የሀቅ አድማስ Official 🔰
517 subscribers
195 photos
74 videos
25 files
106 links
📌የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ ና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ።(እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣በርሱም ምንንም ማንንም ላናጋራ፣ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤በላቸው፡፡እምቢ ቢሉም፦እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡"[📚ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን:64]

🔥"እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙ"[📚ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን:102]!🔥
Download Telegram
ትምህርቱ ለብዙዎች እንዲደርስ በልበ-ቀናነት ሼር ይደረግ ባረከሏሁ ፊኩም🔥

عن سهل بن سعد، أنّه سمع النبيَّ ﷺ يقول: «واللَّهِ لأنْ يهدي اللَّه بك رجلًا واحدًا خيرٌ لك من أن يكون لك حمرُ النَّعَم».

«الدال على الخيرِ كفاعلِه»
5
የኔ ወንድም😁🙃
😁6😭6🤮4
👉Link ሼርርርርርርርር ጀመዓው ወደ 600🔥🔥
Live stream finished (7 minutes)
አንድ የመሬቷ ኦርቶዶክስ ዲያቆን የመለሰልን መልስ ነው🔥
👏5
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: «إِنَّمَا بُعِثْتُ لِأُتَمِّمَ مَكَارِمَ الْأَخْلَاقِ».
(رواه الإمام مالك في الموطأ، والإمام أحمد في مسنده، والبيهقي في شعب الإيمان، وصححه الألباني)


ከአቡ ሁረይራ ተይዞ የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ"እኔ መልካም ሥነ ምግባርን ለማሟላት ተልኬያለሁ።"

[📚 Musnad Ahmad እና Al-Adab al-Mufrad ሸይኽ አልባኒይ ሶሂህ ብለውታል]
2
قال العلامة ابن باز رحمه الله-:

" الدفاع عن الإسلام، والذب عن الشريعة، ونشر العِلْم، ورد الشبهات؛ من أفضل القُربات، ومن الجهاد في سبيل الله، بل هو من أعظم الجهاد في هذا العصر ".

📚مجموع الفتاوى (٣٠٤/٧)

ሸይኽ ኢብኑ ባዝ አሏህ ይርሀማቸውና እንዲህ አሉ▼▼▼▼▼▼▼

«ለዲናል እስላም መከላከል፣ለሸሪዓ ዘብ መቆም፣ዲናዊ ኢልምን(እውቀትን) ማሰራጨትና ማስፋፋት ፣ለሹብሃዎች(ለማምታቻዎች ወይም ማደናገሪያዎች) መልስ መስጠት በአሏህ መንገድ ላይ መታገል ነውና በል እንዲያውም በዚህ ዘመን ከጂሃድም(በአሏህ መንገድ ላይ ከመታገልም) ይበልጣል»።

[📚መጅሙዕ-አል-ፈታዋ 7/304]


➥◈የቴሌግራም ቻናላችን||
https://t.me/Rightpathstudent

ሁላችሁም ጆይን በሉ ሼር ይደረግ!
🥰31
Kesis Solomon
Voice message
ከመሬቷ ኦርቶዶክስ መምህር ቀሲስ ያገኘነው መልስ ነው እንዲያውም ፆታም አላቸው እያሉ ነው!🔥
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
الشيخ الفاضل محمد بن سعيد رسلان المصري حفظه الله تعالى
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
الشيخ محمد بن سعيد رسلان المصري حفظه الله تعالى!
አንዳንድ ሰው እንደህፃን ነው እንዴ የሚያስበው ወረቢ ብቻዬን ልኑርበት እላለሁ Left😂
😁4
💪ጀግናው💪

ሰልማን አል ፋሪስ

               ክፍል 1


ለጋ ወጣት ነው ... ክብርና ስልጣን ፤ ሀይልና ዝና ባለው ቤት ውስጥ አደገ በህዝቦቹ ውስጥ የተከበረ በሀገሩም የተፈራ ነው ፡፡ … ከእኩያዎቹ ቀዳሚ ነወ በዘመኑ ልዩ ሰው ነበር … ሰልማኑል ፋሪሲይ ( ረ.ዐ ) ... እሳት የሚያመልከ መጃስ ነበር አባቱም የህዝቦቹ አለቃ ነው ... አባቱ በጣም የሚወደው ሲሆን ቤቱ ካለ እሳት እንዳይንቀሳቀስ አድርጎታል ፡፡
ሰልማን ከእሳት ጋር ያለው ግንኙነት በጣም ከመብዛቱ የተነሳ የእሳ አቀጣጣይ እስኪሆን ድረስ ለመጁስ ሰርቷል ፡፡ አባቱ የአትክልት ቦታ የነበረው ሲሆን ሁል ጊዜ ወደ አትክልት ቦታው ይሄዳል … .. አንድ ቀን በቤት ግንባታ ተጠመደና ለሰልማን “ ወደ አትክልት ቦታ ሂድና ይህን ይህን ስራ አለው … . ሰልማ ተደሰተ ፡፡ አስሮ ከያዘው ነገርም ወጣ ፡፡ ወደ አትክልት ቦታው እየሄደ በመንገድ ላይ እንዳለ በክርስቲያኖች ቤተክርስቲያን አጠገብ አለፈ ፀሎት ሲያደርጉም ሰማም … ምን እንደሚሰሩ ለማየት ወደ ውስጥ ገባ … ፀሎታቸውን ሲመለከት በጣም ስለደነቀው እነሱን መከተል ፈለገ ... በልቡም፡- ይህ እኛ ካለንበት ሀይማኖት የተሻለ ነው አለ ... ስለ ሀይማኖታቸውም ጠየቃቸው የሀይማኖታች መሰረት ያለው በሻም ነው … በሀይማኖቱም በጣም አዋቂው ያለው እዚያው ነወ አሉት . ፀሀይዋ እስክትገባ ድረስ እነሱ ጋር አሳለፈ ፡፡ ወደ ቤቱ ሲመለስ አባቱ “ ልጄ ሆይ ! የት ነበርክ አለው . በመንገድ ላይ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ ፀሎት ሲያደርጉ ተመለከትኩ … ከነገራቸውና ከፀሎታቸው ያየሁት ነገር በጣም ደነቀኝ … ሀይማኖታቸው ከኛ ሀይማኖት የተሻለ መሆኑን አየሁ አለው ፡፡ አባቱ ደነገጠና ... ልጄ ሆይ ሀይማኖትህና የአባቶችህ ሀይማኖት ከእነሱ ሀይማኖት የተሻለ ነው አለው ፡፡ ልጁም በአላህ ይሁንብኝ አይደለም ... የእነሱ ሀይማኖት በላጭ ነው አለ ፡፡ ልጁ ከመጁስ ሀይማኖት እንዳይወጣ አባቱ ስለፈራ በእግሩ ላይ ማሰሪያ ከአደረገ በኋላ በቤቱ ውስጥ አሰረው … ሰልማን ይሄን ያየ ጊዜ ወደ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሎ መልዕክት ላከ፡- ሀይማኖታችሁን ወድጄዋለሁ .. ወደ ሀይማኖቱም መግባት እፈልጋለሁ ... ከሻም ከርስቲያኖች የሆኑ ቅፍለቶች እናንተ ዘንድ ከመጡ አሳውቁኝ የሻም ቅፍለቶች ብዙም ሳይቆዩ መጡ ፡፡ ወደ ሰልማንም ላኩበት … ሰልማንም ነጋዴዎቹ ጉዳያቸውን ጨርሰው ወደሻም መመለስ ሲፈልጉ ንገሩኝ ብሎ መልዕክተኛ ላከ … ነጋዴዎቹ መመለስ ሲፈልጉ ለሰልማን ላኩበት … በሆነ ቦታ ላይም ተቀጣጠሩ … እግሩ ላይ ያለውን ማሰሪያ ዘዴ ፈልጎ ከፈታው በኋላ ከነሱ ጋር ወደ ሻም ሄደ … ሻም ከገባ በኋላ በዚህ ሀይማኖት በእውቀት የሚበልጠው ማነው ብሎ ጠየቃቸው ... ቤተ - ክርስቲያን ያለው ቄስ ነው አሉት ፡፡ ወደ ቤተከርስቲያኑ ሄደና ቄሱ ታሪኩን ነገረው ፡፡ እንዲህም አለው … .. እኔ ይህንን ሀይማኖት ወድጄዋለሁ … አንተን እንድካድምህ ፣ አብሬህ እንድፀልይና ከአንተም እማር ዘንድ አብሬህ መሆን እፈልጋለሁ … ቄሱም ....

         ከተመቻችሁ

               ይቀጥላል
8
💪🏼ጀግናው 💪🏼
ሰልማን አል ፋሪስ

ክፍል ሁለት (2⃣)

አንተን እንድካድም ፤ አብሬህ እንድፀልይና ከ አንተም እማር ዘንድ አብሬህ መኖር እፈልገለሁ...

ቄሱም ከእሱ ጋር እንዲሆን ፈቀደለት...
ሰልማን በቤተክርስቲያን ውስጥ ከርሱ ጋር አብሮ ቆየ ... ሰልማን መልካም በመስራት ላይ እና በፀሎትና አምላክን በመገዛት ላይ በጣም ጠንካራ ነበር … ቄሰ ግን በሀይማኖቱ ላይ በጣም መጥፎ የሆነ ሰው ነው … ሰዎች ምፅዋት እንዲያወጠ ካዘዛቸውና ካበረታታቸው በኋላ ገንዘቡን ሰብስበው ወደ እርሱ ሲያመጡለት ለራሱ ያጠራቅማል ፡፡ ለሚስኪኖች አይሰጥም ፡፡ ሰልማንም በጣም ጠላው --ነገር ግን ይሄንን የቄሱን ስራ ለማንም መናገር አይቻልም ---- ምክንያቱም ቄሱ በህዝቡ ውስጥ ተሰሚነት አለው ፡፡ ሰልማን ግን እንግዳ ከመሆኑም በተጨማሪ ወደሃይማኖቱ አዲስ የገባ ነዉ -ቄሱ ብዙም ሳይቆይ ሞተ --ህዝቦቹ በእሱ ሞት አዘኑ --ሊቀብሩትም ተሰባሰቡ ሰልማንም አዝነዉ ያያቸዉ ጊዜ ይህ ሰዉ መጥፎ ነበር --- ምጽዋት እንድታመጡ ያዛችሁና ያበረታታችሁ ነበር-- ነገር ግን እናንተ ሰብስባቹሁ ካመጣችሁ በኋላ ለራሱ ነወ የሚጠቀመዉ , ለምስኪን ቅንጣትም አይሰጥም ነበር አላቸዉ እነሱም ማስረጃህ ምንድን ነዉ ? አሉት-- ያጠራቀመዉን ድልብ አሳያችኋለሁ አላቸዉና ገንዘበ ያለበት ቦታ ይዟቸዉ ሄዶ -- ቦታዉን ቆፈረዉ በወርቅና በብር የተሞላዉ ዘጠኝ ጉድጓዶቹን አወጡ-- በአላህ ይሁንብን ! በፍጹም አንቀብረዉም አሉና እንጨት ላይ ሰቅለዉ በድንጋይ ወገሩት ቤተክርስቲያን ዉስጥ በእሱ ቦታ ሌላ ሰወ አምጥተዉ አደረጉ --- ሰልማን አዲሱን ሰዉየ በጣም ወደደዉ . ስለ እሱ እንዲህ ይላል ፦ ከክርስቲያኖች ከእሱ የበለጠ መልካም ሰዉ ... ከእሱ የበለጠ ለአኼራ የሚጓጓ ሰዉ አላየሁም ..ከዚህ በፊት ማንንም እንደሱ ዱኒያን ችላ የሚልና ሌት ከቀን የሚጸልይ ሰዉ አላየሁም .. ከዚህ በፊት ማንንም እንደሰ ወድጄ የማላዉቀዉ የሆነን ዉዴታ ወደድኩት … ሰልማን ሰዉየዉን እስኪሞት ድረስ _ ካድሞታል ..በመሞቱም በጣም _ አዘነ ..ሰልማን ከእሱ ሞት በኋላ በሀይማኖት ላይ ፅናት እንዳያጣ ስለፈራ ..ለሰዉየዉ ፦ እገሌ ሆይ ! በአላህ ትእዛዝ ልትሞት ተቃርበሃል ከማን ጋር እንድሄድ ትመክረኛለህ አለዉ ... ሰዉየዎም .. ልጆ ሆይ ! በአላህ ይሁንብኝ .. እኔ ባለሁበት ሃይማኖት ላይ አንድንም ሰዉ አላዉቅም ሰዎች ሁሉ ጠፍተዋል ዲናቸዉን በርዘዋል-- ከሃይማኖታቸዉ ብዙ ነገሮችን ትተዋል ... በሞሱል ያለ አንድ ሰዉ ሲቀር ... እሱ እኔ ባለሁበት ሃይማኖት ላይ ነዉ .. ከእሱ ጋር ተገናኝ አለዉ ...



ይ ቀ ጥ ላ ል

✍🏼heyru

https://t.me/Rightpathstudent
👍3
💪🏼ጀግናው 💪🏼
ሰልማን አል ፋሪስ

ክፍል ሶስት(3️⃣)


መልካሙ ሰው የሞተ ጊዜ ሰልማን ከሻም ወደ ኢራቅ ሞሱል ካለው ሰው ጋር ተገናኘ  ይህም ሰውየ እስኪሞት ድረስ አብሮት ቆየ ሰውየው ሊሞት ሲል ሰልማን በነሲቢን ከሚገኝ ሰው ጋር እዲሄድ መከረው  ሰልማንም እደገና ወደ ሻም አቀና ...  ከነሲቢን ከሚገኘው ሰውየም ጋር እስኪሞት ድረስ አብሮት ቆየ .. ሰውየው ሊሞት ሲል በሻም ውስጥ ከምትገኝ ዑመር በምትባል ቦታ ከሚገኝ ሰው ጋር እዲግዳኝ መከረው    ሰልማንም ወደ ዑመሪያው ሰውዬ ጋር ሄደ ከሰው ጋር አብሮ መኖር ጀመረ  በዚህ ቆይታውም ብዙ ሀብትና ከብቶች አፈራ ብዙም ሳይቆይ ይህም ሰው ታመመ   ሊሞት ተቃረበ ሰልማንም አዘነ   እከሌ ሆይ ከማን ጋር እድሆን ትመክረኛለህ አለው ። መልካሙም ሰውዬ ሰልማን ሆይ በአላህ ይሁንብኝ አሁን እኛ ባለንበት ሀይማኖት ላይ ያለ ሰው ማንንም አላውቅም    ሰዎች ሀይማኖታውን ለውጠዋል  ነገር ግን በቀጥተኛው የኢብራሂም /ዐ.ሰ/ ሀይማኖት ላይ ነብይ የሚላክበት ዘመን ተቃርቧል ..... በአረብ ምድር ይነሳል በሁለት ተራሮች መካከል ወዳለችና የቴምር ምድር የሆነችው ሀገር  /መዲና/ ይሰደዳል ... በእሱ ላይ የማይደበቁ የሆኑ ምልክትች አሉት ።
📎  ስጦታ ይቀበላል /ይመገባል /
📎 ምጸዋት/ ሰደቃ /አይበላም
📎 በትከሻው መሃከል የነብይነት መሀተም አለው

ያየኸው ጊዜ ታውቀዋለህ ወደዚች ሀገር መሄድ ከቻልክ ሂድ አለው ሰውየውም ሞቶ ተቀበረ .. ሰልማን ነብይ ወደሚላክበት ሀገር የሚወስደውን እየፈለገ በዑመሪያ አላህ የፈቀደውን ያክል ቆየ ። በዚህ ሁኔታ ላይ ከከሊብ ጎሳ የሆኑ ነጋዴወች ጋር ተገናኘ ሀገራቸውን ሲጠይቃቸው ከዐረብ ምድር የመጡ መሆናቸውን ነገሩት እሱም ወደ ሀገራቸው እንዲወስዱት ጠየቃቸው ። እሺ አሉትና ገንዘቡን ሰጣቸው ከእነሱ ጋር አብረው ወሰዱት አንተ በቋጥኛችን ስር ያለህ ባሪያችን ነህ በማለት በደሉት ለአንድ ይሁዳ ሰውየም ሸጡት ሰልማን ከራሱ መከላከል አልቻለም ይሄን የሁዳ እያገለገለ እሱ ጋር ሆነ ከዛም ከበኒ ቁረይሾች የሆነ አንድ የሁዳ ሰልማንን ከዚህ ሰው ገዝቶ ወደ መዲና ወሰደው ሰልማን ሀገሪቷን ዘንባባዎቿን ተራራዎቿን በተመለከተ ጊዜ ቄሱ የገለፀለት ነብይ የሚላክበት ሀገር...


React እያረጋችሁ እሽ ውዶቸ

ይ ቀ ጥ ላ ል


Join my channel

https://t.me/Rightpathstudent
4🔥1
💪🏼ጀግናው 💪🏼
ሰልማን አል ፋሪስ

ክፍል አራት (4️⃣)


ሰልማን ሀገሪቷን ዘንባባዎቿን ተራራዎቿን በተመለከተ ጊዜ ቄሱ የገለፀለት ነብይ የሚላክበት ሀገር መሆኗን አወቀ . መዲና ተቀምጦ የሚላክ ነብይን ወሬ ይጠባበቅ ጀመር ... በዚህ ሁኔታ አመታት አለፉ .. አላህ /ሰ.ወ/ መልእክተኛዉን ላከ .. በመካ እንዲቆዩ ያሻዉን ያክል አቆያቸዉ ሰልማን ዩሁዲዉን በማገልገል በጣም የተወጠረ ስለሆነ ረሱል /ሰ.አ.ወ/ መላካቸዉን አልሰማም ..ከዚያም ነብዩ /ሰ.አ.ወ/ ወደ መዲና ተሰደዉ እዚያዉ መኖር ጀመሩ ሰልማን ስለ እሳቸዉ ምንም አያዉቅም ..አንድ ቀን ከአሳዳሪዉ ዘንባባ ጫፍ ላይ ወጥቶ ይሰራል አሳዳሪዉም እዛዉ ተቀምጧል ፡፡ አንድ ይሁዲ ወደ አሳዳሪዉ መጣና እንትና ሆይ ! አውስና ኸዝረጅን አላህ ያጥፋቸዉ እነሱ አሁን ነብይ ነዉ ብለዉ ከሚያስቡት አንድ ከመካ ከመጣ ሰዉ ጋር በቁባእ ተሰብስበዋል .አለዉ ፡፡ ሰልማን ይህን የሰማ ጊዜ ሰዉነቱ ተርገፈገፈ ..ልቡ በለለች ..አሳዳሪዉ ላይ ሊዎድቅ እስኪቀርብ ድረስ ዘንባባዉ ተወዛወዘ . ሰልማንም ሰዉየውን ምንድንነዉ የምትለዉ ? ወሬዉ ምንድን ነዉ ? እያለ እየጮኸበት ከዘንባባዉ ቶሎ ወረደ ..ይህን በማድረጉም አሳዳሪዉ ተቆጡቶበት በሃይል በጥፊ መታዉ ፡፡ ከእሱ ምን ጉዳይ አለህ ? ወደስራህ ሂድ አለዉ .. ሰልማን ዝም አለ ስራዉን ለመጨረስ ዘንባባዉ ላይ ወጣ ፡፡ ልቡ የነብይነቱ ወሬ ላይ ተጠምዷል .. ቄሱ የገለጡለት የሆኑትን የነብይነት ምልክቶች በዚህ ነብይ ላይ ያሉ መሆናቸዉን ማረጋገጥ ይፈልጋል .. ሀድያ የሚቀበሉ .. ሰደቃ የማይበሉና በትከሻቸዉ መሀከል መሃተም ያላቸዉ መሆኑን ማወቅ ይፈልጋል ፡፡ ሲመሽ ያለዉን ምግብ ሰብስቦ ያዘና ረሱል /ሰ.አ.ወ/ ወዳሉበት መጣ ረሱልና ( ሰ.አ.ወ ) ባልደረቦቻቸዉ በቁባእ ተቀምጠዋል ፡፡ እሱም እናንተ እንግዶችና ባለጉዳይ መሆናቹሁን ሰምቻለሁ ፤ እኔ ዘንድ ለሰደቃ ብየ ያስቀመጥኩት ትንሽ ምግብ ነበረኝ እሱን አምጥቼላችኋለሁ አላቸዉና ምግቡን ረሱል /ሰ.አ.ወ/ ፊት አስቀመጠዉ ፡፡ ትንሽ ራቅ ብሎ ረሱል (ሰ.አ.ወ) ምን እንደሚሰሩ መመልከት ያዘ ፡፡ ረሱል ( ሰ.አ.ወ ) ወደ ምግቡ ከተመለከቱት በኋላ ወደ ሰሃቦቻቸዉ ዞረዉ ብሉ አሏቸዉ ..እሳቸዉ ግን ተቆጠቡ ፤ ሳይበሉ ቀሩ ፡፡ ሰልማን ይህን ያየ ጊዜ በልቡ ይቺ አንዷ ናት ሰደቃ አይበላም ፡፡ ሁለት ይቀራሉ አለ ፡፡ ከቀናት በኋላ ሌላ ምግብ ሌላ ምግብ ይዞ ረሱል ( ሰ.አ.ወ ) ዘንድ መጣ ፡፡ ሰላምታ አቀረበላቸዉና ሰደቃ የማትበላ መሆንህን አይቻለሁ ፡፡ ይቺ ደሞ አንተን በማክበር ያመጣኋት ስጦታ ናት ፡፡ ሰደቃ አይደለችም አላቸዉ ፡፡ ከዚያም ረሱል ( ሰ.አ.ወ ) ፊት ለፊት ላይ አስቀመጠዉ ፡፡ ረሱል ( ሰ.አ.ወ ) ከምግቧ ተመገቡ ሶሃቦችም ተመገቡ ሰልማን ይህን ያየ ጊዜ.....


ይ ቀ ጥ ላ ል

Join my channel 👇🏼👇🏼👇🏼

https://t.me/Rightpathstudent
2👍1
የሀቅ አድማስ Official 🔰
💪🏼ጀግናው 💪🏼 ሰልማን አል ፋሪስ ክፍል አራት (4️⃣) ሰልማን ሀገሪቷን ዘንባባዎቿን ተራራዎቿን በተመለከተ ጊዜ ቄሱ የገለፀለት ነብይ የሚላክበት ሀገር መሆኗን አወቀ . መዲና ተቀምጦ የሚላክ ነብይን ወሬ ይጠባበቅ ጀመር ... በዚህ ሁኔታ አመታት አለፉ .. አላህ /ሰ.ወ/ መልእክተኛዉን ላከ .. በመካ እንዲቆዩ ያሻዉን ያክል አቆያቸዉ ሰልማን ዩሁዲዉን በማገልገል…
💪🏼ጀግናው 💪🏼

ሰልማን አል ፋሪስ

ክፍል አምስት (5️⃣)

በመጀመሪያው ቀን ሰደቃን እንደማይበሉ ካረጋገጠ በኋላ፣ ሰልማን (ረድየላሁ ዐንሁ) ሁለተኛውን ምልክት ለማረጋገጥ ወሰነ።
ሁለተኛው ምልክት – ስጦታን ይቀበላሉ
በሌላ ቀን የተምር ፍሬ ይዞ ወደ ነቢዩ ﷺ መጣና፦
"ይህ ስጦታ ነው።"
አላቸው።
በዚህ ጊዜ ነቢዩ ﷺ ከተምሩ በሉ፣ ለሰሃቦቻቸውም ሰጧቸው።
ሰልማንም በልቡ፦
"ሁለተኛውም ምልክት ተሟልቷል።"
አለ።
ሦስተኛው ምልክት – የነቢይነት ማኅተም
ከጥቂት ቀናት በኋላ ነቢዩ ﷺ በአንድ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ነበሩ።
ሰልማን በቀስታ ወደ ኋላቸው ሄዶ በትከሻዎቻቸው መካከል ያለውን የነቢይነት ማኅተም ለማየት ሞከረ።
ነቢዩ ﷺ የሚፈልገውን ስለተረዱ፣ መደረቢያቸውን ትንሽ ወደ ጎን አደረጉ።
ሰልማንም የነቢይነት ማኅተሙን አየ።
ወዲያውኑ ወደ ነቢዩ ﷺ ቀርቦ በደስታ አለቀሰ።
ከዚያም ነቢዩን ﷺ አቀፈና፣
"እርስዎ የአላህ መልእክተኛ ነዎት።"
ብሎ እስልምናን ተቀበለ።
ታሪኩን ለነቢዩ ﷺ ነገራቸው
ነቢዩ ﷺ ሰልማንን፦
"ታሪክህን ንገረኝ።"
አሉት።
ሰልማንም ከፋርስ ጀምሮ፣ ከመነኮሳቱ ጋር ያሳለፈውን ሕይወት፣ የተታለለበትን ሁሉ በዝርዝር ነገራቸው።
ነቢዩ ﷺ እና ሰሃቦቹም በታሪኩ ተደነቁ።
ከባርነት ነፃ መውጣት
ሰልማን እስልምናን ቢቀበልም አሁንም ባሪያ ነበር።
ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሉት፦
"ከባለቤትህ ጋር የነፃነት ውል (ሙካተባ) አድርግ።"
ባለቤቱም ሁለት ትላልቅ መስፈርቶች አስቀመጠ፦
300 የተምር ችግኞች ተክለህ እስኪያድጉ ድረስ።
40 አውቂያ ወርቅ እንድትሰጠው።
ሙስሊሞች ረዱት
ሰሃቦች እያንዳንዳቸው የተምር ችግኝ አመጡ።
300ውም ተሟሉ።
ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦
"ሰልማን! ጉድጓዶቹን አዘጋጅ፤ ችግኞቹን ግን እኔ እተክላቸዋለሁ።"
ነቢዩ ﷺ 300ውንም በገዛ እጃቸው ተከሉ።
በአላህ ፈቃድ ከእነሱ አንዱም አልደረቀም፤ ሁሉም አደጉ።
ከዚያም ነቢዩ ﷺ የወርቅ ቁራጭ ሰጡት፣ በአላህ በረካም 40 አውቂያ ወርቅ የሚሆን ሆኖ ተገኘ።
በዚህ ሰልማን (ረ.ዐ.) ከባርነት ነፃ ወጣ።


ይ ቀ ጥ ላ

Join my channel
✍🏼https://t.me/Rightpathstudent
5
💪🏼ጀግናው 💪🏼

ሰልማን አል ፋሪስ

ክፍል ስድስት (6️⃣)


ሰልማን (ረድየላሁ ዐንሁ) ከባርነት ነፃ ከወጣ በኋላ ከነቢዩ ﷺ ጋር በሙሉ መኖር ጀመረ። ቁርአንን ይማር፣ ከነቢዩ ﷺ ሀዲስ ይሰማ፣ በጦርነቶችም ይሳተፍ ነበር።
የኸንደቅ ጦርነት
በ5ኛው የሂጅራ ዓመት፣ የቁረይሽ ጎሳ እና ሌሎች ጎሳዎች በአንድነት ተሰብስበው መዲናን ለመውረር ወጡ።
ሙስሊሞች ቁጥራቸው አነስተኛ ነበር፣ ስለዚህ ምን እንደሚያደርጉ ከነቢዩ ﷺ ጋር ተመካከሩ።
የሰልማን ሀሳብ
ሰልማን (ረ.ዐ.) እንዲህ አለ፦
"የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በፋርስ ጠላት ሲመጣብን በከተማው ፊት ኸንደቅ (ጥልቅ ጉድጓድ) እንቆፍር ነበር።"
ይህ በአረቦች ዘንድ ያልተለመደ የጦርነት ስልት ነበር።
ነቢዩ ﷺ ሀሳቡን ወዲያውኑ ተቀበሉ።
ሙስሊሞችም ከተማውን በኩል ኸንደቅ መቆፈር ጀመሩ።
ነቢዩ ﷺ ከሰሃቦች ጋር ሲሠሩ
ነቢዩ ﷺ ራሳቸው ድንጋይ ይሸከሙ ነበር፣ አፈርም ይቆፍሩ ነበር።
ሰልማንም በብርቱ እየሠራ ነበር።
ትልቁ ድንጋይ
አንድ ቀን ሊሰበር የማይችል ትልቅ ድንጋይ አገኙ።
ሰሃቦቹ ነቢዩን ﷺ ጠሩ።
ነቢዩ ﷺ መጥተው መጥረቢያ ያዙ።
የመጀመሪያውን ሲመቱ ታላቅ ብልጭታ ወጣ።
ሁለተኛውን ሲመቱ ሌላ ብልጭታ ወጣ።
ሦስተኛውን ሲመቱ ድንጋዩ ተሰበረ።
ነቢዩ ﷺ በእነዚህ ብልጭታዎች አላህ ወደፊት ለሙስሊሞች የሚሰጣቸውን ድሎች (የፋርስን፣ የሻምን እና ሌሎችን) አበሰሩ።
"ሰልማን ከእኛ ነው"
ከኸንደቅ በፊት ሙሃጂሮች፦
"ሰልማን ከእኛ ነው።"
አሉ።
አንሷሮችም፦
"አይ፣ ሰልማን ከእኛ ነው።"
አሉ።
ነቢዩ ﷺ ግን እንዲህ አሉ፦
"ሰልማን ከእኛ ነው፤ ከአህሉል በይት ነው።"
ይህ ለሰልማን (ረ.ዐ.) የተሰጠ ታላቅ ክብር ነበር።
ከኸንደቅ በኋላ
የጠላቶቹ ጦር ኸንደቁን ማለፍ አልቻለም።
ከዚያም አላህ ኃይለኛ ንፋስ ላከ፣ የጠላቶቹን ድንኳኖች ነቀለ፣ ጦራቸውም ተበተነ።
ሙስሊሞችም በአላህ እርዳታ ድል አደረጉ።
የሰልማን (ረ.ዐ.) አንድ ሀሳብ ለመዲና መዳን ትልቅ ምክንያት ሆነ።


ይ ቀ ጥ ላ ል

Join my channel 👇🏼👇🏼👇🏼
https://t.me/Rightpathstudent
3
وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا

                            በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»
9👍1