SOA COMMUNITY POLICE 2 CAMPUS
605 subscribers
784 photos
39 videos
81 files
34 links
ይህ ድህረ ገፅ የተለያዩ የትምህርት አይነቶች አጠቃሎ የያዘ ሲሆን የሚለቀቁት ጥያቄዎችም ሆኑ ማስታወሻዎች በቀላሉ ታገኛላችሁ። በ👉👉👉SOAPO2
Download Telegram
Forwarded from SOA
Forwarded from SOA
የ2018 ዓ.ም. ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራ ይጀምራሉ ፤ትምህርት ሚኒስቴር

ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ሞባይል ስልክ ፣ ታብሌትና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቀቁሶችን ይዞ ትምህርት ቤት መምጣት ተከልክሏል፡፡

----------------------------------------

(ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም) የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቶች አከፋፈት አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የበይነ-መረብ ምክክር ባደረገበት ወቅት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ እንደገለጹት የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 5/ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል።

በትምህርት ካሌንደሩ መሠረት ዓርብ መስከረም 2 / 2018 ዓ.ም. ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው መምህራንና ተማሪዎች ውይይት የሚያደርጉበትና መስከረም 5/2018 ዓ.ም ደግሞ በይፋ ለሚጀመረው የትምህርት ስራ ቅድመ ዝግጅት የሚያደርጉበት ቀን መሆኑንም ክብርት ወ/ሮ አየለች አስታውቀዋል፡፡

በ2018 የትምህርት ዘመን ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራንና የዘርፉ ባለድርሻዎች የጀመሩትን የንቅናቄ ተግባር አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባና የትምህርት ቤት ምዝገባም እስከ መጨረሻው ቀን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የተማሪዎችን ሥነ ምግባር በተመለከተም ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በየትኛውም ክልልና የከተማ አስተዳደር የሚገኝ ተማሪ ተንቀሳቃሽ ስልክ ፣ ታብሌትና ማናቸውንም የትምህርት ስራ ላይ ተጽእኖ ሚያሳድሩና አዋኪ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ይዞ መገኘት ክልክል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ አስገንዝበዋል፡፡

በበይነ መረብ በተካሄደው ምክክር የትምህርት ጥራትና ፕሮግራሞች መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሀንስ ወጋሶ (ዶ/ ር) የ2018 የትምህረትት ዘመን የትምህርት ቤቶችን አከፋፈት ጋር ተያይዞ የባለድርሻ አካላት ሚና ፣የትምህርት ቤቶች ዝግጅት፣ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርት አካባቢ በመፍጠር፣ በትምህርት ለትውልድና በሌሎችም ዙሪያ ስትራቴጂክ እቅድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በምክክር መድረኩ የተሳተፉ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው ለ2018 የትምህርት ዘመን አከፋፈት ፣በተማሪዎች ምዝገባ ፣ በትምህርት አጀማመር፣ በመማር ማስተማር ስራውና በተማሪዎች ስነ ምገባር ዙሪያ አፈጻጸሞቻቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
Forwarded from SOA
እንኳን ደስ አለን።
Forwarded from SOA
Forwarded from SOA
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር የት አለፈ ?

" ዘንድሮ 8.4 በመቶ ተማሪ ከ 50 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ፈተናውን አልፏል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እየተገለጸ ይገኛል።

በዘንድሮ አመት ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 8.4 በመቶ ተማሪ ከ 50 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ፈተናውን አልፏል ተብሏል።

ከፍተኛ ተማሪዎችን ያሳለፉ ክልሎች ፦
- አዲስ አበባ፣
- ሐረሪ
- አማራ ክልል ናቸው።

ዘንድሮ " የተፈታኙ ቁጥር ቀንሷል ያለፈው ተማሪ ቁጥር ግን ጨምሯል " ያሉት ትምህርት ሚኒስትሩ ዘንድሮ በአጠቃላይ 48,929 ተማሪዎች ማለፋቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው አመት ያለፈው ተማሪ ቁጥር 36,409 ነበር።

በጾታ ስብጥር
30,451 ወንድ ተማሪዎች አልፈዋል።
18,478 ሴት ተማሪ አልፏል።

በተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛ ውጤት

ወንድ 591/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
ሴት 579/600 ብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት

በማህበራዊ ሳይንስ
ወንድ 562/600 አምቦ አምቦ ቦርዲንግ ስኩል።
548 /600 ሴንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት።

አማካይ ውጤት
87 በመቶ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች
86 በመቶ ዓለማቀፍ ትምህርት ቤቶች
5.4 በመቶ የመንግስት ትምህርት ቤቶች
51 በመቶ የግል ትምህርት ቤት ውጤት

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia
Forwarded from SOA
Forwarded from Asegid
የ SOA ተማሪዎች መስቀል ፤ ቅርሶችን መጠበቅ ብሔራዊ መግባባትን ማጠናከር !!
በሚል መሪ ቃል በ ባህል አና ኪነጥበብ ቢሮ አዘጋጅነት እየተካሔደ በሚገኘው ዝግጅት ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ::