https://t.me/amuresponds
አሰላም አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱ ያጀማአ
ንፅፅር መማርና ማወቅ የሚፈልጉ እናም በእስልምና ላይ ለሚነሱ ሹብሀዎች መልሶች ለማግኘት ወይ ለመጠየቅ የሚፈልግ ሰዎች ይሄን ቻናል ተቀላቀሉ በቅርቡም አሪፍ ፕሮግራም የምንጀምር ይሆናል ተቀላቀሉ
ሼርም እያደረጋች የሂዳያ ሰበብ ሁኑ
ሙስሊምም ክርስቲያኑም ኢቲስቱም መቀላቀል ይችላል አላማው እውነታውን መማር ነው

Telegram
Responds
وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًۭا
በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»
(17 : 81)

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወይኔ በላቸው ያዙልኝ🤣
Forwarded from Jake Theology Student (Ja)
አብዱል?
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው።
قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا
(ሕፃኑም) አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል፡፡»
(📗19:30)
ብዙ ዕቅበተ እምነት ላይ እንሰራለን የሚሉ አላዋቂ ክርስትያኖች በውይይት መሃል ሙስሊሞችን ያሸማቀቁ መስሏቸው "አብዱል" ሲሉ ይስተዋላል።
ለመሆኑ እነዚህ አላዋቂ ክርስትያኖች ሙስሊሞችን "አብዱል" ሲሉ ምን ማለት ፈልገው ነው ሲባል መልሱ ያው "አብድ" (ባሪያ) ማለታቸው ነው።
ቅሉ ግን ሙሥሊሞች ባሪያ ማለትም የአሏህ ባሪያ ሲባሉ ያስደስታቸዋል እንጂ በፍጹም አያሸማቅቃቸውም። ምክንያቱም عبد"አብድ" የሚል የአረብኛ ቃል "አበደ" ማለትም አመለከ ተገዛ ከሚል "ሥርወ-ቃል" የመጣ ሲሆን "አምላኪ" "ተገዢ" ማለት ነው።
አንድ እጅና እግሩን ሰጥቶ ለአላህ የሚታዘዝ ሙሥሊም "عَبْدُ اللَّهِ" አብዱሏህ" ማለትም "የአላህ ባሪያ" ይባላል! ውዱ ነቢያችን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሐዲሳቸው አላህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ስሞች "አብዱሏህ" እና "አብዱል ረህማን" ናቸው ብለዋል።
عَنْ أَبِي وَهْبٍ الْجُشَمِيِّ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم "
وَأَحَبُّ الأَسْمَاءِ إِلَى اللَّهِ عَبْدُ اللَّهِ وَعَبْدُ الرَّحْمَنِ
"አቢ ወህብ" አል-ጁሸሚይ"(ረ•ዐ) እንደተረከው የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ብሏል!
አላህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ስሞች አብዱሏህ እና አብዱል ረህማን ናቸው።
{📗ሱነን አቡ ዳውድ,4950}
በአጭሩ እኛ ሙሥሊሞች አብዱሏህ ስንባል ደስታና ኩራት ይሰማናል እንጂ በፍጹም አንሸማቀቅም። የሚያሸማቅቀው አብዱል ቀመር ማለትም የጨረቃ ባሪያ ወይም አብዱል ሸምስ ማለትም የፀሐይ ባሪያ ወይም አብዱል አብድ ማለትም ልክ እንደ ክርስትያኖች "የባሪያ ባሪያ" ወዘተ.. መባል ነው እንጂ የሚያሸማቅቀው የሁሉ ነገር ፈጣሪ የሆነው የአላህ ባሪያ መባል የሚያኮራ እንጂ በፍጹም የሚያሸማቅቅ አይደለም።
እኛ ሙሥሊሞች ባርነታችን የሁሉ ነገር ፈጣሪ ለሆነው ለአላህ ነው።
اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
"አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡
{39:62}
እስቲ አሁን ደግሞ ጦሩን ወደ ክርስትያኖች ዘወር እናድርገውና ክርስቲያኖች የአብዱል አብዱል መሆናቸውን እናሳያቸው!
እንደሚታወቀው በባይብል ውስጥ ነቢያት ሆነ የነቢያት ተከታይ አማኞች ባሪያ መባላቸው የታወቀ ነገር ነው ለምሳሌ! ዳዊትና ተከታዮች የእግዚአብሔር ባሪያ ተብለዋል።
አሁንም ባሪያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
(📗መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 17፤7)
በዚህ አንቀጽ ላይ ባሪያዬ ለሚለው የገባው የእብራይስጥ ቃል "לְעַבְדִּ֣י lə·‘aḇ·dî" ኢቤድ ሲሆን ከአረብኛው عبد አብድ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ቃል ሲሆን ባሪያዬ ማለት ነው።
ሃሌ ሉያ የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ፤ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥
(📗መዝሙረ ዳዊት 135፤1)
ብዙ መጥቀስ ይቻላል ላለማስረዘም ነው እንጂ። ይህ ብቻ አይደለም በሚያሳዝን መልኩ ክርስቲያኖች አምላክ ነው ብለው የሚያመልኩት ኢየሱስ ራሱ ባሪያ ተብሏል።
እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ!
(📗ትንቢተ ኢሳይያስ 42፤1)
አሁንም በዚህ አንቀጽ ላይ "ባሪያዬ" ለሚለው የገባው የእብራይስጥ ቃል ልክ እንደ አረብኛው " עַבְדִּי֙ ‘aḇ·dî" عبدي "አብዲ" ሲሆን ባሪያዬ ማለት ነው።
So በማቴዎስ ወንጌል ዘገባ መሰረት ኢሳያስ 42:1 ላይ ያለው ትንቢት ለኢየሱስ መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው።
በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል።
እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።
(📗የማቴዎስ ወንጌል 12፤16-18
መጽሐፉን እንዳሻቸው የሚበርዙ ቶርጋሚዎች ኢሳያስ ላይ ባሪያዬ ተብሎ የተተነበየውን ትንቢት ማቴዎስ ላይ የትንቢቱን ፍጻሜ ባሪያዬ በሚለው ፋንታ ብላቴናዬ ብለው ቀይረዎታል ቅሉ ግን ትንቢት ላይ የተነገረው ባሪያዬ ተብሎ እንጂ ብላቴናዬ ተብሎ አይደለም። ምክንያቱ በእብራይስጥ ብላቴና ለማለት የሚገባው ቃል"וְהַנַּ֖עַר" wə·han·na·‘ar ነው እንጂ "עֶ֣בֶד e·ḇeḏ" አይደለም። መጽሐፈ ኢያሱ 1:1 ተመልከት።
ስናጠቃልል እኛ ሙሥሊሞች የአላህ ባሪያ ስንባል ደስታና ኩራት ይሰማናል እንጂ በፍጹም አንሸማቀቅም ምክንያቱም የአላህ ባሪያ ስትሉን የአለማቱን ፈጣሪ አምላኪዎች ለአለማቱ ጌታ ተገዢዎች እያላችሁን ነውና።
በተቃራኒው ግን እናንተ የአብዱል አብዱል ማለትም የባሪያው ኢየሱስ ባሪያ ናችሁ የሚያሸማቅቀውና አሳፋሪው የባሪያ ባሪያ መሆን ነውና እናንተ እፈሩ ተሸማቀቁ እንጂ እኛ በፍጹም ለአላህ ታዛዥ ባሪያ በመሆናችን አንሸማቀቅም።
✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12

🔥1
ባይብል እና ብርዛት
ክፍል 1
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህ ሩህ ፣ በጣም አዛኝ በሆነው።
فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ فَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
{ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡}
[📖 አል-በቀረህ 2÷79]
ስለ ብርዛት ሲወሳ ብዙ ጊዜ ክርስትያኖች በሐሰት ላይ በመመስረት እርር እና ምርር ብለው ሶፍስቲክ"sophistic" ሙግቶችን ሰንዝረው ውሸትን እውነት ለማስመሰል አወሳስበው አምታተው ዝም ለማሰኘት ሲንጨረጨሩና ሲንከተከቱ ይስተዋላሉ።
☞ በመጀመርያ ደረጃ "ተሕሪፍ"distortion" ሲባል "ሐረፈ" ማለትም "በረዘ"distorted/corrupted" ከሚል አላፊ ግስ ወይም ስርወ-ግንድ የረባ ሲሆን "ብርዛት" ማለት ሆኖ እውነትን በውሸት መቀላቀል ነው። ይህን አስመልክቶም ባይብል እንደተበረዘ ቁልጭ አርገው ከሚያረጋግጡ ማስረጃዎች መካከልም በአላህ ፈቃድ
➲ የሊቃውንት እና ምሑራን ምስክርቶችትን
➲ የእደ-ክታባት የእርስ በእርስ ልዩነቶችን
➲ የመጽሐፍ ቅዱስ ቨርዥን ተቃርኖዎችን
➲ የአንቀፆች ግጭት እና ፍጭቶችንም እንዳስሳለን
☞ በቅድሚያ የጥንት የእጅ ጽሑፎች"manuscripts" ወይም እደ-ክታባት በመጽሐፍ ቅዱስ ታእማኒነት ላይ ተፅዕኖ እንዳላቸው ግንባር ቀደምና አከርካሪ መሆናቸው እንደ ንጋቱ ፀዳል የተረጋገጠ ነገር ሲሆን ይህን አስመልክቶ ባይብል ላይ የተደረጉ ለውጦችና እርማቶችን ፍንትው አርገው የሚያረጋግጡ እንዲሁም በተለይ የአዲስ ኪዳን ወንጌላት እና መልክቶች ባይተዋርና ባልታወቁ ጸሐፊያን የተዘጋጁ እንደሆኑ ብዙ ብዙ ከምሑራን ምንጮችን መጥቀስ ቢቻልም ላለማንዛዛት ስንል የተወሰኑትን እንመልከታለን -
🎯 “ከአዲስ ኪዳን 5,340 በላይ የግሪክ እጅ ጽሑፎች መካከል ሁለት ተመሳሳይ አንድ አይነት የሆኑ የሉም። በእውነቱ በማንኛውም በዘመን ተቀራራቢ ከሆኑ ሁለት የእጅ ጽሑፎች መካከል እንኳን በእያንዳንዱ ምዕራፍ ከስድስት እስከ አሥር ሊዩነቶች ይኖራሉ። ስለዚህ አንድም የእጅ ጽሑፍ ከብርዛት ያመለጠ አለመሆኑ ግልፅ ነው።"No two of the 5340-plus Greek MSS of the NT are exactly alike. In fact the closest relationships between any two MSS in existence even among the majority average from six to ten variants per chapter. It is obvious therefore that no MS has escaped corruption.”¹
🎯 "ጥናቶች እንደሚያሳዩት በመገልበጥ ሂደት ጊዜ በጽሑፎች ውስጥ የተደረጉ አንዳንድ ለውጦች በፀረ አይሁድ ተነሳሽነት ፣ ሌሎችም በሴቶች ላይ የተወሰነ ጥላቻ ተፅዕኖ ያላቸው እንዲሁም ሌሎቹ ለዐቅብተ እምነት ስጋቶች ፣ ሌሎችም ለሥነ-መለኮታዊ እና ነገረ-ክርስቶሳዊ ግቦች እንደሆኑ ሊብራሩ ይችላሉ።studies have shown that certain changes made by scribes in the process of copying appear to have been motivated by anti Jewish sentiments; others seem influenced by a certain animosity toward women; others by apologetic concerns; and still others can be explained by theological, especially Christological concerns." ²
🎯 “በእኛ ቅጂዎች ውስጥ ብዙ ልዩነት እንዳለ የታወቀ እውነት ነው፣ በአንዳንድ ጸሓፊያን ግድየለሽነትም ሊሆን ይችላል፣ ወይም በጽሑፉ እርማት ላይ በተወሰኑ ጥፋተኞች ግድየለሽነት ፣ ወይም በዘፈቀደ እርማታቸው ላይ ጭማሪዎች ወይም ግድፈቶች በሚያረጉ አንዳንድ ሰዎች ምክንያትም ሊሆን ይችላል።it is a recognized fact that there is much diversity in our copies, whether by the carelessness of certain scribes, or by some culpable rashness in the correction of the text, or by some people making arbitrary additions or omissions in their corrections." ³
🎯 "በአዲስ ኪዳን ውስጥ ካሉ ቃላቶች ይልቅ በእጅ ጽሑፎች መካከል ያሉ ልዩነቶች ይበዛሉ።"There are more variations among our manuscripts than there are words in the New testament.” ⁴
🎯 "ብዙ የእጅ ጽሑፎች እንዳለውኑ የተለያዩ የጽሑፍ ዓይነቶችም አሉ።"There are almost as many forms of text as there are manuscripts.” ⁵
🎯 "ሁሉም መናፍቃን ማለት ይቻላል የቅዱሳት መጻሕፍትን በርዘዋል ተብለው ተከሰው ነበር።"Nearly all the heretics were in turn acccused of falsifying the scripture.” ⁶
🎯 “የኦርቶዶክስ ጸሐፍት የአዲስ ኪዳንን ጽሑፍ ለግል ዓላማ ብለው የቀየሩበት መሠረታዊ ተሲስ በእርግጥ እውነት ነው። በመቶዎች በሚቆጠሩ ቦታዎች የዚህን ማስረጃ ማየት እንችላለን።"basic thesis that orthodox scribes have altered the New Testament text for their own purposes is one that is certainly true. We can see evidence of this in hundreds of places.” ⁷
🎯 ክሬግ ኤል ብሎምበርግ እንዲህ ሲል ያትታል:- በግልፅ ለመናገር ወንጌላት ስም አልባ ጸሐፊዎቻቸው የማይታወቁ እንደሆኑ መቀበል አስፈላጊ ነው።"Craig L. Blomberg, who stated: “It’s important to acknowledge that strictly speaking, the gospels are anonymous.” ⁸
🎯 "ስለ ኤፌሶንም በተመለከተ '80 በመቶ ወሳኝ የሆኑ ሊቃውንቶች' (ጸሐፊው) ስሙ የውሸት እንደሆነ ይቆጥሩታል።"and regarding Ephesians 'about 80 percent of critical scholarship' considers it to be pseudonymous." ⁹
🎯“የቆላስይስ መጽሐፍ በተመለከተ ፣ '60 በመቶ ወሳኝ የሆኑ ሊቃውንቶች' (ጸሐፊው) ስሙ የውሸት እንደሆነ ያምናሉ።"Regarding the book of Colossians, Brown says that 'about 60 percent of critical scholarship' deem it to be pseudonymous." ¹°

❤1
🎯 “እንደ ሬይመንድ ብራውን ገለፃ ፣ 'ከ 80 እስከ 90 በመቶ የሆኑ ሊቃውንቶች' ቲቶስ ፣ 1ኛ እና 2ኛ ጢሞቴዎስ (ጸሓፊያን) ስም የውሸት እንደተጠቀሙ ያምናሉ።"According to Raymond Brown, '80 to 90 percent of critical scholarship' deem Titus, 1 and 2 Timothy to be pseudonymous." ¹¹
🎯“ የ 2ኛ ተሰሎንቄ መልዕክት በተመለከተ ሬይመንድ ብራውን እንዲህ ይላል:- ሊቃውንቶች ጳውሎስ እንደ ፃፈው እኩል ተከፋፍለዋል(ተለያይተዋል)።"II Thessalonians. Raymond Brown states: Scholars are almost evenly divided on whether Paul wrote it,"¹²
ማጣቀሻ 📌
¹ 📒 Gordon D. Fee, “Modern Textual Criticism and the Revival of the Textus Receptus," in Journal of the Evangelical Theological Society 21:1, March 1978, p.23.
² 📒 Kim Haines-Eitzen, Guardians of Letters: Literacy, Power, and the Transmitters of Early Christian Literature, New York: Oxford University, 2000, p. 112.
³ 📒 Origen, Comm. Matt. 15.14.
⁴ 📒 Bart Ehrman, Misquoting Jesus, p.90.
⁵ 📒 Jerome, Ep. Praef. Evang., to Damasus.
⁶ 📒 Eberhard Nestle, introduction to the Textual Criticism Of The Greek New testament, P. 197.
⁷ 📒 Revisiting the Corruption of the New Testament: Manuscript, Patristic, and Apocryphal Evidence ., by Daniel B. Wallace ., pg 43.
⁸ 📒 The Case for Christ (Strobel, Lee) p. 23
⁹ 📒 New Testament Introduction, p. 621
¹° 📒 New Testament Introduction, p. 600
¹¹ 📒 Raymond E. Brown, An Introduction To The New Testament, 1997, Doubleday, p. 639, 654, 673.
¹² 📒 Brown, New Testament Introduction, p. 591

♦️ፎቶ የሚያስከትለዉ ጣጣና መዘዙ❗️
የራስን የምስትን የልጆችን ፎቶ በአልበም በስልክ ማስቀመጥ እንዲሁም ይባስ ብሎ ሚዲያ ለይ መልቀቁ ከአኼራው ቅጣት በፊት ዱንያ ለይ ብዙ ጣጣዎችን ያስከትላል።ይህ የአንዷን ፎቶ ድግምት ሰሪ ዘንድ በመውሰድ እንዴት ሲህር እንደሰሩባት ተመልከቱ።
▪️ብዙ እህቶቻችን ሚዲያ ላይ በሚለቁት ፎቶ ሰበብ ለቡዳ፣ ለአይንናስ፣ ለሲህር፣ ለመስተፋቅርና ለሌላም ከባባድ አደጋዎች በቀላሉ ይጋለጣሉ። ምክንያቱም ድግምት ሰሪዎች ድግምት ለሚያሰራው አካል ድግምት የሚሰራበትን ሰው የሆነ ነገሩ አምጣ ስለሚለው በቀላሉ ፎቶዋን ካገኘ ወስዶ ያንን ይሰጣል። በዚህ ጊዜ በሷ ላይ በቀላሉ ይህንን መስተፋቅር ወይም ሲህር ያሰሩባታል።
▪️በተለይ ፎቶዋን በየ ሚዲያው የምትለቅ ሴት ፎቶውን የሚያይ ሰው ሁሉ ጤነኛ አይደለም ቢባል ማጋነን አይሆንም።የአይን በሽታ ያለበት ሰው ፎቶውን ሲያይ ከማረከውና ካስደነገጠው ወዲያው በአይኑ ይበላታል። እሷ ግን አታውቅም ቆዳዬ ተላጠ፣ አሳከከኝ፣ ልቤ ተጨነቀ፣ ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል፣ ራሴ ሊፈነዳ ደረሰ፣ ሌላም ሌላም እንዲህ እንዲህ ሆንኩ በማለት በህመም ትሰቃያለች።ነገሩ ግን በሚዲያ የለቀቀችው ፎቶ ያመጣባት ጣጣ ሊሆን ይችላል።
▫️እንዲሁም ብዙ ወላጆች የሚያምሩ ልጆቻቸውን ፎቶ በማንሳት እስክሪን ሴቨር ፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግ ሁሉም እንዲመለከታቸው ያደርጋሉ። ስንቱ በአይን እየበላው እዚጋ አመመኝ ብሎ መናገር የማይችለው ምስኪን ልጃቸውን በህመም ያሰቃያሉ።
©️
👌ሴት እህቶችም ወንዶችም አሏህን ፈርታችሁ በተለይም ሴት እህቶቻችን ከዚህ ተግባራችሁ ራቁ አሏህን የሚያስቆጣ በራሳችሁ ላይ ሙሲባ(በላእ) የሚያመጣ ተግባር ነው።
🔀ሁሉም እንዲጠነቀቀው ሼር አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም

👍1
የረመዷንን ሌባ ተጠንቀቁ
➚➚➚➚➚➚➚➚
አንደኛ ሌባ፦ ↙️
📺 ቴሌቪዥን በድራማና ቆሻሻ በሆነ ፕሮግራም ምክንያት የሰዎችን ፆም የሚያበላሽ አጅራቸውንም የሚቀንስ አደገኛ ሌባ ነው ቲቪ እንቅልፍ ከመተኛት ጭምር የሚከለክል አደገኛ ሌባ ነው!!!
ሁለተኛው ሌባ፦ ↙️
🏢 የሱቅ ቦታ፦ ያለ ምንም ገደብ ገንዘብንና ወቅትን ለየት ባለ ሁኔታ የሚያባክን ሲሆን ይህን ለመቆጣጠር ከመሄድህ በፊት አስብበት ተጠንቀቅ!!!
ሶስተኛ ሌባ፦↙️
👁 አለመተኛት፦ ውድ ግዜህን የሚነጥቅ በመጨረሻው አንድ ሶስተኛ ሌሊት ላይ ከተሀጁድ ከስቲግፋር የሚከለክል ከባድ ሌባ ነውና በአግባቡ ማስተዋል ያስፈልጋል።
አራተኛ ሌባ፦ ↙️
🍱 ኩሽና፦ በተለይ ሴቶች!!! ረጅም ግዜ የተለያዩ ምግቦችን በማዘጋጀት ግዜያቸውን በኩሽና ውስጥ የሚጨርሱ አሉ! ደግሞኮ አይበሉትም ቀመስ ቀመስ አድርገው ብዙውን ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ይጨምሩታል!!! (እህቴ ሆይ!!! ረመዷንን የተለያዩ ምግቦችን በማዘጋጀት ግዜሽን አትፍጂ ይህን ስልሽ ጭራሽ ምግብ አትስሪ ማለቴ አይደለም!!! መቼም ግልፅ ነውና ሚዛናዊ ሁኚ ለማለት ነው። ፀሀፊው))
አምስተኛ ሌባ፦ ↙️
📲 ስልክ፦
ስድስተኛ ሌባ፦ ↙️
💵 ስስት፦ የሶደቃን አጅር የሚከለክል በተለይ የረመዷንን ወር ሶደቃ የሚከለክል ሌባ ነው።
ሰባተኛ ሌባ፦
🌴 አላህ የማይወሳበት መጅሊስ፦ ያ ! የቂያማ ቀን በሰውየው ላይ ፀፀት የሚሆን አደገኛ ሌባ!!!
በመጨረሻም፦ ➘ ትልቁ ሌባ
🌐 የመገናኛ ቡዙኃኖች፦ አላህን የሚያስወድድ ስራ ካልተሰራበት አደገኛ የረመዷን ሌባ!!!
አደራ ፍጠኑ! አደራ ፍጠኑ!! ያሉት ቀናቶች በጣም ትንሾች ናቸው። አላህ በሚወደው ስራ የምንጠቀምበት ወር ያድርግልን !!✍✍

ለረጅም ግዜ ወሬ ማብዛት!!! በዛ ላይ ህሜቱ፣ ነገር ማዋሰዱ፣ አለተባለ እያሉ ግዜን መግደልና ሚስጥርን ማባከን እንዲሁም ብዙ የሚታዩ አልባሌ ነገሮችንም አቅፏል። ((አላህ ይድረስልን)) ስድስተኛ ሌባ፦ ↙️
💵 ስስት፦ የሶደቃን አጅር የሚከለክል በተለይ የረመዷንን ወር ሶደቃ የሚከለክል ሌባ ነው።
ሰባተኛ ሌባ፦
🌴 አላህ የማይወሳበት መጅሊስ፦ ያ ! የቂያማ ቀን በሰውየው ላይ ፀፀት የሚሆን አደገኛ ሌባ!!!
በመጨረሻም፦ ➘ ትልቁ ሌባ
🌐 የመገናኛ ቡዙኃኖች፦ አላህን የሚያስወድድ ስራ ካልተሰራበት አደገኛ የረመዷን ሌባ!!!
አደራ ፍጠኑ! አደራ ፍጠኑ!! ያሉት ቀናቶች በጣም ትንሾች ናቸው። አላህ በሚወደው ስራ የምንጠቀምበት ወር ያድርግልን !!✍✍
👉 የፆመኛ ዱዓእ ✍
የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም –
" ለፆመኛ ሰው ተቀባይነት ያለው ዱዓእ አለው " ብለዋል ።
በመሆኑም አንድ ፆመኛ የሆነ ሰው ፀሀይ ከመግባቷ በፊት አፍጥር ሊቃረብ ሲል የሚያደርገው ዱዓእ መቅቡል ስለሆነ ልንዘናጋ አይገባም።ብዙ የተለያየ ሀጃ ያለባችሁ ወንድምና እህቶች በተለይ ከእዳ ጋር፣ከርዝቅ ማጣት ጋር የተያያዘ ሀጃ ያለባችሁ ስንቱ ፊት ቆማችኋል ? እስኪ ይህን አጋጣሚ ተጠቅማችሁ ለሁሉም እንደየፍላጎቱ ሰጥቶ አሁንም ቢጠይቁት የሚወደውን አምላካችሁን ደጅ አንኳኩ።የሰዎች ፊት ከመቆም ከጌታችሁ ፊት ቁሙ ያ አላህ በሉት።በናንተና በአምላካችሁ መካከል ያለውን ወንጀል ያመጣውን ርቀት ከመጝሪብ በፊት ቀደም ብላችሁ መስጂድ ገብታችሁ ኢስቲጝፋር በማድረግና የሱን ቃል በማንበብ አጥብባችሁ ለምኑት።ተዘግቶ የማያውቀውን የራሕመቱ ደጃፍ ቆማችሁ በዱዓእ በር ግቡ።
በዱንያ ላይ ሁሉም የተለያየ ሃጃ አለው።ሁሉንም አንድ የሚያደርገው የአኼራ ሃጃ አለና ሁላችንም የጭንቁን ቀን ከሚያልፉት ባሮቹ እንዲያደርገን አላህን እንማፀነው።ሰዓቱን አስቡት ልባችን ፍፁም ወደ አላህ እያሰበ አዕምሯችን ከሁሉ ነገር ነፃ ሆኖ በረሃብ በተሰባበረ አካል ያ አላህ ስንል ምን ግርዶ ይኖራል ? ለዚህ ነው መልእክተኛው በዛን ሰዓት ለፆመኛ ተቀባይነት ያለው ዱዓእ አለው ያሉት።
ثبت في سنن أبي داوود من حديث عبد الله بن عمر رضي الله عنهما قال: كان رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا أفطر قال: ذهب الظمأ وابتلت العروق وثبت الأجر إن شاء الله. وحسنه الشيخ الألباني.
ሌላው ዘሀበ አዝዘመኡ ( ጥሙ ተወገደ) ወብተለቲል ዑሩቁ ( ስሮች ረጠቡ) ወሰበተል አጅሩ ( አጅሩም ተረጋገጠ) የሚለው ዱዓእ በተምር ወይም በውሃ ካፈጠርን በኋላ ነው ማድረግ ያለብን ። የተለመደውና ብዙዎች የሚያደርጉት ሊያፈጥሩ ሲሉ ነው ይህ ከሐዲሱ መቅሰድ ጋር ይጋጫል።ምክንያቱም ሳያፈጥር ከሆነ መባል የነበረበት ጥሙ ሊወገድ ነው ፣ ስሮች ሊረጥቡ ነው ፣ አጅሩ ሊረጋገጥ ነው ነበር ‼ የአላህ መልእክተኛ ስለሆነና ስለተረጋገጠ ነገር ነው የነገሩን ይህ ደግሞ ካፈጠርን በኋላ ነው እንጂ አይሆንም።ካፈጠርን በኋላ ሲባል ጠግበን ከበላን በኋላ ማለት አይደለም። አንድ ጊዜ እንደተገነጨን ወይም አንድ ተምር እንደበላን ማድረግ እንችላለን ። ይህ ማለት እያፈጠርን እያለን ማለት ነው። አላህ ከተጠቃሚዮች ያድርገን።✍

➦ከላይ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት አንድ ሰው በትከሻው የተሸከመው ከረጢት ነገር ላይ "اجر الصيام" (የጾም ምንዳ/ዋጋ) የሚል ጽሁፍ አለበት።
➦ነገር ግን ከረጢቱ ተቀድዶ የያዘው እህል (ምንዳው) እየፈሰሰ እንደሆነ ያሳያል።
ቀዳዳዎቹ ላይ የተጻፉት ቃላት የጾምን ዋጋ የሚያሳጡ ወይም የሚያጠፉ ተግባራትን እንዲህ በማለት ይገልጻሉ:▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
مسلسلات (ሙሰልሰላት)፦ ጊዜን በከንቱ የሚያባክኑ ተከታታይ ድራማዎች።
غيبة (ጊባ)፦ ሰውን በሌለበት ማማት።
علاقات محرمة (አላቃቱ አል ሙሐረመህ)፦ የተከለከሉ (ሀራም) ግንኙነቶች።
نميمة (ነሚማ)፦ ነገር ማዋሰድ ወይም በሰዎች መካከል ጠብን ለመጫር ወሬ ማመላለስ።
تأخير الصلاة (ተእኺር አስ-ሰላህ)፦ ሶላትን በወቅቱ አለመስገድ (ማዘግየት)።
تبرج (ተበሩጅ)፦ አለባበስንና ውበትን ለባእድ ሰዎች ማሳየት።
اغاني (አጋኒ)፦ ዘፈኖችን ማዳመጥ።
➦ዋናው መልዕክቱ፡▼▼▼▼▼▼
አንድ ሰው ቀኑን ሙሉ ተርቦና ተጠምቶ ሊጾም ይችላል፤ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱትን ስህተቶች የሚሰራ ከሆነ፣ የጾሙን ዋጋ (ምንዳ) ልክ እንደተቀደደ ከረጢት እያፈሰሰው እንደሆነና መጨረሻ ላይ ባዶ እጁን ሊቀር እንደሚችል ለማስጠንቀቅ ነው።
ስለዚህ ምስሉ "ጾምህ ሆድህን ብቻ ሳይሆን ምላስህን፣ አይንህንና ጆሮህንም ይሁን" የሚል ምክር ይዟል።✍️

▣የተቅዋ (አላህን የመፍራት) ትሩፋቶች!
➦ተቅዋ ማለት አላህ ያዘዘውን መፈፀም የከለከለውን መከልከል ነው። የላቀው ጌታችን አላህ ለዚህ ተግባር ብዙ ትሩፋትን አድርጎለታል። ከነዚህ ትሩፋቶች መካከል፦
🔴ተቅዋ የዒልም ምንጭ ነው፦
➦አላህን የሚፈራ ሰው አላህ እውቀትን ይለግሰዋል። ዲኑንም ያሳውቀዋል። ምክንያቱም እውቀት ብርሀን ነው። ይህ ብርሀን ደግሞ ለንፁህ ልቦች ነው የሚለገሰው። የተከበረው አላህ እንዲህ አለ፦
«وَاتَّقَوا اللهَ وَيُعَلِّمُكُمُ اللهُ» البقرة ٢٨٢
«አላህንም ፍሩ።አላህ ያሳውቃቹሀል።» አል-በቀራ 282
🔴ተቅዋ የችግሮች ሁሉ መፍትሄ ምንጭ ነው፦
➦አላህን የሚፈራ አካል ፍራቻው ለሁሉም ችግሮቹ መፍትሄ ምንጭ ይሆነዋል። ምክንያቱም ሁሌም አላህን እያስታወሰ እየፈራ የሚንቀሳቀስ ሰው አላህ በሁሉም ጉዳዩ ከሱ ጋር ይሆንለታልና። የላቀው አላህ እንዲህ አለ፦
«وَمَنْ يَتَّقِ اللهَ يَجْعَلْ لَّهُ مَخْرَجًا» الطلاق ٢
«አሏህን የሚፈራ ሰው ለሱ መውጫ ያበጅለታል» አ'ጦላቅ 2
- እንዲሁም ተቅዋው ችግሮቹን ሁሉ በሸሪአ እንዲመዝን ያደርገዋል። ችግሩን በሸሪአ መዝኖ መፍትሄውን ከሸሪአ የፈለገ ሰው ደግሞ ጥሩ ጥሩ መፍትሄን ያገኛል።
«...ذَلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيْلاً» النساء ٥٩
«...ያ የተሻለ እና መጨረሻውም ያማረ ነው።» አ'ኒሳአእ 59
🔴ተቅዋ ካልታሰበ ቦታ ሪዝቅን ያመጣል፦
➦አላህን የሚፈራ አካል አላህ ካላሰበበት ቦታ ይለግሰዋል። ምክንያቱም ሁሉም ሀሳቡ አኼራው ያደረግ ዱንያ ፈልጋው ትመጣለች። አላህ እንዲህ ይላል፦
«وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ» الطلاق ٣
«ከማያስበው ቦታ ይለግሰዋል።» አ'ጦላቅ 3
- እንዲሁም ተቅዋ ያለው ሰው ለአላህ ብሎ አላህን ፈርቶ ብዙ ነገር ይተዋል። ለአላህ ብሎ አንድን ነገር የተወ ደግሞ የተሻለን ነገር ይተካለታል። መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«ﺇِﻧِّﻚَ ﻟَﻦْ ﺗَﺪَﻉَ ﺷَﻴْﺌﺎً ﻟﻠﻪِ ﻋَﺰَّ ﻭَﺟَﻞَّ ﺇِلَّا ﺑَﺪَّﻟَﻚَ ﺍﻟﻠﻪُ ﺑِﻪِ ﻣَﺎ ﻫُﻮَ ﺧَﻴْﺮٌ ﻟَﻚَ ﻣِﻨْﻪُ» ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺣﻤﺪ
ﻭﻗﺎﻝ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ: ﻭﺳﻨﺪﻩ ﺻﺤﻴﺢ ﻋﻠﻰ ﺷﺮﻁ ﻣﺴﻠﻢ ﺍﻟﺴﻠﺴﻠﺔ ﺍﻟﻀﻌﻴﻔﺔ 1/ 62
«አንተ ለአሏህ ብለህ ምንም ነገር አትተውም አላህ በሱ ቦታ የተሻለወን ቢተካልህ እንጂ!» አህመድ
🔴ተቅዋ የተሻለ ልብስ ነው፦
➦አሏህን መፍራት ከምንም በላይ የተሻለ ልብስ ነው። ልብስ ሲባል ምንድ እንደሆነ ታውቃለህ? ልብስ በዚህ ቦታ ላይ ስራ ማለት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
«وَثِيَابَكَ فَطَهِّرْ» المدثر ٤ روى أبو روق عن الضحاك: "معناه وعملك فأصلح" وقال السدي: "يقال للرجل إذا كان صالحا إنه لطاهر الثياب وإذا كان فاجرا إنه لخبيث الثياب" انظر تفسير البغوي
«ስራህን (ከሽርክ) አፅዳ» አል'ሙደሲር 4
ኢማሙ አ'ደሀክ እንዲህ አሉ፦ «ትርጉሙ ስራህን አስተካክል ማለት ነው!» ኢማሙ አሱደይ ደግሞ እንዲህ አሉ፦ «ሰውዬው ደግ ሲሆን እሱ ልብሱ ንፁህ ነው ይባላል። አመፀኛ ሲሆን ደግሞ እሱ ልብሱ ቆሻሻ ነው ይባላል።» ተፍሲሩል በገዊይ
- እና ስራ ልብስ ነው። የተሻለው ልብስ ደግሞ (ስራ) ተቅዋ እንደሆነ አላህ ይነግረናል፦
«وَلِبَاسُ التَّقْوَى ذَلِكَ خَيْرٌ» الأعراف ٢٦
«አሏህ የመፍራት ልብስ (ስራ) ይህ የተሻለ ነው።» አል'አዕራፍ 26
🔴ተቅዋ የተሻለ ስንቅ ነው፦
➦አንድ ሰው ወደ ሚጓዝበት ቦታ ሲሄድ ስንቅ መሰነቁ አይቀሬ ነው። ሲሰነቅ የስንቁን መጠን የሚያደርገው በጉዞው ርቀት ልክ ነው። የጉዞው ርቀት ትልቅ ከሆነ ትልቅ ስንቅ ይሰነቃል፤ ትንሽ ከሆነ ትንሽ ስንቅ ይሰነቃል። አኼራችን ደግሞ ትልቅ ጉዞ ስለሆነ ትልቅ ስንቅ ልንሰነቅ ይገባል። ከስንቆች ሁሉ የተሻለውም አላህን መፍራት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
«وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَى» البقرة ١٩٧
«ተሰነቁም የተሻለው ስንቅ አላህን መፍራት ነው!» አል'በቀራ 197
🔴ተቅዋ ሀቅ እና ባጢልን መለያ ነው፦
➦ተቅዋ የተውሒድ እና የሽርክ፣የሀቅና የባጢል፣ የቀጥተኛው መንገድና የጥመት መንገድ፣ የሱና እና የቢድአ፣ የሱንይና የቢድኢይ ወዘተ መለያ መሳሪያ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
«يَاأَيُّهَا الذِّينَ إِنْ تَتَّقُوا اللهَ يَجْعَلْ لَّكُمْ فُرْقَانَا» الأنفال ٢٩
«እናንተ ያመናቹ ሆይ አላህን ብትፈሩ መለያን ያደርግላቹሀል!» አል'አንፋል 29
🔴ተቅዋ ጉዳዮችን ያገራል!
➦አሏህን መፍራት ጉዳዮቻችንን ያገራልናል። በጉዳዩ ላይ አላህን ባንፈራ ከበድ የሚል የነበረው ጉዳይ በተቅዋ ሰበብ ክብደቱ ይቀረፋል። አላህ እንዲህ፦
«وَمَنْ يَتَّقِ اللهَ يَجْعَلْ لَهُ مِنْ أَمْرِهِ يُسْرًا» الطلاق ٩
«አሏህን የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለሱ መግራትን ያደርግለታል!» አ'ጦላቅ 4
🔴 ተቅዋ ወንጀል ያስምራል፦
➦አላህን መፍራት ወንጀልን ያስምራል። አላህ እንዲህ ይላል፦
«ﺇِﻥْ ﺗَﺘَّﻘُﻮﺍ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳَﺠْﻌَﻞْ ﻟَﻜُﻢْ ﻓُﺮْﻗَﺎﻧًﺎ ﻭَﻳُﻜَﻔِّﺮْ ﻋَﻨْﻜُﻢْ ﺳَﻴِّﺌَﺎﺗِﻜُﻢْ ﻭَﻳَﻐْﻔِﺮْ ﻟَﻜُﻢْ» ﺍﻷﻧﻔﺎﻝ ٢٩
«አላህ ከፈራቹ መለያን ያደርግላቹሀል። ፅያፍ ስራዎቻቹንም ያራግፍላቹሀል። ይምራቹሀልም!» አል'አንፋል 29
- የተቅዋ አላህን መፍራት ትሩፋቶች ብዙ ናቸው።ደስታን ፈላጊዎች የተቅዋን ምንነት ቢረዱ ኖሮ ከሱ ውጪ ሌላን አማራጭ ባልፈለጉ ነበር። አላህ እሱን ከሚፈሩ ባሮቹ ያድርገን!✍
➲Linኩን እየተቀላቀላችሁ ሼር አድርጉ ባረከሏሁ ፊኩም ጀመዓው

📌تعريفُ الصَّوم، وأقسامُه، وفضائِلُه، والحِكمةُ مِن تَشريعِه
:🔴تعريفُ الصَّوم:
الصَّوم لغةً: الإمساكُ
الصَّوم اصطلاحًا: التعبُّدُ لله سبحانَه وتعالى، بالإمساكِ عن الأكلِ والشُّربِ وسائِرِ المُفَطِّراتِ، مِن طُلوعِ الفَجرِ إلى غُروبِ الشَّمسِ
🔴المبحث الأول: أقسامُ الصَّوم
ينقسِمُ الصَّومُ باعتبارِ كَونِه مأمورًا به، أو منهيًّا عنه شَرعًا، إلى قسمين :
الأول: الصَّومُ المأمورُ به شَرعًا
وهو قِسمانِ:
🔴أ- الصَّومُ الواجب، وهو على نوعينِ:
1- واجبٌ بأصلِ الشَّرعِ- أي بغيرِ سَبَبٍ مِنَ المكلَّفِ-: وهو صومُ شَهرِ رَمضانَ
2- واجبٌ بِسَبَبٍ مِنَ المكلَّف: وهو صومُ النَّذرِ، والكفَّارات، والقَضاء.
🔴ب- الصَّومُ المُستحَبُّ (صوم التطوُّع)
وهو قِسمان:
1- صومُ التطَوُّعِ المُطلَق: وهو ما جاء في النُّصوصِ غيرَ مُقَيَّدٍ بزمَنٍ مُعَيَّنٍ
2- صومُ التطَوُّعِ المقيَّد: وهو ما جاء في النُّصوصِ مقيَّدًا بزمنٍ مُعَينٍ، كصومِ السِّتِّ مِن شوَّالٍ، ويومَيِ الاثنينِ والخميس، ويومِ عَرَفةَ، وعاشوراءَ.
🔴الثاني: الصَّومُ المنهيُّ عنه شرعًا
وهو قِسمانِ:
1- صَومٌ مُحَرَّمٌ: وذلك مثلُ صَومِ يَومَيِ العيدينِ.
2- صومٌ مكروهٌ: وذلك مثلُ صَومِ يومِ عَرَفةَ للحاجِّ.
🔴المبحث الثاني: فضائِلُ الصِّيامِ
للصِّيامِ فضائلُ كثيرةٌ شَهِدَت بها نصوصُ الوَحيينِ؛ منها:
1- أنَّ اللهَ تبارك وتعالى أضافَه إلى نفسه فقال: (الصوم لي وأنا أجزي به ).
2- تجتمِعُ في الصَّومِ أنواعُ الصَّبرِ الثَّلاثةُ.
3- الصِّيامُ يشفَعُ لصاحِبِه يومَ القيامةِ .
4- الصَّومُ مِنَ الأعمالِ التي وعَدَ الله تعالى فاعِلَها بالمغفرةِ والأجرِ العَظيمِ .
5- الصِّيامُ كفَّارةٌ للذُّنُوبِ والخطايا .
6- الصَّومُ جُنَّةٌ وحِصنٌ مِنَ النَّارِ .
7- الإكثارُ مِنَ الصَّومِ سببٌ لدُخُولِ الجَنَّةِ .
8- خُلُوفُ فَمِ الصَّائِم أطيَبُ عند الله تعالى مِن رِيحِ المِسْكِ .
🔴المبحث الثالث: الحِكمةُ مِن تَشريعِ الصِّيامِ
لَمَّا كانت مصالِحُ الصَّومِ مشهودةً بالعُقُولِ السَّليمةِ، والفِطَرِ المستقيمةِ، شَرَعَه اللهُ سبحانه وتعالى لعبادِه؛ رحمةً بهم، وإحسانًا إليهم، وحِمْيَةً لهم وجُنَّةً
🔴فالصِّيامُ له حِكَمٌ عظيمةٌ وفوائدُ جليلةٌ؛ ومنها:
1- أنَّ الصَّومَ وسيلةٌ لتحقيقِ تقوى الله عزَّ وجَلَّ.
2- إشعارُ الصَّائِم بنعمةِ الله تعالى عليه.
3- تربيةُ النَّفسِ على الإرادةِ، وقوَّةِ التحَمُّلِ.
4- في الصَّوم قهرٌ للشَّيطانِ.
5- الصَّومُ موجِبٌ للرَّحمةِ والعَطفِ على المساكينِ.
6- الصَّومُ يُطَهِّرُ البَدَنَ من الأخلاطِ الرَّديئةِ، ويُكسِبُه صحةً وقوةً.

🔴ኦርቶዎች የሚፆሙት ፆም የአብይ ፆም ነው።ጠ/ሚ አብይ ግን እንኳን አደረሳችሁ አላላቸውም እንዴ¡
😁6
▣በማወቅም ባለማወቅም በረመዷን ወር ውስጥ የሚከሰቱ ስህተቶች🚫
➲በረመዳን ወቅት በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች መካከል፦
~~~~
① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣
② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሱሑርን አስቀድሞ በመመገብ ፈጅር ሳይሰግዱ መተኛት፣
③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም/ ሙሰልሰላት ማሳለፍ፣
④ ረመዳንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣
⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣
⑥ ተራዊሕ ላይ በየ አራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣
⑦ የተራዊሕ ኢማሞች ከሶላቱ ይልቅ ለቁኑት ዱዓእ የበለጠ ትኩረትና ጊዜ መስጠት፣
⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣…ብዙ ነው)
⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ " እያሉ በእስፒከር መጮህ፣
(10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣
(11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣
(12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣
(13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣
(14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣
(15) ሴቶች ሽቶ ተቀባብቶ ለተራዊሕ መውጣት፣
(16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች አላስፈላጊ መዝረክረክ፣
(17) ሃሜት፣
(18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣
(19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ፣ ወዘተ ማሳለፍ፣
(20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣
(21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግዴታ ነው። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ይገባል)፣
(22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርአን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።)
(23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣
(24) አንዳንድ አካባቢዎች ዒሻን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣
(25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣
(26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ህዝብን ማዘዝ፣
(27) የምግብ ብክነት ወዘተረፈ.....ናቸው ✍

🔴የእስልምና ህግጋት በዙብኝ...
➦ከዐብዱላህ ቢን ቡስር ረዲየላሁ ዐንሁ እንደተወራው፦ አንድ ሰው እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የእስልምና ሕግጋት (የትርፍ ሥራዎች) በዝተውብኛል፤ ስለዚህ አጥብቄ የምይዘውን የምከተለውን ነገር ንገሩኝ።"
እሳቸውም ﷺ እንዲህ አሉት፦
"ምላስህ ሁልጊዜም አላህን በማውሳት (በዚክር) እንደራሰ ይቆይ።"
(ቲርሚዚ (3375) እና ኢብኑ ማጃህ (3793) ዘግበውታል።)
✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል✍✍
Linኩ ሼር ይደረግ ባረከሏሁ ፊኩም