የሀቅ አድማስ Official apologetics 🔰
565 subscribers
223 photos
79 videos
27 files
103 links
▣የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ ና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ።(እርሷም) አሏህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣በርሱም ምንንም ማንንም ላናጋራ፣ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤በላቸው፡፡እምቢ ቢሉም፦እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡"[📚ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን:64]

🔥"እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙ"[📚ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን:102]!🔥
Download Telegram
♦️ፎቶ  የሚያስከትለዉ ጣጣና መዘዙ❗️

የራስን የምስትን የልጆችን ፎቶ በአልበም በስልክ ማስቀመጥ እንዲሁም ይባስ ብሎ ሚዲያ ለይ መልቀቁ ከአኼራው ቅጣት በፊት ዱንያ ለይ ብዙ ጣጣዎችን ያስከትላል።ይህ የአንዷን ፎቶ ድግምት ሰሪ ዘንድ በመውሰድ እንዴት ሲህር እንደሰሩባት ተመልከቱ።

▪️ብዙ እህቶቻችን ሚዲያ ላይ በሚለቁት ፎቶ ሰበብ ለቡዳ፣ ለአይንናስ፣ ለሲህር፣ ለመስተፋቅርና ለሌላም ከባባድ አደጋዎች በቀላሉ ይጋለጣሉ። ምክንያቱም ድግምት ሰሪዎች ድግምት ለሚያሰራው አካል ድግምት የሚሰራበትን ሰው የሆነ ነገሩ አምጣ ስለሚለው በቀላሉ ፎቶዋን ካገኘ ወስዶ ያንን ይሰጣል። በዚህ ጊዜ በሷ ላይ በቀላሉ ይህንን መስተፋቅር ወይም ሲህር ያሰሩባታል።

▪️በተለይ ፎቶዋን በየ ሚዲያው የምትለቅ ሴት ፎቶውን የሚያይ ሰው ሁሉ ጤነኛ አይደለም ቢባል ማጋነን አይሆንም።የአይን በሽታ ያለበት ሰው ፎቶውን ሲያይ ከማረከውና ካስደነገጠው ወዲያው በአይኑ ይበላታል። እሷ ግን አታውቅም ቆዳዬ ተላጠ፣ አሳከከኝ፣ ልቤ ተጨነቀ፣ ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል፣ ራሴ ሊፈነዳ ደረሰ፣ ሌላም ሌላም እንዲህ እንዲህ ሆንኩ በማለት በህመም ትሰቃያለች።ነገሩ ግን በሚዲያ የለቀቀችው ፎቶ ያመጣባት ጣጣ ሊሆን ይችላል።

▫️እንዲሁም ብዙ ወላጆች የሚያምሩ ልጆቻቸውን ፎቶ በማንሳት እስክሪን ሴቨር ፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግ ሁሉም እንዲመለከታቸው ያደርጋሉ። ስንቱ በአይን እየበላው እዚጋ አመመኝ ብሎ መናገር የማይችለው ምስኪን ልጃቸውን በህመም ያሰቃያሉ።
©️
👌ሴት እህቶችም ወንዶችም አሏህን ፈርታችሁ በተለይም ሴት እህቶቻችን ከዚህ ተግባራችሁ ራቁ አሏህን የሚያስቆጣ በራሳችሁ ላይ ሙሲባ(በላእ) የሚያመጣ ተግባር ነው።

🔀ሁሉም እንዲጠነቀቀው ሼር አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም
👍1
የረመዷንን ሌባ ተጠንቀቁ
➚➚➚➚➚➚➚➚

አንደኛ ሌባ፦ ↙️
      📺 ቴሌቪዥን በድራማና ቆሻሻ በሆነ ፕሮግራም ምክንያት የሰዎችን ፆም የሚያበላሽ አጅራቸውንም የሚቀንስ አደገኛ ሌባ ነው ቲቪ እንቅልፍ ከመተኛት ጭምር የሚከለክል አደገኛ ሌባ ነው!!!

ሁለተኛው ሌባ፦ ↙️
      🏢 የሱቅ ቦታ፦
ያለ ምንም ገደብ ገንዘብንና ወቅትን ለየት ባለ ሁኔታ የሚያባክን ሲሆን ይህን ለመቆጣጠር ከመሄድህ በፊት አስብበት ተጠንቀቅ!!!

ሶስተኛ ሌባ፦↙️
  👁 አለመተኛት፦ ውድ ግዜህን የሚነጥቅ በመጨረሻው አንድ ሶስተኛ ሌሊት ላይ ከተሀጁድ ከስቲግፋር የሚከለክል ከባድ ሌባ ነውና በአግባቡ ማስተዋል ያስፈልጋል።

አራተኛ ሌባ፦ ↙️
         🍱 ኩሽና፦
በተለይ ሴቶች!!! ረጅም ግዜ የተለያዩ ምግቦችን በማዘጋጀት ግዜያቸውን በኩሽና ውስጥ የሚጨርሱ አሉ! ደግሞኮ አይበሉትም ቀመስ ቀመስ አድርገው ብዙውን ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ይጨምሩታል!!! (እህቴ ሆይ!!! ረመዷንን የተለያዩ ምግቦችን በማዘጋጀት ግዜሽን አትፍጂ ይህን ስልሽ ጭራሽ ምግብ አትስሪ ማለቴ አይደለም!!! መቼም ግልፅ ነውና ሚዛናዊ ሁኚ ለማለት ነው። ፀሀፊው))

አምስተኛ ሌባ፦ ↙️
          📲 ስልክ፦ ለረጅም ግዜ ወሬ ማብዛት!!! በዛ ላይ ህሜቱ፣ ነገር ማዋሰዱ፣ አለተባለ እያሉ ግዜን መግደልና ሚስጥርን ማባከን እንዲሁም ብዙ የሚታዩ አልባሌ ነገሮችንም አቅፏል። ((አላህ ይድረስልን))

ስድስተኛ ሌባ፦ ↙️
          💵 ስስት፦
የሶደቃን አጅር የሚከለክል በተለይ የረመዷንን ወር ሶደቃ የሚከለክል ሌባ ነው።

ሰባተኛ ሌባ፦
   🌴 አላህ የማይወሳበት መጅሊስ፦ ያ ! የቂያማ ቀን በሰውየው ላይ ፀፀት የሚሆን አደገኛ ሌባ!!!

በመጨረሻም፦ ➘ ትልቁ ሌባ
      🌐 የመገናኛ ቡዙኃኖች፦
አላህን የሚያስወድድ ስራ ካልተሰራበት አደገኛ የረመዷን ሌባ!!!

አደራ ፍጠኑ! አደራ ፍጠኑ!! ያሉት ቀናቶች በጣም ትንሾች ናቸው። አላህ በሚወደው ስራ የምንጠቀምበት ወር ያድርግልን !!✍✍
👉   የፆመኛ ዱዓእ ✍

     የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም –
" ለፆመኛ ሰው ተቀባይነት ያለው ዱዓእ አለው " ብለዋል ።
   በመሆኑም አንድ ፆመኛ የሆነ ሰው ፀሀይ ከመግባቷ በፊት አፍጥር ሊቃረብ ሲል የሚያደርገው ዱዓእ መቅቡል ስለሆነ ልንዘናጋ አይገባም።ብዙ የተለያየ ሀጃ ያለባችሁ ወንድምና እህቶች በተለይ ከእዳ ጋር፣ከርዝቅ ማጣት ጋር የተያያዘ ሀጃ ያለባችሁ ስንቱ ፊት ቆማችኋል ? እስኪ ይህን አጋጣሚ ተጠቅማችሁ ለሁሉም እንደየፍላጎቱ ሰጥቶ አሁንም ቢጠይቁት የሚወደውን አምላካችሁን ደጅ አንኳኩ።የሰዎች ፊት ከመቆም ከጌታችሁ ፊት ቁሙ ያ አላህ በሉት።በናንተና በአምላካችሁ መካከል ያለውን ወንጀል ያመጣውን ርቀት ከመጝሪብ በፊት ቀደም ብላችሁ መስጂድ ገብታችሁ ኢስቲጝፋር በማድረግና የሱን ቃል በማንበብ አጥብባችሁ ለምኑት።ተዘግቶ የማያውቀውን የራሕመቱ ደጃፍ ቆማችሁ በዱዓእ በር ግቡ።
 
በዱንያ ላይ ሁሉም የተለያየ ሃጃ አለው።ሁሉንም አንድ የሚያደርገው የአኼራ ሃጃ አለና ሁላችንም የጭንቁን ቀን ከሚያልፉት ባሮቹ እንዲያደርገን አላህን እንማፀነው።ሰዓቱን አስቡት ልባችን ፍፁም ወደ አላህ እያሰበ አዕምሯችን ከሁሉ ነገር ነፃ ሆኖ በረሃብ በተሰባበረ አካል ያ አላህ ስንል ምን ግርዶ ይኖራል ? ለዚህ ነው መልእክተኛው በዛን ሰዓት ለፆመኛ ተቀባይነት ያለው ዱዓእ አለው ያሉት።

ثبت  في سنن أبي داوود من حديث عبد الله بن عمر رضي الله عنهما قال: كان رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا أفطر قال: ذهب الظمأ وابتلت العروق وثبت الأجر إن شاء الله. وحسنه الشيخ الألباني. 

ሌላው ዘሀበ አዝዘመኡ ( ጥሙ ተወገደ) ወብተለቲል ዑሩቁ ( ስሮች ረጠቡ) ወሰበተል አጅሩ ( አጅሩም ተረጋገጠ) የሚለው ዱዓእ በተምር ወይም በውሃ ካፈጠርን በኋላ ነው ማድረግ ያለብን ። የተለመደውና ብዙዎች የሚያደርጉት ሊያፈጥሩ ሲሉ ነው ይህ ከሐዲሱ መቅሰድ ጋር ይጋጫል።ምክንያቱም ሳያፈጥር ከሆነ መባል የነበረበት ጥሙ ሊወገድ ነው ፣ ስሮች ሊረጥቡ ነው ፣ አጅሩ ሊረጋገጥ ነው ነበር ‼ የአላህ መልእክተኛ ስለሆነና  ስለተረጋገጠ ነገር ነው የነገሩን ይህ ደግሞ ካፈጠርን በኋላ ነው እንጂ አይሆንም።ካፈጠርን በኋላ ሲባል ጠግበን ከበላን በኋላ ማለት አይደለም። አንድ ጊዜ እንደተገነጨን ወይም አንድ ተምር እንደበላን ማድረግ እንችላለን ። ይህ ማለት እያፈጠርን እያለን ማለት ነው። አላህ ከተጠቃሚዮች ያድርገን።✍
መቼም ቢሆን ባዶነት ኪሳራ ነው‼️በህይወት ዘመናችሁ ማንም በከንቱ እንደዋዛ እንዲጫወታችሁ አትፍቀዱ

TIPS✍✍
➦ከላይ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት አንድ ሰው በትከሻው የተሸከመው ከረጢት ነገር ላይ "اجر الصيام" (የጾም ምንዳ/ዋጋ) የሚል ጽሁፍ አለበት።

➦ነገር ግን ከረጢቱ ተቀድዶ የያዘው እህል (ምንዳው) እየፈሰሰ እንደሆነ ያሳያል።
​ቀዳዳዎቹ ላይ የተጻፉት ቃላት የጾምን ዋጋ የሚያሳጡ ወይም የሚያጠፉ ተግባራትን እንዲህ በማለት ይገልጻሉ:▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
​مسلسلات (ሙሰልሰላት)፦ ጊዜን በከንቱ የሚያባክኑ ተከታታይ ድራማዎች።
​غيبة (ጊባ)፦ ሰውን በሌለበት ማማት።
​علاقات محرمة (አላቃቱ አል ሙሐረመህ)፦ የተከለከሉ (ሀራም) ግንኙነቶች።
​نميمة (ነሚማ)፦ ነገር ማዋሰድ ወይም በሰዎች መካከል ጠብን ለመጫር ወሬ ማመላለስ።
​تأخير الصلاة (ተእኺር አስ-ሰላህ)፦ ሶላትን በወቅቱ አለመስገድ (ማዘግየት)።
​تبرج (ተበሩጅ)፦ አለባበስንና ውበትን ለባእድ ሰዎች ማሳየት።
​اغاني (አጋኒ)፦ ዘፈኖችን ማዳመጥ።

➦​ዋናው መልዕክቱ፡▼▼▼▼▼▼
​አንድ ሰው ቀኑን ሙሉ ተርቦና ተጠምቶ ሊጾም ይችላል፤ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱትን ስህተቶች የሚሰራ ከሆነ፣ የጾሙን ዋጋ (ምንዳ) ልክ እንደተቀደደ ከረጢት እያፈሰሰው እንደሆነና መጨረሻ ላይ ባዶ እጁን ሊቀር እንደሚችል ለማስጠንቀቅ ነው።
​ስለዚህ ምስሉ "ጾምህ ሆድህን ብቻ ሳይሆን ምላስህን፣ አይንህንና ጆሮህንም ይሁን" የሚል ምክር ይዟል።✍️
📌ውዝግቡ ስድቡ ና ተቃውሞው አሁንም ቀጥሏል¡
▣የተቅዋ (አላህን የመፍራት) ትሩፋቶች!

➦ተቅዋ ማለት አላህ ያዘዘውን መፈፀም የከለከለውን መከልከል ነው። የላቀው ጌታችን አላህ ለዚህ ተግባር ብዙ ትሩፋትን አድርጎለታል። ከነዚህ ትሩፋቶች መካከል፦

🔴ተቅዋ የዒልም ምንጭ ነው፦

➦አላህን የሚፈራ ሰው አላህ እውቀትን ይለግሰዋል። ዲኑንም ያሳውቀዋል። ምክንያቱም እውቀት ብርሀን ነው። ይህ ብርሀን ደግሞ ለንፁህ ልቦች ነው የሚለገሰው። የተከበረው አላህ እንዲህ አለ፦

«وَاتَّقَوا اللهَ وَيُعَلِّمُكُمُ اللهُ» البقرة ٢٨٢

«አላህንም ፍሩ።አላህ ያሳውቃቹሀል።» አል-በቀራ 282

🔴ተቅዋ የችግሮች ሁሉ መፍትሄ ምንጭ ነው፦

➦አላህን የሚፈራ አካል ፍራቻው ለሁሉም ችግሮቹ መፍትሄ ምንጭ ይሆነዋል። ምክንያቱም ሁሌም አላህን እያስታወሰ እየፈራ የሚንቀሳቀስ ሰው አላህ በሁሉም ጉዳዩ ከሱ ጋር ይሆንለታልና። የላቀው አላህ እንዲህ አለ፦

«وَمَنْ يَتَّقِ اللهَ يَجْعَلْ لَّهُ مَخْرَجًا» الطلاق ٢

«አሏህን የሚፈራ ሰው ለሱ መውጫ ያበጅለታል» አ'ጦላቅ 2

- እንዲሁም ተቅዋው ችግሮቹን ሁሉ በሸሪአ እንዲመዝን ያደርገዋል። ችግሩን በሸሪአ መዝኖ መፍትሄውን ከሸሪአ የፈለገ ሰው ደግሞ ጥሩ ጥሩ መፍትሄን ያገኛል።

«...ذَلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيْلاً» النساء ٥٩

«...ያ የተሻለ እና መጨረሻውም ያማረ ነው።» አ'ኒሳአእ 59

🔴ተቅዋ ካልታሰበ ቦታ ሪዝቅን ያመጣል፦

➦አላህን የሚፈራ አካል አላህ ካላሰበበት ቦታ ይለግሰዋል። ምክንያቱም ሁሉም ሀሳቡ አኼራው ያደረግ ዱንያ ፈልጋው ትመጣለች። አላህ እንዲህ ይላል፦

«وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ» الطلاق ٣

«ከማያስበው ቦታ ይለግሰዋል።» አ'ጦላቅ 3

- እንዲሁም ተቅዋ ያለው ሰው ለአላህ ብሎ አላህን ፈርቶ ብዙ ነገር ይተዋል። ለአላህ ብሎ አንድን ነገር የተወ ደግሞ የተሻለን ነገር ይተካለታል። መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

«ﺇِﻧِّﻚَ ﻟَﻦْ ﺗَﺪَﻉَ ﺷَﻴْﺌﺎً ﻟﻠﻪِ ﻋَﺰَّ ﻭَﺟَﻞَّ ﺇِلَّا ﺑَﺪَّﻟَﻚَ ﺍﻟﻠﻪُ ﺑِﻪِ ﻣَﺎ ﻫُﻮَ ﺧَﻴْﺮٌ ﻟَﻚَ ﻣِﻨْﻪُ» ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺣﻤﺪ
ﻭﻗﺎﻝ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ: ﻭﺳﻨﺪﻩ ﺻﺤﻴﺢ ﻋﻠﻰ ﺷﺮﻁ ﻣﺴﻠﻢ ﺍﻟﺴﻠﺴﻠﺔ ﺍﻟﻀﻌﻴﻔﺔ ‏1/ 62

«አንተ ለአሏህ ብለህ ምንም ነገር አትተውም አላህ በሱ ቦታ የተሻለወን ቢተካልህ እንጂ!» አህመድ

🔴ተቅዋ የተሻለ ልብስ ነው፦

➦አሏህን መፍራት ከምንም በላይ የተሻለ ልብስ ነው። ልብስ ሲባል ምንድ እንደሆነ ታውቃለህ? ልብስ በዚህ ቦታ ላይ ስራ ማለት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

«وَثِيَابَكَ فَطَهِّرْ» المدثر ٤ روى أبو روق عن الضحاك: "معناه وعملك فأصلح" وقال السدي: "يقال للرجل إذا كان صالحا إنه لطاهر الثياب وإذا كان فاجرا إنه لخبيث الثياب" انظر تفسير البغوي

«ስራህን (ከሽርክ) አፅዳ» አል'ሙደሲር 4
ኢማሙ አ'ደሀክ እንዲህ አሉ፦ «ትርጉሙ ስራህን አስተካክል ማለት ነው!» ኢማሙ አሱደይ ደግሞ እንዲህ አሉ፦ «ሰውዬው ደግ ሲሆን እሱ ልብሱ ንፁህ ነው ይባላል። አመፀኛ ሲሆን ደግሞ እሱ ልብሱ ቆሻሻ ነው ይባላል።» ተፍሲሩል በገዊይ

- እና ስራ ልብስ ነው። የተሻለው ልብስ ደግሞ (ስራ) ተቅዋ እንደሆነ አላህ ይነግረናል፦

«وَلِبَاسُ التَّقْوَى ذَلِكَ خَيْرٌ» الأعراف ٢٦

«አሏህ የመፍራት ልብስ (ስራ) ይህ የተሻለ ነው።» አል'አዕራፍ 26

🔴ተቅዋ የተሻለ ስንቅ ነው፦

➦አንድ ሰው ወደ ሚጓዝበት ቦታ ሲሄድ ስንቅ መሰነቁ አይቀሬ ነው። ሲሰነቅ የስንቁን መጠን የሚያደርገው በጉዞው ርቀት ልክ ነው። የጉዞው ርቀት ትልቅ ከሆነ ትልቅ ስንቅ ይሰነቃል፤ ትንሽ ከሆነ ትንሽ ስንቅ ይሰነቃል። አኼራችን ደግሞ ትልቅ ጉዞ ስለሆነ ትልቅ ስንቅ ልንሰነቅ ይገባል። ከስንቆች ሁሉ የተሻለውም አላህን መፍራት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

«وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَى» البقرة ١٩٧

«ተሰነቁም የተሻለው ስንቅ አላህን መፍራት ነው!» አል'በቀራ 197


🔴ተቅዋ ሀቅ እና ባጢልን መለያ ነው፦

➦ተቅዋ የተውሒድ እና የሽርክ፣የሀቅና  የባጢል፣ የቀጥተኛው መንገድና የጥመት መንገድ፣ የሱና እና የቢድአ፣ የሱንይና የቢድኢይ ወዘተ መለያ መሳሪያ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

«يَاأَيُّهَا الذِّينَ إِنْ تَتَّقُوا اللهَ يَجْعَلْ لَّكُمْ فُرْقَانَا» الأنفال ٢٩

«እናንተ ያመናቹ ሆይ አላህን ብትፈሩ መለያን ያደርግላቹሀል!» አል'አንፋል 29

🔴ተቅዋ ጉዳዮችን ያገራል!

➦አሏህን መፍራት ጉዳዮቻችንን ያገራልናል። በጉዳዩ ላይ አላህን ባንፈራ ከበድ የሚል የነበረው ጉዳይ በተቅዋ ሰበብ ክብደቱ ይቀረፋል። አላህ እንዲህ፦

«وَمَنْ يَتَّقِ اللهَ يَجْعَلْ لَهُ مِنْ أَمْرِهِ يُسْرًا» الطلاق ٩

«አሏህን የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለሱ መግራትን ያደርግለታል!» አ'ጦላቅ 4

🔴 ተቅዋ ወንጀል ያስምራል፦

➦አላህን መፍራት ወንጀልን ያስምራል። አላህ እንዲህ ይላል፦

«ﺇِﻥْ ﺗَﺘَّﻘُﻮﺍ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳَﺠْﻌَﻞْ ﻟَﻜُﻢْ ﻓُﺮْﻗَﺎﻧًﺎ ﻭَﻳُﻜَﻔِّﺮْ ﻋَﻨْﻜُﻢْ ﺳَﻴِّﺌَﺎﺗِﻜُﻢْ ﻭَﻳَﻐْﻔِﺮْ ﻟَﻜُﻢْ» ﺍﻷﻧﻔﺎﻝ ٢٩

«አላህ ከፈራቹ መለያን ያደርግላቹሀል። ፅያፍ ስራዎቻቹንም ያራግፍላቹሀል። ይምራቹሀልም!» አል'አንፋል 29

- የተቅዋ አላህን መፍራት ትሩፋቶች ብዙ ናቸው።ደስታን ፈላጊዎች የተቅዋን ምንነት ቢረዱ ኖሮ ከሱ ውጪ ሌላን አማራጭ ባልፈለጉ ነበር። አላህ እሱን ከሚፈሩ ባሮቹ ያድርገን!✍

➲Linኩን እየተቀላቀላችሁ ሼር አድርጉ ባረከሏሁ ፊኩም ጀመዓው
📌تعريفُ الصَّوم، وأقسامُه، وفضائِلُه، والحِكمةُ مِن تَشريعِه

:🔴تعريفُ الصَّوم:
الصَّوم لغةً: الإمساكُ
الصَّوم اصطلاحًا: التعبُّدُ لله سبحانَه وتعالى، بالإمساكِ عن الأكلِ والشُّربِ وسائِرِ المُفَطِّراتِ، مِن طُلوعِ الفَجرِ إلى غُروبِ الشَّمسِ

🔴المبحث الأول: أقسامُ الصَّوم
ينقسِمُ الصَّومُ باعتبارِ كَونِه مأمورًا به، أو منهيًّا عنه شَرعًا، إلى قسمين :
الأول: الصَّومُ المأمورُ به شَرعًا
وهو قِسمانِ:

🔴أ- الصَّومُ الواجب، وهو على نوعينِ:
1- واجبٌ بأصلِ الشَّرعِ- أي بغيرِ سَبَبٍ مِنَ المكلَّفِ-: وهو صومُ شَهرِ رَمضانَ
2- واجبٌ بِسَبَبٍ مِنَ المكلَّف: وهو صومُ النَّذرِ، والكفَّارات، والقَضاء.

🔴ب- الصَّومُ المُستحَبُّ (صوم التطوُّع)
وهو قِسمان:

1- صومُ التطَوُّعِ المُطلَق: وهو ما جاء في النُّصوصِ غيرَ مُقَيَّدٍ بزمَنٍ مُعَيَّنٍ
2- صومُ التطَوُّعِ المقيَّد: وهو ما جاء في النُّصوصِ مقيَّدًا بزمنٍ مُعَينٍ، كصومِ السِّتِّ مِن شوَّالٍ، ويومَيِ الاثنينِ والخميس، ويومِ عَرَفةَ، وعاشوراءَ.

🔴الثاني: الصَّومُ المنهيُّ عنه شرعًا
وهو قِسمانِ:
1- صَومٌ مُحَرَّمٌ: وذلك مثلُ صَومِ يَومَيِ العيدينِ.
2- صومٌ مكروهٌ: وذلك مثلُ صَومِ يومِ عَرَفةَ للحاجِّ.

🔴المبحث الثاني: فضائِلُ الصِّيامِ
للصِّيامِ فضائلُ كثيرةٌ شَهِدَت بها نصوصُ الوَحيينِ؛ منها:
1- أنَّ اللهَ تبارك وتعالى أضافَه إلى نفسه فقال: (الصوم لي وأنا أجزي به  ).
2- تجتمِعُ في الصَّومِ أنواعُ الصَّبرِ الثَّلاثةُ.
3- الصِّيامُ يشفَعُ لصاحِبِه يومَ القيامةِ  .
4- الصَّومُ مِنَ الأعمالِ التي وعَدَ الله تعالى فاعِلَها بالمغفرةِ والأجرِ العَظيمِ  .
5- الصِّيامُ كفَّارةٌ للذُّنُوبِ والخطايا  .
6- الصَّومُ جُنَّةٌ وحِصنٌ مِنَ النَّارِ  .
7- الإكثارُ مِنَ الصَّومِ سببٌ لدُخُولِ الجَنَّةِ  .
8- خُلُوفُ فَمِ الصَّائِم أطيَبُ عند الله تعالى مِن رِيحِ المِسْكِ  .

🔴المبحث الثالث: الحِكمةُ مِن تَشريعِ الصِّيامِ
لَمَّا كانت مصالِحُ الصَّومِ مشهودةً بالعُقُولِ السَّليمةِ، والفِطَرِ المستقيمةِ، شَرَعَه اللهُ سبحانه وتعالى لعبادِه؛ رحمةً بهم، وإحسانًا إليهم، وحِمْيَةً لهم وجُنَّةً

🔴فالصِّيامُ له حِكَمٌ عظيمةٌ وفوائدُ جليلةٌ؛ ومنها:
1- أنَّ الصَّومَ وسيلةٌ لتحقيقِ تقوى الله عزَّ وجَلَّ.
2- إشعارُ الصَّائِم بنعمةِ الله تعالى عليه.
3- تربيةُ النَّفسِ على الإرادةِ، وقوَّةِ التحَمُّلِ.
4- في الصَّوم قهرٌ للشَّيطانِ.
5- الصَّومُ موجِبٌ للرَّحمةِ والعَطفِ على المساكينِ.
6- الصَّومُ يُطَهِّرُ البَدَنَ من الأخلاطِ الرَّديئةِ، ويُكسِبُه صحةً وقوةً.
🔴ኦርቶዎች የሚፆሙት ፆም የአብይ ፆም ነው።ጠ/ሚ አብይ ግን እንኳን አደረሳችሁ አላላቸውም እንዴ¡
😁6
▣በማወቅም ባለማወቅም በረመዷን ወር ውስጥ የሚከሰቱ ስህተቶች🚫


➲በረመዳን ወቅት በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች መካከል፦
~~~~
① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣

② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሱሑርን አስቀድሞ በመመገብ ፈጅር ሳይሰግዱ መተኛት፣

③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም/ ሙሰልሰላት ማሳለፍ፣

④ ረመዳንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣

⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣

⑥ ተራዊሕ ላይ በየ አራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣

⑦ የተራዊሕ ኢማሞች ከሶላቱ ይልቅ ለቁኑት ዱዓእ የበለጠ ትኩረትና ጊዜ መስጠት፣

⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣…ብዙ ነው)

⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ " እያሉ በእስፒከር መጮህ፣

(10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣

(11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣

(12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣

(13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣

(14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣

(15) ሴቶች ሽቶ ተቀባብቶ ለተራዊሕ መውጣት፣

(16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች አላስፈላጊ መዝረክረክ፣

(17) ሃሜት፣

(18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣

(19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ፣ ወዘተ ማሳለፍ፣

(20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣

(21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግዴታ ነው። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ይገባል)፣

(22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርአን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።)

(23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣

(24) አንዳንድ አካባቢዎች ዒሻን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣

(25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣

(26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ህዝብን ማዘዝ፣

(27) የምግብ ብክነት ወዘተረፈ.....ናቸው ✍
🔴የእስልምና ህግጋት በዙብኝ...

 ➦ከዐብዱላህ ቢን ቡስር ረዲየላሁ ዐንሁ እንደተወራው፦ አንድ ሰው እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የእስልምና ሕግጋት (የትርፍ ሥራዎች) በዝተውብኛል፤ ስለዚህ አጥብቄ የምይዘውን  የምከተለውን ነገር ንገሩኝ።"
​እሳቸውም ﷺ እንዲህ አሉት፦
"ምላስህ ሁልጊዜም አላህን በማውሳት (በዚክር) እንደራሰ ይቆይ።"

​(ቲርሚዚ (3375) እና ኢብኑ ማጃህ (3793) ዘግበውታል።)

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል✍✍

Linኩ ሼር ይደረግ ባረከሏሁ ፊኩም
👍1
🔴​አንተ ሙዕሚን ሆይ! ታገሥ

  ለተንኮለኞች ተንኮልም ትኩረት አትስጥ፤ አላህ ረዳትህ ነውና! ​ሀያሉ አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿كَذَٰلِكَ كِدْنَا لِيُوسُفَ﴾ سورة يوسف، الآية رقم ٧٦
«ለዩሱፍ እንዲሁ ዘዴን ዘየድንለት።»

➦​ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ አል-ፈታዋ አል-ኩብራ (6/132) ላይ እንዲህ ይላሉ፦
"በዩሱፍ ታሪክ ውስጥ የተከለከለን ተንኮል የሚጠነስስ ሰው አላህ ተንኮሉን እንደሚመልስበት ማሳሰቢያ አለበት! ይህ የተከለከሉ ብልሃቶችን ስልቶችን በሚፈጽም ሰው ላይ የአላህ መንገድ (ሱና) ነው ፤ በተጨባጭ እያየነው እንዳለውም አላህ በእነዚህ ብልሃቶቹ ላይ በረካ አይሰጠውም ! 📗

እንዲሁም ሌላው ማሳሰቢያ ደግሞ :- በአላህ ላይ የተመካ ለሆነ አማኝ ፍጡራን ሊተነኩሉበት ቢሞክሩ እንኳን ፣ አላህ ለእርሱ ብሎ ተንኮሉን እንደሚመልስለትና ያለ እርሱም ብርታትና ኃይል ድልን እንደሚሰጠው ማሳሰቢያ አለበት !!

​ሀያሉ አላህ እንዲህም ይላል፦
﴿وَأَنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي كَيْدَ الْخَائِنِينَ﴾ سورة يوسف، الآية رقم ٥٢
«አላህም የከዳተኞችን ተንኮል አያቃናም ።»

➦​ታዋቂው ዓሊም አስ-ሰዕዲይ ተይሲር አል-ከሪም አል-ራህማን (ገፅ 400) ላይ እንዲህ ይላሉ፦
"إن كل خائن، لا بد أن تعود خيانته ومكره على نفسه، ولا بد أن يتبين أمره
ማንኛውም ከዳተኛ፣ ክህደቱና ተንኮሉ በራሱ ላይ መመለሱ አይቀሬ ነው፤ ጉዳዩም ግልጽ መውጣቱም አይቀርም።"📗

➦ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "በምትጠላው ነገር ላይ በመታገሥ ውስጥ ብዙ መልካም ነገር እንዳለ እወቅ፤ ድል ከትዕግሥት ጋር ፣ መገላገል ከጭንቅ ጋር ነው፣ ከችግር ጋርም ምቾት አለ።"📗

➦(ኢማም አሕመድ በሙስነድ ዘግበውታል፤ አልባኒይም ሶሒሕነቱን አረጋግጠዋል።)📘
​
ዶ/ር አሕመድ ቢን ዑመር ቢን ሳሊም ባዝሙል
ረቡዕ፣ ረመዳን 8 ቀን 1447 ሂጅራ
◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️◾️

✔️ ሰዎች አወደሱም አወገዙም በዲንናችን ላይ ቀጥ ለጥ እንላለን እንሻ አሏህ!!✍✍


♨️ጆይን በሉ ሼር ይደረግ ባረከሏሁ ፊኩም
🛑ከፆሙ ረሀብና ጥም እንጂ ከለሊት ሶላቱ እንቅልፍ ማጣት እንጂ የማያተርፍ እንዳትሆን !

عن أبي هريرة – رضي الله عنه – قال : قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم – :
 
" رُبَّ صائمٍ ليس له من صيامه إلا الجوع والعطش، ورب قائم ليس له من قيامه إلا السهر "

        أخرجه النسائي وابن ماجه وصححه الشيخ الألباني

🔹 አቡ ሁረይራ ባወሩትና ኢማሙ ነሳኢይ በዘገቡት እንዲሁም ሸይኽ አልባኒ ሶሒሕ ባሉት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ : –

" ብዙ ፆመኛ አለ ከፆሙ ረሀብና ጥም እንጂ የማያተርፍ , ብዙ ለይል ሰጋጅም አለ ከሶላቱ እንቅልፍ ማጣት እንጂ የሌለው "

🔹 ይህ የነብዩ ንግግር ለፆመኞችና ለይል ሰጋጆች ማስጠንቀቂያ ነው ። አንድ ሰው ፆመኛ ነኝ ብሎ ከምግብና መጠጥ መራቁ ብቻ ምንዳ አያስገኝለትም።

📌ኒያውን አስተካክሎ ከተለያዩ መዕሲያዎች(ወንጀሎች) መራቅ አለበት ። እንደሽርክ ፣ ቢደዓ ፣ ውሸት ፣ ሙዚቃ መስማት ፣ከቁርዓን የሚያዘናጉ ነሺዳዎችን ማደመጥ ፣ ፊልም መመልከት ፣ ወሬ ማዋሰድ ፣ የሰው ሐቅ መብላት ፣ መሳደብና መላፋት ከመሳሰሉ ፆምን አደጋ ላይ ከሚጥሉ ወንጀሎች መራቅ ያስፈልገዋል።
  
📌ለይል የሚቆምም ሰው በዛን ሰዓት እንቅልፉን ትቶ ሰውነቱን አድክሞ ኢኽላስ ከሌለውና ሰጋጅ ለመባልና ለመደነቅ ለይል የሚሰግድ መሆኑ እንዲታወቅለት የሚፈልግ ከሆነ ትርፉ እንቅልፍ ማጣት ነውና መጠንቀቅ ይስፈልጋል።✍✍


➣ጆይን በሉ Share ይደረግ✍
🛑በረመዷን ወር ለአማኞች የተበሰሩ ታላላቅ የምስራቾች አሉ።ጥቂቶቹን እነሆ▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼

➊ኛ የጀነት በሮች መከፈት፦
 ➦ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተናገሩት ረመዳን ሲገባ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፣ የጀሃነም በሮች ይዘጋሉ፣ ሰይጣናትም ይታሰራሉ። ይህ ማለት የአላህ እዝነት የሚወርድበትና ወደ መልካም ስራ ለመሰማራት መንገዱ የሚቀልበት ወር ነው።

➋ኛ የወንጀል መማርያ፦
➦ረመዷንን በእምነትና ከአላህ ምንዳን በመፈለግ የጾመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ እንደሚማርለት ተበስሯል።

ይህ ለአዲስ ሕይወትና ለንጹህ ማንነት ትልቅ አጋጣሚ ነው።

➌ኛ ከአንድ ሺህ ወር የምትበልጥ ሌሊት (ለይለቱል ቀድር)፦
➦በዚህ ወር ውስጥ በውስጧ የሚሰራ መልካም ስራ ከ83 አመታት በላይ ከሚሰራ ስራ የምትበልጥ Laylatul Qadr የተሰኘች ታላቅ ሌሊት ትገኛለች።

➍ኛ የዱዓ ተቀባይነት፦
 ➦ጾመኛ በሚያፈጥርበት ወቅት የሚያደርገው ዱዓ (ጸሎት) ተቀባይነት አለው።

አሏህ በየቀኑና በየሌሊቱ በርካታ ሰዎችን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ወር ነው።

ረመዷን የቁርዓን፣ የሶላት፣ የዚክር እና የሰደቃ ወር ነው።

➦ይህን ወር በህይወት አግኝቶ ለመጠቀም መዘጋጀት ትልቅ እድል ነው።

➛አሏህ  ከሚጠቀሙት ያድርገን!


➣ጆይን በሉ ሼር ይደረግ ባረከሏሁ ፊኩም
➦እንደዚህ አይነት የትወና ሰዎችን ስንመለከት ግርም ይለናል።እኔ የሚገርመኝ የትኛው ኣቂል ሙስሊም ነው የኦርቶ ቤት መድብለ አመልክትን ማምለክ የሚናፍቀው በፍፁም!

➦በጥቅማጥቅም እስካልደለላችሁ ድረስ እንኳን ሙስሊም ፕሮቴስታንት እንኳን ኦርቶ የመሆን ፍላጎት አይኖርምና ምክንያቱ ደግሞ ማብራሪያም አያስፈልግምና‼️

⚠️ለማንኛውም ክርስትና በቃኝ ብሎ ከክርስትና ወደ እስልምና የሚጎርፈውን ሰው የክርስትና ምዕመኑ እንዳይደነግጥ የውሸት ተስፋ እየሰጣችሁ ብሎም በጥቅማጥቅም እየደለላችሁ በንደዚህ አይነት ድራማ ለመሸፈን ደፋ ቀና ማለታችሁ ያስቀናል ብሎም የተቀደሰ ሀሳብ ነው¡¡😜

➦እናንተ በድራማና በስድብ ቀጥሉ እኛ ደግሞ በፍቅር በእውነት እናሰልማለን "በቁጭታችሁ ሙቱ"
!

➣ጆይን በሉ ሼር ይደረግ
🔴Amazing Health Benefits of Date Fruits 🔥🔥
Dates hold immense spiritual, nutritional, and cultural significance in Islam, frequently mentioned in the Quran as a blessing. They are primarily consumed to break the fast (Iftar) during Ramadan, adhering to the Sunnah of Prophet Muhammad (PBUH). Considered a nutritious, energy-boosting food, they are also recommended for daily consumption, especially in the morning for health and protection. 

📌The Seven Science-Backed Health Benefits of Date Fruit
1. Dates Fruit Benefits Your Digestive System

Digestive issues can disrupt your entire day. Dates fruit benefits include serious digestive health support that addresses these problems naturally.
These fruits are loaded with dietary fiber. A 100g serving of dates provides 6.7g of fiber, which is about 27% of your daily requirement.
According to research published in the Journal of Nutritional Science, the insoluble fiber in dates adds bulk to stool and promotes regular bowel movements.✍️✍️
የሀቅ አድማስ Official apologetics 🔰
🔴Amazing Health Benefits of Date Fruits 🔥🔥 Dates hold immense spiritual, nutritional, and cultural significance in Islam, frequently mentioned in the Quran as a blessing. They are primarily consumed to break the fast (Iftar) during Ramadan, adhering to the…
2. Powerful Antioxidants Fight Disease
Your body faces daily attacks from pollution, stress, and processed foods. These create harmful free radicals that damage your cells and accelerate aging.
Dates fruit include high levels of protective compounds:
Carotenoids (beta-carotene: 89 mcg per 100g)
Flavonoids (quercetin and apigenin)
Phenolic compounds (caffeic acid and ferulic acid)

3. Natural Energy Without the Crash
Energy drinks and processed snacks leave you crashing later. Dates fruit include sustained energy that keeps you going throughout the day.
Unlike processed snacks, dates contain a blend of natural sugars that provide sustained energy. These include glucose and fructose (which are typically the predominant sugars in dates) along with sucrose, though the exact proportions vary depending on the date variety and ripeness.
These natural sugars combine with fiber, iron (0.9mg per 100g), and complex carbohydrates. This combination provides clean energy that lasts for hours without blood sugar spikes.
Perfect for busy professionals, students, and anyone needing steady energy throughout the day.