SOA COMMUNITY POLICE 2 CAMPUS
606 subscribers
784 photos
39 videos
81 files
34 links
ይህ ድህረ ገፅ የተለያዩ የትምህርት አይነቶች አጠቃሎ የያዘ ሲሆን የሚለቀቁት ጥያቄዎችም ሆኑ ማስታወሻዎች በቀላሉ ታገኛላችሁ። በ👉👉👉SOAPO2
Download Telegram
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from SOA
Forwarded from SOA
Forwarded from SOA
Forwarded from SOA
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
እርሶስ ቤት ?

" ልጆች ስልክ ከያዙ ጥናታቸውን እስከጭራሹ እየረሱት ተቸገርን። ምን ብናደርግ ይሻላል ? " - ወላጆች

➡️ " ወላጆች አልገባቸውም ገና ለልጆቻቸው ቦምብ ነው እያሳቀፉ ያሉት " - የሥነ ልቦና ባለሙያ

በተለይ በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ያሉ ልጆች ከማጥናት፣ ከመታዘዝ ይልቅ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ላይ በመቸከል በከፋ ሱስ እየተዘፈቁ፣ አልባሌ ነገር እየተለማመዱ መሆኑን ወላጆች ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የልጃቸውን ሁኔታ ያስረዱ አንዲት እናት፣ " አዝዠው የነበረውን ሥራ ለመስራት ‘እሺ’ ካለኝ በኋላ ስልክ ሲጠይቀኝ አይሆንም ስለው ሁሌም ትዕዛዝ አይፈጽምም " ሲሉ ስለ 12 ዓመት ልጃቸው ድርጊት ተናግረዋል።

" የጥናት ጊዜውን ራሱ ስልክ ከያዘ ስለሚረሳው ከአባቱ ጋር ሁሌ ግጭት ነው። ሁሌም ይቀጣል ግን ሊስተካከል አልቻለም " ያሉት እኝሁ እናት፣ " በትምህርቱ አንደኛ ደረጃ ለቆ አያውቅም አሁን ሰንፏል። ምን ባደርገው ይሻላል? " ሲሉ ጠይቀዋል። 

ሌላኛው ወላጅ፣ " ልጄ ስልክ ላይ ከተጣደ አይንቀሳቀስም። መመገብንም ይዘነጋዋል። ዝም ዝዬ ስከታተለው ጌም ብቻ ሳይሆን ሌሎች አስነዋሪ ነገሮችንም ነው የሚመለከተው " ሲሉ ተናግረዋል።

" በተለይ የአዲሱ መፅሐፍ ህትመት በወቅቱ ባለመድረሱ ለሶፍት ኮፒ ማንበቢያ ስልክ ከገዛሁ በኋላ ነው እንዲህ የሆነው " ሲሉ ምንክንያቱን አስረድተዋል።

እኛም የህፃናት የስልክ አጠቃቀማቸው ላይ ምን መደረግ አለበት ? ስንል የሥነ ልቦና ባለሙያ የሆኑትን ቴዎድሮስ ድልነሳውን (ከእርቅ ማዕድ የሥነ ልቦና ማዕከል) አስተያዬት ጠይቀናል።

ባለሙያው አቶ ቴዎድሮስ ድልነሳው ምን አሉ ?

" እኛ አንድ የስልጠና ሴንተር አለን ከባጀት ዩዝና አዲክሽን ጋር የተያያዘ። ክላስ ላይ ራንደም አሰስመንቶች እሰራለሁና ከፍተኛ ነው ቁጥሩ አላግባብ የሆነ ሱስ የማስያዝ ደረጃ የሚደርስ አጠቃቀም ያላቸው።

አብዝተው የሚጠቀሙ፣ ሲቀር ቅር የሚላቸው፣ ክላስ ቁጭ ብለው ስለሱ የሚያስቡ፣ ከሰዎች ጋ ኮኔክት የማያደርጉ፣ ሲታዘዙ በጣም የሚነጫነጩ፣ ብቸኝነት የሚሰማቸው፣ ማቆም የሚከብዳቸው ብዙ ልጆች ናቸው።

ወላጆች ብዙ ፈተና ነው ያለባቸው። ግን ሳይቃጠል በቅጠል ነው መሆን ያለበት። ስልክ፣ ታብሌት አለመስጠት ነው።

ቴሌቪዥንም ህፃናት በአሁኑ ወቅት እቤት እንዲመለከቱ ሪኮመንድ አላርግም በእውነቱ። በሳምትንት አንዴ ወይም ሁለቴ የሚከፈት ካልሆነ በስተቀር። ምክንያቱም ቲቪ ላይ ራሱ ዩቱብ አለው
" ብለዋል።

መፍትሄውን በተመለከተ ባለሙያው ምን አሉ ?

" ስልክን ጨምሮ ሌሎች ዲቫይሶች በሌለበት ቤት ልጆችን ማሳደግ በጣም ጥሩ ነው። ወላጆች ደግሞ ስልካቸው ላይ ስለሚጣዱ ልጆችም ስልክ ላይ ይጣዳሉ። 

ልጆች ስልክ፣ ታብሌት መጠቀም የሚማሩት ከወላጆቻቸው ነው። ወላጅ ሥራ ሰርቶ ሲያበቃ ስልክ እነጎረጎረ መቀመጥን እንደ ኖርማል ካየው ከዚያ ይጀምራል ችግሩ።

ለልጆች ሰዓት መገደብን፣ ዲሲፕሊንድ መሆንን ማስተማር ያስፈልጋል። ሚዲያ ሊትረሲ እንደሚባለው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሊትረሲም አለና የቴክኖልጂ ሊትረሲ ያስፈልጋል።

መጀመሪያ ወላጅ መማር፣ መሰልጠን አለበት። ወላጆች አልገባቸውም ገና ለልጆቻቸው ቦምብ ነው እያሳቀፉ ያሉት። ቢላ ሽንኩርት ይቆርጣል ግን ደግሞ እጅም ይቆርጣልና እንኳን ልጆች ወላጆች እተቆራረጠ ነው እጃቸው
" ሲሉ አስገንዝበዋል።

ወላጆች ለልጆቻቸው ስልክም ሆነ ታብሌት የሚሰጧቸው የልጆቻቸውን ፍላጎት ያሟሉ ስለሚመስላቸው ጨምር ነውና በዚህ ረገድ ምን ማስተዋል አለባቸው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም ባለሙያው ተከታዩን ምክር ለግሰዋል።

ምን አሉ ?

“ ወላጆች ማስተዋል አለባቸው። የግንዛቤ ችግር አለ። ግንዛቤ ሰፊ ሥራ ነው የሚፈልገው። ልጅ የሚያስፈልገው ምንድን ነው ? የሚለው ነው ግንዛቤው።

ልጅ የሚልገው ሌላ ነው የሚያስፈልገው ደግሞ ልላ ነው። ልጆች ጓደኞቻቸው ታብሌት ይዘው ካዩ ይገዛ ሊሉ ይችላሉ ግን የሚያስፈልጋቸውን የሚያውቀው ወላጅ ነው።

ስለዚህ ወላጅ መሪ እንጂ ተመሪ አይደለም። ልጅ የፈገውን  ነገር ሁሉ ማሟላት አይደለም ሥራው። ይህን መረዳትና ማወቅ በጣም ወሳኝ ነው።

ወላጅ ለመሆን ማነው ያስተማረን ? ከየት ነው እውቀታችን የመጣው ? ብለን መጠየቅ መቻል አለብን ካለዛ በመላ ነው ልጆች የምንመራው ማለት ነው።

በመላ የሆነ ነገር  ደግሞ እንደ እድል ነውና ጥሩም መጥፎም ይወጣዋል። ስለዚህ በጥበብ፣ ዘመኑን በዋጀ፣ መንፈሳዊ ህይወትን፣ ባህልን፣ ኑሯችንን ባማከለ መልኩ መኖር ነው ነጥቡ
" ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Forwarded from SOA
Forwarded from SOA
Forwarded from SOA