በ Ibnu Munewor
"አልጠጣም" በቂ መልስ አይደለም
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
"በአላህና በመጨረሻው የሚያምን የሆነ ሰው አስካሪ መጠጥ ከሚጠጣበት ማእድ ላይ እንዳይቀመጥ።"
አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።

ማን ነው ‹‹ሸሂድ (ሰመዓት)፣RIP (Rest in Peace)›› የሚባለው?
አንዳንድ ወንድምና እህቶች በአላህና በመልክተኛው መታመን ባለበት ሁሉ የማያምኑ ካፊሮችን ‹‹ሸሂድ (ሰመዓት)፣ RIP (Rest in Peace)›› ብለው ሲፅፉና ሲናገሩ ይሰማል፡፡ ይሄ ከባድ ስህተት ነው፣ እርምት ይሻል፡፡
አደለም በአላህ፣ በመልክተኛው መታመን ባለበት ሁሉ ያላመነን ካፊር፣ ሙስሊም የሆነን ሰው እንኳን አላህና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከመሰከሩለት ሰው ውጭ እኛ ከመሬት ተነስተን ‹‹ሸሂድ (ሰመዓት)›› አንለውም፡፡
ኢማም አል-ቡኻሪ በሰሂሀል-ቡኻሪ ‹‹እገሌ (እንትና) ሸሂድ (ሰመዓት) አይባልም›› ብለው አርስት አዘጋጅተው የሚከተለውን ሀዲስ ዘግበውልናል
ሰህል ኢብን ሰዓድ አሳኢድይ (ረድየላሁ አንህ) ‹‹የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እና ሙሽሪኮች ፊት ለፊት ጦር ተጋጥመው ነበር፡፡ የአላህ መልክተኛም (ﷺ) ሙሽሪኮችም ወደ ካምፓቸው ሲመለሱ፣ ስለ አንድ ብቻውን ያገኘውን ሙሽሪክ ሁሉ በሰይፉ ስለሚገድል ባልደረባቸው አንድ ሰው አወራ፡፡ እንዲህም አለ ‹‹ዛሬ እንደዛ ሰው በትክክል ስራውን (ውጊያውን) የሰራ የለም››
የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ግን ‹‹ይህ ሰው ከእሳት ሰዎች ነው፡፡›› አሉ፡፡
ከሰዎች አንዱ ይህን ሰው መከታተል አለብኝ አለ (የአላህ መልክተኛ (ﷺ) የእሳት ነው ያሉትን ሰው ማለት ነው)
አብሮትም ሆነ ሲቆም ይቆማል፣ ሲሮጥ ይሮጣል፡፡ (ጀግና) የተባለው ሰውየም ቆሰለ ሞቱንም ማፍጠን ፈለገ፡፡ የሰይፉን መያዣ መሬት ላይ ቀበረውና ሁሉቱ ደረቶቹ መሃል ላይ አድርጎ ሰይፉ ላይ ተኛበት በዛውም ሞተ፡፡
ሌላኛው ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ዘንድ መጥቶ ‹‹የአላህ መልክተኛ መሆኖትን እመሰክራለሁ›› አላቸው፡፡ አል-ቡኻሪ 2898 ……………….
ከዚህ የምንረዳው የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ከመሰከሩለት ሰው ውጭ እኛ አንድን ሰው ሸሂድ ነው፣ ለዲን ሲል ነው የሚታገለው ማለት አንችልም፡፡ ምክንያቱም ለአላህ ብሎ የሚታገለውን አላህ ብቻ እንደሚያውቀው አቡሁረይራ ባስተላለፉት
وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَنْ يُجَاهِدُ فِي سَبِيلِهِ
‹‹አላህ የበለጠ ያውቃል ማን በእሱ መንገድ ላይ እንደሚታገል›› ሀዲስ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ነግረውናል ሰሂሀል አል-ቡኻሪ 2787፡፡
RIP (Rest in Peace) በሰላም እረፍ እንደማለት ነው፡፡ ይህን አባባል ከሙስሊም ውጭ ለሆነ ሰው መጠቀም በፍፁም አይገባም፡፡ ምክንያቱም የሚቀጥለው አለም ጌታ አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላን በትክክለኛ እምነት፣ በንፁህ ልብ፣ በነብዩ (ﷺ) ሱና፣ መታመን ባለበት ሁሉ አምኖ ለሄደ ብቻ ነው ሰላም ያለው፡፡ ከዛ ውጭ ግን ከባድ አደጋ ነው፡፡ አላህ የሚቀጥለው አለም ለነማን እንደሆነ ሰላም ያለው እንዲህ ሲል ይናገራል
ውዱ የአላህ ባርያ ነብየላህ ኢብራሂም (አለይሂ ሰላም) እንዲህ አለ
وَلَا تُخْزِنِى يَوْمَ يُبْعَثُونَ
በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፡፡
يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ
ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡
إِلَّا مَنْ أَتَى ٱللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»
ይህ ነው እንግዲህ ተጨባጩ ሁኔታና እውነታ፡፡ ዛሬ ሙስሊም ያልሆነ ዘፋኝ፣ አርቲስትና የመሳሰለው ሲሞት RIP (Rest in Peace) እያሉ የሚፅፉ ስንቶች ናቸው፡፡ አላህ እውቀትን ይስጠንና፡፡
ማጠቃለያ፡-
1) ለካፊር ሰመዓት (ሸሂድ) አይባልም፣
2) ለሙስሊምም በጥቅሉ በአላህ መንገድ ላይ የሞተ ሸሂድ ነው እንላለን እንጂ እከሌ ብለን አንድን ሰው ነጥለን ሸሂድ ነው አንልም፡፡ ምክንያቱም መለኮታዊ ራእይ የማይለያቸው ነብዩ (ﷺ) ብቻ ናቸው እንዲህ ብለው ሊናገሩ የሚችሉት፡፡ እሳቸው ደግሞ ሞተዋል፡፡ በሳቸው ሞት ደግሞ መለኮታዊ ራእይ ተቋርጧል፡፡ ከሳቸው ባኋላ ማንም ይህን መናገር አይችልም፡፡ ኢንሻ አላህ ሸሂድ ይሆናል ብለን ግን መመኘትና ዱዐ ማድረግ ችግር የለውም፣
3) ለካፊር RIP (Rest in Peace) አይባልም፣
4) ሙስሊም የሆነ ሰው ሲሞት እንዲያውም ዱዓ እናደርግለታለን፡፡ አላህ ይዘንልህ/ሽ፣ ይማርህ/ሽ፣ ቀብርህን/ሽን ያስፋልህ/ልሽ እያልን፡፡
አላህ ሸሪዐችንን ጠንቅቀን የምናውቅ፣ የምንሰራበትም፣ የምንፀናበትም ያድርገን፡፡ ከአላህ ውጭ ሃይልም ጥበብም ብልሃትም የለም፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው፣ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts

እስኪ እንነጋገር!
በሙስሊም መሪ ላይ አምፆ ስለመውጣት ያሉ ብዥታዎችና መልሶቻቸው
▶️ካሉህ: በዳይ መሪ ላይ አምፆ መውጣት የአህሉ ሱንናን መርህ መቃረን ነው?
⏩በላቸው: አዎን!
▶️ካሉህ: የታለ መረጃችሁ?
⏩በላቸው:
"...إلا أن تروا كفرا بواحا"
"...ግልፅ የሆነ ክህደት (ኩፍር) እስክታዩ ድረስ (ከትዕዛዝ አትውጡ)" የሚለው የዑባዳህ ሐዲስ ነው።
▶️ካሉህ: ክህደት (ኩፍር) ማለት ወንጀል ማለት ነው።
⏩በላቸው: ተሳስታችኋል፣ ምክንያቱም በዓውፍ ኢብን ማሊክ ሐዲስ፣
"مَنْ وَلِيَ عَلَيْهِ وَالٍ فَرَآهُ يَأْتِي شَيْئًا مِنْ مَعْصِيَةِ اللَّهِ فَلْيَكْرَهْ مَا يَأْتِي مِنْ مَعْصِيَةِ اللَّهِ ، وَلا يَنْزِعَنَّ يَدًا مِنْ طَاعَةِ اللَّهِ."
"አንድ መሪ የተሾመበት ሰው አላህ የሚታመፅበትን ወንጀል (መሪው) ሲሰራ ካየ ወንጀሉን ይጥላ፣ (መሪውን በማመፅ) አላህን ከመታዘዝ ግን እጁን እንዳያነሳ" ተብሏልና።
"يا أيها الذين آمنوا أطيعوا الله وأطيعوا الرسول وأولوا الأمر منكم" (القرآن)
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ፣ አላህን ታዘዙ፣ መልዕክተኛውንም ታዘዙ፣ ከናንተ የጉዳዩ ባለቤት የሆኑትንም (መሪዎች ታዘዙ)" (ቁርአን)
▶️ካሉህ: ነገር ግን እኮ ዑመር ረዲየሏሁ ዓንሁ " (ቀዊሙኒይ)(ካጠፋሁ) አቃኑኝ" ብሏል።
⏩በላቸው: ሲጀምር ይህ ዘገባ ሙስነድ ኪታብ ውስጥ ፈፅሞ አልሰፈረም። ሰሒሕ ነው እንኳን ብንል ማቃናት (ተቅዊም) ማለት ማስተካከል (ኢስላሕ) ማለት እንጂ መቀየር አይደለም።
▶️ካሉህ: እና እስከመቼ እንታገስ?
⏩በላቸው: በኡሰይድ ሐዲስ ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም
"...فاصبروا حتى تلقوني على الحوض"
"(ከመሪዎች አድሎና ግፍ ቢደርስባችሁ) ሐውድ ላይ እስክታገኙኝ ድረስ #ታገሱ" ብለዋል።
▶️ካሉህ: ሐቃችንን (መብታችንን) እንዴት እንወስዳለን?
⏩በላቸው: አሁንም መረጃችን ሐዲስ ነው። በኢብኑ መስዑድ ሐዲስ፣
"...أدوا الذي عليكم، وتسألون الله الذي لكم"
"እናንተ ላይ ያለባችሁን ሐቅ ተወጡ፣ የናንተን ደግሞ አሏህን ጠይቁ"
▶️ካሉህ: መታዘዝ የሚገባን መርጠን ለወደድነው መሪ እንጂ ስልጣን ላይ ላለ ወይም በሀይል ለያዘው አይደለም!
⏩በላቸው:
"... اسمعوا وأطيعوا وان تآمر عليكم عبد حبشي"
በዒርባድ ረዲየሏሁ ዓንሁ ሐዲስ፣
"(እናንተ ባትወዱትም) የሐበሻ ባሪያ መሪ ከሆነባችሁ ስሙት ታዘዙትም"
▶️ካሉህ: የምንታገሰው በሸሪዓው መሰረት ለሚመራ መሪ ነው። በስሜቱ እንጂ በሸሪዓው ለማይመራ መሪ ይህ ሐዲስ መረጃ አይሆንም።
⏩በላቸው: ዋሻችሁ! ምክንያቱም በሑዘይፋ ረዲየሏሁ ዓንሁ ሐዲስ፣
"يكون بعدي أئمة لا يهتدون بهداي ولا يستنون بسنتي فاسمع وأطع"
"ከእኔ በኋላ በኔ መንገድ የማይጓዙ፣ በሱንናዬም የማይመሩ መሪዎች ይመጣሉ። (እነኝህን መሪዎች) ስማ ታዘዝም"
(አቡ የሕያ ያሲን፣ ሚያዝያ 11,2010)

በአላህ እና በመልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሳያምን የሞተ ሰው “አላህ ይማርህ፣ አላህ ይዘንልህ አይባልም”፡፡ አላህን እንፍራ፡፡
ሙስሊም ወንድም እና እህቶቼ ሆይ! ኢስላም ማለት ሁሉን ነገር አቅፎ የያዘ የተሟላ ውብ ሃይማኖት ነው፡፡ ዛሬ ሃይማኖታዊ እውቀት ከመማር ተዘናግተን ይሀው አላህ የከለከለውን ሁሉ ስንጥስ ይታያል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
مَا كَانَ لِلنَّبِىِّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَن يَسْتَغْفِرُوا۟ لِلْمُشْرِكِينَ وَلَوْ كَانُوٓا۟ أُو۟لِى قُرْبَىٰ مِنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُمْ أَصْحَٰبُ ٱلْجَحِيمِ
ለነቢዩና ለነዚያ ላመኑት ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢኾኑም እንኳ እነሱ (ከሓዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መኾናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ምሕረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም፡፡
ተመልከቱ የሞቱት ዘመዶቻችን ቢሆኑም እንኳን በአላህ ላይ እስካጋሩ ድረስ ምህረትን እንዳንጠይቅ ታዘናል፡፡ አይደለም የማናውቃቸው ግለሰቦች፡፡
ክርስትያኖችን ብትጠይቋቸው “ዘፋኝ የገሃነም ነው” ይሉሃል፡፡ ታድያ እኛ ምን ቤት ሆነን ነው በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ሳያምን የሞተን ሰው “አላህ ይማርህ” የምንለው?
ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “በአላህ ላይ እያጋራ የሞተ ሰው እሳት ገባ ብለዋል፡፡”
ከእስልምና ውጭ ያለ ሃይማኖት ተከታይ አንድ ሰው እስላም ሆኖ ቢሞት በተሳሳተ መንገድ ላይ እንደሞተ ነው የሚያምኑት፡፡ ፈጣሪ ብለው የሚያስቡትም ያንን ግለሰብ እነሱ የሚጓዙበትን መንገድ ስላልተከተለ እንደማይምረው ነው የሚያምኑት፡፡ እኛም ደግሞ የነብያትን ሁሉ ሃይማኖት እስልምናን ሳይቀበል ከሞተ በተሳሳተ መንገድ ላይ እንደሞተ ነው የምናምነው፡፡ እንዲያውም ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ “ከየሁዳና ከነሷራ ስለ እኔ መላክ አይሰማም፣ ከዛም ሳያምንብኝ አይሞትም የእሳት ቢሆን እንጂ፡፡”
አረ አላህን እንፍራ፡፡ መቻቻል ማለት ሃይማኖታችን የከለከለውን ተግባር እየፈፀምን አይደለም፡፡
አላህ ሆይ! እውቀት ለግሰን፡፡

የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምክር መሬትም ጠብ አይል
እንዲህ ሲሉ መክረውን ነበር ‹‹ሙስሊም መሪ በዳይም፣ ጨቋኝም፣ ገንዘብ የሚቀማም፣ የሚማታም ቢሆን፣ በመጥፎ እስካላዘዘ ድረስ ስሙት ታዘዙት፣ ግልፅ ክህደት እስካላያችሁበት ድረስ››
ሊብያ ላይ የነበረውን መሪ አምፀው ጣሉት ይሀው አገሪቱ ለዚህ ሁሉ መከራ ተዳረገች፣ ግብፅ፣ የመን እና ሌሎችም ቦታዎች ላይ የሰው ሰይጣናት ስልጣን ፈልገው በሃይማኖት ስም ፈተናውን ቀስቅሰው ኡማውን ለዚህ ሁሉ መከራ ዳረጉት፡፡
አላህ ሆይ! የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ትዕዛዝ ከሚያከብሩት አድርገን፡፡

ግራጁዌሽን
አላህ ለዋለልን ውለታ ልናመሰግነው እንጂ ልናምፀው አይገባም፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየአመቱ ግራጁዌሽን (ምርቃት) ሲደርስ ኢስላማዊ መፅሄት ማዘጋጀት አለብን፣ ፎቶ መነሳት አለብን …… እና የመሳሰለውን የሚሉ አልጠፉም፡፡ እንደው የማይሰልመውን ሁሉ ካላሰለምን ማለት ምናለ ቢቀርብን፡፡ የወንድም ይሁን የሴት ሙስሊሞች ፎቶ ተለጥፎ ስም ከነአባባሎች ተፅፈው በጎኑ ጥቄት ሀዲሶች ተደባልቀውበት ኢስላማዊ ሊባል አይችልም፡፡
ኢስላም የሚከለክለውን ሳይከለከሉ ኢስላማዊ ማለት ምንኛ ሞኝነት ነው፡፡ አስገራሚው አንዳንዶች ‹‹ዶሩራ (ለችግር ጊዜ የሚደረግ ነው)›› ይላሉ፡፡ እስቲ የሙስሊሞች መፅሄት ተብሎ የወጣት ሴቶችንና ወንዶችን ፎቶ አለመለጠፉ ምኑ ነው ችግር?
እንዲያውም ይሄ ፅድቅ፣ አላህን መታዘዝ እንጂ (ፎቶ አለመለጠፉ)፡፡
ያው ሳታማሃኝ ብላኝ እንዳለው ነው፡፡ ሴትና ወንድ ወጣቶችን መደባለቅ ማለት እሳትና ጭድን የመደባለቅ ያህል ነው፡፡ አስገራሚው ኢስላማዊ የሚል ስም ይሰጡታል፡፡ ተመራቂ ተማሪዎች ሆይ! እንዲህ አይነት አፀያፊ ተግባሮችን ራቋቸው፡፡ ‹‹የአሚር ትዕዛዝ ነው›› የሚባለውንም ቅጥፈት ወደ ጎን ተዉት፡፡ አላህ በሚታመፅበት ጉዳይ ፍጡራንን መታዘዝ የለም ይሉናል የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፡፡
ድሮ የዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበርን ጊዜ ሸውደውን ነበር ‹‹ቁጥራችንን ማሳየት አለብን›› ፎቶ እንነሳ እያሉ፡፡ አላህ መርቶን ከሱና ኡስታዞች ጋር አስተዋውቆን ኢስላም ማለት በስሜት መነዳት እንዳልሆነ፣ ሱናን መከተልና ቢድዐን መራቅ እንደሆነ አስተማሩን፡፡
አልሃምዱሊላህ፡፡
ሙስሊም ተመራቂ ተማሪዎች ሆይ! አላህን ፍሩ ፎቶዋችሁ የሌለበት ከኢስላም አስተምህሮት ለናንተ የሚጠቅሙ ፅሁፎች እና ትምህርቶች ያሉበትን ትምህርት ብቻ አዘጋጁ፡፡ የሴትም ይሁን የወንድ ፎቶ እና አድራሻ መፅሄት ላይ ማስቀመጥ በፍፅም አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም ይሄ መልክቱ ሰዎችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ መምራት ነውና፡፡
አላህን እንፍራ በምርቃት ዙሪያ ከሚሰሩ ኢስላም የሚጠላቸውን ነገሮች ሁሉ እንራቅ፡፡
አላህን የፈራ አላህ መውጫ ቀዳዳ ያደርግለታል፡፡

ማን ነው የመንግስት ቅጥረኛ?
እዩልኝ እነዚህን ደፋሮች?
አንዴ ቱርክ ሄዶ ሃውልት በጀርባው አድርጎ ሱሪውን ከቁርጭምጭሚቱ በታች አድርጎ ፎቶ ተነስቶ ይለቃል፡፡ ዛሬ ደግሞ ሰላት ሲሰግድም ፎቶ ተነስቶ ያውም የሚከተለው ማሞካሻ እና የድፍረት ውዳሴ ታክሎበት ፎቶ ተለቀቀለት
“በዛሬው እለት ጀግናው ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በጠቅላይ ሚኒስተር ደ/ር አብይ አህመድ ቤተመንግስት ውስጥ ያለማንም ፍራቻ በሚገርም ሁኔታ ሰላቱን ሰገደ አላሁአኩበር! አላሁአኩበር….”
ጥያቄ አለኝ “ያለማንም ፍራቻ በሚገርም ሁኔታ ሰላቱን ሰገደ” የሚለው ያለ እውቀት ምስክርነት ነው፡፡ አንድ ሰው የሰራውን ቢሰራ ለማን እንደሰራው የሚያውቀው የሚመሰክረው አላህ እና መለኮታዊ ራእይ የማይለያቸው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ብቻና ብቻ ናቸው፡፡ አሁን እንዲህ በድፍረት ሰው ማደናነቁን ምን አመጣው?
ኢኽዋኖች አንድ ሰው የነሱን ሀሳብ ስላልተቀበለ ብቻ ቀበሌ እናኳን ባያዩት አፋቸውን ሞልተው “የወያኔ ቅጥረኛ፣ የመንግስት ተላላኪ፣ ሙናፊቅ” ይሉታል፡፡ በተጨባጭ ከመንግስት እና ባለስልጣናት ጋር አንድ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ መግለጫ ሲደሰኩር የሚያዩትን ብሎም ቤተመንግስት እንዲህ ሲገባ የሚያዩትን ግለሰብ ግን “ዶ/ር አብይ አህመድ ቤተመንግስት ውስጥ ያለማንም ፍራቻ በሚገርም ሁኔታ ሰላቱን ሰገደ” እያሉ አላህ ብቻ ለማን እንደተሰራ የሚያውቀውን ሰላት እንኳን የሚያውቁትን ምስክር ይመሰክሩለታል፡፡
ካሚል ሸምሱ ቤተመንግስት ምን ሊሰራ ነው የገባው?
ካሚል ሸምሱ ሰላት እየሰገደ ለምን ፎቶ ይነሳል?
ካሚል ሸምሱ እና ጓደኞቹ ለምን ረመዳን ሲፆሙ ከንፈራቸው ደርቆ ፆመኛ ነን ብለው ለምን ፎቶ አይነሱም?
ለፎቶ አፍቃሪያን እስካሁን ያልተሰራው ካሜራ ፆመኝነታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
ሰዎችን ቅጥረኛ ቅጥረኛ እያላችሁ በውሸት ስትለፍፉ ዛሬ በራሳችሁን ስራ እራሳችሁ ፈራጅ ሁኑ፡፡
ቤተመንግስት እና የመንግስት ቤሮዎች እና ስብሰባዎች ላይ ከመዞር በሺርክ፣ በቢድኣ፣ በጫት እና በሌሎች ጎጂ ነገሮች እየተሸደ ያለውን ህዝብ መታጠቂያችሁን ጠበቅ አድርጋችሁ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንደለፉት ይህንን ህዝብ ከዚህ አደገኛ መርዝ ለማውጣት ብትለፉ ነው የሚሻላችሁ፡፡ አለበለዚያ ከዚህ በፊት እንደወደቃችሁት፣ አሁንም እንደወደቃችሁት፣ ለወደፊትም ትወድቃላችሁ፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ውርደትና ክብረቢስነት ትእዛዜን በጣሰ ላይ ሁሉ ሆነ” ብለዋል፡፡

አላማው አንድ ነው፡፡ መገለባበጥ ግን ባህሪያቸው ነው?
- ሀሰን ታጁ ድብን አድርጎ በየመፀሀፉ ሲሰብክ እና ሲተረጉም ሲያደናንቅ እና ኡማውን ሲጣራ የነበረው ወደዚህ ኢኽዋነል ሙስሊሚን ወደተባለ የጥመት ቡድን ነበር፡፡
- አብይ ጣሰው የተባለውም የሀሰን ታጁ እና የኢድሪስ ሙሐመድ ደረሳ በነሱው አካሄድ በመጓዝ ጭራሽ “ሉቅማን” የሚባል መፅሄት ላይ ሰሃባዎችን እያጥላላ ስለ ኢኽዋን መልካምነት ሲሰብክ ነበር፡፡
- ያሲን ኑሩም በመፀሃፎቹ፣ በድምፅ ፋይሎቹ ኢኽዋንን እና መሪዎቹን እያደናነቀ በኳታር ጉዞው የጥመት ባለቤት የሆነውን የፈተናውን ሸህ እሾሁን ቀርዳዊ እጅ አቅፎ ፎቶ ተነስቷል፡፡
ዛሬ ግን እነ አብይ፣ እነ ሀሰን ኢኽዋን እንዳልሆኑ አደርገው ለመናገር በል እንዲያውም የኢኽዋን አካሄድ ላይ ትችት ቢጤ ጣል ሲያደርጉ እና እነሱ “ሱፊ” የተባለው መንገድ ጠበቆች እንደሆነ ለመናገር ይሞክራሉ፡፡ እውነታው ግን የኢኽዋኑ መስራች ሀሰን አል-በና ድብን ያለ ሱፊ መሆኑ ነው፡፡
ያሲን ኑሩ እና ጓደኞቹ በተገላቢጦሹ ከነ ሀሰን ታጁ እና አብይ ጣሰው ጋር ተጣልተናል ቢሉም እነሱም የሱፍያም ይሁን የኢኽዋን ዋና ጠበቆች ናቸው፡፡ ለአንድ ጉዳይ በተለያየ መንገድ የሚጓዙ ተሳስተው ኡማውን የሚያሳስቱ ናቸው፡፡
እነ አብይ ጣሰው አሁን የመጅሊስን ምርጫ ጉዳይ አቡበከር አለሙ ከሚባለው ሌላ አሽአሪ፣ የኢኽዋን አቀንቃኝ ጋር ሰጣ ገባ ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ አቡበክር አለሙ ደግሞ የሀሰን ታጁ የሙሪዶች ሁሉ ሙሪድ ነው፡፡ እዛው ለዛው የተቆላለፉ ናቸው፡፡
እነ ያሲን ኑሩ እና አቡበክር አህመድን ደግሞ ተከታዬቻቸው የኢትዬጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆኑ እያሉ ሁሉ ምኞታቸውን ይፅፋሉ፡፡
የኢትዩጵያ ሙስሊሞች ሆይ! በነዚህ ሰዎች አካሄድ አትደነቁ፡፡ ሲገለባበጡ ለአንድ አላማ ነው፡፡
ኢኽዋን ለአንድ አላማ የተለያየ መስሎ መስራትን ይችሉበታል፡፡ ሁሉም የጋራ ጠላት አላቸው፡፡ ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚጣሩ ሰዎች ሁሉ የነሱ ጠላት ናቸው፡፡ ሺርክን የሚያጨማልቁ ሱፍዬች፣ ቲጃንዬች ጋር ደግሞ አንድ ናቸው፡፡ ወዳጅም ናቸው፡፡ አህባሾችን “ለፖለቲካል አጀንዳቸው ብቻ ነው የምንቃወማቸው” ያለም ደፋር ኢኽዋኒ አለ፡፡
የሚገርመው ግን ስልጣንን የተመኘም አያገኛትም፡፡ አላህ ለፈለገው ስልጣን ይሰጣል፣ ከፈለገው ካይ ይገፋል፡፡ ምናለ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለህዝቡ ቅኑን መንገድ ይፋ እንዳደረጉት እርኩሱን መንገድ ሁላ እናዳጋለጡት የሳቸውን ፈለግ ተከትለው ቢሄዱ?
ለሁላችንም በላጭ ይህ መንገድ ብቻ ነው፡፡
ዛሬ የሚያሳዝነው በጫት ሱስ የሰከረ ግለሰብ አያፍርም መፀሀፍ ፀሀፊ ነኝ ይላል "ጫት በአመት 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኛል" እያለ ለአረንጋዴው መርዝ ጠበቃ ሲሆን አየነው። እነዚሁ ሰዎች ናቸው ካልመራናችሁ፣ እኛ እንዳልናችሁ ሁኑ፣ የህዝብ ወኪሎች ነን፣ የኮሚቴው ወዳጆች ነን የሚሉን፡፡
ጌታዬን ከልቤ የማመሰግነው የነዚህን ሰዎች ተንኮል እና መጥፎ አካሄድ እጠነቀቀው ዘንድ ስለረዳኝ ነው፡፡ አላህ የኢትዬጵያን ሙስሊም ከነዚህ ሰዎች መርዝ ይጠብቀው፡፡

ተመልከቱ እንዲህ አይነቱን አደገኛ መርዛም ቅጠል ነው በጫት ሱስ ያበዱ ያውም ደራሲ ነን ባዬች "ጫት በአመት 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኛል" እያሉ የሚደሰኩሩት፡፡
አላህ ከጠሞ አጥማሚዎች፣ ለህዝብ የማያስቡ መርዛሞች ይጠብቀን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አላህ ከጠሞ አጥማሚዎች፣ ለህዝብ የማያስቡ መርዛሞች ይጠብቀን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አብዛኛው የሀገራችን ህዝብ በሺርክ፣ በቢድኣ፣ በጥንቆላ፣ በባእድ አምልኮ፣ በአደንዛዡ ጫት ተወሯል፡፡ ኢኽዋነል ሙስሊሚን የተባለው የጥመት ቡድን ተከታዬች በዚህ አደገኛ ሰኣት ስለ መጅሊስ ምርጫና ስልጣን አለፍ ሲልም ፓርላማ ለመግባት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡
የሰው ልጆች ሁሉ ፈርጥ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ግን ከምንም በፊት ሺርክን (በአላህ ላይ ማጋራትን) ነበር የተዋጉት፡፡ ስልጣን እንስጥህ ዝም በል ሲባሉም እምቢ ነበር ያሉት፡፡
የሀገራችን ኢኽዋኖች ከአዲስ አበባ ሰዎች “ጎዙ ወደ አብሬት” ብለው ቀብር ሊያመልኩ ሲሄዱ፣ ብሎም መንገድ ላይ መኪና ተገልብጦ የሞቱትን “ሬሳውን አንሰጥም ለአብሬት ነይቶ ነው የወጣው” ሲባል ሁሉ እየተሰማ እነሱ ግን ዝም ነው የሚሉት፡፡
- ከዚህ የበለጠ ወንጀል አላህ ዘንድ አለ?
- እደግመዋለሁ ከዚህ የበለጠ ወንጀል አላህ ዘንድ አለ?
- እደግመዋለሁ ከዚህ የበለጠ ወንጀል አላህ ዘንድ አለ?
ታድያ እሳቸውን በተግባር ሳይከተሉ “ፊዳከ” እያሉ መዝፈኑ ምን ዋጋ አለው? ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለድል የበቁት የአላህን መብት አላስነካ ብለው ነው፡፡ ዛሬ ኢኽዋኖች በመውሊድ ሰበብ አላህ ላይ ሲጋራ ከመቃወም ይልቅ “አይለያየንም” ብለው አረፉት፡፡ አስገራሚው ግን መጅሊስ ላይ የተቀመጡትም ይሁን ከዚህ በፊት የነበሩት የሽርክ መናሃሪያ የሆነውን መውሊድ አግበስባሾች ናቸው፡፡ ታድያ ለምን ይሆን ለመጅሊሱ ስልጣን ሲሆን “አንለያይም ብትመሩንም ችግር የለውም” ያላሏቸው?
መቼም የኢኽዋኖችን ተንኮል አላህ ያስረዳው ሰው አላህን ከልቡ ሊያመሰግን ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም በጣም አታላይ እና ሸዋጆች ናቸው፡፡
ከዚህ በፊት ከመንግስት ጋር ሰላም በነበሩ ጊዜ “ለኢስላም ነው” አሉ፡፡ ከመንግስት ጋር ሲጣሉ እና ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ጓደኛ ሲሆኑ “ለኢስላም ነው” አሉ፡፡ አሁንም መልሰው ጓደኛ ሲሆኑ መንግስትን ማወደሱን ይዘዋል፡፡ ደግሞ ነገ ሲጣሉ ዝም ብላችሁ ታዘቧቸው፡፡ ገርሞ የሚገርመው ግን ጭፍን ተከታያቸው ነው፡፡ ቢያንስ ቢያንስ የራሳቸውን አቋም መመዘኛ አድርጎ ቢያየው እኮ እጅ ከፍንጅ ይይዛቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ጭፍን ተከታይነት መርዝ ነው፡፡ አላህ ሀቅን በሀቅነቱ ያሳየን የምንቀበለውም ያድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ ያሳየን የምንርቀውም ያድርገን፡፡

"አቶ ሐሰን" ወደ ቤተ መግስት ጥሪ ከተደረገላቸው ሰዎች ጋር አብሮ ተጋበዘ። እዚያው ሳለም የሶላት ወቅት ደረሰበትና ተነስቶ ሶላት ሰገደ።
አሁን ይሄ ዜና መሆን የሚችል ርእስ ነው? አሁን ይሄ ጀብድ ሆኖ የሚወራ ጉዳይ ነው? ምነው የሰዎቹ የአስተሳሰብ እድገት እንደ ካሮት ቁልቁል ሆነሳ?
ቤተ መንግስት በመግባት የመጀመሪያ ሙስሊሞች የሆኑ መሰላቸው? ወይስ እስከዛሬ የሚገቡት ሙስሊሞች ሳይሰግዱ ነበር የሚመለሱት ብለው ነው የሚያስቡት?
የለም የለም! ከዚህ በፊትም ብዙ ሙስሊሞች ገብተዋል። በጀማዐም ጭምር የሰገዱ አሉ። ልዩነቱ ግን እነዚያ ቤተ መንግስት መግባታቸውን ትልቅ ነገር አድርገው ሲኮፈሱበት አልገጠመንም። ለጌታቸው የሰገዱትን ሶላት በፎቶ አስደግፈው ለህዝብ "እዩልን" ብለው ሊበትኑ ይቅርና።
ዛሬ ግን እዩኝ የነገሰበት ህብረት ሐረካቱንም ሰከናቱንም በካሜራ እየቀለመ በመበተን ጢባጢቢ የሚጫወትበት መንጋ ማግኘቱ ገርሞ ገርሞ የሚገርም ነው።

ቤተመንግስት ውስጥ ሰላት መስገድ?
ምድር ሁሉ የአላህ ናት፡፡ አንድ ሙስሊም ሰላት ወቅቱ ሲደርስበት አውሮፕላን ላይም፣ መርከብ ላይ የትም ይሁን የት ይሰግደዋል፡፡ ዱርዬ የሚባለው ሙስሊም እንኳን ሰላት ሲሰግድ ፎቶ አይነሳም፡፡ ዛሬ ዛሬ እነ ጋሽ ብርቂ ግን ቤተመንግስት ውስጥ መስገድ እንደ ትልቅ ጀብዱ ይቆጥሩታል፡፡ እሱንም በፎቶ ተነስተው “ቤተመንግስት ውስጥ ያለማንም ፍራቻ በሚገርም ሁኔታ ሰላቱን ሰገደ” ይባልላቸዋል፡፡ እውነት ቤተመንግስት ውስጥ ሰላት ለመስገድ እነሱ የመጀመሪያው ናቸው እንዴ? ወይንስ ከነሱ በፊት የሰገዱት እና ፎቶ ያልተነሱት ለጣኦት ነበር የሰገዱት? ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡
- አንድ ሰው እናቱን ቢስም እና ቢንከባከብ አላህ ስላዘዘው ነው፡፡ እሱ ብቻም አይደለም እናቱን የሚወደው፡፡ እነ ጋሽ ብርቄ እናታቸውን ለመዘየር ሲሄዱ ካሜራ ማኖቻቸው አሉ፡፡ የእናታቸው ጉልበት ሲስሙ ካሜራ ማኖቻቸው ቀጭ አድርገው ያነሷቸዋል፡፡ እነሱም አይከለክሉም፣ ከዛም ያቺ ፎቶ “አሚራችን እናቱን ሲስም፡፡ ጀነት በእናት እግር ስር ናት” የሚባል መለወሻ ተጨምሮባት ትለቀቃለች፡፡
- እነ ጋሽ ብርቄ መስጊድ ውስጥ ገብተው ህፃናትን ከኋላቸው አድርገው እራሳቸውን ሰልፊ ያነሳሉ፡፡ ከዛም ሶሺያል ሚድያ ላይ ይለቁታል፡፡
- እነ ጋሽ ብርቂ አረብ ሀገር ካሉ ሴቶች ተሰብስቦ የመጣውን ብር ለደሃ ሲሰጡ ልክ ፖለቲከኞች እርዳታ ሲሰጡ ፎቶ እንደሚነሱት እነሱን ይነሳሉ፡፡
- እነ ጋሽ ብርቄ የውሃ ቦቴ ትልቅ መኪና ውስጥ በካሜራ ለማንሳት አልታይ ሲላቸው በሹፊሩ በኩል ያለውን በር ከፍተው ይነሳሉ፡፡ የሚያሳዝነው ካሜራ ማኖቻቸው መሰላል ላይ ቢወጡም መስታዎቱ ስለሚከልላቸው የሹፊሩን በኩል በር ከፍተው አጅሬ የከባድ መኪና መሪ ይዞ ፎቶ ይነሳል፡፡
- ከሁሉ የሚገርመው እነ ጋሽ ብርቄ ለድሆች የሚሰጥ እህል ተሸክመው ፎቶ ለመነሳት ያለ አቅማቸው ሁለት ሰው የሚሸከመውን ለብቻቸው እሸከማለሁ ሲሉ ወደቀባቸው፡፡ ይህም በቪድዬ ተቀርፆ ፌስ ቡክ ላይ ተለቀቀ፡፡
ከነሱ ሌላ ለድሃ የሚረዳ እንደሌለ፣ ከነሱ ሌላ ለዲኑ የሚለፋ እንደሌለ፣ ከነሱ ሌላ በሽተኛ የሚጠይቅ እንደሌለ በፎቶ እና ቪድዬ ፕሮፖጋንዳ ልክ እንደ ፖለቲከኞች ህዝቡ ላይ ሊደግሙበት ይፈልጋሉ፡፡
ማንን አስበው ይሆን ስራን የሚሰሩት ቤተመንግስት፣ ሀረም፣ ዋይት ሀውስ፣ ባህርም ላይ፣ ሰማይም ላይ አላህ ይመለካል፡፡ አንድ ሰው ደግሞ አላህን የሚያመልከው ለእራሱ ሲል እንጂ ለሰዎች ሲል አይደለም፡፡ አንድ ሰው ቤተመንግስትም ይሁን ዩናይትድ ኔሽን ላይ የሚሰግደው ለነፍሱ ሲል ነው፡፡ ጀብዱም አይደለም ግዴታ እንጂ፡፡
ይልቁንስ ትላትን “የተቃውሞ ሰልፉን የሚቃወሙ የመንግስት ቅጥረኛ ናቸው፡፡” ሲሉ እንዳልነበር ዛሬ ቤተመንግስት ድረስ ግብዣ ተደርጎላቸው ገብተዋል፡፡
የሱና ኡለማዎችን “የቤተመንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች” ሲሉ ነበር፡፡
እነ ጋሽ ብርቂ ቤተመንግስት ሲገቡም ተከታዬቻቸው ጥያቄ እንዳያነሱ “ለኢስላም ነው፡፡” የሚል ቅብ ይቀቡላቸዋል፡፡ ከመንግስት ጋር ሲጣሉም “ተው እንጂ ከመንግስት ጋር ጓደኛ አይደላችሁ እንዴ?” ሲባሉ “ኢስላም አደጋ ላይ ስለወደቀ ነው” የሚል ቅብ ይቀቡታል፡፡
አላህ ግን ምስጋና ይገባው እነዚህ ሰዎች የያዙትን ይፋ እያደረጉ አላህም እያጋለጣቸው ሙስሊሙ ቀስ በቀስ እያጋለጣቸው ነው፡፡
ትላንት ሀሰን ታጁ አብሯቸው ነበር፡፡ መሃል ላይ የተለያዩ መሰሉ፡፡ ዛሬ ደግሞ አብረው ቤተ መንግስት ገቡ፡፡
ቤተመንግስት መግባት ለነሱ ሲሆን ………..?
አላህ ሆይ! ኡመተል ኢስላምን ከማታለል ባንተ እንጠበቃለን፡፡

የረመዳን ቱሩፋቶች
1) የጀነት በሮች ይከፈታሉ፣ የጀሃነም በሮች ይዘጋሉ፣ ሰይጣናት ይጠፈራሉ፣
2) አምኖ እና ሂሳቤን አላህ ይከፍለኛል ብሎ ለፆመው ወንጀል ያስምራል፣
3) ትክክለኛ ፆም አላህን መፍራት ያላብሳል፣
4) ከ 1000 ወራት የምትበልጠዋ ልዩ ለሊት በረመዳን ውስጥ ትገኛለች፣
5) በረመዳን ወር ኡምራ ማድረግ ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር ሀጅ እንደማድረግ ይቆጠራል፣
6) ፆም የቸርነት ወር ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቸር ነበሩ፣ ይብልጥ ደግሞ በረመዳን ቸር ነበሩ፣
7) ፆም ጋሻ ነው፣
8) ፆመኛ ሰው ሁለት ደስታ አለው አንድ ሲያፈጥር ሁለት ጌታውን ሲገናኝ፣
9) ፆም ያማልዳል፣
10) ረመዳን የአንድነት ወር ነው እና ሌሎችም፡፡
አላህ ረመዳን ደርሰው ከሚጠቀሙበት ያድርገን፡፡

ረመዳን አልደረሰምን….?
ጠለሃ ኢብን ኡበይዳህ (ረድየላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት
ሁለት ሰዎች ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘንድ መጥተው በእኩል ወቅት እስልምናን ተቀበሉ፡፡ አንደኛው ከሌላኛው በላይ ጂሀድ ላይ ይሳተፍ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ጀሀድ ተሳትፎ ሰመኣት ሆነ፡፡ ሌላኛው ከዚህኛው አንድ አመት ያህል ቆይቶ ከዛም ሞተ፡፡
ጠለሀ እንዲህ አለ
“በህልሜ የጀነት በር ላይ ሆኜ አየሁ፡፡ ከሁለቱም ጋር ነበርኩ፡፡ አንድ ሰው ከጀነት ውስጥ መጥቶ ዘግይቶ የሞተውን ቀድሞ እንዲገባ አደረገው፡፡ ከዛም ድጋሚ መጥቶ ሰመኣቱን እንዲገባ አደረገው፡፡ ከዛም ተመልሶ መጣና አንተ ተመለስ ጊዜህ አልደረሰም አለኝ፡፡”
ጠለሀ (ከእንቅልፉ) ከነቃ በኋላ ለሰዎች ስለ ሁኔታው ተናገረ፡፡ ሁሉም ተገረሙ፡፡ ይህ ጉዳይ መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጋር ደረሰ፡፡ ለመልክተኛውም ጉዳዩ ሲነገራቸው
እሳቸውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
من أي ذلك تعجبون؟ قالوا: يا رسول اللهّ هذا كان أشد الرجلين اجتهاداً ثم استشهد ودخل هذا الآخر الجنة قبله فقال رسول الله (صلى الله عليه وسلم) : أليس قد مكث هذا بعده سنة؟ قالوا: بلى. قال: أدرك رمضان فصام وصلى كذا وكذا من سجدة في السنة؟ قالوا: بلى. قال رسول الله (صلى الله عليه وسلم): فما بينهما أبعد مما بين السماء والأرض
“ምንድን ነው የሚገርማችሁ?”
እነሱም አሉ
“የ አላህ መልክተኛ ሆይ! ከሁለቱም ይህኛው በጣም ታግሏል (በጂሃድ) ሰመኣትም ሆነ፡፡ ነገር ግን ይህኛው ቀድሞት ጀነት ገባ፡፡”
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ከሱ በኋላ አንድ አመት ወደ ኋላ አልቀረምን?” አሉ
እነሱም “አዎ ቀርቷል” አሉ
እሳቸውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ረመዳን አልደረሰምን፣ አልፆመምን፣ ይህን ይህን ያህል ሱጁዶች በዚህ አመት አልሰገደምን?” አሉ
እነሱም “አዎን (ደርሷል)” አሉ
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “በሁለቱ መሃል ያለው ልዩነት በሰማይ እና ምድር ካለው ልዩነት ይበልጣል” አሉ
ኢብን ማጃህ የዘገቡት ትክክለኛ ዘገባ (2/345 346) እና አልባኒ አስ-ሲልሲላህ አስ-ሰሂሃ
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ረመዳንን በአግባቡ እንጠቀምበት፡፡ ይህን ያህል ታላቅ ምንዳ አለው፡፡

ሙነሺዶቹና ፊልም ሰሪዎች ለምን ረመዳንን ይመርጣሉ?
እነሱ የፈለገ መልካም አስበን ነው ቢሉም ሙስሊሙን ከረመዳን ወር እያዘናጉት ነው፡፡
ውዴታ በተግባር ይገለፃል፡፡
ረመዳን ቁርዓን የወረደበት፣ ሰይጣን የሚታሰርበት፣ የጀነት በሮች የሚከፈቱበት፣ የእሳት በሮች የሚዘጉበት፣ ቁርዓን በብዛት የሚቀራበት፣ ተራዊህ የሚሰገድበት፣ ሰደቃ የሚበዛበት ታላቁ የአምልኮ ወር ነው፡፡
ሰይጣን እና ሰራዊቶቹ “ከአላህ ጋር ልናጣላችሁ ነው” ብለው በግልፅ ቢመጡ ማንም አይቀበላቸውም፡፡ እነሱ ግን ይህን አይደለም የሚያደርጉት ይልቁንስ ከዚህ በተገላቢጦሹ አዛኝ፣ መካሪና ተቆርቋሪ መስለው ነው እራሳቸውን የሚያቀርቡት፡፡ ሰይጣን አደም እና ሀዋን አላህ የከለከላቸውን ፍሪ እንዲበሉ ሲጎተጉት እንዲህ ነበር ያላቸው
وَقَاسَمَهُمَآ إِنِّى لَكُمَا لَمِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ
“እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ” ሲልም አማለላቸው፡፡
ተመልከቱ “እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ” ሲል ሽነገላቸው፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ እስቲ ተመልከቱ በዚህ በተከበረ ወር ሰዎች ቁርኣንን እንዳይቀሩ ለማዘናጋት “ኢስላማዊ ፊልም፣ ኢስላማዊ ነሺዳ፣ ኢስላማዊ ድራማ” እየተባለ ሰዉን ያዘናጉታል፡፡
አስገራሚው በአላህ ፍቃድ ከዘፈን የተመለሰው ሙሐመድ አወል ሳላህ ዛሬ ፂሙን ላጭቶ “ዉዴታ እስከ ጀነት” ሲል ይሰብካል፡፡ ሙኣዝ የተባለው ደግሞ ፀጉሩን ፓንክ ተቆርጦ “እኔን” ይላል፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ፂማችሁን ልቀቁት፣ ቀድሞ ቀመሳችሁን (ከንፈር ላይ ያለውን) ቁረጡት” ሲሉ ያውም ዛሬ እንደ ሙሐመድ አወል ሳላህ ያሉት ኢስላማዊ ሙነሺድ ተብለው የነብዩን ትዕዛዝ ተቃርኖ ፂሙን ይላጫል ሱሪውንም ይለቃል፡፡ ሙኣዝም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ፀጉራችሁን ስትቆረጡ አንዱን ካንዱ አታበላልጡት” የሚለውን የነብዩ ትዕዛዝ ጥሶ “ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ” ሲል ይቀጣጥፋል፡፡ አሳዛኙ የአላህ መስጂድ ቤቶች በሮቻቸው በእንዲህ አይነት ግለሰቦች ፎቶ ተበላሽተዋል፡፡ የአላህ ቤቶች ከማንኛውም ምስል መፅዳት ሲገባቸው፡፡
እንደሚታወቀው ረመዳን ሲወጣ ብዙ ሰዎች ከመስጂድ እና ከመልካም ነገሮች ይርቃሉ፡፡ እንዲህ አይነት በሽታዎችን በአላህ ፍቃድ የሚያሽረው የጌታችን የአላህ ቃል ቁርኣን ነው፡፡ እነዚህ መንዙማ፣ ነሺዳ ባዬች፣ ፊልም አክተሮች ከመስጂድ ርቆ የነበረውን ሙስሊም የአላህን ቃል እንዳይቀራ፣ እንዳያዳምጥ ጋሬጣ ሆነውበታል፡፡
ቁርኣን ፀጥ ብሎ ላዳመጠው የአላህን እዝነት ያስገኛል፡፡ ከቀራው በእያንዳንዱ ሀርፍ 10 ያስከፍላል፡፡ ፊልም የሚሉት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ አይመልከት፣ ሴት ልጅ ወንድ ልጅን አትመልከት” ያሉትን ነብያዊ ትእዛዝ ተቃርኖ በውሸት ገፀ ባህሪ ሙስሊሙን ያጠማል፡፡ አጅር አይገኝበትም፡፡ ሙነሺድ ተብየዎቹም በሸሪኣ የተቀመጠው ግጥም ሆኖ ሳለ ይዘፍናሉ፣ ያዜማሉ….. የመሳሰለውን፡፡ ይህም ለሙስሊሙ ምንም አይፈይድም፡፡ ምክንያቱም አንድ አምልኮ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ኢኽላስ እና ሙታበኣን (የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና ገጥሞ መገኘት አለበት) ሊኖረው ግድ ይላል፡፡
ከማንም በላይ አላህን እና መልክተኛውን በተግባር ወደው ያሳዩን ሰሃባዎች በረመዳንም ይሁን ከረመዳን ውጭ ፊልምና ድራማ እየሰሩ ሱሙንም “ኢስላማዊ” እያሉ አልነበረም፡፡ ኢስላማዊ ነሺዳ ብለውም የእራሳቸውንም ከነሱ በኋላ የመጡትን ጊዜ አላባከኑም ነበር፡፡
ፊልም፣ ነሺዳ፣ መፀሀፍ ምርቃት እያሉ ቲያትር ቤት ሰዎችን ጠርተው ወንድ እና ሴቶችን ያለ መጋረጃ ሳይለዩ በተለያየ ረድፍ አስቀምጠው ለፈተና መዳረግ መሰልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው፡፡
አላህን እንፍራ፡፡
ዉዴታ በተግባር ይገለፃል፡፡ ሰሃባዎች ከእኛ በላይ አላህን እና መልክተኛውን ይወዳሉ፡፡ እነሱ ረመዳናቸውን በቁርኣን፣ በተራዊህ በሰደቃ እንዳሳለፉት እኛም እናሳልፍ፡፡
መልካም ሁሉ ሰለፉነ ሷሊሂንን በመከተል ላይ ነው፡፡ መጥፎ ሁሉ መጤ መንገዶች እና አስተሳሰቦችን በመከተል ላይ ነው፡፡