ግልፅ በሆኑ ጉዳዬች ላይ “የአዋቂዎች” ዝምታ አይገባም፡፡
ዛሬ ዛሬ ግልፅ ጥፋቶችን እያዩ ዝም ማለት “ሂክመኛ”፣ “ለኡማው አሳቢና አዛኝ”፣ “አርቆ አሳቢ”፣ “የትልቅ ባህሪ”፣ “የአዋቂነት መገለጫ” ተደርጎ መታየት እየጀመረ ነው፡፡ አሳዛኙ ነገር ይህ ደካማ አስተሳሰብ ከፊል እራሳቸውን ወደ ሱና የሚያስጠጉ ሰዎች ላይ መታየቱ ነው፡፡ ትክክለኛው ለኡማው የማሰብ፣ የሂክማ (ነገሮችን በተገቢ መልኩ ማስተላለፍ)፣ አርቆ አሳቢነት የሚገለፅበት ሃቅን ማብራራት፣ ጥፋትን በይፋ ለሰዎች ማብራራትና ማስተካከል፣ ሰዎችን ከጥፋት መታደግ ነው፡፡
በዘመናችን ታላላቅ የሱና ኡለማዎች እንደ ሸይኽ ኢብን ባዝ (ረሂመሁላህ)፣ ሸይኽ አልባኒ (ረሂመሁላህ)፣ ሸይኽ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ)፣ ሸይኽ አቡ ዘይድ (ረሂመሁላህ)፣ ሸይኽ ፈውዛን (ሃፊዘሁላህ) እና ሌሎችም ብርቅዬ የሱና ኡለማዎች ሀቅን በባጢል አይደበልቁም ነበር፣ ባጢል ከነባለቤቶቹ በአደባባይ ሲፈነጩና ሲሰራጭ ዝም አይሉም ነበር፡፡ ኡለማዎቻችን ይህ ነበር አቋማቸው፡፡
አላህ ሃቅን በባጢል የሚቀላቅሉትን፣ እያወቁ ሃቅን ሲደብቁ የነበሩትን የኢስራኢል ልጆች እንዲህ ሲል ይገልፃቸዋል
وَلَا تَلْبِسُوا۟ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُوا۟ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡
ተመልከቱ የአላህ ባሪያዎች እውቀት ብቻውን ያለተግባር ቢጠቅም ኖሮ አላህ የኢስራኢልን ልጆች እንዲህ ሲል ባልወቀሳቸው ነበር፡፡ ሃቅን መደበቅ አደጋው ከባድ ነው፡፡ አብዛኛው ማህበረሰብ አጥፊና ጥፋቱ፣ ከሃቅና ከባለቤቶቹ በማስረጃ ካልተለየለት ያንን ጥፋት ዲን ነው ብሎ ሊከተለው ይችላል፡፡
ሃቅ በመብራራቱ የሚገኙ ጥቅሞች
- ሐቅም ባጢልም ከነባለቤቶቻቸው ለማህበረሰቡ ግልፅ ይሆናሉ፣
- አጥፊዎች በአላህ ፍቃድ ይመለሳሉ፡፡ አብዛኛው ማህበረሰብ ከስህተቱ ይታረማል፣
- ሰዎች ያሉትን ቢሉ ተናጋሪው ግዴታውን ይወጣል፡፡ አላህም ዘንድ በአላህ ፍቃድ ምንዳውን ያገኛል፤
- አንመለስም ብለው ባጢል ላይ ክችች ያሉት ላይ ሁጃ (ማስረጃ) ይቆምባቸዋል እና የመሳሰሉት
አላህ አንቀፆቹን ያብራራልን ሀቅን ከባጢል እንለይ ዘንድ ነው፡፡ አንተ የአላህ ባሪያ ሆይ! ንቃ ሐቅን ግልፅ አድርግ፡፡ ሐቅን እርዳ፡፡ ለባጢልና ባለቤቶቹ በርህን እና ልብህን በዝምታ ከፍተህ አትስጥ፡፡
አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ቀጥተኛውን ጎዳና ይምራን፡፡

አል-ጀዚራ ጁምኣ ጁምኣ አረብ ሙስሊም ሀገራት ላይ የተቀጣጠለውን የፈተና እሳት ከኳታር ሆኖ ቤንዚል እየጨመረ አቀጣጠለው፡፡ ይሀው አሁን ሙስሊም አረብ አገራት ለደረሱበት ከባድ ችግር ዋና ሰበብ ሆነ፡፡
አልጀዚራ ላይ “ፊቂሁ ሰውራት (የሰላማዊ ሰልፍ አረዳድ እና ግንዛቤ ስልቶች)” የሚል ሁሉ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ህዝቦች በመሪዎች ላይ እንዲያምፁና ለጠላት በራቸውን እንዲከፍቱ “ነፃነት፣ ጭቆናው ይብቃ፣ ዩስማዕ ሰውተና (ድምፃችን ይሰማ)” በሚል ብሄል ይሀው ሙስሊም ሀገራትን የጠላት መጫወቻ በማድረግ የዩሁዳዎችን ግዛታቸውን የማስፋፋት አላማ ያስፈፅማል፡፡ አልጀዚራ እንደፈለገ እራሱን ቢጠራም ለነዚህ ሙስሊም አረብ ሀገራት መውደቅ ቁጥር አንድ ተጠያቂ ነው፡፡ አልጀዚራንም የልቡን እንዲፈነጭ ከጀርባ ሆና ጣቢያውን የመሰረተችው፣ የፈተናው ጣቢያ ዋና ማሰራጫና መቀመጫ ኳታር ኢንሻ አላህ አላህ ፊት ትጠየቃለች፡፡
አልጀዚራ ፈጠና አቀጣጣይ ጣቢያ፡፡ አላህ ከአልጀዚራም ይሁን ከሌሎች መጥፎ እርኩስ ቻናሎች መርዝ ይጠብቀን፡፡

የኢኽዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት
(ተከታታይ፣ ክፍል ስድስት)
ኢኽዋን እና ሙዚቃ
የላቀው ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَكَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ وَلِتَسْتَبِينَ سَبِيلُ الْمُجْرِمِينَ) [سورة اﻷنعام 55]
“እንደዚሁም (እውነቱ እንዲገለፅና) የወንጀለኞችም መንገድ ትብራራ ዘንድ አንቀፆችን እንገልፃለን፡፡ [አልአንዓም፡ 55]
ሰሞኑን ከሳዑዲ ጋር በተያያዘ ኢኽዋኖች መወራጨት እንዳበዙ እያየን ነው፡፡ የሚያነሱት ማምታቻ በተጋለጠባቸው ቁጥር ወደሌላ እየዘለሉ ይበልጥ ማንነታቸውን ለተሸወዱ ተከታዮቻቸው እያጋለጡ ነው፡፡ ይሄው ደግሞ አንዱ የሆነ አርቲስት በሪያድ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያዘጋጅ ነው ሲል ሳዑዲን ለማብጠልጠል ለጥፏል፡፡ በመጀመሪያ ወሬው እውነት ይሁን አይሁን አላውቅም፡፡ ከኢኽዋን ሰፈር ውሸት ቀርቶ ሺርክም ብርቅ አይደለም፡፡ እውነት ከሆነም እንዲህ አይነት ነገሮች በተደጋጋሚ ከታሰቡ በኋላ ሲዘጉ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በተረፈ ሙዚቃ በማንም ቢዘጋጅ ሸሪዐዊ መሰረት የሌለው ፀያፍ ምግባር ነው፡፡ ስለዚህ እውነት ከሆነ በምንም መልኩ ጥፋቱን አንደግፍም፡፡
ግን ኢኽዋን ሰፈር ሙዚቃ ይህን ያክል ባደባባይ ለማብጠልል የሚበቃ ወንጀል ነው ወይ? ኧረ እባካችሁ አንድ አይና ባፈር አይጫወትም!! እስኪ በሃገራችን ለሙዚቃ ሽንጡን ገትሮ የሚሟገተው ሐሰን ታጁ አይደለምን? ይህን ያክል ዘመቻ ከፍታችሁበታልን?! መድረክስ ዘግታችሁበታል? ሙዚቃው ቀርቶ ባደባባይ ወደ ሺርክ እየተጣራ እሱን ከማስተዋወቅ፣ መድረክ ከመስጠት ተመልሳችኋል?! ቢያንስ ሰልፋችሁን ሲቃወማችሁ ያሳያችሁትን ቅሬታ ያክል እንኳን ተቀይማችሁታል?! የለም፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው የኢኽዋን ቡድናዊ ገመድ ስለሚያስተሳስራችሁ ብቻ ነው፡፡ ግን ይሄ የተንሸዋረረ እይታችሁ መቼ ይሆን የሚታረቀው? ሰዎችን በተክፊርነት ትወነጅላላችሁ፡፡ የሰይድ ቁጥብን የተክፊር አካሄድ ግን አትነቅፉም፡፡ ከሺዐ ጋር አያይዛችሁ ትወነጅላላችሁ፡፡ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ ከሺዐ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ያለውን ኢኽዋንን ግን ዝም ትላላችሁ፡፡ የዐረብ መሪዎችን ሰው ሰራሽ ህግ ዘረጉ ብላችሁ ታከፍራላችሁ፡፡ እራሳችሁ ግን በሰው ሰራሽ ህግ ትጓዛላችሁ፡፡ ስለ ዑለማእ ክብር ትጮሃላችሁ፡፡ የሱንና ዑለማዎችን ግን ማብጠልጠል ግፋ ሲልም ማክፈር ቀዳሚ ስራችሁ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ጭራሽ በሙዚቃ መጣችሁ! በዚህ ዘመን ሙዚቃን እየፈቀዱ ህዝብን ወደ ስነ ምግባር ዝቅጠት እየገፉ ያሉት ኢኽዋኖች እንጂ ማናቸውና?! ጥቂት ምሳሌዎችን ልጥቀስ፡-
1. ቀርዷዊ፡- ሙዚቃን በመፍቀድ በሰፊው የሚታወቅ ነው፡፡ ለምሳሌ እንዲህ ይላል፡-
“ነፍሶች ዘና ከሚሉበት፣ ልቦች ከሚመቱበት፣ ጆሮዎች ከሚረኩበት ዝንባሌዎች ውስጥ አንዱ ዘፈን ነው፡፡ ብልግናና ለወንጀል ማነሳሳትን እስካላካተተ ድረስ ኢስላም ፈቅዶታል፡፡ ስሜት ቀስቃሽ ያልሆኑ የሙዚቃ መሳሪያዎች ቢያጅቡትም ችግር የለውም፡፡” [አልሐላል ወልሐራም፡ 218+] “ዘፈን በራሱ ከሙዚቃ መሳሪያ ጋርም ሆነ ያለሙዚቃ መሳሪያ ሐራም አይደለም፡፡” [ሰይዪደቲ፡ ቁ. 678] በራሱም ሙዚቃ ያደምጥ ነበር፡፡ “እውነት ለመናገር ዘፈን ለመስማት ቢዚ ነኝ” ካለ በኋላ የሚያዳምጣቸውን ሙዚቀኞች ከ 14 ዘፈኖቻቸው ጋር ዘርዝሯል፡፡ ቢዚ ስለሆነ የሚያዳምጠው እነዚህን የመሰሉ “ጥቂት” ዘፈኖችን ብቻ ነው፡፡ ቢዚ ባይሆንስ? “ከአዲሱ ትውልድ ማንን እንደማዳምጥ አትጠይቀኝ፡፡ ምክንያቱም እኔ ከቀድሞው ትውልድ ነኝ፡፡ እናም የቀድሞዎቹ አቀንቃኞች ከአዲሶቹ ይልቅ ይበልጥ ለነፍሴ የቀረቡ እንደሆኑ ይሰማኛል” ይላል፡፡ [አርራያህ መፅሔት፡ ቁ. 5970]
2. ዑመር አትቲልሚሳኒ (3ኛው የኢኽዋን ሙርሺድ ነው)፡- እየከፈለ የፈረንጅ ዳንስ ተምሯል፡- “በዒማዱዲን ሳሎን ውስጥ የፈረንጅ ዳንስ ተምሬያለሁ፡፡ አንድ ዳንስ ለመማር ክፍያው ሶስት ፓውንድ ነበር፡፡ ደን ሲት፣ ፎክስ ትሮት፣ ሻርሊስቶን፣ ታንጎ የተባሉ የዳንስ አይነቶችን ተምሬያለሁ፡፡ በጊታር መጫወትም ተምሬያለሁ፡፡” [ዚክሪያት ላ ሙዘኪራት፡ 48]
ሲኒማ ለማየት ብሎ የጁሙዐ ሶላት ይተው ነበር፡፡ “ጠበቃ ሆኜ እሰራ በነበረበት ወቅት አንዳንድ የሲኒማ ፊልሞችን ለማየት ጁሙዐ ቀን እወጣ ነበር፡፡ ከሲኒማ ቤቱ አንድ ጥግ ላይ ዙህርና ዐስር ሶላቶችን በአንድ ሰብስቤ፣ አሳጥሬ ለመስገድ የእረፍት ሰዓቱን እጠቀም ነበር፡፡” [ዚክሪያት፡ 13]
እነዚህ ናቸው እንግዲህ ኺላፋን ሊመልሱ የሚሰሩት፡፡ ምናልባት ቶብቶ ከሆነስ እንዳይሉ “በህይወቴ ውስጥ ከኢኽዋንም ይሁን ከሌላ አንዳንድ ጠርዘኞችን የማያስደስቱ ነገሮች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ የፈረንጅ ዳንስና ሙዚቃን ይመስል፡፡ በህይወቴ የትኛውም ሃይማኖት የማያዘው ከሆነው ማጠባበቅ ርቄ ፈታ ማለትን መውደዴም እንዲሁ - በተለይም ደግሞ ነብያችን ‘ገርና ልዝብ ነው፡፡ ማንም አያጠብቀውም የሚረታው ቢሆን እንጂ’ ሲሉ የገለፁት ኢስላማችን፡፡” [ዚክሪያት፡ 3]
ይቀጥላል፡- “አንዳንድ ጠርዘኞች ‘አላህ የሸፈነልህን ሸፍን’ ሊሉ ይችላሉ፡፡ በኔ ላይ ይሄ ንግግር አይሰራም፡፡ ምክንያቱም ይሄ ንግግር አላህን የሚያስቆጣ ነገር ለፈፀመ ሰው የሚባል ነው፡፡ እኔ ሆን ብዬ አላህን ላስቆጣ እንደሞከርኩ አላስብም፡፡ እኔ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ጋር ነው የምጓዘው፡፡ እሳቸው ደግሞ ሁለት ምርጫዎች ሲቀርቡላቸው ወንጀል እስካልሆነ ድረስ ቀላሉን ነበር የሚመርጡት፡፡ ስለዚህ መከፋትም ሆነ መቃወም አይገባም፡፡” [ዚክሪያት፡ 78]
3. ሰዕድ አልከታቲኒ (በግብፅ የኢኽዋን የፖለቲካ ክንፍ ሒዝቡል ሑርያ ወልዐዳላ ዋና ፀሐፊ የነበረ)፡-
“ፓርቲው በሃገሪቱ ስልጣን ላይ ቢደርስ በመኖሪያ ቤቶችና በሆቴሎች አስካሪ መጠጥን አይከለክልም፡፡ የብልግና ድረ ገፆችን አይዘጋም፡፡ ሸሪዐዊ ቅጣቶችን አይተገብርም፡፡ በባህር ዳርቻዎች የሚጎበኙ ቱሪስቶች ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡” “አስካሪ መጠጥ መጠጣት እንደ መኖሪያ ቤቶች ባሉ የግል ቦታዎች እስከሆነ ድረስ ከግለሰባዊ መብቶች ውስጥ ይቆጠራል፡፡ ሆቴሎችም ከግል ቦታዎች ነው የሚቆጠሩት፡፡ ለሙስሊሞች በግለሰብ ነፃነት ውስጥ ወይም በግል ህይወት ውስጥ ጣልቃ መግባት አይፈቀድም” ይላል፡፡ [አልአህራም፡ ዲሴምበር 10/2011]
በርግጥ ይህን የሚሉት ህዝቡ ገና አልተዘጋጀም በሚል ነው፡፡ ግን እነሱ እራሳቸው ዝግጁ ናቸው ወይ? ሙስሊሞችን ከሺርክ ለማውጣት በቂ ጥረት የማያደርጉ፣ “ኢስላማዊ” ሙዚቃ እያሉ ወደ ስነ ምግባር ዝቅጠት የሚጣሩ፣ ሶሻሊዝምን የሚሰብኩ፣ ሶሐቦችን የሚሳደቡ፣ የሱንና ዑለማዎችን የሚያብጠለጥሉ፣ በትንሽ በትልቁ ከህዝብ እስከመሪ የሚያከፍሩ፣… አይደሉምን? በመሪዎች ደረጃ ባደባባይ መደነሱንስ ምን አመጣው?! ደግሞስ ህዝቡ ገና ነው በሚል ሸሪዐን ለመተግበር የሚያመካኙ ከሆነ ለምን ሌሎች መሪዎችን ያከፍራሉ?
“ኢስላማዊ ሙዚቃ”

ኢኽዋኖች በርካታ እንግዳ ነገሮችን “ኢስላማዊ” የሚል ታፔላ እየለጠፉላቸው ሊያሰልሟቸው ሲውተረተሩ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ሙዚቃ ነው፡፡ “አልኢኽዋን አልሙስሊሙን” የተሰኘው ጋዜጣቸው “ኢስላማዊ ሙዚቃ” በሚል ርእስ ስር እንዲህ ይላል፡- “ሲምፎኒያ፡ እንደ ቤትሆቨን፣ ሾርፕ፣ ሞዛርት፣ ቻይኮቪስኪ፣ ያሉ የሙዚቃ ዝነኞች የደረሱበት ከፍተኛው የሙዚቃ ስልት ነው፡፡ … የግብፅ የሲምፎኒያ ክበብም በክርስቲያን ወጣቶች ማህበር እየታገዘ ከ30 በላይ ሙዚቀኞችን አቅፏል፡፡ ክበቡ በአሜሪካ የኒቨርሲቲ ዘፈኑን አቅርቧል፡፡ ይሄ ነገር ምንኛ የሚያስፈልገን ነው?! በሙዚቃው አለም ባለድል የሚሆንና አለም አቀፍ መራመድ እንዲኖር የሚያግዝ ምንኛ አዲስ አይነት ዳዒያ ያስፈልገናል?! በዚህን ጊዜ የአለምን ልቦና የሚቆጣጠር ልዩ ቀለም ይነግሳል፡፡ እሱም የምስራቁን፣… ሙዚቃ የሚተካ ኢስላማዊ ሙዚቃ ነው!!” [አልኢኽዋን አልሙስሊሙን፡ ቁ. 5]
እነዚህ ጥፋቶች፣ እነዚህ የሞራል ዝቅጠቶች የነ ኢብኑ ባዝ፣ የነ ፈውዛን አይደሉም፡፡ የነ ቀርዷዊ፣ የነ ቲልሚሳኒ እንጂ፡፡ ይሄ ሙዚቃን “ኢስላማዊ” የሚል ቅጥያ እየለጠፉ የማጥመቅ ዘመቻ የሰለፊያ ጥሪ አይደለም፡፡ የኢኽዋን ቆሻሻ ስራ እንጂ፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡-
1. “በእርግጥም ከህዝቦቼ ውስጥ ዝሙትን፣ ሐርን፣ አስካሪ መጠጦችን እና የዘፈን መሳሪያዎችን የሚፈቅዱ ሰዎች ይመጣሉ፡፡” [ቡኻሪ፡ 5590] እነማን ሆኑ?!
2. “በህዝቦቼ ላይ የምፈራው አጥማሚ የሆኑ መሪዎችን ነው፡፡” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 1773]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 4/2009)

ኢኽዋን - “ባለህበት ሂድ!!
ታላቁ ሙሐዲሥ ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ የኢኽዋነል ሙስሊሚንን ከንቱ የፖለቲካ ድካም “ልክ ባለህበት ሂድ እንደተባለ ወታደር ነው” በማለት ባጭር ገልጸውታል፡፡ ድንቅ አገላለፅ!! ይሄው ይሄ የጥፋት አንጃ ከተመሰረተ 89 አመቱ፡፡ እስካሁን ድረስ የአሸዋ ክምር ላይ እንደሚወጣ ባተሌ ጫፍ ደረሰ ሲባል እየተንከባለለ ከተነሳበት ያርፋል፡፡ በአላህ ፈቃድ ወደፊትም እንዲሁ ይቀጥላል፡፡ በከዕባ ጌታ እምላለሁ ኢኽዋን መቼም አይሳካለትም፡፡ ነብዩ ﷺ “ውርደትና የበታችነት ትእዛዜን በጣሰ ላይ ተደርጓል” ማለታቸው ይሰመርበት፡፡
ታዲያ ቡድኑ የውርደት ካባ በተከናነበ ቁጥር ጣቱን የሚቀስረው ወደ ሳዑዲ መሪዎች ነው፡፡ የሚደንቀው ግን በየትኛውም መመዘኛ ከሚተቿቸው አካላት የማይሻሉ መሆናቸው ነው፡፡ “በወህኒ ቤት ሳለን ፂማችንን የምንላጭበት ምላጭ ተከለከልን” የሚሉ ማፈሪያዎች ኢስላምን ሲወክሉ ማየት ምንኛ የሚያሳዝን ነው?!
ይሄው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ በሳዑዲ ላይ ከወትሮው የተለየ የጥላቻ ዘመቻ አቀጣጥለዋል፡፡ ሁሌ ስለ ኤርዶጋን፣ ኳታር፣ ግብፅ፣ ሳዑዲ እያወሩ ዲን ከማስተማር ይልቅ የውሸት ፖለቲካ ይሰብካሉ፡፡ ምናልባት “እናንተስ ሁሌ ከሳዑዲ ትከላከሉ የለም ወይ?” ሊሉ ይችላሉ፡፡ አዎ እንከላከላለን፡፡ ምክንያቱም የነዚህ ገልቱዎች አላማ በሳዑዲ አመራር በኩል ተሻግረው የሰለፍያ ደዕዋን እና የሱንና ዑለማዎችን ማንቋሸሽ እንደሆነ ደጋግመን በተግባር አይተነዋልና፡፡ እንጂማ በየትኛው መመዘኛ ነው የኳታር መንግስት ከሳዑዲ የሚሻለው?! በኳታር ከቀርዷዊ መኖሪያ በቅርብ ርቀት ትልቅ የአሜሪካ የጦር ካምፕ ይገኛል! እስኪ ቀርዷዊ ስለዚያ ተንፍሶ ያውቃል?! የኛዎቹ በቀቀኖችስ ስለዚህ ይተነፍሳሉ?! ወፍ የለም!! በቅርቡ ንጉስ ሰልማን የትራንፕን ሚስት ጨበጠ ብለው አቧራ ሲያስነሱ ነበር፡፡ ጥሩ፡፡ ግን ኤርዶጋን ባደባባይ ግብረ ሰዶም ሲፈቅድ ተመሳሳይ ተቃውሞ ቀርቶ ኮሽታ አሰምተዋልን?! እስኪ የትኛው ጥፋት ነው የሚከብደው? ሰዎቹ ህሊናቸውን ሽጠው የበሉ ቆሻሻዎች ናቸው፡፡ ቀርዷዊ የኳታሩን መሪ ሚስት ሲጨብጥስ ኮሽታ አሰምተዋል?! መጨበጥ ብቻ አይደለም፡፡ አጅነቢ መጨበጥ ይቻላል የሚል ነው ቀርዷዊ፡፡ እስኪ ከዚህ ጥፋትና ከሰልማን ጥፋት የቱ ይከብዳል? ስሜታቸውን ተከትለው የሚወዛወዙ ፍጡሮች!!
[ሀ] ይሄው እራሱን “ሃምሳ ሃምሳ” እያለ የሚጠራ አንድ ኢኽዋኒ ሳዑዲን ለማብጠልጠል ሲሆን “በኢስላም አስተምህሮትም ሆነ በኢስላም ታሪክ የንጉሳዊ አገዛዝን ስርዓተ መንግስት ይሁንታ የሚሰጥ ማስረጃ የለምና … አልሳዑድ ወለድ ዑለማ እንዴት ዝምታን መረጠ” እያለ ዑለማዎቹን ጭምር ይወርፋል፡፡
ጥያቄ፡- ንጉሳዊ አገዛዝ በኢስላም ታሪክ እውቅና ከሌለው ለምን የኦቶማን ቱርክ “ኺላፋ” ፈረሰ ብላችሁ ታለቅሳላችሁ? እስኪ አሁን የኦቶማን አገዛዝ ንጉሳዊ ስርኣት እንደነበረው የማያውቅ መሀይም ስለታሪክ ሊያወራ ይገባል? ለምንስ ስለ ኳታር ታላዝናላችሁ?! ለመሆኑ ኳታር በሸሪዐ ነው የምትመራው ወይስ በዴሞክራሲ?! የታል የፖለቲካ እውቀታችሁ?!
[ለ] ቀጥሎ እንዲህ ነበር ያለው፡- “የቀደመው ዘመን ትልቁ የኢስላም አበርክቶ ጥልቅና ምጡቅ እውቀትና ሁለንተናዊ የትምህርት ዘይቤን ላለም ስልጣኔ ለሰው ዘር ሁሉ ማበርከቱ ነበር፡፡ ነገር ግን ከዘመነ ሳዑድ ንግስና፡ ከኦቶማን መፈራረስና ከዑመቱ መለያየት ወዲህ ያለው ዘመነ መከራ ወ ሰቆቃ የአልሳዑድና የወቅቱ አጋሮቹ ደባ ወጤት መሆኑ እንደምን ተዘንግቶ”
መልስ፡-
1. በመጀመሪያ ንግግሩ እጅ እጅ እንዲል ያደረገው ጌታ ምስጋና ይድረሰው፡፡ ለወትሮው እንኳን ወሬ አያጥራቸውም ነበር፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን ብእራቸውም እየከዳቸው መጥቷል፡፡
2. በተረፈ ሙስሊሙ ዛሬ ላለበት ውድቀት ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት በኢስላም ስም የሚነግዱ የከሸፉ የኢኽዋን ፖለቲከኞች ናቸው፡፡ ለሚያስተውል በዐረቡ “ጸደይ” ምክንያት በሙስሊሙ አለም ላይ የደረሰው ብቻውን ለዚህ በቂ ምስክር ነው፡፡
3. በየሄዱበት “እስፔን የኛ ነበረች” እያሉ የሚያላዝኑት ኢኽዋኖች ንጉሳዊ አገዛዝ ልክ በሳዑድ ቤተሰብ እንደተጀመረ አድርገው እያቀረቡ ነው፡፡ በ14 ክ/ዘመናት ውስጥ ያለፈው የኢስላም ታሪክና ስልጣኔ ግን እንዳለ ንጉሳዊ አገዛዝ ነው፡፡ ደግሞም ኢኽዋኖች እንኳን የንጉሳውያንና የነብዩ ﷺ ምርጥ ሶሐባና አማቻቸው የሆኑት የዑሥማን ኢብኑ ዐፋን አገዛዝ የሚያረካቸው አይደሉም፡፡ ይሄው ዛሬም ድረስ (የኡስማን ረዲየላሁ ዐንሁ የኺላፋ ዘመን በሶስቱ ኸሊፋዎች ዘመን ውስጥ የገባ ክፍተት እንጂ የእውነት የነገሰው እሱ ሳይሆን መርዋን ነው፤ ዑስማን በስልጣኑ ተከልሎ የሙስሊሙን ገንዘብ ያላግባብ የተጠቀመ፣ ለዘመዶቹ እያዳላ የነብዩን ወዳጆች ያራቀ፣ ኸሊፋ ሊሆን በማይገባው እድሜ ስልጣን ይዞ የመርዋን መጫወቻ የሆነ፣ አገዛዙ ከኢስላም ሩህ የራቀ ነበር፣ ከኡስማን ይልቅ የኡስማን ገዳዮች ለኢስላማዊ ሩሕ የቀረቡ ነበሩ ለሚለው ሰይድ ቁጥብ ሽንጣቸውን ገትረው እንደተከላከሉ ናቸው፡፡ (አልዐዳለቱል ኢጅቲማዒያህ፡ 160-186 ተመልከት፡፡)
[ሐ] “የሽብርተኝነት አስተሳሰብና ጠንሳሾች፡ ሰፖንሰሮችና የፅንፈኛ ቡድኖች አቃፊና ደጋፊዎቹ አይተኛ ምንጮች እነማን ሆኑና” “የመስከረም 11ዱን ጥቃት አድራሾች እኮ የሳዑዲ የግብፅና የኢማራትስ ሀገራት ዜጎች እንጂ መች የሌላ ሆኑና” ይላል ከብእር ስም ጀርባ ያደፈጠው ኢኽዋኒ፡፡
መልስ፡-
1. ይህን ሁሉ የሚለው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የዐረብ ሃገራት ከኳታር አንፃር የያዙትን አቋም ተከትሎ ነው፡፡ ኳታር የኢኽዋኖች መነሃሪያ ስለሆነች በደመ ነፍስ በመወገን እንጂ የእውነት ፖለቲካው ገብቶት አይደለም፡፡
2. በተረፈ ኢኽዋን ከመነሻው የጥፋት አንጃ እንደሆነ የተናገሩት ከሳዑዲ መሪዎች በፊት የግብፅ ምሁራን ናቸው፡፡ ታላቁ ግብፃዊ ዓሊም ሸይኽ አሕመድ ሻኪር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “የሸይኽ ሐሰነል በና እና የሙስሊም ወንድማማቾቹ ንቅናቄ የኢስላማዊ ደዕዋን ወደ አፍራሽ የጥፋት ስብከት የገለበጡ ናቸው፡፡ ኮሙኒስቶች እና አይሁዳውያን እንደሚረዱት በተጨባጭ እናውቃለን፡፡” [ሹኡኑ አትተዕሊም ወልቀዳእ፡ 48]
3. እነ ቢንላደንና መሰል የጥፋት ሃይሎች የኢኽዋን አስተሳሰብ አራማጆች እንደሆኑ የራሳቸው የትግል አጋሮች መስክረዋል፡፡ አጥፍቶ ጠፊዎች የሚታጠቁት ቦምብም የተጀመረው በኢኽዋኖች እንደሆነ እራሳቸው ፅፈዋል፡፡ ድልድዮችን፣ የመብራት ታወሮችን፣ ተቋማትን ሲያጋዩ እንደነበር በራሳቸው ሰዎች ጭምር የተፃፉ ታሪኮች ያስረዳሉ፡፡
4. አሸባሪዎች የሱንና ዑለማዎችንና የሳዑዲ መሪዎች ያከፍራሉ፣ ይዝቱባቸዋልም፡፡ እነ ሰይድ ቁጥብን እነ ሐሰን አልበናን ግን ያወድሳሉ፡፡ ይህም ሽብርና ጠርዘኝነት ከኢኽዋን ጋር ስጋዊ ዝምድና እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡
5. ደግሞም የሳዑዲ አሸባሪዎች በሳዑዲ ዑለማዎች የሚብጠለጠሉ፣ በሳዑዲ መንግስት የሚሳደዱ እንጂ የሚደገፉ አይደሉም፡፡ እነ ቢንላደንን፣ እነ ሚስዐሪን ያጋለጧቸው እነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑል ዑሠይሚን፣ ፈውዛን፣ … እንጂ እነ ቀርዷዊ አይደሉም፡፡ የኢኽዋን በቀቀኖች እነዚህን የጥፋት ሃይሎች “ጀግኖች” አድርገው በየሚዲያው በሃገራችንም ጭምር ሲያቀርቡ ነበር፡፡

6. የዘመናዊ የተክፊር አስተሳሰብ መሰረቱ ኢኽዋን ነው፡፡ “እሄ የምንኖርበት ማህበረሰብ እራሱ ሙስሊም ማህበረሰብ አይደለም፡፡” “ጉዳዩ የማመንና የመክፈር ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች እንደሚሞግቱት ሙስሊሞች አይደሉም፣ የሚኖሩት የጃሂሊያ ህይወት ነው፣ ደዐዋችን የተነሳው እነኚህን ጃሂሊዮች ወደ ኢስላም ለመመለስ ነው-እንደ አዲስ ሙስሊም ለማድረግ፡፡” እነዚህ የኢኽዋኒው ሰይድ ቁጥብ ንግግሮች ናቸው፡፡(ፊ ዚላሊል ቁርኣን፡ 3/1816) (መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 173)
7. ኢኽዋኖች ከዘመናችን ሙስሊሞችም አልፈው ሶሐባ ሳይቀር የሚያከፍሩ ናቸው፡፡ "የአቡ ሱፍያንን እስልምና “የከንፈርና የምላስ እስልምና እንጂ የልብ ኢማንና እውነቱን የማግኘት አይደለም፡፡ ኢስላም ወደዚህ ሰውየ ልብ አልሰረፀም፣ ከሰለመ በኋላም የሙስሊሞችን ሽንፈት ሲመኝ የነበረ ነው!!” የሚለው ሰይድ ቁጥብ አይደለምን? “በኑ ኡመያ በጥቅሉ ኢማን ከልባቸው አልሰረፀም፡፡ ኢስላም ለነሱ እንደ ጥቅማቸው ሲያሻቸው የሚለብሱት ሲፈልጉ የሚያወልቁት ካፖርት ማለት ነው፣ ስነ ምግባር፣ ዲን፣ ልቦና የማይገታቸው ሰዎች ናቸው…” የሚለው ሰይድ ቁጥብ አይደለምን? (አልዐዳላህ፡172)
[መ] ይሄው ሃምሳ ሃምሳ የተሰኘው ዋልጌ “የሳዑዲ ንጉሳዊ ቤተሰቦች የአይሁድ ቤተሰብ ርዝራዦች ናቸው” ይላል፡፡ መልስ፡-
1. የሰዑድ ቤተሰብ ታሪክ በዝርዝር የሚታወቅ ስለሆነ ስለሱ አላወራም፡፡
2. ግን የአይሁድ ቤተሰብ ቢሆኑ ምንድን ነው ችግሩ?! እነ ዐብደላህ ኢብኑ ሰላማ፣ እነ ዐጢያ አልቁረዚ፣ እነ ከዕቡል አሕባር የአይሁድ ዘር አይደሉምን?! ታላላቅ የኢስላም ስብእናዎች ውስጥ የአይሁድ ዘር ያላቸው አላለፉምን?! ነው ወይስ አይሁዳዊ ዘር ቢሰልምም የማይፀዳ ቆሻሻ ነው?
3. ነው ወይስ የሰዑድ ቤተሰቦች የሰለሙ መስለው በኢስላምና በሙስሊሞች ላይ የሚያሴሩ ስውር አይሁዶች ናቸው ለማለት ነው?! እነዚህ ናቸው እንግዲህ ሙስሊሞችን እያከፈሩ ከዚያም ሰዎችን ተክፊሮች እያሉ የሚወነጅሉት የኸዋሪጅ ወራሾች!!
ልመለስ እችላለሁ፡፡ (ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 3/2009)

ወዴት እየሄድን ነው?
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡
ለሂጅራ ቱብ የተሰጠ ማስተካከያና ማስገንዘቢያ፡፡
እግር ኳስ ስንቱን ሙስሊም ከጌታው ያራቀ፣ ጀመአ ሰላትን የሚያዘናጋ ከባድ ፈተና ሆኖ ሳለ እራሱን “Hijra Tube ኢስላማዊ ድህረ ገፅ” ብሎ የሚጠራው ስለ አንድ ታዳጊ ፓንክ የተቆረጠ ሙስሊም ወጣት በምስሉ ላይ እንደምታዩት እያደናነቀ የለቀቀው ጉድ አስገራሚ ነው፡፡
እንዲህም ይላል “ታዳጊ ኡመር አስገራሚ የኳስ ብቃት የአርሰናል የወደፊት ተስፋ ተብሏል ማሻ አላህ በሉት ሙስሊም በሁሉም ዘርፍ ስኬታማና ዝነኛ ሲሆን ማበረታታት ይገባናል” ይላል፡፡
እንግዲህ እራሱን “ኢስላማዊ ድህረ ገፅ” ብሎ የሚጠራው ይህን ያህል የሀይማኖት እውቀት ክፍተት ካለበት ሌላው ሰው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ነው፡፡ ማሻ አላህ የሚባለውን እና የማይባለውን እንኳን አለማወቁ ያሳዝናል፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ፀጉራችሁን ስትቆረጡ አንዱን ከአንዱ አታበላልጡ” ብለው አዘው ሲያበቁ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)ን ትእዛዝ ተቃርኖ ፓንክ የተቆረጠው ብሎም ስትራይፕ መስመር ያወጣው ወጣት ምኑ ነው የሚደነቀው?
ምኑስ ነው ማሻ አላህ የሚባለው?
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በወጣትነቱ ጌታውን ያመለከ ወደ ጀመኣ ሰላት የተሯሯጠ ጥላ በሌለበት ቀን “አርሽ ጥላ ስር” እንደሚሆን ነግረውን ሲያበቁ ለምን ይሆን ወጣቶች እንዲህ አይነት ከኢስላማዊ እውቀት እና አምልኮ ከሚያርቃቸው ነገር ላይ ቢዚ እንዲሆኑ የሚበረታቱት?
ሱብሃነላህ ያሳዝናል፡፡
“ሙስሊም በሁሉም ዘርፍ ስኬታማና ዝነኛ ሲሆን ማበረታታት ይገባናል” ሲልም ድህረ ገፁ ፅፏል፡፡
ስኬታማነት እና እድለኝነት በምን እንደሆነ አለማወቅ ከባድ አደጋ ነው፡፡ በኢስላም እና ሱና አላህን ፈርቶ የአላህን እና የመልክተኛውን ትዕዛዝ እየተገበሩ እና እነሱን ከመቃረን በመራቅ ቢሆን እንጂ ስኬት እና እድለኝነት አይገኝም፡፡
ዝነኝነት …….
እባካችሁ ሂጅራዎች ወይንም ሌሎች ኡመተል ኢስላምን በተለይ ወጣቱን ትውልድ እንዲህ ሰንካላ ወደ ሚያደርጉት ተግባሮች አትጥሩት፣ አታበረታቱት፡፡
እኛ ከኢስላም በላይ ፀጋ የለንም፡፡ ኢስላምን ሙሉ በሙሉ ከተከተልን በዱንያም በአኸይራም የተከበርን ነን፡፡ ሌላ ሚዛን አታምጡብን፡፡ እናንተ ከአማኞች መሪ ኡመር (ረድየላሁ አንሁም) በላይ አታውቁም፡፡
ኢስላም የሙስሊም ወጣቶችን በኢስላማዊ እውቀት እና ትክክለኛው አምልኮ ላይ ቢዚ እንዲሆን እንጂ ኳስ፣ ድራማ፣ ፊልም፣ የመናገር ብቃት፣ የስነፅሁፍ ምሽት ምናምን እያሉ በማይረባ ጠፊ አለም ታዋቂነት እና ዝነኝነት ላይ ቢዚ የሚሆኑ ትውልዶች እንዲኖሩ አይፈልግም፡፡
የሚገርም ነው፡፡ ትክክለኛውን የመልክተኞች ጥሪ የሚጣሩ ኡለማዎችና ዱኣቶች ከኳስ ራቁ፣ ጀመኣ ሰላት ኑ ይላሉ፡፡ በዚህ በኩል ደግሞ እግር ኳስ ተጫዋቹ ሙስሊም ስለሆነ ብቻ “ሙስሊም በሁሉም ዘርፍ ስኬታማና ዝነኛ ሲሆን ማበረታታት ይገባናል” የሚሉ አፍራሽ ዳእዋዎችን እንዲህ አይነት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሰዎች ጋር ሊደርሱ የሚችሉ ፔጆችን ይዘው የሚያሰራጩም አሉ፡፡
አንድ ነገር ብዬ ላቁም ሙስሊሞች ሆይ! አላህን እንፍራ እኛ ሁላችንም አንድ ብቸኛ የሆነችውን የሐቅ መንገድ እንከተል፡፡ ይሄ ለሁለት አገር ስኬት ያበቃል፡፡ አለበለዚያ ጫት የሚቅም ብሎም ጫት እንዲቃም የሚያበረታታ የመስጂድ ኢማም፣ አጅነቢ የሚጨብጥ ታዋቂ ሙስሊም፣ ሰላት የማይሰግድ ወይንም ሰላት የሚያሳልፍ ዶክተር ፓይለት ኢንጂነር፣ ሂጃብ የማትለብስ ታዋቂ ጋዜጠኛ ሴት፣ መስጂድ የማይመጣ የስፖርት ዘጋቢ፣ ያለ ጠባቂ አለምን የምትዞርና የምትጓዝ የዱንያ ትምህርት በጣም የተማረች አንደበተ ርቱእ ሴት፣ ፓንክ የሚቆረጡ ወጣት ሙስሊሞች፣ ጫት መጠጥ ሀሺሽ የሚጠቀሙ ሙስሊም ወጣቶች፣ ፂማቸውን የሚላጩ ኦ የሚቆረጡ ቃሪያ እና ሲኪኒ ሱሪ የሚለብሱ ሙነሺዶች፣ ለአቂዳ ቦታ የማይሰጡ ወይንም የሚገባውን ያህል ትኩረት የማይሰጡ ዱኣቶች፣ ፈጅር ሰላትን ተነስተው በሰኣቱ በአላህ ቤት የማይሰግዱ ወንዶች፣ ለድራማ ነው ብለው አጅነቢ የሆኑ ወንድ እና ሴቶች የሚጨባበጡ ሙስሊሞች እና ሌሎችም ነፍሳቸውን እየጎዱ ነው፡፡ ኢስላምን እና ሙስሊሞችን እንጠቅማለን ከማለታቸው በፊት ነፍሳቸውን ሸሪኣዊ እውቀት ተምረው መለወጥ ነው ያለባቸው፡፡
አንዳንዶች ለምን በግል አትነግራቸውም ለሚሉ የምለው አንድ ነገር ነው፡፡ በአደባባይ ለመቶ ሺዎች የተሰራጨ ስህተት በአደባባይ ይታረማል፡፡
ስለዚህ ሁላችንም እራሳችንን አላህን ፈርተን ኢስላም የሚለንን እንከተል፡፡

በውሸት ማሸነፍ አይቻልም፡፡
ነገሮች ሁሉ የማይሰወሩት አላህ እነ ያሲን ኑሩን ሳውዲ ላይ በምን እንደታሰሩ ማን እጁ እንዳለበት ማን እጁ እንደሌለበት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ “ሳዳት ከማል አሳስሯቸዋል” ብሎ አንድ የሚያወራ ግለሰብ ተቀድቶ የላከው ኦዲዬ ደረሰኝ፡፡ ምን እላለሁ ሁሉን ቻይ እና አሸናፊ ሀቁን ያውጣው ከማለት ውጭ፡፡ እኔ ሳውዲ መሄዳቸውንም ያው በየቦታው እየተነሱ ሶሺያል ሚድያ ላይ ከሚለቀቀው ፎቶዋቸው ነው ያወቅኩት፡፡
ከእስር ቤት ሲወጡ ቀናችሁ ይላሉ፡፡ እስር ቤት ሲገቡ እገሌ ነው ያሳሰራቸው ይባላል፡፡ አሁን ይህ ግለሰብ ማስረጃ አምጣ ተብሎ ቢጠየቅ ከየት ያመጣል?
እኔ ግር እንዳይላችሁ ግልፅ ማድረግ የምፈልገው ሙስሊም የሆነ ሰው ሲቸገር፣ ሲታሰር የምደሰት አይደለሁም፡፡ እነ ያሲን ኑሩ በአደባባይ በሚረጩት የተበላሸ አስተምህሮት አበሳጫለሁ፡፡ እጄንም አጣጥፊ አልቀመጥም መልስ ከወንድሞች ጋር ተማክሪ እንሰጥባቸዋለን፡፡ ከዛ ውጭ የነሱን ጥፋት ዝም ያላለ ሁሉ የኢስላም ጠላት ነው የሚባል የኸዋሪጅ አካሄድ ነው፡፡
አልሐምዱሊላህ እነሱም መርዛቸውን ይረጫሉ እኛም መልስ እንሰጣለን ጥፋታቸውን እናርማለን ሐቁ ከእለት እለት ግልፅ እየወጣ ነው፡፡ እነሱ ላይ መልስ በመስጠታችን ሐቁ ግልፅ እየሆነ ሰዎች ከተሳሳተው መንገድ እየወጡ ስለሆነ ጌታዬን ከልብ አመሰግነዋለሁ፡፡ በአላህ እርዳታ እና ሀይል ቢሆን እንጂ እኛ ደካማዎች እና አቅመቢሶች ነን፡፡ የስሜት ተከታዬች አለ የሚሉትን ሚድያ፣ ቻናል፣ መስጂዶች፣ የመስጂድ ኮሚቴዎች፣ ባለሃብቶችንና አብዛኛውን ጭፍን ተከታዬቻቸውን ተጠቅመው የረጩትን መርዝ በአላህ ፍቃድ እና እገዛ በመታገዝ እና በመታገስ ይሀው ዛሬ ጥቂቶች የማይባሉ ከተበላሹ መንገዶች ወጥተው ወደ ሀቁ ጎዳና በአላህ ፍቃድ ተቀንተዋል፡፡
አልሐምዱሊላህ አሁንም አልሐምዱሊላህ፡፡

Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ገንዘብ ከፍለው የተቀዳደ ልብስ የሚለብሱት ለምንድን ነው?
አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ “ፋሽን፣ እስታይል” እየተባለ ከተማው ላይ ታፋ፣ ጉልበትና ሌላም ቦታ የተቦጫጨቀ እና የተቀደደ ከዛም አልፎ ሀፍረተ ገላን በጣም ወጥሮ የሚያሳይ ልብስ ወንዶችና ሴትች መልበሳቸው እየተለመደ መጥቷል፡፡ አረ አላህን እንፍራ ሰይጣን አደም እና ሀዋን ከሀፍረተ ገላቸው ሊገልፅባቸው እንደጎተጎታቸው ጌታችን አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡፡
فَوَسْوَسَ لَهُمَا ٱلشَّيْطَٰنُ لِيُبْدِىَ لَهُمَا مَا وُۥرِىَ عَنْهُمَا مِن سَوْءَٰتِهِمَا
ሰይጣንም ከሐፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ለእነርሱ ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው፡፡
ድሮ ሰው የተቀደደ ልብስ የሚለብሰው ወይ ቸግሮት ወይ አብዶ ነበር፡፡ ዛሬ ስንት እና ስንት ገንዘብ አውጥተው “ባለትራክ….” ምናምን እያሉ የተቀደደ ልብስ ይለብሳሉ፡፡ አላህ የልብ መመልከቻችንን ያብራልን፡፡ ወጣቶች ሆይ! ሰይጣን የአባታችን አደም እና የዝርያዎቹ ጠላት ነው፡፡ ጠላት አድርገን እንያዘው፡፡
ወጣቶች ሆይ! አላህን ፍሩ አለባበሳችሁን አስተካክሉ፡፡ እስልምና ውስጥ ጠቅለል ብሎ መግባት ኋላ ቀርነት ወይንም ፋርነት አይደለም፡፡ ነቃ እንበል ብልጥ ማለት ለማይጠፋው አገሩ የሚሆን ስንቅ የሚሰንቅ ነው፡፡
አላህ ወደሱ በንሰሀ ተመላሾች፣ እሱን አመስጋኞች፣ ለሚቀጥለው አለም ከሚዘጋጁ ባሪያዎቹ ያድርገን፡፡

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም፡፡
*************************************
ምስጋና ለአላህ ነው፤ ሁለት የመደሰቻ በአላትን የደነገገ፡፡ አሁንም ምስጋና ይገባው ይህንን ሸሪዓ ከመበረዝ እጠብቀዋለሁ ብሎ ቃል የገባው አላህ፤ የሃይማኖት ድንጋጊን ሁላ ለራሱ ብቻ ያደረገ፤ በዚህም ላይ ታላቅ ጥበቡን ያሳየ፡፡ እንደሌሎቸ ሀይማኖቶች፤ ቀሳውስት እንደበረዙት (እንደጨመሩበት እና እንደቀነሱበት) እንዳይሆን በግልፅ ሸሪዓዊ ድንጋጌን ለራሱ ብቸኛ አውጪ ያደረገ፡፡
ሱና ፆም ፆመን ዝም ብሎ ማለፍ እንጂ ከአላህ የተደነገገ በዓል የለም፡፡ ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር፤ ከነብያችንም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፤ ከሰሃባዎቻቸው (ሪድዋኑላሂ አለይሂም)፤ ከ3 ምርጥ ትውልድ፤ ከ4 አኢማዎች አላገኘንም፡፡ ታድያ ለምንድን ነው እኛ ያልታዘዝነውን የምንሰራው???
ሰኞ እና ሀሙስ ፆመን ምንም በአል ከሌለ፤ 13፣14፣15 ፆመን ምንም በአል ከሌለ፤ የሸዋል 6 ከየት መጣ??? አላህን እንፍራ፡፡
አንዳንድ ቦታ ያውም ከዋናው ኢድ በላይ ይህን ቀን ያከብሩታል፡፡
እወቅ የአላህ ባሪያ ከሽርክ ቀጥሎ ሸይጧን ዘንድ የተወደደው ወንጀል ቢድዓ ነው፡፡ ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ ለእሳት ነው፡፡
አላህ በደነገገልን 2 ኢዶች፤ ከዛ በጁምዓ ብቻ እንብቃቃ፡፡ ሁሉ ነገር የሌለው ይቀላውጣል፡፡ አላህ ግን ይህን ዲን ሞልቶታል፤ ታድያ እንደ አህለል ኪታብ መጨማመሩ ምን አስፈለገ፤ የአላህን ቁጣ ለመውረስ ካልሆነ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም፡፡ ተጠንቀቁ አስጠንቅቁ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት እና ሩሱሎች ኢማም ላይ ይሁን፡፡

ለኡማው አሳቢዎቹ ብልጦቹ የሳውዲ ኡለማዎች፡፡
==============================
የሳኡዲ ኡለሞዎች አልሐምዱሊላህ ብልጦች ናቸው ማንም አላዋቂ ያለውን ቢላቸው የሰይጣንንም ሆነ የአሜሪካን ህልም አያስፈፅሙም፡፡
አላዋቂዎች እና ስሜት የሚጋልባቸው ሰዎች አንድን ሰው “ኡለማ ደፋርና የማይፈራ” የሚሉት ደም የሚያፋስ፣ ሙስሊሞችን ለችግር የሚዳርግ፣ ሙስሊም አገራትን ለጠላት በር ለመክፈት ሰበብ የሚሆንን ግለሰብ ነው፡፡
ሳውዲ እና ኡለማዎቿ አላዋቂዎች እንደሚሉት የአሜሪካ ወዳጆች አይደሉም፡፡ አላዋቂዎች የአሜሪካ ምኞት ምን እንደሆነ ቢያውቁ ለዚህች ውድ የተውሒድ አገር ጥብቅና ይቆሙ ነበር፡፡ ነገር ግን አለማወቅ ከባድ በሽታ ነው፡፡ አለማወቃቸውን አለማወቅ ሲደረብበት ደግሞ የበሽታም በሽታ ነው፡፡
አሜሪካ ሳውዲን አራት ቦታ እንድትከፋፈል እና ልፍስፍስ አገር እንድትሆን ትመኛለች፡፡ ከመመኘትም አልፎ ሙከራዎችን አድርገዋል፡፡ ሌሎች አገራት ላይ ሰልፍ እንደሚቀሰቀሰው ሳውዲም ላይ ሰልፍ ተብሎ ተቀስቅሶ ይህች የተቀደሰች አገር ወደ ብጥብጥ ገብታ እንድትፈራርስ ይፈልጋሉ፡፡ የነብያት ወራሾች፣ ለዲናቸው ታማኝ የሆኑት እነዚህ ብርቅዬ ኡለማዎች ህዝባቸውን ባለው የሙስሊም መሪ ላይ አምፀው እንዳይወጡ፣ ህዝቡ መሪው ላይ ለሚያየው ስህተት ዱኣ እንዲያደርግ እና እንዲታገስ በማድረግ ይሀው አገሪቷ ከአላህ በታች በነዚህ ብርቅዬ ኡለማዎች ሙስሊሞች ደማቸው ሳይፈስ ጠላትም አይኑ እንዳፈጠጠ ቀረ፡፡ አላህ ሳውዲንም ይሁን ሌሎች የሙስሊም አገራትን ከውስጥም ከውጭም ጠላት ይጠብቃቸው፡፡
አስገራሚው ደፋር ተብዬዎቹ የፈተና ቀስቃሾች በሰላም ካሉበት ተቀምጠው ሙስሊም አገራትን እና ህዝባቸውን አሁን ላሉበት አደጋ ዳርገዋል፡፡ የጠላትንም አላማ አሳክተዋል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለሙስሊሞች መሪን አስመልክቶ የመከሩት ይህን ነበር፡፡
- “የሀበሻ ባሪያም ቢሾምባችሁ ስሙት ታዘዙት”፣
- “እጅህን ጠምዝዞ አንገትህን ይዞ ገንዘብህን ቢቀማህ ሰላትን እስካቋቋሙ ድረስ ……. ስሙ ታዘዙ”፣
- ሰሃባዎች የአላህ መልክተኛን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ጠየቁ “የእሱን ሀቅ የሚጠይቀን የእኛን ሀቅ የማይሞላልን መሪ ካጋጠመን ምን እናድርግ” የአላህ መልክተኛም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ስሙት ታዘዙት” ሲል ይግባኝ የሌለውን ፍርዳቸውን ሰጡ፡፡ እናም ሌሎች ትምህርቶችንም ሰጥተዋል፡፡
አሳዛኙ ዛሬ የነ አሜሪካ ጠላት ነን እያሉ የነ አሜሪካን ህልም የሚያስፈፅሙ በኢስላም ስም የሚንቀሳቀሱ መኖራቸው ነው፡፡ አገራችንም ላይ ይሁን ከአገራችን ውጭ የሳውዲ ለሙስሊሙ መልካም አሳቢ የሆኑትን ኡለሞች የሚያከፍሩና የሚወርፉትን ተመልከቷቸው በኩፍር እና ሺርክ የተሞሉትን ሺአ ራፊዳዎች ምንም ሲሉ አትሰሟቸውም፡፡ ምክንያቱም እነሱ ዘንድ ለአላህ ብሎ መውደድ እና ለአላህ ብሎ መጥላት የለም፡፡ ስልጣን ፍለጋ ማድረግ ያለባቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ እንዲያውም የግብፁ ኢኽዋን መሪ ሙሐመድ ሙርሲ ስልጣን ሲይዝ ሰሃባዎችን የሚያከፍሩ፣ በኩፍር የተጨማለቁ፣ ቀን እና ለሊት ሰሃባዎችን የሚራገሙትን የኢራን ሺአዎች ግብፅ ላይ በሩን ከፈተላቸው አላህ እሳት ለቀቀበት፡፡ ሰው የዘራውን ያጭዳል፡፡
አሜሪካን ተመልከቱ ኢራንን ላይ ላዩን አሸባሪ ትላታላች ግን የሱንዬችን አገር ኢራቅ ወራ ስልጣኑን ለኢራን አስረክባ ነው የወጣችው፡፡
አረ የአእምሮ ባለቤቶች እንንቃ፡፡ ሳውዲ እና የሳውዲ መሪዎች ልንከላከልላቸው ይገባል ስንል ከስህተት የፀዱ ናቸው እያልኩ አይደለም፡፡ ነገር ግን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሙስሊም መሪ ሲያጠፋ ለብቻው ዞር ተደርጎ እንደሚመከር ስለነገሩን እኛም የሙስሊም መሪዎችን ስህተት አደባባይ ላይ አይለቀቅም የምንለው፡፡ ተወደደም ተጠላም አለም ላይ ተውሒድ እና ሱና የበላይ የሆነባት ሺርክና ቢድኣ የተዋረደባት አገር እንደ ሳዉዲ የለም፡፡ አላህ ሳውዲንም አሁን ካለችበት የተሻለ ያድርጋት፣ ሌሎች ሙስሊም አገሮችንም አላህ ወደሚፈልገው መልካም ይምራቸው፡፡
የሳውዲ እንቁዎች ግን ሰው ያለውን ቢላቸው ሰይጣንን እና መሰሎቹን እየተቃረኑ ኢስላም የሚለውን በግልፅ ያስተምራሉ፡፡ ኡለማ ያልሆኑ በዲን ስም የሚንቀሳቀሱት ደግሞ ሰይጣን እየጋለባቸው የጠላትን አጀንዳ እያስፈፀሙ ሙስሊሞችን እና ሙስሊም አገራትን ለመከራ ይዳርጋሉ፡፡
በነገራችን ላይ አገራችንም ላይ ይሁን ሌሎች ቦታዎች ላይ ስሜታቸውን አምላኪዎች የሳውዲ ኡለሞችን “የንጉሳዊያን ስልጣን ጠባቂዎች”፣ “የአምባገነኖች ምርኩዞች”፣ “የቤተሰመንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች” እንዳሏቸው ሁሉ ነብዩ ሙሐመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምን ሊሏቸው ነው?
ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ከእኔ በኋላ የማያዝኑላችሁ መሪዎች ይመጣሉ… ስሟቸው ታዘዟቸው” ብለዋልና ? ? ? ? ? ?
እኮ መልስ ይስጡና ???
የነዚህ ሰዎች ምሳሌ አላህ ቁርኣን ላይ እንዲህ ሲል እንደገለፃቸው ነው
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ قَالُوٓا۟ إِنَّمَا نَحْنُ مُصْلِحُونَ
ለነርሱም «በምድር ላይ አታበላሹ» በተባሉ ጊዜ «እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡
እነሱ አሳማሪ ነን የሙስሊሙ መብት ያስጨንቀናል ቢሉም አላህ እንዲህ ሲል መልስ ሰጣቸው
أَلَآ إِنَّهُمْ هُمُ ٱلْمُفْسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشْعُرُونَ
ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡
አላህ ሆይ! በዲን ስም ዲን ከመናድ በአንተው እንጠበቃለን፡፡ ሀቁን መንገድ ምራን በጠላቶቻችን ላይ ድልን አጎናፅፈን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምረሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

ጥፋታቸውን በዲን ሽፋን ቀብተው ይለቁና ሲጋለጡ እንዲህ ይሉናል
“የሰውን ነውር አትከታተሉ”
እኛም እንዲህ እንላቸዋለን
“ነውር ከሆነ ለምን ለቀቁት?”
ስለዚህ በዲን ስም የሚለቀቅ ጥፋታቸውን ህዝብ ይጠነቀቀው ዘንድ እኛም በአደባባይ እናጋልጠዋለን፡፡ የግል ጉዳይ ከዲን ጋር የማይገናኝ ከሆነ የሙስሊም ነውር ስለሚሸፈን እኛም እንሸፍነዋለን፡፡ የእኛንም አላህ ሸፍኖልናል፡፡ አላህም የሁላችንንም የግል ወንጀል ይሸፍንልን፡፡
“የሰውን ነውር አትከታተሉ”
እኛም እንዲህ እንላቸዋለን
“ነውር ከሆነ ለምን ለቀቁት?”
ስለዚህ በዲን ስም የሚለቀቅ ጥፋታቸውን ህዝብ ይጠነቀቀው ዘንድ እኛም በአደባባይ እናጋልጠዋለን፡፡ የግል ጉዳይ ከዲን ጋር የማይገናኝ ከሆነ የሙስሊም ነውር ስለሚሸፈን እኛም እንሸፍነዋለን፡፡ የእኛንም አላህ ሸፍኖልናል፡፡ አላህም የሁላችንንም የግል ወንጀል ይሸፍንልን፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
👆🏻እነሱ ሳይፈልጉ ተከታዬቻቸው ነው ፎቶዋቸውን ፖስት የሚያደርጉት ለሚሉ ወንድም እና እህቶች ማስረጃ ይሆናቸው ዘንድ እና እነሱ እራሳቸው ፎቶዋቸውን ኡምራ ሲያደርጉ፣ ሰደቃ ሲሰጡ እና ሌላም ሲያደርጉ አምነውበት ለመሆኑ ይህችን ማስረጃ እንካችሁ፡፡ አንድ ወንድሜ እንዲህ አለ
አላህ በሀዲሰል ቁድስ እንዲህ አለ፦
«ፆም የእኔ ነው በእርሱም የምመነዳው እኔው ነኝ!»
ይህን ገለፃ ይበልጥ የሚያጠናክረው ነገር ቢኖር ሰዎች ዑምራቸውን እንደሚፖስቱት ሁሉ ፆማቸውን መፖሰት አለመቻላቸው ነው!
ዐጃኢብ!!!!!
አላህ በሀዲሰል ቁድስ እንዲህ አለ፦
«ፆም የእኔ ነው በእርሱም የምመነዳው እኔው ነኝ!»
ይህን ገለፃ ይበልጥ የሚያጠናክረው ነገር ቢኖር ሰዎች ዑምራቸውን እንደሚፖስቱት ሁሉ ፆማቸውን መፖሰት አለመቻላቸው ነው!
ዐጃኢብ!!!!!
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
የኢኽዋኖች ሚዛን?
አሁን ያለው የኳታር መሪ (አላህ ይጠብቀው) አባቱ እና አያቱ?
አሁን ያለው የኳታር መሪ (አላህ ይጠብቀው) አባትየው ከአያትየው በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ሲቀማ ኢኽዋኖች ዝም አሉ፡፡ አሁን ያለው የግብፅ መሪ ሲሲ (አላህ ይጠብቀው) ከሙሐመድ ሙርሲ ስልጣን በመፈንቅለ መንግስት ሲቀማ ኢኽዋኖች ሁሉ ተንጫጩ፡፡
ለምን?
አሁን ያለው የኳታር መሪ (አላህ ይጠብቀው) ከአባቱ ስልጣንን ሲረከብ ኢኽዋኖች ዝም አሉ፣ ጭራሽ አደናነቁት፡፡
ታላቁ ሰሃባ ሙአዊያ ኢብን አቡ ሱፍያን (ረድየላሁ አንሁ) ለልጁ ስልጣን ሲያስተላልፍ የሚከተለውን አሉ “ይሄ በኢስላም መሰረት የለውም” ነው እና የመሳሰለውን አሉ፡፡
ሳውዲዎቹ መሪዎች (አላህ ይጠብቃቸውና) ወንድም ለወንድሙ ወይንም አባት ለልጁ ስልጣን ሲያስረክብ ኢኽዋኖች “ስልጣን በዘር መወራረስ በኢስላም የለም” አሉ፡፡
ለኳታር ሲሆን ዝምታ ለሳውዲ ሲሆን ተቃውሞ የሆነው በምን ምክንያት ነው?
አህሉሱና ወል ጀመኣ ሙስሊም መሪ በሰላምም ይያዝ በሃይል በመልካም እስካዘዘ ድረስ ለሱ መስማት እና መታዘዝ አለ ይላሉ፡፡ ኢኽዋንን የመሰሉ የጥመት ቡድኖች እነሱ የሚፈልጉት ሲነግስ መስማት እና መታዘዝ አለብን እሱን መቃወም ክልክል ነው ይላሉ፡፡ እነሱ የማይፈልጉት ሲሆን ስሙን ያጠፉታል፡፡ በሰይጣናዊዉ አልጀዚራ ጣቢያቸው ህዝብ እንዲያምፅበት ይቀሰቅሳሉ፡፡
አላህ ሙስሊም መሪዎችን በጠቅላላ ባሉበት ይጠብቃቸው፡፡ ህዝባቸውንም መሪዎቹንም አላህ ለመልካሙ ይለግሳቸው፡፡ አላህ በመሪዎቹ መካከልም ይሁን በህዝባቸው መካከል መስማማትን ይለግሳቸው፡፡
ኢኽዋኖች ተንቅቶባችኋል፡፡