በዛሬው እለት ማለትም ቅዳሜ /ታህሳስ 18,2016 ዓ.ም.የአዲስ አበባ ከተማ ባህል እና ቅርስ እንክብካቤ ቢሮ ለተማሪዎች ባዘጋጀው ስለ ኢትዮጵያ ቅርሶች አያያዝ፣እንክብካቤ እና ማስተዋወቅ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ትምህርት ቤታችን ስኩል ኦፍ አሜሪካና በመርሃ ግብሩ ላይ ተማሪዎቹ እንዲሳተፉ በቀረበለት ግብዣ መሰረት ተማሪዎቻችን በመርሃ ግብሩ ላይ ታድመው ነበር።በመድረኩ በቅርስ ጥናት "ኤክሰፐርት"ለዝግጅቱ ታዳሚ ተማሪዎች ስለ ኢትዮጵያ ቅርሶች እንክብካቤ እና ጥበቃ በቂ እውቀት እና ግንዛቤ እንዲጨብጡ ይረዳቸው ዘንድ "ሌክቸር"ተሰጥቷቸዋል።
የት/ቤታችን ስኩል ኦፍ አሜሪካና ተማሪዎች በመርሃ ግብሩ ላይ ላሳዩት ንቁ ተሳትፎ ከፍተኛ ምስጋና እና ክብር የተቸራቸው ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ ከተሳተፉት ት/ቤቶች እጅግ የላቀ ተሳትፎ እና አፈፃፀም በማሳየታቸው በልዩ ሁኔታ አክብሮት እና እውቅና
ለት/ቤታችን እና ለተማሪዎቻችን የተሰጣቸው ሲሆን ሌሎች አቻ ት/ቤቶች
ከ ስኩል ኦፍ አሜሪካና አርአያነት ልምድ እንዲቀስሙ ከመድረኩ አስተባባሪዎች ጥቆማ ተሰጥቷቸዋል፡፡

Forwarded from Adane Eshete