Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
የአላህን መብቶች ያሟላን ጊዜ የእኛም መብቶች ይሟላሉ፡፡
የፈጣሪን መብት ሳናሟላ ፍጡራን መብቶቻችንን አያሟሉልንም፡፡
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
https://t.me/SadatTextPosts
ታላቁ በደል ለምን ያህል ዘመን?
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በመልክተኞች ሁሉ መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸውና ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
የዛሬው አርእስት ልብ የሚያደማ ነው፡፡ አላህ መቼም ከናታችን ሆድ ስንወጣ ምንም የማናውቅ የነበርን ብንሆንም፣ መስሚያን፣ መመልከቻን ልቦናንን አድርጎልናል፡፡ የመልክተኞች ሁሉ ኢማም የሆኑትን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ላከልን፡፡ ቁርኣንን አወረደልን፡፡ ምስጋና ሁሉ ጥራት ለተገባው አላህ ይሁን፡፡ መቼም ይህን ሁሉ አድርጎልን ሀቁን ከባጢሉ ታላቁን በደል ከታላቁ በደል በታች ካሉት ለይተን ማወቂያ አእምሮን ሰጥቶናል፡፡
እኛ ሀበሾች ከማንም በፊት የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጥርት ያለች ጥሪ እንደደረሰን ይታወቃል፡፡ ታድያ የበደሎች ሁሉ በደል ምን እንደሆነ ኢስላም ነግሮናል አልነገረንም? ነግሮናል እንጂ
አላህ እንዲህ ይላል
وَإِذْ قَالَ لُقْمَٰنُ لِٱبْنِهِۦ وَهُوَ يَعِظُهُۥ يَٰبُنَىَّ لَا تُشْرِكْ بِٱللَّهِ ۖ إِنَّ ٱلشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ
ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን «ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፡፡ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና» ያለውን (አስታውስ)፡፡
አላህ ይሀው በግልፅ እንደነገረን ታላቁ በደል በእሱ ላይ ማንንም ይሁን ምንንም ማጋራት ነው፡፡ ሀገራችንንም ላይ ይሁን አለም ላይ በአላህ ላይ ሺርክን በመፈፀም ታላቁ በደል ይሰራል፡፡ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡
ታላቁ በደል (ሺርክ) ሁለት አገር ያጨልማል፡፡ የታላቁ በደል ተቃራኒ አላህን በብቸኝነት ማምለክ ነው፡፡ አላህን በብቸኝነት ማምለክ (ተውሒድ) የፍትሆች ሁሉ ፍትህ ነው፡፡ ሁለት ሀገር ለስኬት ያበቃል፡፡
የአላህን መብት እናሟላ የእኛም መብቶች እንዲሟሉልን፡፡ በሁለት ሀገር ስኬታማ እንድንሆን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ሐቅን መደበቅ ከባድ አደጋ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
وَإِذْ أَخَذَ ٱللَّهُ مِيثَٰقَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ لَتُبَيِّنُنَّهُۥ لِلنَّاسِ وَلَا تَكْتُمُونَهُۥ فَنَبَذُوهُ وَرَآءَ ظُهُورِهِمْ وَٱشْتَرَوْا۟ بِهِۦ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ فَبِئْسَ مَا يَشْتَرُونَ
አላህ የነዚያን መጽሐፉን የተሰጡትን ቃል ኪዳን ለሰዎች በእርግጥ ታብራሩታላችሁ አትደብቁትምም በማለት የያዘባቸውን (አስታውሱ)፡፡ በጀርባዎቻቸውም ኋላ ጣሉት፡፡ በርሱም ጥቂትን ዋጋ ገዙ፡፡ የሚገዙትም ነገር ከፋ!
https://t.me/SadatTextPosts
እውር አሞራ ቀላቢውን አላህ የካዱ፡፡
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ አሳዛኙ የአገራችን እውነታ፡፡
ጥርት ያለችው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጥሪ ከማንም በፊት ለሀበሾች ደርሶ ሲያበቃ፣ እዚሁ አገር ላይ ብቸኛውን ቀላቢ ትተው ፍጡር የሆኑትን ተቀላቢዎች እንደሚከተለው ከአላህ ውጭ ቀላቢ ናቸው ሲሉ የአላህን ስልጣን አሳልፈው ይሰጣሉ
1) አባድር ፆም አያሳድር፣
2) አላሁመ ሰሊ አላ ሙሐመዲ፣ መገን ነቢ የሁሉ ቀላቢ፣
3) ላክም አንቱ ነው ያ ነቢ፣ ለመላውም ኸልቅ ቀላቢ
አላህ ግን በግልፅ ቀላቢነቱን እንዲህ እያለ ሱረቱል ሁድ ላይ ነግሮን ሲያበቃ
۞ وَمَا مِن دَآبَّةٍ فِى ٱلْأَرْضِ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ رِزْقُهَا وَيَعْلَمُ مُسْتَقَرَّهَا وَمُسْتَوْدَعَهَا ۚ كُلٌّ فِى كِتَٰبٍ مُّبِينٍ
በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ማረፊያዋንም መርጊያዋንም ያውቃል፡፡ ሁሉም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህን እንፍራ፡፡ ኡለማዎችና ዱአቶች አደራችሁን ተወጡ፡፡ ህዝቡን ከምንም በፊት እምነቱን እንዲያስተካክል አስተምሩት፡፡ ይህም ከአላህ የተሰጣችሁት አደራ ነውና፡፡ የአላህን አደራ መብላት ከምንም በላይ ከባድ ወንጀል ነው፡፡ አብዛኛው አስታዋሽ ካጣ የአላህ ቁጣ ሲመጣ አደጋው ሁላችንንም ያገኘናል፡፡ አላህ በፍፁም የማይምረው ሺርክን ነው፡፡ ከሺርክ በታች ያለውን ለሻው ሰው ይምራል፡፡ ያ ከሺርክ በታች ወንጀሎችን የሰራ ሰው አላህ ከቀጣው እንኳን የጥፋቱን ያህል ተቀጥቶ ወደ ጀነት ይመለሳል፡፡ ነገር ግን በሺርክ ላይ የሞተ ሰው ዘላለሙን ከእሳት አይወጣም፡፡ ታድያ ይህን የተገነዘቡ ኡለማዎችና ዱአቶች ለምን ከምንም አርእስት በላይ ይህንን ጉዳይ አበክረው አይመክሩም?
አሳዛኙ እውነታ አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ አብዛኛው ይህን አይነት ከባድ ሺርክ የሚሰራባቸው አገሮች ላይ ሌላ አርእስት በማውራት ቢዚ የሆኑ ሰዎችን መመልከት ነው፡፡
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ ለቀላቢው ያልታመነ ለፍጡራን አይታመንም፡፡ ቀላቢውን ያላወቀ ከእንስሳት በታች ነው፡፡
አላህ የተውሒድን ብርሃን አውቀው አጥብቀው ከሚይዙትና ወደሱም ከሚጣሩት ያድርገን፡፡ የሺርክን ጨለማ አውቀው ከሚጠነቀቁት፣ ከሚያስጠነቅቁትና ከሚርቁት ያድርገን፡፡ አሚን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የቱን እንምረጥ የእውነቱን ወይንስ የውሸቱን አንድነት?
አላህ የልብ መመልከቻችንን ያብራልን፡፡
አላህ ሐቁን ይምራን፡፡ የውስጥ መመልከቻ ሲታወር የላይኛው አይን ቢመለከትም አያይም፡፡
እስቲ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ በሰጠን ንጹህ አእምሮ እንየው እንዴት ነው እውነተኛው ብቸኛ አንድ መንገድ አንድ ያደርጋል፣ እሷም ላይ እንሰብሰብ ማለት “ሙቡታተን” በተገላቢጦሹ ደግሞ አላህ ያወገዘውን የሰይጣን መንገዶች መከተል እና ልዩነት “አንድነት” ተብሎ የሚጠራው?
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ነፍሳችንን እንጠይቅ
1) ሃቅ ስንት ናት?
መልሱም አንድ እና አንድ ብቻ ናት፡፡ ለዚህም ማስረጃው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አብደላህ ኢብን መስኡድ ባስተላለፉት ሀዲስ “መሬት ላይ ቀጥተኛ መስመር አሰመሩ ይህም የአላህ ቀጥተኛው መንገድ ነው አሉ”
“ከዛም በጎን እና በጎን ሌሎች መስመሮች አሰመሩ እነዚህም መንገዶች ናቸው እያንዳንዱ መንገድ ላይ የሰይጣን ተጣሪ አለበት” አሉ፡፡
እስቲ ሀቅ ፈላጊዎች ሆይ! ሰይጣን የሚጣራባቸው የጥመት መንገዶች ብዙ መሆናቸው እና ሃቅ ብቸኛ አንድ መንገድ መሆኗ በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አንደበት ተነገረን ወይንስ አልተነገረንም?
መልሱም ተነገረን ነው፡፡
2) የትኛው ነው የሃቅ መንገድ?
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቁጥር አንድ ላይ ባየነው ነጥብ መሰረት ሃቅ አንድ መሆኗን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በመቀጠል እቺን ብቸኛ የሀቅ ጎዳና እናውቃት ዘንድ የቷ ናት?
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ “የሁዳዎች 71 ቦታ ይከፈላሉ፣ ነሷራዎች 72 ቦታ ይከፈላሉ፣ ይህም ኡመት 73 ቦታ ይከፈላል ሁሉም የእሳት ናቸው አንዷ ስትቀር”
የአላህ መልክተኛ አሁንም የሀቅ መንገድ አንድ ብቻ መሆኗን ጠቀሱ
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አንዷ የሀቅ መንገድ የትኛዋናት ተብለው ሲጠየቁ
“እኔ እና ሰሃባዎቼ ዛሬ ያለንባት መንገድ ናት” አሉ፡፡
በሌላ ሀዲስ ደግሞ
“ከሰዎች ሁሉ በላጭ እኔ ያለሁባቸው (ሰሃባዎች)፣ ከዛም ቀጥሎ ያሉት (ታቢኢን)፣ ከዛም ከጥሎ ያሉት (አትባኡ ታቢኢን)”
ይህ ነው እንግዲህ ብቸኛው የሁለት አገር ደህንነት እና ሰላም ዋስትና፣ የሰለፍያ ጎዳና፣ ብቸኛው ሃቅ፣ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ኹለፋኡ ራሺዲን፣ ሰሃባዎች፣ ታቢኢዬች፣ አትባኡታቢኢን የሄዱበት መንገድ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ግልጽ ሆነልን ሀቅ አንድ ብቻ መሆኗ?
ባረከላሁ ፊኩም፡፡ ሰይጣን የሚጣራባቸው የእሳት፣ የጥመት እና የጥፋት መንገዶች የትኛዎቹ ናቸው የሚለውን በሚቀጥለው ነጥብ እንመልከት፡፡
3) የትኛዎቹ ናቸውስ የትፋት መንገዶች?
ማንኛውም የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና የሰሃባዎቻቸው፣ የሰለፉነ ሷሊሂንን መንገድ ያልተከተለ እና የተቃረነ እዚህ የጥፋት እና የጥመት መንገድ ውስጥ ይገባል፡፡ ይህ ተቃርኖ በእምነት ጉዳይም ይሁን በአካሄድ ብቸኛዋን የሃቅ መንገድ የተቃረን ሁሉ እዚህ ሰይጣን የሚጣራበት የጥፋት መንገድ ውስጥ ገብቷል፡፡
በአላህ ፍቃድ እዚህ ጋር የጥመት ቡድኖችን ስም እጠቅሳለሁ፡፡ ልክ የሀቋ ብቸኛ ሰለፊያ ጎዳናን እንደጠቀስኩት ሁሉ፡፡
- ቀደሪያ፣
- ኸዋሪጅ፣ ሀሩሪያ፣ ኡባዲያ፣
- ራፊዳ ሺኣ፣
- ሙእተዚላ፣
- ማትሩድያ፣
- ጀህሚያ፣
- አሽአሪያ፣
- ኩላቢያ፣
- ሱፊያ ቃዲርያ፣
- ሱፍያ ቲጃንያ፣
- ሱፍያ ነቅሸበንዲያ……፣
- ኢኽዋን፣ ቁጥቢያ፣ ሱሩሪያ፣ ተብሊግ፣ አህባሽ፣ …….. እና ሌሎችም
እዚህ የተዘረዘሩት ሁላ ብቸኛዋን የሃቅ ጎዳና ሰለፊያ የተቃረኑ ናቸው፡፡ መንገድ የሳቱ ቡድኖች ለመሆናቸው ይሄ ማስረጃ ነው፡፡
4) ከላይ ቁጥር 3 ላይ የተዘረዘሩት ስንት ናቸው?
እንደሚታወቀው ቁጥር ሶስት ላይ የተዘረዘሩት ከአንድ በላይ ናቸው፡፡ ከዛም አልፎ ከብቸኛው የሰለፎች ጎዳና የተቃረኑ የጥመት ጎዳናዎች ናቸው፡፡
5) የመጀመሪያ ነጥብ ላይ ሃቅ ስንት እንደሆነች ነበር ያየነው?
መልሱም አንድ ብቻ ናት፡፡
6) ታድያ ለምን የውሸት አንድነት አስፈለገ?
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ በዚህ ዘመን ሙስሊሙ በአንድ ሀቅ ላይ እንዳይሰባሰብ “ሁሉም ጀመኣ የራሱ ድክመት አለው”፣ “ሰው ሆኖ የማይሳሳት የለም” እና የመሳሰለውን እያሉ የሚበታትኑት እና ተለያይቶ “አንድ ነን” እያለ እንዲዋሽ የሚያደርጉት የጥመት ቡድን የሆኑት ኢኽዋነል ሙስሊሚን ፍልስፍናን ተከታዬች ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡-
ሀሰን አል በና የተባለው የዚህ ጥመት ፖለቲካዊ ቡድን መስራች እንዲህ ይላል
اعلموا أنَّ أهل السنة والشيعة مسلمون تجمعهم كلمة لا إله إلاَّ الله وأنَّ محمداً رسول الله وهذا أصل العقيدة ,والسنة والشيعة فيه سواء وعلى التقاء ,أما الخلاف بينهما فهو في أمور من الممكن التقريب فيها بينهما
(ذكريات لا مذكرات)ط1- دار الاعتصام 1985 يقول الأستاذ عمر التلمساني ص249 و250
“እወቅ አህለሱና እና ሺአ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመዱ ረሱሉላህ የምትለው ቃል አንድ ታደርጋቸዋለች፡፡ ይህችም የአቂዳ መሰረት ናት፡፡ ሱና እና ሺኣ በዚህ ጉዳይ አንድ ናቸው፣ እኩል (የሚገናኙ፣ የሚጣጣሙ) ናቸው፡፡ በመካከላቸው ያለው ልዩነት እማ ሁለቱንም ማቀራረብ የሚቻል ነው (እንደ ልዩነት አይቆጠርም፡፡ ብዙ የሚያስቆጣ አይደለም፡፡)”
እውነታው ግን ሀሰን አል በና እንዳለው ሳይሆን ከሺአ ራፊዳዎች ጋር አንድ መሆን በፍጹም አንችልም፡፡ ልዩነታችንም የእምነት እና የክህደት ጉዳይ ነው፡፡
ምክንያቱን እነሱ ማለት እምነታቸው እና ተግባራቸው እንደሚከተለው በክህደት የተጨማለቀ ነው
- 12ቱ ኢማም ብለው የሚያምኑባቸውን ‹‹ከነብያት በላይ ናቸው፡፡ ከነብያት ይበልጣሉ›› ይላሉ፡፡ ይህ አባባላቸው ክህደት ነው፡፡
- ከአላህ ውጭ ‹‹ያ ሁሴን፣ ያ አልይ፣ ያ ፋጢማ፣ ያ ዘይነብ………›› እያሉ ይጣራሉ፡፡ ይሄም ሽርክ ነው፡፡ ጥሪ የሚገባው ለአላህ ብቻ ነው፡፡
- “ቁርዐን ተቀንሷል፤ ሱረቱል ዊላያ የሚባል ሱራ አለ ያላሉ” ይህ የክህደት እምነት ነው ምክንያቱም አላህ “ቁርዐንን እኛ ነን ያወረድነው እኛው እንጠብቀዋለን” ስለሚል ነው፤
- ሀዲስንም አይቀበሉም ቡኻሪ፤ ሙስሊም፤ አህመድ የመሳሰሉትን፡፡ በሱና የሚክድ ካፊር ነው፡፡
- እንዲህ ብለው ነሺዳ ሲያነሽዱም ተሰምተዋል “አንተ ሁሴን ከአላህ በላይ ትልቅ ነህ” ይሄም ኩፍር ነው፡፡
- የሺዐ መሪ ከነበሩት አንዱ ሃያቶላ ኹመይኒ እንዲህ ይላል “አነዚህ ሙሽሪኮች መዲናን መውረርና እነዛን ሁለት ጣዖቶች (አቡበክር እና ኡመርን) ማስወገድ ፈለጉ” ተመልከት ሱንዬ ወንድሜ ሆይ! ኢኽዋኖች ለማን አሳልፈው እየሰጡህ እንደሆነ? አቡበክርና ኡመርን (ረድየላሁ አንሁማ) ጣኦት ብሎ የሚጠራ ሸይጧን፡፡
- ከሺዐዎች መሪ አንዱም ስለ ምዕመናን እናት አኢሻ እንዲህ አለ “አኢሻ በእርግጥ ካሃዲ(ካፊር) ናት” የአላህ እና የረጋሚዎች እርግማን ሁሉ በርሱ ላይ ይሁን፡፡ ይህም ኩፍር ነው፡፡
- ከሺዐዎች አንዱም ተጠየቀ “ሱንዩ አለም ሙስሊም ይባላል ወይ?” እሱም “አይባሉም፤ ምክንያቱም ሙስሊም የሆነ ሰው አቡበክርን እና ኡመርን አይወድም” በማለት መለሰ፡፡ የአላህ ቁጣ በሱ ላይ ይሁንና፡፡ አቡበክርና ኡመርን በመውደድ ወደ አላህ እንቃረባለን፡፡
- የኡመር ኢብነል ኸጣብን ገዳይ አቡ አላ አልመጁሲን የዲን ጀግና ነው ብለው አላህን ከዚህ የተረገመ ሰው ጋር እንዲቀሰቅሳቸው ዱዐ ያደርጋሉ፤
- ኡመር የተገደለበትን ቀን የኢድ ቀን አድርገው ይዘዋል፤
- አቡበክርና ኡመር ከሸይጧን በታች ጀሀነም ውስጥ እየተቀጡ ነው ይላሉ፤
- ኢራን ላይ ሱንዬችን በክሪን ላይ ሰቅላ ትገድላለች፡፡ አላህ ያዋርዳቸውና
- እንደዚሁም ከነሱ ሸሆች አንዱ በVCD እየታየ ነብያችን አስሩን ጀነት ያበሰሩዋቸውን ሰሃባዎች አላህ ይርገማቸው ብሎ ዱዐ ያደርጋል፤
- ሌላው ሀሰን ነስረላህ በመባል የሚታወቀው የሂዝቦላህ መሪ ታላቁን ሰሃባ አቡሱፍያንን ሲያከፍር በቴሌቭዥን ታይቷል፤
- ኢብነል ቀይም እንደገለፃቸው “አንድም የውጭ ጠላት እስላምን ለማጥቃት አይመጣም ሺዐዎች እየመሩ ቢያመጡት እንጂ”፤ የሺዐዎች ጉድ ተነግሮ አያልቅም፡፡
አገራችንም ላይ የዚሁ የጥመት አስተምህሮት የኢኽዋን ተከታዬች የሽርክ መነሃሪያ የሆነውን መውሊድ የሚያከብሩ ሱፍዬችን፣ የሽርክ መንዙማ የሚያቀነቅኑ ሰዎችን፣ በቢድአ የታጨቁትን ተብሊጎች ቀን ከለሊት ከዚህ ሽርክ እና ቢድአቸው እንዲወጡ ከማስተማር ይልቅ “አንድ ነን እኛ ምንም አይለየን”፣ “መውሊድ አይለያየንም”፣ “መውሊድ ቅርንጫፍ ነው”፣ “ሱፊዬች ወንድሞቻችን ናቸው”፣ “መውሊድ አቂዳ አይደለም” ከዚህም አልፈው አለቃቸው አንዱ ኢኽዋኒ “መውሊድ” የሚል መጸሀፍ ጻፈ፡፡
7) የቱን እንምረጥ የእውነቱን ወይንስ የውሸቱን አንድነት?
አላህ ያዘዘን የሀቅ አንድነት ላይ እንድንሰባሰብ ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም) ሆነ ሰሃባዎቻቸው በሃቅ ላይ ተሰበሰቡ ቀጥተኛዋን መንገድ ከተቃረኑ ሰዎች ራቁ፡፡
ለዚህም ታላቁ ምሳሌ ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን ኡመር ነው፡፡ ኢራቅ በስራ አካባቢ ቀደርያዎች ሲከሰቱ የእሱ መልስ የነበረው የሚከተለው ነው፡፡
“ንገሯቸው እኔም ከነሱ አይደለሁም እነሱም ከእኔ አይደሉም”፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ግልጽ ሆነላችሁ?
እኛ አላህ ያዘዘን በሀቁ አንድነት ላይ እንድንሰባሰብ ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ኡማው እንደሚለያይ እና ያ ልዩነት በተፈጠረ ሰኣት ሃቋ ላይ እንድንጸና ነው የነገሩን፡፡
ነፍሴንም እናንተንም የጥንት የጠዋቷን መንገድ አጥብቆ በመያዝ ላይ አደራ አደራ አደራ፡፡
ብቸኛዋ የመዳኛ መንገድ ዳእዋ ሰለፊያ ከነተከታዬቿ
- ከምንም በፊት ነብያት ሁሉ ቅድሚያ ለተውሒድ እና ሱና እንደሰጡት ትሰጣለች፣
- ቁርኣን እና ሀዲስን በሰለፉነ ሷሊሂን አረዳድ ትረዳለች፣
- ተስፊያ እና ተርቢያ ላይ ታተኩራለች፣
- ከማንኛውም የጥመት ቡድን ያስጠነቅቃሉ፣
- ሀቅ አንድ ብቻ መሆኑን ያጸድቃሉ……….
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ለነፍሳችን እንዘንላት ሁሉንም የጥመት ቡድኖች ትተን ብቸኛዋን ቃል የተገባላትን የሃቅ መንገድ እንከተል፡፡ ይህን ማድረግ አንድነትን መጠበቅ ሲባል፣ ከዚህ ውጭ ያለው አንድነትን ማፍረስ ይባላል፡፡ ምክንያቱም የሙስሊሞችን አንድነት ኸዋሪጆች፣ ራፊዳዎች፣ ቀደሪያዎች፣ ጀበሪያዎች፣ ሙእተዚላዎች፣ ማትሩድያዎች… ሱፍዬች፣ ኢኽዋኖች፣ ተብሊጎች፣ አህባሾች መጥተው በትነውታልና፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በጥመት ቡድኖች መሃል ያለው የጥመት ደረጃ ቢለያይም ሁሉም ግን ጥመት ነው፡፡ ከአህባሽ ጋር አንድ ነን እንደማንለው ሁሉ ለምን ከሁሉም የጥመት ቡድኖች ወይንም ለነዚህ የጥመት ቡድኖች ከለላ ከሚሰጡ ግለሰቦች ርቀን የሃቁ አንድነት ላይ አንሰባሰብም? ይህ መንገድ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው የነበሩበት ብቸኛ የዋስትና መንገድ ነውና፡፡
አላህ ሆይ! የእውነተኛ አንድነት ስጠን ከውሸት አንድነት ጠብቀን፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኛው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ አሚን
https://t.me/SadatTextPosts
ጫት የዱኣ መሳሪያም የእስልምና አካል አይደለም፡፡
ያ ምርጡ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የመጡበት ውብ ሃይማኖት እስልምና በሰርጎ ገቦች ብዙ መጥፎ ነገሮችን የኢስላም አካል አስመስለው ሰግስገውበታል፡፡ የኢስላም ምርጥ ሊቃውንትም በየጊዜው እነዚህ ሰርጎ ገብ እምነቶች እና መጥፎ ተግባራት ከኢስላም አካል አለመሆናቸውን የተቃወመ ቢቃወማቸውም አብራርተው አስረድተዋል፡፡
ጫት እንደሚታወቀው ሙስሊሙን አሽመድምዶ ከጌታው ጋር ያለንም ይሁን ከፍጡራን ጋር ያለውን መብት አንድ ቃሚ እንዲያጓድል ሰበብ የሆነ አደገኛ መጥፎ ቅጠል ነው፡፡ አሳዛኙ እውቀት አላቸው ተብለው ሙስሊሙን ኡማ የሚቅመው በርትቶ እንዲቅም፣ የማይቅመው እንዲቅም ጫትን የኢስላም አካል እና የዱኣ መሳሪያ አድርገው የሚሰብኩ ሆድ አደሩዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ በመንዙማቸው፣ ሌላኛዎቹ ባገኙት መድረክ ላይ ጫትን እንደጥሩ ነገር ለሙስሊሙ ያስተዋውቃሉ፡፡ ሙስሊሞች ሊረዱ የሚገባቸው ጫት በጣም አደገኛ ነው፡፡ ይህም በተግባር የምናየው የት ይደርሳሉ የተባሉ ትዳሮች ሲበተኑ፣ የት ይደርሳሉ የተባሉ ወንድም እና እህቶች ተበለሻሽታ ማየታችን ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው፡፡
በመንዙማዎች ላይ ስለ ጫት ከተሰበኩ አደገኛ ስንኞች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
 “ጁሉሱ ሰኣቲን ጥቂት ቃቅምና (ጫት ቃምና ትንሽ ተቀመጥ)
ንገረው ለመውላህ እበሩ ቁምና”
 “እነሱ ይበራሉ በመቶ ሃምሳ ጀት፣ እኛ ቀደም ናቸው በአንድ ዘርባ ጫት”
 “ፍየል ቅጠል በልታ ትወልዳለች መንታ፣
መቼም እርባን የለው በጫት የተመታ”
 “ዝናቡ ዘነበ ጫቱ ለመለመ፣ የሚቅመው ቢያገኝ እያጉረመረመ”
 ከ አስር ሺህ መትረየስ አጥምዶ ከቆመ፣
ከሺህ ፈረሰኛ ተባብሮ ለቆመ፣
ይበልጣል ደግበል አጥብቆ የቃመ፣
ጠላቱንም ጎድቶ ወዳጁን ጠቀመ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ በዚህ ሱስ የተያዙትን በጠቅላላ እንዲያወጣቸው ዱኣ እና ምክር አይለያቸው፡፡ ጫት የምትቅሙ ወንድም እና እህቶች ሆይ! አላህ የውመል ቂያማ ጊዜያችንን በምን እንዳሳለፍነው ይጠይቀናል፡፡ ከዚህ ጊዜን እና ስብእናን ከሚገድል እርኩስ ቅጠል አላህን ለምናችሁ ለእሱ ስትሉ አቁሙ፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀደሬ፣ ወለኔ፣ … አረብ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ እና የመሳሰለው ሁሉም
የዘር ሀረጋቸውን ወደላይ ሄዶ ሄዶ ከሰው ልጆች አባት ነብዩላህ አደም (አለይሂ ሰላም) ውጭ አይደለም፡፡ አደም ደግሞ የተፈጠረው ከአፈር ነው፡፡ ከአፈር የተፈጠረው የሰው ልጅ ደግሞ ሲሞት ወደ አፈር ይመለሳል፡፡
ታድያ ለምን ይሆን ዘሩን እንዲህ የሚመፃደቅበት እና አንዱ አንዱን የሚያንቋሽሽበት?
የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ፣ ብቸኛው አምላክ አላህ የሰው ልጆች የሚለያዩት ለእርሱ ባላቸው ፍራቻ ብቻና ብቻ እንደሆነ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡
አንድ አምላክ ዘንድ የሰው ልጆች የሚበላለጡት እሱን በመፍራታቸው ብቻና ብቻ ነው፡፡
ለአእምሮ ባለቤቶች ይህ ትልቅ ትምህርት አለበትና ዘረኝነትን ሁላችንም እንራቀው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የከባድም ከባድ
=============
አብደላህ (ረድየላሁ አንሁ) የአላህ መልክተኛን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አላህ ዘንድ ታላቁ ወንጀል የቱ ነው? ብዬ ጠየቋቸው፡፡
እሳቸውም ‹‹አላህ ብቻውን ፈጥሮህ ሲያበቃ፤ በእርሱ ላይ ባላንጣን (ሸሪካን፤ ቢጤን) ማድረግ››
‹‹ይህ ታላቅ በደል ነው›› አልኩ
ከዚህ ቀጥሎስ? ብዬ ጠየቅኩ
እሳቸውም ‹‹ልጄ ምግቤን ይሻማዋል ብለህ ልጅህ መግደል›› ነው፡፡
ከዚህ ቀጥሎስ? ብዬ ጠየቅኩ
እሳቸውም ‹‹ከጎረቤትህ ሚስት ጋር ዝሙት መፈፀም›› ነው አሉ፡፡ ሰሂህ አል ቡኻሪ 6/4477

ከሃዲሱ የምንወስደው ትምህርት
==========================
ሁሉም ወንጀል እኩል አይደለም፡፡ ወንጀሉ አንድ አይነት ሆኖ፤ ከቦታ እና ሁኔታ አኳያ ይለያል፡፡ ለምሳሌ ነፍስ ማጥፋት ከባድ ወንጀል ሆኖ ሳለ፤ የገዛ ልጅህን ምግቤን ይሻማኛል ብሎ መግደል ደግሞ ከባድ ነፍስ ማጥፋ ነው፡፡

ጎረቤት ሃቁ ሊጠበቅለት፤ እሱ ለስራም ይሁን ለዘመቻ በሄደበት፤ ሚስት እና ልጆቹን በአማና ጥሎ ሄዶ ከእርሱ ሚስት ጋር ዝሙት መስራት እንደማንኛውም ዝሙት አይደለም፡፡

የወንጀሎች ሁሉ ታላቅ ወንጀል፤ በአላህ ላይ ማሻረክ እና ማጋራት፡፡ አላህ ብቸኛው ፈጣሪ ከሆነ ለምን የአምልኮ ክፍሎች ከእርሱ ውጭ ለፍጡራን ይደረጋሉ? ይህ ነው የበደሎች ሁሉ በደል፡፡

የመካ ሙሽሪኮች ሲጠየቁ ሰማይ እና ምድርን ማን ነው የፈጠረው? አለሙን የሚያስተናብረው ማን ነው? እናንተን የፈጠራችሁ ማን ነው? እና ሌሎች የአላህን ብቸኛ ፈጣሪነት የሚያረጋግጡ ጥያቄዎች ሲጠየቁ ‹‹አላህ›› ብለው መልስ ይሰጣሉ፡፡

ነሳራዎች ሰማይ እና ምድርን ማን ነው የፈጠረው ሲባሉ ‹‹አንድዬ›› ብለው አንድ መሆኑን እና ብቸኛ ፈጣሪ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

ታድያ ለምን ይሆን ከአላህ ውጭ ያሉ መላኢካም ይሁን (ጂብሪልን፤ ሚካኤልን (አለይሂሙሰላም)) ይመስል፤ ነብያት (ኢሳን፤ ኡዘይርን፤ ሙሃመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም))፤ ሷሊሆችን (አልይ፤ ሁሴን፤ ሀሰን፤ ፋጢማ (ረድየላሁ አንሁማ)) እና የመሳሰሉት ይመስል ከአላህ ውጭ ፍጡራን ሆነው ሳለ የሚመለኩት????????????

አላህ ለእርሱ ፍፁም አምልኮዋቸውን ካደረጉት ባሪያዎቹ ያድርገን፤ ከከባባድ ወንጀሎችም ይጠብቀን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
90 ደቂቃ አኸይራ ላይ ስንት ያስከፍል?????
ኳስ ለማየት 90 ደቂቃ ያለ አግባብ፣ ያውም በንዴት ስድብ ሁሉ እየተሰዳደቡ፣ ከዚህም አልፎ አላህ በወንድ ልጅ ላይ ያውም አይነ ስውር የሆነ ሰው ሁሉ አዛን እስከሰማ ድረስ፣ መስጊድ ሄዶ መስገድ ግዴታው ሆኖ ሳለ።ዲሽ ቤት እና ቴሌቭዥን ላይ 90 ደቂቃ ነገ አኸይራ ላይ ስንት ያስከፍል ይሆን?????ሰላት ወቅት አላት ጀሃድ ላይ እንኳን በሰአቱ ይሰገዳል፣ ኳስ በማየት ሰላት ያሳለፈ ምን ይዋጠው?????አላህ ሁኔታችን ያስተካክለው።
https://t.me/SadatTextPosts
የሰዎች ሁኔታም የሚስተካከለው የሀይማኖታቸው ሁኔታ ሲስተካከል ነው የሀይማኖታቸው ሁኔታ በተበላሸ መጠን ሁኔታቸውም ይበላሻል

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ፈለጋቸውን ሁሉ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ የሰዎች ሁኔታም የሚስተካከለው የሃይማኖታቸው ሁኔታ ሲስተካከል ነው፡፡የሃይማኖታቸው ሁኔታ በተበላሸ መጠን ሁኔታቸውም ይበላሻል፡፡ይህ ነገር ግልፅ እንዲሆንለት የፈለገ ሰው የሚከተለውን የቁርዓን አንቀፅ ያንብብ፡-
﴿وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْقُرَى ءَامَنُواْ وَاتَّقَوْاْ لَفَتَحْنَا عَلَيْهِم بَرَكَـتٍ مِّنَ السَّمَآءِ وَالاٌّرْضِ وَلَـكِن كَذَّبُواْ فَأَخَذْنَـهُمْ بِمَا كَانُواْ يَكْسِبُونَ - أَفَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَى أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا بَيَـتاً وَهُمْ نَآئِمُونَ - أَوَ أَمِنَ أَهْلُ الْقُرَى أَن يَأْتِيَهُمْ بَأْسُنَا ضُحًى وَهُمْ يَلْعَبُونَ - أَفَأَمِنُواْ مَكْرَ اللَّهِ فَلاَ يَأْمَنُ مَكْرَ اللَّهِ إِلاَّ الْقَوْمُ الْخَـسِرُونَ ﴾ (الأعراف 096-099)

‹‹የመንደሯም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፤ ግን አስተባበሉ፤ ይሰሩት በነበሩበትም ሃጢአት ያዝናቸው፡፡ የመንደሯ ሰዎች እንሱ የተኙ ሆነው ቅጣታችን ሌሊት እንዳይመጣባቸው አይፈሩምን? የመንደሯ ሰዎች እነሱ የሚጫወቱ ሆነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፈደ እንዳይመጣባቸው አይፈሩምን? የአላህንም አዘናግቶ መያዝ አይፈሩምን? የአላህን አዘናግቶ መያዝ ከከሳሪዎች ህዝቦች በስተቀር የሚተማመን የለም፡፡
ያለፉትን ሰዎች ታሪክ ይመልከቱ ልብ ብለው ካስተዋሉ ታሪክ ውስጥ ተስተምህሮት አለና፡፡ ልቡ ያልተሸፈነበት ሰው ሊያስተውል ይችላል፡፡ እርዳታ የሚፈለገው ከአላህ ብቻ ነው፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ፈለጋቸውን ሁሉ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡﴿وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْقُرَى ءَامَنُواْ وَاتَّقَوْاْ لَفَتَحْنَا عَلَيْهِم بَرَكَـتٍ مِّنَ السَّمَآءِ وَالاٌّرْضِ وَلَـكِن كَذَّبُواْ فَأَخَذْنَـهُمْ بِمَا كَانُواْ يَكْسِبُونَ - أَفَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَى أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا بَيَـتاً وَهُمْ نَآئِمُونَ - أَوَ أَمِنَ أَهْلُ الْقُرَى أَن يَأْتِيَهُمْ بَأْسُنَا ضُحًى وَهُمْ يَلْعَبُونَ - أَفَأَمِنُواْ مَكْرَ اللَّهِ فَلاَ يَأْمَنُ مَكْرَ اللَّهِ إِلاَّ الْقَوْمُ الْخَـسِرُونَ ﴾ (الأعراف 096-099)
‹‹የመንደሯም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፤ ግን አስተባበሉ፤ ይሰሩት በነበሩበትም ሃጢአት ያዝናቸው፡፡ የመንደሯ ሰዎች እንሱ የተኙ ሆነው ቅጣታችን ሌሊት እንዳይመጣባቸው አይፈሩምን? የመንደሯ ሰዎች እነሱ የሚጫወቱ ሆነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፈደ እንዳይመጣባቸው አይፈሩምን? የአላህንም አዘናግቶ መያዝ አይፈሩምን? የአላህን አዘናግቶ መያዝ ከከሳሪዎች ህዝቦች በስተቀር የሚተማመን የለም፡፡ያለፉትን ሰዎች ታሪክ ይመልከቱ ልብ ብለው ካስተዋሉ ታሪክ ውስጥ ተስተምህሮት አለና፡፡ ልቡ ያልተሸፈነበት ሰው ሊያስተውል ይችላል፡፡ እርዳታ የሚፈለገው ከአላህ ብቻ ነው፡፡የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ፈለጋቸውን ሁሉ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በእስልምና የሰው ስም አንስቶ መናገር ይቻላል ወይ?
***************************************
የሰው ስም ማንሳት የሚቻልባቸው ወቅቶች አሉ፡፡ ኢማመ ነወዊ (አላህ ይዘንላቸውና) የሚከተሉትን ስድስት ነጥቦች ‹‹ሪያዱ ሷሊሂን›› የተባለው ኪታባቸው ላይ ከቁርዐንና ከሀዲስ ጨምቀው እንዲህ በማለት አስቀምጠዋል፡፡ እወቅ ሀሜት ትክክለኛ ለሆነ አላማ ይቻላል፡፡ ከዚህ መንገድ ውጭ (ስም አንስቶ መናገር) ሌላ አማራጭ ከሌለ፤ እሱም በስድስት ምክንያት ነው፡፡
1. የተበደለ ሰው፡- የተበደለ ሰው ለሚመለከተው አካል፤ ለዳኛ ወይንም ለባለስልጣን፤ ለመሪ ሰውየው በሌለበት እገሌ በድሎኛል ቢል አይከለከልም፡፡
2. መጥፎን ነገር ለማስቆም (ለማገድ)፡- ለምሳሌ አከሌ መጥፎ ስራ እየወራ ነው፤ መጠጥ እየጠጣ ነው፤ እያጭበረበረ ነው ብለህ ለማስቆም ወይንም ለመምከር አቅም ላለው ሰው መናገር፡፡ ይህን ሲያደርግ ሰውየውን ለመመለስ ብቻ መሆን አለበት፡፡
3. ፈትዋ ለመጠየቅ፡- ለምሳሌ ለዳኛ አባቴ፤ ወንድሜ፤ ሚስቴ ወይንም እገሌ በድሎኛል፡፡ ለዚህ አካል ይሄ ይገባዋልን? ይበቃለታል ወይ? የሚሻለው ግን አባቴ፤ ወንድሜ ሳይሉ አንድ ሰው ነበር እንዲህ አደረገ ብሎ መጠየቅ ይሻላል፡፡
4. ሙስሊሞችን ከሸር ለማስጠንቀቅና ለመምከር፡- ለምሳሌ የሀዲስ ዘጋቢዎችና መስካሪዎችን ችግር ካለባቸው ችግር አለባቸው ማለት (ለምሳሌ የሚረሱ ከሆነ ይረሳሉ ብሎ መናገር)፤ እንዲያውም ይህ ዋጂብ ግዴታ ነው፡፡ ሌላ ምሳሌ፡- እገሌን ልጄን ልድረው ነበር፤ እገሌን ንግዴ ላይ ሸሪካ ላደርገው ነበር ምንትላለህ ተብሎ ከተጠየቀ፤ የተጠየቀው ሰው ሀቁን መናገር አለበት፡፡ ሌላው፡- አንድን ጡላበል ኢልም (የዲን ትምህርት የሚቀስም) ሙብተዲዕ (ቢድዐ የሚያራምድ ሰው) ጋር ወይንም ፋሲቅ ዘንድ ዲን ሊማር ሲመላለስ ካየሀው የሰውየውን ማንነት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ መስፈርቱም ምክርን አስቦ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰዎች የሚሳሳቱበት በመሆኑ ነው፤ ምክንያቱም ተናጋሪውን ምቀኝነት ሊያነሳሳው ይችላል፡፡ ሸይጧን ምክር ነው ብሎ ሊያመሳስልበት ይችላል፤ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ ሌላው፡- ሰውየው ሀላፍትና ቦታ ይቀመጥና ሀላፍትናውን የማይወጣ ከሆነ ወይ ሀላፍትና ላይ የተቀመጠው ሰው ለቦታው ብቁ ካልሆነ ወይንም ፋሲቅ ከሆነ ለሚመለከተው አካል፤ አከሌ ተነስቶ አከሌ ቢቀመጥ ብሎ መናገር ይቻላል፡፡
5. ሰውየው ወንጀሉንና ቢድዐውን ግልፅ የሚያደርግ ከሆነ፡- በግልፅ እየሰሩ ያሉትን በግልፅ ለማህበረሰቡ ስም አንስቶ መጥቀስ6. ለማስተዋወቅ፡- አንድ ሰው በሚታወቅበት ቅፅል ስም ማንሳት ለምሳሌ ሶስት ሙሀመዶች ቢኖኑ አንዱን ሙሀመድ የሚያነክሰው ተብሎ ቢጠራ፡፡ ልብ ሊባል የሚገባው ለመለየት ብቻ እንጂ ለማነወር ከሆነ አይቻልም፡፡1. የተበደለ ሰው፡- የተበደለ ሰው ለሚመለከተው አካል፤ ለዳኛ ወይንም ለባለስልጣን፤ ለመሪ ሰውየው በሌለበት እገሌ በድሎኛል ቢል አይከለከልም፡፡2. መጥፎን ነገር ለማስቆም (ለማገድ)፡- ለምሳሌ አከሌ መጥፎ ስራ እየወራ ነው፤ መጠጥ እየጠጣ ነው፤ እያጭበረበረ ነው ብለህ ለማስቆም ወይንም ለመምከር አቅም ላለው ሰው መናገር፡፡ ይህን ሲያደርግ ሰውየውን ለመመለስ ብቻ መሆን አለበት፡፡3. ፈትዋ ለመጠየቅ፡- ለምሳሌ ለዳኛ አባቴ፤ ወንድሜ፤ ሚስቴ ወይንም እገሌ በድሎኛል፡፡ ለዚህ አካል ይሄ ይገባዋልን? ይበቃለታል ወይ? የሚሻለው ግን አባቴ፤ ወንድሜ ሳይሉ አንድ ሰው ነበር እንዲህ አደረገ ብሎ መጠየቅ ይሻላል፡፡4. ሙስሊሞችን ከሸር ለማስጠንቀቅና ለመምከር፡- ለምሳሌ የሀዲስ ዘጋቢዎችና መስካሪዎችን ችግር ካለባቸው ችግር አለባቸው ማለት (ለምሳሌ የሚረሱ ከሆነ ይረሳሉ ብሎ መናገር)፤ እንዲያውም ይህ ዋጂብ ግዴታ ነው፡፡ ሌላ ምሳሌ፡- እገሌን ልጄን ልድረው ነበር፤ እገሌን ንግዴ ላይ ሸሪካ ላደርገው ነበር ምንትላለህ ተብሎ ከተጠየቀ፤ የተጠየቀው ሰው ሀቁን መናገር አለበት፡፡ ሌላው፡- አንድን ጡላበል ኢልም (የዲን ትምህርት የሚቀስም) ሙብተዲዕ (ቢድዐ የሚያራምድ ሰው) ጋር ወይንም ፋሲቅ ዘንድ ዲን ሊማር ሲመላለስ ካየሀው የሰውየውን ማንነት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ መስፈርቱም ምክርን አስቦ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰዎች የሚሳሳቱበት በመሆኑ ነው፤ ምክንያቱም ተናጋሪውን ምቀኝነት ሊያነሳሳው ይችላል፡፡ ሸይጧን ምክር ነው ብሎ ሊያመሳስልበት ይችላል፤ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ ሌላው፡- ሰውየው ሀላፍትና ቦታ ይቀመጥና ሀላፍትናውን የማይወጣ ከሆነ ወይ ሀላፍትና ላይ የተቀመጠው ሰው ለቦታው ብቁ ካልሆነ ወይንም ፋሲቅ ከሆነ ለሚመለከተው አካል፤ አከሌ ተነስቶ አከሌ ቢቀመጥ ብሎ መናገር ይቻላል፡፡5. ሰውየው ወንጀሉንና ቢድዐውን ግልፅ የሚያደርግ ከሆነ፡- በግልፅ እየሰሩ ያሉትን በግልፅ ለማህበረሰቡ ስም አንስቶ መጥቀስ6. ለማስተዋወቅ፡- አንድ ሰው በሚታወቅበት ቅፅል ስም ማንሳት ለምሳሌ ሶስት ሙሀመዶች ቢኖኑ አንዱን ሙሀመድ የሚያነክሰው ተብሎ ቢጠራ፡፡ ልብ ሊባል የሚገባው ለመለየት ብቻ እንጂ ለማነወር ከሆነ አይቻልም፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ቀብር ላይ ሱረቱል ፋቲሃ እና ሌላን ሱራ መቅራት?
የቱን ይከተላሉ አላህ ያወረደውን ወይንስ “የአባቶቻችን መንገድ” ብለው የሚጠሩትን?
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
መቼም እስልምናችን ውብ እና ሙሉ፣ ለየትኛውም ዘመን እና ቦታ ከበቂ በላይ የሆነ ነው፡፡ ታማኙ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከአላህ የተላኩበትን ማንኛውም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ቀብር ስንዘይር ምን ማለት እንዳለብንም አስተምረዋል፡፡ የሚከተለው ሀዲስ ላይ እንደተዘገበው
وعن بريدة رضي الله عنه قال‏:‏ كان النبي صلى الله عليه وسلم يعلمهم إذا خرجوا إلى المقابر أن يقول قائلهم‏:‏ “السلام عليكم أهل الديار من المؤمنين والمسلمين وإنا إن شاء الله بكم للاحقون، أسأل الله لنا ولكم العافية” ‏(‌‏(‏رواه مسلم‏)‌‏)‌‏.‏
የአላህ ሰላም በናንተ የዚህ መኖሪያ (ቀብር) ባለቤቶች ላይ ይሁን፡፡ ከአማኞች እና ከሙስሊሞች፡፡ እኛ በአላህ ፍቃድ ወደ እናንተ የምንከተል (ሟቾች) ነን፡፡ አላህን ለእኛም ለእናንተ አፊያን እንዲያደርግ እንጠይቀዋለን፡፡
ከዚህ ሀዲስ የምንወስደው ዋና ቁምነገር
- በህይወት ያለ ሰው ነው ለሙታን ዱዓ የሚያደርገው፣
- ሙታን ዱዓ ይደረግላቸዋል እንጂ እነሱ አይለመኑም፣
- ዛሬ ሺርክ ላይ የወደቁ ሰዎች ህያው የሆነውን፣ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ የሆነውን፣ የማይሞት አላህ ትተው ስራቸው የተቋረጠባቸውን፣ ምንም ማድረግ የማይችሉ፣ ቢጠሩ የማይሰሙ፣ ቢሰሙም ኖሮ መልስ መስጠት የማይችሉ ሙታኖችን እርዳታ ይለምናሉ፣ ቀብራቸው ላይ ሄደው ያርዳሉ፣ ቀብራቸው ላይ ጠዋፍ ያደርጋሉ፡፡
በዚህ ሀዲስ መሰረት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያስተማሩን ወንድ ልጅ ቀብር ሲሄድ ይህንን ዱኣ እንዲል ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሱረቱል ፋቲሃንም ይሁን ሌሎች ሱራዎችን በተለይ አገራችን ላይ በጀመዓ ቁርኣንን እየጮሁ የሚቀሩት ቢድዓ (በዲን ላይ የተጨመረ ፈጠራ) ነው፡፡ ከአላህ ቀጥሎ ለማንም በላይ እንወዳቸዋለን እያልን የምንጠራቸው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይሉናል “የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው፡፡” (ስራው ተቀባይነት የለውም)፡፡ ቀብር ላይ ሄዶ ሱረቱል ፋቲሃንም ይሁን ሌላን ሱና በጀመዓም ይሁን በነጠላ መቅራት የታለ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያዘዙበት? መልሱም አላዘዙበትም፡፡ ስለዚህ ቀብር ላይ እሳቸው ያስተማሩትን ብቻ እንበል፡፡
እኛ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ተከታዬች ነን ካልን በሁሉ ነገር ልንከተላቸው እና እሳቸው ያልሰሩትን ልንርቅ ይገባናል፡፡ ከዛ ውጭ የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ትእዛዝ ለሸሁም፣ ለኡስታዙም፣ ለአባቶቹም ሲል የተወ ሰው ከባድ አደጋ ውስጥ ገብቷል፡፡ ምክንያቱም ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከማንም በላይ እኛ ዘንድ እስካልተወደዱ (እስካልተከተልናቸው እና በዲን ላይ ከሚደረግ ፈጠራ እስካልራቅን) ድረስ እውነተኛ አማኞች አልሆንም፡፡
የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አስተምህሮት ሱና እንዲህ ሁሉን ነገር ገላልፆ ሲያበቃ የአባቶቻችን መንገድ ብሎ ሱናን መቃረን ለከባድ አደጋ ይዳርጋል፡፡
የአባቶቻችን መንገድ የተባለው ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ከገጠመ በደስታ እንቀበለዋለን፡፡ ከአባት ከእናታችን በላይ ውድና በላጭ የሆኑትን የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንገድ ከተቃረን አሽቀንጥረን እንወረውረዋለን፡፡ ምክንያቱም የሰይጣን መንገድ ነውና፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
[2:170] وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُوا۟ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُوا۟ بَلْ نَتَّبِعُ مَآ أَلْفَيْنَا عَلَيْهِ ءَابَآءَنَآ ۗ أَوَلَوْ كَانَ ءَابَآؤُهُمْ لَا يَعْقِلُونَ شَيْـًٔا وَلَا يَهْتَدُونَ
ለእነርሱም “አላህ ያወረደውን ተከተሉ” በተባሉ ጊዜ “አይደለም አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር እንከተላለን” ይላሉ፡፡ አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና (ወደ እውነት) የማይመሩም ቢኾኑ (ይከተሉዋቸዋልን?)
[31:21] وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُوا۟ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُوا۟ بَلْ نَتَّبِعُ مَا وَجَدْنَا عَلَيْهِ ءَابَآءَنَآ ۚ أَوَلَوْ كَانَ ٱلشَّيْطَٰنُ يَدْعُوهُمْ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ
ለእነርሱም አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ አይደለም በእርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን ይላሉ፡፡ ሰይጣን ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም (ይከተሉዋቸዋልን?)
ይሀው እነዚህ ሁለት አንቀፆች በግልፅ እንዳስቀመጡት “የአባቶቻችን መንገድ” እየተባለ አገራችን ላይ የሚነሳው የጥንቶቹም የሚያነሱት ብዥታ ነበር፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና እሳቸውን በየዘመኑ የሚከተሉ ኡለማዎች እና ተጣሪዎች የሚያዙት “አላህ ያወረደውን ተከተሉ (እንከተል)” ሲሉ ነው፡፡ የነብያትን መንገድ የሚቃረኑ ሰዎች ደግሞ በየዘመኑ መልሳቸው “አይደለም አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር እንከተላለን” የሚል ነው፡፡
አላህ ግን እንዲህ ሲል ጠየቀ
- “አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና (ወደ እውነት) የማይመሩም ቢኾኑ (ይከተሉዋቸዋልን?)”
- “ሰይጣን ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም (ይከተሉዋቸዋልን?)”
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡ አንዳንዴ የአባቶቻችን መንገድ የሚሉትን ልክ አይደለም ሲባሉ እና በማስረጃ መልስ ሲሰጠው “እናንተ ከእነ ሸህ እከሌ በላይ ታውቃላችሁን?” ሲሉም ይደመጣል፡፡ ጥያቄው እነዚህ ሸህ ተብየዎች ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ከሰሃባዎቻቸው በላይ ያውቃሉን? በፍፁም፡፡ እኛ አላህ እና መልክተኛው በእውቀታቸው፣ በአማኝነታቸው፣ በእውነተኝነታቸው፣ በታጋሽነታቸው፣ በቁርጠኝነታቸው የመሰከሩላቸውን መልክተኛውን እና ሰሃባዎቻቸውን መንገድ ነው የምንከተለው፡፡
አላህ ያወረደውን የማይከተል ሰይጣን ወደ እሳት የሚጣራበትን መንገድ እየተከተለ ነው፡፡
አገራችን ላይ አብዛኛውን ጥፋት “የአባቶቻችን መንገድ” እየተባለ ይፈፀማል፡፡ አባቶቻችንን ሳይሆን አላህ ያወረደውን እንድንከተል ነው የታዘዝነው፡፡ መልካም ማለት እኛ መልካም ያለነው አይደለም፡፡ መልካም ማለት ዲን መልካም ያለው ነው፡፡
አምነው ለሞቱ አባቶቻችን በጠቅላላ አላህ ወንጀላቸውን እንዲምር ደረጃቸውን ከፍ እንዲያደርግ ቀብራቸውን እንዲያሰፋ እለምነዋለሁ፡፡ አላህ እኛንም ሙስሊም አድርጎ እንዲገድለን እለምነዋለሁ፡፡
አላህ እሱ ባወረደው፣ በነብዩ ሱና ከሚብቃቁት፣ ከሺርክና ከቢድኣ ከሚርቁት ያድርገን፡፡ በአላህ ቢሆን እንጂ ሀይልም ብልሀትም የለም፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የአብሬት ሸህ እና ደርግ?
Degami Yeteposete
አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው የሁሉ ፈጣሪ፣ ህያው፣የማይሞተው፣ አሸናፊ ለሆነው አላህ ብቻ ነው፡፡ ሰሞኑን ጉዞ ወደ አብሬት ብለው ሰዎች የሚሄዱለት የአብሬት ሸይኽ በመባል ይታወቃሉ፡፡ አገራችን ላይ በጣም ድንበር ከሚታለፍባቸው ግለሰቦች ውስጥ ከቶፕ 5 ውስጥ ናቸው፡፡
እዚህ ትምህርት ላይ ማንሳት የፈለግኩት ምን አይነት ሰው ነበሩ? የሚለውን አይደለም፡፡ ነገር ግን መጥቀስ የምፈልገው ምን ያህል ድንበር እንደታለፈባቸው ነው፡፡
የአብሬት ሸይኽ አዲስ አበባ አውቶብስ ተራ ወረድ ብሎ ያለ አካባቢ “ጠቅላይ ቢሮ” የሚባል ቦታ ውስጥ እራሳቸውን አሟቸው በተኙበት ከሳቸው “ሙሪዶች” አንዱ ቤቱን 7 ጊዜ ዞሮ ፊዳ ልሁን እኔ ብሎ እራሱን በቢላዋ አርዶ ገድሏል፡፡
ሌላው የአብሬት ሸይኽን በጣም ብዙ ሰዎች ለአላህ ብቻ የሚገባውን አምልኮ ሲፈፅሙላቸው ይታያል፡፡ አሳዛኙ ግን የአብሬት ሸይኽም ይሁን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለራሳቸውም ይሁን ለጠየቃቸው ጥቅምን ማምጣት፣ መስጠት አይችሉም፡፡ ከጉዳትም እራሳቸውንም ሆነ ጠብቀኝ ያላቸውን መከላከል አይችሉም፡፡
የአብሬት ሸይኽ ደርግ ወስዷቸው እርምጃ እንደወሰደባቸው ቤተሰቦቻቸውም የእሳቸውን ሞት ሁሉ ተቀብለው ተቀምጠው ሳለ፣ ተከታዬቻቸው “አባባ ይመጣሉ”፣ “አባባ አልሞቱም” እያሉ ብዙ ችግር ውስጥ ገብተዋል፡፡
አምልኮ ከደርግ እራሳቸውን ማስጣል ለማይችሉት ለደካማው አብሬት አይገባም፡፡ ይሄ ሺርክ ነው፡፡
አምልኮ ሃያል፣ ህያው፣ የማይሞት፣ አሸናፊ ለሆነው አላህ ብቻ እና ብቻ ነው የሚገባው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
Channel photo updated
👆🏻ተውሒድ እና ሺርክ መፅሀፍ በሶፍት ኮፒ