SOA COMMUNITY POLICE 2 CAMPUS
606 subscribers
784 photos
39 videos
81 files
34 links
ይህ ድህረ ገፅ የተለያዩ የትምህርት አይነቶች አጠቃሎ የያዘ ሲሆን የሚለቀቁት ጥያቄዎችም ሆኑ ማስታወሻዎች በቀላሉ ታገኛላችሁ። በ👉👉👉SOAPO2
Download Telegram
Forwarded from SOA COMMUNITY KG (SOA)
ጥብቅ ማሳሰቢያ:- ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የተማሪ ወላጆች (አሳዳጊዎች) በሙሉ
👉👉የ2018 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች የሚኒስትሪ online ምዝገባ በይፋ የጀመርን መሆኑን እያሳወቅን ከዚህ ቀደም ሁሉም ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ እንዲያወጡ የተደረገ መሆኑን ይታወቃል። ሆኖም ፋይዳ መታወቂያ ቁጥር (FAN) ያላመጣ ተማሪ መመዝገብ የማይችል መሆኑን እያሳወቅን ያላወጣ ተማሪ ካለ የምዝገባ ቀኑ እንዳያልፋቸው ባጭር ቀን ውስጥ እንዲያወጡ በጥብቅ እናሳስባለን።
Forwarded from SOA
ዋ ! አድዋ !
ዋ !…
አድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ የአድማስ ጥጉዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
አድዋ …
በአንቺ ብቻ ህልዉና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና …
ዋ !
አድዋ የዘር አፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነቱዋ
በሞት ከባርነት ስርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰውብሽ እለት
አድዋ …
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ
አድዋ ..
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
አፅምሽ በትንሳዔ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ህዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘዉ መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው በለው በለው በለው
ዋ …አድዋ !…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በለው በለው
ዋ …አድዋ …
አድዋ የትናንትናዋ
ይኸው ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሱ እንደገና ::
ዋ ! . . . . .ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ . . . ..

(ሎሬት ፀጋዬ ገ /መድኅን ቀዌሳ)