ወንድማችን ስለ ነሺዳ ያስተማረበትን ሙሐደራ ለማዳመጥ የሚከተለውን ሊንክ ክሊክ አድርጉ
https://t.me/daawaa_fi_barnoota/184

Telegram
Da'awaa Fi Barnoota Afaan Oromoo
Chaanaaliinkun Barnootaafi Da'awaalee Tu Irrati Barsiifama ustaazoota Sunnaa Gara Garaatiin.
➢Ustaaz Abuu Muslim Al-Aruusii
➢Ustaaz Fu'aad Muhammad #Fi
➢Ustaaz Ismaa'iil Umar
Chanaalii Sheer Gochuu hin Iraan fatinaa.

አልሐምዱሊላህ ሰው እንደዚህ ሲለወጥ ደስ ይላል፡፡
ከሺርክ እና ከቢድኣ በአላህ ፍቃድ ሰዎች እንደተለወጡት ሁሉ አሁን ደግሞ ስለ ነሺዳና መንዙማ ከቁርዓን አዘናጊነት ትምህርት ከተለቀቀ በኋላ አንድ የዩቲዩብ ተጠቃሚ እንዲህ ሲል ኮሜንት ፅፏል
"ውይ እኔ ነሺዳ ማዳመጥ አንድ ቁጥር ነኝ ቁርዓኑ ግን አንድ ሁለት ሱራ እደቀራሁ እንቅልፍ ይደፍኛል ……ከዛሬ ጀምሬ ስልኬ ላይ ነሺዳ ሚባል ሁላ አዎጣለሁ"
አልሐምዱሊላህ ገና ይቀጥላል ሙስሊሙ ኡማ ከጫትም ከሌሎችም መጥፎ ነገሮች በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ይለወጣል፡፡