🌅ኦርቶዶክሳዊ_የክርስትና_ሕይወት🌅
1.08K subscribers
2 photos
1 file
5 links
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
📗ይህ ችልናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ምዕመናንን መንፈሳዊ ሕይወት ለማበርታት፣ ለማጠንከርና ለማጽናት ይረዳ ዘንዳ📗
🌄🌄 ✅የምክር፣
🌄🌄✅የተግሳፅ፣
🌄🌄✅የህይወትና
🌄🌄✅የሥርዓት ትምህርቶችና ጽሑፎች የሚቀርቡበት ቻናል ነው።

🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
Download Telegram
🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄

📗አሳድጉኝ📗
(.............. የቀጠለ ............)

🌷የክርስቶስ ወጣቶች🌷
👉ዘመናዊ አረመኔነት።👈

እስክንድርያ ውስጥ በሚገኝ የመድኃኒት ቅመማ ጥናት (pharmacology) የምታጠና ግብጻዊት ልጃገረድና ጀርመን ውስጥ ይህንኑ ጥናት የምታጠና ጀርመናዊት ልጃገረድ በአንድ ወቅት ሲገናኙ የመጀመሪያይቱ ልጃገረድ ለሁለተኛይቱ የሰው ልጆችን አፍቃሪ ስለሆነው፣ የሰዎችን ወዳጅነት ስለሚፈልገውና ስሜቶቻቸውን ስለሚጋራ ስለ እግዚአብሔር ነገረቻት። ጀርመናዊቷ ተማሪ ይህን ስትሰማ ግብጻዊቷን ተማሪ ገና ያልሰለጠነች አድርጋ ቁልቁል እየተመለከተች ሳቀችባት፤ ተሳለቀችባትም። ይህን ያደረገችውም እስከዛሬ ድረስ እግዚአብሔር አለ ብላ በማመኗ ወደእርሱ በመጸለይዋ ነበር። ግብጻዊቷ ወደሃገሯ ከተመለሰች በኋላ ከጀረመናዊቱ ተማሪ የእንኳን ደስ አለሽ ደብዳቤ ደረሳት። በደብዳቤውም ውስጥ እንዲህ የሚሉ ዓረፍተ ነገሮች ይነበባሉ፦ “አንቺ የሚረዳሽ እግዚአብሔር ስላለሽ እድለኛ ነሽ። እኔ ግን የውስጤ ጥልቀት ባዶ ሆኖ ሳለ ባንቺ ላይ ተሳልቄ ነበር።”

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

ወጣቶች ከእግዚአብሔር ለማምለጥ የሚመኙት ለምንድን ነው? ሌሎች በእርሱ እጆች ውስጥ መደላደል የሚሹትስ ለምንድን ነው? ምስጋና ይግባውና አንዳንድ ወጣቶች እግዚአብሔርን በገነት ውስጥ ለብቻው እየኖረ የሰው ልጆችን ከእውነታው አርቆ የሚያንቀሳቅሳት አካል አድርገው ይመለከቱታል። እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን የሚመለከቱበት መመሪያዎችና ትእዛዝ የሚሰጥ አድርገው ብቻ ነው። ብዙ ወጣቶች ወደ እግዚአብሔር የሚመለከቱት ያለ ምንም ጥልቅ ስሜት፣ ፍላጎት፣ ጉጉት፣ ድካም ወይም ፍርሃት ነው።

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

በአንድ ወቅት አንድ ሰው ከኪዩቤክ ካናድ ከመጣ ከሌላ ሰው ጋር ይገናኛል። ካናዳዊው ሰው የእግዚአብሔርን ህልውና ይክዳል። በዚህ ጊዜ ሌላኛው ሰው “ክርስቶስ ድንገት መጥቶ ቢያገኝህ ምን ታደርጋለህ?” በማለት ይጠይቀዋል። ካናዳዊውም “ላየው እንደማልፈልግ እነግረዋለሁ!” ብሎ መልሶለታል። እንደርሱ ከሆነ ይህ ምላሽ እግዚአብሔር የሰዎችን ነጻነት የሚጨቁንና የሰውን ልጆች ህይወት እውነትነትን ችላ የሚል አድርጎ የሚያሳይ ነው።

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

ይህ አሳብ ህያው ከሆነው ከእኛ ክርስቶስና ክርስቲያናዊው እውነት የራቀ ነው። የእኛ እግዚአብሔር ወደዚህ ምድር የወረደው ህያው እግዚአብሔር ነው። የእኛ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚኖርና በወዳጅነትና በፍቅር እናገኘው ዘንድ የእኛን ተፈጥሮ የተጋራ እግዚአብሔር ነው። እርሱ በእርሱ ዘንድ ተወዳጅ አድርጎ የመረጠው ገና ሃያ አምስት ዓመት ያልሆነው ቅዱስ ዮሐንስ ነው።

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

“... በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤...” መክ 12፥1። ይህ ቃል እንዲሁ ትእዛዝ ብቻ አይደለም፤ ወጣቶች ወደ እርሱ በመመለስ ሃጢአትን እንዲያስወግዱ የሚጠይቅ እንጂ። እግዚአብሔር በፍቅር አከባቢ ውስጥ ከእያንዳንዱ ወንድ ልጅና ሴት ልጃገረድ ጋር ያለ ማቋረጥ ለመሆን መፈለጉን ስለሚያውጅላቸው ይህ የፍቅር ግብዣ ነው።

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

እርሱ እነርሱን የሚጋብዛቸው ለእርሱ ያላቸውን ፍቅራቸውን ተቀባብሎ የእርሱን ፍቅር ለእነርሱ ሊሞላላቸው ነው። እርሱ ጥልቅ ወደ ሆነ ሕይወታቸው ሲገባ ነው የልባቸውን ሚስጥር የሚረዳላቸው። እርሱ እጆቹን የሚዘረጋላቸው እነርሱን ለመርገም ወይም ለመውቀስ አይደለም፤ ሊያቅፋቸውና ጥማቸውን ሊያረካላቸው ነው። እርሱ ይህን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “... ማንም የተጠማ ቢኖር ወደእኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ የህይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል...” ዮሐ 7፥37-38።

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🌷እኔ ዘላለማዊ ወጣት ነኝ።🌷

ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ገና ወጣት ሳለ ነው። ጌታ ሞቶ የተነሳው የአዋቂነት የእድሜ ደረጃ ውስጥ ሳይገባ በወጣትነት ዕድሜ ነበር፤ ምክንያቱም እርሱ ወጣቶችን ይወድ ስለ ነበር ነው። እርሱ ህዝቦቹ ሁሉ የወጣትነትን ህይወት በወጣት መንፈስና ልብ እንዲኖሩት ይፈልጋል። በመጸሐፍ “ጎልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።” (መዝ 102፥5) ተብሎ ተጽፏል።

⬜️️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️️⬜️⬜️⬜️

ዘላለማዊው የእኛ ክርስቶስ ውስጣችንን ወጣት ያደርግልን ዘንድ መንፈስ ቅዱስን አድሎናል። እርሱ የተሽመደመደ ልጅነትን ወይም የጃጀ ድካምን እንድናለፍ ፈጽሞ አልፈቀደም። ይልቁንም የማይቋረጥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዲኖረን አደረገ እንጂ። “የጎበዛዝት ክብር ጉልበታቸው ናት፤ ...” ምሳ 20፥29

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

የክርስቶስ ደቀ መዛሙርትና ሐዋርያት የኖሩት ድካምንና መከራን ሁሉ ድል በነሣ ብርቱ የወጣትነት መንፈስ ነው።

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

“ጎበዞች ሆይ፤ ብርቱዎች ስለሆናችሁ፤ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር፤ ክፉውንም ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።” 1ኛ ዮሐ 2፥14

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።” ፊልጵ 4፥13

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

“ ....... ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፤ .....” 2ኛ ጢሞ 4፥17

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

“ሞት ሆይ፤ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፤ ድል መንሳትህ የት አለ?” 1ኛ ቆሮ 15፥55

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

የእኛ ጌታ “ ... ድልም እየነሣ ወጣ፤ .... ” ራእ 6፥2 ተብሎ ተጽፎለታል። እርሱ እጅ ሰጥተው በቃሬዛ ላይ ተሸክመው እየተጫጫሁ የሚወስዷቸውን የደከሙ ወጣቶች አይፈልግም። ጌታ እነዚህን ወጣቶች እንዲህ በማለት ነው የሚጠራቸው፦ “ ..... አንተ ጎበዝ፤ እልሃለሁ ተነሣ።” ሉቃ 7፥14

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

ሰማያዊው የእኛ ሙሽራ ቤተ ክርስቲያኑ እንዲህ በመንፈስ ቅዱስ ሕያውና ብርቱ ሆና ማየት ነው የሚፈልገው። እርሱ ቤተ ክርስቲያኑ ያለ ማቋረጥ ወጣት ስትሆን አንድ ወጣት የወጣትነት ሚስቱን ሲያገባ የሚደሰተውን ያህል እርሱም በእርሷ (በቤተ ክርስቲያን) ይደሰታል። ምሳ 5፥18
እርሱ መላእክቱን ለአገልግሎት ወደ እርሷ በመላክ ልቧን በሚታደስ ሕይወት ደስ ያሰኛታል። ያ ስጦታ ደግሞ የእርሱ ትንሣኤ ነው። ይህን ያደረገውም ወደ መቃብሩ ሲገቡ ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በስተቀኝ በኩል ተቀምጦ ለተመለከቱት ሴቶች እንዳደረገው ጎልማሳ በስተቀኝ በኩል ተቀምጦ ለተቀመጡት ሴቶች እንዳደረገው ነው፤ ማር 16፥5 ። እነዙህ ወጣቶች የእርሱን ትንሣኤ አብስረዋል፤ ሐዋርያቱ የተነሣውን ክርስቶስ እንዲመለከቱ ወደ ገሊላ ይወጡ ዘንድ እንዲነግሯቸው በእርሱ ተልከዋል።

ታድሮስ ያ ቆብ ማላቲ (የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባት)

ይቀጥላል............

🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄
🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄

🌷ከብጹዕ አቡነ ሺኖዳ አንደበት🌷

👉"አስታውስ"👈

🍇 ደካማነትህን አስታውስ ፣ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ
በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም፡፡
@ORTHODOXFAITH
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🍇 የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ ፣ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል፡፡ በእግዚአብሔር
ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል።
@SPIRTUALITY
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🍇 የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ ፡፡
የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ
ይገባሃልን?

የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል፡፡

ሞት እንዳለ አስታውስ ፣ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ፡፡

̋̋̋ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው፡፡˝ መክብብ 1፡14 ማለትን ትረዳለህ።
@mnenteyiklo
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🍇 በእግዚአብሔርፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ ፣ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና።
@ORTHODOXFAITH
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🍇 ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ። በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ
ይሆናል፣ ስለዚህም
በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣ "በዋጋ ተገዝታችኋልና" 1ኛ ቆሮ.6:20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።
@SPIRTUALITY
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🍇 በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ።
@mnenteyiklo
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🍇 በዚህ ዓለም እንግዳመሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ
ዘወትር አስታውስ። ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ።
@ORTHODOXFAITH
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🍇 በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ። ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ
የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና።
@SPIRTUALITY
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🍇 ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ፣ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ።
@mnenteyiklo
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🍇 የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ።
እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል።
@ORTHODOXFAITH
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

🍇 የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ። በውስጥህ
ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን። ዘወትርም ቅዱስ
የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን፡፡

⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
@ORTHODOXFAITH⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️@SPIRTUALITY ⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️ @mnenteyiklo ⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄
🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄


🌷የአባቶች ምክር🌷

🍇"ብቸኝነት የሚሰማን ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ስንርቅ ነው"!!!

🍇☞«ሰው የለኝም፤» በማለት በተሟጠጠ ተስፋ ይህንን ቃል የተናገረው መጻጉዕ ነው።(ዮሐ 5፥7)

🍇►"ወዳጄ " አንተም እንደ መፃጉዕ በዙርያህ ሰው አጥተህ ሰው የለኝም ብለህ ተስፋ ቆርጠህ ይሆናል ።

🍇►የሚቀርብህ ሁሉ ያለህን ነገር ብቻ አይቶ እንደሚጠጋህ አውቀህ የልብ ወዳጅ በማጣትህ አዝነህ ይሆናል።

🍇►ብትወድቅ ቀና የሚያረግህ ብትደናቀፍ ከልቡ እኔን የሚልህ የልብ ጓደኛ የለኝም ትል ይሆናል።

🍇►ትናንትና በሰርግህ ላይ ነጭ ለብሰው ካንተ ጋር "ሲዘምሩ" የነበሩ ሰዎች ዛሬ በለቅሶክ ላይ ብን ብለው
ጠፍተው ከሰው ተስፋ እንድትቆርጥ አድርገውክ ይሆናል።

🍇►ትናንት አጀቢ የበዛልህ ሰው ዛሬ ብቻህን ቆመህ ይሆናል።

🍇☞ወንድሜ በዚህ አትደነቅ ።

🍇ከክርስቶስ እጅ እንጀራና አሳ በበረከት ሲበሉ የነበሩ ሰዎች መች በ"መስቀሉ" ቀን ከእርሱ ጋር ቆሙ።

🍇ውሃው ወደ ወይን ጠጅ ሲቀየር በሰርጉ ላይ ነበሩ፤ ደሙ ሲፈስ ግን በቀራኒዮ አልነበሩም ።

🍇☞ታዲያ ህይወት ለሰጣቸውና ለሞተላቸው ምግበ ነፍስ
ምግበ ስጋ ለሰጣቸው ለክርስቶስ ያልሆነ ሰው ላንተ ይሆናል ብለህ ታስባለህ? በፍፁም አይሆንም !!

✅ሰው ሸንበቆ ነው ከተደገፍከው ይሰበራል ።

✅ተሰብሮም አይቀርም ይወጋሀል ።

🍇☞ወንድሜ ያንተም ነገር ይሄ ነው !!

★ወዳጆችህ ቀን አይተው ቢከዱህ፣

★ዘመዶችህ ማጣትህን አይተው ገሸሽ ቢያረጉህ፣

★ብቻህን ከራስህ ጋር ብትቆም አትደነቅ።

🍇☞ ግን በዚህ መካከል አንድ ነገር አስተዉል:-

🔷ጊዜን አይቶ የማይከዳ፣

🔷በሁኔታዎች የማይለዋወጥ፣

🔷ሁል ጊዜ ሰው ለሌላቸው ቀድሞ የሚደርስ፣

🔷የጭንቅ ቀን ባለ ውለታ፣

🔷የቁርጥ ቀን ወዳጅ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው።

🍇☞ እርሱ ካንተ ጋር መሆኑን ካመንክ ሰው የለኝም እያልክ የምታንጎራጉረው መዝሙር ግጥሙም ዜማውም ይቀየራል !!!

<> <> <> <> <>

🔰ወዳጄ፦

🍇☞ወደ ዋላ ተመለስና ታሪክ አጥና ፦

1⃣ዮሴፍን ወንድሞቹ ሸጠውት ወደ ግብፅ ሲወርድ ሰው አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን በጌታው በጲጥፋራ ቤት ከፍ ከፍ አደረገው።

2⃣በጌታው ሚስት ተንኰል ወደ ወኅኒ ቤት በተወረወረ ጊዜም ሰው አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን ከወኅኒ
ቤት አውጥቶ በባዕድ ሀገር ገዥ አደረገው።

3⃣ሙሴ በሕፃንነቱ ወንዝ ዳር ሲጣል ሰው አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን ከተጣለበት አንሥቶ በፈርዖን ቤተ
መንግሥት፥ የንጉሥ የልጅ ልጅ ተብሎ እንዲያድግ አደረገው። (ዘፍ 39፥1-23፤ 41፥1-50።)

4⃣ብላቴናው ዳዊት በኃያሉ በጐልያድ ፊት በቆመ ጊዜ ሰው አልነበረውም፥ ከወንጭፉ በስተቀር መሣሪያም አልነበረውም፥ እግዚአብሔር ግን ጐልያድን በአንዲት ጠጠር ግንባሩን ፈርክሶ ጣለለት።( ዘጸ 2፥1-10)

5⃣ዳንኤልና ሠለስቱ ደቂቅ ተማርከው ወደ ባቢሎን ሲወርዱ ሰው አልነበራቸውም፥ እግዚአብሔር ግን ጥበብን ሰጥቶ በባቢሎን ጠቢባን እና አውራጃዎች ላይ እንዲሾሙ አደረጋቸው። (1ኛሳሙ 17፥35-55።)

6⃣በሰዎች ተንኰል፥ ሠለስቱ ደቂቅ ወደ ዕቶነ እሳት፥ ዳንኤል ደግሞ ወደ አናብስት ጉድጓድ በተጣሉም ጊዜ
ሰው አልነበራቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ቅዱስ ሚካኤልን እና ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አዳናቸው። (ዳን 1 እና 2፤ )

7⃣አልዓዛር በሞት ተይዞ፥ ተገንዞ፥ ወደ መቃብር በወረደ ጊዜ ሰው አልነበረውም፤ ጌታ ግን ከመቃብር አወጣው። (ዳን 3፥24፣6፥6 )

8⃣ቅዱስ ጴጥሮስ በሰንሰለት ታስሮ ወደ ጨለማው ወኅኒ ቤት ሲወረወር ሰው አልነበረውም፥ ጌታ ግን መልአኩን ልኰ ከወኅኒ ቤት አወጣው።(ዮሐ 11፥28-34)

9⃣ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ ወደ ወኅኒ ቤት ተወርውረው፥ ከግንድ ጋርም አጣብቀው ሲያስሯቸው ሰው አልነበራቸውም። (የሐዋ 12፥1-11)

🍇►በመንፈቀ ሌሊትም ይጸልዩ፥ እግዚአብሔርንም በዜማ ያመሰግኑ ነበር።

🍇►ጌታም የእግር ብረቱን፥ የእጅ ሰንሰለቱን ፈትቶ፥ በሩንም ከፍቶ አውጥቶአቸዋል።(የሐዋ 16፥16-30።)

<> <> <> <> <>

🍇☞ታዲያ ወዳጄ ይህ ላንተም ነው ። ይህ ህግ ዛሬም በህይወትህ ዉስጥ ይሰራል ። ብቻህን አይደለህም ።

🔶ዘመድ ላይኖርህ ይችላል ታማኝ ጓደኛ ላይወጣልህ ይችላል

🔶እናት ወይም የስጋ አባት ላይኖርህ ይችላል

🍇ግን ከሁሉ በላይ የሆነውን ወዳጅ ፣ ዘመድ ጓደኛ የሚተካ ፤ ከሁሉ በላይ ሆኖ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ የሆነ ወዳጅ "አባት" አለህ!! በዚህ ኩራት ይሰማህ !!!

🍇ክብር ምስጋና ለዚህ ጌታ ለአባታችን ለፈጣሪያችን ለአምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ይሁን !!(አሜን)

[☞ወስብሐት ለእግዚአብሔር☜

ሐቴርሳታ
🌅🌄🌅🌄🌅🌅🌄🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄
🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄

🌷"እናንተ ደካሞች…"🌷

# በቅዱሰ .ዮሐንስ አፈወርቅ #

👉እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-

✅“እናንተ ኃጢአት ሸክም የሆነችባችሁ፣
✅እናንተ ጭንቀት አላኖር አላስቀምጥ ያላችሁ፣
✅እናንተ ሐዘን የደቆሳችሁ፣
✅እናንተ ትእዛዛቴን በመተላለፍ ቅስማችሁን የተሰበራችሁ፣
✅እናንተ በሐፍረት ካባ ተከናንባችሁ የምትቆዝሙ፣
✅እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ አበቃልኝ በቃኝ ብላችሁ
ያንገሸገሻችሁ፣
✅እናንተ ለመናገር እንኳን ድፍረት ያጣችሁ…

🍇ምንም እንኳን ዝሙት ብትሠሩም፣
🍇ምንም እንኳን ዋሽታችሁ ቢሆንም፣
🍇ምንም እንኳን ሰርቃችሁ ቢሆንም፣
🍇ምንም እንኳን መናገር የማትችሉት ከባድ የምትሉት ኃጢአት ብትሠሩም፣
🍇ምንም እንኳን “ከእንግዲህ ወዲህ በቃ እግዚአብሔር ይቅር አይለኝም” ብትሉም

💗የእኔ ፍቅር፣ የእኔ ቸርነት

🔷ይህን ሁሉ ኃጢአታችሁን
🔷ይህን ሁሉ ሸክማችሁን
🔷ይህን ሁሉ ሐዘናችሁን
🔷ይህን ሁሉ ከባድ የምትሉትን ነገራችሁን መደምሰስ የሚችል ነውና ኑ፡፡

👊# ኑና ላሳርፋችሁ፤

🔶ኑና ስለ እናንተ የቆሰለውን እጄ ተደገፉ፤
🔶ኑና ፍቅሬን ቅመሱ፤
🔶ኑና ቸርነቴን አጣጥሙ፤
🔶ኑና ሸክማችሁን ሁሉ በእኔ ላይ አራግፉ፡፡

👉ብቻ እናንተ ፈቅዳችሁ ኑ እንጂ ከእኔ አቅም በላይ የሆነ ሸክም የለባችሁምና አትስጉ፡፡

🔶ኑና ሥርየተ ኃጢአትን ልስጣችሁ፤
🔶ኑና ዕረፍተ ነፍስን ሰጥቼ ላሳርፋችሁ፤

👉# ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንኳ እንደ አመዳይ አነጻላችኋለሁ፤
እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ አጠራላችኋለሁ፡፡

👉# ስለዚህ ኃጢአታችሁን እየቆጠራችሁ ከምትቆዝሙ ቀና
በሉና ወደ እኔ ኑ፡፡

👉እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና ልጆቼ ወደ እኔ ቅረቡ፡፡ እኔም ልቅረባችሁ፡፡ “ቀንበሬን ተሸከሙ” ስላችሁ በሩቁ አትፍሩኝ፡፡ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና፡፡

👉# ደግሞም ይህ ቀንበር አንገታችሁን ለማለዘብ (ለመላጥ) ሳይሆን በቀጭኒቱ መንገድ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳትሉ
እኔ ወዳዘጋጀሁላችሁ ርስት መንግሥት የምታደርስ ናትና በሩቁ አትፍሯት፡፡

👉#ስለዚህ እናንተ ደካሞች፣ እናንተ ዓቅመ ቢሶች፣ እናንተ ከእኔ ውጪ ምንም ማድረግ የማትችሉ በገዛ ደሜም
የገዛኋችሁ ልጆቼ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ማዳን ብቻ ሳይሆን አሳርፋችኋለሁ፡፡”

ሐቴርሳታ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@SPIRTUALITY
@SPIRTUALITY
🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄
🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄

🌷በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ🌷

ክብርና ምስጋና ለስሙ ይሁንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “በአረጀ ልብስ አዲስ ዕራፊ የሚያኖር የለም መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና” ሲል ተናግሯል። /ማቴ 9፥16 ፣ ማር 2፥21/

በውስጡ አሮጌው ሰው ያለው ማንም ቢኖር አሁንም ገና የጥምቀት ጸጋ ያልተቀበለ ነው፤ ምክንያቱም በጥምቀት አሮጌው ሰው ተሰቅሏልና ። /ሮሜ 6፥6/ ስለዚህ በዳግም ልደት በመታጠብ በመንፈስ ቅዱስም በመታደስ የሆነ አዲስ ልደት የተወለደ ነው። /ቲቶ 3፥5/

ስለዚህ አሮጌው ልብስ በዚያ ሰው የነበሩ ነገር ግን አሁን ያላስወገድናቸውን የኃጢያት ልማዶችን ይመስላል። በውስጡ አሁንም ዓለምን የመውደድ ቅሪት፣ ሀብት ንብረትን መውደድ፣ ኃጢያትን የመውደድ ቅሪት አሉበት። ከእነዚህ ቅሪቶች ጋር ሆኖ ከክርስቶስ ህብረት ሊኖረው አይሽልም። ካልሆነ ግን አዲስ መልካም ሥራው በአሮጌ ልብስ ላይ አዲስ መጣፊያ ይሆናል።
እዚህ ላይ በትንቢተ አሳይያስ መጽሐፍ በመጀመሪያው ምዕራፍ የተጠቀሰውንና በኃጢያት ከሚኖሩ ሰዎች ጋር አምልኮና የአምልኮ ሥርዓትን መፈጸምን እግዚአብሔር ሲከላከል እንዲህ ማለቱን እናነባለን “ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ሥር አስወግዱ” /ኢሳ 1፥11-16/ እጃቸው በደም የተሞላ እነዚህን ሰዎች የሚቃጠል መሥዋዕታችሁ የሃይማኖት ሥርዓታችሁ፣ በዓላትን ማክበራችሁ ለዚያም መጨነቃችሁ ጥቅሙ ምንድን ነው? ብሏቸዋል። ያን ልታገሳችሁ አልችልም ይላቸዋል። ምክንያቱም ሃይማኖት አዲስ ዕራፊ በደም በተበከለ ኃጢያት ልብስ ላይ ማስቀመጥ ነውና።

እግዚአብሔር በኃጢያት የተጨማለቀ /የተበከለ/ ልብ ያለውን ሃይማኖተኛ የሚመስል የሐሰት ገጽታን አይፈልግም። ለዚህም ነው “እጆችህን በዘረጋህ ጊዜ ዓይኖቼን ከአንተ እሰውራለሁ፤ ብዙ ጸሎትን ብታቀርብ እንኳ አልሰማህም፤ እጆችህ በደም ተሞልተዋልና” ያለው። ዳግመኛ እንዲህ አለ። “የክፉ ሰው ጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ጸያፍ ነው” ምክንያቱም እግዚአብሔር ከንጹሐ ልብ የሚወጣ ጸሎትን ይወዳልና። ነገር ግን እጆቻቸውን በደም የበከሉ ለጸሎት ቢቆሙ እግዚአብሔር ጸሎቱን አይሰማም።

ሌላው ምሳሌ በፈሪሳዊና በቀራጩ ጸሎት ውስጥ የምናየው ነው። ፈሪሳዊው ጻድቅ እንደሆነ በራሱ አምኖ ነገር ግን በትዕቢት በመፍረድ፣ ራስን ከፍ ከፍ በማድረግ የተሞላ ሆኖ በጸሎት ያለው ሌላው ቃል እንዳለ ሆኖ እንዲህ ማለቱን ግን እናነባለን “እግዚአብሔር ሆይ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ ቀማኞችና አመጸኞች አመንዝሮችም ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላሎንሁ አመሰግንሃለሁ” /ሉቃ 18፥11-12/ እግዚአብሔር በአሮጌው ልብስ ያደረገውን አዲስ መጣፊያ ሁሉ አልተቀበለም። ለዚህም ነው በንስሐ በጸጸት ውስጥ ያለውን ትሑቱን ቀራጭ የመሰለ የጽድቅ መቅደስ ያልተወው።

ሌላው ምሳሌ የአስቆሮቱ ይሁዳ ነው። እርሱም አዱስ መጣፊያ ከሆነው ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር መጓዙን ከከሃዲነት፣ አሳልፎ በመስጠት ከተመላ ልብ፣ ከስርቆትና ገንዘብን በመውደድ ጋር ይዞ ነበርና። ነገር ግን ይህንን ክፋት ሁሉ ከአዲስ መጣፊያ ኋላ ሰውሮት ነበር፣ እርሱ ከዐሥሩ ሁለቱ አንዱ ሆኖ አጋንንትን ሁሉ የማውጣት ሥልጣን ተሰጥቶት ነበርና።

ሌላው ምሳሌ ደግሞ ሐናንያና ሰጲራ ናቸው። /ሐዋ 5/ እነርሱም ገንዘብን ይወዱ ነበር። ስለ ገንዘብ ፍቅር ሁሉ ሲዋሹ የማይጨንቃቸው ነበሩ። ያመኑት ሁሉ ያላቸውን ሽጠው የሽያጭ ዋጋውን በሐዋርያት እግር ሥር ሲያስቀምጡ አዩ። ይህ መልክ እንዲኖራቸው እነርሱም ፈለጉ። ይህን አዲስ መጣፊያ ግን በአሮጌው ልብሳቸው ገንዘብን በመውደድና በሐሰት ላይ ማስቀመጥ ፈለጉ። ስለዚህ ያላቸውን ሸጡ። ነገር ግን ከሸጡበት ዋጋ ከፊሉን ግን አቀረቡ፣ ሁሉንም የሽያጩን ዋጋ ያቀረቡ መስለው በሐዋርያትም እግር ሥር አስቀመጡ።

ቅዱስ ጴጥሮስ ግን የሐሰት ሥራቸውን ገለጠ። መንፈስ ቅዱስን አታለዋልና በእግሩ ሥር ወደቁ፣ ተቀሰፉም። የእነርሱ ምጽዋት ለእነርሱ ምንም ጥቅም የማይሰጥ በአሮጌ ጨርቅ ላይ አዲስ መጣፊያ ነው። ይህ ኃጢያትንና ሐሰትን በያዘ ልብ የሚታይ የተጭበረበረ መንፈሳዊነት ገጽታ ነው።
ይህ ደግሞ ክርስቶስን በእንግድነት በቤቱ መጥራት የሚፈልግ መልክ የነበረውን የፈሪሳዊን ስምዖን ታሪክ ያስታውሰናል። በውስጡ ግን ክርስቶስን አይወደውም። ይልቁንም ሊያገኘው፣ ሊታዘበው በእርሱም ላይ በደልን ያገኝ እንደሆነ ይፈልግ ነበር እንጂ። ስለዚህም ክርስቶስን ወደ ልቡ ሳይሆን ወደ ቤቱ ጋበዘው።

ያቺ ኃጢያተኛ ሴት በመጣች ጊዜ፤ በእንባዋም እግሮቹን ማጠብ በጀመረች ጊዜ በጸጉሯም ስታደርቅ ባያት ጊዜ ፈሪሳዊ እውነተኛ ማንነት መውጣት ጀመረ። በልቡም “ይህስ ነቢይ ቢሆን ይህቺ የምትዳስሰው ማን እንደሆነች እንዴትስ እንደነበረች ባወቀ ነበር” አለ። /ሉቃ 7፥39/ ለዚህም ነው ጌታችን በአሮጌው ጨርቅ ላይ ያረፈውን አዲስ መጣፊያ የሆነውን ፍላጎቱን መግለጽ የጀመረው። ለስምዖንም ከእርሱ ይልቅ ኃጢያተኛዋ ሴት እንደምትሻል ጌታን በመጋበዝ አዲስ መጣፊያ የሰወረውን ብዙ ኃጢያቱን አሳየው።

የፈሪሳዊው ስምዖን ታሪክ በልቡ እውነተኛ ፍቅር ሳይኖረው ነገር ግን በጥሩ ቃላት ወይም ደብዳቤ ባልንጀራውን እንደሚወደው የሚገልጽ ሰውን ያስታውሳል። እንዲህ ያሉ ሙከራዎች ሁሉ አዲስ ቁራጭ ጨርቅን በአሮጌ ልብስ ላይ እንደመጣፍ የሚቆጠሩ ናቸው።

ይህ ነገር አሁንም ደግሞ ሌላ ምሳሌን ያስታውሰናል። አገልግሎቱንና የሚያገለግለውን መንጋ የሚያፈቅርን የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ፣ በአገልግሎት ስም መታወቁ፣ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎቱ ባለዝና መሆኑ እዚህ ላይ አዲሱን መጣፊያ ሆኗል፤ ይህ ግን በአሮጌ ልብስ ላይ ያረፈ ነው፤ ለእግዚአብሔርና ለሕዝቡ ፍቅር አጥቷልና።

ሌላው ምሳሌ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቅ ብሎ በጠራው በሎጥ ሕይወት ውስጥ አይተነው የነበረ ታሪክ ነው። እርሱ ከአባታችን እግዚአብሔር “አንተ የተባረክ ነህ” ካለው አብርሃም ጋር ለመኖር የሚወድበት መልክ ነበረው። በውስጡ ግን የለመለመውን መስክ፣ የእግዚአብሔር ገነት የሚመስለውን ምድር የግብፅንም ማራኪ ምድር የሚመስለውን ሥፍራ ከአባታችን ከአብርሃም መለየትን እስኪመርጥ ድረስ ወዶታል። /ዘፍ 13፥10/ ስለዚህም ከክፉዎች የሰዶም ሰዎች ጋር መኖርን መረጠ። ስለዚህ ጻድቁ ሰው በእነርሱ መካከል ሲኖር የእነርሱን ሕግ የለሽ ተግባር በማየትና በመስማት ነፍሱን ያስጨንቅ ነበር። /1ጴጥ 2፥8/
በዚህም ከአብርሃም አባት ጋር የሚኖርበትን እንኳን አዲስ እራፊ ጨርቅ አጣ፤ የሰዶም ምርኮኛ ሆኖ ተሰጠ። አብርሃም በምልጃው ቢያድነውም ዳግም ወደ ሰዶም ተመልሷልና በሰዶም ጥፋት ጊዜ መልአኩ ከሰዶም እንዲለቅ እስኪያደርገው በዚያ ነበር። /ዘፍ 19/

ሌላው ምሳሌ ደግሞ ኃጢያቱን የሚያምን ነገር ግን ንስሐ የማይገባ ሰው ነው። የዚህ ማስረጃ እንደ አመነ ወደ ንስሐ ከመግባት ይልቅ ካመነ ከተናዘዘ ሥጋውንና ደሙን አዲሱን መጣፊያ ከተቀበለ በኋላ አሮጌውን ልብስ ወደ ንስሐ ሕይወት አለመግባት ወደዚያም አለመድረስ ላይ አስቀምጧል። አሮጌው ሰው መንፈሳዊ መልክ በማስመሰል ብቻ ይዞ በአሮጌነቱ ጸንቷል።

ይህም ራሱን በወንድሙ ፊት ዝቅ እንደሚያደርግ ነገር ግን ጥፋት ስሕተት ለመሥራቱ እውነተኛ ስሜት ጸጸትም የሌለበትን ሰው ይመስላል። ለወንድሙ ይለዋል “ወንድ
ሜ ሆይ በእኔ ተቆጣህ? አሳዘንኩህ?” ይህ በአፍኣ ያለ ገጽታ ብቻ ነው። በአሮጌው ልብስ ላይ አዲስ መጣፊያ የሆነው ስሕተት መሥራቱን አለማመኑ ነው።

ስለዚህ ከህሊና /ልብ መታደስ የተነሣ በአፍኣም የሆነ መታመንን ለማግኘት ሰው ውስጡ መለወጥ አለበት። /ሮሜ 12፥12/ ይህም ማለት አስቀድሞ አእምሮውን ማደስ አለበት። በዚህ ምክንያት ልቡናው ሁሉ ይታደሳል። እንዲህ ሲሆን ልቡናው አሮጌ ልብስ መሆኑ ይበቃል። ያለጥርጥር እንደ አዲሱ ልብስ ይሆናልና።

ስለዚህ ከዚህ በኋላ ይቅርታም ሲጠየቅ ከልቡ ይሆናል፤ ስሕተትን ክፋትን ሠራሁ ብሎ ሲናገርም ለመናገር ብቻ ብሎ ሳይሆን ከልቡ ከስሜቱ ሥር በመነጨ ይላልና።

ሲጸልይም በአፉ ብቻ ቃላትን ከመናገር ባለፈ ከልቡ ሥር ይጸልያል፤ ይጮኻልና። ከስሜቱም ሁሉ በመነጨ። ካልሆነ ግን እግዚአብሔር “ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው” በማለት የገሰጻቸውን ወገኖች ይመስላል። እንዲህ ያሉት አዲስ ዕራፊ ጨርቅ ባሮጌ ልብስ ላይ ይሆናሉና ተቀባይነት የላቸውም።

ሌላው ምሳሌ ደግሞ ልቡ ዓለምን ከመውደድ ያላቆመ ሰው ነው። እንዲህ ያለ ሰው ምንኩስና ለዓለም ሙት መሆን ሆነ ሳለ ወደ ምንኩስና ሥርዓት ውስጥ ሊገባ ይችላል። ይህ ሰው ልቡ ከምንኩስና ሕይወት ተለይቶ ሳለ በምንኩስና ሥርዓት አዲስ መጣፊያ ለይ ዐረፈ። አዲስ ስም ወስዶ አዲስ መልክ ወሰደ። ነገር ግን ምንኩስና ስም አይደለም። መልክ ወይም ልብስ አይደለም። ይህ ሁሉ ግን አዲሱን መጣፊያ በአሮጌ ጨርቅ እንደ ማድረግ ሆኗል። ምክንያቱም ልቡ ከዓለም ከምኞቱ አልተቆጠበምና።

ይህን በጾም ሥርዓት ውስጥም እናየዋለን። በእርግጥ ጾም የአትክልት ምግብ መብላት ብቻ ነው? ወይስ አትክልት መብላት ከክፋት ከመጠበቅና ራስን ከመግዛት ተለይቶ የሚታይ አዲስ መጣፊያ። ስለዚህ አፋችን ሲጾም ምላሳችን መጾም አለበት። ከክፉ ነገርም መጠበቅ አለበት። ልቡናው ከክፉ ምኞት ሁሉ፣ ስሜቶቹንም አግባብ ካልሆኑ ነገሮች ሁሉ መቆጠብ አለበት። እንዲህ ካልሆነ ግን ጾሙ በአሮጌ ልብስ ላይ አዲስ መጣፊያ ይሆናል።

አዲሱን መጣፊያ በአሮጌ ልብስ ላይ ካላስቀመጡ ሰዎች መካከል ንጉሥ ሳዖል ሊጠቀስ ይችላል። እርሱ ለእስራኤል የተቀባ የመጀመሪያው ንጉሥ ነው። እግዚአብሔርም ሲንቀው የታየ የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ ነው። /1ሳሙ 16፥14/ ቅዱስ ቅባት ተሰጥቶት ነበር። ትንቢትን እንደ ነቢያት የተናገረ ስለራሱም “ሳዖል ከነቢያት አንዱ ነውን?” ብሎ የተናገረ ነው። /1ሳሙ 10፥11/ እነዚህ ሁሉ አዲስ ዕራፊዎች ግን በትዕቢት በተሞላ፣ ከአንድ ጊዜ ባላይ ሊገድለው ዳዊትን በፈለገበት የመራራ ጥላቻ ጨርቅ ላይ አድርጓቸዋል።

ቅዱሱን ቅባት ተቀበለ፤ ቅዱሱን ሥራ ግን ከልቡ ጣለ። በዚህም ምክንያት በእግዚአብሔት ተጣለ። ነቢዩ ሳሙኤል ለሳዖል ባለቀሰ ጊዜ እግዚአብሔር “እስሥራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳዖል የምታለቅስለት እስከመቼ ነው?” ሲል ተናገረው። /1ሳሙ 16፥1/

ሌላው ምሳሌ ደግሞ በአምልኮ ሥርዓት ውስጥ የሚታይ ነው። ይህም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቆሞ ዳዊት እንደሚደግም ውዳሴ እንደሚያደርስ ነገር ግን በውስጡ ስሜትና መንፈስ የሌለበት ሰው መሆን ነው። እንዲህ ያለው ሰው ከዝማሬው ከውዳሴው ያገኘው ጥቅም የለም፤ ነፍሱ ከዜማ ምቱ ጋር አብራ አልተራመደችምና።
ወይም በካህን የተባረከ ነጭ ልብሰ ተክህኖ የለበሰ፣ በመሰዊያ ፊት የቆመ ዲያቆን ቢሆን ነገር ግን መሰዊያውን የሚያከብር በውስጡ ለትሕትና ለየዋህነት ግድ የሌለው፤ ከጸሎት ይልቅ በሌላ ብዙ የዓለም ሐሳብ ራሱን የወጠረ ቢሆን፤ በልብ ንጽሕና ምሳሌ የሆነው ይህ ነጩ ልብሰ ተክህኖ በዚህ ጊዜ ምንድን ነው? በዚህም አገልጋይ ሕይወት ውስጥ የምናየው አዲሱን ዕራፊ መጣፊያ በአሮጌ ጨርቅ ላይ ሆኖ ነው።

ስለዚህ በውስጡ የልብ ንጽሕና ያለው እግዚአብሔርን የሚወድ በአፍአም እግዚአብሔር የሚከብርበት መልካሙ ሥራ ያለውን ሰው እንፈልጋለን።

የኤልኬራዛ በረከቶች

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄🌅🌄
🌼🍀መንፈሳዊ ንግድ 🍀🌼

🍃 መንፈሳዊ አካለ መጠን የሚፈተሽበት ፣ ክብረት ሚፈልቅበት የኁልቆ ዘመን መጠይቅ ፣ የፊቱ ሥእል ባለበት ድንኳን ፊት ሞገስን ገንዘብ የምናደርግበት ኃይል ፣ በባእለ ፀጋው ፊት የምናዜመው ብል የማይበላው ፣ ነቀዝ የማያበላሸው ድምፀ ቃና ፣ ሌቦች ግድግዳውን ምሰው ፣ ናሱን አፍርሰው የማያጠፉት የዘመን ዘመናት áˆ˝áˆáˆ›á‰ľ ፣ ከምግባችን ቆርሰን ለከርሠ ርኁባን አጉርሰን ፤ ከልብሳችን ቀደን ለዘባነ ዕሩቃን አልብሰን ፤ ከመጠጣችን ቀድተን ለጉርዔ ፅሙዓን አጠጥተን ፤ ዳጎስ ያለ ፍቅር የምንሸምትበት የእርካታ አደባባይ ፤ የሰማይ መዝገብ የነፍስ ቀለብ መከማቻ ሙዳይ " ከፈጣሪ ጋር የሚከወን መንፈሳዊ ንግድ " የሆነውን የምፅዋት ግብይት እንዲህ እንቋደስ ።
:
"እልፍ ከሲታዎች ቀጥነው የሞገጉ
ሥጋችን የት ሔደ ብለው ሲፈልጉ
አስሰው (2×) በምድር በሰማይ
ቦርጭ ሆኖ አገኙት አንድ ሰው ገላ ላይ"
                    ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም
:
🌼 ተካፍሎ ከመራዳት ፣ ላጡ ከማበርከት ፤ የራስ ላይ ደምሮ ድርሻን ማስፋት ፣ ኑሮዬ ይበቃኛል አለማለት የህይወት እርምጃ ሳህናችን ላይ የነገሠ ማዕድ ሆኗል ። ለከሱት መጠገኛ ፣ ላዘኑት መፅናኛ ከሚሆን ፤ ለቦርጫችን ማፅኛ ፣ ለኁልቆ ቢስ ምኞታችን መከወኛ ቢሆን ባይ ያልሞተ የብቻ ጥቅም አዚም በቀጭን ደም ሥራችን ተነድፏል ። ግራ ቀኝ ከማየት ፣ የልብን አንገት አዙሮ ከመመልከት መሀል ራስን መገንባት ፣ ቀምተን ማስነባት የሠርክ አጀንዳችን ነው ። በመካፈል ውስጥ መጉደልን የሚያጎላ መነፅራችን ዛሬም አልተሰበረም ። በፍቅር ካለው ንፁህ ትርፍ በፍቅር አልቦነት ባለ ሸቃባ ኪሳራ መቆንጠጥ(ቆ ጠብቆ ይነበብ) የህመም ስሜት አይጭርብንም ። ይህ ግጥም በሚንቦገቦግ ብእር ነፍሱን ለወዳጆቹ የሚሰጥ ፍቅር ወልዶህ አንተን ሳይሆን ያለህን ለባልንጀራህ ለማካፈል አትስነፍ áˆ€á‰Ľá‰ľáˆ… የድኾች መዋጮ ነውና አጋራው ብሎ ብርሃናዊ ድምፅ ይጮኻል ።

🌷 እኛ ጋር የተረፈው ዛሬም በፍለጋ ለተሰማሩ ፣ ውሃ ሽተው ድንጋይ ለሚቆፍሩ የጎደለው ነው ።
እኛ የናቅነው ደጋፊ አጥተው ፣ በመቅበዝበዝ ተሞልተው ለሚዳክሩ ምርኩዝ ምሰሶ ነው ። እኛ ቅያሪ ያደረግነው ብርድ ልብስ ፤ ብርድ ለብሰው ለሚያድሩ  የሙቀት ኪዳን ነው ። እኛ የሰለቸን ጫማ ደንጊያ ለሚጥሰው ፣ እሾህ ለሚበሳው እግረኛ ዘመነኛ የምቾት ምንጭ ነው ። እኛ የጣልነው ሎሎች ሊያነሱት የሚናፍቁት የምኞት ጥግ ነው ። እኛን ያሳዘነን ክስተት ሌሎችን በደስታ የሚያረጥብ ቀላየ ፍስሐ ነው ። እኛ የቀረበን ሌሎች የራቃቸው ፣ ተለጥጠው የማይደርሱት የፍለጋ ጣራ ፣ ከዝቅታ የሚያዩት ረጅም ተራራ ነው ።

💦💦ቁራሽ እንጀራ ቢያገኙ እስትንፋሳቸው የሚቀጠል ፣ ህላዌያቸው የሚቀጥል ፤ ጥርኝ ውሃ ቢጠጡ በእርካታ ወደሞት ከሚወስድ ሸለብታ የሚነቁ ፣ በጭላጭ ውለታ ዘለው 'ሚቦርቁ ፣ እንደ አደይ አበባ የሚፈነድቁ ፤ ከአልጋ አውርዶ ከሚባረከው ውሃ የሚጨምራቸው ቢያገኙ በደዌ ዳኛ ከመያዝ ፣ በአልጋ ቀራኝነት ካለመጓዝ የሚፈቱ ፣ ደዌ ሥጋን የሚረቱ ፤ ገፀ ሰብእ ከዋእየ ፀሐይ በላይ ባያቃጥላቸው ፣ ሌሎች መጠቋቆምያ ባያደርጓቸው ፣ በቀትር ፀሐይ ከመቃጠል ፣ በብቸኝነት ከመብሰልሰል የሚድኑ ፤

🌹 መልካም አቀባበል የሚያደርግላቸው ቢኖር በኃጢአት እሳት ከመቃጠል ፣ በፀፀት አዙሪት ከመጠለል ፣ የሚተርፉ ብዙዎች ሳሉ በሁላችን አስተዋፅዖ በተገነባ መሰረተ ፅኑዕ ስንፍና ና ቸልተኝነት የተነሳ ከማይነሱበት ወድቀው ፣ ከማይጠገኑበት ተሰብረው ፣ ከማይወጡበት ገብተው ፣ ከማይፈወሱበት ህመም ዘልቀው እንደሆነ የምናስተውልበት ቅፅበት (ይህ ቅፅበት ማህደሩ ለቅል ነው ከሌሎች ጋ ከመጠቅለል ያረገ ነው ያልተኖረ ዘመንን ይሽራልና ) ለምን ራቀ ? ለመለወጥ የቀጠርነው ነገ የስንት ዲናር መንገድ ነው ? ቆም እንበል ፡ ጠሊቅ ቁጭት ይቆራኘን ፣ የሚጎመዝዝ ወቃሲ ትውስታ በማወቂያችን ሰገነት ላይ ይመላለስ ፤ ወዲህ ቅዱስ የተግባር ውቅያኖስ ያለንን ይዘን ገባር ሆነን እንፍሰስ ያለፈውን በሚመጣው እንካስ !

✝☁️✝☁️✝☁️✝☁️✝

💞 እነሆ መፍትሔ በደጃችን ቆሞ ያንኳኳል ፣ ብንከፍትለት ከኛ ጋራ የፍስሃ እራት ይቆርሳል ፣ ላንዱ ህመም ለሌላው እጦት ይደርሳል ፣ ጣቱን ለነከረ የበረከት ፅዋ ያቀምሳል ፣ ከጎኑ በሚፈልቅ ፣ ተቀድቶ በማያልቅ የሰማይ መዝገብ ጠል አጥንትን ያርሳል ። የነፍስ ቅድስና የመንፈስ ንፅህና ፤ የኅሊና እርካታ የልብ ደስታ ለራቀው ሁሉ እንደ ወሮታ ከፋይ ፣ በረከት አዳይ የአፋልጉኝ ጥሪ ዘውትር ያቃጭላል ።

🍇 ተወዳጆች ሆይ ፡ እስኪ ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ ፣ አዝኖ ከመሻገር የተረፈ ፣ በፍቅር ህዋ የተንሳፈፈ ተጨባጭ ነገር እንሥራ !

🌱 ወንድሜ ሆይ : ጣትህ የዳሰሰውን ኅብስት የሚናፍቅ የተራበ ብጤህ አፍ ፤ የሰላምህ መፍሰሻ áŁ ደስታህ የተቀበረበት ዋሻ ነው ።

🌱 እህቴ ሆይ : ከፀጥታ ጊዜሽ ከፍለሽ ፣ ፅሙናዋ ለደፈረሰ ፣ እንባዋ እንደ ጅረት ለፈሰሰ ባልንጀራሽ አስበሽ ፤ ያልተሰማ ድምጿን የተጋራሽበት ሠርክ ለሥጋሽ መዳን ፣ ለነፍስሽ መጠገን የተጠነሰሰበት የንጋት ወጋገን ነው  ።

🌱 ወንድሜ ሆይ : ዘመኑን በመገፋት የገፋ ፣ በጥልቁ የተከፋ አቻህን ከፍቅር አፎት በተመዘዘ የመፅናናት ሰይፍ ብቸኝነቱን የቦረሽክበት ፣ ስእለ ፍቅርን በልቡ የሳልክበት ቅፅበት ነፍስያህ ዘለዓለምን 'ሚዛመድበት ፣ ልብህ ከፈጣሪ 'ሚወዳጅበት ጣፋጭ ስንቅ ነው ።

🍃እግዚአብሔር ገጸ ምህረቱን ካንተ አላራቀምና ፊትህን ከችግረኛ አትመልስ 🍃 መ.ጦቢ ፬ ፥ ፯
:
"አፍላጋትን እያፈሰሰ ፣ ነፋሳትን እያነፈሰ ፣ ብርሃናትን እያመላለሰ" ፣ ወቅት እያፈራረቀ ፣ ተክል እያፀደቀ ፣ ምድርን በሥነ ፅጌያት እያሸበረቀ ፣ á‰ á‹áŠ“áˆ እያበቀለ ፣ በፀሐይ እያበሰለ ላቆመን በኛ ቅንነት ያልተመረኮዘ መለኮታዊ ደግነቱ ክብር ይሁንና ለታመሙ ፈውስን ፣ ለታረዙ ልብስን ፣ ለተሰደዱ ሰላም መመለስን ለረከሱ ፍፁም መቀደስን ፤ ከማይነፍግ ልግስናው የሚያድል á‰ áˆ°áˆ›á‹Ťá‰ľ ያለ ባዕለ ጸጋ አባታችን ከምግባር ነዳያን የሆንን እኛን በፀጋው የሚያኖረን ፤ አርአያውን ተከትለን ፣ እርሱን መስለን ከብዕል ነዳያን ለሆኑ ምህረት ሥጋዊን ፣ በአእምሮ በእውቀት ነዳያን ከሆኑት ጥበብ እና እውቀትን ፣ ከፍቅር ነዳያን ለሆኑ ወንድማዊ መውደድን እንዳንሰስት ጭምር መሆኑን እንገንዘብ !

🌳 መስቀል ላይ የተሠራ ሰላም ፍሬዎች ነንና ቀዶ ማልበስ ፣ ቆርሶ ማጉረስ ፣ ቀድቶ ማረስረስ ፣ ድጋፍን በሚሻ ዘውግ ፈጥኖ መድረስ ፤ መልካም ንግግር ፣ በጎ ተግባር ፤ ለኔ ያልነውን የፅሙና ጊዜ መሰዋት ፣ የተከዙትን ማፅናናት ፣ የደከሙትን ማበርታት እና በመሰል ተግባራት መትጋት ( መሰል ተግባራት ውስጥ ብዙው አለ ) .... በምፅዋት ጥላ ሥር ያሉ ቅርንጫፎች እንደሆኑ አስተውለን ፣ ከኔነት አጥር የሸሸ ህይወት ተላብሰን እንድንገኝ ነፍሱን የሰጠን አምላክ ያበርታን !

©ዲ/ን ደረጀ ዘለቀ
🌼☘🌼☘🌼☘🌼☘🌼☘🌼☘🌼
#ልጆቼ! የእግዚአብሔር ትእዛዝ እንዴት ቀላል እንደሆነ የምታስተውሉ ሁኑ፡፡ ምክንያቱም ታስሬ አስፈትታችሁኛልና ሳይሆን ጠይቃችሁኛልና፤ ታምሜ አድናችሁኛልና ሳይሆን ጠይቃችሁኛልና፤ ተርቤ በየዓይነቱና ውድ የሆነ መዓድ ሳይሆን አንዲት ዳቦ አብልታችሁኛልና፤ ተጠምቼ በየዓይነቱና ውድ የሆነ መጠጥ ሳይሆን አንዲት ቀዝቃዛ ኩባያ ውኃ አጠጥታችሁኛልና ነው የሚለን፡፡

በጣም የሚያቀለው ደግሞ እነዚህን ቀላል ትእዛዛት በራሳችን ጥረት የምናደርጋቸው አይደሉም፡፡ ምክንያቱም በቃሉ "ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም" ስለሚለን ጸጋ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ አድርገን ነው፡፡ #እንግዲያውስ_ድሀ_ስለሆንኩ_እነዚህን_ማድረግ_አልችልም_ብለን_ራሳችን_ሰነፎች_የምናደርግ_አንሁን_ሺህ_ጊዜ_ደሀ_ብንሆን_ሁለት_ሳንቲም_ከሰጠችው_መበለት_በላይ_ድሀ_ልንሆን_አንችልምና፡፡ ስለዚህ ስንፍናን ከእኛ እናርቅ፡፡

ልጆቼ! እነዚህን በእርሱ እርዳታ ስላደርግንስ ምን እንደምንባል ትገነዘባላችሁን? “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን!” ካላደረግንስ? “እናንተ ርጉማን ከእኔ ዘንድ ሂዱ!” እንግዲያውስ ለእኛ ሳይሆን ለሰይጣንና ለመላእክቱ የተዘጋጀውን እሳት ከሚያገኘን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለእኛ የተዘጋጀውን መንግሥት እንወርስ ዘንድ ዛሬ አብዝተን ዘይት የምንገዛ እንሁን፡፡ እንደነዚያ ሰነፍ ደናግላን እዚያ መግዛት በማይቻልበት ቦታ ሄደን ከምንጠይቅ ዛሬ ሳይመሽብን የሚበቃንን ያህል ዘይት እንግዛ፡፡ #ዘይቱ_የሚገዛውስ_የት_ነው?#የታመሙት_ጋር_እስረኞች_ጋር_ቁርና_ሀሩር_በሚፈራረቅባቸው_ወንድሞቻችንና_እኅቶቻችን_ጋር፡፡

ልጆቼ! እንደ ነዌ እዚህ ምድር ባለጸጎች ሆነን ያኔ ከምንለምን ዛሬ አልዓዛርን ልናስበው ይገባል፡፡

(ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ)

@SPIRTUALITY @SPIRTUALITY
☘☘☘☘🌂☘☘☘🌂☘☘☘☘
#እግዚአብሔርን_የሚያምንና_የሚወድ_ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡

በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡
በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡
መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡

ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡
መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡

ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡
በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡

ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤ ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!

ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
መልካም በዓል!
💐💐💐💐🍀🍀🍀💐💐💐💐
🌅ኦርቶዶክሳዊ_የክርስትና_ሕይወት🌅 pinned «🌼🍀መንፈሳዊ ንግድ 🍀🌼 🍃 መንፈሳዊ አካለ መጠን የሚፈተሽበት ፣ ክብረት ሚፈልቅበት የኁልቆ ዘመን መጠይቅ ፣ የፊቱ ሥእል ባለበት ድንኳን ፊት ሞገስን ገንዘብ የምናደርግበት ኃይል ፣ በባእለ ፀጋው ፊት የምናዜመው ብል የማይበላው ፣ ነቀዝ የማያበላሸው ድምፀ ቃና ፣ ሌቦች ግድግዳውን ምሰው ፣ ናሱን አፍርሰው የማያጠፉት የዘመን ዘመናት áˆ˝áˆáˆ›á‰ľ ፣ ከምግባችን ቆርሰን ለከርሠ ርኁባን አጉርሰን ፤ ከልብሳችን…»
❖ ❖ ❖ #ልዩ_ትንሣኤ ❖ ❖ ❖

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተነሣ ብለን ስንናገር በመነሣቱ ውስጥ ያሉትን ድንቅ ነገሮችን ማወቅ እጅግ መሠረታዊ ጉዳይ ነው። ጌታችን በትንሣኤው ለዓለም የገለጠውን ድንቅ ምሥጢር ዐይናማዎቹ አጥርተው ሲያዩ፣ ውሳጣዊ ዐይናቸው በጥርጥር አፈር የተሞላባቸው ደግሞ ራሳቸውን ወድደውና ፈቅደው ከማሳወራቸው የተነሣ ተሰውሮባቸዋል።

ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጌታችን የትንሣኤ በዓል የበዐላት
ኹሉ በዐል ነውና ሊቃውንቷም እንዲህ ብለው ዕለቲቱን ይሰይሟታል፤ ቅዱስ ዮስጢኖስ ሰማዕት #በዓለ_ፋሲካ ይላታል፤ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
ደግሞ #የድኅነታችን_ቅዱስ_ቀን_በዓለ_ድኅነታችን ይለው ነበር፤ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙም ዕለቲቱን #የዕለታት_ንግሥት_በዓሉንም_የበዓላት_በዓል_የክብራችን_ኹሉ_ክብር_ሲል_ይገልጻቸው_ነበር።(በዓላት በዲ/ን ብርሀኑ አድማስ ገጽ 85)።

💠 💠 @SPIRTUALITY 💠 💠
እስኪ አኹን ደግሞ የጌታችንን ትንሣኤው ልዩ የሚያደርጉትን ነገሮች በጥቂቱም ቢኾን እንመልከት፦

💠 የጌታችን ትንሣኤ የአዳም ሰውነት ፈርሶ እንደገና ታድሶ የተነሣበት ትንሣኤ ነው። በዮሐ 2፥18 "ጌታችን ኢየሱስም 'ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስተኛውም ቀን አነሣዋለሁ' ብሎ
መለሰላቸው። አይሁድም ይህ ቤተመቅደስ በአርባ ስድስት ዓመት ተሠራ አንተስ በሦስት ቀናት ውስጥ ታነሣዋለህን? አሉት። እርሱ ግን ይህን
የተናገረው ቤተመቅደስ ስለተባለ ሰውነቱ ነበር።"ተብሎ ተጽፏል። ይህ ንባብ የሚያስረዳን የአምላካችንን በሦስተኛ ቀን ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ብቻ ሳይኾን የአዳምንም ሰውነት አፍርሶ እንደገና መገንባቱንም የሚያስረዳ ጭምር ነው! ታላቁ ሊቅ አውግስጢኖስ ይሄን ሲተረጉም አርባ ስድስት ቁጥር የሚገልጠው አዳምን ነው ይላል። ADAM(አዳም) የሚለው ቃል በግሪኩ እያንዳንዷን ቀለም ስናስተረጉም A- አልፋ ማለት ነው ያም አንድ ቁጥርን ይወክላል፤ D ዴልታ ማለት ነው ያም አራት ማለት ነው፤ M ሜይ ማለት ነው ያም አርባ ማለት ነው፤ በአጠቃላይ ADAM=1+4+1+40=46 ማለት ነው። በመኾኑም #ይህን_ቤተመቅደስ_አፍርሱት_ማለት_የአዳምን_ሰውነት_አጋንንት_ቢያፈርሱትም_እኔ_የአዳምን_ሥጋና_ነፍስ_ነሥቼ_ሰው_ኾኜለት_የፈረሰውን_ሰውነቱን_አስነሣለታለሁ_ሲል_ነው። ስለዚህ የጌታ
ትንሣኤ አዳምን ከነልጅ ልጅቹ ያስነሣ ትንሣኤ ነው።
🔰🔰🔰 @SPIRTUALITY 🔰🔰🔰

💠2 የጌታ ትንሣኤ ሞትን ያጠፋ ትንሣኤ ነው። ሞት የሰው ሰውነትን በመቃብር ይዞ የማስቀረት ኃይሉ የተሰበረበት፣ ራሱ ሞት መሞቱም የተረጋገጠበት ትንሣኤ ነው። ቅዱስ ቄርሎስም በጌታ ሞት ሞት
ሞተ በማለት የሚደነቀው ለዚህ ነው። ጌታችን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋ ሲለይ ይዞ በጌታችን አማካኝነት ሞተ! በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ሲወርድ መለኮት ተዋሕዶታልና መቃብራትን በአጠቃላይ አለመለማቸው፤ የሚዘራባቸውን የሰውን ዘር የሚሰጡበትን ኃይል ሰጣቸው። አዳም ዕፀበለስን በልቶ በሰው ልጆች ላይ በሙሉ ሞትን ቢዘራ አምላካችን ክርስቶስ ግን አዳም የዘራትን የሞት ዘር ይነቅል ዘንድ የአዳምን ሥጋ ለብሶ ሞታችንን በሞቱ ነቅሎ ዘለዓለማዊነት ዘራብንና
ለዚያም መግቢያ በሩን ትንሣኤው ሰጠን። አኹን ሰው ወደ መቃብር የሚገባው ሊበሰብስ ሳይኾን
ለዘለዐማዊው ሕይወት ሊወለድ ነው። ለ5500 ዘመን በአዳም ምክንያት መካን የኾነችውን መቃብር በጌታችን ምክንያት ወላድ ወደ መኾን ተሸጋገረች! ሞት ኾይ መውጊያህ ወዴት አለ የሚለውንም መዝሙር እንዘምር ዘንድ በቸርነቱ ኃይልን ሰጠን! በመኾኑም የጌታችን ትንሣኤ በሰው ልጆች ላይ ነግሦ ያለውን ሞትን ያጠፋ፣ የመቃብርን ይዞ የማስቀረት ወላድ ያስወገደ የሰው ልጆችንም ሥጋ
ክቡርነት ያረጋገጠ ግሩምና ድንቅ ትንሣኤ ነው።
🔰🔰🔰 @SPIRTUALITY 🔰🔰🔰

💠3 #የጌታችን_ትንሣኤ_ሌላው_ልዩ_መገለጫው "የትንሣኤ ትንሣኤ" መኾኑ ነው። ከጌታችን በፊትም ኾነ በኃላ "ትንሣኤ ተነሥቶ አያውቅም!" ጌታችን ብዙዎችን ከሙታን መካከል አሥነስቷል ለምን ትሉ እንደኾን? እርሱ ትንሣኤ ነዋ! ብለን እንመልሳለን። እጅግ የሚያስደንቀው ነገር እርሱ ራሱ ትንሣኤ ሲኾን ተነሣ መባሉ ነው!!! በዚህ ኹሉ መንገድ የምንረዳው ምሥጢር ጌታችን ተነሣ መባሉ የእኛን መነሣት ማሳያ መኾኑን ነው እንጂ እርሱስ ክብር ምስጋና ለስም አጠራሩ ይኹንና የሚጎድለው ነገር ኖሮ እጠቀም ብሎ አይደለም። እርሱ መነሣት ሳያስፈልገው የተነሣ ነዋ!!! በዮሐ 11፦25 "ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ" ብሏልና። የጌታ ሞቱ የእኛን ሞት ለማራቅ እንደኾነ ትንሣኤውም እኛን ከወደቅንበት የመቃብር ጉድጓድ ሊያነሣን ነው። የሕይወትን መሞትና የትንሣኤን መነሣት ሰምቶ የማያደንቅ ማን አለ? ለዚህም አይደል እንዴ ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው የሚለውን አበው ሲተረጉሙ #ሌላ_አሥነሽ_ሽቶ_የሚነሣ_አይደለም_በእርሱ_ዘንድ_ያለች_እግዚአብሔርነቱ_አሥነሣችው_ማለት_ነው እንጂ የሚሉን። ቃል ከሥጋ ጋር መዋሐዱን ካመንን፤ ቃል የተነሣ እንጂ መነሣትን የሚሻ አይደለምና ቃልነቱ የተዋሐደውን ሥጋ አሥነሣው ማለት ነው። ሞት ወደነበረበት መቃብር ሕይወትና ትንሣኤ እኔ ነኝ ያለ ጌታ ገባና ሞታችንን በሕይወት ተክቶ በስብሶ መቅረትን አጥፍቶ በትንሣኤው በኩል ከምድር ከፍ አደረገን።
🔰🔰🔰@SPIRTUALITY 🔰🔰🔰

💠4 #መጪውንም_ኃላፊውንም_ሕይወት_ያሳየ_ትንሣኤ_ነው። አንድ ታላቅ አባት የዮሴፍን ንጽህና ሲገልጥ የጲጥፋራ ሚስት የዮሴፍን ጃኬት ባወለቀችበት ጊዜ አዳም ጥንት በገነት የነበረው
ዐይነት ንጹህ መኾኑ ታየ እንዳለ የጌታችን ትንሣኤ በቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ገለጻ የሰውን ልጅ መጀመርያና መጨረሻ የሚያሣይ ትንሣኤ መኾኑን ገልጿል። ሰው ጥንቱን ሲፈጠር ምድራዊ ልብስን ሳይኾን ያጌጠው ብርሃናዊውን የጸጋ ልብስ ነበር የለበሰው። ይህን ልብሱን ባለማመንና ባለመታዘዝ ሳያጣው በጌታችን ትንሣኤ ምክንያት እንደሚያገኘው ተስፋ ተሰጠው። ስለዚህ የጌታችን ትንሣኤ አዳም በገነት ልብስ እንደማያስፈልገው እንዲኹም ደግሞ ከዳግም ምጽአትም በኃላ አፍአዊ ልብስ የሚቀርለትና ጸጋ እግዚአብሔር ለብሶና ተጫምቶ የሚኖር መኾኑን ያረጋግጥለት ዘንድ #ጌታ_ሲነሣ_የመግነዙን_ጨርቅ_ጥሎ_ተነሣ_ካሁን_ወዲህ_አፍአዊ_ጌጥ_ቀረላችሁ_ጌጣችሁ_እኔ_ራሴ_ነኝ_ሲል። ለዚህም እኮ ነው ቅዱስ ኤፍሬም በጥምቀት የምናገኘውን ነገር ሲገልፅ አዳም ዕፅ በልቶ ያጣትን የብርሀን ልብስ የጥምቀት ገንዳ ውስጥ ስንገባ ዳግመኛ
እናገኛታለን። ይህቺን ልብስ መልበሳችን እውን ኾኖ የሚታይባት በር ትንሣኤ ናትና የመግነዙን ጨርቅ ጥሎ ተነሣ። የመግነዙን ጨርቅና የራሱን ጥምጣም በመቃብሩ ላይ በየቦታቸው የመኾናቸው ነገር አንሥቶ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የክርስቶስ ትንሣኤ ሕያው ምስክሮች አድርጎ አቅርቧቸዋል። ክስተቱም በሥርዓት የተደረገ እንጂ በጥድፊያ የኾነ አይደለም፤ ሌቦች የሠረቁት ቢኾን በየቦታቸው አይገኙም ነበር በማለት የጌታን ትንሣኤ አማናዊነትና እኛም መጨረሻችን መጨረሻች ጨርቃችንን ጥለን መነሣት መኾኑን አስረግጦልናል። ከትንሣኤ በኃላ መራብ መጠማት ቀርቶልን መላእክትን በምታስመስል ልዩ ምስጋና ውስጥ በመንፈስ ገብተን አብረን ስናመሰግን እንኖራለን።
፨፨፨፨፨፨፨👇👇👇👇፨፨፨፨፨፨፨
♦♦♦♦__♦♦__♦♦__♦♦
@SPRITUALITY @SPRITUALITY

💠5 የሰማይ ፍጥረታት ያወጁት ትንሣኤ ነው። ጌታ ወደ መስቀል ላይ ሲወጣ ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨልሞ ነበር ይህም እውነተኛው ብርሀን እስከ ስድስተኛው ሺ ሲያበራ ኖሮ ማለትም በክብሩ ነበረ በመጨረሻው ግን ሰው ኾኖ ሲመጣ አምላክነቱ በሰዎች ጥርጣሬና አለማመን የተነሣበልባቸው ጨለመባቸው። መለኮቱን ሊያዩት አልቻሉምና ሥግውን ቃል ሰው ነው ብለው መከራ አደረሱበት። ለሦስት ሰዓት የሰማይ ፍጥረታት እንደጨለሙ ለሦስት ቀንና ሌሊት ጌታችን በመቃብር አደረ። በዚህም መቃብር የኾነውን አስተሳሰባቸውን ሊያጠፋ የመጣ መኾኑን አስረግጦ አስረዳ!!!

ከጨለማ ወደ ብርሃን ፍጥረታትን
አሸጋገረ፤ ለዚህም አይደል እንዴ እነዚያ የሰማይ ፍጥረታት የጥጦስን ልብ በሐዘናቸው ቀድደው ገብተው የጥርጥር ጨለማውን አርቀው ከአማናዊው ብርሀን ጋር የሚገናኝበትን ዕድል ራሳቸውን በማጨለም የሰጡት። ለሦስት ሰዓት መጨለማቸውና ከዚያን ማብራታቸው ጌታችን ለሦስት ቀንና ሌሊት በመቃብር ከቆየ በኃላ መነሣቱን የሚያውጁ አዋጆች ነበሩ። ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊም እንዲህ ነበር ያለው፦
#ፍጥረታት_ኹሉ_በሥቃዩ_አብረውት_ተሰቃዩ_ሲሰቀልም_እንዳታየው_ፀሐይ_ፊቷን_ሸሸገች_ከእርሱም_ጋር_አብራ_ልትሞት_ብርሃንዋን_አጠፋች_ለሦስት_ሰዓታት_ጨለማ_ከኾነ_በኃላ_ግን_መልሳ_አበራች_ይህም_በሦስተኛው_ቀን_እንደሚነሣ_ስትመሰክር_ነው_በማለት_እንደገለጸው የጌታን ትንሣኤ ነቢያት በትንቢት ቢናገሩም ከሐዋርያት ቀድማ አምና የመሰከረችው ፀሐይ ናት!!!
የጌታን ትንሣኤ ለማያምኑ ሰዎች ፀሐይ ብርሀኗን እንዳትከለክላቸው ይጠይቋት እንላለን! ይቆየን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
በ ዲ/ን ዮሐንስ
@SPRITUALITY @SPRITUALITY
♦♦♦♦__♦♦__♦♦__♦♦
❤️ ፍቅር ቊስል ነው ❤️

እውነቱ ይህ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው።
እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል። እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል። #ምክንያቱም_ፍቅር_የሚታየው_በታገስነው_ቊስል_ውስጥ_ነው

#ፍቅር የሚታወቀው የተለዋወጥናቸውን ቃላት ሳይሆን በምንታገሠው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነውን መሥዋዕትነትና በተካፈልነውን ብርሃን ነው።

ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር።
"ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው። አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማረስጃ እንዲሆናችሁ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ! ነው ያላቸው። ፍቅር ቊስል ነው።
በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው።

ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቆስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ "እዩት ቊስሌን አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው።
እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት።

ጸሐፊ: Fr.Haralambos Libyos Papadopoulos
ተርጓሚ: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
✝🔰🔰🔰✝🔰🔰🔰✝🔰🔰🔰✝
✝መጽሐፍን በመመርመር ተወስነህ እንድትኖር ዕወቅ በዚያውም ጸንተህ እንድትኖር ዕወቅ ይህን ያደረግህ እንደሆነ ራስህን ታድናለህ´´✝
📚📚📚 📚📚📚
📙መምህረ አሕዛብ ቅዱስ ጳውሎስ ከጻፋቸው መልእክታት መካከል ለግል ሰዎች የተላኩ መልእክታትም ይጠቃለላሉ። ከእነዚህም ወደ ጢሞቴዎስ የላካቸው ሁለቱ መልእክታት በኤጲስ ቆጶስነት ሲያገለግል ሊጠነቀቅባቸው የሚገቡ ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ የሚያስገነዝቡ ናቸው። በቤተ ክርስቲያን ደረጃ ሊኖር የሚገባውን ትክክለኛ ሥርዓት ከዘረዘረ በኋላ የሕዝቡ መሪ ሆኖ የተሾመው ራሱ ጢሞቴዎስ በሕዋሳቱ ላይ ሊሠራ የሚገባውን ሥርዓት አያይዞ ይጽፍለታል። ከእነዚሀ ምክሮች መካከል ከላይ በርእሳችን የጠቀስነው ኃይለ ቃል አንዱና ዋነኛው ነው። ቃሉ ሁልጊዜ መጻሕፍትን በመመልከት መኖር እንደሚገባ ይህን ማድረግም ያለውን በረከትም ይገልፃል። «ራስህንና የሚሰሙህን ታድናለህ» በማለት። ይህም መጻሕፍትን መመልከት የመዳንና ያለመዳን (የህልውና) ጉዳይ መሆኑን ያሳየናል። ነቢዩ በትንቢቱ «ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል» ያለውን ቃል ጌታ በወንጌል «ስኅትክሙ በኢያእምሮ መጻሕፍት» «መጻሕፍትን ባለማወቅ ሳታችሁ።» ብሎ ምክንያቱን ከመጻሕፍት ጋር ማገናኘቱ እውነትም መጻሕፍትን ካለማንበብ ስኅተት ሲብስም ጥፋት የሚመጣ መሆኑን ያስተምረናል። ሐዋርያው ደግሞ የጉዳዩን ታላቅነት በሚያስረዳ መልኩ «ወዘልፈ ሀሉ ባቲ» «ሁልጊዜ በእርሱ ኑር» በማለት መጻሕፍትን መመልከት የጥቂት ጊዜያት ሥራ አለመሆኑን አያይዞ ገልጿል።
📚📚📚 📚📚📚
📘በሁለተኛው መልእክቱ ላይ ደግሞ «ተአምር በኀበ መኑ ተምህርከ እምንዕስከ መጽሐፈ ቅዱሰ በሃይማኖተ ኢየሱስ ክርስቶስ» «ከሕፃንነትህ ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማን እንደተማርክ ታውቃለህና» በማለት በመጀመሪያው መልእክቱ ላይ የጠቀሳቸውን ትእዛዛት የበለጠ አብራርቷቸዋል። ሁልጊዜ አንብብ ብሎ ያዘዛቸው መጻሕፍት ከመጻሕፍተ ጥንቆላ የተለዩ ንጹሐት ከመጻሕፍተ ምኑናት የተለዩ ክቡራት እንደሆኑ ለማሳየት «ቅዱሳት መጻሕፍት» ብሎ ሲጠራቸው እነዚህም ልብ እንደፈቀደ የሚነበቡ ብቻ ሳይሆኑ የምንማራቸው መሆኑን ለማሳየት «እንደተማርከው» የሚል ቃልን አስቀምጦልናል። መማሩም ከሐሰተኛ መምህር እንደሆነ «ዕውርን ዕውር ቢመራው» ይሉት ብሂል ይፈፀማልና «ከእኔ እንደተማርከው ታውቃለህና» በማለት ለገበታ ሰው እንዲመርጡ ለትምህርትም (ለመፅሐፍትም) መምህር መምረጥ እንደሚገባ ተናግሯል።

📚📚📚 📚📚📚

📗ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ በትእዛዝ ደረጃ ብቻ የተገለፁ ሳይሆኑ በቅዱሳንና በቅዱሳን አምላክ በጌታ ሕይወት ውስጥ የተገለጡ እውነታዎች ናቸው። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ ጌታችን ወደ ምኩራብ ገብቶ የነቢዩ የኢሳይያስን መጽሐፍ ገልጦ እንዳነበበ ተጽፏል። ሾለ ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም ታሪክ የተፃፈባቸው መጻሕፍትም እመቤታችን ቅዱሳት መጻሕፍትን ታነብ እንደነበር በተለይም «ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች» ከሚለው ክፍለ ትንቢት ስትደርስ «በዘመኗ ደርሼ ምነው ባገልገልኳት» እያለች ትመኝ እንደ ነበር ይተርካሉ። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል «ደስ ይበልሽ» እያለ ሲያበሥራት ከመዝኑ እንጋ አምኃ ይትአምኁ›› ‹‹እንዲህ ያለ ሰላምታን እንዴት ይቀበሉታል?›› ብላ መናገሯ እናቷ ሔዋን የሳተችበትን ታሪክ ከኦሪት መጻሕፍት መማሯን ያሳያል። በእነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በእነ ቅዱስ ቄርሎስ በገዳማት ብቻቸውን ተጥለው ባሉ በቅዱሳን ዘንድ መጻሕፍት  የነበራቸውን ታላቅነት «እንዳንተርክ ጊዜ ያጥርብናል።»
📚📚📚 📚📚📚
📕በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ታዋቂነትን ያገኙ ሰዎች፣ ታላላቅ መሪዎችና ርቱዕ አንደበት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሰዎች በእርግጠኝነት አንድ የጋራ ነገር አላቸው ይህም ምንም እንኳን ምኑናት ቢሆኑም መጻሕፍትን ማንበባቸው ነው። መጻሕፍትን ማንበብ ነፍስን ለማዳን ለሌላውም የሕይወት መንገድ ከመሆንም ሌላ ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ ለመመልከትና አእምሮንም ለማስፋት ይረዳሉ። የመጻሕፍትን ጥቅም ለመናገር እጅግ ብዙ መጻሕፍትን ብንጽፍ እንኳ ሁሉን ዘርዝረን አንዘልቀውም። በተለይም ደግሞ ኢትዮጵያውያን የራሳቸው ቋንቋና ጽሑፍ ያላቸው እንደመሆናቸውና አንባቢያን የሆኑ ሊቃውንት በፊታቸው እንደ አብነት ሳሉላቸው በንባብ የሰነፉ መሆናቸው ምንም ዓይነት ምክንያት ሊሰጠው አይችልም።
📚📚📚 📚📚📚
📒ስለዚህም እንደ ጢሞቴዎስ «ከሕፃንነትህ ጀምረህ» የሚለው ምስክርነት ባይሰጠንም እንኳ ለራሳችን ሕይወትና ሌሎቹንም ማዳን የሚገኝበትን ጥበብ የሚያስተምሩትን ቅዱሳት መጻሕፍት እናንብብ ከእውነተኛ መምህራን እንማር! «የተፃፈው ሁሉ እኛን ለመምከር ተፅፏል።» ተብሎ ተጽፏልና። ሮሜ 15፥3

📖ወስበሐት ለእግዚአብሔር!📖
❖❖ #ከሰማይ_ከወረደ_በቀር ❖❖❖

በዚህ ሳምንት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን የጌታችንን ከሰማያት መውረድ ታስተምረናለች። #ከሰማይ_ከወረደው_በቀር_ወደ_ሰማይ_የወጣ_ማንም_የለም_እርሱም_በሰማይ_የሚኖር_የሰው_ልጅ_ነው ዮሐ 3፥13 የሚለው ምንባብ ይነበባል። በዚህ ሳምንትም ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለሚተነተን ማብራርያውን መመልከት ተገቢ ነው። ስለ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ስንናገር በውሰጡ #ስለ_አምላክነቱ_ፈጣሪነቱ_እግዚአብሔርነቱ_ስለ_ምሥጢረ_ተዋሕዶም_ጭምር_ነው_የምንነጋገረው። እያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በሐዋርያትና በሊቃውንት መንፈስ ኾነው ለሚረዱ እውነተኛና ሐዋርያዊ ምእመናን የቅዱሳት መጻሕፍት ምሥጢር ተቀድቶ እንደ
ማያልቅ የውኃ ምንጭ ስለኾነ ነፍሳቸው በትርጓሜ ትረካለች። አንዲት ቅድስት
ቤተክርስቲያንን እውነተኛና ትክክለኛ ከሚያደርጓት ዐበይት ነገሮች ውስጥ
አንዱ በሐዋርትና በሊቃውንት ትርጓሜ ላይ መመሥረቷ ነው። የሐዋርያትን ትምህርት የማትቀበል ጉባዔ በምንም መልኩ ትክክል ልትኾን አትችልም፤
በዚህም መሠረታዊ ምክንያት በአንድ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ትርጓሜ ላይ ክርክር ሲነሣ ሐዋርትና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ምን ብለው ተረጎሙት ብሎ መጠየቅ ቀዳማዊ ሊኾን
ይገባዋል። ነቢያትና ሐዋርያት የጻፉትን መጽሐፍ ቅዱስ ብለን የምንጠራውን እንቀበለዋለን። ይህ መጽሐፍ ልክ እንዳልታረደ በሬ ነውና የግድ ምግብ ኾኖ ለመበላት ሦስተኞቹን የቤተክርስቲያን አባቶችን ይፈልጋል፤እነርሱም ልክ እንደ አራጆችና ሠርተው እንደሚያበሉ ሰዎች ናቸው። እንግዲህ አንድ ሰው ነቢያትንና ሐዋርያትን እቀበላለሁ ብሎ በእነርሱ የተጻፉትን ቅዱሳት መጻሕፍት ባያጣጥምና ባይመገባቸው እቀበላለሁ ማለቱ ስለምንድነው? በእርግጥ በሬ ሳይታረድ ሊበላ የሚችለው ለጅቦች እንጂ ለሰዎች እንዳይደለ የታወቀ የተረዳም ነገር ነው። ማንም ሰው ቢኾን እኔ ክርስቲያን ነኝ ካለ በነቢያት ትንቢት በሐዋርያት ስብከትና በሊቃውንት ትርጓሜ ማመን ግድ ይለዋል። ካልኾነ በጉን ይዞ አርዶ መብላት ባለመቻሉ ብቻ ሳይጠቀምበት ያልፋልና። እስኪ አኹን ያነሳነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በዚህ መንፈስ እንመርምረው፦

👉 ከሰማይ ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ሲል #አንደኛ_ከሰማይ_የወረደ_ሰማያዊ_የኾነ_ደግሞም_ወደ_ሰማይ_የወጣ_ማንም_የለም_ማለት_ነው። ሰማይ ያለው በወል ስም ነው እንጂ ከአንደኛው ሰማይ ሲል አይደልም፤ ከአርያም የወረደ ወደ አርያምም የወጣ ማንም የለም ሲል ነው እንጂ። ቅዱሳን ሲጀመር ከሰማይ የመጡ አይደሉም በመኾኑም ከሰማይ ከወረደ የሚለው እነርሱን የማይመለከት መኾኑን ከተረዳን የሄኖክ፣ የኤልያስ፣ የዕዝራእና የሌሎችም ቅዱሳን ዕርገት። ከዚኛው ጋር አንድ እንዳልኾነ ግልጽና የተረዳ ነው። እነርሱ ከምድር ዐርገው ወደ ብሔረ ብፁዐን የሔዱ እንጂ ጥንቱን ከሰማይ የወረዱ አይደሉምና ለእነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተገለጸው ጋር ፈጽሞ አይጋጭም። እንዲያውም ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ተወሰደ፤ ሄኖክን እግዚአብሔር ወሰደው። ለእነዚህ ለኹለቱ ረዳት አስፈልጓቸዋል፤ ጌታችን ግን በራሱ ሥልጣን ምንም ረዳት ሳይሻ ነው ያረገው ይልና እነዚህ ኹለቱ ቅዱሳን የክርስቶስን ዕርገት በምሳሌነት የሚያሳዩ ናቸው፤ ሄኖክ ከሕገ ኦሪት በፊት ላሉት፤ ኤልያስ ደግሞ በሕገ ኦሪት ላሉት የክርስቶስን ሥጋዌና የተዋሐደውን ሥጋ ይዞ ማረግ የሚያመለክቱ ናቸው በማለት ወደተለየና ድንቅ ወደ ኾነ ምሥጢር ይስበናል።
❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖
👉 #ኹለተኛ ከሰማይ ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ሲል ወረደ የሚለው ሥጋዌውን የሚያስረዳ ነው፤ ለእግዚአብሔር መውጣት መውረድ የለበትምና። ኢየሱስ ክርስቶስ
እግዚአብሔር መኾኑ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ውስጥ የሚገኝ እውነታ ነው። ዮሐ 1፥1 የሐዋ 20፥ 28፤ ፊል 2፥7። ወጣ የሚለው ደግሞ የተዋሐውን ሥጋ አሣረገ ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ባለጸጋው እኛ በእርሱ ድህነት ባለጸጋ እንኾን ዘንድ ደሀ ኾነ በማለት እንደተናገረ፤ ዝቅ ብሎ እኛን ከፍ አደረገን ማለት ነው። በመጽሐፍ የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ እንደተባለ የእኛን መዋረድ ዐይቶ ሰው ኾኖ ሥጋ ማርያምን ተዋሕዶ ተዋርደን የነበርነውን ከፍ አደረገን ማለት ነው። በትሕትናው ልዕልናን ሰጠን ሲል ነው።
❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖

#ሦስተኛ አይሁዳዊያን ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ወደሰማይ ዐርጎ ዓሥርቱን ትዕዛዛት ይዞ መጣ ብለው ያምኑ ስለነበር #ከሰማይ_የወረድኩት_እኔ_ነኝ_እንጂ_ሌላ_ማንም_አይደለም_ብሎ_የአይሁድን_የተሳሳተ_እምነት_በመምህራቸው_በኒቆዲሞስ_በኩል_ለመግለጥ_ስለፈለገ ከሰማይ ከወረደ በቀር ወደሰማይ የወጣ ማንም የለም አለ። ከእንግዲህ ወዲህ ሙሴ ወደ ሰማይ ዐርጎ ነው ትዕዛዛትን ይዞ የመጣው አትበሉ ከሰማይ የመጣሁት እኔ ነኝ ሙሴ ወደ ሰማይ ሔዶ አልመጣም ሲል ነው።
❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖

#አራተኛ_ምሥጢረ_ተዋሕዶን_ሲያስረዳ_ነው። ከማይ ከወረደው በቀር ወደሰማይ የወጣ ማንም የለም ርሱም በሰማይ የሚኖር የሰው ልጅ ነው ይላል። ይህንን ንግግር ሲናገር ጌታችን በሥጋው
በምድር ነው የነበረው ኾኖም ግን በሰማይ የሚኖር የሰው ልጅ አለ በማለት ገለጸ፤ #ለምን_ቢባል_እግዚአብሔር_በኹሉም_ቦታ_ስላለ_ያን_በኹሉ_ቦታ_መኖርን_በተዋሐድኩት_ሥጋ_ገንዘብ_አድርጌዋለሁኝ። ሥጋ ከመለኮት ጋር ሲዋሐድ አንዱ የአንዱን ገንዘብ ገንዘብ ስለሚያደርግ፤ ምንም እንኳ ሥጋ ውስን ቢኾንም በምሥጢረ ተዋሕዶ ምሉእ በኩለሄ የኾነውን የእግዚአብሔርን የባሕርይ መገለጫ ገንዘብ አድርጌዋለሁ ሲል ነው። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ "ይህ የወረደው ኹሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ኹሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው "ኤፌ 4፥10 ያለው። የወረደውና የወጣው በተዋሕዶ አንድ ኾነዋል ሲልነው። ወዴት እንደወጣም ሲናገር ከሰማያት ኹሉ በላይ ነው የሚለው ይህም የሚያስረዳው አምለክነቱን ነው
ከሰማያት ኹሉ በላይ ያለው አምላክ ነውና። ለዚህ ነው ቅዱስ ቄርሎስ ጌታችንን መድኃኒታችንን የሚከፍለው ኹለት አካል ኹለት ባሕርይ የሚለው
ከአብ የተወለደው ወልድ ወደ ሰማይ ካረገው ልዩ እንደኾነ ወደ ሰማይ ያረገው ሰው ከአብ ከተወለደው ልዩ እንደኾነ የሚናገር አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደኾነ የማያምን የተወገዘ የተለየ ይኹን" ያለው ድር.ቄር ገጽ 265።
❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖
#አምስተኛ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞነበር ኒቆዲሞስ በመጀመር ላይ እንደ አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ
የተመለከተው። "ከእግዚአብሔር ዘንድ
እንደመጣህ እናውቃለን "ሲልም ከእግዚአብሔር የተላከ ነቢይ ብቻ መስሎት ስለነበር ነው። ጌታችን
ግን ከሰማይ ተልኮ የመጣ መኾኑንና ነቢይ አለመኾኑን በኹሉም ቦታ ያለ መኾኑን በማብራራት አስተምሯል።
በመኾኑም #ኒቆዲሞስ_ኾይ_እኔ_እዚህም_እዛም_አለኹኝ_እንደነቢያት_የምላላክ_አይደለኹም_በሰማይም_ከሰማይም_በታች_አለኹኝ_ሲል_ነው። ይህ እንግዲህ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዌ የመለኮትን ምሉዕ በኩለሄ መኾን አለማስቀረቱን ያስገነዝበናል። አይሁድ ለከባድ ስሕተት የተጋለጡት ክርስቶስን ውስን አድርገው እንደራሳቸው በማየት ነው። የሚናገራቸው ንግግሮች ይገባቸዋል ነገር ግን አይቀበሉትም። እርሱ እናንተ ሥጋዬን ብቻ በማየታችሁ ምክንያት ተራ ዕሩቅ ብእሲ ነህ ትሉኛላችሁ እኔ ግን በሰማይም በምድርም የመላኹ ነኝ በማለት ከሰማይ ከወረደው በቀር በሰማይ የሚኖር ማንም የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው እንጂ በማለት በአንቀጸ ኒቆዲሞስ ለአይሁድ ያስረዳው።
❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖
@SPIRTUALITY @SPIRTUALITY
#ስድስተኛ_ከሰማይ_የወረደው_በራሱ_ፈቃድ_እንደኾነ_ወደ_ሰማይም_ያረገው_በራሱ_ፈቃድ_መኾኑን_ሲያስረዳ_ነው።
ሌሎች ቢያርጉ እግዚአብሔር ነው የሚያሳርጋቸው የሚወስዳቸው ርሱ ግን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ስለኾነ በራሱ ሥልጣን ነው ያረገው። ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ማለት በሥልጣኑ ወረደ በሥልጣኑ ወጣ ማለት ነው። ለዚህ ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ድል መንሣት ባለበት የነጋሪት ድምፅ እግዚአብሔር ዐረገ አለ(መዝ 46፥5)፤ ርሱ ዐረገ አለ እንጂ መላእክት አሳረጉት አላለም፤ በፊቱ መንገድ የሚመራ አልፈለገም፤ በዚያው ጎዳና ርሱ ዐረገ እንጂ፤ ኤልያስ በዚያ መንገድ እንደ ክርስቶስ እንዲህ ሊያርግ አልቻለምና የኤልያስ ባሕርይ በዚኽ መንገድ ሊያርግ አልቻለም፤ መላእክት ወደ ታዘዙበት ቦታ ወሰዱት እንጂ(2ነገ 2፥11) አንድ አካል አንድ ባሕርይ የሚኾን የእግዚአብሔር ቃል መላእክትን የፈጠረ ነውና በሥልጣኑ ዐረገ፤ ስለዚህም ወንጌላዊው ሉቃስ የሐዋርያትን ሥራ በሚናገር መጽሐፍ ወደ ሰማይ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ርሱ አቅንተው ያዩ እንደነበር ተናገረ፤ አሳረጉት አላለም ወይም ተሸከሙት አላለም፤ ያረገበት ቦታ ገንዘቡ ነውና" ሃይ ዘቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ ምዕ 67 ክፍል 13 ቁጥር 12-15። ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም የጌታን ዕርገት እንዲህ ይገልጽልናል "#በራሱ_ሥልጣን_ተነሣ_ርሱን_ያስነሣው_ማንም_አይደለም_በሚያርግም_ጊዜ_ማንም_ርሱን_ያሳረገ_አይደለም። ኤልያስን አስመልክቶ ዕርገቱ በጌታ አማካኝነት የኾነ ነውና እንዲያርግ ያደረገው ጌታ ነው፤ ከዚህም የተነሣ በሠረገላ እና በእሳት ፈረስ የከበረ ሥነ ሥርዐት ተደረገለት(2 ነገ2፥11)፣ ምክንያቱም ወደ ዐረገበት ቦታ በራሱ ማረግ አይቻለውምና፤ የጌታችን ግን እንደተጻፈ ተለየ፤ ወደ ላይ ለመነሣት ምንም ዐይነት መንኮራኩር አላስፈለገውም፤ በአንድ ቦታ በተወሰነ ጊዜ የሚቀመጡት ሰው በአጋዥ መውጣት ያስፈልገዋል፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ብቻ ነውና፤ የእግዚአብሔር ልጅ ግን ራሱ እግዚአብሔር ነውና መንኮራኩር አያስፈልገውም "(ነገረ ክርስቶስ ገጽ 219-220)። በመኾኑም ጌታችን ከሰማይ በራሱ ሥልጣን
የተዋሐደውንም ሥጋ በራሱ ሥልጣን እንዳሳረገ የሚያስረዳ ንባብ ነው። ሰማያዊ ሥልጣን ያለው የሥልጣን ባለቤት መኾኑን ማቴ 10 ላይ ለዐሥራ እንደወረደኹለቱ ሐዋርያት ሙታንን የማስነሣት፣ ድዊያንን የመፈወስ፣ አጋንንትን የማስወጣት ሥልጣን እንደሰጣቸው ያስገነዝበናል። ያም ብቻ የቅድስት ሥላሴን ልጅነት የምናገኘው እርሱን አምላክ ነው ብለን ስንቀበለው በሚሰጠን ሥልጣን ነው። መጽሐፍ ለተቀበሉት ኹሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይኾኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው ተብሎ በዮሐ 1 ላይ ሳይኾንተጽፏል።
❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖
@SPIRTUALITY @SPIRTUALITY
#ሰባተኛ_ቅዱስ_አውግስጢኖስ_ደግሞ_ወደ_ሰማይ_የምንወጣበትን_መንገድ_ሊሰጠን_መውረዱንና_ወደ_ሰማይ_ይዞን_ወጥቶ_ደግሞ_የእግዚአብሔርን_ፈቃድ_የምናደርግበትን_ኃይል_ለእኛ_እንደሰጠን_ሲያስረዳ_ነው ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም የተባለው። ከሰማይ ከወረደው ሲል መንገዱን እንደሰጠን፤ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ሲል የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንረዳበትን ኃይል እንደሰጠን የሚያስረዳ ነው።

#በኢየሱስ_ክርስቶስ_አምላክነት_ሥጋዌ_ስናምን_የሰማዩን_የእግዚአብሔርን_ፈቃድ_የምንረዳበትን_ጥበብ_ኃይል_እናገኛለን_ሲል_ነው። እንግዲህ መንገዷ ማለት እውነተኛይቱ ሃይማኖት ናት፤ነብዩ ሆሴዕ የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ናት ጻድቃን ይሔዱባታል ኃጥአን ግን ይወድቁባታል በማለት የገለጸልን ንጽሕት መንገዳች አንዲቷ ሃይማኖታችን ናት። በዚህች ርትእት መንገድ ስንጓዝ ፈጻሚያነ ፈቃደ እግዚአብሔር ወደ መኾን እንሸጋገራለን።
❖ ❖ ❖✝ ✝ ✝❖ ❖ ❖
@SPIRTUALITY @SPIRTUALITY
ስምንተኛ አኹንም ቅዱስ አውግስጢኖስ እንዲህ ይላል። #ባል_እናትና_አባቱን_ይተዋል_ከሚስቱም_ጋር_አንድ_ይኾናል_እንደተባለ_የቤተክርስቲያን_ሙሽራ_ክርስቶስም_አብን_አባቱን_ትቶ_ሲባል_ቅዱስ_ጻውሎስ_እንዳለው "እርሱ የእግዚአብሔር መልኩ ነው ቀምቶ እግዚአብሔር የኾነ አይደለም። ነገርግን የባሪያውን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ኾኖ ራሱን ዝቅ አደረገ። ፊል 2፥7 በሚለው ነው። #እናቱን_ትቶ_ሲል_ከእናቱ_መወለዱን_ሲል_ነው_ከሚስቱ_ማለትም_ከሙሽሪት_ቤተክርስቲያን_ጋር_አንድ_ኾነ_ማለት_ነው።
በዚህም ምክንያት ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ሲል፦ ከሰማይ ከወረደው ጋር አንድ አካል ያልኾነ ወይም ከሰማይ የወረደው ያላደረበት ማንም ወደ ሰማይ ሊወጣ አይችልም። ከሰማይ በወረደው በእግዚአብሔር አሳራጊነት ካልኾነ በቀር ማንም ሊያርግ አይችልም። ይህ የሚያሳየው አንድነትን ነው። ቤተክርስቲያንን ያለ ክርስቶስ ማረግ አትችልም ሲል ነው። ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ሲኾን ቤተክርስቲያን ደግሞ አካሉ ናትና የቅዱሳን ኹሉ ዕርገት በባላቸው በክርስቶስ ወይም በራሳቸው
በክርስቶስ የሚኾንና ርሱም አንድ መኾኑን የሚያስረዳ ነው። ስለዚህ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጎምደው ራሳቸውን በነፍስ በሽታ ውስጥ እንደከተቱት መናፍቃን ሳይኾን በቅድስናና በንጽህና አጥርነት ራሳቸውን ጠብቀው በእግዚአብሔር መንፈስ በተረዱት በአባቶቻችን ትርጓሜ መሠረት የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር እንድንጠጣ እግዚአብሔር ይርዳን አሜን።

@SPIRTUALITY @SPIRTUALITY
❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር!❖
በዲ/ን ዮሐንስ
🔥 🔥 #እሳቱን_እንቆስቁስ 🔥 🔥


አንዲት ሴት ነበረች። እንጀራ ልትጋግር እሳት አያይዛ ምጣዷን ጣደች። እዛው ኩሽናዋ ውስጥ ስትንጎዳጎድ ለአፍታ ቆይታ ወደ ምጣዷ ዘወር ብትል... አንድ ትልቅ አይጥ መኻል ምጣዱ ላይ ጉብ ብሎበት ተመለከተች። ነደዳት፤ ተበሳጨች። በእልኽ እሳቱን ልትቆሰቁስበት፣ ልታነደውም ያዘጋጀችውን ፍልጥ የአይጡን ወገብ ትልበት ዘንድ አነሣች። (የአይጡን ወገብ ስትሰብር የምጣዱ 'ወገብ' እንደሚሰበር ትዝም አላላት።) ፍልጡን በኹለት እጇ ጠበቅ አ'ርጋ ይዛ ወደ አይጡ በማነጣጠር ከአናቷ በላይ አንደረደረችው። ካንደረደረችበት ወደ ፊት ከመሰንዘሯ በፊት ግን ነገሩን ኹሉ በሽንቁር አጮልቃ ስትከታተል የቆየችው ጎረቤቷ "እቴ! ፍልጡን ተይው! እሳቱን ቆስቁሺው" አለቻት። (እሳቱ ሲያቃጥለው በራሱ ይሔዳል በሚል እሳቤ)።
...
#ምጣድ_የተባለ_ሰውነታችን_ነው_ሰብእናችን። #እሳት_የተባለች_ሃይማኖት_ናት_ተዋሕዶ። "እሳተ አምጻእኩ ለብሔር" እንዲል። (ሉቃ. 12:49)።
ምጣድ የተባለ ሰውነታችንን እሳት በተባለች ሃይማኖት ላይ ስንጥድ ኹሌም ቢሆን አይጡ ይመጣል። ካለ ምንም ኃፍረት መኻል ምጣዳችን ላይ ጉብ ይላል።

#ዘረኝነት_አይጥ_ነው_ድንገት_ሳናስበው_በጣድነው_ምጣድ_ላይ_ጉብ_የሚል። ሰማያዊም ምድራዊም እንጀራን ለማብሰል የሚያስችል ግለት ሳይኖረን የሚሰፍርብን ጥቁር አይጥ። በመንፈሳዊነት ዋዕይ ካላቃጠልነው ሊቦጠቡጠን የተጫነን ሸክም። #አይጥ_ልብስን_ይቀዳል_በአንድነት_የተሰፋውን_ይለያያል_ዘረኝነትም_እንዲሁ_ነው_ሰብእናን_ይቀዳል፤ በአንዲት ሃይማኖት የአንድ አካል ብልት የሆንነውን ይለያያል።

#ተሐድሶ_አይጥ_ነው_ምንፍቅና_ከተባለው_የአይጥ_ዝርያ_የተገኘና_በክሕደት_የሰባ_ጠብደል_አይጥ። እሳቱን ቶሎ ቆስቁሰን ምጣዳችንን አግለን ተለብልቦ ካልሔደ አደገኛና መርዛማ ነው፤ በ'ኩሱ' እንኳን ምጣዳችንን ለመበከል ወደ ኋላ የማይል ነውረኛ አይጥ ነው። ከቻለ ምጣዳችን እንዲሰበር ካልቻለ ደግሞ እንዲሰነጠቅ የማያደርገው ጥረት የለም። መዝሙር በሚመስል ዘፈን፣ ሽብሸባ በሚመስል ዝላይ ምጣዳችንን በማወዛወዝ ዱቄት ሊያደርግ የሚጥርና ተመስጦን የሚረብሽ አይጥ ነው። ያሰስነው ምጣድ ላይ ተቀምጦ እኛን በማበሳጨት ፍልጡን እንድናነሣ ዘወትር ይጋብዘናል፤ ዋና ዓላማው የምጣዱ መሰበር ነዋ!

ዋናዎቹን አነሣን እንጂ እሳቱ ላይ ስንጣድ የሚወጡብን አይጦች ብዙ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ወዳጆቻችንም አይጥ ሆነው ይመጣሉ። ቤታችን ሽንቁር እስካለው ድረስ ብዙ የአይጥ ዝርያዎች ምጣዱ ላይ ለመውጣት መሽቀዳደማቸው አይቀርም።

በዚህን ጊዜ ታዲያ እሳቱን በመቆስቆስ ፈንታ ፍልጡን ካነሣን የአይጦቹን ዓላማ አሳካን ማለት ነው።

#በሃይማኖት_ፍቅር_ልቡ_የነደደ_ስንቱ_አይጡን_ለማባረር_ፍልጡን_አዘውትሮ_እያነሣ_ስንት_ምጣድ_ሰበረ!

ወዳጄ ሆይ! አይጡ ተቃጥሎ እንዲሔድ እሳቱን ቆስቁሰው 'ባክህ። #ጸሎት_መቆስቆሻው_ነው_ጾም_ስግደት_ትምህርት_ቅዳሴ_ጉባኤ_ንስሐ_ቁርባን_ሱባኤ_ምጽዋት_ምግባር_ኹሉ_መቆስቆሻዎች_ናቸው።

ይህ ማለት ግን በሰበቡ ተዘናጋ ማለት አይደለም። ዋና ዓላማህ እንጀራ የሚገኝብህ ምጣድ መኾን ነው። መቼስ አይጥ ባለበት ምጣድ እንጀራ እንደማይጋገር ግልጽ ነው። ስለዚህ እንጀራን ለማግኘት አይጡ መሔድ አለበት። መጀመሪያ አይጥ መሆኑን አረጋግጥ፤ ከዚያም አባረው!

ግን አባራለው ብለኽ ምጣዱን እንዳትሰብር ተጠንቀቅ፤ እሳቱ መንደዱን አረጋግጥ፤ በርትተህ ቆስቁስ...

የኔና ያንተ ትልቁ ችግር ለመቆስቆስ አዋጅ መጠበቃችን ነው። "እነ እንትና ለምን ለ3 ቀን ቆስቁሱ የሚል አዋጅ አያውጁም?" እንላለን። "አትቆስቁሱ" እንዳላሉ እንዘነጋለን። ላለመቆስቆስ ሰበባችን ብዛቱ! ታዲያ ምጣዱ እንዴት አይቀዘቅዝ!? ባልጋለው ምጣዳችን ላይስ አይጦቹ እንዴት አይፈነጩበት!?

ወዳጄ ሆይ!
#ለምጣዳችን_ደኅንነት_እሳቱን_እንቆስቁስ!

✍ ዲ/ን ሕሊና በለጠ

🔥🔥 @SPIRITUALITY 🔥🔥
🔥🔥 @SPIRITUALITY 🔥🔥
የቅዳሴ ተሰጥኦ መቀበያ.pdf
1.5 MB
እነሆ የቅዳሴ ተሰጥኦ መቀበያ
በግዕዝ በአማርኛና በእንግሊዘኛ
ለምዕመናን ያጋሩ
@ethiopianorthodoxs
"ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ...ክብር ለሚገባው ክብርን ሥጡ"!
ሮሜ 13፡7

ቅድስናን፤እምነት፤ሰማእትነትን፤ ከሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተገኘ አምላክም በአንተ አምላክነቱ ተገለጠ ተመሰገነ፤ በአንተ እምነት ተደስቷልና። ቅድስናህን፣ክብርህን በመጠጥ ስም ሊነገድበት ሊጎድፍ አይገባውምና ስምህ ክብርህ በአምላክ ዘንድ ሞገስን አጊንቷልና....

እግዚአብሔርን እስከሞት ድረስ ታምነው ያከበሩት ቅዱሳኑን እግዚአብሔር ደግሞ የድል አክሊልን፣ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ሰጥቶ አክብሯቸዋልና እኛም በቃልኪዳናቸው በምልጃቸው ከጥፋት እንዲታደገን ቅዱሳኑን እናክብር!

#ክብር_ለሚገባው_ክብር_እንስጥ!

❌ በሰማዕቱ ስም እና ስዕል የሚደረገውን የመጠጥ ንግድ እንቃወማለን!❌

@Mnenteyiklo @Mnenteyiklo
💐🍀💐🍀💐🍀💐🍀💐🍀💐🍀
ለኦርቶዶክሳውያን !

+ አባቶቻችን ነገ ነሐሴ 30 ቀን አስቸኳይ ስብሰባ ያደርጋሉ፡፡

+ ለምን ታዲያ እኛስ እንደ ምእመንነታችን ማድረግ የምንችለውን አናደርግም?

+ ለምን እነርሱ ሲሰበሰቡ እኛም አብረን የዓቅማችንን ያህል በፈቃደኝነት አንጾምም?

+ ለምን የዓቅማችንን ያህል ሌላ ጊዜ ከምንጸልየው በተጨማሪ ጸሎት አናደርስም?

+ አሕዛብ የነበሩ የነነዌ ሰዎች ሊመጣ ከነበረው መዓት በእውነተኛ ንስሐቸው በጾም በጸሎት ከተረፉ፥ ክርስቲያን የኾንን እኛ'ማ እንዲህ እንደ ዓቅማችን ብናደርግ እግዚአብሔር የበለጠ ይሰማናል፡፡

+ ስለዚህ ይህን ጽሑፍ የምታነቡ ወገኖቼ መንግሥት የሚሠራውን በቁዔት የለሽ ድራማ ትተን ይህን ሠናይ ሥራ ብናደርግ መልካም ነው፡፡

@yohansafework
እንኳን ደስ አላችሁ የማህበረ ቅዱሳን የቴሌቭዥን ጣብያ የሙከራ ስርጭቱን ጀመረ!

ማህበረ ቅዱሳን (EOTCMK)
NILESAT 7W...../Eutelsat 7/8
11555 V 27500
♻️♻️♻️🌑♻️♻️♻️🌑♻️♻️♻️