SOBR🌺
1.2K subscribers
353 photos
933 videos
3 files
170 links
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

"የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም "  

አላህ በጎ ከሚሠሩት ያርገን ያረብ🤲
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Quality button
🦋ይህ ሰው በርሲሳ ይባላል። አላህን ተገዢ ነበረ። ከእለታት አንድ ቀን ግን ነገራቶች መቀያየር ይጀምራሉ። ሸይጧን በሰው ተመስሎ መጥቶ ሊያጠመው ይሞክራል። ብዙ ሰዎችን ልክፍት ያሳምምና መልሶ መጥቶ ወደ ልክት ሚያክም ሰው ልውሰዳቹ እያለ ወደሱ ይወስዳቸዋል። ከዛም መጨረሻ ላይ ከንጉስ ቤተሰብ የሆነችን ሴት ያሳምምና ወደሱ ያመጣታል። እሱም ያክማታል ነገርግን ሲያማማት በጣም ትገላለጥ ነበረ።
በርሲሳም በተደጋጋሚ ባየው ነገር
ይማረክና ከሷ ጋር.......Read More

🦋ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከታች
ያለውን 𝐑𝐄𝐀𝐃 𝐌𝐎𝐑𝐄 ይጫኑ🕹

▽▾▾▾▾▾▾▾▾▾▿▾▿▿▿▿▿▿▿▾▿▾▾▿▿▾▾▿▾▾▿▾▿▿▼
🟠𝐀𝐝𝐝 ሱናና 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🟠
        👇👇👇👇
🛰WAVE :-@ezedinm1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ቁርዐን የረሱል (ﷺ) ሀዲሶች🫀 (لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ)
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

ወደፊት ከህዝቦቼ ውስጥ ዝሙትን፣ ሐር መልበስን፣ አስካሪ መጠጥን፣ የሙዚቃ መሳሪያ መጠቀምን የሚፈቅዱሰዎች ይኖራሉ።”

📘 ቡኻሪ ዘግበውታል (5590)
​ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

​"ዱንያ ከአኺራ (አንጻር) ሲታይ እኮ (አንደኛችሁ) ጣቱን ባህር ውስጥ አስገብቶ እንደማውጣት ነው፤ (ጣቱ) በምን እንደሚመለስ (ምን ያህል ውሃ ይዞ እንደሚወጣ) ይመልከት።

​        ☘ሙስሊም  (2858)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ረሱል(ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ اللَّهَ لَيَرْضى عَنِ العَبْدِ أَنْ يَأْكُلَ الأكْلَةَ فَيَحْمَدَهُ عَلَيْها، أَوْ يَشْرَبَ الشَّرْبَةَ فَيَحْمَدَهُ عَلَيْها﴾

“አላህ ከባሪያው ላይ ይወዳል ምግብን ከተመገበ በኃላ በሷ እንዲያመሰግነው። ወይም መጠጥንም ከጠጣ በኋላ በሷ እንዲያመሰግነው።”


🍃 ሙስሊም ዘግበውታል: (2734)
❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ረሱል ( ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

"ከቤቱ (ዑዱ) አድርጎ ''ዋጂብ'' ሶላት ለመስገድ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ምንዳው 'ልክ (ሀጅ) እንደሚያደርግ ሰው ምንዳ' ያክል ነው።

          ☘ሶሂህ ተርጊብ (675)

   
❤2
ሰላት ከማሰላመትህ በፊት ከአራት ነገሮች በአላህ ተጠበቅ!!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

إِذا فَرَغَ أَحَدُكُمْ مِنَ التَّشَهُّدِ الآخِرِ، فَلْيَتَعَوَّذْ باللَّهِ مِن أَرْبَعٍ: مِن عَذابِ جَهَنَّمَ، وَمِنْ عَذابِ القَبْرِ، وَمِنْ فِتْنَةِ المَحْيا والْمَماتِ، وَمِنْ شَرِّ المَسِيحِ الدَّجّالِ.

“አንዳችሁ በመጨረሻው ተሸሁድ ላይ በሆነ ግዜ ከአራት ነገሮች በአላህ ይጠበቅ፦ ከጀሀነም ቅጣት ከቀብር ቅጣት ከህይወትና ከሞት ፈተና እንዲሁም ከመሲሁ ደጃል ፈተና።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 588 ቃሉ የኢብኑ ማጃህ ነው
❤2
ከአብደላህ ኢብኑ መስዑድ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦

﴿أَيُّ الذَّنْبِ أَعْظَمُ عِنْدَ اللَّهِ ؟ قَالَ : " أَنْ تَجْعَلَ لِلَّهِ نِدًّا وَهُوَ خَلَقَكَ ". قُلْتُ : إِنَّ ذَلِكَ لَعَظِيمٌ، قُلْتُ : ثُمَّ أَيُّ ؟ قَالَ : " وَأَنْ تَقْتُلَ وَلَدَكَ ؛ تَخَافُ أَنْ يَطْعَمَ مَعَكَ ". قُلْتُ : ثُمَّ أَيُّ ؟ قَالَ : " أَنْ تُزَانِيَ حَلِيلَةَ جَارِكَ﴾

“ነብዩን (ﷺ) ከወንጀል ሁሉ አላህ ዘንድ ከባዱ የትኛው ነው? ስል ጠየቅኳቸው። እሳቸውም፦ የፈጠረህ እሱ ሆኖ ሳለ ለአላህ ብጤን ማድረግህ ነው አሉኝ። ይሄ በርግጥም ከባድ ነው! አልኩኝ። ከዚያ ቀጥሎስ የትኛው ነው? ስላቸው፡ ካንተ ጋር መብላቱን ሰግተህ ልጅህን መግደልህ ነው አሉኝ። ከዚያ ቀጥሎስ የትኛው ነው? አልኩኝ። ከጎረቤትህ ሚስት ጋር ዝሙት መፈፀምህ ነው አሉኝ።”

(📚ቡኻሪ 4477 ሙስሊም 267 ዘግበውታል)
❤1
ረሱል (ﷺ)  እንዲህ ብለዋል፦
﴿اجْتَنِبُوا السَّبْعَ المُوبِقاتِ، قالوا: يا رَسولَ اللَّهِ وما هُنَّ؟ قالَ: الشِّرْكُ باللَّهِ، والسِّحْرُ، وقَتْلُ النَّفْسِ الَّتي حَرَّمَ اللَّهُ إلّا بالحَقِّ، وأَكْلُ الرِّبا، وأَكْلُ مالِ اليَتِيمِ، والتَّوَلِّي يَومَ الزَّحْفِ، وقَذْفُ المُحْصَناتِ المُؤْمِناتِ الغافِلاتِ.﴾

“ከሰባት አጥፊ ወንጀሎች ራቁ። አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!  እነሱ እነማን ናቸው ብለው ሶሃቦች ጠየቁ፦ ‘ሺርክ’ በአላህ ላይ ማጋራት፣ ድግምት፣ ያለ አግባብ አላህ እርም ያደረገውን የሰዎች ነፍስ ማጥፋት፣ ‘አራጣ’ ወለድ መብላት፣ ‘የቲምን’ የሙትን ልጅ ገንዘብ መብላት፣ ከተፋፋመ ውጊያ ወደ ኋላ ማፈግፈግ፣ ጥብቅ የሆኑ ሙስሊም ሴቶችን በዝሙት ማጉደፍ ናቸው።”

ቡኻሪ ዘግበውታል: 2766
❤2
ከጃቢር (رضيﷲ عنه) ተይዞ፡ ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

‏(مُعَلِّمُ الْخَيْرِ يَسْتَغْفِرُ لَهُ كُلُّ شَيْءٍ، حَتَّى الحيتانُ فِي الْبَحْرِ )

“የኸይር አስተማሪ ለሱ ሁሉ ነገር ምህረት ይጠይቅለታል፣ በባህር ውስጥ ያሉ አሳዎች ሳይቀሩ።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 5883
❤2
አሰላሙ  አለይኩም  ወራህመቱላሂ  ወበረካትሁ  ውድና  የተከበራችሁ   እህት ወንድሞቼ ነገ  ሀሙስ  ነው  የውዱና  የተከበሩት  የሰለዋቱ  ረቢ   ወሰላሙ  አለይህ  ምርጡ ሱናቸው  እየተተወ  ስለሆነ  እስኪ  ይህ  የጠፋ  ሱናቸውን  እናስቀጥል ዝግጁ  ናችሁ ??
❤3
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿اسْأَلُوا اللَّهَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ ؛ فَإِنَّ أَحَدًا لَمْ يُعْطَ بَعْدَ الْيَقِينِ خَيْرًا مِنَ الْعَافِيَةِ﴾

“አላህን ይቅርታንና ጤንነትን ጠይቁት። ማንም በአላህ በእርግጠኝነት ከማመን ቀጥሎ እንደ ጤንነት መልካም ነገር አልተሰጠውም።”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል፡ 3558
❤2
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لَيُوشِكَنَّ أَنْ يَنْزِلَ فِيكُمُ ابْنُ مَرْيَمَ حَكَمًا عَدْلًا، فَيَكْسِرَ الصَّلِيبَ، وَيَقْتُلَ الْخِنْزِيرَ، وَيَضَعَ الْجِزْيَةَ، وَيَفِيضَ الْمَالُ حَتَّى لَا يَقْبَلَهُ أَحَدٌ، حَتَّى تَكُونَ السَّجْدَةُ الْوَاحِدَةُ خَيْرًا مِنَ الدُّنْيَا وَمَا فِيهَا﴾

“ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! የመርየም ልጅ (ዒሳ) በእናንተ መካከል ፍትሐዊ ዳኛ ሆኖ በቅርቡ ይወርዳል። መስቀሉንም ይሰብራል። አሳማ ይገድላል። ‘ጂዚያህ’ ያስቆማል። ገንዘብም ማንም አልቀበልም ብሎ እስኪመልሰውና፤ አንዲት ሱጁድ ከዱንያ እና ከውስጧ ካለው ነገር የተሻለ እስክትሆን ድረስ ሀብት (እንደጉድ) ይጎርፋል።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 3448
🥰2💔2
ረሱል (ﷺ )እንዲህ ብለዋል፦

﴿الحبَّةُ السَّوداءُ شفاءٌ من كلِّ داءٍ إلّا السّامَ﴾

“ጥቁር አዝሙድ ሞት ሲቀር ለሁሉም በሽታ መድኃኒት ነው።”

🌴 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5688
❤3
اللَّهم صَلِّ وَسَلَّم عَلَى نَبِيِّنَا وَحبيبُنا مُحَمَّد، ﷺ🫶
❤2
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

“አምስቱ ሰላቶች፣ ከጁምዓ እስከ ጁምዓ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው ያሉትን ኃጢአቶች ያብሳሉ ታላላቅ ወንጀሎችን ሲቀር፡፡”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 233


اللهم صّلِ وسَلّمْ عَلۓِ نَبِيْنَا مُحَمد ﷺ 🤍
❤4