የሀቅ አድማስ Official apologetics 🔰
557 subscribers
223 photos
79 videos
27 files
103 links
▣የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ ና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ።(እርሷም) አሏህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣በርሱም ምንንም ማንንም ላናጋራ፣ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤በላቸው፡፡እምቢ ቢሉም፦እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡"[📚ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን:64]

🔥"እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙ"[📚ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን:102]!🔥
Download Telegram
መክተፊያና ክርስትና😁‼️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወይኔ በላቸው ዘመወዛገብ ዘማወዛገብ😂
ተመልከቱ እንግዲህ የክርስቲያኖችን ጉድ በዚህ ልክ ይወርዳሉ😀
😁2
Forwarded from [Christianity🎯]
🔺የሎዶቅያ መልዕክት?

ጳውሎስ ወደ ሎዶቅያ የላከው በፊት ላይ ተቀባይነት የነበረው ዛሬ ላይ ግን የተወገደ መልዕክት እንደነበረው ያውቁ ኖሯል?

ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ በላከው መልዕክቱ ላይ ወደ ሎዶቅያ የላከው መልዕክት እንዳለ ጽፏል፦

“ይህችም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበች በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምትገኘውን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።”
  — ቆላስይስ 4፥16

አንዳንድ የእንግሊዘኛ ትርጉሞች በግልጽ "የጻፍኩላቸውን መልዕክት/the letter I wrote to them" ብለው አስቀምጠውታል፦

Colossians 4:16 (NLT) "After you have read this letter, pass it on to the church at *Laodicea* so they can read it, too. And you should read the letter I wrote to them."

አውዱ ላይ "የጻፍኩላቸው" እያለ ያለው ለሎዶቅያ እንደሆነ ግልጽ ያለ ፍንትውም ያለ ጉዳይ ነው። ይህም ለሮሜ፣ ለኤፌሶን፣ ለቆሮንጦስ ሰዎች ለሌሎችም መልዕክታትን ጽፎ እንደነበረው ሁሉ ለሎዶቅያ ሰዎችም መልዕክትን ጽፎላቸው እንደነበረ ማሳያ ነው።

"Commentary Critical and Explanatory on the Whole Bible" የተባለ የባይብል ማብራሪያም "ከሎዶቅያ የምትገኘውን መልዕክት" የሚለውን የጳውሎስን ንግግር "the Epistle which I wrote to the Laodiceans" በማለት *ለሎዶቅያ(ሰዎች) የጻፍኩት መልዕክት* ማለቱ እንደሆነ አብራርቶታል።

በዚህ ብቻ አያበቃም ይህ መልዕክት በጣም ብዙ በሆኑ ከ6-15ተኛ ክፍለ ዘመን በሚገኙ የባይብል እደ-ክታባት ውስጥ የሚገኝ ነው[1]።ለአብነት ያክል በVictor አማካኝነት Capua ላይ የተዘጋጀው Codex Fuldensis(541-546 A.D) ውስጥ ይህ መልዕክት ይገኛል[2]&[5]።

በጣም የሚገርመው ነገር ኤጲፋንየስ የተባለው የ4ተኛ ክፍለ ዘመን የቤተ-ክርስቲያን አባትም ይሄንን መልዕክት የጳውሎስ መሆኑን አጽድቆታል[3]።በተጨማሪም ኤጲፋንየስ የሎዶቅያ መልዕክትን ከጳውሎስ መልዕክታት መካከል 15ተኛ አድርጎ እንደመደበው ታዋቂው የNew Testament scholar የሆነው Bart D. Ehrman ያረጋግጣል[4]።

ይህ መልዕክት በዋናነት በሁለተኛው የኒቂያ ጉባኤ(787 CE) ላይ ውድቅ ተደርጓል። ሆኖም በጉባኤ ደረጃ ውድቅ ከተደረገ ቡሃላ ለራሱ በብዙ የባይብል እደ-ክታባት ላይ ተካቷል፤ German bibles ከሉተር በፊት ተካቷል, Czech Bibles ላይ በቆላስይስ እና በ1ደኛ ተሰሎንቄ መልዕክት መካከል ከአስራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን በፊት ተካቷል[5]።

እንግዲህ ይህ መልዕክት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተቀባይነት ነበረው በተለይ በምዕራብ የተከበረ መልዕክት ነበር፤ በትርጉሞች ሳይቀር ተካቶ የነበረ ነበር። ይህ ከሆነ አሁን ማስወገድ ምን አስፈለገ?

ይህ የሚያሳየን ባይብል እጅግ ሲበዛ ተዓማኒነት የጎደለው መጽሐፍ መሆኑን ነው፤ ማንም ተነስቶ የሚጨምርበት የሚቀንስበት የሆነ መጽሐፍ መሆኑን ያሳየናል። ሲያሻቸው የጳውሎስ ጹሁፍ አድርገው ይቀበሉታል ከሌሎች የባይብል ክፍሎች ጋር አካተው ቅዱስና የፈጣሪ ቃል ከሚሏቸው ጹሁፎች መካከል ያስቀምጡታል፤ ሲያሻቸው አሽቀንጥረው ይጥሉታል ይህ የሚያሳየው የፈጣሪ መልዕክት ነው ተብሎ የሚታሰበው ባይብል ላይ በዘመናት ውስጥ ሲጨመርበት ሲቀነስበት እንደኖረ ነው። ወጥ የሆነም ባይብል እንዳልነበረ አሁንም እንደለለ አለም አቀፋዊ ሐቅ ነው። በፊት ላይ እንደ ፈጣሪ ቃል ሲነበቡ የኖሩ አሁን በጉባኤና በተወሰኑ ሰዎች አማካኝነት የተወገዱበት ባይብል በምንም ሂሳብ ተዓማኝ ሊሆን አይችልም!
📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎
1] Forgery and Counter Forgery Bart D. Ehrman p.798
2] The Text Of The New Testament p.108
3] The panarion of Epiphanius of salamis Book 1 p.315
4] Forgery and Counter Forgery Bart D. Ehrman p.799
5] Forgery and Counter Forgery Bart D. Ehrman p.800

https://t.me/Christianity_With_History
👍1
Forwarded from Murad|⛉
ባይብል ተጠብቋልን?

_ክፍል ሁለት_

ወደ ክርስትናው ስንመጣ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የክርስትና ቀደምት ቅዱሳን አባቶችና ሊቃውንቶች በባይብል ዙሪያ ያላቸው አቋም ከሌሎች አባቶች ጋር ከመጋጨቱ በተጨማሪ የዛሬውን ባይብል ገደል የሚከት የጋራ አቋምም ነበራቸው።

በክርስትና ታሪክ ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ ድረስ አንድ ወጥ የሆነ በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ባይብል እንደለለ ይታወቃል። ለምሳሌ ፕሮቴስታንቶች 66 ሲቀበሉ ኦርቶዶክሶች 81 ይቀበላሉ ካቶሊኮች ደግሞ 73 ይቀበላሉ። ነገር ግን ከነዚህ መጽሃፍት ውጪም የነበሩ እንደ አምላክ ቃልነት ተቀባይነት የነበራቸው መጽሐፍት ነበሩ፤ ከነዚህ መካክል ሆነው ደግሞ በጥንት አባቶች ተቀባይነት ያልነበራቸው ነበሩ።

ለምሳሌ ዛሬ ላይ ሦስቱም የክርስትና ሴክቶች በሚቀበሏቸው ባይብል ዘንድ የማይገኘውን "የሔርማስ መልዕክትን" ->ኢራንየስ(2 Century)[1] ->ቀሌሚንጦስ ዘአሌክሳንደሪያ(2-3 Century)[2] ->ጠርጡሊያኖስ(2-3 Century)[3] ልክ እንደ መለኮታዊ ራዕይ ወይም እንደ Scripture አድርገው ይቀበሉት ነበር።

/በዝርዝር ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንመልከት/

የአሌክሳንደርያው ቀለሚንጦስ ዛሬ ባይብል ላይ የለሉትን እነ Didache'ን ጨምሮ የሔርማስ'ን መልዕክት ልክ እንደ በመለኮታዊ መሪነት እንደተጻፉ ነበር የሚያያቸው፦

"በግብፅ፤ የአዲስ ኪዳን ቀኖና ታሪክ ከእስክንድርያው ቀሌምንጦስ (ከ217 ዓ.ም በኋላ ያረፈ) በፊት የነበረው ሁኔታ ግልጽ አይደለም። ቀሌምንጦስ፣ ምናልባት ከያዕቆብ፣ ከ2ኛ ጴጥሮስ እና ከ3ኛ ዮሐንስ በስተቀር፣ በኋላ ላይ የተወሰኑትን 27ቱን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ ያውቃቸው እንደነበር ይገመታል። ሆኖም ለሌሎች በርካታ መጻሕፍትም ከፍተኛ ሥልጣን (ተቀባይነት) ሰጥቶ ነበር። ከእነዚህም መካከል እንደ ዲዳኬ (Didache)፣ ሄርማስ እረኛው (Shepherd of Hermas)፣ የጴጥሮስ ስብከት (Kerygma of Peter) እና ምናልባትም 1ኛ ቀሌምንጦስን የመሳሰሉትን በመለኮታዊ መሪነት እንደተጻፉ (divinely inspired) አድርጎ ይቆጥራቸው ነበር።"
(New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.30-1)

ኢራንየስ'ም(2 Century) የእብራዊያን መልዕክትን የጳውሎስ መሆኑን አይቀበልም ነበር፤ ከአሌክሳንደርያው ቀለሚንጦስ በተመሳሳይ የሔርማስ መልዕክትንም እንደ Scripture ነበር የሚቀበለው፦

"ወደ ፊልሞን የተላከውን መልእክት አይጠቅስም፤ እንዲሁም ወደ ዕብራውያን የተላከውን መልእክት ቢያውቀውም፣ ጸሐፊው ጳውሎስ መሆኑን አይቀበልም። 'እረኛው ሔርማስ' (Shepherd of Hermas) የተሰኘውን መጽሐፍ 'መጽሐፍ እንዲህ ይላል' (Scripture says) በሚለው አገላለጽ ያስተዋውቀዋል።"
(New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.31)

Hippolytus'ም 21 የአዲስ ኪዳን መጽሐፍቶችን የሚቀበል ሲሆን ከመምህሩ ኢራንየስ በተመሳሳይ የእብራዊያን መልዕክትን የጳውሎስ እንደሆነ አይቀበልም ነበር ለእርሱ ይህ መጽሃፍ ቀኖናዊ አልነበረም፦

"የኢራንየስ ደቀ መዝሙር የሆነው የሮሙ ቅዱስ ሂፖሊተስ (በ235 ዓ.ም. ያረፈ)፣ የሁለቱን ኪዳናት ቅዱሳት መጻሕፍት 'የክርስቶስ ሁለት ጡቶች' ሲል ይጠራቸዋል፤ ይህም በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው ቃል ውስጥ ያለውን የጠበቀ የምግብ (የምገባ) ግንኙነት ያመለክታል። የእርሱ አዲስ ኪዳን ቢያንስ 21 መጻሕፍትን ያካትታል። የዕብራውያንን መልእክት የጳውሎስ እንደሆነ አድርጎ ስለማይቆጥር፣ ለእርሱ ቀኖናዊ (የመጽሐፍ ቅዱስ አካል) አይደለም። [በጽሑፎቹ ውስጥ] ፊልሞንን፣ 2ኛ ወይም 3ኛ ዮሐንስን፣ ያዕቆብን ወይም ይሁዳን አይጠቀምም።"
(New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.31)

በተጨማሪ Philip schaff'ም ጥንታዊ አባቶች "የሔርማስ መልዕክት" መለኮታዊ እንደሆነ እንደሚያምኑ ተናግሯል።
ለምሳሌ ያክል ኢራንየስ፣ የአሌክሳንደርያው ቀለሚንጦስ እንዲሁም አርጌንስ  የሔርማስ መልዕክት መለኮታዊ መሆኑን በጹሁፎቻቸው መግለጻቸውን አስፍሯል፦

"የጥንት ጸሐፊዎች መጽሐፉ በእርግጥም በመንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፈ ያምናሉ። ኢራኒየስ እንደ ቅዱስ መጽሐፍ ይጠቅሰዋል፤ የእስክንድርያው ቀሌምንጦስ ስለ መጽሐፉ ሲናገር አባባሎቹ "መለኮታዊ" እንደሆኑ ይገልጻል፤ አርጌንስም ቢሆን፣ አንዳንድ አገላለጾቹ በአንዳንዶች ዘንድ ጥርጣሬን የሚያሳዩ ተደርገው ቢታዩም፣ እርሱ ግን "በመለኮታዊ አነሳሽነት እንደተጻፈ" ያለ ጥርጥር አስተያየቱን ይሰጣል።"
(Fathers of the Second Century by Philip Schaff p.8)

የሔርማስ መልዕክት 4ተኛ ክፍለ ዘመን ላይ እንደተጻፈ የሚገመተውና እጅግ ጠቃሚ ከሚባሉ የባይብል እደ-ክታባት መካከል የሚመደበው Codex Sinaiticus ውስጥም የሚገኝ ነው።[4]

የMuratorian ቀኖናም እንደ New Catholic Encyclopedia 22/23 የአዲስ ኪዳን መጽሐፎች ብቻ ነው የያዘው(24 የሚሉም ምሁራኖች አሉ)፦

"በኢጣሊያ፤ ምናልባት ከ180 እስከ 190 ዓ.ም. ገደማ (ምናልባትም በሂፖሊተስ) የተዘጋጀው የሙራቶሪያን ፍራግመንት (Muratorian Fragment) ቀኖና፣ (ጸረ-ማርሲዮናዊ የሆኑትን የወንጌላት መቅድሞች ካልቆጠርን) የቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው የአዲስ ኪዳን ቀኖና ዝርዝር ነው። ይህም 22 (ወይም 23) የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ይዘረዝራል።"
(New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.31)

ይህ የMuratorian Canon በተመሳሳይ ማለትም ልክ እነ ኢራንየስ እነ ሂፖላይተስ የእብራዊያን መልዕክትን እንደ ጳውሎስ መልዕክት እንደማይቀበሉት ሁሉ ይህ ቀኖናም የእብራዊያንን መልዕክት ከቀኖና ገለል ያደረገ ነበር።[5]

3ተኛ ክፍለ ዘመን አካባቢም ላይ የኖረው ጠርጡሊያኖስ የእብራዊያን  መልዕክትን አይቀበልም ነበር፦

"በአፍሪካ፣ ተርቱሊያን ከ2ኛ ጴጥሮስ እንዲሁም ከ2ኛ እና 3ኛ ዮሐንስ በስተቀር ሁሉንም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ይጠቀም ነበር። ምንም እንኳን የዕብራውያን መልእክት በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በስፋት ጥቅም ላይ እንደሚውል ቢቀበልም፣ የጻፈው በርናባስ ነው በማለት ከቅዱሳት መጻሕፍት (ከቀኖና) ያስወጣዋል።"
(New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.32)

ታዲያ ይህ ሁሉ የቤተ-ክርስቲያን አባት እንደ አምላክ ቃል የተቀበለውን መጽሐፍ አሁን ማስወገድ ያስወገዱትን ደግሞ መቀበል የጤና ነው? ስጀምር "የዛሬውን ባይብል ገደል የሚከት የጋራ አቋምም ነበራቸው" ያልኩት ለዚህ ነው!

የቤተ-ክርስቲያን ታላላቅ አባቶች፣ ሊቃውንቶች በዚህ መልኩ አሁን ካለው ባይብል ጋር ፈጽሞ የራቀ አቋም ነበራቸው የሚገርመው ልዩነታቸው ግዝፈቱ *በመጽሃፍት* ደረጃ ነበር የሚለያዩት። ከአሁኑ የባይብል ቀኖናዎች ጋርም እርስ በራሳቸውም ሲጋጩ ነው የኖሩት። ለዘመናት ምንም ወጥ ያልሆነ በገዛ ቅዱሳን አባቶቹና ሊቃውንቶቹ ዘንድ ውድቀትን መለያየትን ያስተናገደ መጽሐፍ እንደ ባይብል ማን አለ? ማንም! 

1] Irenaeus Against Haer; 4.20.2
2] Clement of Alexandria Stromata; 1.17.29
3] Tertullian De Orat; 16
4] Fathers of the Second Century by Philip Schaff p.9
5] The text of New testament p.49

https://t.me/Murad11145
❤2
https://t.me/amuresponds


አሰላም አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱ ያጀማአ

ንፅፅር መማርና ማወቅ የሚፈልጉ እናም በእስልምና ላይ ለሚነሱ ሹብሀዎች መልሶች ለማግኘት ወይ ለመጠየቅ የሚፈልግ ሰዎች ይሄን ቻናል ተቀላቀሉ በቅርቡም አሪፍ ፕሮግራም የምንጀምር ይሆናል ተቀላቀሉ

ሼርም እያደረጋች የሂዳያ ሰበብ ሁኑ

ሙስሊምም ክርስቲያኑም ኢቲስቱም መቀላቀል ይችላል አላማው እውነታውን መማር ነው
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንደዚህ አይነት ውርደት በማንም አይድረስ😁
😁6
Forwarded from Jake Theology Student (Ja)
አብዱል?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው።

قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا

(ሕፃኑም) አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል፡፡»
(📗19:30)

ብዙ ዕቅበተ እምነት ላይ እንሰራለን የሚሉ አላዋቂ ክርስትያኖች በውይይት መሃል ሙስሊሞችን ያሸማቀቁ መስሏቸው "አብዱል" ሲሉ ይስተዋላል።

ለመሆኑ እነዚህ አላዋቂ ክርስትያኖች ሙስሊሞችን "አብዱል" ሲሉ ምን ማለት ፈልገው ነው ሲባል መልሱ ያው "አብድ" (ባሪያ) ማለታቸው ነው።

ቅሉ ግን ሙሥሊሞች ባሪያ ማለትም የአሏህ ባሪያ ሲባሉ ያስደስታቸዋል እንጂ በፍጹም አያሸማቅቃቸውም። ምክንያቱም  عبد"አብድ" የሚል የአረብኛ ቃል "አበደ" ማለትም አመለከ ተገዛ ከሚል "ሥርወ-ቃል" የመጣ ሲሆን "አምላኪ" "ተገዢ" ማለት ነው።

አንድ  እጅና እግሩን ሰጥቶ ለአላህ የሚታዘዝ ሙሥሊም "عَبْدُ اللَّهِ" አብዱሏህ" ማለትም "የአላህ ባሪያ" ይባላል! ውዱ ነቢያችን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሐዲሳቸው አላህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ስሞች "አብዱሏህ" እና "አብዱል ረህማን" ናቸው ብለዋል።

عَنْ أَبِي وَهْبٍ الْجُشَمِيِّ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏
وَأَحَبُّ الأَسْمَاءِ إِلَى اللَّهِ عَبْدُ اللَّهِ وَعَبْدُ الرَّحْمَنِ

"አቢ ወህብ" አል-ጁሸሚይ"(ረ•ዐ) እንደተረከው የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ብሏል!
አላህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ስሞች አብዱሏህ እና አብዱል ረህማን ናቸው።
{📗ሱነን አቡ ዳውድ,4950}

በአጭሩ እኛ ሙሥሊሞች አብዱሏህ ስንባል ደስታና ኩራት ይሰማናል እንጂ በፍጹም አንሸማቀቅም። የሚያሸማቅቀው አብዱል ቀመር ማለትም የጨረቃ ባሪያ ወይም አብዱል ሸምስ ማለትም የፀሐይ ባሪያ ወይም አብዱል አብድ ማለትም ልክ እንደ ክርስትያኖች "የባሪያ ባሪያ" ወዘተ.. መባል ነው እንጂ የሚያሸማቅቀው የሁሉ ነገር ፈጣሪ የሆነው የአላህ ባሪያ መባል የሚያኮራ እንጂ በፍጹም የሚያሸማቅቅ አይደለም።

እኛ ሙሥሊሞች ባርነታችን የሁሉ ነገር ፈጣሪ ለሆነው ለአላህ ነው።

اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
"አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡
{39:62}

እስቲ አሁን ደግሞ ጦሩን ወደ ክርስትያኖች ዘወር እናድርገውና ክርስቲያኖች የአብዱል አብዱል መሆናቸውን እናሳያቸው!

እንደሚታወቀው በባይብል ውስጥ ነቢያት ሆነ የነቢያት ተከታይ አማኞች ባሪያ መባላቸው የታወቀ ነገር ነው ለምሳሌ! ዳዊትና ተከታዮች የእግዚአብሔር ባሪያ ተብለዋል።

አሁንም ባሪያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
(📗መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 17፤7)
በዚህ አንቀጽ ላይ ባሪያዬ ለሚለው የገባው የእብራይስጥ ቃል "לְעַבְדִּ֣י lə·‘aḇ·dî" ኢቤድ ሲሆን ከአረብኛው عبد አብድ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ቃል ሲሆን ባሪያዬ ማለት ነው።

ሃሌ ሉያ የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ፤ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥
(📗መዝሙረ ዳዊት 135፤1)

ብዙ መጥቀስ ይቻላል ላለማስረዘም ነው እንጂ። ይህ ብቻ አይደለም በሚያሳዝን መልኩ ክርስቲያኖች አምላክ ነው ብለው የሚያመልኩት ኢየሱስ ራሱ ባሪያ ተብሏል።

እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ!
(📗ትንቢተ ኢሳይያስ 42፤1)

አሁንም በዚህ አንቀጽ ላይ "ባሪያዬ" ለሚለው የገባው የእብራይስጥ ቃል ልክ እንደ አረብኛው " עַבְדִּי֙ ‘aḇ·dî" عبدي "አብዲ" ሲሆን ባሪያዬ ማለት ነው።

So በማቴዎስ ወንጌል ዘገባ መሰረት ኢሳያስ 42:1 ላይ ያለው ትንቢት ለኢየሱስ መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው።

በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል።
እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።
(📗የማቴዎስ ወንጌል 12፤16-18

መጽሐፉን እንዳሻቸው የሚበርዙ ቶርጋሚዎች ኢሳያስ ላይ ባሪያዬ ተብሎ የተተነበየውን ትንቢት ማቴዎስ ላይ የትንቢቱን ፍጻሜ ባሪያዬ በሚለው ፋንታ ብላቴናዬ ብለው ቀይረዎታል ቅሉ ግን ትንቢት ላይ የተነገረው ባሪያዬ ተብሎ እንጂ ብላቴናዬ ተብሎ አይደለም። ምክንያቱ በእብራይስጥ ብላቴና ለማለት የሚገባው ቃል"וְהַנַּ֖עַר" wə·han·na·‘ar ነው እንጂ "עֶ֣בֶד e·ḇeḏ" አይደለም። መጽሐፈ ኢያሱ 1:1 ተመልከት።

ስናጠቃልል እኛ ሙሥሊሞች የአላህ ባሪያ ስንባል ደስታና ኩራት ይሰማናል እንጂ በፍጹም አንሸማቀቅም ምክንያቱም የአላህ ባሪያ ስትሉን የአለማቱን ፈጣሪ አምላኪዎች ለአለማቱ ጌታ ተገዢዎች እያላችሁን ነውና።

በተቃራኒው ግን እናንተ የአብዱል አብዱል ማለትም የባሪያው ኢየሱስ ባሪያ ናችሁ የሚያሸማቅቀውና አሳፋሪው የባሪያ ባሪያ መሆን ነውና እናንተ እፈሩ ተሸማቀቁ እንጂ እኛ በፍጹም ለአላህ ታዛዥ ባሪያ በመሆናችን አንሸማቀቅም።

✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12
🔥1
ባይብል እና ብርዛት

ክፍል 1

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህ ሩህ ፣ በጣም አዛኝ በሆነው።

فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۖ فَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
{ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡}
[📖 አል-በቀረህ 2÷79]


ስለ ብርዛት ሲወሳ ብዙ ጊዜ ክርስትያኖች በሐሰት ላይ በመመስረት እርር እና ምርር ብለው ሶፍስቲክ"sophistic" ሙግቶችን ሰንዝረው ውሸትን እውነት ለማስመሰል አወሳስበው አምታተው ዝም ለማሰኘት ሲንጨረጨሩና ሲንከተከቱ ይስተዋላሉ።

☞ በመጀመርያ ደረጃ "ተሕሪፍ"distortion" ሲባል "ሐረፈ" ማለትም "በረዘ"distorted/corrupted" ከሚል አላፊ ግስ ወይም ስርወ-ግንድ የረባ ሲሆን "ብርዛት" ማለት ሆኖ እውነትን በውሸት መቀላቀል ነው። ይህን አስመልክቶም ባይብል እንደተበረዘ ቁልጭ አርገው ከሚያረጋግጡ ማስረጃዎች መካከልም በአላህ ፈቃድ

➲ የሊቃውንት እና ምሑራን ምስክርቶችትን
➲ የእደ-ክታባት የእርስ በእርስ ልዩነቶችን
➲ የመጽሐፍ ቅዱስ ቨርዥን ተቃርኖዎችን
➲ የአንቀፆች ግጭት እና ፍጭቶችንም
እንዳስሳለን


☞ በቅድሚያ የጥንት የእጅ ጽሑፎች"manuscripts" ወይም እደ-ክታባት በመጽሐፍ ቅዱስ ታእማኒነት ላይ ተፅዕኖ እንዳላቸው ግንባር ቀደምና አከርካሪ መሆናቸው እንደ ንጋቱ ፀዳል የተረጋገጠ ነገር ሲሆን ይህን አስመልክቶ ባይብል ላይ የተደረጉ ለውጦችና እርማቶችን ፍንትው አርገው የሚያረጋግጡ እንዲሁም በተለይ የአዲስ ኪዳን ወንጌላት እና መልክቶች ባይተዋርና ባልታወቁ ጸሐፊያን የተዘጋጁ እንደሆኑ ብዙ ብዙ ከምሑራን ምንጮችን መጥቀስ ቢቻልም ላለማንዛዛት ስንል የተወሰኑትን እንመልከታለን -


🎯 “ከአዲስ ኪዳን 5,340 በላይ የግሪክ እጅ ጽሑፎች መካከል ሁለት ተመሳሳይ አንድ አይነት የሆኑ የሉም። በእውነቱ በማንኛውም በዘመን ተቀራራቢ ከሆኑ ሁለት የእጅ ጽሑፎች መካከል እንኳን በእያንዳንዱ ምዕራፍ ከስድስት እስከ አሥር ሊዩነቶች ይኖራሉ። ስለዚህ አንድም የእጅ ጽሑፍ ከብርዛት ያመለጠ አለመሆኑ ግልፅ ነው።"No two of the 5340-plus Greek MSS of the NT are exactly alike. In fact the closest relationships between any two MSS in existence even among the majority average from six to ten variants per chapter. It is obvious therefore that no MS has escaped corruption.”¹


🎯 "ጥናቶች እንደሚያሳዩት በመገልበጥ ሂደት ጊዜ በጽሑፎች ውስጥ የተደረጉ አንዳንድ ለውጦች በፀረ አይሁድ ተነሳሽነት ፣ ሌሎችም በሴቶች ላይ የተወሰነ ጥላቻ ተፅዕኖ ያላቸው እንዲሁም ሌሎቹ ለዐቅብተ እምነት ስጋቶች ፣ ሌሎችም ለሥነ-መለኮታዊ እና ነገረ-ክርስቶሳዊ ግቦች እንደሆኑ ሊብራሩ ይችላሉ።studies have shown that certain changes made by scribes in the process of copying appear to have been motivated by anti Jewish sentiments; others seem influenced by a certain animosity toward women; others by apologetic concerns; and still others can be explained by theological, especially Christological concerns." ²


🎯 “በእኛ ቅጂዎች ውስጥ ብዙ ልዩነት እንዳለ የታወቀ እውነት ነው፣ በአንዳንድ ጸሓፊያን ግድየለሽነትም ሊሆን ይችላል፣ ወይም በጽሑፉ እርማት ላይ በተወሰኑ ጥፋተኞች ግድየለሽነት ፣ ወይም በዘፈቀደ እርማታቸው ላይ ጭማሪዎች ወይም ግድፈቶች በሚያረጉ አንዳንድ ሰዎች ምክንያትም ሊሆን ይችላል።it is a recognized fact that there is much diversity in our copies, whether by the carelessness of certain scribes, or by some culpable rashness in the correction of the text, or by some people making arbitrary additions or omissions in their corrections." ³


🎯 "በአዲስ ኪዳን ውስጥ ካሉ ቃላቶች ይልቅ በእጅ ጽሑፎች መካከል ያሉ ልዩነቶች ይበዛሉ።"There are more variations among our manuscripts than there are words in the New testament.” ⁴


🎯 "ብዙ የእጅ ጽሑፎች እንዳለውኑ የተለያዩ የጽሑፍ ዓይነቶችም አሉ።"There are almost as many forms of text as there are manuscripts.” ⁵


🎯 "ሁሉም መናፍቃን ማለት ይቻላል የቅዱሳት መጻሕፍትን በርዘዋል ተብለው ተከሰው ነበር።"Nearly all the heretics were in turn acccused of falsifying the scripture.” ⁶


🎯 “የኦርቶዶክስ ጸሐፍት የአዲስ ኪዳንን ጽሑፍ ለግል ዓላማ ብለው የቀየሩበት መሠረታዊ ተሲስ በእርግጥ እውነት ነው። በመቶዎች በሚቆጠሩ ቦታዎች የዚህን ማስረጃ ማየት እንችላለን።"basic thesis that orthodox scribes have altered the New Testament text for their own purposes is one that is certainly true. We can see evidence of this in hundreds of places.” ⁷


🎯 ክሬግ ኤል ብሎምበርግ እንዲህ ሲል ያትታል:- በግልፅ ለመናገር ወንጌላት ስም አልባ ጸሐፊዎቻቸው የማይታወቁ እንደሆኑ መቀበል አስፈላጊ ነው።"Craig L. Blomberg, who stated: “It’s important to acknowledge that strictly speaking, the gospels are anonymous.” ⁸


🎯 "ስለ ኤፌሶንም በተመለከተ '80 በመቶ ወሳኝ የሆኑ ሊቃውንቶች' (ጸሐፊው) ስሙ የውሸት እንደሆነ ይቆጥሩታል።"and regarding Ephesians 'about 80 percent of critical scholarship' considers it to be pseudonymous." ⁹


🎯“የቆላስይስ መጽሐፍ በተመለከተ ፣ '60 በመቶ ወሳኝ የሆኑ ሊቃውንቶች' (ጸሐፊው) ስሙ የውሸት እንደሆነ ያምናሉ።"Regarding the book of Colossians, Brown says that 'about 60 percent of critical scholarship' deem it to be pseudonymous." ¹°
❤1
🎯 “እንደ ሬይመንድ ብራውን ገለፃ ፣ 'ከ 80 እስከ 90 በመቶ የሆኑ ሊቃውንቶች' ቲቶስ ፣ 1ኛ እና 2ኛ ጢሞቴዎስ (ጸሓፊያን) ስም የውሸት እንደተጠቀሙ ያምናሉ።"According to Raymond Brown, '80 to 90 percent of critical scholarship' deem Titus, 1 and 2 Timothy to be pseudonymous." ¹¹

🎯“ የ 2ኛ ተሰሎንቄ መልዕክት በተመለከተ ሬይመንድ ብራውን እንዲህ ይላል:- ሊቃውንቶች ጳውሎስ እንደ ፃፈው እኩል ተከፋፍለዋል(ተለያይተዋል)።"II Thessalonians. Raymond Brown states: Scholars are almost evenly divided on whether Paul wrote it,"¹²


ማጣቀሻ 📌


¹ 📒 Gordon D. Fee, “Modern Textual Criticism and the Revival of the Textus Receptus," in Journal of the Evangelical Theological Society 21:1, March 1978, p.23.

² 📒 Kim Haines-Eitzen, Guardians of Letters: Literacy, Power, and the Transmitters of Early Christian Literature, New York: Oxford University, 2000, p. 112.

³ 📒 Origen, Comm. Matt. 15.14.

⁴ 📒 Bart Ehrman, Misquoting Jesus, p.90.

⁵ 📒 Jerome, Ep. Praef. Evang., to Damasus.

⁶ 📒 Eberhard Nestle, introduction to the Textual Criticism Of The Greek New testament, P. 197.

⁷ 📒 Revisiting the Corruption of the New Testament: Manuscript, Patristic, and Apocryphal Evidence ., by Daniel B. Wallace ., pg 43.

⁸ 📒 The Case for Christ (Strobel, Lee) p. 23

⁹ 📒 New Testament Introduction, p. 621

¹° 📒 New Testament Introduction, p. 600

¹¹ 📒 Raymond E. Brown, An Introduction To The New Testament, 1997, Doubleday, p. 639, 654, 673.

¹² 📒 Brown, New Testament Introduction, p. 591
♦️ፎቶ  የሚያስከትለዉ ጣጣና መዘዙ❗️

የራስን የምስትን የልጆችን ፎቶ በአልበም በስልክ ማስቀመጥ እንዲሁም ይባስ ብሎ ሚዲያ ለይ መልቀቁ ከአኼራው ቅጣት በፊት ዱንያ ለይ ብዙ ጣጣዎችን ያስከትላል።ይህ የአንዷን ፎቶ ድግምት ሰሪ ዘንድ በመውሰድ እንዴት ሲህር እንደሰሩባት ተመልከቱ።

▪️ብዙ እህቶቻችን ሚዲያ ላይ በሚለቁት ፎቶ ሰበብ ለቡዳ፣ ለአይንናስ፣ ለሲህር፣ ለመስተፋቅርና ለሌላም ከባባድ አደጋዎች በቀላሉ ይጋለጣሉ። ምክንያቱም ድግምት ሰሪዎች ድግምት ለሚያሰራው አካል ድግምት የሚሰራበትን ሰው የሆነ ነገሩ አምጣ ስለሚለው በቀላሉ ፎቶዋን ካገኘ ወስዶ ያንን ይሰጣል። በዚህ ጊዜ በሷ ላይ በቀላሉ ይህንን መስተፋቅር ወይም ሲህር ያሰሩባታል።

▪️በተለይ ፎቶዋን በየ ሚዲያው የምትለቅ ሴት ፎቶውን የሚያይ ሰው ሁሉ ጤነኛ አይደለም ቢባል ማጋነን አይሆንም።የአይን በሽታ ያለበት ሰው ፎቶውን ሲያይ ከማረከውና ካስደነገጠው ወዲያው በአይኑ ይበላታል። እሷ ግን አታውቅም ቆዳዬ ተላጠ፣ አሳከከኝ፣ ልቤ ተጨነቀ፣ ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል፣ ራሴ ሊፈነዳ ደረሰ፣ ሌላም ሌላም እንዲህ እንዲህ ሆንኩ በማለት በህመም ትሰቃያለች።ነገሩ ግን በሚዲያ የለቀቀችው ፎቶ ያመጣባት ጣጣ ሊሆን ይችላል።

▫️እንዲሁም ብዙ ወላጆች የሚያምሩ ልጆቻቸውን ፎቶ በማንሳት እስክሪን ሴቨር ፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግ ሁሉም እንዲመለከታቸው ያደርጋሉ። ስንቱ በአይን እየበላው እዚጋ አመመኝ ብሎ መናገር የማይችለው ምስኪን ልጃቸውን በህመም ያሰቃያሉ።
©️
👌ሴት እህቶችም ወንዶችም አሏህን ፈርታችሁ በተለይም ሴት እህቶቻችን ከዚህ ተግባራችሁ ራቁ አሏህን የሚያስቆጣ በራሳችሁ ላይ ሙሲባ(በላእ) የሚያመጣ ተግባር ነው።

🔀ሁሉም እንዲጠነቀቀው ሼር አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም
👍1
የረመዷንን ሌባ ተጠንቀቁ
➚➚➚➚➚➚➚➚

አንደኛ ሌባ፦ ↙️
      📺 ቴሌቪዥን በድራማና ቆሻሻ በሆነ ፕሮግራም ምክንያት የሰዎችን ፆም የሚያበላሽ አጅራቸውንም የሚቀንስ አደገኛ ሌባ ነው ቲቪ እንቅልፍ ከመተኛት ጭምር የሚከለክል አደገኛ ሌባ ነው!!!

ሁለተኛው ሌባ፦ ↙️
      🏢 የሱቅ ቦታ፦
ያለ ምንም ገደብ ገንዘብንና ወቅትን ለየት ባለ ሁኔታ የሚያባክን ሲሆን ይህን ለመቆጣጠር ከመሄድህ በፊት አስብበት ተጠንቀቅ!!!

ሶስተኛ ሌባ፦↙️
  👁 አለመተኛት፦ ውድ ግዜህን የሚነጥቅ በመጨረሻው አንድ ሶስተኛ ሌሊት ላይ ከተሀጁድ ከስቲግፋር የሚከለክል ከባድ ሌባ ነውና በአግባቡ ማስተዋል ያስፈልጋል።

አራተኛ ሌባ፦ ↙️
         🍱 ኩሽና፦
በተለይ ሴቶች!!! ረጅም ግዜ የተለያዩ ምግቦችን በማዘጋጀት ግዜያቸውን በኩሽና ውስጥ የሚጨርሱ አሉ! ደግሞኮ አይበሉትም ቀመስ ቀመስ አድርገው ብዙውን ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ይጨምሩታል!!! (እህቴ ሆይ!!! ረመዷንን የተለያዩ ምግቦችን በማዘጋጀት ግዜሽን አትፍጂ ይህን ስልሽ ጭራሽ ምግብ አትስሪ ማለቴ አይደለም!!! መቼም ግልፅ ነውና ሚዛናዊ ሁኚ ለማለት ነው። ፀሀፊው))

አምስተኛ ሌባ፦ ↙️
          📲 ስልክ፦ ለረጅም ግዜ ወሬ ማብዛት!!! በዛ ላይ ህሜቱ፣ ነገር ማዋሰዱ፣ አለተባለ እያሉ ግዜን መግደልና ሚስጥርን ማባከን እንዲሁም ብዙ የሚታዩ አልባሌ ነገሮችንም አቅፏል። ((አላህ ይድረስልን))

ስድስተኛ ሌባ፦ ↙️
          💵 ስስት፦
የሶደቃን አጅር የሚከለክል በተለይ የረመዷንን ወር ሶደቃ የሚከለክል ሌባ ነው።

ሰባተኛ ሌባ፦
   🌴 አላህ የማይወሳበት መጅሊስ፦ ያ ! የቂያማ ቀን በሰውየው ላይ ፀፀት የሚሆን አደገኛ ሌባ!!!

በመጨረሻም፦ ➘ ትልቁ ሌባ
      🌐 የመገናኛ ቡዙኃኖች፦
አላህን የሚያስወድድ ስራ ካልተሰራበት አደገኛ የረመዷን ሌባ!!!

አደራ ፍጠኑ! አደራ ፍጠኑ!! ያሉት ቀናቶች በጣም ትንሾች ናቸው። አላህ በሚወደው ስራ የምንጠቀምበት ወር ያድርግልን !!✍✍
👉   የፆመኛ ዱዓእ ✍

     የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም –
" ለፆመኛ ሰው ተቀባይነት ያለው ዱዓእ አለው " ብለዋል ።
   በመሆኑም አንድ ፆመኛ የሆነ ሰው ፀሀይ ከመግባቷ በፊት አፍጥር ሊቃረብ ሲል የሚያደርገው ዱዓእ መቅቡል ስለሆነ ልንዘናጋ አይገባም።ብዙ የተለያየ ሀጃ ያለባችሁ ወንድምና እህቶች በተለይ ከእዳ ጋር፣ከርዝቅ ማጣት ጋር የተያያዘ ሀጃ ያለባችሁ ስንቱ ፊት ቆማችኋል ? እስኪ ይህን አጋጣሚ ተጠቅማችሁ ለሁሉም እንደየፍላጎቱ ሰጥቶ አሁንም ቢጠይቁት የሚወደውን አምላካችሁን ደጅ አንኳኩ።የሰዎች ፊት ከመቆም ከጌታችሁ ፊት ቁሙ ያ አላህ በሉት።በናንተና በአምላካችሁ መካከል ያለውን ወንጀል ያመጣውን ርቀት ከመጝሪብ በፊት ቀደም ብላችሁ መስጂድ ገብታችሁ ኢስቲጝፋር በማድረግና የሱን ቃል በማንበብ አጥብባችሁ ለምኑት።ተዘግቶ የማያውቀውን የራሕመቱ ደጃፍ ቆማችሁ በዱዓእ በር ግቡ።
 
በዱንያ ላይ ሁሉም የተለያየ ሃጃ አለው።ሁሉንም አንድ የሚያደርገው የአኼራ ሃጃ አለና ሁላችንም የጭንቁን ቀን ከሚያልፉት ባሮቹ እንዲያደርገን አላህን እንማፀነው።ሰዓቱን አስቡት ልባችን ፍፁም ወደ አላህ እያሰበ አዕምሯችን ከሁሉ ነገር ነፃ ሆኖ በረሃብ በተሰባበረ አካል ያ አላህ ስንል ምን ግርዶ ይኖራል ? ለዚህ ነው መልእክተኛው በዛን ሰዓት ለፆመኛ ተቀባይነት ያለው ዱዓእ አለው ያሉት።

ثبت  في سنن أبي داوود من حديث عبد الله بن عمر رضي الله عنهما قال: كان رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا أفطر قال: ذهب الظمأ وابتلت العروق وثبت الأجر إن شاء الله. وحسنه الشيخ الألباني. 

ሌላው ዘሀበ አዝዘመኡ ( ጥሙ ተወገደ) ወብተለቲል ዑሩቁ ( ስሮች ረጠቡ) ወሰበተል አጅሩ ( አጅሩም ተረጋገጠ) የሚለው ዱዓእ በተምር ወይም በውሃ ካፈጠርን በኋላ ነው ማድረግ ያለብን ። የተለመደውና ብዙዎች የሚያደርጉት ሊያፈጥሩ ሲሉ ነው ይህ ከሐዲሱ መቅሰድ ጋር ይጋጫል።ምክንያቱም ሳያፈጥር ከሆነ መባል የነበረበት ጥሙ ሊወገድ ነው ፣ ስሮች ሊረጥቡ ነው ፣ አጅሩ ሊረጋገጥ ነው ነበር ‼ የአላህ መልእክተኛ ስለሆነና  ስለተረጋገጠ ነገር ነው የነገሩን ይህ ደግሞ ካፈጠርን በኋላ ነው እንጂ አይሆንም።ካፈጠርን በኋላ ሲባል ጠግበን ከበላን በኋላ ማለት አይደለም። አንድ ጊዜ እንደተገነጨን ወይም አንድ ተምር እንደበላን ማድረግ እንችላለን ። ይህ ማለት እያፈጠርን እያለን ማለት ነው። አላህ ከተጠቃሚዮች ያድርገን።✍
መቼም ቢሆን ባዶነት ኪሳራ ነው‼️በህይወት ዘመናችሁ ማንም በከንቱ እንደዋዛ እንዲጫወታችሁ አትፍቀዱ

TIPS✍✍
➦ከላይ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት አንድ ሰው በትከሻው የተሸከመው ከረጢት ነገር ላይ "اجر الصيام" (የጾም ምንዳ/ዋጋ) የሚል ጽሁፍ አለበት።

➦ነገር ግን ከረጢቱ ተቀድዶ የያዘው እህል (ምንዳው) እየፈሰሰ እንደሆነ ያሳያል።
​ቀዳዳዎቹ ላይ የተጻፉት ቃላት የጾምን ዋጋ የሚያሳጡ ወይም የሚያጠፉ ተግባራትን እንዲህ በማለት ይገልጻሉ:▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
​مسلسلات (ሙሰልሰላት)፦ ጊዜን በከንቱ የሚያባክኑ ተከታታይ ድራማዎች።
​غيبة (ጊባ)፦ ሰውን በሌለበት ማማት።
​علاقات محرمة (አላቃቱ አል ሙሐረመህ)፦ የተከለከሉ (ሀራም) ግንኙነቶች።
​نميمة (ነሚማ)፦ ነገር ማዋሰድ ወይም በሰዎች መካከል ጠብን ለመጫር ወሬ ማመላለስ።
​تأخير الصلاة (ተእኺር አስ-ሰላህ)፦ ሶላትን በወቅቱ አለመስገድ (ማዘግየት)።
​تبرج (ተበሩጅ)፦ አለባበስንና ውበትን ለባእድ ሰዎች ማሳየት።
​اغاني (አጋኒ)፦ ዘፈኖችን ማዳመጥ።

➦​ዋናው መልዕክቱ፡▼▼▼▼▼▼
​አንድ ሰው ቀኑን ሙሉ ተርቦና ተጠምቶ ሊጾም ይችላል፤ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱትን ስህተቶች የሚሰራ ከሆነ፣ የጾሙን ዋጋ (ምንዳ) ልክ እንደተቀደደ ከረጢት እያፈሰሰው እንደሆነና መጨረሻ ላይ ባዶ እጁን ሊቀር እንደሚችል ለማስጠንቀቅ ነው።
​ስለዚህ ምስሉ "ጾምህ ሆድህን ብቻ ሳይሆን ምላስህን፣ አይንህንና ጆሮህንም ይሁን" የሚል ምክር ይዟል።✍️
📌ውዝግቡ ስድቡ ና ተቃውሞው አሁንም ቀጥሏል¡