Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
👆🏻ተውሒድ እና ሺርክ መፅሀፍ በሶፍት ኮፒ
የጥመት ተጣሪዎች እና አላህ የረገመው ዊግ ቀጣይ…
ተመልከቱ አፍሪካ ቲቪ ላይ ከሚቀርቡ በኢስላም ስም ከሚያላግጡ ደፋሮች ውስጥ አላህ የረገመውን ዊግ (አርቴፊሻል ፀጉር) ቀጥሎ ስለ ዲን ላወራ ነው ይላል፡፡
የጥመት ተጣሪዎች ይህን ያህል ደርሰዋል፡፡ ሀሺሽም ሳብ የሚያደርግ እያስመለ፣ አፉንም በጫት ይወጥር አይወጥር አላህ ነው የሚያውቀው በዚህ መንገድ ካላስተማርኩ ይላል፡፡
እስቲ በአላህ ይሁንባችሁ፡፡ ስለ ዝሙት አስከፊነት ለማስተማር ሴትና ወንድ ድራማ ካልሰሩ፣ ካልተሳሳሙ፣ ካልተጨባበጡ ይባላልን?
በፍፁም፡፡
አላህ “ዝሙትን አትቅረቡት ብሏል” ብቻ ብሎ የአላህን ቃል ለሙስሊሞች ማስተማር ከበቂ በላይ ነው፡፡
ዲንን ለማስተማር ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ሰሃባዎችና የነሱን መንገድ የተከተሉ መልካም ሰዎች የሄዱበት መንገድ ብቻ ይበቃል፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የከለከሉትን ፓንክ ተቆርጦ ስለ ዲን ሊያወራ ብቅ ከሚል ደፋር የበለጠ ማን ጋጠወጥ አለ?
አፍሪካ ቲቪ እና አዘጋጆቹ ደጋፊዎቹ እንዲህ አይነት አጥፊዎችን እና ጥመትን እስካስተላለፋችሁ ድረስ ወደዳችሁም ጠላችሁም መልስ ይሰጥባችኋል፡፡
ለአጥፊዎች መልስ መስጠት ለኡማው ከማዘን ነው፡፡ ይሄም በፍፁም ሀሜት አይደለም፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እንዲህ አይነት ጠሞ አጥማሚዎችን አስጠንቅቁ፡፡ ለምን ለብቻው አትመክሩትም ብለው የእንቅልፍ ኪኒን ሊወጓችሁ የሚሞክሩትንም አትስሟቸው፡፡ እሱ በአደባባይ ጥፋቱን እየረጨ እኛ ዝም እንድንለው ወይንም በጓዳ ተው እንድንለው ማሰብ ለሀቅ መቆርቆር አይደለም፡፡ ለሐቅ መቆርቆር በነበር እሱ በአደባባይ ይህን ጥፋት ሲያጠፋ ከፍቷቸው በተቃወሙት ነበር፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በየመስጂዱ ያሉ ኢማሞች ኹጥባቸው ስለ ዘረኝነት አደጋ መሆን አለበት፡፡ ኡለማዎች ዱዐቶች የሀገር ሽማግሌዎች ከምንም በላይ ይህንን የዘረኝነት ሰደድ እሳት ለማጥፋት ከባድ ጥረት ማድረግና አለ በሚባል በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለ ዘረኝነት አስከፊነት ማስተማር አለባቸው፡፡ አለበለዚያ የፍርዱ ቀን ባለቤት እራቁታችንን አድርጎ ሲጠይቀን ከባድ ቅጣትን ይከናነቧታል፡፡ ኡለማና ጃሂል እኩል አይጠየቅም፡፡ ኡለሞችና ዱአቶች ሀላፍትናችሁን ተወጡ፡፡ የአላህን አደራ አትብሉ፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የነብዩ ሀዲስ ለትግሬውም፣ ለአማራውም፣ ለኦሮሞውም፣ ለስልጤመውም፣ ለጉዳጌውም፣ ለወለኔውም፣ ለሀደሬውም በአጠቃላይ ለአጀሙም፣ ለአረቡም፣ ለጂኑም ለሰውም ነው፡፡
የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምክር አንዱን ዘር የለየ አይደለም ለሁላችንም ነው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) መቃረን እና አለመቀበል ከባድ አደጋ አለው፡፡ ጀሀነም እሳት ውስጥ ያስገባል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ ٱلْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِۦ جَهَنَّمَ ۖ وَسَآءَتْ مَصِيرًا
ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች!
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ዘረኝነት ጥምብ ናት ተዋት” ብለዋል ሲባል የነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ንግግር ላለመቀበል “ለእንትን ዘሮች ንገራቸው የሚሉ” ነፍሳቸውን አምላኪ ማየት ልብ ያደማል፡፡
የነብዩ ሀዲስ ለትግሬውም፣ ለአማራውም፣ ለኦሮሞውም፣ ለስልጤመውም፣ ለጉራጌውም፣ ለወለኔውም፣ ለሀደሬውም በአጠቃላይ ለአጀሙም፣ ለአረቡም፣ ለጂኑም ለሰውም ነው፡፡ እሳቸው የተናገሩትን የማይቀበል የሰይጣን ወንድም ነው፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡
በዚህ ዘረኝነት የተነሳ ይሀው ሙስሊም ናቸው የሚባሉ ሰዎች ላኢላሃ ኢለላህ ያሉ ሰዎች እና ንፁሀንን እርስ በእርስ እየተጋደሉ እያየን ነው፡፡ በየመስጂዱ ያሉ ኢማሞች ኹጥባቸው ስለ ዘረኝነት አደጋ መሆን አለበት፡፡ ኡለማዎች ዱዐቶች የሀገር ሽማግሌዎች ከምንም በላይ ይህንን የዘረኝነት ሰደድ እሳት ለማጥፋት ከባድ ጥረት ማድረግና አለ በሚባል በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለ ዘረኝነት አስከፊነት ማስተማር አለባቸው፡፡ አለበለዚያ የፍርዱ ቀን ባለቤት እራቁታችንን አድርጎ ሲጠይቀን ከባድ ቅጣትን ይከናነቧታል፡፡ ኡለማና ጃሂል እኩል አይጠየቅም፡፡ ኡለሞችና ዱአቶች ሀላፍትናችሁን ተወጡ፡፡ የአላህን አደራ አትብሉ፡፡
አሁንም እደግመዋለሁ ማንም ዘር ከማንም ዘር አይበልጥም፡፡ አደለም ሀበሻ ሀበሻን ሊበልጠው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘሮች አረቦች እንኳን ሀበሻን አይበልጡም፡፡ የሰው ልጅ የሚበላለጠው እና የሚለያየው በእምነቱ ነው፡፡
አላህ በሚታመንበት ሁሉ አምነው እሱን ከሚገናኙት ያድርገን፡፡ አላህ ሆይ! ሀገራችን ላይ የመጣው የዘረኝነት ፈተና አንሳልን፡፡ ከዚህ እርኩስ ተግባር ጠብቀን፡፡ የንፁሃንን ደምና ክብር ታደግልን፡፡ አንተም ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ ነህ፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
“የአራዳ ልጅ” ለሚባሉት ዳእዋ ለማድረግ አዲስ አይነት ስልት አያስፈልግም፡፡ ቁርኣን እና ሀዲስን ጠቅሶ ማስተማር ብቻ ከበቂ በላይ ነው፡፡ በአላህ ፍቃድ የተመራ ይመራል፡፡ ሰሃባዎች ከሄዱበት መንገድ ውጭ ያለን መንገድ የሄደ የጥመት መንገድን በእርግጥ ተጉዟል፡፡ የጥፋት መንገድም ተከታዩ የፈለገውን ያህል ቢበዛ ኪሳራን እንጂ ሌላን አያመጣም፡፡ ቁርኣን እና ሀዲስ ያልቀየረውን ድራማ፣ ውሸት፣ ፊልም፣ ፓንክ፣ ቀልድ አይቀይረውም፡፡ ይህ መልክት በእርግጥ ለቁርኣን እና ለሀዲስ እጃቸውን ለሰጡ ህዝቦች መገሰጫ ነው፡፡
ከሰዎች ሁሉ መጥፎ ሰዎች ማለት በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አንደበት ዳእዋ ተደርጎላቸው ያስተባበሉት ናቸው፡፡ ለእኛ ህዝብ ወጣትም ይሁን ሽማግሌ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሀባዎቻቸው ከዛም እነሱን የተከተሉ ያደረጉትን ጥሪ ብቻ ማድረግ ከበቂም በላይ ነው፡፡
ከሐቅ በኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ?
የትኛው ኡለማ ነው የሀሺሽን አደገኝነት ለማስተማር “ዊግ ጭንቅላቱ ላይ ጣል አድርጎ፣ ሀሺሽ መሳይ ነገር እንደሚያጨስ አስመስሎ እየተንገዳገደ” ያስጠነቀቀው?
ኢኽዋነል ሙስሊሚን የተባለው የጥመት ቡድን የዘራቸው መርዞች ይሀው በቅለው አገራችን ላይ እንዲህ ጥመታቸውን ሙስሊሙን ኡማ ሊበርዙበት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ አስገራሚው አህባሽ የሆነ ሰው ይህን ቢሰራው ይሀው ኡመተል ኢስላምን ሊያወድሙት ነው ተብሎ ይጮሃል፡፡ ልክ አህባሽ የሚያጠፋውን ያህል ኢኽዋን ሲያጠፋ ለሀቅ ከለላ መሆን ሲገባቸው አብዛኞች ለኢኽዋን ጠበቃ ቆመው ይንጫጫሉ፡፡ እንዲህ አይነት አጥፊዎችን እዚህ ያደረሷቸው ሰዎችና ቻናሎች ካልቶበቱ የእጃቸውን ሳይቀምሱ አይቀራትም፡፡
እኛ ዘንድ ከማንም በላይ ተወዳጅ ሊሆን የሚገባው ሐቅ ብቻና ብቻ ነው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
በሚናገረው ጉዳይ ላይ ትንሽየ እውቀት እንኳን ባይኖረው በድፍረት የሚናገር አቋሙ ብልሹ የሆነ ሰው መሆኑን ካወቅኩ ቆየሁ ። አቡበክር አህመድ።

سلامة الصدر
የተባለ ሙሃደራውን ባዳመጥኩ ግዜ ግን ሰውየው በእጅጉ የወረደ ደፋር መሆኑን ይበልጥ ተረዳሁ! እዚህ ሙሃደራ ላይ የኡለሞችን ስም ከነኪታቦቻቸው ስም ሰሲያዛባ ከዚህም አልፎ የነብዩን ሐዲስ ባልተዘገበ ለፍዝ እያዛባ ሲያወራ ሰምቼ በእጅጉ ደነገጥኩ— والله በጣም ነበር ያሰደነገጠኝ ( ያንን ያህል የወረደ መሆኑ)
ዛሬ ደሞ በነሺዳ ዙሪያ ላይ ያለውን።ሰምቼ ደመመኝ! ! الله ይምራው ። የሰውየው ሁኔታ አሳዛኝና አሰወደንጋጭ ነው። ደህና አቋም።ያለው አዋቂ አገኘን ብለው የሚጠይቁት ይበልጥ ያሳዝናሉ ።

የዘመናችንን ብልሹ ነሺዳዎች የፈቀደበት ድምፅ ላይ ስለ ታላላቅ ሶሐቦች ምን እንደሚል ተመልከቱ ፣
" ሙዐዝ ፈቂህ ነው ሌላ ቦታ ላይ አናገኘውም
... ኢብኑ መስዑድ ቁርአን ላይ ነው ሌላ ቦታ ለይ አናገኘውም
አብዱላህ ኢብኑ ኡመር ሐዲስ ላይ ነው ሌላ ቦታ ላይ አናገኘውም"።

ምናለ አቡበክር ስላልዳሰስከውና ስለማታወቀው ነገር ባታወራ?! ዝምታ በብዙ መልኩ የተሻለ ነበር ላንተ!! እንዲህ አይነቱን አደብ ያጣ ንግግር በነዚሀ ታላቅ ሶሓቦች ላይ ከምትሰነዝር በርህን ዘግተህ ብታርፍ ይሻልህ ነበር!!!
ቅጥ ያጣ የመሃይም ድፍረት ማለት ይሄ ነው!! እነዚህ ታላላቅ ሶሀቦች አቡበክር በጠቀሰላቸው መልካም ላይ እንጂ ሌሎች ስራዎች አይገኙም ነበር?!! አይታዩም ነበር?!

እኛ ግን የተጠቀሱትን ሶሀቦች በሙሉ ሐዲስ ላይ እናገኛቸዋለን ። ጂሀድ ላይ ፣ ዙህድ ላይ ፣ ፈትዋ ላይ ፣ ማስተማርና ዳዕዋላይ፣ ሌሎችም በርካታ ስራዎች ላይ እናገኛቸዋለን!! የነሱ መልካም ስራ ተቆጥሮ አይዘለቅም!!
አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው!
ነሽዳ በኢስላም እይታ ለ አቡበከር አህመድ የተሰጠ መላሽ mp3
https://goo.gl/51sqWg
#ቅድሚያ ለተውሒድ #

ልጅ ከአባቱ በሂወት እያለ መውረስ ያለበት ኢልምን ነበር አባቱ ሲሞት ሃብትን ነበር
ነገር ግን አሁን የምንሰማው በተቃራኒው ነው>አባት ሲሞት ልጅ አባቴ የሚያርደው በየአመቱ (ለጂን የቢገብረው )እሱ ሲሞት ወደኔ ዞረ በማለት ሺርክን ካባቱ ይወርሳል ወይ ደሞ አባቱ በሂወት እያለ ሰወችን ወደራሱ የሚጣራ ( ጣኦት )ከሆነ አባት ሲሞት ልጅ (የሺርክ አልጋ ወራሽ ) ይሆንና የአባቱን። አልጋ ከነ ሙሪዶቹ ይረከባል ይህ ነው ባገራች የምንሰማው ሰወች ከከተማ ወደገጠር (ሼይኽ ፉላንጋ ) በማለት እያመሩ ሺርክ የለም አትበሉ ።

Hayat bint Nure
https://t.me/SadatTextPosts
ጥቂት ስለሱፍያ ከዓሊሞች አንደበት

① ኢማሙ ማሊክ (179 ሂጅራ):–
"እኛ ዘንድ ሱፍያ የሚባሉ ሰዎች አሉ። በብዛት ይበሉና ከዚያ ያንጎራጉራሉ። ከዚያም ተነስተው ይጨፍራሉ" ሲሏቸው "ህፃናት ናቸው?" ብለው ጠየቁ። "አይደሉም" ሲሏቸው "እብዶች ናቸው?" ብለው ሲጠይቁ "አይደሉም ሸይኾች ናቸው" አሏቸው። "እኔ ከኢስላም ሰዎች ይህን የሚሰራ አንድም አልሰማሁም" አሉ። [ተርቲቡል መዳሪክ: 2/53]
② ኢማሙ አሽሻፍዒይ (204 ሂጅራ):–
"ተሶውፍ የተገነባው ስንፍና ላይ ነው" ይላሉ። [ተልቢሱ ኢብሊስ: 320] በተጨማሪም "አንድ ሰው ጧት ሱፊ ከሆነ ቀትር በሱ ላይ አይደርስም ሞኝ ሆኖ የምታገኘው ቢሆን አንጂ!!" ብለዋል። [መናቂቡ አሽሻፍዒይ: 2/207]
③ ኢብኑ በጥጧህ አልዑክበሪ (387 ሂጅራ):–
"ዘፈንን ማዳመጥ ዑለማዎች የሚጠሉት ግና ቂሎች የሚወዱት ነገር ነው። ይህንን የሚሰሩተደ ሱፍያ የሚባሉ ክፍሎች ናቸው። … የዘቀጡ አላማዎች እና የፈጠራ እምነት በሰለቤቶች ናቸው። … ልጆችን እና ሴቶችን በማሰማት ይዘፍናሉ። ይጮሃሉ፣ ራሳቸውን ስተው ይወድቃሉ፣ የሞቱ መስለው ለሰዎች ይታያሉ። ይህ ሁሉ የሚሆነው ለጌታቸው ካላቸው ብርቱ ወዴታ እና ናፍቆት የተነሳ እንደሆነ ይሞግታሉ። እነዚህ መሀይሞች ከሚሉት ነገር አላህ ከፍ ያለ መላቅን ላቀ።" [ተልቢሱ ኢብሊስ: 211]
④ አልቃዲ አቡ አጥጦይብ አጥጦበሪ (451 ሂጅራ):– "ይህቺ ቡድን (ሱፍያ) ለሙስሊሙ ጀማዐህ ተፃራሪ ነች። ምክንያቱም ዘፈንን ዲንና መቃረቢያ አድርገዋልና።" [አስሰማዕ ሊብኒል ቀይዪም: 262]
⑤ አቡበክር አጥጦርጡሺ (451 ሂጅራ):– "የሱፍያ አካሄድ ቦዘኔነት፣ መሀይምነት እና ጥመት ነው።" [ተፍሲሩል ቁርጡቢ: 11/238]
⑥ ኢብኑ ዐቂል (513 ሂጅራ):– "ሱፍዮች ስራን ያበላሻሉ። የእምነት መሰረቶችን ያናጋሉ። ቦዘኔነትንና ዜማ ማዳመጥን ይወዳሉ።" "በሸሪዐ ላይ እንደ ዒልመል ከላም ሰዎች እና እንደ ሱፍያ ያለ አደጋ የለም።" [ተልቢሱ ኢብሊስ: 375]
⑦ ቁርጡቢ (671 ሂጅራ):– "ሱፍዮች የፈጠሩትን (ዜማ) በተመለከተ በክልክልነቱ ላይ ውዝግብ ከማይነሳባቸው ነገሮች ነው። ነገር ግን ብዙ በጥሩ የሚታሰቡ ሰዎችን ስሜት አሸንፏቸዋል። ብዙዎቹ ላይ የእብዶችና የህፃናት ስራዎች እስከሚታዩባቸውና በተጠናመልኩ እስከሚደንሱ ደርሰዋል። ከዚያም ከፊል ሰዎች መቃረቢያና መልካም ስራ ስራ እስከማድረግ ደረሱ።" [ተፍሲሩል ቁርጡቢ: 14/54]
⑧ ከማሉዲን አልአድፈዊ (748 ሂጅራ):– "ማንቀላፋትና መሀይምነት ሱፍዮች መሀል የተንሰራፋ ነው። አንዳንዶቻቸው ድንቁርናቸው ልክ በማለፉ ግልፅ የሆኑ ህሊናዊ እውነታዎችን ይክዳሉ። ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ባንድ ላይ ሰብስበው ያምናሉ።" [አጥጧሊዑ አስሰዒድ: 133]
By Ibnu Munewor
ዝናብ… ሰላም?
ዝናብ ሲጠፋ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ ከሰማያት በላይ ወዳለው አላህ አንጋጠን እንለምናልን፡፡ እሱም ያዘንብልናል፡፡ ከዝናብ በላይ የሆነው ሰላም ሲጠፋ አላህ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ ነውና ሰላምን እና ፍትህን እንዲያመጣ አላህን እንለምን፡፡ ፈተናን ማንሳት የሚችለው አላህ ብቻ ነው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የመልክተኞች ተዐምር ከአላህ የተሰጠና በእርሱም የተመረጠ ነው፡፡
=====================================
አምልኮ በጠቅላላ የሚገባው ለነብያትም ተዓምራቱን የሰጠው፣ ለወልዬች ከራማውን ለለገሰው የሁሉ ባለቤት ሸሪካ የሌለው አላህ ብቻና ብቻ ነው፡፡

መልክተኞች የተለያየ ታዓምርን በአላህ ፍቃድ ይፈፅማሉ፡፡ ለምሳሌ ነብየላህ ኢሳ (አለይሂ ሰላም) ለምጣምን ማዳኑ፣ የሞተን መቀስቀሱ ይህ ሁሉም በአላህ ፍቃድ ብቻና ብቻ ነው የተከሰተው፡፡ ነብየላህ ሙሳም (አለይሂ ሰላም) ብትራቸው በአላህ ፍቃድ ታዓምር ማሳያ ሆናቸው፡፡ ነብዩ ሙሐመድም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከአላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይህን ዘመን የማያልፍበት ተዓምር ቁርዓን (ፉርቃን) አወረደላቸው፣ ከእጃቸው ውሃ እንዲፈስ አደረገ፣ ጨረቃ እንድትከፈልላቸው አደረገ እና ሌላም ሌላም፡፡

ከዚህ የምንወስደው ታላቅ ትምህርት አለ፡፡ ነብያት በአላህ ፍቃድ እንጂ በራሳቸው ምንም ማድረግ እንደማይችሉ፡፡ ከነብያት ጋር ጭራሽ ሊወዳደር የማይችል አላህ ለወልዬች የሰጠው ከራማ አለ፡፡ የአላህ ወልዬች ማን እንደሆኑ ደግሞ የሚያውቃቸው አላህ ብቻ ነው፡፡ ነብያት ይህን ሁሉ ተዓምራት ከአላህ የተሰጣቸውን በእጃቸው ይዘው ምንም አይነት አምልኮ ለነሱ አይገባቸውም፡፡ ታድያ አንዳንዶች ዘንድ ከራማ አለው ተብሎ ሰዎች በመገመታቸው ብቻ የአላህን መብት አሳልፈው ሲሰጧቸውና አምልኮን ሲፈፅሙላቸው ይታያል፡፡ ይሄ ታላቁ በደል ሸርክ ነው፡፡ አምልኮ በጠቅላላ የሚገባው ለነብያትም ተዓምራቱን የሰጠው፣ ለወልዬች ከራማውን ለለገሰው የሁሉ ባለቤት ሸሪካ የሌለው አላህ ብቻና ብቻ ነው፡፡
ሌላው ለአንዱ መልክተኛ የተሰጠውና የተመረጠለት ታዐምር ለሌላው መልክተኛ ላይሰጥ ይችላል፡፡ አላህ ለእያንዳንዱ መልክተኛ የመረጠለትን ተዓምር ይለግሰዋል፡፡ ለመልክተኞች ከተሰጡ ተዓምሮች ሁሉ በላጭ አላህ ለነብያት ሁሉ መደምደሚያ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያወረደው ቁርዓን ነው፡፡
አላህ የመልክተኞች ተዓምር ከእርሱ የተሰጠ መሆኑን እንዲህ ሲል ይነግረናል
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ وَجَعَلْنَا لَهُمْ أَزْوَٰجًا وَذُرِّيَّةً ۚ وَمَا كَانَ لِرَسُولٍ أَن يَأْتِىَ بِـَٔايَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ ٱللَّهِ ۗ لِكُلِّ أَجَلٍ كِتَابٌ
ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ለእነርሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል፡፡ ለማንኛውም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ ተዓምር ሊያመጣ አይገባውም፡፡ ለጊዜው ሁሉ ጽሑፍ አለው፡፡

አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላን በታላቁ ውድ ነብያችን ላይ ዘመን የማይሽረው ታላቁን ተዓምር ቁርዓንን ስላወረደልን እናመሰግነዋለን፣ ሃቁን የምንጠብቀውም ያድርገን፡፡ የፀጋዎች ሁሉ ሰጪ አላህ ብቻና ብቻ መሆኑን አውቀው አምልኮዋቸውን ለእርሱ ብቻ ከሚያደርጉት በእርሱም ላይ ምንንም ማንንም ከማያጋሩት ባርያዎቹ ያድርገን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም ታላቁ ታዓምር ቁርዓን በወረደባቸው ነብይ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
አሳዛኝ ጉድ፡፡ ከባድ አደጋ፡፡ በገጠር በከተማ፡፡
- 3 ዶሮ ለጂን አርዶ 3 ቀን ከቤት ውስጥ አለመውጣት፣
- ሶስቱ ዶሮዎች ለጂን የሚገበሩት በሶስት የተለያየ ቢላዋ ነው…. በጣም የሚገርመው ለሰይጣን ለመገበር “ቢስሚላህ” ብሎ ቃልቻ ተብየው ያርዳል፣
- ስንፈተ ወሲብ ያለበት ጥቁር ሴት ዶሮ ብልቱ ላይ አሽቶ ከዛም ጭንቅላቱ ላይ ደባብሶ መልቀቅ ይፈውሰዋል፣
- ድቤ እየተደበደበ ሰይጣንን መጥራት፣
- ደግሞ ለሰይጣን የሚታረደውንም ወደ ቂልባ ተዙሮ ነው ይላሉ፣
- ደረሳ ቃልቻ ተብየው ለሰዎች ተወክሎ ለጂን ሲያድር፣
- “ከአላህ ጋር ተጣልተው ነው ይህን ተግባር የሚፈፅሙት” ተብሎ ቃልቻ ተብየው ሲጠየቅ “አዎ” ብሎ መለሰ….
- አገራችን ላይ ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ጂኖች ሰይፉ ጨንገሬ፣ አንበሶ፣ አዳል ሞቴ፣ ዘባዲ……
ባእድ አምልኮ፣ አላህ ከወንጀሎች ሁሉ ታላቁ ወንጀል ነው ያለው፣ ይህን እየሰራ የሞተ ዘላለም የጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪ የሚሆንበት ታላቅ ወንጀል በባህል እና በሌላም ስም ይነሳል፡፡
ይህ ሁሉ የአላህ መብት የሚጣስበት ሀገር ላይ ስለ ፖለቲካና ስለ ሌላ አርእስት መደስኮር የት ያደርሳል?
የአላህ መብት ሳይሟላ የእኛ መብት ይገኛል ብለን እንገምታለን?
አንሳሳት
የአላህን ህግጋት ስንፈፅም አላህም ይረዳናል፡፡
ለዚህ ሲባል ነው ከምንም በፊት ቅድሚያ ለተውሒድ የሚባለው፡፡
የአላህ መብት እየተጣሰ እያየን ስለ እኛ መብት ላንቃችን እስኪቀደድ ብንጮህ ትርፉ ጩሀትና ጉንጭ ማልፋት ነው፡፡ መቼ ይሄ ብቻ አላህ አያያዙ የበረታ ነው፡፡ ቅጣትን ያነባብርልናል፡፡
አላህ ሆይ! የነብያትህን ፈለግ ከሚከተሉት፣ ያንተ መብት ከሚያንገበግባቸው አድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አላህ ታጋሽና ቻይ፣ አያያዙም የበረታ ነው፡፡
ዛሬ አለም ላይ የንፁሀንን ደም የሚያፈሱ ስንቶች ናቸው፡፡ አላህ የፍርዱ ቀን ባለቤት ነው፡፡ አላህ ታግሶም ወቅቱ ሲደርስ “ታላቁ ጌታችሁ እኔ ነኝ” ያለውን፣ በምድር ላይ የተንጠባረረውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውን ያርድ የነበረውን ፊርአውን አይቀጡ ቅጣት እንደቀጣው ሁሉ አነዚህም በዳዮች የፊርአውን እጣ ይገጥማቸዋል፡፡
አላህ ሆይ! በሶሪያና በመላው አለም ላይ በግፈኞች እየተገደሉና እየተበደሉ ያሉትን ሁሉ እርዳቸው፡፡ በዳዮቹንም በፍትህህ ቅጣትን አቅምሳቸው፡፡ ሀይልም ጥበብም ካንተ ውጭ የለምና፡፡
“ኢንተርናሽናሉ ኮሚኒቲ ምንድን ነው የሚጠብቀው?” ብላችሁ የምትጠይቁ እነሱ የራሳቸው ጥቅም እስካልተነካ ድረስ በሚሊዬኖች ቢያልቁ ምንም አያደርጉም፡፡ ይልቁንስ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ የሆነውን ጌታችንን እንለምነው፡፡ ከልባችን ካለቀስን፣ ወደ አላህ ትእዛዛት ከተመለስን፣ ከወንጀሎቻችን ንሰሃ ከገባን መጨረሻው የሚያምረው ለእርሱ መልካም ባሪያዎች ነውና አደራ አደራ ዱኣ ላይ እንበርታ፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ሌላኛው ደባቸው ሲጋለጥ፡፡
አሁንም በስሜ ሌላ ፔጅ ተከፍቶ፣ የኔን ፕሮፋይል ፒክቸር ተጠቅሞ እኔን የማይወክል ፅሁፍ የሚፅፉ ብቅ ብሏል፡፡ የምለው ወደ አላህ እቃረብበታለሁ ብሎ ከሆነ ለምን በስሙ አይፅፍም፣ ምክንያቱም መላኢካዎች ጥሩም ይስራ መጥፎ በስሙ ስለሚመዘግቡ እና አላህም ለዛ ሰው በማንነቱ ነው የሚከፍለው፡፡
መቼም የፈለጉትን ያህል ሴራ ቢያሴሩ አላህ ያለው እንጂ ሌላ አይሆንም፡፡
አላህ ሆይ! ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
By Ibnu Munewor
ግን ለምን ከሳዑዲ እንከላከላለን?
አንዳንዶች ከሳዑዲ የምንከላከለው ሳዑዲንና ችግሮቿን በቅርብ ሆነን ስላላየን ይመስላቸዋል። በመጀመሪያ ሳዑዲ ውስጥ ብዙ ተጨባጭ ችግሮች እንዳሉ በሚገባ እናውቃለን። ስለዚህ "ባታዩ ነው"፣ "ባታውቁ ነው" አይነት ምክንያቶች ውሃ የማያነሱ ከንቱ ሙግቶች እንደሆኑ ይሰመርበት። "እናስ ችግሮች እንዳሉ ካወቃችሁ ለምን ትከላከላላችሁ?" ከተባለ
① ችግሮቻቸው ከሌሎች ሃገራት አንፃር ሲታዩ የቀለሉ ናቸው። ሺርኩ፣ አስካሪ መጠጡ፣ ብልግናው፣… በመንግስት ቁጥጥር የሚደረግበት ሀገር እና በህግ የሚፈቀድበት ሀገር እኩል ነውን?
② ከየትኛውም ሀገርና ቡድን በተለየ ለተውሒድ፣ ለኢስላም ሰፊ ጥረት ያደርጋሉ። ከሃገራቸው አልፈው በመላው አለም ተውሒድን ለማሰራጨት እጅግ ብዙ ገንዘብ ያፈሳሉ። ጠላት ሳይቀር ይህን ተገንዝቦ "የሳዑዲ ፔትሮ ዶላር" እያለ እያላዘነ ነው። ከመላው አለም ወጣቶችን እየተቀበሉ በዩኒቨርሲቲዎቻቸው ያስተምራሉ። ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች፣ ኢስላማዊ ጉዳዮች፣ ደዕዋና ኢርሻድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል ባለስልጣን መስሪያ ቤት፣ የታላላቅ ዑለማዎች ምክር ቤት፣ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ ወዘተ ለኢስላም ምን ያክል ትኩረት እንደሚሰጡ ህያው ምስክር የሆኑ በመንግስት የሚመሩ የሀይማኖት ተቋማት ናቸው። እስኪ በየት ሀገር ነው እንዲህ አይነት ተቋማት ያሉት?
③ ከየትኛውም ሙስሊም ሀገር በበለጠ ከባባድ አደጋ ላይ ለወደቁ ሙስሊም ህዝቦች ከፍተኛውን እርዳታ የምታደርግ በመሆኗ። ለማረጋገጥ ለፍልስጤም፣ ለዒራቅ፣ ለሶሪያ፣ ለየመን፣ ለፓኪስታን፣ ለበርማ ሙስሊሞች ሳዑዲ የረዳችውን ኳታር ወይም ቱርክ ከረዳችው ጋር ያወዳድሩት። ጭራሽ አይቀራረብም።
④ የሙስሊሞችን ጉዳይ በአለም አቀፍ መድረክ ላይ አፅንኦት ሰጥታ ታነሳለች። የፍልስጤም፣ የቁድስ፣ የሶሪያ ጉዳይ ለዚህ ዋቢ መሆን ይችላሉ። "ሀሰት" የሚል ካለ "አላውቅም" ቢል ይሻለዋል። ተዘንባይ ሚዲያዎችን ከተከታተልክ በርግጥም እንደሚገባ አታውቅም።
⑤ ሌላው ከሳዑዲ የምንከላከልበት ምክንያት ሳዑዲን የሚኮንኑት አካላት በራሳቸው ከሳዑዲ የማይሻሉ ወይም ከሳዑዲ ለማይሻሉ ሀገራትና ቡድኖች ጥብቅና የሚቆሙ ናቸው። እስኪ ከሙስሊም ሀገራት ሁሉ የትኛው ነው ለሸሪዐ የቀረበ ድባብ የሚታይበት? ደግሞስ ሳዑዲ ውስጥ የሙዚቃ ድግስ ቀረበ ብሎ መሪዎቹን የሚያብጠለጥል አካል ለምንድን ነው ቀርዷዊን ጨምሮ ብዙ ኢኽዋኖች ሙዚቃን ሲፈቅዱ ዝም የሚለው? ለመሆኑ ሐራምን ከመፈፀምና ሐራምን ሐላል ከማድረግ የቱ ይከፋል? የሳዑዲ መሪ "አጅነቢ ሴት ሲጨብጥ የምታራግቡ ሁሉ ለምንድን ነው ጠበቃ የምትሆኑላቸው መሪዎች ሲፈፅሙት የማታራግቡት? ለምንድን ነው ቀርዷዊ ሴት ሲጨብጥ ዝም የምትሉት? ከዚህም አልፎ መጨበጥ ይቻላል ሲልስ ለምን ዝም ትላላችሁ? እውነት አላማችሁ ዲን ነው ወይስ ቡድናዊ ትርፍ?
⑥ ከፊሎቹ ዘመቻዎች ለኢስላም ወይም ለሳዑዲ ጥላቻ ካላቸው የሚዲያ ተቋማት የሚለቀቁ ሀሰተኛ ውንጀላዎችና ያልተረጋገጡ ዘገባዎች ናቸው። በዚህ ረገድ በሀገሪቱም በመሪዎቹም ላይ የሚነዙ እጅግ በርካታ ውንጀላዎችን ማየት የተለመደ ነው። አብዛኛው ግን ወይ ከማስረጃ የተራቆተ ነው። ወይ ደግሞ ተንሻፎ የቀረበ ነው። ለዚህ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ። "ሳዑዲ ሽብርን ትደግፋለች" ይላሉ። ማስረጃውስ?" ስትሉ "የመስከረም 11ዱን ጥቃት ካደረሱት ውስጥ ከ19ኙ 15ቱ ሳዑዲዎች ናቸው" ይላል። እዩ ይህንን ከማገናዘብ የፀዳ ጭንቅላት! ሀበሾች በሳዑዲ፣ በሱዳን፣ በኢማራት፣ … እየሰረቁ የሚያስቸግሩት የኢትዮጵያ መንግስት ልኳቸው ነው ማለት ነው። የአሜሪካ ወታደሮች ጃፓን ውስጥ አስገድዶ መድፈር የፈፀሙት መንግስታዊ ተልእኮ ተሰጥቷቸው ነው ማለት ነው። የካቶሊክ ቄሶች በተለያዩ አለማት ወንድ ህፃናትን የሚደፍሩት ቫቲካን ልካቸው ነው ማለት ነው። ሳዑዲ ሽብርን የምትደግፍ ከሆነች ለምን የአሸባሪዎች ጥቃት ይደርስባታል? ለምንስ ዑለማዎቿ አሸባሪዎችን በግልፅ ያወግዛሉ? ይልቅ ወደ ሽብር የሚጣሩት እነ ቀርዷዊ ናቸው። አሸባሪዎቹ የኢኽዋን አባል የሆኑት እነ ቢን ላደን ናቸው። ነጋዴዎቹ ግን ቡድናዊ ስሜት ስላወራቸው አይታያቸውም።
⑦ በተጨማሪም ከሳዑዲ የምንከላከለው የሙስሊም መሪዎችን ነውር መዘርዘር ሸሪዐችን ስለማይፈቅደው ነው። ይሄ በሶሒሕ ማስረጃዎች የፀና የሰለፎች አቋም እንጂ የዲን ነጋዴዎች እንደሚገልፁት "የመድኸልያ ፈጠራ" አይደለም። እውነት የመሪዎችን ጥፋቶች ማሰራጨት ይቻላል ብለው ካመኑ ለምን የግብረ ሰዶማውያን መብት በህግ መከበር አለበት የሚለውን፣ ልክ እንደ አሕባሾች የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን የሚያስተባብለውን፣ ዶሪሕ የሚዘይረውን፣ ፍልስጤማውያንን ከሚጨፈጭፈው አይሁድ ጋር ጠንካራ ትብብር የሚያደርገውን ያልፋሉ?
ነጋዴዎቹ ግን በመረጣ የተካኑ ናቸው። ምክንያቱም የሚያስጨንቃቸው ቡድን እንጂ ዲን አይደለምና።
⑧ አንዳንዶቹ ከሌሎች ሃገራት በተለየ ለሳዑዲ ብቻ ሲሆን እንደ ከባድ ጥፋት የሚቆጠሯቸውን ጉዳዮች በኢኽዋኖች ሲፈፀሙ ግን እንደ ኖርማል ነገር ያዩዋቸዋል። ለምሳሌ ቱርክም፣ ኳታርም፣ ሳዑዲም ከአሜሪካ ጋር ጠንካራ ግንኙነት አላቸው። ተለይቶ የሚብጠለጠለው ግን የሳዑዲ ነው። ለምን? ሳዑዲ ከእስራኤል ጋር ኦፊሻል ግንኙነት የላትም። ሌላው ቀርቶ የእስራኤል አውሮፕላን በሳዑዲ አየር ላይ አይበርም። በአንፃሩ ቱርክና እስራኤል ጠንካራ የሆነ የንግድ፣ የዲፕሎማሲ እና የጦር ትብብር አላቸው። ነጋዴዎቹ ግን ስለዚህ ትንፍሽ አይሉም። ኳታርም ከእስራኤል ጋር ይፋዊ የሆነ ግንኙነት ጀምራለች። ይህም አይወራም። የሚወራው ኦፊሻል ያልሆነው፣ የሆኑ ሳዑዲያውያን ከእስራኤል ባለስልጣን ጋር መገናኘታቸው ነው። ልብ በሉ! እኔ የንግድና የዲፕሎማሲ ግንኙነቶቹ ስህተት ናቸው አይደሉም ውስጥ አልገባሁም። ግና "ኮካ የእስራኤል ምርት ነው አትጠጡ። እሱን መጠጣት የፍልስጤሞችን ደም መጠጣት ነው" እያለ የሚያራግብ አካል የነ ቱርክን የንግድ ግንኙነት እያለፈ ሳዑዲን ያውም በሌለችበት ሲወነጅል አይደንቅም?