SOA COMMUNITY POLICE 2 CAMPUS
606 subscribers
784 photos
39 videos
81 files
34 links
ይህ ድህረ ገፅ የተለያዩ የትምህርት አይነቶች አጠቃሎ የያዘ ሲሆን የሚለቀቁት ጥያቄዎችም ሆኑ ማስታወሻዎች በቀላሉ ታገኛላችሁ። በ👉👉👉SOAPO2
Download Telegram
ውድ የተከበራችሁ ወላጆች /አሳዳጊዎች፦
ዘግይቶ ከክፍለከተማ የትምህርት ፅህፈት ቢሮ በወረደ መመሪያ መሰረት በነገዉ እለት 10/05/2015 ትምህርት ሙሉ ቀን የማይኖር መሆኑን እየገለፅን ሐሙስ እና አርብም በተመሳሳይ ሁኔታ ትምህርት አይኖርም።

ፈተና ሰኞ ይጀምራል::

መልካም ጥናት።

ሪሀና 0911532699
አዳነ 0926397951
ውቢት 0913562132
አሸብር 0912 061560
አሰግድ 0922105847
📖📖📖📖📖📖 🖊️🖊️🖊️🖊️🖊️🖊️

Dear parents / Guardians

According to the late arrived command from the  govt education office, we would like to inform you that tomorrow,January 18/2023, there will be no school for the whole day. Besides, there will be no school on Thursday and Friday too.

> Exam will commence on Monday
Enjoy your study
Rank Students 2022/23👍👍👍
(ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን)
ዋ! ..... ያቺ ዓድዋ
ዋ! ...
ዓድዋ ሩቋ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋቋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋቋ።

ዓድዋ.....
ባንቺ ብቻ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና፣
አበው ታደሙ እንደገና።

ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስቷ፣
የደም ትቢያ መቀነቷ።
በሞት ከባርነት ሥርየት፣
በደም በነፃነት ስለት፣
አበው የተሰውብሽ ለት።
ዓድዋ!
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ፣
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ።

ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ፣
ታድማ በመዘንበልዋ።
ዐፅምሽ በትንሳኤ ንፋስ፣
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ።
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ፣
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ፣
ብር ትር ሲል ጥሪዋ፣
ድው እልም ሲል ጋሻዋ፣
ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ።

ያባ መቻል ያባ ዳኘው፣
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣
ያባ በለው በለው ሲለው፣
በለው በለው በለው በለው።

ዋ! ...... ዓድዋ .....
ያንቺን ፅዋ ያንቺን አይጣል፣
ማስቻል ያለው አባ መቻል።
በዳኘው ልብ በአባ መላው፣
በገበየሁ በአባ ጎራው፣
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው፣
በለው ብሎ በለው በለው።

ዋ! ...... ዓድዋ .....
ዓድዋ የትናንትናዋ፣
ይኸው ባንቺ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና፣
በነፃነት ቅርስሽ ዜና፣
አበው ተነሱ እንደገና።

....... ዋ! ........ ያቺ ዓድዋ፣
ዓድዋ ሩቅዋ ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ።
ዓድዋ .......
የካቲት - (፲፱፻፷፬ -ዓድዋ)
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን/
¶ ዓድዋ ¶
የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የተፈጥሮ ቅርስ መዘክር ማዕከል
ቀን 1/7/2015 ዓ.ም

ማስታወቂያ!

በ2015 የትምህርት ዘመን 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ እና ሀገራቀፍ ፈተና ተፈታኝ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ

ቀደም ሲል በቀጥታ / ኦላይን መመዝገባችሁ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋርም በተያያዘ የተመዘገባችሁበትን መረጃ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንዲቻል

ለ6ኛ ክፍል https://aa6.ministry.et እና

ለ8ኛ ክፍል https://aa.ministry.et ሊንኮችን በመጫን View Result የሚለውን በመጫን የመለያ ቁጥራችሁን እና ስም / Registration Number and First Name በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ስህተት ካለበት ለትምህርት ቤታችሁ በስቸኳይ እንድታሳውቁ እናሳስባለን፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
ክብሩን እንደያዘ ሞቱን ያስቀደመው ቦረና....

የሞያሌ ከተማ ምክትል ከንቲባ ከሆነው ጉዮ ጋር እያወጋን ባለበት እንድ የሚከነክነኝን ጥያቄ ጣል አደረኩለት

"ቦረና ይህን ያህል ለምን ጉዳት ሊደርስበት ቻለ? ለምን በግዜ ጉዳቱን ለማወቅ ተሳናቹህ"

ወጣቱ ምክትል ከንቲባ ተናገረ " በቦረና ዘንድ ማጣት እጅግ ነውር ነው። ያ... ትናንት ውሀ ሲጠይቁት ወተት የሚያጠጣው ህዝባችን በቤቱ የሚቀምሰውን ሲያጣ ወደ አደባባይ አልወጣም ። ማጣቱን ጭምር ማንም እንዲያውቅበት አይፈቅድም። ማጣት ለቦረና ከሞት ባልተናነሰ መልኩ የሚታይ በመሆኑ ቦረና ረሀቡን ወደ ውጭ ማውጣት አልደፈረም።

እኛም ይህን ባህሉን ስለምናውቅ ቤት ለቤት እየዞርን የምግብ እጥረት ያለባቸውን ለመለየት የሄድንበት መንገድ አዋጭ አልሆነልንም። ረሀብ እንደጸናባቸው ለእኛም ጭምር ሊነግሩን ስላልፈቀዱ ረሀቡ በጸናባቸው መንደሮች ላይ አንድ ውሳኔያችንን ለህዝቡ አሳወቅነው...

"ከየትኛውም ነዋሪዎች ቤት ውስጥ ጪስ ሲጨስ ካልተመለከቱ ጎረቤቶቻቸው ለእኛ ሪፖርት እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ህግን ጣልንባቸው።(ጪስ ካልጨሰ ምግብ እንደሌላቸው የሚታወቅበት ዘዴ ) እናም ብዙዎች ከተፈራው ጉዳት ለማገገም ቻሉ"
ከጉማ
Students in their school from the ETV entertainment program.
1. Creative work
2. Literature
3. Painting
4. Dance