St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሣችሁ!
በ2016 ዓ.ም የሚሰጠው የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተናን ይመለከታል
ለሁሉም የድህረ ምረቃ ትምህርት ለመማር ያመለከታችሁ በሙሉ፡ የመግቢያ ፈተና የሚሰጠዉ ከመስከረም 21-23/2016 ዓ.ም በመሆኑ ሁሉም ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Testing (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ከመስከረም 11-20/2016 ዓ.ም መመዝገብ ይኖርባቹሃል፡፡ ለዝርዝር መረጃ ከዚህ መልዕክት ጋር ተያይዞ የተለጠፈዉን በትምህርት ሚኒስትር የተላከዉን መመሪያ ያንብቡ
Dr. Hailemichael Desalegn abstract for the ECHO project was accepted for an oral presentation and has gained global recognition with the integration of the WhatsApp-ECHO platform and testimonials. It will now be presented in a Ted-style talk. He is invited to talk at Albuquerque,  University of New Mexico, USA.
New Year, New Topic! We are kicking off the new year, welcoming all Healthcare Professionals!

The topic of discussion: Navigating the path to career advancement in the Healthcare system.

If you are working in the healthcare system, this event is for you! Our discussion will be centered around Panelists from different Organizations to give you information and resources on how you can get the job you're looking for.

The event will be held at the Satchmo Center at the American Embassy from 2:00 - 4:00 PM (8:00 local time), supported by St. Paul's Hospital Millennium Medical College- SPHMMC, and Boston’s Salon & Day Spa.

Reminders:
1) Please remember you must register in advance
2) Bring your ID with you to enter the program
3) Leave all electronics except your cell phones at home. (laptops, tablets etc...). You wont enter with those devices.

Register for the event here: https://t.ly/qOTnz

Register for Satchmo Center Entrance: https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

We can't wait to see you all there!
በሙያቸው ሐኪም ሆነው ረጅም ልብወለድ የጻፉ አትዮጵያውያን ቁጥር አሁን ሶስት ደርሷል፡፡ሁሉም ደግሞ ሣይካትሪስቶች ናቸው፡፡ ይህን የደራሲዎች ዓለም የተቀላቀሉት ዶ/ር ዳዊት አሰፋ ይባላሉ፡፡ደራሲው ከአስር አመታት በላይ በአእምሮ ሐኪምነት በአማኑኤል እና በኮተቤ ሆስፒታል አገልግሏል። ከዚህ የአገልግሎት ዘመኑ ግማሽ ያህሉን አማኑኤል ሆስፒታልን በዋና ስራ አስኪያጅነት በመምራት አሳልፏል።

በሆስፒታሉ በሃላፊነት ከሰራቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል ኪነጥበብ ተኮር ሕክምናን የመደበኛ አእምሮ ሕክምናው አንዱ አካል እንዲሆን ሲያደርግ የነበረው ጥረት ተጠቃሽ ነው። በዚህም ኪነጥበብን ከአእምሮ ሕክምና ጋር በማቀናጀት የጥበብ ሕክምናን (art therapy)ን ለማስፋፋት በተደረገው እንቅስቃሴ በርካታ የአገራችን የስነፅሁፍ፣ የሙዚቃ፣ የስዕል፣ የፊልም እና የቲያትር እውቅ ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ተደርጓል።

ደራሲውበአገራችንታሉ ስራአስኪያጅነት ባሻገር የአእምሮ ሕክምና አገልግሎትን በአገራችን ለማስፋፋት በጤና ሚንስቴር የተዘጋጁ የተለያዩ ፕሮግራሞችን መርቷል። የኢትዮጵያ አእምሮ ሕክምና ማህበርን ለሶስት አመታት በፕሬዝዳንትነት አገልግሏል።

ባለትዳር እና የሶስት ልጆች አባት የሆነው ዶ/ር ዳዊት አሰፋ ዛሬ ደግሞ "የሁሉ" የተሰኘችውን የመጀመሪያ ረጅም ልቦለድ ስራውን ለአንባቢያን አቅርቧል።
በቅርቡ ነውወ
ስለ "የሁሉ" የተቀላቀለው

"የሁሉ" የደራሲው የመጀመሪያ ረጅም ልቦለድ መፅሃፉ ናት።

"የሁሉ" ትኩረቷን በአእምሮ ጤና እና በአገራችን አንኳር ማህበረ - ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች ላይ ታደርጋለች።
የልቦለድ ስራ ብትሆንም ከደራሲው ሰፊ የአገልግሎት፣ የአመራር እና የማህበራዊ ህይወት ተሞክሮ የተቀዳች ናት።
Successful Completion of Conference on One Health Approach to Child and Adolescent Mental Health
We are excited to announce the successful completion of a two-day conference on a “One Health Approach to Child and Adolescent Mental Health”. The conference was held on September 21 and 22, 2023 at the Grand Palace Hotel. SPHMMC, Department of Psychiatry, and the Center for International Health, Ludwig Maximilian University (CIHLMU) collaborated in organizing the conference.
The conference brought together key stakeholders from Ethiopia and Germany to discuss the importance of a One Health Approach to Child and Adolescent Mental Health. His Excellency Mr. Lelisa Amanuel, SMO advisor welcomed everyone and spoke about the MOH's efforts to enhance child and adolescent mental health. Key note speakers and experts from various ministries, government and private institutions, professional associations, NGOs, special needs schools, journalists, and adolescents were invited.
The conference provided an overview of the One Health Approach, as well as viewpoints on child and adolescent mental health care perspectives from Ethiopia and Germany. Keynote speakers and workshops addressed a variety of topics, including neurodiversity, the consequences of trauma on child and adolescent mental health, the public health element of child and adolescent mental health, the One Health aspect of schools as sites for change, and urbanization as an important  One Health factor influencing child and adolescent mental health.
The conference was a great success and was a thought-provoking and networking event for all participants. The take-home messages from the conference will be used to strengthen joint efforts to promote wellness and improve youth mental health care. This will help to ensure that our future world is safe and healthy for all children and adolescents.
We would like to express our appreciation to the funder (DAAD), the organizing team, and all participants for their contributions to the success of this conference.
We would also like to thank Dr. Surafel Worku (Psychiatrist), for his role in organizing the conference.
#ማስታወቂያ
የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ምዝገባና ፈተና ጊዜ ተራዝሟል።
የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (Graduate Admission Test) ከመስከረም 28-30/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ይሰጣል።
በመሆኑም የድህረምረቃ ተማሪዎች ከመስከረም 21-25/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፖርታል https://portal.aau.edu.et በመጠቀም እንድትመዘገቡ እንገልጻለን ።
The Federal Ministry of Health (FMOH) of Ethiopia, St. Paul’s Hospital Millennium Medical College
School of Public Health (SPHMMC) and University of California San Francisco (UCSF) have developed ‘A
contraceptive counseling pocketbook for family planning service providers’. The pocket book is
intended to be used by contraceptive counselors to improve their counseling skills and promote
empathy and respect in communication with clients.
The SPHMMC team, led by Dr. Ewenat Gebrehanna, and the UCSF team, led by Dr. Kelsey Holt, were
invited to collaborate with the FMOH on the pocket book after having conducted a series of studies
since 2018 through their ‘Quality of Contraceptive Counseling (QCC)' project. The aim of the QCC
Project was to adapt and validate a QCC Scale to measure client experience with counseling and
leverage it for use in monitoring quality of contraceptive care in Ethiopia. The tool was originally
developed in Mexico by Dr. Holt's team. The long version
(https://www.ncbi.nlm.nih.gov/pmc/articles/PMC10065231/ ) and short version
(https://www.sciencedirect.com/.../pii/S0010782422003833) of the validated tool are
published and available in the links provided. Researchers are welcome to contact the PIs for further
information. Further information on related activities can be found here:
https://qccscale.ucsf.edu/overview
We would like to congratulate Dr. Ewenat Gebrehanna and School of Public Health(SPH) of SPHMMC
and Dr. Kelsey Holt of UCSF for this achievement. Special thanks goes to Mr. Hailemichael Bizuneh (SPH,
SPHHMC), the coordinator for the contraceptive counselling project, and the SPHMMC community
who contributed to this achievement.
David & Lucile Packard Foundation sponsored the development of this pocketbook and the team’s
research activities since 2018 as part of the QCC Project to improve the quality of contraceptive counselling
in Ethiopia.
የጥንዶቹ ድንቅ ተምሳሌታዊ ተግባር
ማቴዎስ ወንዱ ገና የሁለተኛ ዓመት ልደት ሻማውን በለኮሰ ከጥቂት ቀናት በኃላ በሉክሚያ( ALL-type Leukemia) በተባለ የደም ካንሰር ሕመም እንዳለበት በሐኪም ተረጋገጠ፡፡
ወላጆቹ ትንሹ ልጃቸውን በሕይወት ለማዳን ከሀገር ውስጥ ጀምሮ እስከ ባህር ማዶ የዘለቀ ጥረት አደረጉ፡፡ አባትና እናት ከመላው ዘመዶች ጋር በመሆን ያላቸውን ጥሪት አሟጠው ሕክምናው ይገኛል በተባለበት በደቡብ አፍሪካ ፣ በአውሮፓ፣ በሕንድና በአሜሪካ ብዙ ሞክረዋል፡፡ በመጨረሻም አሜሪካን አገር ሕጻኑን ማቲዎስን ይዘው ለመሄድ ሲዘጋጁ መስከረም 13 ቀን 1996 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
ልጃቸውን በሞት ያጡት ወ/ሮ አምሳለ በየነና አቶ ወንዱ በቀለ ማቲን የሚዘክርና በሕመሙ እየተሰቃዩ ያሉትን ለመርዳት የመሰረቱት ማቲዎስ ወንዱ-የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ሕሙማንና ቤተሰቦቻቸውን እየደገፈ ይገኛል፡፡
በትንሹ ማቴዎስ ስም የተጀመረው የሶሳይቲው ሥራ በእጅጉ አድጎ ዛሬ ለብዙ ሕሙማን መድህን ለመሆን ችሏል ሶሳይቲው በአሁኑ ሰዓት 1ሺህ 400 አባላት፣ 500 በጎ ፈቃደኞች ፣ 30 ቋሚ ሰራተኞችን ይዞ ትልቅ ድርጅት ለመሆን በቅቷል፡፡ በቁጥር 152 የሚደርሱ የካንሰር ህሙማንንና ቤተሰቦቻቸውን ትርጉም ባለው ሁኔታ ይደግፋል፡፡ በተጨማሪም ሕክምና በሚሰጥበት የጤና ተቋማት የማይገኙ የመድኃኒት፣ የላቦራቶሪና የራዲዮሎጂ ሕክምና ወጪዎችን ይሸፍናል፡፡ ለሕሙማንና ቤተሰቦች ለትራንስፖርት የሚሆን ሙሉ ወጪ በየወሩ ይሰጣል፡፡ ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ለሚማሩ ሕጻናት ታካሚዎች ድርጅቱ ሙሉ የትምህርት ወጪያቸውን ይሸፍናል፡፡ ከክልሎች በመምጣት በአዲስ አበባ ሕክምናቸውን ለሚከታተሉ ሕሙማን በማቆያ ማዕከሉ የመጠለያና የምግብ አገልግሎት በነፃ ይሰጣል ፡፡ እነዚህ ሕሙማንና ቤተሰቦቻቸው የሳይኮ ሶሻል አገልግሎትም ያገኛሉ፡፡
ይህ ማህበር በዚህ ዓመት 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከብራል፡፡ልጆቻቸው የካንሰር ሕመም ያለባቸውን ወላጆች እየደገፉ እና ሕክምናውን በአግባቡ ተከታትለው እንዲድኑ በመርዳት አገልግሎት ሁለት አስርተ ዓመታት ሊደፍን ጥቂት ወራት ይቀረዋል፡፡ ባለፉት 20 ዐመታት ከመላው ኢትዮጵያየመጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወላጆች በዚህ ድርጅት ተደግፈዋል፡፡ እነዚህ ሁለት ጥንዶች አሁንም ራዕያቸው ትልቅ ነው፡፡ በካንሰር ህመም የተጠቁ ልጆች ያላቸዉ ቤተሰቦችን ለመርዳትና ልጆቻቸዉን ለመታደግ ውጥናቸው ሰፊ ነው፡፡ አሁንም ይህ በጎ ተግባራቸው ዳር እንዲደርስ እንደግፋቸው! እናበረታታቸው!
እንኳን ለ20ኛ የምስረታ በዓል አደረሳችሁ!
እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! !
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሰዎ!
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ የእምነቱ አባቶች በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ተገኝተው ሕክምና በመከታተል ላይ የሚገኙ ሕሙማንን ጎብኝተዋል፡፡
ለምክር ቤቱ አባላት የኮሌጁ ሕክምና አገልግሎት ምክትል ፕሮቮስት ዶክተር ውለታው ጫኔ እና ሌሎች ከፍተኛ ስፔሳሊስት ሐኪሞች ጋር በመሆን ስለ ሕክምና አገልግሎቱ አሰጣጥ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡ በተለይ የጽኑ ሕሙማን ክፍል ተኝቶ ታካሚዎችን እና የኩላሊት እጥበት የሚደረግላቸው ሕሙማንን ጎብኝተዋል፡፡
ሕሙማኑ የሚያስፈልጋቸው መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው እየጨመረ በመሆኑ የሃይማኖት ተቋማት ምዕመናንን በማስተባበር የገንዘብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሕሙማንን በገንዘብ፣ የሕክምና ተቋማቱን ደግሞ በሕክምና መሣሪያ እንዲያግዙ ዶክተር ውለታው ጫኔ ጥሪ አቅርበዋል።
የሃይማኖት አባቶች አማኞች ጤናቸውን እንዲጠብቁና የቅድመ ምርመራ ባህል እንዲያዳብሩ በማስተማር እንዲያግዙም ኃላፊው ጠይቀዋል።