Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
የአላህ አንድነት ያልተረጋገጠበት አንድነት አንድነት ተብሎም አይጠራም፡፡
=========================
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ፡፡
የተሳሳተ አባባል
=========
‹‹የአላህን አንድነት አስጠብቃለሁ ስትል የኡማውን አንድነት በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት››
ትክክለኛው አባባል
==========
‹‹የኡማው አንድነት መገንባት ያለበት የአላህን አንድነት (ብቸኛ ተመላኪነት) እስከተረጋገጠ ድረስ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡››
ማብራሪያ፡-
የአንድነት መመስረቻው አንድ የሆነውን አላህ አንድ አድርጎ መገዛት ብቻ ነው፡፡ በዛም ላይ መሰባሰብ ነው፡፡ ሽርክ ተንሰራፍቶ ግን የኡማው ‹‹አንድነት›› እንዳይከፋፈል በሚል ማማካኛ የአላህን አንድነት ከማስከበር ይልቅ ሽርኩን ማድበስበስም ይሁን ሂክማ በሚል ስም መደባበቅ የውሸት አንድነት ነው፡፡ አላህም ዘንድ የተወደሰ አንድነት አይሆንም፡፡ ይልቁንስ አላህ ዘንድ የሚያስወቅስ ቢሆን እንጂ፡፡
አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) የይሁዳዎችን አንድት አስመልክቶ ‹‹አንድ ናቸው ብለህ ትገምታለህ ልቦቻቸው የተለያዩ ናቸው›› ይላል፡፡ ይሄ እምነቱ አንድ ሳይሆን አንድ ነን ለሚል ሰው መልስ ይሆነዋል፡፡
የእውነተኛውን አንድነት ደግሞ ሰጪው እና ባለቤቱ አላህ ብቻ ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንኳን የሰሃባዎችን ልብ ማስማማት እንደማይችሉ እና ይህ የአላህ ስልጣን ብቻ መሆኑን አላህ ተናግሯል፡፡ የአላህን አንድነት ሳያረጋግጡ ደግሞ አላህ አንድ አያደርጋቸውም፡፡ የአላህ አንድነት ያልተረጋገጠበት አንድነት አንድነት ተብሎም አይጠራም፡፡
በኢስላም አንድነት በጣም የተወደሰ፤ ልዩነት በጣም የተወገዘ ነገር ነው፡፡ ይህ ሲባል ግን አንድነት ማለት ከአላህ ውጭ የሚያመልከውን ሁሉ መሰብሰብ ሳይሆን አላህን በማምለክ ላይ መሰባሰብ ነው፡፡ ከአላህ ውጭ ላሉ አካላት ከሚፈፀመውም አምልኮ ሆነ፣ ከአላህ ውጭ ከሚያመልኩት አካላት መራቅ ነው፡፡ አላህም ‹‹የአላህን የማመን ገመድ አጥብቃችሁ ያዙ አትለያዩ›› ነው ያለው፡፡ ከዚህ ሁለት ዋና ነጥቦችን እንይዛለን፡፡
1) የአላህን የማመን ገመድ ያዙ፡፡ ይሄ የአንድነት ምንጭ ነው፡፡ አንድ ለመሆን ይህን ማሟላት ግድ ይላል፡፡ የዚህ ተገላቢጦሽ ደግሞ የመለያየት ሰበብ ነው፡፡ ይህ አንቀፅ ቁጥርን ስለማብዛት ሳይሆን ያዘዘው በሃቅ ላይ፤ በአላህ የማመን ገመድ ላይ መሰባሰብን ብቻ ነው፡፡ ቁጥሩም ቢያንስ የሚፈለገው የአላህን የማመን ገመድ አጥብቆ መያዝ ነው፡፡
2) አትለያዩ፡፡ ትዕዛዝ ነው፡፡ ለልዩነት ሰበብ የሚሆኑ ነገሮችን ሁሉ ራቁ፡፡ የአላህ ገመድ የተባለው ቁርዓን ነው ተብሏል፡፡ የመለያያ ሰበቦች ሽርክ፤ ቢድዐ፤ ስሜትን መከተል እና ወንጀሎችም ተፅኖ አላቸው፡፡ ተውሂድ እና ሱና በሰሃባዎች አረዳድ መረዳት እና በዛ ላይ መሰባሰብ ከመጣ በኋላ፤ ልዩነት የተወገዘ ነው፡፡
ሌላ ማብራሪያ የሚሻ ንግግር አለ
‹‹አንድ መሆን የማይቻል ቢሆን ኖሮ አላህ በቁርዓን ላይ አንድ ሁኑ ብሎ ባላዘዘ ነበር››፡፡
ይህ አባባል አሻሚነት አለው፣ ሊብራራ ይገባዋል፡፡ አላህ አንድ ሁኑ ብሏል በሚል አካሄድ ለምሳሌ
1) ከአህባሽ ጋር አንድ መሆን ይቻላል? አይቻልም፡፡
2) ቻግኒ ላይ የተደረገው አይነት ከቲጃኒዬች ከባባድ ሽርክ ካለባቸው ሰዎች ጋር አንድ መሆን ይቻላል? በፍፁም፡፡
3) ቁርኣን ተቀንሷል ከሚሉት፤ አቡበክር እና ኡመርን (ረድየላሁ አንሁም) ከሚራገሙት፤ የምዕመናን እናትን አኢሻን ከሚያከፍሯት ሺዐዎች ጋር አንድ መሆን ይቻላልን? በፍፁም፡፡
4) ከአላህ ውጭ ሺርክን ከሚያጨማልቁ ሱፍዬች ጋር አንድ መሆን ይቻላል? በፍፁም፡፡
ስለዚህ አላህ አንድ ሁኑ ብሏል ብሎ ሽርክን፤ ከባባድ ቢድዐ ከሚያግበሰብሰው ጋር ሁሉ አንድ ነን አይባልም፡፡ አላህ አንድ ሁኑ ሲል ከነማን ጋር መሆን እንዳለበት፣ በምን መስፈርት መሆን እንዳለበት በሚገባ አስቀምጧል፡፡ ሙሉ የሆነውን የኢስላም መልክት ለሚፈልጉት አላማ ቆርጦ መጠቀም ዬሁዳ ባህሪ ነው፡፡ አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ የሚባል ነገር አይሰራም፡፡ አላህ ወደ እስልምና ጥቅልል ብላችሁ ግቡ ነው ያለን፡፡ መደረግ ያለበት እነሱን አንድ ነን እያሉ መሸንገል፤ ባሉበት የጥመት መንገድ ላይ መተው ሳይሆን ሃቁን መንገር፣ የተሳሳተ መንገድ ላይ እንዳሉ መንገር ነው፡፡ ሃቅ አንድ ብቻ እና ብቻ መሆኗን ማስተማር፡፡ ሸይኽ ሙሐመድ አወል ሰኢድ (ሀፊዘሁላህ) “ልዩነት እያለ ልዩነት የለም ማለት ተጨፈን እና ላሞኝህ ማለት ነው” ብለዋል፡፡
አንድ የሚነሳ አባባል አለ፤ ይህ እውነት ሲነገር ‹‹ጠላት ሊያጠፋን አሰፍስፎ ተነስቶ….አሁን ይህንን አርእስት ለምን ታነሱታላችሁ›› የሚሉ አሉ፡፡ መልሱም ቀላል ነው፡፡ የአላህን አንድነት እስካስጠበቅን፣ በሐቅ ላይ እስከተሰባሰብን፣ ሺርክና ቢድዓን ከየትኛውን ቡድን ይምጣ የመጅሊስ ስልጣን የያዘውን አህባሽ እንደምንቃወመው እስከተቃወምን እና እስከተዋጋን ድረስ አላህ በጠላቶቻችን ልብ ውስጥ የአማኞችን ፍርሃት ይለቅባቸዋል፡፡ አላህ ካሃዲያንን በአማኞች ላይ መንገድን አያደርግላቸውም፡፡ የአላህ ባርያ ሆኖ መገኘት እንጂ አላህ እንዲህ ይላል ‹‹አላህ ባርያውን በቂ አይደለምን?›› ነው እንጂ፡፡
የተለያዩ አካላትን ከአላህ ውጭ ለምሳሌ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን)፤ አልይን፤ ሁሴንን፤ ጀይላኒን፤ ኑር ሁሴንን፤ አብሬትን፤ ቃጥባሬን፤ አልከሶን፤ አሊ ጎንደርን እና የመሳሰሉትን መጥራት ከባድ ወንጀል፤ ታላቅ በደል፤ አንድነትን፤ ድልን፤ እርዳታን ከአላህ የማያስገኝ ሆኖ ሳለ፤ በተገላቢጦሽ የአላህን ቁጣ፤ የጠላት መጫወቻ ሰበቡ ይሄ ሆኖ ሳለ፤ ይህን የከፋ ሽርክ እና ቢድዐን አቅፎ መሄድ የባሰ አደጋ ያመጣል እንጂ ለውጥ የለውም፡፡
ሃቅ አንድ ናት፡፡ እሷም የጥንት የጠዋቱ ቁርዓን እና ሀዲስን የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች እና የነሱን ፈለግ የተከተሉ የሄዱበት የሰለፎቹ ጎዳና ናት፡፡
ልብ ሊባል የሚገባው ሌላ ነጥብ አለ፡፡ እሱም ፈተና አማኞችን እምነታቸውን ለመፈተንም ይመጣል፡፡ አምኖም መፈተን አይቀርም፡፡በግልፅ ሽርክ እና ቢድዐ ተንሰራፍቶ እየታየ ግን ጠላት ተጫወተብን ማለት ቂልነት ነው፡፡ አላህ የእሱን ህግጋት ስንረዳ ነው የሚረዳን፡፡ ሰዎች ዘራቸው፣ የግል መብታቸው ሲነካ የሚነዝራቸውን ያህል የአላህ መብት ሲጣስ ምንም ካልመሰላቸው ከባድ አደጋ ላይ ወድቀዋል፡፡ የጠላት መጫወቻም ለመሆን እራሳቸው ከሰበቡ ውስጥ አሉበት፡፡
ይህን ኡመት ከሌላ ኡመቶች የለየው በጥሩ ማዘዙ ከመጥፎ መከልከሉ ነው፡፡ ይህን የማያደርጉት አላህ የረገማቸው የሁዳዎች ናቸው፡፡
ሰው በተፈጥሮው ስህተቱን ካልነገሩት ሃቅ ላይ ያለ መስሎ ይሰማዋል፡፡ ሽርክን በየአይነታው ለሚሰራ ሰው ‹‹አንድ ነን›› ካልከው እራሱን በቁርዓን እና ሀዲስ በሰለፎች አረዳድ እንዳይገመግም እንቅፋት እየሆንክበት ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ደግሞ ‹‹ያታለለ ከእኛ አይደለም›› ይላሉ፡፡ ሽርክ ያለበትን አንድ ነን ብሎ መሸንገል ማታለል ነው፡፡
የአንድነት መስፈርቱ በሌለበት ቦታ ላይ አንድ ሁኑ ብሎ አላህ አላስገደደም፡፡ የአላህ አንድነት ባልተረጋገጠበት ቦታ ወደ አላህ መንገድ የሚጣራ ሰው ስለ አላህ አንድነት አስተምሮ ሁጃ (መረጃ) ካቆመ በኋላ ሽርኩንም፤ ሽርክ የሚሰሩ ሰዎችንም ጥሎ እና ርቆ መሄድ ነው ያለበት፡፡ ይሄም በራእ ይባላል፡፡ ወላ እና በራእ በኢስላም ታላቁን ቦታ ይይዛል፡፡ ወላ እና በራእ ማለት ለአላህ ብሎ መወዳጀት እና ለአላህ ብሎ መጥላት እና ጠላት ማድረግ ነው፡፡
አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ኢብራሂም አለይሂ ሰላምን አስመልክቶ ሽርክ የሚሰሩትን ማህበረሰቦቹን እና ሽርካቸውን ጥሎ በሄደ ግዜ ‹‹ኢስሃቅ እና ያእቁብን ሰጠነው፤ ሁሉንም (ሁለቱንም) ነብይ አደረግን›› ይላል፡፡ እንደሚታወቀው ነብየላህ ኢብራም ህዝባቸውን አባታቸውን ጨምሮ እስኪገባቸው ድረስ በተለያየ መንገድ ስለ ሽርክ አስከፊነት ስለ ተውሂድ ታላቅነት አስረድተዋል፡፡ ይህን ካደረጉ በኋላ አልሰማ ሲሏቸው ብሎም እሳት ውስጥ እስከመወርወር ሁሉ ሲደርሱ ህዝባቸውን ተገንጥለው ወጡ፡፡
አላህም የኢብራሂምን መንገድ ተከተሉ ብሎ አዘዘ፡፡ ጥሪ ወደ አላህ ማድረግን ከዛም ማስረጃን ካቆሙ በኋላ ሽርክን እና ባለቤቶቹን መራቅን፡፡
የተፃፈ ሁሉ ሃቅ ነው ማለት አይደለም፡፡ በቁርዓን እና ሀዲስ በሰለፎች ግንዛቤ ተመዝኖ እስካላለፈ ድረስ፡፡ ኢስላም የነብያት ሁሉ ሃይማኖት ቅድሚያ የሰጠውን ቅድሚያ መስጠት በማንም ላይ ግድ ይላል፡፡ ልቡን ለታመመ ሰው የራስ ምታት ኪኒን እንደማይሰጠው ሁሉ ሽርክ እና ቢድዐ በተንሰራፋበት ሁኔታ ላይ የተውሂድ እና ሱና መድሃኒት፤ የሰለፎች አረዳድ ብቻ እና ብቻ ነው የሚሰጠው፡፡ አለበለዚያ በሽታው እና መድሃኒቱ ካልተገናኘ ጭራሽ በሽታው ሊብስ ይችላል፤ ብሎም ሊገድል፡፡
የኡማው አንድነት የሚመጣበትን ሰበብ ትቶ ሌላ መንገድ ቢኳተን ግዜን ማጥፋት ብቻ እንጂ ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ‹‹በምድር ያለን በጠቅላላ ብታወጣ ልቦቻቸውን አታስማማም፡፡ አላህ ግን በልቦቻቸው መሃል አስማማ›› ብሎ ይህ የአላህ ስልጣን ብቻ እንደሆነ ይነግረናል፡፡
ታድያ ምን ነው ሰሚ የጠፋ ይመስል፣ ሽርክ እና ቢድዐ ለሚሰሩ ሰዎች ነብያት እንዳደረጉት ቅድሚያ ለሚገባው ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ ተውሂድ እና ሱና ካልተስተካከል ፍሬ የማያፈሩ አርስቶችን ማራገቡ ለምን አስፈለገ???
አማና ማለት ይህ ነው? አላህ የእርሱን አማና ከሚጠብቁት ያድርገን፡፡
አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፤ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
እኔ ሙስሊም፣ ሱኒ፣ ሰለፊ ነኝ፡፡
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ፡፡
እኔ ሱኒ ነኝ ሺአ አይደለሁም ብል
“አላህ ሙስሊም ብሎ ነው የጠራን አትከፋፍሉን፡፡ መለየት አያስፈልገንም” የሚለኝ አይኖርም፡፡
አንድ ሰው እራሱን ሱኒ ነኝ ሲል ሙስሊም አይደለሁም እያለ አይደለም፡፡ እንዲያውም ሺአዎች እራሳቸውን ሙስሊም ነኝ ብለው ቢጠሩም ትክክለኛ ሙስሊም አይደሉም፣ እነሱ የሄዱበትን መንገድ አልሄድበትም፣ አልቀበለውም፣ እኔ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሰሃባዎቻቸውን እና የሰለፉነ ሷሊሂንን መንገድ የምከተል ሙስሊም ነኝ ማለቴ ነው፡፡
እኔ ሰለፊ (ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም፣ ሰሃባዎቻቸው እና ሰለፉነ ሷሊሂንን የምከተል) ነኝ፡፡ ቀደርያም፣ ጀበርያም፣ ኸዋሪጅም፣ ሺኣም፣ ሙእተዚላም፣ ሙርጂኣም፣ ማትሩድያም፣ አሽአሪያም፣ ኩላቢያም፣ ሱፍያም፣ ….. ኢኽዋንም፣ ተብሊግም፣ አህባሽም ሌላንም የምከተል ….. አይደለሁም ብል
“አላህ ሙስሊም ብሎ ነው የጠራን አትከፋፍሉን፡፡ መለየት አያስፈልገንም” የሚለኝ አውቆ አጥፊ ብቅ ይላል፡፡ ኡለማም አይደለም፡፡ ግን ሰለፊ ብሎ እራስን መጥራት አይቻልም ሲል አፉን ሞልቶ ይናገራል፡፡ በጣም የሚገርመው ሰዎች እራሳቸውን ተብሊጎች ነን፣ ኢኽዋን ነን፣ አሽአሪ ነን፣ ሱፊ ነን ሲሉ “አላህ ሙስሊም ብሎ ነው የጠራን አትከፋፍሉን” ብሎ ሲናገር አትሰሙትም፡፡
አላሁል ሙስተኣን አውቆ አጥፊዎች ጥፋታቸው ንብርብር ነው፡፡ ምክንያቱም ብዙ አላዋቂ ተከታያቸው አዋቂ ብሎ ይከተላቸዋልና፡፡
አሁንም እንላለን እኛ በአላህ ፍቃድ ሁሉንም የጥመት ቡድን አንቀበለም፡፡ የመጅሊስ ስልጣን የያዘውን አህባሽም ይሁን ያልያዘውን ኢኽዋን፡፡ እኛ የጥንት የጠዋቱን የሰለፉነ ሷሊሂንን መንገድ ነው የምንከተለው፡፡ ይህ ማለት እኛ ሙስሊሞች ነን ቁርኣንና ሀዲስን የጥንት የጠዋት የሆኑት ቀደምት መልካም አርአያዎቻችን በተረዱት መንገድ የምንረዳ፡፡ ከሰለፉነ ሷሊሂን በኋላ የመጡትን የትኛውንም አይነት ቡድኖች እና አስተሳሰቦች የጥመት ደረጃቸው ቢለያይም እንቃወማለን፣ አንቀበለም፡፡
ከሐቅ በኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ? የሐቋ መንገድ አንድና አንድ ብቻ ናት፡፡ እሷም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው የነበሩባት፣ እነሱንም በእምነት የተከተሉት መንገድ ብቻና ብቻ ናት፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ስለ ተውሒድ ማወቅ ስለ ሰላት እና ስለ ዘካ ከማወቅ በላይ አንገብጋቢ ነው፡፡ ስለ ሺርክ አደገኝነት ማወቅ ስለ ሶላትን ከሚያበላሸው ነገር እውቀት በላይ መታወቁ ግድ ይላል፡፡ ተውሒድ ፊቂሁል አክበር (ታላቁ ፊቂህ) ተብሏል፡፡ ተውሒድ ከሌለ ምንም ነገር የለም፡፡ ሁሉም ኢባዳዎች ሰላት፣ ዘካ፣ ፆም ተውሒዱ ለተስተካከለ ብቻና ብቻ ነው ጥቅም ያላቸው፡፡ መቀደም ያለበትን እና ትኩረት ሊሰጠው ለሚገባው ትኩረት እንስጥ፡፡
አላህ በተውሒድ ላይ አኑሮ በተውሒድ ላይ ይግደለን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ኢኽዋኖቹ
"ደም ሲለግሱ " ፣ የታመመን ሲጠይቁ፣ ለተጎዳ
ገንዘብ "ሲረዱ" አንዳንዴም ሲዘሉ እና ጆተኒ ሲጫወቱ ፎቶ መነሳት! ማንሳት! ማሰራጨት!! አንዳንዴ የተቀባዩን ልብ በሚነካ መልኩ እሱንም አብረው ያስነሱታል— እነሱ እየሰጡ እሱ እየተቀበለ!!
እናቱን ሲዘይርም የተለመደው ካሜራ ፊት ለፊቱ ይደቀንና የተለመደውን ስራ ይሰራል! ዳዕዋም ላይ እንደዚሁ!!
ከዛም የናቱን ሐቅ የሚወጣ ጀግና! ቸር ፣ አዛኝ፣ "የገባውና ፈታ ያለ" ዳዒ ይባላል!
እንዲህ አይነቱ ስም በአፍንጫ ይውጣ!!

በመጨረሻማ፣ ያለ አቅማቸው ያለ እውቀታቸው "ተሰቅለው" ቀሩ!! ያለ ብቃት መሪ ሆነው ተሾሙ! በድፍረት በየ ርእሱ በማን አለብኝነት መዘባረቅን መንገዳቸው አድርገው ያዙ!! "አናውቅም " ለነሱ ባእድ ሆነ! ከሱም ጋር ተኮራረፉ! ያሻቸውን እንዳሻቸው ደሰኮሩ! ምስኪኑም በጭፍን ይከተላቸው ያዘ!! ተጎድተው ጎዱ!!
ከዛማ፣ የተጎዳን ሲረዳ ፣ በሽታን ሲጠይቅ ፣ እናቱን ሲዘይር ፎቶ የማይነሳውን ሁሉ ተከታዮቻቸው " አንተ ደግሞ ምን ሰርተህ ነው?!! " ይሉ ጀመር ተከታዮቻቸው። ፎቶ መነሳት ለመልካም ስራዎች መስፈርት እስኪመስል ድረስ ነገሩን አጦዙት ። ያሳዝናል ።
በ Muhammedsirage MuhammedNur Gidey

*******************************
በ Ibnu Munewor ሰው መስጠት እንዲለምድ እየሰጡ ፎቶ መነሳት፣ ሰው መዝለል እንዲለምድ እየዘለሉ ፎቶ መነሳት፣ ሰው እናቱን ማክበር እንዲለምድ እግር እየሳሙ ፎቶ መነሳት፣ ሰው ሐጅና ዑምራ እንዲለምድ የኢሕራም ልብስ ለብሶ ከዕባ አጠገብ ፎቶ መነሳት፣ ሰው ዱዓ እንዲለምድ እጆቹን አንስቶ ዱዓ እያደረጉ መነሳት፣ ሰው ቀርዷዊን እንዲወድ ከቀርዷዊ ጋር ፎቶ መነሳት፣ ሰው ፈገግታን እንዲለምድ ከካሜራ ፊት ፈገግ ማለት፣ …
ከዚያም ለዚህ ሁሉ "እዩኝ" ለነገሰበት አካሄድ አስፈላጊ ሲሆን ሶደቃን በግልፅ መስራት እንደሚቻል/ እንደሚበልጥ የሚጠቁመውን ማስረጀስ ማጣቀስ። ታወቀና ተሞተ
https://t.me/SadatTextPosts
ወፍ ከአምሳያዎቿ ጋር ታርፋለች (ዘመድ ከዘመዱ .....)

ያሲን ኑሩ ከዚህ ጠሞ አጥማሚ ኢኽዋኒ ዩሱፍ አልቀርዳዊ ጋር ምን ፈልጎ ነው አብሮት ፎቶ የሚነሳው?
ዩሱፍ አልቀርዳዊን ለማታውቁት የሚከተሉት ጥመቶችን የተሸከመ ሰው ነው፡፡

• የኩፍር ንግግሩ፡- የጁምዐ ሁለተኛ ኹጥባ ላይ የሚከተለውን ተናግሯል ‹‹ኹጥባዬን ጨርሼ ከመውረዴ በፊት ትንሽ ስለ እስራኤል ምርጫ መናገር እፈልጋለሁ፡፡ አረቡቹ በጠቅላላ ነዳህ ጲሪዝ ያሸንፋል ብለው ተስፋቸውን ጥለው ነበር፤ ነገር ግን ተሸነፈ፡፡ ከእስራኤል የምንወድላትም ይህንን ነው፡፡ የእኛም ሀገር እነደዚህች አገር እንድትሆን እንመኛለን እንፈልጋለን፡፡ በጥቂት ሰዎች አማካኝነት ሲመራ የነበረው ስልጣኑን አጥቷል፡፡ አገራችን ላይ እንደለመድነው 94% ወይንም 95% (ድምፅ) አይደለም ነገር ግን 99% (አዎን 99%፤ ምንድን ነው ይሄ?) አላህ ለሰው ልጆች እራሱን ተመራጭ አድርጎ ቢያቀርብ ይህንን ያህል ድምፅ አያገኝም ፡፡ይሄ (አረብ አገር ላይ የምናየው ምርጫ) ውሸት ማጭበርበር እና የመሳሰሉት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እስራኤልን እሰየው እንላታለን››፡፡ ምድር በዚህ የኩፍር ንግግር አትሰነጠቅምን? ለሸይኽ ኢሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) ይህ ቃል በድምፅ ተከፍቶላቸው ከሰሙ በኋላ የሚከተለውን ተናገሩ ‹‹በአላህ እጠበቃለሁ፡፡ ይህ ሰው መቶበት ግድ ይለዋል፤ እምቢ ካለ እንደ ሙርተድ (ሀይማኖቱን እንደከዳ ሰው) ይገደል፡፡ ፍጡራንን ከፋጣሪ ስላስበለጠ፡፡ ተውበት ካደረገ አላህ የባሪያውን ወንጀል መሀሪ ነው፤ ካልሆነ ውላቱል አምር (የሙስሊም መንግስት) አንገቱን (በሰይፍ) ይቀንጥሰው፡፡››

• ‹‹ከይሁዳዎችን ጋር የእምነት ጦርነት የለንም የመሬት እንጂ፡፡ ካሃዲያንን ካሃዲያን ስለሆኑ አይደለም የምንዋጋቸው መሪታችንና ቤቶቻችንን ያላግባብ ስለቀሙን እንጂ›› (አራያህ መፅሄት ቁጥር 4696፣ 24 ሸዕባን 1995 ኢ.አ)፡፡ አላህ እና መልክተኛው ምን እንደሚሉ እንስማ፡፡ ይሁዳዎች ከሰዎች ሁሉ ከነሳራም ለአማኞች ጠላትነታቸው የበረታ ነው አለህም እንዲህ ይላል ‹‹ለአማኞች ከጠላትነት በኩል ዩሁዳንና ጣዖታዊያንን ታገኛለህ››ሱረቱል ማኢዳ

• ዘፈንና ሙዚቃን መፍቀዱ፤ እንዲያውም ጥሩ ነገር ነው ማለቱን ‹‹አል ሀራም ወል ሀላል›› ‹‹ፈትዋ ሙዐሲራ›› እና በመሳሰሉ መፀሃፎቹ መግለፁ፡፡ እራሱ እንደተናገረው ‹‹የፋይዛ አህመድ፤ ሻዲያ፤ ኡሙ ኩልሱም፤ ፊሩዝ እና የመሳሰሉትን ሴቶች ዘፈን መከታተል ይወድ እንደነበር ጠቅሷለል›› (አራያህ የሚባል የኳታር መፅሄት ቁጥር 5969 ቀን 19/ ጁማዱል ኡላ 1419 ሂጅሪ)፡፡ ዘፈን ሃራም ለመሆኑ የነብያችን አንድ ሀዲስ ሀቅን ለሚፈልግ ትበቃዋከች ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) ከኔ ኡመት ሰዎች ይመጣሉ ለወንድ ልጅ ሀር ልብስን የሚፈቅዱ፤ መጠጥን እና የሙዚቃ መሳሪያን የሚፈቅዱ›› ኢማሙ ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ የአላህ ባሪያዎች እንደው እናንተው ፍረዱት፡፡

ኡለማዐል ኢስላም ከሰሃባዎች ጀምሮ፤ አቡ ሀኒፋ፤ ኢማሙ ማሊክ፤ ኢማሙ ሻፊዕ፤ ኢማሙ አህመድ፤ ሙሀዲስ ቡኻሪ፤ ሙስሊም ሁሉም በአንድነት ዘፈንን ከልክለዋል፡፡
ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ ‹‹እኛ ጋር ዘፈን የሚያዳምጥ ፋሲቅ ነው›› ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን መስዑድ (አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና) እንዲህ ይላል ‹‹ዘፈን ማዳመጥ በቀልብ ኒፋቅን ያበቅላል ውሃ አዝርትን እንደሚያበቅል ሁሉ›› ፡፡ ቃዲ ኢያድ የተባሉ የማሊክ መዝሃብ ተከታይ ታላቅ አሊም ዘፈን ሀራም ለመሆኑ ኢጅማዕ ጠቅሰዋል፡፡
የሙዚቃ መሳሪያን አስመልክቶ ኢማሙ አህመድና አቡዳውድ የዘገቡት ሰሂህ ሀዲስ እንጨምር፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ‹‹አላህ መጠጥን፤ ቁማርን፤ ከበሮ መምታትን ሀራም አደረገ›› ብለዋል፡፡

• የካቶሊኩ ፓፓስ በሞተ ጊዜ ‹‹አላህ ይማረው ማለቱ››፡፡ አላህ ግን መልክተኛውንም ሆነ አማኞችን ለነዛ በኩፍር ላይ ለሞቱ ሰዎች ምህረትን እንዳይጠይቁ አዟል፡፡

• አረቡ አለም ላይ የተነሳውን የስንት ሙስሊሞች ህይወት የጠፋበትን፣ አገር ጥለው የተሰደዱበትን፣ የጠላት መጫወቻ የሆኑበትን፣ ንብረታቸው የተዘረፈበትን ፈተና ቢንዚል በማርከፍከፍ ፊትና ሲቀሰቅስ የነበረ ሰው ነው፡፡

ዩሱፍ አልቀርዳዊ ይህንን እና ብዙ መሰል ከባባድ ስህተቶች አሉበት፡፡
የዩሱፍ አልቀርዳዊን አጥማሚነት ያላወቃችሁ ወንድም እና እህቶች ተጠንቀቁት፣ ወደ ተውሂድ ሳይሆን ወደ ፖለቲካ እና ወደ ጥመት የሚጣራ የፊትና ሰው ነው፡፡ አላህ ከጠሞ አጥማሚዎች ይጠብቀን፡፡

ያሲን ኑሩ ከዚህ በፊትም እንደተናገርነው ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚጣራ ሰው አይደለም፡፡ ሙስሊሞች ከሱ ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡ ‹‹የተውሂድ አድማስ›› በተሰኘው መፀሀፉም ላይ ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ፣ ሰይድ ቁጡብና ሌሎችም መንገድ የሳቱ ሰዎችን እንደ ጥሩ አድርጎ ለኢትዬጵያ ሙስሊም ያስተዋወቀ ሰው ነው፡፡ ያሲን ኑሩና ጓደኞቹ ያሉበትን የተሳሳተ መንገድ ትተው ወደ አላህ ተመልሰው የጥንት የጠዋቷን መንገድ መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ እስኪሆን ድረስ ግን የኢትዬጵያ ሙስሊም ከነሱ እራሱን፣ ቤተሰቦቹን ያስጠነቅቅ ዘንድ እመክራለሁ፡፡ እንደሜታወቀው ሃቅ በሰዎች አይለካም፣ ሰዎች በሃቅ ይለካሉ እንጂ፡፡

እዚህ ጋር አንዳንድ ወንድሞች የዩሱፍ አል-ቀርዳዊን ስሀተት ተረድተናል ግን ለያሲን ኑሩ ለምን በድብቅ አትመክረውም ይሉ ይሆናል፡፡ መልሱም እሱ ይህን ፎቶ እንደትልቅ ነገር ሲነሳ ከዚህ ጠሞ አጥማሚ ጋር ብሎም ለኢትዬጵያ ሙስሊም በገሃድ እያስተዋወቀው ይህን ግለሰብ እኔ ለምንድን ነው በድብቅ የምመክረው?
እንዲህ በአደባባይ የወጣን ጥመት ማጋለጥ ላይ ሰውየውን በድብቅ መምከር የሚባል መስፈርት የለም፡፡
ያሲን ኑሩ የዩሱፍ አል-ቀርዳዊ ስህተቶች ተዘርዝረውለት ሲያበቁ በአደባባይ ሚድያን ተጠቅሞ ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ ጥመት ላይ እንደሆነ እና እሱም ቀርዳዊን ለኢትዬጵያ ሙስሊም በማስተዋወቁ ለአላህ ተውበት በማድረግ ለህዝቡ ደግሞ ከስህተቱ በመመለስ ሃቁን ግልፅ ሊያደርግ ግድ ይለዋል፡፡ ይህን ሳያደርግ ለቀርዳዊ ወግኖ ጥፋቱን ሸፍኖለት አስተዋውቀዋለሁ ቢል ከራሱ ጀምሮ ባጠመማቸው ሰዎች ልክ ወንጀሉን ይሸከማል፡፡

እኛ ደግሞ እውነት እራሳችንንና ኡማውን ከጥመት ለመጠበቅ ከሆነ ወደ ጥመት የሚጣሩ ሰዎች መጋለጣቸው ሊያሳስበን አይገባም፡፡ እኛ ዘንድ ከምንምና ከማንም በላይ ተወዳጅ ሊሆን የሚገባው ሃቅ ነው፡፡

አላህ ሆይ ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንከተለውም አድርገን፣ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብየት ሁሉ መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
1) ቀርዳዊ ሙዚቃን ሀላል ያደረገበት ።

https://youtu.be/UnOaiYvKv3s

https://youtu.be/F91XFPHnCLg

2) ቀርዳዊ ሴት መጨበጥን ሀላል ያደረገበት

https://youtu.be/0OW4Y5UXRXs

3) ሪባን ( ወለድን ) ሀላል ያደረገበት

https://youtu.be/sfn5GiZ9s8E

4) ሂጃብ ማውለቅን የፈቀደበት

https://youtu.be/0Y5sJ6HfAWo

5) ከሸሪአ ህግ ይልቅ የፖለቲካ ህግ ይሻላል ብሎ የከፈረበት ንግግር

https://youtu.be/jM01nmeoc6I

6) አላህን የተሳደበበትና ኡለማዎች የፈረዱበት ፍርድ

https://youtu.be/Q6jKlgiOpPM

7) የአለማችን ስመ ጥርና ታላላቅ ኡለማዎች ከቀርዳዊ ያስጠነቀቁበት ሙሉ ዝርዝር መረጃ ።
አላህ እንዲህ ይላል

قُلِ ٱللَّهُمَّ مَٰلِكَ ٱلْمُلْكِ تُؤْتِى ٱلْمُلْكَ مَن تَشَآءُ وَتَنزِعُ ٱلْمُلْكَ مِمَّن تَشَآءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَآءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَآءُ ۖ بِيَدِكَ ٱلْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ
(ሙሐመድ ሆይ!) በል፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ (በችሎታህ) ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡»
https://t.me/SadatTextPosts
“ፌስቡክ ላይ ተቀምጣችሁ ሺርክ ሺርክ አትበሉ፡፡”
“ሺርክን ክፍለ ሀገር ገብታችሁ አስተምሩ፡፡”
“ሺርክ የሚሰሩ ሰዎች ፌስቡክ አይጠቀሙም ክፍለ ሀገር ነው ያሉት፡፡” ይሉናል፡፡

ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ብቸኛ ለሆነው እና አጋር ለሌለው ለአላህ ይገባው፡፡ የአላህ ሰላትና እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ተውሒድን ባስተማሩ ሺርክን ባጋለጡ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

ስለ ሺርክ በፌስ ቡክ ሲለቀቅ፣ እነ አቡበክር አሕመድ፣ እነ ያሲን ኑሩ እና ጓደኞቻቸው ሺርክ ያለበት ሀገር ላይ ተቀምጠን ሌላ አርእስት ውስጥ አይግቡ፣ የአላህን አማና ይወጡ፡፡ እንደነ አፍሪካ ቲቪ አይነት አሉ የሚባሉ ሚድያዎቻቸው ላይ የሺርክን አስከፊነት በዝርዝር እና ሀገራችን ላይ የሚሰራውን ሺርክ በማስረጃ ይናገሩ ሲባል የሚከተሉትን አሉባልታዎች ተከታዬቻቸው ያሰማሉ

- “ፌስቡክ ላይ ተቀምጣችሁ ሺርክ ሺርክ አትበሉ፡፡”
- “ሺርክን ክፍለ ሀገር ገብታችሁ አስተምሩ፡፡”
- “ሺርክ የሚሰሩ ሰዎች ፌስቡክ አይጠቀሙም ክፍለ ሀገር ነው ያሉት፡፡” ይሉናል፡፡

በአላህ ፍቃድ እኛም እንዲህ እንላለን፡፡ እናመሰግናችኋለን ሺርክ ሀገራችን ላይ እንዳለ ስላመናችሁልን፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሺርክን ከመዋጋት በፊት ወደ ሌላ አርእስት ገብተው ነበር ወይ?
መልሱም በፍፁም አልነበረም፡፡
ታድያ የሁላችንም አርአያ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ናቸው “ፊዳከ አቢ ወኡሚ” የምንል ከሆነ እነ አቡበክር አሕመድ ለምን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በሄዱበት መንገድ አይሄዱም?
- ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በላይ አውቀው ነውን?
- ወይንስ ከሳቸው በላይ ለኡማው አሳቢ፣ አዛኝ ሆነው ነውን?
መልሱም ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በላይ አዋቂ፣ አዛኝ፣ አሳቢም አይደሉም፡፡ መልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መቃረን እንዲያውም ሁለት ሀገር ለክስረት ይዳርጋል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ ٱلْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِۦ جَهَنَّمَ ۖ وَسَآءَتْ مَصِيرًا
ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች!
ስለዚህ አቡበክርም ይሁን ጓደኞቹ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሄዱበትን መንገድ ተቃርነው ኡማውን ወደ ሌላ መንገድ እየመሩና ለክስረት እየዳረጉት ነው፡፡
እኛን “ለምን ገጠር ሄዳችሁ ለገጠሩ ህዝብ ስለ ሸርክ አስከፊነት አትናገሩም? እዚህ ፌስቡክ ላይ ሺርክ ሺርክ አትበሉን” ለሚሉን ጥቂት ልበላቸው
1) በአላህ ፍቃድ እና እገዛ አብዛኛው ተቀድቶ እየተላለፈላችሁ ያሉት ሙሀደራዎች ክፍለ ሀገር ላይ የተቀዱ ናቸው፡፡ ግን ክፍለ ሀገር መሄዳችንን መኪና ውስጥ ስንገባ፣ መንገድ ላይ ተሰባስበን፣ ዳእዋ ስናደርግ፣ እዛ አካባቢ ላሉ የገጠር ነዋሪዎች ኪታቦች ስናከፋፍል ፎቶ ተነስተን ለማስረጃ እና እናንተ እንድታዩ መልቀቅ አይጠበቅብንም፡፡ ምክንያቱም ሂሳብ ከፋዩ አላህ እንጂ እናንተ አይደላችሁም፡፡
2) በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ክፍለ ሀገር ያሉ ሰዎች ሁሉ ኢንተርኔት ተጠቅመው፣ በሜሞሪ፣ በሲዲ የተላለፉ መልክቶችን ሁሉ እየተጠቀሙና ለሌሎችም እየሰጡ ብዙ ሰው በአላህ እዝነት ከተውሒድ ዳእዋ ተጠቃሚ ሆኖዋል፡፡
3) ደግሞ ሺርክን ለገጠር ሰው ብቻ ያደረገው ማን ነው?
- ይሀው ከተማችን ላይ በየጠንቋይ ቤቱ ህዝቡ ይመላለስ የለ ወይ?
- ሴት እህቶቻችን ላይ ድግምት የሚያሰሩባቸው እነማን ናቸው?
- አንድ አንዱ ላይ ድግምት የሚያሰራው እዚሁ አዲስ አበባ ላይ አይደለምን?
- ጉዞ ወደ አብሬት፣ ወደ ቃጥባሬ፣ ወደ አልከሶ፣ ወደ ዳና፣ ወደ ዳንግላ እየተባለ የሚኬደው ከዚሁ ከአዲስ አበባ አይደለምን?
- ጉለሌ እስላም መቃብር ላይ ትልልቅ ቀብሮች ተገንብተው፣ በል እንዲያውም “ሸህ ሀሰን በቱል” የሚባል እላዩ ላይ ሚናራ የተሰራበት ቀብር አዲስ አበባ ጉለሌ እስላም መቃብር ላይ አይደለምን?
- አዲስ አበባ ውስጥ ነው አይደለም ቀን ለይተው ከቤት አንወጣም የሚሉ ሰዎች ያሉት?
- አዲስ አበባ ውስጥ ነው አይደለም በየዶሮ ተራው፣ በግ ተራው፣ እጣን ተራው ስንቶች ለየት ያለ ከለር ለሰይጣን ለመገበር ሲሉ በብዙ ብር እንስሳ ገዝተው የሚሰዉት?
- እዚሁ አዲስ አበባ ላይ ነው አይደለም ታምራት ጠንቋዩ ቤት ሲመላለሱ ከነበሩት ውስጥ ኒቃብ የለበሰች ሴት ሁሉ የታየችው?

ስለዚህ የማይሆን ወቀሳ አታንሱ፡፡ ይልቁንስ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ፈለግ የተቃረኑትን ኡስታዞቻችሁን አላህን ፈርተው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከምንም በፊት ያስቀደሙትን አርእስት እንዲያስቀድሙ ንገሯቸው፡፡
ቅድሚያ ለተውሒድ?
በጣም የሚገርመው በዚሁ በፌስ ቡክ ስለ ሰላማዊ ሰልፍ ስለ ሌላ አርእስቶች ሲለቀቅ “በክልል ከተሞች” ሁሉ እየተባለ አልነበረምን?
ምነው ታድያ ለፖለቲካ ሲሆን ከተማ ገጠሩን በኢንተርኔት ያዳረሰው የናንተ ዳእዋ ተውሒድን (የአላህን መብት) አብራርቶ መናገር ላይ ትንፋሽ ያጠረው?
ችግር ስላለባችሁ ነው ወይንስ አይደለም?
የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) አስተምህሮት ስለምትቃረኑ ነው ወይንስ አይደለም?
ዛሬ ወደድነውም ጠላነውም እኛ ከተማ ገብተን ብንኖርም፣ መሰረታችን ቤተሰቦቻችን ከገጠር ነው የመጡት፡፡ አሁንም ድረስ አብዛኛው ቤተሰብ ገጠር ነው የሚኖረው፡፡ ገጠር ላይ ሺርክ እንዳለ ካመናችሁ፡፡ ሺርክ (በአላህ ላይ እያጋራ) የሞተ ሰው ደግሞ አላህ በእርሱ ላይ ጀነትን እርም አድርጎበት፣ ዘላለም መኖሪያው እሳት ሆኖ ሳለ ለምን የኢስላም አስተማሪ ነን የሚሉት ይህንን አርእስት ዝም ይላሉ?
ጨካኞች አይደሉምን?
መቼም ለቅርብ ቤተሰቦቹ ያልሆነ ለሌላው አይሆንም፡፡ ከራስ በላይ ንፋስ ይላል የሀገሬ ሰው፡፡ ስለዚህ ገጠር መሄዳችንን ፎቶ ተነስተን መልቀቅ የለብንም እና እባካችሁ እንዲህ የወረዱ ጥያቄዎችን አታንሱ፡፡ ሐቁን ብቻ ተቀበሉ፡፡
ኩራተኛ ሰው ማለት ሐቅ ሲነገረው የማይቀበል ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሺርክ እያዩ ዝም አይሉም ነበር፡፡ ቢድኣ እያዩ ያውም የቢድአ ሁሉ ቁንጮ መውሊድን “መውሊድ አይለያየንም” አይሉም ይልቁንስ “አዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ፡፡ ሁሉም መጤ ነገር ቢድአ ነው፡፡ ቢድአ ሁሉ ጥመት ነው፡፡” ነበር ያሉት፡፡
ጥያቄው ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንገድ እና እሳቸውን ከማይከተሉት ሰዎች መንገድ የቱን ትመርጣላችሁ ነው?
አላህን የፈራና ነፍሱን ከእሳት ማውጣት የፈለገ የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንገድ ይመርጣል፡፡
ለነፍሳችን እንዘን የማንም ንግግር ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ንግግር አይቀደምም፡፡
ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ከሰሃባዎችቻው፣ ከሰለፉነ ሷሊሂን መንገድ ውጭ ያለ የትኛውም መንገድ ጥመት ነው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሺርክን እያዩ ዝም አላሉም፣ ወደ ሌላ አርእስትም አልገቡም፡፡ ይሄ ታላቅ ስብእና ማናችንንም ያለንበትን መንገድ መመዘኛ ነው፡፡
አላህ ሆይ! ሐቅን በሐቅነቱ አሳየን የምንከተለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት መደምደሚያ ላይ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በ Ibnu Munewor

ባለመንዙማው ሙሐመድ አወል መንዙማውን ተጠቅሞ እጅግ በርካታ የሽርክ ስንኞች ወደ ህዝብ ያሰረገ የጥፋት ሰው ነው። ከህዝባችን ውስጥ ከፊሉ መልእክቱ ላይ ብዙም ሳያተኩር እንዲሁ ዜማውን የሚያቀነቅን አለ። በአንድ ወቅት አንድ የዚህን ሰውየ መንዙማ የሚያዳምጥን ሰው ካሴቱን እያቆምኩኝ "አንተ በዚህ መልኩ ነው የምታምነው?" ብየ ብጠይቀው "አይደለም" አለኝ። "እናስ ለምን ታዳምጣለህ?" ስለው "እኛኮ ዜማው ላይ እንጂ ብዙም ወደ ወደ ውስጥ ገብተን አናስተውለውም" ብሎኛል።
የሆነ ሆኖ የሰውየው ስራዎች ሲበዛ አውዳሚ ናቸው። በዚያ ላይ ልክ እንደ አሕባሾቹ "አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን" እያለ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን የሚያስተባብልበት ስንኝ አለው። አንዳንዱ ግን ማስተዋል ያቅተዋል። አሕባሽን ተቃውሞ እንዳልጮኸ ቀዳሚውን የአሕባሽ ጥፋት ሌሎች ሲፈፅሙት ግን አይሞቀው፣ አይበርደው። ይሄ በራስ አቋም ሳይዙ ሌሎችን ተከትሎ መንፈስ ያመጣው ጣጣ ነው።
መጪው ረመዳን ስለሆነ የጥፋት ሰዎች ከያቅጣጫው ወከባ ያበዛሉ። ስለዚህ ቤተሰቦቻችንን፣ ወገናችንን፣ በቅድሚያም እራሳችንን ልናተርፍ ይገባል።
ወንድሜ! አላህን ፍራ! እህቴ ሆይ! አላህን ፍሪ!! ህይወት ማለት የዱንያ ህይወት ማለት አይደለም፡፡ ይቺማ ጤዛ እኮ ናት፡፡ ይልቅ ነብዩ ﷺ ምን እንደሚሉ ተመልከት፡- “አንድ ሰው የሚያገኘው ገንዘብ ከሐላል ይሁን ከሐራም ደንታ የማይኖርበት ዘመን በሰዎች ላይ ይመጣል፡፡” [ቡኻሪ፡ 2059] ልብህ ካልሞተ ይሄ አስፈሪ መልእክት አለው፡፡ ሰው እንዴት እራሱን የቂያማ ምልክት ያደርጋል? ፍጥጥ ባለ መልኩ ሐራም ላይ መግባት ሲኖርስ? ያውም በአራጣ? አላህ ለሸሪዐዊ ትእዛዝ እጅ የምንሰጥ፣ ከዱንያ ይልቅ ኣኺራን የምናስቀድም ያድርገን፡፡ ኣሚን፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 23/2010)
የወለድ አደጋዎች
ዘመናችን በርካታ የቂያማ ምልክቶች የሚታዩበት አስፈሪ ዘመን ነው፡፡ ከነዚህ ምልክቶች ውስጥ አንዱ የወለድ መንሰራፋት ነው፡፡ ወለድ በቁርኣን፣ በሐዲሥና በምሁራን ኢጅማዕ የተወገዘ እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው፡፡ ወንጀሉ ምንም እንኳን አደገኛ ቢሆንም ነገር ግን እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ ነው፡፡ ከጥፋቱ መስፋፋት በላይ ይበልጥ የሚደንቀው ግን በተለያዩ ስልቶች ኢስላማዊ ሽፋን ሊሰጡት አጉል የሚባዝኑ ስራዎች ብቅ ብቅ ማለታቸው ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥም አንዱ “የወረቀት ገንዘብ እና ወለድ” በሚል ርእስ በቅርቡ የወጣው መፅሐፍ ነው፡፡ ፀሐፊው ጥራዝ ነጠቅ ብቻ ሳይሆን ሲበዛ ደፋር ነው፡፡ ስለ መፅሐፉ በሌላ ጊዜ እመለሳለሁ፣ ኢንሻአላህ፡፡ ላሁን የወለድን አስከፊነት የሚያሳዩ ማስረጃዎችን እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ፡፡
1. ወለድ ከሰባት ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ” ይላሉ፡፡ “ምን ምን ናቸው እነሱ?” ሲባሉ፡-
((الشرك بالله، والسحر، وقتل النفس التي حرّم اللَّهُ إلا بالحق، وأكل الربا، وأكل مال اليتيم، والتّولّي يوم الزّحف، وقذف المحصنات الغافلات المؤمنات))
“በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ ጥብቅ ያደረጋት ነፍስ መግደል - በሐቅ ካልሆነ በስተቀር፣ ወለድን መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ በጦርነት ጊዜ መሸሽ፣ ጥብቅና (ከጥፋት) የዘነጉ አማኝ ሴቶችን በዝሙት መወንጀል፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ወለድ ከምን አይነት ወንጀሎች ጋር እንደተቆጠረ ተመልከት፡፡
2. ወለድ እንኳን ለአኺራ ለዱንያም አይጠቅምም፡፡ ይሄውና አላህ ምን እንደሚል፡-
{يَمْحَقُ اللَّهُ الرِّبا وَيُرْبِي الصَّدَقَاتِ }
“አላህ አራጣን ያጠፋል፡፡ ምፅዋቶችንም ያስፋፋል፡፡” [በቀራህ፡ 276]
በየገጠሩ ገበሬውን ባዶውን ያስቀሩት የቁጠባ ተቋማት ናቸው፡፡ ወለድ የገባው ሁሉ እንስሶቹ እያለቁ፣ ሰብሉ እየጠፋ፣ ንግዱ እየከሰረ መቀመቅ የገባው እጅግ በርካታ ህዝብ ነው፡፡ ወላሂ በአራቱም የሃገሪቱ አቅጣጫዎች የወጣ ከዚህ ጋር የተያያዘ ብዙ ለቅሶ ይሰማል፡፡ መሬት ላይ ያለው እውነት በኢቲቪ እንደሚደሰኮረው አይደለም፡፡ ነብዩ ﷺ “አንድ ሰው ከወለድ አያበዛም ፍፃሜው መመናመን ቢሆን እንጂ” ይላሉ፡፡ [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 5/120]
3. ያለ አስገዳጅ ሁኔታ ከወለድ ጋር የሚነካካ በሁሉም አቅጣጫ የተረገመ ነው፡፡ ሶሐባው ጃቢር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡-
((لعن رسول الله - صلى الله عليه وسلم -: آكل الربا، وموكله، وكاتبه، وشاهديه))، وقال: ((هم سواء))
“የአላህ መልእክተኛ ﷺ ወለድ የሚበላንም፣ የሚያበላውንም፣ ፀሐፊውንም፣ ምስክሮቹንም ተራግመዋል፡፡ ‘ሁሉም በወንጀሉ እኩል ናቸው!!’ ብለዋል፡፡” [ሙስሊም፡ 1598]
“እኔ ቢቸግረኝ ወሰድኩ እንጂ አራጣ አበዳሪ አይደለሁም” ብለህ እንዳትሸወድ፡፡ ያለፈውን ሐዲሥ ተመልከት፡፡ በተጨማሪም ነብዩ ﷺ “ወሳጅም ሰጪም እኩል ናቸው” ማለታቸውን ያዝ፡፡ [ሙስሊም፡ 1584] ስለዚህ ሙስሊም የሆነ ሰው ሌላው ቀርቶ በወለድ ተቋማት ውስጥ ጥበቃና ፅዳት እንኳን ሊሰራ አይገባውም፡፡
4. ወለድ ውስጥ የገባ ሰው ከአላህ ጋር ጦርነት ውስጥ ነው የገባው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
{يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَذَرُوا مَا بَقِيَ مِنَ الرِّبا إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ * فَإِنْ لَمْ تَفْعَلُوا فَأْذَنُوا بِحَرْبٍ مِنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ}
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ከአራጣም የቀረውን ተዉ፡፡ አማኞች እንደሆናችሁ (ተጠንቀቁ፡፡) (የታዘዛችሁትን) ባትሰሩም ከአላህና ከመልእክተኛው በሆነች ጦር (መወጋታችሁን) እወቁ፡፡” [አልበቀራ፡ 278-279]
ይቺ በነብዩ ﷺ ላይ መጨረሻ ላይ የወረደች አንቀፅ ነች ይላሉ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ፡፡ [ቡኻሪ፡ 2086]
5. ወለድ የሚበላ ሰው ከቀብር የሚነሳው ልክ በጂን እንደተለከፈ ሰው እየተሳከረ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
{الَّذِينَ يَأْكُلُونَ الرِّبَا لا يَقُومُونَ إِلَّا كَمَا يَقُومُ الَّذِي يَتَخَبَّطُهُ الشَّيْطَانُ مِنَ الْمَسِّ}
“እነዚያ አራጣን የሚበሉ ያ ሰይጣን ከመንካቱ የተነሳ የሚጥለው ሰው (ከአውድቁ) እንደሚነሳ ብጤ እንጂ (ከመቃብራቸው) አይነሱም፡፡” [አልበቀራ፡ 275]
6. ወለድ ምህረት የለሸ ወንጀል ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ምህረት ከማያገኙ ወንጀሎች ተጠንቀቅ፡፡ … ወለድን መብላት፡፡ ወለድን የበላ ሰው በቂያማ ቀን ሸይጧን የሚጥለው እብድ ሆኖ ነው የሚነሳው” ካሉ በኋላ የላይኛውን አንቀፅ አነበቡ፡፡ ስለዚህ ትክክለኛ ተውበት ካልኖነ ጥፋቱ አደገኛ ነው፡፡
7. ወለድ የከሃዲዎቹ አይሁዳውያን ተግባር ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
{وَأَخْذِهِمُ الرِّبا وَقَدْ نُهُوا عَنْهُ وَأَكْلِهِمْ أَمْوَالَ النَّاسِ بِالْبَاطِلِ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ مِنْهُمْ عَذَاباً أَلِيماً}
“ከርሱ በቁርጥ የተከለከሉ ሲሆኑ አራጣንም በመያዛቸውና የሰዎችን ገንዘቦች ያለ አግባብ በመብላታቸውም ሳቢያ (የተፈቀደላቸውን እርም አደረግንባቸው፡፡) ከነሱም ለከሃዲዎቹ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጀን፡፡” [አንኒሳእ፡ 161]
8. የወለድ መብዛት የቂያማ ምልክት ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ቂያማ ሲቃረብ ወለድ፣ ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ይበዛል” ይላሉ፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 1861]
9. ወለድ የሚበላ ሰው አሰቃቂ ስቃይ አለበት፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡-
“ዛሬ ሌሊት ሁለት ሰዎችን አየሁኝ፡፡ ወደተቀደሰች ምድርም ይዘውኝ ወጡ፡፡ ደም የሚጎርፍበት ወንዝ እስከምንደርስም ተጓዝን፡፡ በውስጡ አንድ የቆመ ሰው አለ፡፡ ከወንዙ ዳርቻ አንድ ሰው አለ፡፡ ከፊት ለፊቱ ድንጋዮች አሉ፡፡ ወንዙ ውስጥ ያለው ሰውየ ሊወጣ ሲያመራ ዳር ላይ ያለው ሰውየ አፍ አፉን በድንጋይ እየመታ ወደነበረበት ይመልሰዋል፡፡ ሊወጣ በሞከረ ቁጥር ድንጋይ እየወረወረ አፍ አፉን ይመታዋል፡፡ ከዚያም ወደነበረበት ይመለሳል፡፡ ‘ማነው ይሄ ወንዙ ውስጥ ያየሁት?’ ስል ‘ወለድ የሚበላ ነው’ ይለኛል፡፡” [ቡኻሪ፡ 2085]
10. ወለድ ከምናስበው በላይ እጅግ የገዘፈ ወንጀል ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ወለድ ሰባ ሶስት አይነት ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ቀላሉ አንድ ሰው እናቱ ላይ ዝሙት እንደመስራት ነው” ይላሉ፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 1851]
11. የወለድ መብዛት በምድር ላይ የአላህን ቅጣት ያስከትላል፡፡ ነብዩ ﷺ “ዝሙትና ወለድ በአንድ ሃገር ላይ ከበዛ በራሳቸው ላይ የአላህን ቅጣት አስወስነዋል” ይላሉ፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 1859]
የሽንት ቤት አጠቃቀም ስነ ስርኣት

ፅሑፉን ለማሳጠር ስል በእያንዳንዱ ነጥብ ስር ያሉትን ማስረጃዎች አልጠቀስኩም። ሆኖም ግን ማስረጃዎቹ የሚገኙበትን ምንጭ ስለጠቀስኩ ያስፈለገው በቁጥሩ ማግኘት ይችላል።

① እንዳይሰረቁ ወይም እንዳይጠፋ ካልሰጉ በስተቀር የአላህ ስም ያለበት ነገር ይዞ ሽንት ቤት ውስጥ አለመግባት።
② የሚፀዳዱት ሜዳ ላይ ከሆነ ከሰው እይታ ራቅ/ ሰወር ማለት። [ሶሒሕ ኢብኑ ማጃህ: 1/ 60]
③ በሰው መተላለፊያ መንገድ ላይ ወይ አጠገብ፣ ሰዎች ከሚጠለሉበት ዛፍ ስር፣ ፍሬው ከሚበላ ዛፍ ስር፣ የፍራፍሬ ዛፍና አትክልቶች አጠገብ፣ ወራጅ ባልሆነ ውሃ ላይ፣ የውሃ ምንጭ ላይ፣ በሙስሊሞች መቃብር ውስጥ አለመፀዳዳት። [ኢርዋኡል ገሊል: 1/100] [ሙስሊም: 269፣ 281] [ኢርዋእ: 1/102]
④ ንፋስ ወደሚነፍስበት አቅጣጫ ዙሮ አለመፀዳዳት፣ ይህን ትኩረት መስጠት ለጤናም፣ ለንፅህናም የተሻለ ነው።
⑤ የተሰነጠቀ መሬት ላይ ወይም ቀዳዳዎች ላይ አለመፀዳዳት። [አቡ ዳውድ: 29]
⑥ ውጭ ላይ የሚፀዳዱ ከሆነ ወደ መሬት ዝቅ እስከሚሉ ልብስን አለመሰብሰብ ወይም አለማውረድ። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 4652]
⑦ ውጭ ላይ በሚፀዳዱ ጊዜ ወደ ቂብላ አለመዞር፣ ጀርባንም ለቂብላ አለመስጠት። ሽንት ቤት ውስጥ ከሆነ ወይም ከፊት የሚጋርድ (ግድግዳና መሰል) ነገር ከኖረ ችግር የለውም። ይህንንም ቢሆን ከተቻለ መጠንቀቅ። [ቡኻሪና ሙስሊም] [ኢርዋእ: ቁ· 61]
⑧ ሽንት ቤት ሲገቡ ግራ እግርን ማስቀደም፣
⑨ ሽንት ቤት ሲገቡ "ቢስሚላህ። አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹቡሢ ወልኸባኢሥ" ብሎ ከሸይጧን መጠበቂያ ዱዓ ማድረግ። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 3611] [ቡኻሪና ሙስሊም]
(10) በሚፀዳዱ ጊዜ ብልትን በቀኝ እጅ አለመንካት፣ በቀኝ እጅ አለመፀዳዳት፣ [ቡኻሪና ሙስሊም]
(11) በሚፀዳዱበት ጊዜ በተቻለ መጠን ከማውራት መቆጠብ። [ሙስሊም: 370]
(12) ቢያንስ በሶስት ድንጋይ፣ ሶፍት፣ ወረቀትና መሰል ነገር መፀዳዳት። አንድም ቢሆን ሶስት የተለያዩ ጎኖች ወይም ገፆች ከኖሩትም በቂ ሊሆን ይችላል። ወይም በውሃ መጠቀም። አጥንት፣ ፋንዲያ፣ ምግብ ነክ ነገር እና ንፁህ ያልሆነ ነገር ለመፀዳጃነት አይውልም። [ሙስሊም: 262፣ 263፣ 271]
(12) ከሽንት ቤት ሲወጡ ቀኝ እግርን አስቀድሞ መውጣት።
(13) ከሽንት ቤት ሲወጡ "ጉፍራነክ" ማለት። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 4707]

(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 23/2010)
የሴቶችን ድንግልና የሚወስደው ማን ነው?
ይህን ፅሁፍ ለማዘጋጀት ያነሳሳኝ አብዛኛውን ጊዜ አንዳንድ ወደ እስልምና እንጣራለን የሚሉ ሰዎች ህግጋቱን ሁሉ ሴቶች ላይ ጫን አድርገው ወንዶችን ብዙም ሲሉ አይሰማም፡፡
ሰሞኑን አላዋቂዎች ብዙ ሲሳለቁ እና እራሳቸውንም መግለጫ ሰጪ አድርገው ሲያዩ ተመልክተናል፡፡ የሴት ልጅ ድንግልና በብዙ መንገድ ይሄዳል፡፡ ለምሳሌ ሴት ልጆችን በገዛ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው በመደፈር ሁሉ ያጡታል፡፡ ሴት ልጆች ሲደፈሩ ያውም ደፋሪያቸው እየታወቀ “በቃ ዝም በይ” አይነት ማስጠንቀቂያዎች ይሰጧታል፡፡ ድንግልና ያለ ግንኙነትም ሊጠፋ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ዑለማዎችም ሀኪሞችም ይገልፃሉ። ስለዚህ ድንግልና የሌላት ሁሉ ብልግና ፈፅማለች ማለት ዝቅ ሲል አላዋቂነት ከፍ ሲል ብልግና ነው። በሌሎችም መንገዶች ድንግልና ይሄዳል፡፡
አብዛኛዎቹ ሴቶች ልጅ በነበሩበት ሰኣት በጣም አይን አፋር እና ድንጉጥ ናቸው፡፡ ወንድን መቅረብ አይፈልጉም፡፡ ሴቶቹን ወደ መጥፎ ነገር የሚመሩዋቸው መጥፎ ሴት ጓደኞች እና ምላሳም ወንዶች ናቸው፡፡
መቼም ወንድ ከሌለ ሴቶች በራሳቸው ድንግልናቸውን አጠፉት አይባልም፡፡ አንድ ሴት ልጅ ድንግልናዋን ስታጣ እሷን ብቻ ከመውቀስ በምላሱ አታሎ፣ አጭበርብሮ ድንግልናዋን የወሰደባትን ለምን በደንብ አይኮንኑትም?
አስገራሚው ሴት ልጅ ስትሰራ ከነበረችው መጥፎ ነገር ቶብታለች ሲባል “እሷ እኮ…. ነበረች…. መጠንቀቅ ነው …. ምን ይታወቃል” እና የመሳሰለውን ትንኮሳዎች ይተበተባሉ፡፡
ወንድ ልጅ ግን ለምሳሌ አንዴ በድፍረት 21 ወይንም 22 አመት የሚጠጋው ወንድ ለጓደኞቹ “ከ180 እስከ 200 ሴቶች ጋር ግንኙነት ፈፅሚያለሁ” እንዳላቸው ሲናገሩ ሰምቻለሁ (የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የእኔ ኡመቶች ወንጀል ይማራል ግልፅ የሚያወጣው ሲቀር ብለዋል፡፡ ወንጀልን እንደቁም ነገር እና ጀብዱ የምታወሩ ሰዎች አላህን ፍሩ)፡፡ ለምሳሌ ይህን ሁሉ ሴት የነካካ ወንድ ቶብቷል ቢባል “አቤት እሱ እኮ ሷሊህ ነው፡፡ አቤት አኽላቁ፡፡ አቤት እሱን ያገኘች” ተብሎ ይለፈፋል፡፡
ለምን?
አላህ በተከበረው ቁርኣን ላይ
- ዝሙትን በተመለከት ተከልከሉ ሲል ለወንዱም ለሴቱም ነው፡፡
- ዝሙት ከፈፀሙ ያላገቡ ከሆኑ 100 ጅራፉ ይገረፉ ሲል ወንዱንም ሴቷንም ነው፡፡
- ዝሙትን የፈፀሙት ያገቡ ከሆነ በድንጋይ ተቀጥቅጠው ይገደሉ ሲል ወንድንም ሴትንም ነው፡፡
ታድያ ለምን ይሄን ያህል ሁለቱንም የሚመለከተውን ህግ ሴቶች ላይ ብቻ ጫን ማለት አስፈለገ፡፡ እንጨት ለምሳሌ በራሱ አይቀጣጠልም እሳት ሲቀላቀልበት ቢሆን እንጂ፡፡ ስለዚህ ወንድ እና ሴት በፈፀሙት ወንጀል አንዱን ብቻ ጠንከር አድርጎ መውቀሱ በተለይ ከኢስላም ውጭ ያሉ ሰዎች “ኢስላም ሴትን ይበድላል” እንዲሉ የሚያደርጋቸው ይህ ነው፡፡
ፍትሀዊ የሆነ ሀይማኖት ይዘን ፍትህ የሌለ አስመስለን አናቅርበው፡፡ ያለ እውቀት መናገር ሁሌም ጣጣው ከሚታሰበው በላይ ነው፡፡
የቶበቱ ሰዎችን አስመልክቶ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ወደ አላህ የተመለሰ ወንጀል እንደሌለበት ነው፡፡” ብለው ሲያበቁ ወደ አላህ የተመለሱ ሰዎችን እያጣጣሉ መናገር መሀይምነትን በይፋ የሚያሳይ ነው፡፡
አስገራሚው ግልፅ ቢድኣና ሺርክን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የሌላቸውን ጥንካሪ እና ድፍረት ወንጀል ላይ የወደቁት ላይ ሲያደርጉት እንመለከታለን፡፡
ወንጀል በድብቅ የሰራ ሰው አይቡ ይደበቅለታል፡፡ ቢድኣን እና ሺርክን በአደባባይ የሚፈፅም ደግሞ በአደባባይ ሙስሊሞች እንዲጠነቀቁት መልስ ይሰጥበታል ይህ ነው ፍትህ እና ሚዛናዊነት፡፡
ዛሬ የቢድኣ ካዝና ለሆኖ ሰዎች ጥብቅና ቆመው እነሱን አናስነካም፡፡ እነሱን የነካ “አይባቸውን እንዳወጣ ነው” ሲሉ ይቆዩና ተደብቀው ወንጀል የሚሰሩ ሰዎችን “ተከታትለን በካሜራ እናጋልጣለን” ብለው ስሜት አምላኪነታቸውን ያሳዩናል፡፡
እንዲህ አይነት መሀይማን ጉዳታቸው እጅጉን የከፋ ነው፡፡

ፅሁፌን ስጨርስ ሴቶችን እንደነ መርየም ድንግልናችሁን ጠብቁ ስንል፣ ወንዶችንም ልክ እንደነ ኡስማን ኢብን አፋን ሁኑ ከዝሙት ራቁ፡፡ ወንድ እና ሴቶች ሆይ! አላህን ፈርታችሁ ቶሎ ተጋቡ፡፡ በኢስላም ትዳር ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ከትዳር ያለ አስገዳጅ ሀጃ በመዘግየታችሁ ምንም የምትጨምሩት ነገር የለም፡፡ የምታጡት ነገር ቢብስ እንጂ፡፡
ስለ ትዳር የበሰሉ ሃያእ ያላቸውን ታላቆችን አማክሩ፡፡
https://t.me/SadatTextPosts