SRH information - YMCA Ethiopia
271 subscribers
84 photos
14 videos
14 files
15 links
የስነ ተዋልዶ ጤና መረጃ ለወጣቶች (Sexual reproductive health information for young people)
Download Telegram
ድንገተኛ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖች መጠቀም ያለብን ያለእቅዳችን ለመጡ አጋጣሚ ጊዜዎች ብቻ ነው እንጂ በየጊዜው የሚወሰዱ የወሊድ መከላከያ ክኒን አይደሉም!


#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generation
ዛሬ ደግሞ ስለጨብጥ እንወያይ

ጨብጥ ፡ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ኢንፌክሽን ሲሆን  (bacterium Neisseria gonorrhoeae) ነው። ጥንቃቄ በጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት (በብልት፣ በአፍ ወይም በፊንጢጣ) በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በሚደረግ ወሲብ ሊተላለፍ ይችላል።

ምልክቶቹ ፡ከተለመደው ውጪ የሆነ የብልት ፈሳሽ ፣ በሽንት ጊዜ ህመም መስማት ወይም ማቃጠል ሊያካትቱ ይችላሉ ፡፡ አንዳንዴ ምንም ምልክቶች ላይኖር ይችላል።

ካልታከመ ጨብጥ ወደ ከባድ የጤና ችግሮች ሊያመራ ይችላል።በየጊዜው መመርመር፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ እና ኢንፌክሽን ከጠረጠሩ አፋጣኝ የሕክምና ክትትል ማግኘት አስፈላጊ ነው።
#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generation
የአይምሮ🧠 ህመም ማለት....
፨ከተለመደውና ትክክለኛ ከሚባለው ውጪ የአስተሳሰብ፣ የስሜት ወይም የባህሪ ለውጥ ሲኖርና ከባድ የአይምሮ ጭንቀት ሲያስከትል
፨በሰላማዊ ማህበራዊ ግንኙነት 🤝ወይም ከሰዎች ጋር በመግባባት አብሮ ለመኖር እንቅፋት የሚሆን ከሆነ
፨ከነባራዊ እውነታዎች መውጣትና ሌሎች ሊጋሯቸው በማይችሉት የራስ አለም🌍 ዉስጥ መገኘት
፨በራሱ በግለሰቡ ወይም በሌሎች ላይ የአካል፣ የመንፈስ፣ ወይም ማህበራዊ ቀዉስን የሚያስከትል ከሆነ
፨ ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት😨፣ ድብርትና🤦‍♀️ እንቅልፍ ማጣት ሲኖር ነው።
#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generetion
የዘር ፍሬ አካባቢ እብጠት ምክንያቱና ህክምናው /

📌የዘር ፍሬ አካባቢ እብጠት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል ከነዚህም መካከል የሚከተሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው
1) የዘር ፍሬ ዙሪያ ፈሳሽ መከማቸት /HYDROCELE
የዚህ ችግር መንስኤ ብዙ ጊዜ ባይታወቅም አልፎ አልፎ ግን ከአባላዘር በሽታ ጋር ተያይዞ ይከሰታል ።
ህክምናውም ቀላል ቀዶ ህክምና ሲሆን በዘር ፍሬ ዙሪያ  የተከማቸውን ፈሳሽ በማፍሰስ መልሶ እንዳይከማች ማድረግ ነው ።
2)በዘር ፍሬ አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች ማበጥ/VARICOCELE
በዘር ፍሬ አካባቢ የሚገኙ  የደም ስሮች(veins) ማበጥ ከ ቀላል የዘር ፍሬ አካባቢ ህመም ባሻገር ለወንዶች የመካንነት ችግር ያጋልጣል ።
3)የዘር ፍሬ ካንሰር/ TESTICULAR TUMOR
የዘር ፍሬ ካንሰር ብዙ ጊዜ እድሜያቸው ከ15-35  ውስጥ በሚገኙ ወጣት ወንዶች  ላይ ይከሰታል ።
የዚህ ካንሰር ዋናው ምልክት ህመም የሌለው እብጠት ነው/ painless testicular swelling ነው::
ይህ ካንሰር ሳይሠራጭ ቶሎ ከተገኘ ውጤታማ የሆነ ህክምና ሲኖረው ፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ከዘር ፍሬ እብጠት ባሻገር  ህመም ስለማይፈጥር ሰዎች ወደ ህክምና ተቋም የሚመጡት በጣም ዘግይተው ነው ። ይህም ህክምናውን ከባድ ያደርገዋል።
.....
Part 2...
በቅርብ ቀን
#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generation
ስለየማህፀን ጫፍ ካንሰር የቅድመ ካንሰር ምርመራ እናውራ

(ህዋሶች ) ከተለመደው ወጣ ባለ እና ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ እና ሲባዙ ካንሰር ይፈጠራል።

 የማህጸን በር ካንሰር በማህጸን አካባቢ ያሉ የሰውነት ክፍሎችን ሊወር፣ ወደሌላ የሰውነት ክፍሎቻችንም ሊሰራጭ ይችላል።
- በአለማችን ያሉ ሴቶችን በብዛት ከሚያጠቁ የካንሰር በሽታዎች አራተኛውን ደረጃ ይይዛል። ይህን በሽታ ለየት የሚያደርገው ከ80% በላይ የሚያጠቃዉ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች የሚኖሩ ሴቶችን መሆኑ ነው። ነገር ግን ቅድሚያ በሚሰጡ ክትባቶች እንዲሁም በግዜ አግኝቶ ለማከም የሚረዳውን (pap smear) የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ በማድረግ መከላከል ይቻላል፡፡

🛑አጋላጭ መንገዶች
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ዋናዎቹ አጋላጭ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ(HPV) በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፍ ቫይረስ ሲሆን  የማህጸን በር ካንሰር ዋናው አጋላጭ ነው። ከ99% በላይ የሚሆነው የማህፀን በር ካንሰር ከዚህ ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነው።
- ሲጋራ ማጨስ
- ግብረስጋ ግንኙነት በአፍላ እድሜ መጀመር

 🔴ምልክቶች
- ከወር አበባ ውጪ ከማህፀን የደም መፍሰስ
- በግንኙነት ጊዜ ህመም ወይም መድማት መኖር
- ሀይለኛ ሽታ ያለው የማህፀን ፈሳሽ መኖር

🔴የቅድመ ካንሰር ምርመራ
ማንኛዋም ሴት እድሜዋ 21 አመት ከሆነበት ወይም ግንኙነት ከጀመረችበት ከ3 አመት ጀምሮ በየ3  አመቱ ፓፕ ስሚር የተሰኘውን ምርመራ ብታደርግ ይመከራል፡፡
#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generation
ውጥረት(stress) በሴቶች ላይ

ውጥረት(stress) በሴቶች ላይ ትልቅ ተጽእኖ አለው, መጥፎ ስሜት እንዲሰማቸው እና በህይወታቸው ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ💆‍♀። ሴቶች ብዙ ሀላፊነቶች አለባቸው እና በስራ እና በህብረተሰብ ውስጥ የሚጠበቁትን ለማሟላት ጫና ይደርስባቸዋል።

እንደ የወር አበባ፣ እርግዝና እና ማረጥ ያሉ ከሥነ ተዋልዶ ጤንነታቸው ጋር የተያያዘ ጭንቀትን ይቋቋማሉ። ይህ ጭንቀት, ሀዘን, የእንቅልፍ ችግሮች እና አካላዊ ጉዳዮችን ሊያስከትል ይችላል።

ሴቶች የተሻለ ስሜት እንዲሰማቸው እና በሕይወታቸው ላይ የበለጠ ቁጥጥር እንዲኖራቸው እነዚህን ልዩ የጭንቀት ምንጮች ማወቅ እና ማስተናገድ አስፈላጊ ነው።
#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generation
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች 🤗
➡️ https://t.me/SRHinfo ⬅️
ይህንን Link ከጓደኞቻችሁ ጋር SHARE በማድረግ ቻናላችንን እንዲቀላቀሉ በአክብሮት እንጠይቃለን
ፌስቱላ በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡
ሀ. እውነት
ለ. ሀሰት

ለመልሳቹ በቂ ማብራሪያ ስጡ!
ትክክለኛውን መልስ በደንብ አብራርቶ ቶሎ የመለሰ የ100 ብር ካርድ ተሸላሚ ይሆናል።
👏👏👏👏👏የዛሬው  100 ብር የሚያስገኘውን ጥያቄ አሸናፊ የሆነው @feviiiiiiii ነው።

የጥያቄው ትክክለኛው መልስ :-

ሀስት ነው ።
ፌስቱላ በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ አይደለም።

ፌስቱላ ማለት በሁለት አካላት (organs) መካከል የሚፈጠር መኖር የሌለበት ክፍተት/ ግንኙነት ወይም ቀዳዳ ነው ::

@feviiiiiiii በውስጥ መስመር የ100 ብር ካርዱን እልክሎታለው

ይሄንን ቻናል ሼር ማረግን እንዳይረሱ።

እናመሰግናለን።
በቀጣይ ሳምንት እስክንገናኝ መልካም ሳምንት።
ስለፌስቱላ (Fistula) የተወሰነ እንወያይ

ፌስቱላ ማለት በሁለት አካላት (organs) መካከል የሚፈጠር መኖር የሌለበት ክፍተት/ ግንኙነት ወይም ቀዳዳ ነው ።

ስነ ተዋልዶ ጤናን በተመለከተ፤ ፌስቱላ በአብዛኛው የሚከሰተው በመረብያ አካላት አካባቢ ሲሆን ቀዳዳው በእምስ እና በሽንት ትቦ መካከል ወይም በእምስ እና ፊንጢጣ መካከል ነው። በዚህ ወቅት ሽንት ወይም ዓይነ ምድር፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሁለቱንም መቆጣጠር ሳይችሉ ቀርተው ሊያመልጣቸው ይችላል።

የፌስቱላ መንስኤዎች ፡-
- በፆታዊ ጥቃት (መደፈር)
- አቅመ ሄዋን ያልደረሰች ወይም በልጅነት የተከሰተ እርግዝና (Teenage Pregnancy)
- ያለዕድሜ ጋብቻ
- የምጥ መብዛትና መርዘም
- የኪንታሮት በሽታ ተገቢውን ህክምና አለማግኘት
- የህፃን ልጅ ጭንቅላት ከመጠን በላይ መተለቅ በወሊድ ጊዜ
- በእርግዝና ወቅት የልጅ አቀማመጥ ትክክል አለመሆን ፣ የመሳሰሉት ናቸው ።

#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generation
ቁንጅና🌹 ላንቺ ምንድን ነው???
ላንቺስ ምንድን ነው🤔??? ካልሺኝ
- በራሷ የምትተማመን👍
-ከራሷ አልፋ ለሌሎች የምታበራ
- ባላት ነገር ሁሌ ፅድት ብላ የምትታይ💃
- እራሷን ከአባላዘር በሽታዎች(STI) እንዲሁም አጠቃላይ ጤናዋን የምትጠብቅ🏃‍♀️
- አላማ ያላት ለራሷ ጊዜ የምትሰጥ🧖‍♀️
- የውሳኔ ሴት 💪 ካለችበት 1 እርምጃ 👣 ለመጨመር የምትታትር
- ለቤተሰቧ👨‍👩‍👦‍👦 ጊዜ የምትሰጥ
አንቺ 👈 ይሄንን የምታነቢው ☝️ ይሄንን ሁሉ ስለምታደርጊ አንቺም የውቦች ሁሉ ውብ ነሽ። ለአንዷ ውብ ጓደኛሽ 👭Share ማድረግሽን አትርሺ።
                🙏 መልካም ሰንበት🙏
#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generetion
🤗ሠላም ቤተሠቦች ከአእምሮ ጤና መታወክ ወይም እክሎች ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ላይ በተወሰነ መልኩ እንመልከት

🧩የመጀመርያው ትልቁ ችግር ከማህበረሠብ መገለል ነው ጭንቀት🫨 ሲበዛ ውጥረት ሲበዛ ከሰው መገለልን ነው እንደ መፍትሄ የምንወስደው ነገር ግን ልክ አይደም የበለጠ ያባብሰዋል በዛው ከቀጠለ ወደ ሱሶች መሳብ ይኖራል እራስን መጉዳት
በተደጋጋሚ እራስን የማጥፋት ሀሳቦችና ሙከራዎች እስከማድረግ ሊደርስ ይችላል
ስለዚህ እነዚህን ስሜቶች እንዴት ቀስ ብለን አባብለን እንዴት የአእምሮአችንን ጤና እንመልሳለን ሚለውን እንመካከር
🧩የመጀመሪያው እራስን ማወቅ ምንድነው የሚያስጨንቀን የሚያስፈልገን የሚያሳዝነን ብለን በደንብ የጥሞና ጊዜ መውሰድ ማብሰልሰል ድክመቴ ጥንካሬዬ ምንድነው ብሎ ጊዜ ሠጥቶ ማብሰልሠል
🧩በተጨማሪ የአእምሮ ጤንነት ለመጠበቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን መስራት
አመስጋኝነትን መለማመድ ከማህበረቡ ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነትን መፍጠር
ጤናማ አመጋገብ እና ውሃ በበቂ ሁኔታ መጠጣት ጥሩ እንቅልፍ ለማግኘት መሞከር እና በተጨማሪ የ ጤና ባለሙያ ማማከር ቀስ በቀስ የተሻለ የአእምሮ ጤና ይኖረናል 💪
Part 2....

የዘር ፍሬ አካባቢ እብጠት(Scrotal Swelling) ምክንያቱና ህክምናው

4)የዘር ፍሬ መታጠፍ (TESTICULAR TORSION)
- ይህ ችግር እጅግ በጣም ድንገተኛና አጣዳፊ ከመሆኑም ባሻገር ከፍተኛ የሆነ ህመም አለዉ። ይህ ችግር ቡዙ ጊዜ በታዳጊ ወጣቶች ላይ ይከሰታል ።ይህ ችግር የሚስተካከለው በአስቸኳይ ቀዶ ህክምና ሲሆን በስድስት ሰአታት ውስጥ ካልተስተካከለ ወደ ዘር ፍሬ የሚሄደው ደም ስለሚቋረጥ ለመካነነት ችግር ይዳርጋል።

5) የዘር ፍሬ እና አካባቢው ኢንፌክሽን(EPIDIDYMO-ORCHITIS)
- ይህ ችግር በአብዛኛው ከአባላዘር በሽታ ወይም  ከሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ጋር የተያያዘ ሲሆን ባክቴሪያዎች ከሽንት ቧንቧ ወደ ዘር ፍሬ በማለፍ ኢንፌክሽን ወይም መቆጣት ሲፈጥሩ የሚከሰት ችግር  ነው።ምልክቶቹም ከፍተኛ የሆነ የዘር ፍሬ አካባቢ ህመም ፣ትኩሳት ፣ ሲሸኑ ማቃጠል እንዲሁም ከብልት የሚወጣ ፈሳሽ ተጠቃሽ ናቸው።

6) የልብ ድካም ፣ የኩላሊት እንዲሁም የጉበት ችግሮች
- እነዚህ በሽታዎች በተለያዩ የሰውነታችን ክፍል  ፈሳሽ  እንዲጠራቀም የሚያደርጉ ሲሆን ለምሳሌ እግር ላይ ፣ ፊት ላይ እንዲሁም አንዳንዴ የዘር ፍሬ አካባቢ ላይ ፈሳሽ እንዲጠራቀም በማድረግ ሊያሳብጡት ይችላሉ።በአጠቃላይ የዘር ፍሬ እብጠት ከቀላል እስከ ከባድ በሆኑ  ችግሮች ምክንያት ሊከሰት ይችላል።
# ከዚህ በተጨማሪ የዘር ፍሬ ካንሰር የመጀመሪያው ምልክት ህመም-አልባ የዘር ፍሬ ላይ እንደ ጠጠር ያለ እብጠት ሲሆን

ችግሩ ሳይባባስ ቀድሞ ለማወቅ በየጊዜው የዘር ፍሬዎት ላይ እብጠት መኖር አለመኖሩን  ቼክ ማድረግ ያስፈልጋል።

#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generation
የአእምሮ ጤና መታወክ ማለት ምንድን ነው?  እና ስንት አይነት የአእምሮ ጤና መታወክ እንዳሉስ ያውቃሉ?

ለመልሳቹ በቂ ማብራሪያ ስጡ!
ትክክለኛውን መልስ በደንብ አብራርቶ ቶሎ የመለሰ የ100 ብር ካርድ ተሸላሚ ይሆናል
👏👏👏👏👏የዛሬው  100 ብር የሚያስገኘውን ጥያቄ አሸናፊ የሆነችው @Azab-Hayla ናት።

የጥያቄው ትክክለኛው መልስ :-የአእምሮ ጤና መታወክ ማለት..
 
የግለሰቡን ስሜታዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ደህንነት የሚነኩ የተለያዩ ሁኔታዎችን ያጠቃልላል።

የተለመዱ የአእምሮ ጤና እክሎች ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል:-

የመንፈስ ጭንቀት,በጭንቀት መታወክ,ባይፖላር ዲስኦርደር,ስኪዞፈሪንያ,ትኩረት የመሰብሰብ ችግር, 
የሚጠቀሱት ናቸው ።

@Azab-Hayla  በውስጥ መስመር የ100 ብር ካርዱን እልክሎታለው

ይሄንን ቻናል ሼር ማረግን እንዳይረሱ።

እናመሰግናለን።
በቀጣይ ሳምንት እስክንገናኝ መልካም ሳምንት።
### ስለ የአእምሮ ጤና መታወክ የተወሰነ እንወያይ
  
የአእምሮ ጤና መታወክ የግለሰቡን ስሜታዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ደህንነት የሚነኩ የተለያዩ ሁኔታዎችን ያጠቃልላል።  እነዚህ ሁኔታዎች በአስተሳሰባችን፣በሚሰማን እና በምግባራችን ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ፣ እና በእለት ከእለት ህይወታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።  የተለመዱ የአእምሮ ጤና ጉዳዮች የመንፈስ ጭንቀት፣ የጭንቀት መታወክ፣ ባይፖላር ዲስኦርደር፣ ስኪዞፈሪንያ እና የስብዕና መታወክ ያካትታሉ።

#### የተለመዱ የአእምሮ ጤና እክሎች መካከል ሚጠቀሱት መክከል:-

1. የመንፈስ ጭንቀት፡- የማያቋርጥ ሀዘን፣ የእንቅስቃሴ ፍላጎት ማጣት እና የተለያዩ ስሜታዊ እና አካላዊ ችግሮች ተለይተው ይታወቃሉ።

2. የጭንቀት መታወክ፡- እነዚህ እንደ አጠቃላይ የጭንቀት መታወክ (GAD)፣ ፓኒክ ዲስኦርደር እና የማህበራዊ ጭንቀት ዲስኦርደር ያሉ በሽታዎችን ያካትታሉ።

3. ባይፖላር ዲስኦርደር፡- ስሜታዊ ከፍታዎችን (ማኒያ ወይም ሃይፖማኒያ) እና ዝቅተኛ (ድብርት) የሚያካትቱ ከፍተኛ የስሜት መለዋወጥን ያካትታል።

4. ስኪዞፈሪንያ፡ ከባድ የአእምሮ መታወክ የሰውን አስተሳሰብ፣ ስሜት እና ባህሪ ይነካል።

#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generation
የወሊድ መቆጣጠሪያ  እንክብል
⭕️በአፍ የሚወሰዱ እንክብሎች ሲሆኑ በውስጣቸው የያዙአቸው ሆርሞኖች በተፈጥሮ በሰውነታችን ውስጥም የሚመረቱ እና ከወር አበባ እና እርግዝና ጋር የተያያዙ  ሂደቶችን የሚቆጣጠሩ ናቸው።እንክብሎቹ በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት መወሰድ ይኖርባቸዋል።

⭕️በትክክለኛው መንገድ ከተጠቀሙት እርግዝና የመከሰት እድሉ  99% እርግዝናን መከላከል ይችላል ። ነገር ግን በአጠቃቀም ጊዜ ከሚኖሩ ስህተቶች ጋር ተያይዞ እርግዝና የመከሰት እድሉ እስከ 7/100 ድረስ ከፍ ሊል ይችላል፡
እንክብሎቹን መጠቀም ካቆሙ በኃላ ማርገዝ ቢፈለግ በ 3 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀድሞ የልጅ መውለድ  አቅም መመለስ ይቻላል፡፡ ነገርግን በመዘናጋት እንክብሉን ሳንውጥ ብንረሳ ለተከታታይ ሁለት ቀን ሌላ የ እርግዝና መከላከያ ለምሳሌ እንደ ኮንዶም ያሉትን ብንጠቀም ይመከራል
እስከዛው ደም ውስጥ ያለው የሆርሞን መዛባትን ይስተካከላል
መድሀኒቱን ደግሞ  ባስታወሰንበት ቀን ጀምረን መዋጥ እንችላለን  ነገር ግን  ከሁለት ቀን በላይ በተከታታይ ከ ዘለልን  የጤና ባለሙያ ማማከር እና ማስተካከል ይኖርብናል።

⭕️በተጨማሪ  እንክብሉን  የወር አበባ ህመምን እና መዛባትን ለማስተካክል እንጠቀመዋለን።
⭕️ተጓዳኝ ጉዳቶች
እንክብሉን መውሰድ የተጀመረበት የመጀመሪያ ወራት ላይ የወር አበባ ለውጦች ሊከሰት ይችላል። 
⭕️የራስ ምታት
⭕️ማቅለሽለሽ
አልፎ አልፎም እንደመድሀኒቱ  አይነት የሚወሰን ሆኖ ለደም መርጋት የማጋለጥ ባህሪ ሊኖረው ስለሚችል  ከጤና ባለሞያ ጋር መማከር ይኖርብናል😊
#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generation
ያልተፈለገ እርግዝና መንስኤዎች🤰

ወደ ያልተፈለገ እርግዝና ሊመሩ የሚችሉ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡🤔🤔
1. ያለ እድሜ ጋብቻ
2. የጓደኛ ግፊት
3. የወሲብ ሙከራ
4. የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት አለመገኘት
5. በሴት/ወንድ ጾታዊነት ላይ የተሳሳቱ መረጃዎች ወይም አፈ ታሪኮች
6. ስለ የወሊድ መከላከያ አጠቃቀም ፍርሃት ወይም አፈ ታሪኮች
7. የእርግዝና መከላከያዎችን አለመጠቀም
8. የእውቀት ወይም የመረጃ እጥረት
የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን በአግባቡ አለመጠቀም
9. አላማን ካለማገናዘብ
10. ጥቃት፣ እንደ መደፈር ..ወ.ዘ.ተ ሲሆኑ

ስለዚህ ራሳችንን ካልተፈለገ እርግዝና እና ወሲባዊ ግንኙነት እንቆጥብ😉

#ymcaethiopia
#ወወክማ_ኢትዮጵያ
#srh
#ስነተዋልዶ_ጤና
#empowering_the_young_generation
ጥያቄ : የስነ ተዋልዶ ጤና ስንል ምን ማለታችን ነው?ስለ ስነ ተዋልዶ ጤና ማወቃችን ያለው ጠቀሜታስ ምንድን ነው ?

ለመልሳቹ በቂ ማብራሪያ ስጡ!
ትክክለኛውን መልስ በደንብ አብራርቶ ቶሎ የመለሰ የ100 ብር ካርድ ተሸላሚ ይሆናል።
👏👏👏👏👏የዛሬው  100 ብር የሚያስገኘውን ጥያቄ አሸናፊ የሆነችው @Moanasbb ናት።

የጥያቄው ትክክለኛው መልስ :-

የስነ-ተዋልዶ ጤና (SRH) የአጠቃላይ ጤና እና ደህንነት ወሳኝ ገጽታ ነው, ይህም በተለያዩ የህይወት ደረጃዎች ውስጥ ያሉ ግለሰቦችን የሚነኩ ብዙ ጉዳዮችን ያካትታል.  የበሽታ ወይም የአካል ጉዳት አለመኖር ብቻ ሳይሆን ከሥነ ተዋልዶ ሥርዓት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ሁሉ የተሟላ የአካል፣ የአእምሮ እና የማህበራዊ ደህንነት ሁኔታ ነው።  ይህ መመሪያ የፆታ እና የስነ ተዋልዶ ጤናን ለማራመድ ክፍሎችን፣ አስፈላጊነትን እና መንገዶችን በጥልቀት ይመለከታል።

@Moanasbb በውስጥ መስመር የ100 ብር ካርዱን እልክሎታለው

ይሄንን ቻናል ሼር ማረግን እንዳይረሱ።

እናመሰግናለን።
በቀጣይ ሳምንት እስክንገናኝ መልካም ሳምንት።