Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
ስለ ተውሒድ ማወቅ ስለ ሰላት እና ስለ ዘካ ከማወቅ በላይ አንገብጋቢ ነው፡፡ ስለ ሺርክ አደገኝነት ማወቅ ስለ ሶላትን ከሚያበላሸው ነገር እውቀት በላይ መታወቁ ግድ ይላል፡፡ ተውሒድ ፊቂሁል አክበር (ታላቁ ፊቂህ) ተብሏል፡፡ ተውሒድ ከሌለ ምንም ነገር የለም፡፡ ሁሉም ኢባዳዎች ሰላት፣ ዘካ፣ ፆም ተውሒዱ ለተስተካከለ ብቻና ብቻ ነው ጥቅም ያላቸው፡፡ መቀደም ያለበትን እና ትኩረት ሊሰጠው ለሚገባው ትኩረት እንስጥ፡፡
አላህ በተውሒድ ላይ አኑሮ በተውሒድ ላይ ይግደለን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ኢኽዋኖቹ
"ደም ሲለግሱ " ፣ የታመመን ሲጠይቁ፣ ለተጎዳ
ገንዘብ "ሲረዱ" አንዳንዴም ሲዘሉ እና ጆተኒ ሲጫወቱ ፎቶ መነሳት! ማንሳት! ማሰራጨት!! አንዳንዴ የተቀባዩን ልብ በሚነካ መልኩ እሱንም አብረው ያስነሱታል— እነሱ እየሰጡ እሱ እየተቀበለ!!
እናቱን ሲዘይርም የተለመደው ካሜራ ፊት ለፊቱ ይደቀንና የተለመደውን ስራ ይሰራል! ዳዕዋም ላይ እንደዚሁ!!
ከዛም የናቱን ሐቅ የሚወጣ ጀግና! ቸር ፣ አዛኝ፣ "የገባውና ፈታ ያለ" ዳዒ ይባላል!
እንዲህ አይነቱ ስም በአፍንጫ ይውጣ!!

በመጨረሻማ፣ ያለ አቅማቸው ያለ እውቀታቸው "ተሰቅለው" ቀሩ!! ያለ ብቃት መሪ ሆነው ተሾሙ! በድፍረት በየ ርእሱ በማን አለብኝነት መዘባረቅን መንገዳቸው አድርገው ያዙ!! "አናውቅም " ለነሱ ባእድ ሆነ! ከሱም ጋር ተኮራረፉ! ያሻቸውን እንዳሻቸው ደሰኮሩ! ምስኪኑም በጭፍን ይከተላቸው ያዘ!! ተጎድተው ጎዱ!!
ከዛማ፣ የተጎዳን ሲረዳ ፣ በሽታን ሲጠይቅ ፣ እናቱን ሲዘይር ፎቶ የማይነሳውን ሁሉ ተከታዮቻቸው " አንተ ደግሞ ምን ሰርተህ ነው?!! " ይሉ ጀመር ተከታዮቻቸው። ፎቶ መነሳት ለመልካም ስራዎች መስፈርት እስኪመስል ድረስ ነገሩን አጦዙት ። ያሳዝናል ።
በ Muhammedsirage MuhammedNur Gidey

*******************************
በ Ibnu Munewor ሰው መስጠት እንዲለምድ እየሰጡ ፎቶ መነሳት፣ ሰው መዝለል እንዲለምድ እየዘለሉ ፎቶ መነሳት፣ ሰው እናቱን ማክበር እንዲለምድ እግር እየሳሙ ፎቶ መነሳት፣ ሰው ሐጅና ዑምራ እንዲለምድ የኢሕራም ልብስ ለብሶ ከዕባ አጠገብ ፎቶ መነሳት፣ ሰው ዱዓ እንዲለምድ እጆቹን አንስቶ ዱዓ እያደረጉ መነሳት፣ ሰው ቀርዷዊን እንዲወድ ከቀርዷዊ ጋር ፎቶ መነሳት፣ ሰው ፈገግታን እንዲለምድ ከካሜራ ፊት ፈገግ ማለት፣ …
ከዚያም ለዚህ ሁሉ "እዩኝ" ለነገሰበት አካሄድ አስፈላጊ ሲሆን ሶደቃን በግልፅ መስራት እንደሚቻል/ እንደሚበልጥ የሚጠቁመውን ማስረጀስ ማጣቀስ። ታወቀና ተሞተ
https://t.me/SadatTextPosts
ወፍ ከአምሳያዎቿ ጋር ታርፋለች (ዘመድ ከዘመዱ .....)

ያሲን ኑሩ ከዚህ ጠሞ አጥማሚ ኢኽዋኒ ዩሱፍ አልቀርዳዊ ጋር ምን ፈልጎ ነው አብሮት ፎቶ የሚነሳው?
ዩሱፍ አልቀርዳዊን ለማታውቁት የሚከተሉት ጥመቶችን የተሸከመ ሰው ነው፡፡

• የኩፍር ንግግሩ፡- የጁምዐ ሁለተኛ ኹጥባ ላይ የሚከተለውን ተናግሯል ‹‹ኹጥባዬን ጨርሼ ከመውረዴ በፊት ትንሽ ስለ እስራኤል ምርጫ መናገር እፈልጋለሁ፡፡ አረቡቹ በጠቅላላ ነዳህ ጲሪዝ ያሸንፋል ብለው ተስፋቸውን ጥለው ነበር፤ ነገር ግን ተሸነፈ፡፡ ከእስራኤል የምንወድላትም ይህንን ነው፡፡ የእኛም ሀገር እነደዚህች አገር እንድትሆን እንመኛለን እንፈልጋለን፡፡ በጥቂት ሰዎች አማካኝነት ሲመራ የነበረው ስልጣኑን አጥቷል፡፡ አገራችን ላይ እንደለመድነው 94% ወይንም 95% (ድምፅ) አይደለም ነገር ግን 99% (አዎን 99%፤ ምንድን ነው ይሄ?) አላህ ለሰው ልጆች እራሱን ተመራጭ አድርጎ ቢያቀርብ ይህንን ያህል ድምፅ አያገኝም ፡፡ይሄ (አረብ አገር ላይ የምናየው ምርጫ) ውሸት ማጭበርበር እና የመሳሰሉት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እስራኤልን እሰየው እንላታለን››፡፡ ምድር በዚህ የኩፍር ንግግር አትሰነጠቅምን? ለሸይኽ ኢሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) ይህ ቃል በድምፅ ተከፍቶላቸው ከሰሙ በኋላ የሚከተለውን ተናገሩ ‹‹በአላህ እጠበቃለሁ፡፡ ይህ ሰው መቶበት ግድ ይለዋል፤ እምቢ ካለ እንደ ሙርተድ (ሀይማኖቱን እንደከዳ ሰው) ይገደል፡፡ ፍጡራንን ከፋጣሪ ስላስበለጠ፡፡ ተውበት ካደረገ አላህ የባሪያውን ወንጀል መሀሪ ነው፤ ካልሆነ ውላቱል አምር (የሙስሊም መንግስት) አንገቱን (በሰይፍ) ይቀንጥሰው፡፡››

• ‹‹ከይሁዳዎችን ጋር የእምነት ጦርነት የለንም የመሬት እንጂ፡፡ ካሃዲያንን ካሃዲያን ስለሆኑ አይደለም የምንዋጋቸው መሪታችንና ቤቶቻችንን ያላግባብ ስለቀሙን እንጂ›› (አራያህ መፅሄት ቁጥር 4696፣ 24 ሸዕባን 1995 ኢ.አ)፡፡ አላህ እና መልክተኛው ምን እንደሚሉ እንስማ፡፡ ይሁዳዎች ከሰዎች ሁሉ ከነሳራም ለአማኞች ጠላትነታቸው የበረታ ነው አለህም እንዲህ ይላል ‹‹ለአማኞች ከጠላትነት በኩል ዩሁዳንና ጣዖታዊያንን ታገኛለህ››ሱረቱል ማኢዳ

• ዘፈንና ሙዚቃን መፍቀዱ፤ እንዲያውም ጥሩ ነገር ነው ማለቱን ‹‹አል ሀራም ወል ሀላል›› ‹‹ፈትዋ ሙዐሲራ›› እና በመሳሰሉ መፀሃፎቹ መግለፁ፡፡ እራሱ እንደተናገረው ‹‹የፋይዛ አህመድ፤ ሻዲያ፤ ኡሙ ኩልሱም፤ ፊሩዝ እና የመሳሰሉትን ሴቶች ዘፈን መከታተል ይወድ እንደነበር ጠቅሷለል›› (አራያህ የሚባል የኳታር መፅሄት ቁጥር 5969 ቀን 19/ ጁማዱል ኡላ 1419 ሂጅሪ)፡፡ ዘፈን ሃራም ለመሆኑ የነብያችን አንድ ሀዲስ ሀቅን ለሚፈልግ ትበቃዋከች ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) ከኔ ኡመት ሰዎች ይመጣሉ ለወንድ ልጅ ሀር ልብስን የሚፈቅዱ፤ መጠጥን እና የሙዚቃ መሳሪያን የሚፈቅዱ›› ኢማሙ ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ የአላህ ባሪያዎች እንደው እናንተው ፍረዱት፡፡

ኡለማዐል ኢስላም ከሰሃባዎች ጀምሮ፤ አቡ ሀኒፋ፤ ኢማሙ ማሊክ፤ ኢማሙ ሻፊዕ፤ ኢማሙ አህመድ፤ ሙሀዲስ ቡኻሪ፤ ሙስሊም ሁሉም በአንድነት ዘፈንን ከልክለዋል፡፡
ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ ‹‹እኛ ጋር ዘፈን የሚያዳምጥ ፋሲቅ ነው›› ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን መስዑድ (አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና) እንዲህ ይላል ‹‹ዘፈን ማዳመጥ በቀልብ ኒፋቅን ያበቅላል ውሃ አዝርትን እንደሚያበቅል ሁሉ›› ፡፡ ቃዲ ኢያድ የተባሉ የማሊክ መዝሃብ ተከታይ ታላቅ አሊም ዘፈን ሀራም ለመሆኑ ኢጅማዕ ጠቅሰዋል፡፡
የሙዚቃ መሳሪያን አስመልክቶ ኢማሙ አህመድና አቡዳውድ የዘገቡት ሰሂህ ሀዲስ እንጨምር፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ‹‹አላህ መጠጥን፤ ቁማርን፤ ከበሮ መምታትን ሀራም አደረገ›› ብለዋል፡፡

• የካቶሊኩ ፓፓስ በሞተ ጊዜ ‹‹አላህ ይማረው ማለቱ››፡፡ አላህ ግን መልክተኛውንም ሆነ አማኞችን ለነዛ በኩፍር ላይ ለሞቱ ሰዎች ምህረትን እንዳይጠይቁ አዟል፡፡

• አረቡ አለም ላይ የተነሳውን የስንት ሙስሊሞች ህይወት የጠፋበትን፣ አገር ጥለው የተሰደዱበትን፣ የጠላት መጫወቻ የሆኑበትን፣ ንብረታቸው የተዘረፈበትን ፈተና ቢንዚል በማርከፍከፍ ፊትና ሲቀሰቅስ የነበረ ሰው ነው፡፡

ዩሱፍ አልቀርዳዊ ይህንን እና ብዙ መሰል ከባባድ ስህተቶች አሉበት፡፡
የዩሱፍ አልቀርዳዊን አጥማሚነት ያላወቃችሁ ወንድም እና እህቶች ተጠንቀቁት፣ ወደ ተውሂድ ሳይሆን ወደ ፖለቲካ እና ወደ ጥመት የሚጣራ የፊትና ሰው ነው፡፡ አላህ ከጠሞ አጥማሚዎች ይጠብቀን፡፡

ያሲን ኑሩ ከዚህ በፊትም እንደተናገርነው ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚጣራ ሰው አይደለም፡፡ ሙስሊሞች ከሱ ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡ ‹‹የተውሂድ አድማስ›› በተሰኘው መፀሀፉም ላይ ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ፣ ሰይድ ቁጡብና ሌሎችም መንገድ የሳቱ ሰዎችን እንደ ጥሩ አድርጎ ለኢትዬጵያ ሙስሊም ያስተዋወቀ ሰው ነው፡፡ ያሲን ኑሩና ጓደኞቹ ያሉበትን የተሳሳተ መንገድ ትተው ወደ አላህ ተመልሰው የጥንት የጠዋቷን መንገድ መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ እስኪሆን ድረስ ግን የኢትዬጵያ ሙስሊም ከነሱ እራሱን፣ ቤተሰቦቹን ያስጠነቅቅ ዘንድ እመክራለሁ፡፡ እንደሜታወቀው ሃቅ በሰዎች አይለካም፣ ሰዎች በሃቅ ይለካሉ እንጂ፡፡

እዚህ ጋር አንዳንድ ወንድሞች የዩሱፍ አል-ቀርዳዊን ስሀተት ተረድተናል ግን ለያሲን ኑሩ ለምን በድብቅ አትመክረውም ይሉ ይሆናል፡፡ መልሱም እሱ ይህን ፎቶ እንደትልቅ ነገር ሲነሳ ከዚህ ጠሞ አጥማሚ ጋር ብሎም ለኢትዬጵያ ሙስሊም በገሃድ እያስተዋወቀው ይህን ግለሰብ እኔ ለምንድን ነው በድብቅ የምመክረው?
እንዲህ በአደባባይ የወጣን ጥመት ማጋለጥ ላይ ሰውየውን በድብቅ መምከር የሚባል መስፈርት የለም፡፡
ያሲን ኑሩ የዩሱፍ አል-ቀርዳዊ ስህተቶች ተዘርዝረውለት ሲያበቁ በአደባባይ ሚድያን ተጠቅሞ ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ ጥመት ላይ እንደሆነ እና እሱም ቀርዳዊን ለኢትዬጵያ ሙስሊም በማስተዋወቁ ለአላህ ተውበት በማድረግ ለህዝቡ ደግሞ ከስህተቱ በመመለስ ሃቁን ግልፅ ሊያደርግ ግድ ይለዋል፡፡ ይህን ሳያደርግ ለቀርዳዊ ወግኖ ጥፋቱን ሸፍኖለት አስተዋውቀዋለሁ ቢል ከራሱ ጀምሮ ባጠመማቸው ሰዎች ልክ ወንጀሉን ይሸከማል፡፡

እኛ ደግሞ እውነት እራሳችንንና ኡማውን ከጥመት ለመጠበቅ ከሆነ ወደ ጥመት የሚጣሩ ሰዎች መጋለጣቸው ሊያሳስበን አይገባም፡፡ እኛ ዘንድ ከምንምና ከማንም በላይ ተወዳጅ ሊሆን የሚገባው ሃቅ ነው፡፡

አላህ ሆይ ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንከተለውም አድርገን፣ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብየት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
1) ቀርዳዊ ሙዚቃን ሀላል ያደረገበት ።

https://youtu.be/UnOaiYvKv3s

https://youtu.be/F91XFPHnCLg

2) ቀርዳዊ ሴት መጨበጥን ሀላል ያደረገበት

https://youtu.be/0OW4Y5UXRXs

3) ሪባን ( ወለድን ) ሀላል ያደረገበት

https://youtu.be/sfn5GiZ9s8E

4) ሂጃብ ማውለቅን የፈቀደበት

https://youtu.be/0Y5sJ6HfAWo

5) ከሸሪአ ህግ ይልቅ የፖለቲካ ህግ ይሻላል ብሎ የከፈረበት ንግግር

https://youtu.be/jM01nmeoc6I

6) አላህን የተሳደበበትና ኡለማዎች የፈረዱበት ፍርድ

https://youtu.be/Q6jKlgiOpPM

7) የአለማችን ስመ ጥርና ታላላቅ ኡለማዎች ከቀርዳዊ ያስጠነቀቁበት ሙሉ ዝርዝር መረጃ ።
አላህ እንዲህ ይላል

قُلِ ٱللَّهُمَّ مَٰلِكَ ٱلْمُلْكِ تُؤْتِى ٱلْمُلْكَ مَن تَشَآءُ وَتَنزِعُ ٱلْمُلْكَ مِمَّن تَشَآءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَآءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَآءُ ۖ بِيَدِكَ ٱلْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
(ሙሐመድ ሆይ!) በል፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ (በችሎታህ) ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡»
https://t.me/SadatTextPosts
“ፌስቡክ ላይ ተቀምጣችሁ ሺርክ ሺርክ አትበሉ፡፡”
“ሺርክን ክፍለ ሀገር ገብታችሁ አስተምሩ፡፡”
“ሺርክ የሚሰሩ ሰዎች ፌስቡክ አይጠቀሙም ክፍለ ሀገር ነው ያሉት፡፡” ይሉናል፡፡

ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ብቸኛ ለሆነው እና አጋር ለሌለው ለአላህ ይገባው፡፡ የአላህ ሰላትና እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ተውሒድን ባስተማሩ ሺርክን ባጋለጡ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

ስለ ሺርክ በፌስ ቡክ ሲለቀቅ፣ እነ አቡበክር አሕመድ፣ እነ ያሲን ኑሩ እና ጓደኞቻቸው ሺርክ ያለበት ሀገር ላይ ተቀምጠን ሌላ አርእስት ውስጥ አይግቡ፣ የአላህን አማና ይወጡ፡፡ እንደነ አፍሪካ ቲቪ አይነት አሉ የሚባሉ ሚድያዎቻቸው ላይ የሺርክን አስከፊነት በዝርዝር እና ሀገራችን ላይ የሚሰራውን ሺርክ በማስረጃ ይናገሩ ሲባል የሚከተሉትን አሉባልታዎች ተከታዬቻቸው ያሰማሉ

- “ፌስቡክ ላይ ተቀምጣችሁ ሺርክ ሺርክ አትበሉ፡፡”
- “ሺርክን ክፍለ ሀገር ገብታችሁ አስተምሩ፡፡”
- “ሺርክ የሚሰሩ ሰዎች ፌስቡክ አይጠቀሙም ክፍለ ሀገር ነው ያሉት፡፡” ይሉናል፡፡

በአላህ ፍቃድ እኛም እንዲህ እንላለን፡፡ እናመሰግናችኋለን ሺርክ ሀገራችን ላይ እንዳለ ስላመናችሁልን፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሺርክን ከመዋጋት በፊት ወደ ሌላ አርእስት ገብተው ነበር ወይ?
መልሱም በፍፁም አልነበረም፡፡
ታድያ የሁላችንም አርአያ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ናቸው “ፊዳከ አቢ ወኡሚ” የምንል ከሆነ እነ አቡበክር አሕመድ ለምን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በሄዱበት መንገድ አይሄዱም?
- ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በላይ አውቀው ነውን?
- ወይንስ ከሳቸው በላይ ለኡማው አሳቢ፣ አዛኝ ሆነው ነውን?
መልሱም ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በላይ አዋቂ፣ አዛኝ፣ አሳቢም አይደሉም፡፡ መልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መቃረን እንዲያውም ሁለት ሀገር ለክስረት ይዳርጋል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ ٱلْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِۦ جَهَنَّمَ ۖ وَسَآءَتْ مَصِيرًا
ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች!
ስለዚህ አቡበክርም ይሁን ጓደኞቹ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሄዱበትን መንገድ ተቃርነው ኡማውን ወደ ሌላ መንገድ እየመሩና ለክስረት እየዳረጉት ነው፡፡
እኛን “ለምን ገጠር ሄዳችሁ ለገጠሩ ህዝብ ስለ ሸርክ አስከፊነት አትናገሩም? እዚህ ፌስቡክ ላይ ሺርክ ሺርክ አትበሉን” ለሚሉን ጥቂት ልበላቸው
1) በአላህ ፍቃድ እና እገዛ አብዛኛው ተቀድቶ እየተላለፈላችሁ ያሉት ሙሀደራዎች ክፍለ ሀገር ላይ የተቀዱ ናቸው፡፡ ግን ክፍለ ሀገር መሄዳችንን መኪና ውስጥ ስንገባ፣ መንገድ ላይ ተሰባስበን፣ ዳእዋ ስናደርግ፣ እዛ አካባቢ ላሉ የገጠር ነዋሪዎች ኪታቦች ስናከፋፍል ፎቶ ተነስተን ለማስረጃ እና እናንተ እንድታዩ መልቀቅ አይጠበቅብንም፡፡ ምክንያቱም ሂሳብ ከፋዩ አላህ እንጂ እናንተ አይደላችሁም፡፡
2) በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ክፍለ ሀገር ያሉ ሰዎች ሁሉ ኢንተርኔት ተጠቅመው፣ በሜሞሪ፣ በሲዲ የተላለፉ መልክቶችን ሁሉ እየተጠቀሙና ለሌሎችም እየሰጡ ብዙ ሰው በአላህ እዝነት ከተውሒድ ዳእዋ ተጠቃሚ ሆኖዋል፡፡
3) ደግሞ ሺርክን ለገጠር ሰው ብቻ ያደረገው ማን ነው?
- ይሀው ከተማችን ላይ በየጠንቋይ ቤቱ ህዝቡ ይመላለስ የለ ወይ?
- ሴት እህቶቻችን ላይ ድግምት የሚያሰሩባቸው እነማን ናቸው?
- አንድ አንዱ ላይ ድግምት የሚያሰራው እዚሁ አዲስ አበባ ላይ አይደለምን?
- ጉዞ ወደ አብሬት፣ ወደ ቃጥባሬ፣ ወደ አልከሶ፣ ወደ ዳና፣ ወደ ዳንግላ እየተባለ የሚኬደው ከዚሁ ከአዲስ አበባ አይደለምን?
- ጉለሌ እስላም መቃብር ላይ ትልልቅ ቀብሮች ተገንብተው፣ በል እንዲያውም “ሸህ ሀሰን በቱል” የሚባል እላዩ ላይ ሚናራ የተሰራበት ቀብር አዲስ አበባ ጉለሌ እስላም መቃብር ላይ አይደለምን?
- አዲስ አበባ ውስጥ ነው አይደለም ቀን ለይተው ከቤት አንወጣም የሚሉ ሰዎች ያሉት?
- አዲስ አበባ ውስጥ ነው አይደለም በየዶሮ ተራው፣ በግ ተራው፣ እጣን ተራው ስንቶች ለየት ያለ ከለር ለሰይጣን ለመገበር ሲሉ በብዙ ብር እንስሳ ገዝተው የሚሰዉት?
- እዚሁ አዲስ አበባ ላይ ነው አይደለም ታምራት ጠንቋዩ ቤት ሲመላለሱ ከነበሩት ውስጥ ኒቃብ የለበሰች ሴት ሁሉ የታየችው?

ስለዚህ የማይሆን ወቀሳ አታንሱ፡፡ ይልቁንስ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ፈለግ የተቃረኑትን ኡስታዞቻችሁን አላህን ፈርተው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከምንም በፊት ያስቀደሙትን አርእስት እንዲያስቀድሙ ንገሯቸው፡፡
ቅድሚያ ለተውሒድ?
በጣም የሚገርመው በዚሁ በፌስ ቡክ ስለ ሰላማዊ ሰልፍ ስለ ሌላ አርእስቶች ሲለቀቅ “በክልል ከተሞች” ሁሉ እየተባለ አልነበረምን?
ምነው ታድያ ለፖለቲካ ሲሆን ከተማ ገጠሩን በኢንተርኔት ያዳረሰው የናንተ ዳእዋ ተውሒድን (የአላህን መብት) አብራርቶ መናገር ላይ ትንፋሽ ያጠረው?
ችግር ስላለባችሁ ነው ወይንስ አይደለም?
የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) አስተምህሮት ስለምትቃረኑ ነው ወይንስ አይደለም?
ዛሬ ወደድነውም ጠላነውም እኛ ከተማ ገብተን ብንኖርም፣ መሰረታችን ቤተሰቦቻችን ከገጠር ነው የመጡት፡፡ አሁንም ድረስ አብዛኛው ቤተሰብ ገጠር ነው የሚኖረው፡፡ ገጠር ላይ ሺርክ እንዳለ ካመናችሁ፡፡ ሺርክ (በአላህ ላይ እያጋራ) የሞተ ሰው ደግሞ አላህ በእርሱ ላይ ጀነትን እርም አድርጎበት፣ ዘላለም መኖሪያው እሳት ሆኖ ሳለ ለምን የኢስላም አስተማሪ ነን የሚሉት ይህንን አርእስት ዝም ይላሉ?
ጨካኞች አይደሉምን?
መቼም ለቅርብ ቤተሰቦቹ ያልሆነ ለሌላው አይሆንም፡፡ ከራስ በላይ ንፋስ ይላል የሀገሬ ሰው፡፡ ስለዚህ ገጠር መሄዳችንን ፎቶ ተነስተን መልቀቅ የለብንም እና እባካችሁ እንዲህ የወረዱ ጥያቄዎችን አታንሱ፡፡ ሐቁን ብቻ ተቀበሉ፡፡
ኩራተኛ ሰው ማለት ሐቅ ሲነገረው የማይቀበል ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሺርክ እያዩ ዝም አይሉም ነበር፡፡ ቢድኣ እያዩ ያውም የቢድአ ሁሉ ቁንጮ መውሊድን “መውሊድ አይለያየንም” አይሉም ይልቁንስ “አዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ፡፡ ሁሉም መጤ ነገር ቢድአ ነው፡፡ ቢድአ ሁሉ ጥመት ነው፡፡” ነበር ያሉት፡፡
ጥያቄው ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንገድ እና እሳቸውን ከማይከተሉት ሰዎች መንገድ የቱን ትመርጣላችሁ ነው?
አላህን የፈራና ነፍሱን ከእሳት ማውጣት የፈለገ የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንገድ ይመርጣል፡፡
ለነፍሳችን እንዘን የማንም ንግግር ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ንግግር አይቀደምም፡፡
ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ከሰሃባዎችቻው፣ ከሰለፉነ ሷሊሂን መንገድ ውጭ ያለ የትኛውም መንገድ ጥመት ነው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሺርክን እያዩ ዝም አላሉም፣ ወደ ሌላ አርእስትም አልገቡም፡፡ ይሄ ታላቅ ስብእና ማናችንንም ያለንበትን መንገድ መመዘኛ ነው፡፡
አላህ ሆይ! ሐቅን በሐቅነቱ አሳየን የምንከተለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት መደምደሚያ ላይ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በ Ibnu Munewor

ባለመንዙማው ሙሐመድ አወል መንዙማውን ተጠቅሞ እጅግ በርካታ የሽርክ ስንኞች ወደ ህዝብ ያሰረገ የጥፋት ሰው ነው። ከህዝባችን ውስጥ ከፊሉ መልእክቱ ላይ ብዙም ሳያተኩር እንዲሁ ዜማውን የሚያቀነቅን አለ። በአንድ ወቅት አንድ የዚህን ሰውየ መንዙማ የሚያዳምጥን ሰው ካሴቱን እያቆምኩኝ "አንተ በዚህ መልኩ ነው የምታምነው?" ብየ ብጠይቀው "አይደለም" አለኝ። "እናስ ለምን ታዳምጣለህ?" ስለው "እኛኮ ዜማው ላይ እንጂ ብዙም ወደ ወደ ውስጥ ገብተን አናስተውለውም" ብሎኛል።
የሆነ ሆኖ የሰውየው ስራዎች ሲበዛ አውዳሚ ናቸው። በዚያ ላይ ልክ እንደ አሕባሾቹ "አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን" እያለ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን የሚያስተባብልበት ስንኝ አለው። አንዳንዱ ግን ማስተዋል ያቅተዋል። አሕባሽን ተቃውሞ እንዳልጮኸ ቀዳሚውን የአሕባሽ ጥፋት ሌሎች ሲፈፅሙት ግን አይሞቀው፣ አይበርደው። ይሄ በራስ አቋም ሳይዙ ሌሎችን ተከትሎ መንፈስ ያመጣው ጣጣ ነው።
መጪው ረመዳን ስለሆነ የጥፋት ሰዎች ከያቅጣጫው ወከባ ያበዛሉ። ስለዚህ ቤተሰቦቻችንን፣ ወገናችንን፣ በቅድሚያም እራሳችንን ልናተርፍ ይገባል።
ወንድሜ! አላህን ፍራ! እህቴ ሆይ! አላህን ፍሪ!! ህይወት ማለት የዱንያ ህይወት ማለት አይደለም፡፡ ይቺማ ጤዛ እኮ ናት፡፡ ይልቅ ነብዩ ﷺ ምን እንደሚሉ ተመልከት፡- “አንድ ሰው የሚያገኘው ገንዘብ ከሐላል ይሁን ከሐራም ደንታ የማይኖርበት ዘመን በሰዎች ላይ ይመጣል፡፡” [ቡኻሪ፡ 2059] ልብህ ካልሞተ ይሄ አስፈሪ መልእክት አለው፡፡ ሰው እንዴት እራሱን የቂያማ ምልክት ያደርጋል? ፍጥጥ ባለ መልኩ ሐራም ላይ መግባት ሲኖርስ? ያውም በአራጣ? አላህ ለሸሪዐዊ ትእዛዝ እጅ የምንሰጥ፣ ከዱንያ ይልቅ ኣኺራን የምናስቀድም ያድርገን፡፡ ኣሚን፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 23/2010)
የወለድ አደጋዎች
ዘመናችን በርካታ የቂያማ ምልክቶች የሚታዩበት አስፈሪ ዘመን ነው፡፡ ከነዚህ ምልክቶች ውስጥ አንዱ የወለድ መንሰራፋት ነው፡፡ ወለድ በቁርኣን፣ በሐዲሥና በምሁራን ኢጅማዕ የተወገዘ እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው፡፡ ወንጀሉ ምንም እንኳን አደገኛ ቢሆንም ነገር ግን እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ ነው፡፡ ከጥፋቱ መስፋፋት በላይ ይበልጥ የሚደንቀው ግን በተለያዩ ስልቶች ኢስላማዊ ሽፋን ሊሰጡት አጉል የሚባዝኑ ስራዎች ብቅ ብቅ ማለታቸው ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥም አንዱ “የወረቀት ገንዘብ እና ወለድ” በሚል ርእስ በቅርቡ የወጣው መፅሐፍ ነው፡፡ ፀሐፊው ጥራዝ ነጠቅ ብቻ ሳይሆን ሲበዛ ደፋር ነው፡፡ ስለ መፅሐፉ በሌላ ጊዜ እመለሳለሁ፣ ኢንሻአላህ፡፡ ላሁን የወለድን አስከፊነት የሚያሳዩ ማስረጃዎችን እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ፡፡
1. ወለድ ከሰባት ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ” ይላሉ፡፡ “ምን ምን ናቸው እነሱ?” ሲባሉ፡-
((الشرك بالله، والسحر، وقتل النفس التي حرّم اللَّهُ إلا بالحق، وأكل الربا، وأكل مال اليتيم، والتّولّي يوم الزّحف، وقذف المحصنات الغافلات المؤمنات))
“በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ ጥብቅ ያደረጋት ነፍስ መግደል - በሐቅ ካልሆነ በስተቀር፣ ወለድን መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ በጦርነት ጊዜ መሸሽ፣ ጥብቅና (ከጥፋት) የዘነጉ አማኝ ሴቶችን በዝሙት መወንጀል፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ወለድ ከምን አይነት ወንጀሎች ጋር እንደተቆጠረ ተመልከት፡፡
2. ወለድ እንኳን ለአኺራ ለዱንያም አይጠቅምም፡፡ ይሄውና አላህ ምን እንደሚል፡-
{يَمْحَقُ اللَّهُ الرِّبا وَيُرْبِي الصَّدَقَاتِ }
“አላህ አራጣን ያጠፋል፡፡ ምፅዋቶችንም ያስፋፋል፡፡” [በቀራህ፡ 276]
በየገጠሩ ገበሬውን ባዶውን ያስቀሩት የቁጠባ ተቋማት ናቸው፡፡ ወለድ የገባው ሁሉ እንስሶቹ እያለቁ፣ ሰብሉ እየጠፋ፣ ንግዱ እየከሰረ መቀመቅ የገባው እጅግ በርካታ ህዝብ ነው፡፡ ወላሂ በአራቱም የሃገሪቱ አቅጣጫዎች የወጣ ከዚህ ጋር የተያያዘ ብዙ ለቅሶ ይሰማል፡፡ መሬት ላይ ያለው እውነት በኢቲቪ እንደሚደሰኮረው አይደለም፡፡ ነብዩ ﷺ “አንድ ሰው ከወለድ አያበዛም ፍፃሜው መመናመን ቢሆን እንጂ” ይላሉ፡፡ [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 5/120]
3. ያለ አስገዳጅ ሁኔታ ከወለድ ጋር የሚነካካ በሁሉም አቅጣጫ የተረገመ ነው፡፡ ሶሐባው ጃቢር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡-
((لعن رسول الله - صلى الله عليه وسلم -: آكل الربا، وموكله، وكاتبه، وشاهديه))، وقال: ((هم سواء))
“የአላህ መልእክተኛ ﷺ ወለድ የሚበላንም፣ የሚያበላውንም፣ ፀሐፊውንም፣ ምስክሮቹንም ተራግመዋል፡፡ ‘ሁሉም በወንጀሉ እኩል ናቸው!!’ ብለዋል፡፡” [ሙስሊም፡ 1598]
“እኔ ቢቸግረኝ ወሰድኩ እንጂ አራጣ አበዳሪ አይደለሁም” ብለህ እንዳትሸወድ፡፡ ያለፈውን ሐዲሥ ተመልከት፡፡ በተጨማሪም ነብዩ ﷺ “ወሳጅም ሰጪም እኩል ናቸው” ማለታቸውን ያዝ፡፡ [ሙስሊም፡ 1584] ስለዚህ ሙስሊም የሆነ ሰው ሌላው ቀርቶ በወለድ ተቋማት ውስጥ ጥበቃና ፅዳት እንኳን ሊሰራ አይገባውም፡፡
4. ወለድ ውስጥ የገባ ሰው ከአላህ ጋር ጦርነት ውስጥ ነው የገባው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
{يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَذَرُوا مَا بَقِيَ مِنَ الرِّبا إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ * فَإِنْ لَمْ تَفْعَلُوا فَأْذَنُوا بِحَرْبٍ مِنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ}
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ከአራጣም የቀረውን ተዉ፡፡ አማኞች እንደሆናችሁ (ተጠንቀቁ፡፡) (የታዘዛችሁትን) ባትሰሩም ከአላህና ከመልእክተኛው በሆነች ጦር (መወጋታችሁን) እወቁ፡፡” [አልበቀራ፡ 278-279]
ይቺ በነብዩ ﷺ ላይ መጨረሻ ላይ የወረደች አንቀፅ ነች ይላሉ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ፡፡ [ቡኻሪ፡ 2086]
5. ወለድ የሚበላ ሰው ከቀብር የሚነሳው ልክ በጂን እንደተለከፈ ሰው እየተሳከረ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
{الَّذِينَ يَأْكُلُونَ الرِّبَا لا يَقُومُونَ إِلَّا كَمَا يَقُومُ الَّذِي يَتَخَبَّطُهُ الشَّيْطَانُ مِنَ الْمَسِّ}
“እነዚያ አራጣን የሚበሉ ያ ሰይጣን ከመንካቱ የተነሳ የሚጥለው ሰው (ከአውድቁ) እንደሚነሳ ብጤ እንጂ (ከመቃብራቸው) አይነሱም፡፡” [አልበቀራ፡ 275]
6. ወለድ ምህረት የለሸ ወንጀል ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ምህረት ከማያገኙ ወንጀሎች ተጠንቀቅ፡፡ … ወለድን መብላት፡፡ ወለድን የበላ ሰው በቂያማ ቀን ሸይጧን የሚጥለው እብድ ሆኖ ነው የሚነሳው” ካሉ በኋላ የላይኛውን አንቀፅ አነበቡ፡፡ ስለዚህ ትክክለኛ ተውበት ካልኖነ ጥፋቱ አደገኛ ነው፡፡
7. ወለድ የከሃዲዎቹ አይሁዳውያን ተግባር ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
{وَأَخْذِهِمُ الرِّبا وَقَدْ نُهُوا عَنْهُ وَأَكْلِهِمْ أَمْوَالَ النَّاسِ بِالْبَاطِلِ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ مِنْهُمْ عَذَاباً أَلِيماً}
“ከርሱ በቁርጥ የተከለከሉ ሲሆኑ አራጣንም በመያዛቸውና የሰዎችን ገንዘቦች ያለ አግባብ በመብላታቸውም ሳቢያ (የተፈቀደላቸውን እርም አደረግንባቸው፡፡) ከነሱም ለከሃዲዎቹ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጀን፡፡” [አንኒሳእ፡ 161]
8. የወለድ መብዛት የቂያማ ምልክት ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ቂያማ ሲቃረብ ወለድ፣ ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ይበዛል” ይላሉ፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 1861]
9. ወለድ የሚበላ ሰው አሰቃቂ ስቃይ አለበት፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡-
“ዛሬ ሌሊት ሁለት ሰዎችን አየሁኝ፡፡ ወደተቀደሰች ምድርም ይዘውኝ ወጡ፡፡ ደም የሚጎርፍበት ወንዝ እስከምንደርስም ተጓዝን፡፡ በውስጡ አንድ የቆመ ሰው አለ፡፡ ከወንዙ ዳርቻ አንድ ሰው አለ፡፡ ከፊት ለፊቱ ድንጋዮች አሉ፡፡ ወንዙ ውስጥ ያለው ሰውየ ሊወጣ ሲያመራ ዳር ላይ ያለው ሰውየ አፍ አፉን በድንጋይ እየመታ ወደነበረበት ይመልሰዋል፡፡ ሊወጣ በሞከረ ቁጥር ድንጋይ እየወረወረ አፍ አፉን ይመታዋል፡፡ ከዚያም ወደነበረበት ይመለሳል፡፡ ‘ማነው ይሄ ወንዙ ውስጥ ያየሁት?’ ስል ‘ወለድ የሚበላ ነው’ ይለኛል፡፡” [ቡኻሪ፡ 2085]
10. ወለድ ከምናስበው በላይ እጅግ የገዘፈ ወንጀል ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ወለድ ሰባ ሶስት አይነት ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ቀላሉ አንድ ሰው እናቱ ላይ ዝሙት እንደመስራት ነው” ይላሉ፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 1851]
11. የወለድ መብዛት በምድር ላይ የአላህን ቅጣት ያስከትላል፡፡ ነብዩ ﷺ “ዝሙትና ወለድ በአንድ ሃገር ላይ ከበዛ በራሳቸው ላይ የአላህን ቅጣት አስወስነዋል” ይላሉ፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 1859]
የሽንት ቤት አጠቃቀም ስነ ስርኣት

ፅሑፉን ለማሳጠር ስል በእያንዳንዱ ነጥብ ስር ያሉትን ማስረጃዎች አልጠቀስኩም። ሆኖም ግን ማስረጃዎቹ የሚገኙበትን ምንጭ ስለጠቀስኩ ያስፈለገው በቁጥሩ ማግኘት ይችላል።

① እንዳይሰረቁ ወይም እንዳይጠፋ ካልሰጉ በስተቀር የአላህ ስም ያለበት ነገር ይዞ ሽንት ቤት ውስጥ አለመግባት።
② የሚፀዳዱት ሜዳ ላይ ከሆነ ከሰው እይታ ራቅ/ ሰወር ማለት። [ሶሒሕ ኢብኑ ማጃህ: 1/ 60]
③ በሰው መተላለፊያ መንገድ ላይ ወይ አጠገብ፣ ሰዎች ከሚጠለሉበት ዛፍ ስር፣ ፍሬው ከሚበላ ዛፍ ስር፣ የፍራፍሬ ዛፍና አትክልቶች አጠገብ፣ ወራጅ ባልሆነ ውሃ ላይ፣ የውሃ ምንጭ ላይ፣ በሙስሊሞች መቃብር ውስጥ አለመፀዳዳት። [ኢርዋኡል ገሊል: 1/100] [ሙስሊም: 269፣ 281] [ኢርዋእ: 1/102]
④ ንፋስ ወደሚነፍስበት አቅጣጫ ዙሮ አለመፀዳዳት፣ ይህን ትኩረት መስጠት ለጤናም፣ ለንፅህናም የተሻለ ነው።
⑤ የተሰነጠቀ መሬት ላይ ወይም ቀዳዳዎች ላይ አለመፀዳዳት። [አቡ ዳውድ: 29]
⑥ ውጭ ላይ የሚፀዳዱ ከሆነ ወደ መሬት ዝቅ እስከሚሉ ልብስን አለመሰብሰብ ወይም አለማውረድ። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 4652]
⑦ ውጭ ላይ በሚፀዳዱ ጊዜ ወደ ቂብላ አለመዞር፣ ጀርባንም ለቂብላ አለመስጠት። ሽንት ቤት ውስጥ ከሆነ ወይም ከፊት የሚጋርድ (ግድግዳና መሰል) ነገር ከኖረ ችግር የለውም። ይህንንም ቢሆን ከተቻለ መጠንቀቅ። [ቡኻሪና ሙስሊም] [ኢርዋእ: ቁ· 61]
⑧ ሽንት ቤት ሲገቡ ግራ እግርን ማስቀደም፣
⑨ ሽንት ቤት ሲገቡ "ቢስሚላህ። አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹቡሢ ወልኸባኢሥ" ብሎ ከሸይጧን መጠበቂያ ዱዓ ማድረግ። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 3611] [ቡኻሪና ሙስሊም]
(10) በሚፀዳዱ ጊዜ ብልትን በቀኝ እጅ አለመንካት፣ በቀኝ እጅ አለመፀዳዳት፣ [ቡኻሪና ሙስሊም]
(11) በሚፀዳዱበት ጊዜ በተቻለ መጠን ከማውራት መቆጠብ። [ሙስሊም: 370]
(12) ቢያንስ በሶስት ድንጋይ፣ ሶፍት፣ ወረቀትና መሰል ነገር መፀዳዳት። አንድም ቢሆን ሶስት የተለያዩ ጎኖች ወይም ገፆች ከኖሩትም በቂ ሊሆን ይችላል። ወይም በውሃ መጠቀም። አጥንት፣ ፋንዲያ፣ ምግብ ነክ ነገር እና ንፁህ ያልሆነ ነገር ለመፀዳጃነት አይውልም። [ሙስሊም: 262፣ 263፣ 271]
(12) ከሽንት ቤት ሲወጡ ቀኝ እግርን አስቀድሞ መውጣት።
(13) ከሽንት ቤት ሲወጡ "ጉፍራነክ" ማለት። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 4707]

(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 23/2010)
የሴቶችን ድንግልና የሚወስደው ማን ነው?
ይህን ፅሁፍ ለማዘጋጀት ያነሳሳኝ አብዛኛውን ጊዜ አንዳንድ ወደ እስልምና እንጣራለን የሚሉ ሰዎች ህግጋቱን ሁሉ ሴቶች ላይ ጫን አድርገው ወንዶችን ብዙም ሲሉ አይሰማም፡፡
ሰሞኑን አላዋቂዎች ብዙ ሲሳለቁ እና እራሳቸውንም መግለጫ ሰጪ አድርገው ሲያዩ ተመልክተናል፡፡ የሴት ልጅ ድንግልና በብዙ መንገድ ይሄዳል፡፡ ለምሳሌ ሴት ልጆችን በገዛ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው በመደፈር ሁሉ ያጡታል፡፡ ሴት ልጆች ሲደፈሩ ያውም ደፋሪያቸው እየታወቀ “በቃ ዝም በይ” አይነት ማስጠንቀቂያዎች ይሰጧታል፡፡ ድንግልና ያለ ግንኙነትም ሊጠፋ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ዑለማዎችም ሀኪሞችም ይገልፃሉ። ስለዚህ ድንግልና የሌላት ሁሉ ብልግና ፈፅማለች ማለት ዝቅ ሲል አላዋቂነት ከፍ ሲል ብልግና ነው። በሌሎችም መንገዶች ድንግልና ይሄዳል፡፡
አብዛኛዎቹ ሴቶች ልጅ በነበሩበት ሰኣት በጣም አይን አፋር እና ድንጉጥ ናቸው፡፡ ወንድን መቅረብ አይፈልጉም፡፡ ሴቶቹን ወደ መጥፎ ነገር የሚመሩዋቸው መጥፎ ሴት ጓደኞች እና ምላሳም ወንዶች ናቸው፡፡
መቼም ወንድ ከሌለ ሴቶች በራሳቸው ድንግልናቸውን አጠፉት አይባልም፡፡ አንድ ሴት ልጅ ድንግልናዋን ስታጣ እሷን ብቻ ከመውቀስ በምላሱ አታሎ፣ አጭበርብሮ ድንግልናዋን የወሰደባትን ለምን በደንብ አይኮንኑትም?
አስገራሚው ሴት ልጅ ስትሰራ ከነበረችው መጥፎ ነገር ቶብታለች ሲባል “እሷ እኮ…. ነበረች…. መጠንቀቅ ነው …. ምን ይታወቃል” እና የመሳሰለውን ትንኮሳዎች ይተበተባሉ፡፡
ወንድ ልጅ ግን ለምሳሌ አንዴ በድፍረት 21 ወይንም 22 አመት የሚጠጋው ወንድ ለጓደኞቹ “ከ180 እስከ 200 ሴቶች ጋር ግንኙነት ፈፅሚያለሁ” እንዳላቸው ሲናገሩ ሰምቻለሁ (የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የእኔ ኡመቶች ወንጀል ይማራል ግልፅ የሚያወጣው ሲቀር ብለዋል፡፡ ወንጀልን እንደቁም ነገር እና ጀብዱ የምታወሩ ሰዎች አላህን ፍሩ)፡፡ ለምሳሌ ይህን ሁሉ ሴት የነካካ ወንድ ቶብቷል ቢባል “አቤት እሱ እኮ ሷሊህ ነው፡፡ አቤት አኽላቁ፡፡ አቤት እሱን ያገኘች” ተብሎ ይለፈፋል፡፡
ለምን?
አላህ በተከበረው ቁርኣን ላይ
- ዝሙትን በተመለከት ተከልከሉ ሲል ለወንዱም ለሴቱም ነው፡፡
- ዝሙት ከፈፀሙ ያላገቡ ከሆኑ 100 ጅራፉ ይገረፉ ሲል ወንዱንም ሴቷንም ነው፡፡
- ዝሙትን የፈፀሙት ያገቡ ከሆነ በድንጋይ ተቀጥቅጠው ይገደሉ ሲል ወንድንም ሴትንም ነው፡፡
ታድያ ለምን ይሄን ያህል ሁለቱንም የሚመለከተውን ህግ ሴቶች ላይ ብቻ ጫን ማለት አስፈለገ፡፡ እንጨት ለምሳሌ በራሱ አይቀጣጠልም እሳት ሲቀላቀልበት ቢሆን እንጂ፡፡ ስለዚህ ወንድ እና ሴት በፈፀሙት ወንጀል አንዱን ብቻ ጠንከር አድርጎ መውቀሱ በተለይ ከኢስላም ውጭ ያሉ ሰዎች “ኢስላም ሴትን ይበድላል” እንዲሉ የሚያደርጋቸው ይህ ነው፡፡
ፍትሀዊ የሆነ ሀይማኖት ይዘን ፍትህ የሌለ አስመስለን አናቅርበው፡፡ ያለ እውቀት መናገር ሁሌም ጣጣው ከሚታሰበው በላይ ነው፡፡
የቶበቱ ሰዎችን አስመልክቶ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ወደ አላህ የተመለሰ ወንጀል እንደሌለበት ነው፡፡” ብለው ሲያበቁ ወደ አላህ የተመለሱ ሰዎችን እያጣጣሉ መናገር መሀይምነትን በይፋ የሚያሳይ ነው፡፡
አስገራሚው ግልፅ ቢድኣና ሺርክን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የሌላቸውን ጥንካሪ እና ድፍረት ወንጀል ላይ የወደቁት ላይ ሲያደርጉት እንመለከታለን፡፡
ወንጀል በድብቅ የሰራ ሰው አይቡ ይደበቅለታል፡፡ ቢድኣን እና ሺርክን በአደባባይ የሚፈፅም ደግሞ በአደባባይ ሙስሊሞች እንዲጠነቀቁት መልስ ይሰጥበታል ይህ ነው ፍትህ እና ሚዛናዊነት፡፡
ዛሬ የቢድኣ ካዝና ለሆኖ ሰዎች ጥብቅና ቆመው እነሱን አናስነካም፡፡ እነሱን የነካ “አይባቸውን እንዳወጣ ነው” ሲሉ ይቆዩና ተደብቀው ወንጀል የሚሰሩ ሰዎችን “ተከታትለን በካሜራ እናጋልጣለን” ብለው ስሜት አምላኪነታቸውን ያሳዩናል፡፡
እንዲህ አይነት መሀይማን ጉዳታቸው እጅጉን የከፋ ነው፡፡

ፅሁፌን ስጨርስ ሴቶችን እንደነ መርየም ድንግልናችሁን ጠብቁ ስንል፣ ወንዶችንም ልክ እንደነ ኡስማን ኢብን አፋን ሁኑ ከዝሙት ራቁ፡፡ ወንድ እና ሴቶች ሆይ! አላህን ፈርታችሁ ቶሎ ተጋቡ፡፡ በኢስላም ትዳር ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ከትዳር ያለ አስገዳጅ ሀጃ በመዘግየታችሁ ምንም የምትጨምሩት ነገር የለም፡፡ የምታጡት ነገር ቢብስ እንጂ፡፡
ስለ ትዳር የበሰሉ ሃያእ ያላቸውን ታላቆችን አማክሩ፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አስተማሪና መሳጭ ታሪክ!
በስዑዲ የሚኖር አንድ የመኒ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያጋጠመውን ታሪክ እንዲህ ይተርከዋል፡፡
ከፊሌ የዘካ ገንዘብ ሊያከፋፍል ፈልጎ ከሱ ጋር ወጣሁ፡፡ የድሃ መንደሮች ወዳሉባቸው ጠረፍ አካባቢ ተጓዝን፡፡ የዘካው ገንዘቦች በፖስታ የታሸጉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ፖስታ በውስጡ 5 ሺ ሪያል ይዟል፡፡ ከአንዱ መንደር ወጥተን የጂዳ-ጂዛን መስመር ስንይዝ አንድ የ70 አመት አካባቢ ሽማግሌ አገኘን፡፡ ሽማግሌው ብርቱና ጤናማ ነው፡፡ ጎዳናውን ይዞ ይጓዛል፡፡
ወዳጄ “ይሄ ደግሞ በዚህ ሰዓት በዚህ በረሃ ምን ይሰራል?” አለኝ፡፡
ሹፌሩ “ህገ ወጥ የመኒ ነው” አለ፡፡
ካጠገቡ ደርሰን ቆምንና ሰላም አልነው፡፡
“ከየት ነው ወንድም?”
“ከየመን”
“የት ነው የምትሄደው?”
“የአላህን ቤት ናፍቄያለሁ”
“ህጋዊ ነህ?”
“አይደለሁም”
“ለምን ህጋዊ አልሆንክም?”
“ለዋስትና 2 ሺ ሪያል ማስያዝ ይጠበቅብኛል፡፡ እኔ ያለኝ 200 ብቻ ነው፡፡ በመቶዋ ተሳፈርኩባት፡፡ የቀረኝ መቶ ብቻ ነው” አለ፡፡
“እሺ አጎቴ! በጉዞ ላይ ምን ያክል ሆነህ?” አለው ጓደኛየ፡፡
“ስድስት ቀን!”
“እየፆምክ አይደለም?”
“አይ ፆመኛ ነኝ፡፡”
“ጥሩ፡፡ አንተ ከ 5 በላይ የፍተሸ ኬላዎችን አልፈሃል፡፡ እንዴት ነበር የምታልፋቸው?” ሲለው
“ከሱ በስተቀር እውነተኛ አምላክ በሌለው አላህ እምላለሁ! የማልፈው በነሱው ዘንድ ነው፡፡ ግን አንድም ያናገረኝ የለም!!” አለ፡፡
“ለስራ ነው አመጣጥህ?”
“በጭራሽ ወላሂ! እኔ የአላህን ቤት ናፍቄ ነው የመጣሁት፡፡ ዑምራ ማድረግ ነው የምፈልገው፡፡ ወደ መካ ነው የምጓዘው፡፡”
“በአስፋልት ላይ ስትጓዝ ተዘዋዋሪ ዘቦች /ፓትሮል/ አልያዙህም?”
“ከግማሽ ሰዓት በፊት በ 50 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ ይዘውኝ ነበር፡፡ እዚህ ከመድረሴ አንድ ኪ. ሜ. ቀደም ብሎ ድረስ እነሱ ናቸው ያመጡኝ፡፡ የት እንደምሄድ ሲይቁኝ በአላህ ምየ የአላህን ቤት እንደምፈልግ ስነግራቸው ለቀቁኝ” አለ፡፡
“ሱብሓነላህ! ጭራሽ እስከዚህ ቦታ በፍጥነት እንዲያደርሱህ አላህ ፓትሮሎችን አመቻቸልህ” አልኩኝ በውስጤ፡፡
ወዳጄ ሁለት ፖስታዎችን እየሰጠው “እነዚህን ያዝ፡፡ ዘካ ነው” አለው፡፡
እየተቀበለ “ጀዛኩሙላህ ኸይር” አለ፡፡
በፖስታዎቹ ያለው ገንዘብ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ አያውቅም፡፡
“የሰዑዲን ብር ታውቃለህ?” አልኩት፡፡
“አዎ!” አለ፡፡
“ጥሩ፡፡ ፖስታውን ክፈትና እንዳይጠፋብህ ገንዘቡን በቀበቶህ (በሒዛምህ) ውስጥ ደብቅ” አልኩት፡፡
ሲከፍተው 10 ሺህ ሪያል!!
“ይህ ሁሉ ለኔ ነው?” አለ፡፡
“አዎ ላንተ ነው” አልነው፡፡
ከመኪናው ላይ ወደቀ፡፡ እራሱን ሳተ፡፡ ከመኪናው ወርደን በላዩ ላይ ውሃ መርጨት ያዝን፡፡
“ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው? ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው?” እያለ መጮህ ያዘ፡፡ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ቀጠለ፡፡
ወዳጄ፡ “ከኛ ጋር ትንሽ ወደ ፊት እንውሰደው” አለ፡፡
ከኛ ጋር መኪና ላይ ወጣ፡፡ ትንሽ ሲረጋጋ ጠየቅኩት፡
“ምንድን ነው ይህ ሁሉ ለቅሶ?” አልኩት፡፡
“እኔ የመን ውስጥ ከቤቴ ጎን ቦታ አለችኝ፡፡ ለአላህ ሰጥቻታለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቦቼ በሷ ላይ በጭቃና በድንጋይ አድርገን መስጅድ ገንብተንባታል፡፡ ግንባታው ቢጠናቀቅም ምንጣፍና ጥቂት ነገሮች ቀርተውት ነበር፡፡ ለዚህ መስጂድ እንዴት ምንጣፍ እንደማገኝ ተቀምጬ አስብ ነበር” አለ፡፡
ይህን ሲል የእውነት ሁላችንም አለቀስን፡፡ “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው ዱንያ እንዳለች ትመጣለታለች” የሚለውና “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃቱን ከልቡ ውስጥ ያደርግለታል፡፡ ነገሩንም ይሰበስብለታል፡፡ ዱንያ በግዷ ወደሱ ትመጣለች፡፡ አሳቡ ዱንያ የሆነ ደግሞ አላህ ድህነቱን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል፡፡ ነገሩንም ይበትንበታል፡፡ ከዱንያም የተወሰነለት ብቻ እንጂ አይመጣለትም” የሚለው የነብዩ ﷺ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡
በዚህን ጊዜ ወዳጄን ለሰውየው እንዲጨምረው ጠየቅኩት፡፡ ተጨማሪ 2 እሽግ ፖስታ ሰጠው፡፡ በድምሩ 20 ሺ ሪያል አገኘ ሰውየው፡፡ ሰውየው ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እያለቀሰ ያጉተመትምና ዱዓ ያደርግ ነበር፡፡
“በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ልክ ወፍን እንደሚረዝቀው ይረዝቃችሁ ነበር፡፡ ተርባ ወጥታ ጠግባ ትመለሳለች” የሚለው የነብዩ ﷺ ሐዲሥ መጣብኝ፡፡
የተተረጎመ
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 25/2010)
ለአቅመ አዳም ወይም ለአቅመ ሄዋን የሚደረሰው መቼ ነው?!

ብዙ ሰዎች ሸሪዐዊ ሃላፊነት ለመሸከም የሚደረስበትን እድሜ ሲያስቡ 15 አመት መድረስን ብቻ ነው ከግንዛቤ የሚያስገቡት፡፡ እውነታው ግን ሌሎች ተጨማሪ መለኪያዎች መኖራቸው ነው፡፡ በጥቅሉ አንድ ሰው እንደማንኛውም "አዋቂ" ሙስሊም ተቆጥሮ በሚሰራው መልካም ስራ የሚመነዳበት እና በሚሰራው ጥፋት የሚቀጣበት (ባጭሩ ስራዎቹ የሚመዘገቡበት) የእድሜ ክልል የሚደርሰው ከሚከተሉት አራት ምልክቶች ውስጥ ቀድሞ በተከሰተው ነው፡-
1. በህልምም ይሁን በውን የዘር ፈሳሽ መርጨት መጀመር
2. በብልት ዙሪያ ፀጉር መብቀል (መባለቅ)፡-
መጠኑም ፀጉሩ ለመላጨት የደረሰ ብዛት ሲኖረው ነው፡፡ እዚህ ላይ የፂም ወይም የብብት ፀጉር መለኪያ አይሆንም፡፡ የጡት መውጣት፣ የድምፅ መጎርነንና መቅጠን መለኪያ አይደሉም።
3. ለሴት የወር አበባ ማየት፡-
እነዚህ ሶስት ምልክቶች ከታዩ ልጅዎት ለሸሪዐዊ ሃላፊነት ደርሷል ወይም ደርሳለችና ያስገንዝቡ ይከታተሉ፡፡ 15 አመት መድረስን እየጠበቁ ተዘናግተው እንዳያዘናጉ፡፡ ደግሞም ከልጆችዎት ጋር ለጉዳዩ የሚያስፈልገውን ያክል ግልፅ ውይይትና መነጋገር ይኑር፡፡ ጉዳዩን ቀድሞው ካወቁ እራሳቸውን ለሃላፊነት ያዘጋጃሉና፡፡ ካላወቁ ግን እድሜያቸው ደርሶ ላይሰግዱ ላይፆሙ ይችላሉ፡፡ ልክ እንዲሁ ካላወቁ ወይም ደግሞ አጉል መተፋፈር የሚኖር ከሆነ ከነ ጀናባቸው ሊሰግዱ፣ የወር አበባ ላይ ሆነው ሊፆሙና ሊሰግዱ ይችላሉ፡፡ ይሄ ከባድ ጥፋት ነው። ስለዚህ ለልጆችዎት ወይም ደግሞ ለእህት ወንድሞችዎት በቂ ግንዛቤ ያድርሱ፡፡ መተፋፈሩ ሐቅ እንዳይሸፍንም ይጠንቀቁ፡፡
4. የመጨረሻው ምልክት 15 አመት መድረስ ነው።
ከላይ ከተራ ቁጥር አንድ እስከ ሶስት የተጠቀሱት ምልክቶች ባይታዩም 15 ከተደረሰ ቀጥታ የልጅነት የእድሜ ክልል ታልፏል ማለት ነው፡፡
ምልክቶቹ ከ 15 አመት ቀድሞ መታየት የጀመሩ ከሆነ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እንደማንኛውም አዋቂ ሰው ሸሪዐዊ ህግጋትን በጥብቅ መከታተል ይገባል፡፡ ምልክቶቹ ቀድመው ታይተው ሳለ ሳይፆም የታለፈ የረመዳን ፆም ካለ ቀዷ ማውጣት ግድ ይላል ይላሉ ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን ረሒመሁላህ፡፡ በማህበረሰቡ ዘንድ ስለጉዳዩ ጭራሽ ግንዛቤ ከሌለ ግን ቀዷ ማውጣቱ ግዴታ እንዳልሆነ ፍንጭ የሰጡበት ፈትዋ አለ፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡ ዝርዝር መረጃ ወይም ግልፅ እና ቀጥተኛ ፈትዋ ያገኘ ሰው ከስር ቢያሰፍረው ሁላችንንም ይጠቅማል፡፡
በነገራችን ላይ 15 አመት መድረስ ሲባል የሚፈለገው በኢስላማዊው የሂጅራ አቆጣጠር እንጂ በፀሐይ አቆጣጠር አይደለም፡፡ (የሂጅራው አቆጣጠር የጨረቃ አቆጣጠር ሲሆን የኢትዮጵያውና የፈረንጆቹ ግን የፀሐይ አቆጣጠር እንደሚባል ያስተውሉ፡፡) በጨረቃ አቆጣጠር አንድ አመት 354 ቀን ከ 9 ሰዓት አካባቢ ሲሆን በፀሐይ አቆጣጠር ግን 365 ቀን ከ 6 አካባቢ ነው፡፡ እናም አንድ ልጅ በሂጅራው አቆጣጠር 15 አመት የሚደርሰው ከፀሐዩ አቆጣጠር ቢያንስ ከ 5 ወራት በፊት ቀድሞ ነው ማለት ነው፡፡
ስለዚህ አንድ ልጅ ከ 15 ዓመት በፊት ከላይ ከአንድ እስከ ሶስት ካሉት ምልክቶች አንዱ ከታየበት ወይም ደግሞ እነዚህ ሳይታዩ ቀርተው 15 አመት ከደረሰ ጊዜ ጀምሮ እንደማንኛውም አዋቂ ሰው ለሸሪዐዊ ህግጋት ተገዥ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ በኋላ ሴቶችን መጨበጥ፣ መመልከት፣ ከአንዲት ሴት ጋር ለብቻ ተገልሎ መቀመጥ የለበትም፡፡ በቃ ከዚህ በኋላ በደረሱ ወንዶች ላይ የሚከለከሉ ነገሮች ሁሉ ለሱም ክልክል ናቸው፡፡ የደረሱ ወንዶችን የሚመለከቱ ግዴታዎች ሁሉ ይመለከቱታል፡፡ ሴቷንም እንዲሁ፡፡ አለባበስን ጨምሮ ነገሮችን በጥንቃቄ ልትከታተል ይገባታል፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 2/2009)
በ Ibnu Munewor
በኢኽዋን የተሸወዱ ወገኖችን ለማንቃት

በኢኽዋን ቡድን ከንቱ ማምታቻ ከተሸወዱ ወገኖች ውስጥ ከፊሎቹ የሱፍያን ብልሹ አቋም የሚያውቁና የሚፀየፉ ናቸው። እነዚህ ወገኖች ስለኢኽዋን እንዲነቁ ከፈለግን ቡድኑ ከሱፍዮች ጋር ያለው ጥብቅ ትስስር ማሳየት ይገባል። እንዲያውም ቡድኑ እራሱ ከምስረታው ጀምሮ ሱፊ እንደሆነ፣ መስራቹ ሐሰን አልበንናም የሻዚሊያ–ሐሷፊያ ጦሪቃ ተከታይ እንደነበር የራሱ ኪታብ እያጣቀሱ ማስረዳት ይገባል።
በኢኽዋን ቡድን ከንቱ ማምታቻ ከተሸወዱ ወገኖች ውስጥ ብዙዎቹ የሺዐዎችን መሰሪነት ጠማማነት ከሞላ ጎደል ያውቃል። ስለዚህ ኢኽዋን ከሺዐ ጋር ያለውን ጥብቅ ትስስር በማስረጃ በማጋለጥ ሰዎች የኢኽዋንን ትክክለኛ ማንነት እንዲያውቁ ማድረግ ይቻላል። ለዚህም የቡድኑ ቁንጮ የሆኑ ሰዎች ስራዎች ከበቂ በላይ ማስረጃ መሆን ይችላሉ።
በኢኽዋን ቡድን ከንቱ ማምታቻ ከተሸወዱ ወገኖች ውስጥ ብዙዎቹ የተክፊር አካሄድን ክፉኛ የሚፀየፉ ናቸው። ሆኖም ግን በኢኽዋን ደጋሚዎች ስለተደገመባቸው የቡድኑን ኸዋሪጃዊ አካሄድ አያውቁም። ስለዚህ ለዘመናዊ የኸዋሪጅ አስተሳሰብ የመሰረት ድንጋይ የጣለው ኢኽዋኒው ሰይድ ቁጥብ እንደሆነ በራሱ ኪታብ በማሳየት፣ የራሱን ደጋፊዎች ምስክር በማድረግ ውጤታማ ስራ መስራት ይቻላል።