St.Paul's Hospital Millennium Medical College
20K subscribers
3.03K photos
33 videos
21 files
524 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
ከሶስት ሺህ ሰዎች በላይ ነጻ የጤና ምርመራ የሚያገኙበት አገልግሎት በፈረንሣይ ለጋሲዮን አካባቢ መስጠት ተጀመረ: :

በየካ ክፍለ ከተማ ፈረንሣይ አካባቢ በሚገኘው ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
አዳራሽ ለሶስት ቀናት የሚሠጠውን ይህን ነጻ የጤና ምርመራ መርሐ ግብር በይፋ የከፈቱት የጤና ማኒስትር ክብርት ዶር መቅደስ ዳባ ናቸው: :
ክብርት ሚኒስትርዋ የነጻ ምርመራውን በይፋ ሲከፍቱ እንደገለጹት የጤና ምርመራ ማድረግ ለማንኛውም ሰው አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸው:
አስቀድሞ የጤና ምርመራ ማድረግ ብልህነት ነው ብለዋል: :
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሕክምና ኮሌጅ ፕሮቮስት ዶር ሙሉቀን ተስፋዬ በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ በበኩላቸው እንደተናገሩት ኮሌጁ በዚህ ክረምት ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ዜጎች ነጻ የጤና ምርመራ አገልግሎት መሥጠቱን አስታውሰው ወደፊትም ኮሌጁ ለሕብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል: :

ይህ ነጻ የጤና ምርመራ የተዘጋጀው በጤና ሚኒስቴር፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል እና በፈረንሳይና ቤላ የወንድማማቾች ጤና ስፖርት ቡድን ነው: :
Finance Ministers Visit SPHMMC’s New Medical Facilities Under Construction

The Ethiopian Minister of Finance, H.E. Ahmed Shide, together with H.E. Dr. Eyob Tekalign, State Minister of Fiscal Policy and Public Finance, visited St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) to visited SPHMMC to learn about the new specialty centers being built.

The delegation was received by H.E. Dr. Mekdes Daba, Minister of Health, along with Dr. Muluken Tesfaye, Provost of SPHMMC, and Dr. Lemi Belay, Vice Provost for Medical Services and Acadamic .

During the visit, the Ministers toured specialized centers under development, including the Cardiac Center, the Gastrointestinal (GI) Center, and the Oncology Center. These centers are designed to provide advanced, high-standard medical care that will greatly strengthen Ethiopia’s capacity for specialized health services.

The discussions held between the Ministry of Finance, the Ministry of Health, and SPHMMC leadership emphasized the importance of aligning financial strategies with the hospital’s future role in delivering world-class healthcare. The visit also enabled the Finance Ministry to gain a deeper understanding of the institution’s growing capacity and its significance in advancing the country’s medical service standards.
🚨 Milestone Alert

This week, the St. Paul’s Cardiology Team, in collaboration with the Cardiovascular Education Foundation (CVEF), is on a transformative medical mission.

Today, history was made!
For the first time in a government facility, we successfully performed:
CRT -P
ICD
CRT-D implantations

This milestone was made possible with the support of Dr. Theofanie Mela (Boston) and Dr. Joseph Galvin (Ireland), both renowned electrophysiologists — who generously shared their expertise with our team.

Our heartfelt thanks go to St. Paul’s Hospital Millennium Medical College and St. Peter Hospital management for their facilitation and unwavering support.

Special gratitude to CVEF for coordinating this mission and facilitating the donation of devices, making these life-saving procedures accessible to our patients.

#Cardiology #MedicalMission #Electrophysiology #DeviceImplantation
የነርሲንግ ስፔሻሊቲ ፖስት ቤዚክ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ምዝገባ ማስታወቂያ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በአምስት የነርሲንግ ፖስት ቤዚክ ስፔሻሊቲ ማለትም በ Emergency and Critical Care Nursing፣ በ operating Theater Nurse፣ በ neonatal Nursing፣ በ pediatric Nursing እና በ surgical Nursing ለመማር የምትፈልጉ እና መስፈርቱ የምታሟሉ ከ 29/12/2017- 05/01/2018 ዓ.ም Online https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement እንድትመዘገቡ እናሳወቃለን፡፡
 የመመዝገቢያ መስፈርቶች፣
• በነርሲንግ ዲፕሎማ ደረጃ 4 የተመረቀች/የተመረቀ በሁሉም ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች መወዳደር ይችላሉ፣
• የሚድዋይፍሪ ዲፕሎማ ደረጃ የተመረቀች /የተመረቀ በህፃናትና በጨቅላ ህፃናት ነርሲንግ መመዝገብ ይችላል፣
• ከመስሪያ ቤታቸው የስፖንሰር ሺፕ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል/የሚትችል ወይም ከፍሎ መማር የሚችሉ ፡፡
• ኮሌጁ የሚያዘጋጀውን የቃል እና የፁሑፍ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል፣
• ሙሉ ጤነኛ የሆነ/የሆነች
• አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ ያላት
ማሳሰቢያ፡
 የመመዝገቢያ የማይመለስ 100 ብር በኮሌጁ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000006577192 በማስገባት ደረሰኝ አፕሎድ ማድረግ
 ዲፕሎማ፤ትራንስክሪፕት እና የስራ ልምድ upload ማድረግ
 አስፈላጊውን ዶክመንት ያላሟላ ፈተናው ላይ እንደማይቀመጥ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
 ኮሌጁ ማደሪያና ምግብ አያዘጋጅም

ለመመዝገብ ወደ ሲስተሙ ስትገቡ ማድረግ ያለባቹ
 ወደ መመዝገቢያ ሊንኩ ከገባቹ በኃላ
 Apply now / Apply for admission የሚለውን ሊንክ መጫን
 የሚፈልጉትን ፕሮግራም በመምረጥ Apply ማለት
 ቀጥሎ basic information በማስገባት summit ሲባል Application has successfully submitted የሚል ኖቲፊኬሽን ከApplication number ጋር አብሮ ይመጣል Application number ለቀጣይ ዶክመንት ለማስገባት ስለሚጠቅም ቁጥሩን መያዝ ግዴታ ነው።
 ቀጥሎ upload receipt የሚለውን በመጫን የመመዝገቢያ 100 ብር የተከፈለበትን ደረሰኝ upload ማድረግ
 ቀጥሎ upload document ላይ በመግባት ዶክመንታቹን አስገብታቹ ስትጨርሱ Summit document የሚለውን በመጫን ምዝገባውን ታጠናቅቃላቹ።
ሬጅስትራር ጽ/ቤት