የሀቅ አድማስ Official apologetics 🔰
557 subscribers
223 photos
79 videos
27 files
102 links
▣የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ ና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ።(እርሷም) አሏህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣በርሱም ምንንም ማንንም ላናጋራ፣ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤በላቸው፡፡እምቢ ቢሉም፦እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡"[📚ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን:64]

🔥"እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙ"[📚ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን:102]!🔥
Download Telegram
▣ማርቲን ሉተር

➲ማርቲን ሉተር እንዲህ  አለ«እየሱስ(ክርስቶስ) ከጉድጓድ አጠገብ ከነበረችው ሴት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ አመንዝሮ ነበር፤ምክንያቱም ደግሞ [በዮሐንስ 4፥27] ከእርሷ ጋር ምን እያደረገ እንደሆነ ማንም አያውቅም’ ተብሎ ነበርና።እንደገናም ከመግደላዊት ማርያም ጋርም አመንዝሮ ነበር፤እንዲሁም [በዮሐንስ 8÷2–11] ከተጠቀሰችው አመንዝራ ሴት ጋርም አመንዝሯል፣እርሷንም በቀላሉ ነጻ አወጣት።ስለዚህም መልካሙ ክርስቶስ ከመሞቱ(ከህልፈቱ) በፊት አመንዝራ መሆን ነበረበትና።»

[📚Table talk ቅጽ 54 ገጽ 154]

➦ወረድ ብሎ እዛው መፅሐፍ ላይ በሕዳግ ማስታወሻ ላይ እንዲህ የሚል ነገር እናገኛለን▼▼▼▼▼▼▼▼▼

“ማርቲን ሉተር እንዳረጋገጠው(እንደገለጸው) ከሆነ፣ክርስቶስ በዓለም ሰዎች ውስጥ ሆዳም(በልቶ የማይጠግብ)፣የወይን ጠጅ የሚጠጣ፣እንዲያውም አመንዝራ ተብሎ ይወቀስ ነበር።”

[📚Table talk ቅጽ 54 ገጽ 154]

➦እንዲህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ የክርስቲያን Pseudo-apologistቶች ይህንን ንግግር ሉተር አልተናገራም ተማሪዎቹ ናቸው ስሉ ይደመጣሉ! ያም ሆነ ይህ John Schlaginhaufen የሉተር የቅርብ ተማሪና ፓስተር(ቄስ) እንዲሁም Table talkን በመሰብሰብና በመመዝገብ የሚታወቅ እንደሆነ ይታመናል!
➦So እዚህ ጋ ልሰመርበት የሚገባው ነገር John Schlaginhaufen ከመሬት ተነስቶ እንዲህ ልል አይችልም! Coz most of the time ተማሪ ከመምህሩ የተማረውን ነውና የሚያንጸባርቀው!

➦Btw እየሱስ(ኢሳ ዐለይሂ ሰላም)  ከእንደዚህ አይነት ቆሻሻ ንግግር የጸዳና የጠራ ነቢይ እንደሆነ እኛ ሙስሊሞች እናምናለን🔥

➥◈የቴሌግራም ቻናላችን||
https://t.me/Rightpathstudent

ሁላችሁም ጆይን በሉ ሼር ይደረግ!

➲አሏህ ሂዳያ ይስጣቸው🔥
❤1
የሀቅ አድማስ Official apologetics 🔰
Photo
▣Flavius Josephusና የስቅለት ቅሰጣ!

➦ብዙ ጊዜ ክርስቲያን ወገኖቻችን ስቅለትን በተመለከተ ከታሪክ አንፃር ከሚደገፉባቸው የታሪክ ፀሃፊያን መካካል የሮማውያን የታሪክ ፀሃፊ የሆነው ታሲተስ(Tacitus)ና የአይሁዳውያን የታሪክ ፀሃፊ ፍላቪየስ ጆሴፈስ(Flavius Josephus) ተጠቃሽ ናቸው!

➦ሆኖም ግን ከምሁራን እይታ አንፃር አንዳንድ የተዋሹ ነገሮችን እንደሚከተለው እንመልከት እስቲ

➲ይህንንም በተመለከተ በ1859 ተወልዶ በ1934 አካባቢ የሞተው ታዋቂ Theologian ሊቅ ወይም ምሁር የነበረ OSCAR HOLTZMANN እንዲህ በማለት በግልጽ ይናገራል
▼▼▼▽▼▼▽▼▼▽▼▼

“በመሆኑም፣ለጆሴፈስ (Flavius Josephus) በመስጠት የቀረበው ይህ ክፍል ያለምንም ጥርጥር የሐሰት(spurious or fabricated) ጽሑፍ ነው።በውስጡም ከራሱ ጽሑፍ ጋር የሚጣረስ ተፈጥሯዊ ተቃርኖ ስለሌለ ከጠቅላላው ሐሰተኛ ጽሑፍ ውስጥ እውነተኛ የሆነ ክፍልን ለይቶ ለማውጣት መሞከር ፍጹም ያልተመሠረተ ግምት ነው።

ከዚህ በተቃራኒው፣አሁን ያለን ጽሑፍ በኋለኛ ዘመን ለክርስቲያኖች በሚስማማ መልኩ በሌላ ፅሑፍ በምትክ የገባ መሆኑን መቀበል ግድ ይለናል።ይህ አይነት መተካት የተካሄደበትና የተከሰተበት ጊዜ ደግሞ ያለምንም ጥርጥር በኦሪገን(Origen) እና በአውሳቢየስ(Eusebius) መካከል ባለው ዘመን ነበር።

በዚህን ጊዜ ሥልጣን ለመያዝ  እየታገለችና ጥረት ስታደርግ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን፣በሰፊው የሚነበብና በብዙ መንገድ ለእርሷ ጠቃሚ የነበረውን ድርሰት(ጽሑፍ) አውሳቢየስን በመጠቀም፣ለእርሷ አስጸያፊ ሆኖ የታየውን አንድ ክፍል ከጽሑፉ አስወግዳ፣ለእርሷ በሚመቻት መልኩ በእርሷ አመለካከት እርሷን የማይቃወም ሌላ ጽሑፍ በምትኩ አስገባች(ተካች)።”

[📚THE LIFE OF JESUS PAGE 16]

➲እንዲሁም ታዋቂ ከሚባሉ ምሁራን መካካል
➛DR.H.OORT
➛DR.I.HOOYKAAS
➛DR.A.KUENEN
እንዲህ በማለት ይናገራሉ

▼▼▽▼▼▽▼▽▼▼

➦“ፍላቪየስ ጆሴፈስ(Flavius Josephus)፣በአይሁዳውያን ሕዝብ ዘንድ በጣም የሚታወቅ የታሪክ ፀሃፊ የሆነው፣ከክርስቶስ ውልደት(ልደት) በኋላ በ37 A.D፣ከኢየሱስ ህልፈት ከሁለት ዓመት በኋላ ተወለደ።ሆኖም ግን ሥራው ኢየሱስና ሐዋርያቱ በተነሱበት(በተገለጡበት) ዘመን ሁኔታዎች ላይ እንደ ዋና ምንጭ ሆኖ እጅግ የማይተመን ዋጋ ቢኖረውም፣ኢየሱስን ግን እራሱን እንደጠቀሰው አይታይም።ያም ሆነ ይህ፣በ“አይሁድ ጥንታዊ ታሪኮች”(Jewish Antiquities) በሚለው ውስጥ እርሱን የሚመለከተው ክፍል በእርግጥ ሐሰተኛ(spurious) የሆነ ነው፣እና በኋላ በነበረ ክርስቲያናዊ እጅ ወይም ጸሐፊ የተጨመረ ነው።”

[📚BIBLE FOR LEARNERS PAGE 27]

➦ከስቅለት ጋር ተያይዞ ለሚነሳው ነገር ማንም ምን ይበል እኛ ሙስሊሞች እየሱስ(ኢሳ ዐለይሂ ሰላም) አልሞተም አልተሰቀለም ብለን እናምናለን!

➦ዳሩ ግን ሳይሞት ሳይሰቀል አምላካችን አሏህ ከጠላቶቹ እጅ አድኖ ወደ ሰማይ ከፍ አድርጓል ብለን እናምናለን! በዕለተ ትንሳኤ ቀን(በቂያማ ቀን) ተመልሶ እንደሚመጣም ሳንጠራጠር እናምናለን!

➦እናም እንደማንኛውም ሰው ከዚህ በፊት ሞትን ስላልቀመሰ ለተወሰነ ጊዜ በእስልምና ሸሪዓ ላይ ቆይቶ ይሞታል ይቀበራል።

➲ይህንንም እውነታ ለመረዳት ቀለል ባለ መልኩ ከቁርዓንና ከባይብል በማስረጃ እንደሚከተለው እንመልከት▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼

➻ከቁርዓን

وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا ٱلْمَسِيحَ عِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ ٱللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ لَفِى شَكٍّۢ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِۦ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا ٱتِّبَاعَ ٱلظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًۢا بَل رَّفَعَهُ ٱللَّهُ إِلَيْهِ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًۭا



«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)። አልገደሉትም አልሰቀሉትምም።ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ።እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው።ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም።በእርግጥም አልገደሉትም።ይልቁንስ አላህ (ኢሳን) ወደርሱ አነሳው።አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡

[📚ሱረቱ አንኒሳዕ: 157-158]

إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَىَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَجَاعِلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوكَ فَوْقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ ۖ ثُمَّ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ
አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፡፡ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡

[📚ሱረቱ ኣሊ ኢምራን:55]

➻ከባይብል

መዝሙር 91
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
¹² እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
¹³ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
¹⁴ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።
¹⁵ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
¹⁶ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።

➦ይህ ጥቅስ ደግሞ prophecyው ለእየሱስ እንደሆነ በማቴ 4÷6ና ሉቃስ 4÷9-11 ላይ Quote ተደርጓል!

ዮሐንስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³³ ኢየሱስም፦ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ ወደ ላከኝም እሄዳለሁ።
³⁴ ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም አለ።

ማርቆስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁵ ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በምድርም ወድቆ፥ ይቻልስ ቢሆን ሰዓቲቱ ከእርሱ እንድታልፍ ጸለየና፦
³⁶ አባ አባት ሆይ፥ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ
፤ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ።

“ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።”
— ማቴዎስ 26፥39

“እርሱም(እየሱስም) በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤”
— ዕብራውያን 5፥7

➲ስለዚህ ክርስቲያኖች ሆይ በሰከነ መልኩ የመረጃና የማስረጃ ምንጮቻችሁን በማጣራት እውነተኛውን መንገድ እንዲትይዙ Recommend ለማድረግ እንወዳለን🔥

➥◈የቴሌግራም ቻናላችን||
https://t.me/Rightpathstudent

ሁላችሁም ጆይን በሉ ሼር ይደረግ!
▣ሰይጣንን(ዲያብሎስን) በፈስ ማባረር ይቻላል እንዴ ጎበዝ🤭¿

➦ማርቲን ሉተር እንዲህ አለ
▼▽▼▽▼▽▼▽▼▽▼▽
«እንዲህ መሆኑን ባውቅም፣በቀን ውስጥ አሥር ጊዜ ያህል ሀሳቤ(አዕምሮዬ) ይለወጣል ይቀየራል ወይም የተለየ አስተሳሰብ ይኖረኛል።ነገር ግን ዲያብሎስን(ሰይጣንን) እቃወማለሁ፤ እናም ብዙ ጊዜ በፈስ እንኳ አባርረዋለሁ።እሱም(ሰይጣንም) በጥቃቅን ኃጢአቶች ሲፈትነኝ፣ዲያብሎስ ሆይ፣ትናንትም ፈስ አውጥቼ አስፈታሁ እለዋለሁ።»

[📚Table Talk Vol 54 page 16]

◈የቴሌግራም ቻናላችን||
https://t.me/Rightpathstudent

ሁላችሁም ጆይን በሉ ሼር ይደረግ!
😁4
እኛ ሙስሊሞች ነን ጳጉሜ ብድዓ(መጤ) ናት ክርስቲያኖች🔥ሰምታችኋል!
❒ ነብዩሏህ ሁድ ዐለይሂ ሰላም ❒

ክፍል አንድ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኑህ ዐ ሰ እና በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ከሞቱ በኋላ አንዱ አንዱን ሲተካ ምድር ዳግም በሰዎች ትሞላ ጀመር።

ያ ዘመን ካለፈ በኋላ የነበሩ ህዝቦችም ማንም አምልኮ ከምያውቀው በላይ ጣኦትን ማምለክ ተያያዙት።የህዝቡ መለያ ስማቸውም (ዓድ) ይባላል።

በመጀመርያ የዓድን ህዝቦች ላስተዋውቃችሁ...
የዓድ ህዝቦች በዐረቢያ ምድር በየመን ግዛት አህቃፍ በሚባል አካባቢ ኢረም በተባለች ከተማ የሚኖሩ በጣም ትላልቅ ቁመና ያላቸው ህዝቦች ሲሆኑ፤አላህ ስፍር ቁጥር የሌለውን የፀጋ አይነት ያትረፈረፈባቸው ህዝቦች ናቸው።

ሰውነታቸውም በጣም ግዙፎች እና ረጃጅሞችም ነበሩ።
ከሰውነታቸው መግዘፍ የተነሳ አንድን የቴምር ዘንባባ በሁለት ጣታቸው ይነቅሉ ነበር።(የተምር ዛፎች ምን ያህል ግዙፍ እንደሆኑ ዐረብ ሀገር ያላችሁ ውዶች ታውቁታላችሁ)

ነገር ግን አላህ ለዋለላቸው እንዲህ አይነት ኒዕማ ምላሻቸው ምስጋና ሳይሆን ድንበር ያለፈ አመፅ እና መኩራራት ነበር።

የኑህ ህዝቦች ያደርጉት የነበረውን የጣኦት አምልኮ አሟሙቀው ጀመሩት።ያም አላንስ ብሏቸው ምድርን በተለያዩ የወንጀል አይነቶች ይሞሏትም ጀመር።

ነገር ግን ለቅጣት የማይቸኩለው አላህ በእዝነት አዘል ጥበቡ ከመጥፎ ከልክሎ ወደ መልካም የሚመራቸውን (ሁድ) የተባለውን መልዕክተኛ ከመሀከላቸው ላከላቸው።


ሁድ ዐ ሰ መልካም፣ቁጥብ፣የተረጋጉ እና አንደበተ ርቱዕ እና ዐረብኛ ቋንቋን ለመጀመርያ ግዜ የተናገሩ ሰው ናቸው።አላህም እሳቸውን ወደ ህዝባቸው በመሄድ የጌታቸውን ተልዕኮ እንዲያደርሱ አዘዛቸው።

ሁድ'ም ዐ ሰ የጌታቸውን ትዕዛዝ በመቀበል ወደ ዝባቸው ሄደው፦"እኔ ከጌታችሁ የተላክሁ ነብይ ስሆን፤በዚህ አለምም አላህ የሚባል ጌታ አላ።ከሱ ሌላ አምላክ የለም እነዚህ ከተለያዩ ድንጋይ እና እንጨት ጠርባችሁ ምታመልኳቸው ጣኦታት መጥቀምም መጉዳትም የማይችሉ ደካማ ሲሆኑ ከናንተ ጥበቃን ይሻሉ እንጂ እራሳቸውንም አይጠብቁም።

እኔን የታዘዘኝ ከሞት በኋላ ጀነት ይገባል እኔንም ያስተባበለኝ ጀሀነም መቀመጫው ስትሆን መቀመጫነቷስ ምንኛ ከፋ።" ብለው ማስጠንቀቅ ጀመሩ።

እነሱም ነቢያቸው በሚናገረው ግራ በመጋባት፦"እንዴት ነው አማልክቶቻችንን ትተን አንድን ፈጣሪ ብቻ ምንገዛው!!! ይህ ሰውዬ ምን አይነት ቂልነት ነው ይዞብን የመጣው" ይሉ ነበር።

ሁድ ዐ ሰ ህዝቦቹ የሚያሳዩት የመልስ ምት ለቅፅበት እንኳን ተስፋ አላስቆረጣቸውም ነበር። ይልቁኑ፦"እኔ ከናንተ ዘንድ የፈጣሪያችሁን ጥሪ ለማድረስ ከመሀከላችሁ የተመረጥኩ ስሆን፤የተላክሁበትንም ተልዕኮ ያለመሰላቸት በተደጋጋሚ ወደ እናንተ አደርሳለሁ።

እስቲ ፀሀይን እና ጨረቃን ተመልከቱ...ማን ነው የሚያፈራርቃቸው!!!
ማን ነው'ስ የፈጠራቸው!!!
ምድርንና ሰማይንም ተመልከቱ ማን ነው ምድርን አንጥፎ ሰማይን ያለ መሶሶ ያንጣለለው!!!

ተዉ ህዝቦቼ ጌታችሁን አምልኩት።ተጠንቀቁ እናንተ ከሞታችሁ በኋላ ትቀሰቀሱ'ና በሰራችሁት ትተሳሰባላችሁ።መልካም የሰራ ለነፍሱ ነው መጥፎ የሰራም ከከሳሪዎችም ይሆናል" እያሉ ይጠሯቸው ነበር።

ይህን የነቢያቸውን ጥሪ በሰሙ ግዜ፦"ይህን ሰው ከአማልክቶቻችን አንዱ በመጥፎ ተመልክቶታል(አብዷል)" በማለትም ይተቹት ጀመር።

አንዳንዴም፦"ይሄ ሂሳብ፣ጀነት፣ጀሀነም፣መቀስቀስ....ምናምን ምትለው ምን ማለት ነው?" እያሉም ይከራከሩታል።

https://t.me/Rightpathstudent

ይቀጥላል
🥰1
▣ትኩስ ዜና እናሰማለን!

➲ከሰሞኑ በነበረው debate ላይ ኦሮቶዶክሳውያንና ፕሮቴስታንት ወገንታት ጊዜያዊ ጋብቻ በGift መጋባታቸው ተሰማ😂

➦ከዚያ በኋላ ከጀርባ ሄደው አንተ መናፍቅ፣አንተ እንትን......የሚሉ...ያንተ እየሱስ የኛ እየሱስ አይደለም እያሉ እርስ በእርስ የሚባሉ ሰዎች መሆናቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል 🤭

➦ለጊዜያዊው ፖለቲካዊ ጥቅማ ጥቅማቸው ብለው ከኛ ሙስሊሞች ጋር ውይይት ስኖር ይታረቃሉ ነገ ደግሞ ይፋታሉ ስሉ አዳማጮች ቅሬታቸውን አቅርበዋል🫣

➦የሚገርማችሁ ከክርስቲያን ወገኖቻችን በኩል አሉ ተብለው ከሚጠበቁ Apologist ከሚባሉ ልጆች መካካል ወደ 9 ዓመት በሙሉ Theology ተምሬያለሁ ብሎ ህዝቡ ላይ Game ስጫወት የነበረው ዳንኤል እውነት ለሁሉ ነበርና🫣🫢 ዳሩ ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ውይይቱ ላይ ባልጠበቀው መልኩ ከባባድ የሚሳኤል ድብደባ በመግጠሙ ምክንያት Cooked,debunked ሆኖ መገኘቱ አይዘነጋም!

➦ከዚያም ከጨዋታ ውጪ ሆኖ የአርቲክል አጤረራ ጋዜጠኝነት ሙያ አግኝቶ ዋንጫ መውሰዱ ይታወሳል¡!

➦የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚያሳዩት እንደ እውነታው ከሆነ በኛ በኩል ግሩም በሆነ ሁኔታ በማታው debate ላይ ከባባድ ድሮኖዎችና ሚሳኤሎችን በማዝነብና በማስወንጨፍ በሁሉም አቅጣጫ በጣም ፀዴ የተሳካ ውይይት እንደነበር ይታወሳል🔥

➦በመጨረሻም እኛም ማሻ አሏህ ብለናል ለነሱም አሏህ ሂዳያ ይስጣቸው ስንል በአክብሮት እንማፀናለን🔥
😁7👍2
የሀቅ አድማስ Official apologetics 🔰
❒ ነብዩሏህ ሁድ ዐለይሂ ሰላም ❒ ክፍል አንድ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኑህ ዐ ሰ እና በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ከሞቱ በኋላ አንዱ አንዱን ሲተካ ምድር ዳግም በሰዎች ትሞላ ጀመር። ያ ዘመን ካለፈ በኋላ የነበሩ ህዝቦችም ማንም አምልኮ ከምያውቀው በላይ ጣኦትን ማምለክ ተያያዙት።የህዝቡ መለያ ስማቸውም (ዓድ) ይባላል። በመጀመርያ የዓድን ህዝቦች ላስተዋውቃችሁ... የዓድ ህዝቦች በዐረቢያ…
❒ ነብዩሏህ ሁድ ዐለይሂ ሰላም ❒

     ክፍል ሁለት

   የዓድ ህዝቦችም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፡፡ «ከእኛ ይበልጥ በኀይል ብርቱ ማን ነው?» አሉም፡፡ ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኀይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መኾኑን አያዩምን? በተዓምራታችንም ይክዱ ነበሩ። (ሱረቱል ፉሲለት)
ሁድ ዐ ሰ የህዝቡ ሁኔታ ተስፋ ሲያስቆርጠው፦"እናንተ ከምትሰሩት ሁሉ እኔ ነፃ መሆኔን ምስካሪ ሁኑ" እያለ የሱን ጥሪ ባለመቀበላቸው በዱንያ የሚወርድባቸውንም ቅጣት ያበስራቸውም ጀመር።
እነሱም፦"ምንድነው ዝም ብለህ ቅጣት ቅጣት...እያልክ ምታስፈራራን!!! እንደውም እስቲ ቅጣት ምትለውን አምጣው" እያሉ ሲያሾፉ
ሁድም ዐ ሰ፦"ይህ የማስጠንቅቃችሁ ቅጣት በናንተ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል። አትጠራጠሩ" አሏቸው። በመጨረሻም ሁድ ዐ ሰ በህዝባቸው ላይ ዱዓ ማድረግ ጀመሩ።
ከዚያም አላህ የቅጣቱን አርጩሜ በህዝቡ ላይ ሊያወርድ መጀመርያ ለረጅም አመታት ዝናብ በማቋረጥ ምድሪቱን አድርቆ እንስሳቶቻቸውን አጠፋባቸው።
ሁድም ዐ ሰ፦"ከዚህ ሁሉ እንግልት ሊያድናችሁ እሚችለው በጌታችሁ ማመን ብቻ ነው" አላቸው።
እነሱም፦"በረሀብ እና በጥማት እንሞታታለን እንጂ ከጣኦቶቻችን ሌላ ማንንም አንለምንም" በማለት ጣኦታት ዘንድ እየሄዱ ኡኡኡ... ይሉ ጀመር።
ጣኦቶቻቸው ዘንድ ሄደው እሪ ብለው ሲወጡ ሰማይን በደመና ተሞልቶ አገኙት።በጣምም ተደሰቱ አማልክቱ ፀሎቶቻቸውንም እንደሰሙ አመኑ ጥሩ ዝናብ ሊዘንብልን ነው በማለትም ተመፃደቁ።
ያን ግዜ ሁድ ዐ ሰ፦"ይህ እኮ አምጣልን ያላችሁት የቅጣት ደመና ነው እንጂ እናንተ እንደምትሉት ዝናብ አይደለም" አላቸው።
ከዚያም ከፍተኛ ጉልበት የለው ንፋስ ከተማቸውን ያናውጥላቸው ጀመር።ቀስ በቀስ ንፋሱ አስፈሪ ድምፅን እየቀላቀለ በክፍተኛ ጩሀት ህዝቡን ወደ ሰማይ ማፈናጠር ጀመረ።
ለ7 ሌሊትና ለ8 ተከታታይ ቀናት ያህል ንፋሱ ዘለቀ። በነዚያ የቅጣት ቀናት ሰውም እንስሳትም ምንም አይነት ፍጥረት አልቀረም ነበር።በሁድ ዐ ሰ ያመኑት ምዕመናን ሲቀሩ ሁሉም የመቅሰፍቱ ሰለባ ሆኑ.....

አሏህ ሱበሃነሁ ወተዓላ ነቢዩሏህ ሁድን ዐ ሰ እና ከሱጋ ያመኑት አዳነቸው፡፡ 

          •••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿•••
❒ የነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ ❒
          •••✿❒  ይቀጥላል❒✿•••
🥰2
▣በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

➲ኢብኑ ተይሚያን ሙስሊም ነን የሚሉ በርካታ ጭፍራዎች "ካፊር ነው" እና መሰል ትችቶችን እያቀረቡ እሱን ለማዋረድ ጥረት እያደረጉ ባለበት ተጨባጭ የምዕራባውያን ምሁራኖች እና ታላላቅ የአካዳሚክ ተቋማት ስለ ኢብኑ ተይሚያህ ጥናት እያካሄዱ ነው።

➦አዎ ኢብኑ ተይሚያህ ለዓለም ህዝብ የሚጠቅሙ ስራዎች አሉትና ሊጠና ሊመረመር እንዲሁም ደረጃው ሊታወቅ ይገባል።!

➦የዘመናዊ አካዳሚክ ምሁራን ኢብኑ ተይሚያህን እንደ “የሰለፍያ ምሁር” ብቻ ሳይሆን የመካከለኛው ዘመን ታሪክ የተለያዩ ዘርፎች ምሁር አድርገው ያጠኑታል።ከነዚህ የምዕራቡ ዓለም 🌍 ምሁራን መካከል
▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼

1) Jon Hoover — ጆን ሁቨር

➦በዘመኑ ከኢብኑ ተይሚያህ ጥናት ጋር በጣም የተያያዘ ምሁር ነው።

➻ዋና ዋና የጥናት መስኮቹ
▼▼▼▼▼▼▼▼▼
የኢብኑ ተይሚያህ የዐቂዳ አስተሳሰብ
➛የአሏህ ባህሪያት
ምክንያትና ወሕይ
➛የኢብኑ ተይሚያህ ሥራዎች የእጅ ጽሑፍ ምንጮች የኢብኑ ተይሚያህ ቅርስ
➛በተጨማሪም የኢብኑ ተይሚያህ የአረብኛ የእጅ ጽሑፎችንና የታተሙ እትሞችን ለምርምር የሚጠቅም ሰፊ መመሪያ አዘጋጅቷል።

2) Carl Sharif El-Tobgui — ካርል ሻሪፍ ኤል-ቶብጊ

በተለይ درء تعارض العقل والنقل
በተሰኘው የኢብኑ ተይሚያህ ኪታብ ላይ ጥልቅ ጥናት አድርጓል። ይህ የሸይኹል ኢስላም ኪታብ አቅል ማለትም አእምሮ እና ቁርኣን ወይም አድስ ይጋጫሉን የሚለውን ጉዳይ የዘረዘረበት ነው።

ይህ ምሁር Ibn Taymiyya on Reason and Revelation በማለት ሰፊ ጥናት አስቀምጧል።

3) Yossef Rapoport — ዮሴፍ ራፖፖርት

በኢብኑ ተይሚያህ የፊቅህና የሕግ አስተሳሰብ ላይ ጥናት አድርጓል።

4) Shahab Ahmed — ሻሃብ አህመድ
ከRapoport ጋር በመሆን Ibn Taymiyya and His Times የተባለውን መጽሐፍ አዘጋጅቷል።

ይህ መጽሐፍ ከተለያዩ ምሁራን የተሰበሰቡ ጥናቶችን ይዟል፤ ዐቂዳ፣ ተፍሲር፣ ፊቅህ፣ ሺዓ–ሱኒ ውይይት፣ ክርስትና ጋር ያለው ክርክርና የኢብኑ ተይሚያህ ተፅእኖ ይዳስሳል።

5) Caterina Bori — ካተሪና ቦሪ

የኢብኑ ተይሚያህን የሕይወት ታሪክ፣ ተማሪዎቹንና የእርሱን ምሁራዊ ጥበብ አጥንታለች።

6) Yahya Michot — ያሕያ ሚሾ

ኢብኑ ተይሚያህን በተለይ በፖለቲካ፣ በጂሃድ ፋታዋዎችና በዘመናዊ እንቅስቃሴዎች የተጠቀሰበት መንገድ ላይ አጥንቷል። የኢብኑ ተይሚያህን ጽሑፎች ከኋለኛው ዘመን የጽንፈኝነት ትርጓሜዎች መለየት እንዳለበት ያስረዳል።


14) Rachael Omari

የኢብኑ ተይሚያህን በሱና ዙሪያ ያለውን እይታ "Theology of the Sunna" በሚል ያጠናች ሲሆን በተጨማሪም ከአአሻኢራዎች ጋር ያለውን የክርክር ታሪክ አጥንታለች።

15) David Thomas
በኢብኑ ተይሚያህ ከክርስትና ጋር ያደረገውን የክርክር ሥራ፣ በተለይ
الجواب الصحيح لمن بدل دين المسيح
የተሰኘው ኪታብ ላይ ጥናት አድርጓል።

♻️ አሁን ያሉ በጣም አዳዲስ ጥናቶች

● Mehdi Berriah — መህዲ በሪያህ
   እና
● Arjan Post — አርጃን ፖስት

➹ እነዚህ ሁለቱ በ2026 አንድ አዲስ እና ክፍት የሆነ የአካዳሚክ መጽሐፍ አዘጋጅተዋል፦
Ibn Taymiyya’s Thought: Corpus, Reception, and Legacy
ይህ በLeuven University Press የታተመ 282 ገጽ ያለው መጽሐፍ ነው። የኢብኑ ተይሚያህን ጽሑፎች፣ አስተሳሰብ፣ በታሪክ ያለው አቀባበል እና ዘመናዊ ትርጓሜዎች ይመረምራል።

➦ከዋና ዋና ተቋማት መካከል▼▼▼
ኢብኑ ተይሚያህ ጥናት በአንድ ተቋም ብቻ አይካሄድም።በተለይም እነዚህ ቦታዎች ጠንካራ የእስላማዊ ጥናት ሥራ አላቸው▼▼▼▼▼▼▼▼

1/ University of Oxford – Islamic Studies

2/ Princeton University – Department of Near Eastern Studies

3/ KU Leuven – Arabic and Islamic Studies

4/ University of Nottingham – Islamic Studies

5/ Leiden University / Brill – Islamic Studies

6/ Cambridge University – Islamic Studies

7/ Harvard University – Islamic Studies

8/ SOAS University of London
French Institute for the Near East (Ifpo)

9/ Leuven University Press

➦©opy !
❤1
❒ ነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ ❒

        ክፍል አንድ

     የሰሙድ ህዝቦች ከሁድ ህዝቦች በኋላ የመጡ ሲሆኑ በጣም ትዕቢተኛ እና ኩራተኛ ናቸው።

በሳውዲ ዐረቢያ ምድር በሂጃዝ እና በተቡክ መሀከል የሚገኝውን ግዙፍ ተራራ በመፈልፈል ከዘመኑ ጋር የማይመጣጠን ውብ ውብ... ህንፃዎችን ሰርተው ነበር የሚኖሩት።በጣም ትላልቅ ናቸው አሁን ያለው ትውልድ በጉልበትም ሆነ በግዝፈት ከነሱ አይስተካከልም።

ምንም እንኳን ድንጋያማ አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ቢሆኑም አላህ ምድራቸውን ለቡቃያ ምቹ አድርጓት የምንጮቹንም ብዛት ለጉድ አድርጎታል።

ግዜው ከአባቶቻቸው የወረሱርትን የጣኦት አምልኮ አጧጡፈው የያዙበት ዘመን ነበር።
በዱንያ ሰክረው...አላህን ረስተው...በወንጀል ተጨማልቀው ሳለ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ሳሊህ ኢብን ዑበይድ ኢብን ሂሻም ኢብን.....ዓድ ኢብን ኣርም ኢብን ሳም ኢብን ኑህ (ዐ ሰ) የተባለን መልካም ነቢይ ከመሀከላቸው ላከላቸው።

ሳሊህ ዐ ሰ በነቢይነት ከመመረጣቸው በፊት ህዝቡ ዘንድ በምልካም ስነ ምግባራቸው የሚታወቁ፣ከከበርቴ ቤተሰብ የተወለዱ፣ከዚያም አልፎ ሰዎች ለፍርድ ሚያስቸግር ክርክር ሲገጥማቸው እሳቸው ጋር የሚሄዱ ምርጥ የአላህ ባርያ ናቸው።
ወደፊት ሀገሪቷን በንግስና ያስተዳድሯታል ተብሎም ይገመት ነበር።
በንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ሳለ ሳሊህ ዐ ሰ የጌታቸውን ተልዕኮ እንደተቀበሉ በትኩስነቱ፦" ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ ከዓድም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ ባስቀመጣችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ ከሜዳዎቿ (ሸክላ) ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ፡፡ ከተራራዎችም ቤቶችን ትጠርባላችሁ፡፡ ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ" በማለት ጥሪውን አስተጋባ።

ይህን በሰሙ ግዜ ትዕቢታቸው አናታቸው ላይ ወጣ...ኩራታቸው ገነፈለ...የከተማይቱ መሳፍንትም፦"አንተ ሳሊህ! ቆይ አንተ ከኛ በምን ተሽለህ ነው አላህ መልዕክተኛ አድርጎ ሊመርጥህ የቻለው? ይልቁኑ አማልክቶቻችን በመጥፎ አይን ሳያዩህ አልቀሩም'ና አብደሀል" አሉት።

ከዚያም እንደተለመደው ሳሊህ(ዐ ሰ) የድሆች እና ምስኪኖች ተከታይ ይበራከቱለት ጀመር።ይሁን እንጂ በለፀጋዎች እና ጉልበተኞቹ ዝም ማለትን አልመረጡም'ና ምእመናኑ ዘንድ በመሄድ፦"እናንተ ባመናችሁት ነገር እኛ ክደናል" በማለት ይሳለቁባቸው ነበር።

ከዛላችሁ እነዚህ አመፀኛ ህዝቦች አንደ ቀን የሳሊህን ዐ ሰ ጥሪ ለማስቆም እና ተከታዮቹን ከሱ ለማራቅ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሊመካከሩ አንድ ቦታ ተሰበሰቡ።ብዙ ከመከሩ በኋላ በመጨረሻም ሳሊህን (ዐ ሰ).....


        •••✿ ❒ይቀጥላል❒✿•••
የሀቅ አድማስ Official apologetics 🔰
❒ ነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ ❒         ክፍል አንድ      የሰሙድ ህዝቦች ከሁድ ህዝቦች በኋላ የመጡ ሲሆኑ በጣም ትዕቢተኛ እና ኩራተኛ ናቸው። በሳውዲ ዐረቢያ ምድር በሂጃዝ እና በተቡክ መሀከል የሚገኝውን ግዙፍ ተራራ በመፈልፈል ከዘመኑ ጋር የማይመጣጠን ውብ ውብ... ህንፃዎችን ሰርተው ነበር የሚኖሩት።በጣም ትላልቅ ናቸው አሁን ያለው ትውልድ በጉልበትም ሆነ በግዝፈት ከነሱ አይስተካከልም።…
❒ ነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ ❒
 
               ክፍል ሁለት

  ብዙ ከመከሩ በኋላ በመጨረሻም ሳሊህን (ዐ ሰ) ያለ ተከታይ ብቻውን ለማስቀረት አንድ መፍትሄ አገኙ።

እሱም፦"ሳሊህን የሚከተል ከአማልክቱ በኩል የማይድንን በሽታ ይይዘዋል።ከሳሊህም የሚርቅ ከነዚህ ነገሮች የተጠበቀ ይሆናል" በማለት ከተማይቷን ቀወጧት።

ነገር ግን ትክክለኛይቱ የዳዕዋ ጥሪ መንገዷን ይዛ ቀጥላለች።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ አንድ ቀን ሳሊህ ዐ ሰ ጥሪያቸውን በህዝብ ፊት ሲያደርሱ ህዝቡም፦"አንተ ሳሊህ እውን አንተ ነቢይ ከሆንክ ማረጋገጫ ይሆነን ዘንድ እስቲ ተዐምር አምጣልን" አሉት።

የከተማይቱ ሹማምንት እና የተከበሩ ሰዎች በቦታው ነበሩ።የማይችለውን ነገር በመጠየቅ እንዳደናገሩት በማሰብ የማላገጥን ሳቅ ይስቁበትም ጀመር።(ወላሂ ነቢያቶች አላህ ምንዳቸውን ከፍ ያድርግላቸው።በገዛ ሀገራቸው ይሳቀቃሉ)

ከመሳፍንቱ መሀክል አንዱ ቆመ'ና፦"አንተ ሳሊህ ተዐምር ማሳየት እችላለሁ የምትል ከሆነ የተዐምሩን አይነት እኛ ነን ምንመርጠው ያንተ ስራ እኛ የመረጥነውን ተዐምር መተግበር ብቻ ነው" አሉት

እኛ እያየን ከዚህ ተራራ ውስጥ በግዝፈቷ አቻ የሌላት የአስር ወር እርጉዝ የሆነች፣መልኳም ቀይ የሆነ፣ከግዝፈቷ የተነሳ የከተማይቱ ይዝብ እና እንስሳት የሚጠጡትን ውሀ በአንዴው መጠጣት የምትችል ትልቅ ግመል አውጣልን"አሉት።

ነቢዩላህ ሳሊህም (ዐ ሰ) ህዝቡ ሁሉ ተዐምሩን አይተው በማመን ከጀሀነም ይድኑ ዘንድ የከተማይቱ ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ አዘዙ'ና ሁሉም ተሰበሰቡ።

ከዚያም ሳሊህ (ዐ ሰ) ለጌታቸው ሱጁድ በመውረድ ጌታቸውን ይማፀኑ ጀመር።አላህም የሱን መልዕክተኞች በህዝባቸው ፊት አያሳፍራቸውም'ና ተራራው በጣም መንቀጥቀጥ ጀመረ።

ህዝቡ ሁሉ አይኑን ተራራው ላይ ተክሏል።ካሁን አሁን ምን ሊከሰት ነው በማለት እርስ በርስ ይተያያሉ...

             ይቀጥላል
❤1
ሰምታችኋል እኛ ግን የለንበትም😐
😁5
➲ሳትመራመሩ ብሉ😭አንድ በአንድ ልዘርዝር ብዬ.....ዳሩ ግን የምግብ ፍላጎታችሁን እንዳይዘጋ ብዬ በመስጋት ዝርዝሩን ለናንተ ትቻለሁ🔥

➥◈የቴሌግራም ቻናላችን||
https://t.me/Rightpathstudent

ሁላችሁም ጆይን በሉ ሼር ይደረግ!
🙈2
የሀቅ አድማስ Official apologetics 🔰
❒ ነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ ❒                  ክፍል ሁለት   ብዙ ከመከሩ በኋላ በመጨረሻም ሳሊህን (ዐ ሰ) ያለ ተከታይ ብቻውን ለማስቀረት አንድ መፍትሄ አገኙ። እሱም፦"ሳሊህን የሚከተል ከአማልክቱ በኩል የማይድንን በሽታ ይይዘዋል።ከሳሊህም የሚርቅ ከነዚህ ነገሮች የተጠበቀ ይሆናል" በማለት ከተማይቷን ቀወጧት። ነገር ግን ትክክለኛይቱ የዳዕዋ ጥሪ መንገዷን ይዛ ቀጥላለች።በዚህ…
❒ ነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ ❒

             ክፍል ሶስት

   ሳሊህ (ዐ ሰ) ለጌታቸው ሱጁድ በመውረድ ጌታቸውን ይማፀኑ ጀመር።አላህም የሱን መልዕክተኞች በህዝባቸው ፊት አያሳፍራቸውም'ና ተራራው በጣም መንቀጥቀጥ ጀመረ።

ህዝቡ ሁሉ አይኑን ተራራው ላይ ተክሏል።ካሁን አሁን ምን ሊከሰት ነው በማለት እርስ በርስ ይተያያሉ።

በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ተራራው ከፍተኛ ጩኸት ካስተጋባ በኋላ በጣም በመሰንጠቅ ከመሀከሉ ህዝቡ በጠየቀው መልኩ ትልቅ እና እርጉዝ ቀይ ግመል ወጣች።

ይህን ባዩ ግዜ አይኖቻቸው ፈጠጠ፣ አንደበታቸው ደረቀ፣ምላሶቻቸው ተሳሰሩ።ሳሊህም ዐ ሰ፦"ህዝቦቼ ሆይ! ይህች ግመል የአላህ ተዐምር ናት።

ታይዋታላችሁ፤ ትዳስሷታላችሁም እናንተ ዘንድም ትኖራለች።
ባስቀመጣችሁት መስፈርት መሰረት ትልቅ እና እርጉዝ ሴት ግመል እንደመሆኗ መጠን ካሁን በኋላ ውሀችሁንም ለጋራ ነው ምትጠጡት።

አንድ ቀን ግመሊቱ ስትጠጣ ቀጣይ ቀን እናንተ ትጠጣላችሁ። ምክንያቱም መጀመርያ ያስቀመጣችሁት መስፈርት ይህ ነው'ና።

ነገር ግን ይህችን ግመል አንዳችሁ በመጥፎ ከተተናኮላችኋት የአላህ ፈጣኑ ቅጣት ይወርድባችኋል" በማለት አስረዳቸው።
ከዚያም ህዝቡ ለሳሊህ ዐ ሰ ያለው አመለካከት 100% ተቀየረ።ሁሉም ከማንም በላይ ሳሊህን ያከብር ጀመረ።ብዙ ሺህ ሰውም የሳሊህ ተከታይ ሆነ።

ይህ ያሳሰባቸው የከተማይቱ ሹማምንት አንድ ቀን ተሰብስበው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲወያዩ ውለው በመጨረሻም ግመሊቱን በመግደል ተስማሙ።

ይህ የተወሰነውም በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው ነበር።አጋጣሚ እዛው መጠጥ ቤት ሳሉ የመጠጥ ጥማቸው ሳይቋረጥም ከመጠጡ ቤት ጓዳ "መጠጥ አልቋል" የሚል መርዶ ደረሳቸው።

ሹመንቱም፦"ለምንድነው በርከት አድርጋችሁ ማትሰሩት" ብለው ሲጮሁባቸው
የመጠጥ ቤቱ ባለቤት፦

"ዛሬ ውሀ የግመሊቱ ተራ ስለሆነ ውሀ የለም'ና ብዙ መስራት አልቻንም" ብላ መለሰችላቸው።
ከመሀከላቸውም አንድ ቀዳር ኢብን ሳሊፍ ኢብን ጁንደዕ የተባለ አመፀኛ ከመሰል ጓደኛው ጋር ተነሳ'ና ግመሏን ሊገድል ጉዞ ጀመረ።

በጉዞ ላይ ሳሉም ሌላ ሰባት ሰዎችን መንገድ ላይ በመቀላቀል ዘጠኝ ሁነው ግመሏ ውሀ የምትጠጣበት ስፍራ ደረሱ።
ውሀው ዘንድም ደረሱ'ና በያዙት ሰይፍ ገደሏት።ከአጠገቧ ግልገሏ ነበር'ና ግልገሏንም አሳድደው በትልቅ ተራራ ላይ ይዘውት ገደሉት።ከሙጅሪምነታቸው የተነሳ የግመሊቱን ስጋ ቀኑኑ ተከፋፈሉት።

ሳሊህም ዐ ሰ ይህን በተመለከተ ግዜ፦"አሁን የጌታችሁን ቅጣት ተጠባበቁ።

የጌታችሁ ቅጣት ከመውረዱም በፊት ስጋውን ተሎ ተሎ በልታችሁ ጨርሱ" አላቸው።


      ይቀጥላል
➲ልክ እንደ ሴቶች የመርገም ደም(የወር አበባ) የሚያይ ወንድ ልጅ ተመልከቱልኝማ😐Btw የቤ/ክርስቲያን ጠባቂ ዘበኛ ነበር አሉ🤭መቼስ ከክርስቲያኖች ጓዳ የማይሰማ ጉድ የለም!

➥◈የቴሌግራም ቻናላችን||
https://t.me/Rightpathstudent

ሁላችሁም ጆይን በሉ ሼር ይደረግ!