St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
Happy International Women's Day
Happy International Women's Day
MISS IT NOT!!
Mandela Ethiopia Doctors in collaboration with St. Paul Millennium Medical College presents you a Panel Discussion “Safe Space For Health Care- The Way Forward” on Saturday March 9, 2019 starting from 2:30pm. It’s open for all, come and have your say for sexual harassment free health facilities.
Location- Ethiopian Public Health Institute
ሐኪሟ በሠዓሊው ብሩሽ
ሠዓሊ: ሣሙዔል እንዳለማው
የዘይት ቅብ

t.me/spmmc
ኮሌጁ የካንሰር በሽታን ለመከላከል መርሐ ግብር ቀርፆ እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፡- ብዙ ሴቶችን የሚያጠቃው የጡት ካንሰርንና የማህፀን ጫፍ ካንሰርን ለመከላከል መርሐግብር ቀርፆ እየሰራ እንደሚገኝ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ገለፀ። በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ሐኪሙ ዶክተር ሙሉጌታ ካሳሁን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ ሰባት ወራትን ያስቆጠረው መርሐ ግብር በቅድሚያ በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 9 ጊዜያዊ ካምፕ በመስራት የተጀመረ ሲሆን፤ በአካባቢው ላሉ 110 እናቶች ምርመራ ተካሂዶ በአምስት ሴቶች ላይ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ተገኝቷል፤ ህክምናም ተደርጎላቸው መዳን ችለዋል።

 በመድኃኒዓለም ሁለተኛና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ከጤና ጥበቃ ጋር በመተባበር በተካሄደው ዘመቻ ለ800 ሴቶች የጡትእና የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ የተካሄደ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ በቅድም ምርመራ ላይ ያለው ግንዛቤ እንዲያድግ ትምህርት ተሰጥቷል። መርሐ ግብሩ በአዲስ አበባ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል፣ በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለሚሰሩ በአማካኝ በእያንዳንዱ ተቋም ለመቶ ሴቶች ምርመራ ተካሂዷል። በተደረገውም ምርመራ ተጨማሪ ምርመራ የሚያስፈልጋቸውን በመለየት ጉዳያቸውን እንዲከታተሉና መታከም ያለባቸውም እንዲታከሙ ተደርጓል። በዚህም ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸው እና የባሰባቸውም እንዲታከሙ ተደርጓል።

በክልል ደረጃም በጉራጌ ዞን ወራቤ ላይ መርሐግብሩ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፤ በአካባቢው ምንም እንኳ የጡት ካንሰር ያለባቸውን ማግኘት ባይቻልም፤ የማህፀን ጫፍ ካንሰር የታየባቸው ሴቶች እንደነበሩ ተናግረዋል። በተለይ አንደኛዋ ሴት፣ ካንሰሩ ባይሰራጭባትም ምልክቱ በደንብ ስለታየባት በቀዶ ጥገና ከበሽታው እንድትድን ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል። እንደ ዶክተር ሙሉጌታ ገለፃ፤ ‹‹ካንሰር ኬር›› የተሰኘውን ይህን መርሐግብር ተግባራዊ ለማድረግ የታቀደው በዚህ በሽታ የሚጠቁ አብዛኞቹ ሰዎች ወደ ሐኪም ቤት የሚመጡት መዳን በማይችሉበት ደረጃ ላይ ከደረሱ በኋላ ነው።

 በተጨማሪ በሽታው በስፋት እየታየ ሲሆን፤ ቀድሞ በመመርመር ከበሽታው ለመዳን ያለው ዝግጁነት አነስተኛ ሆኖ በመገኘቱ ነው። ‹‹ካንሰር ህክምና የሌለው በሽታ አይደለም። ቀድሞ ከተደረሰበት መታከምና መዳን ይቻላል›› ያሉት ዶክተሩ፤ ሆኖም ‹‹በካንሰር መያዜን ባውቅ ባላውቅ መዳን ስለማይቻል ምንም ዋጋ የለውም›› ከሚለው አስተሳሰብ መውጣት እንዳለበትም አሳስበዋል።

አዲስ ዘመን የካቲት 29/2011

በምህረት ሞገስ
የልጆች ምኞት
St. Paul’s has made a video message on the proper handling of surgical biopsies. You may freely use the video for instruction in classroom. The video is available upon request from the department of Communication or Anatomic Pathology. It will also be posted on YouTube. We are grateful to the department of Anatomic Pathology and the department of Capacity Building for taking the initiative to make the video.
በበረራ ቁጥር ET 302 ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ ይበር በነበረው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነው B-737-800MAX አውሮፕላን ላይ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የተሰማንን ልባዊ ሀዘን እየገለፅን በአደጋው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ መፅናናትን እንመኛለን።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሕክምና ኮሌጅ የድንገተኛ አደጋ ቡድንም አደጋው የደረሰበት ሥፍራ ተጉዟል ።
Today is world Kidney day.
World Kidney Day is a global awareness campaign aimed at raising awareness of the importance of our kidneys.

ዛሬ የዓለም የኩላሊት ጤና ቀን ነው። በዚህ ቀን ስለ ኩላሊት ጤና በመላው ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ይካሄዳሉ።