የሀቅ አድማስ Official apologetics 🔰
557 subscribers
223 photos
79 videos
27 files
102 links
▣የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ ና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ።(እርሷም) አሏህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣በርሱም ምንንም ማንንም ላናጋራ፣ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤በላቸው፡፡እምቢ ቢሉም፦እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡"[📚ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን:64]

🔥"እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙ"[📚ሱረቱ ኣሊ-ኢምራን:102]!🔥
Download Telegram
አልሐምዱሊላህ


ፈዲለቱ አሸይኽ ዶክተር ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን ኢብኒ ዐብዲላህ አልፈውዛን ሐፊዘሁሏህ የስዑዲያ ጠቅላይ ሙፍቲ ተደርገው ተሹመዋል። አላህ በመልካም ስራ ላይ እድሜያቸውን ያርዝመው። አላህ ሀገሪቷን፣ መሪዎቿን፣ ዑለማዎቿንና ህዝቦቿን ከመጥፎ ነገር ሁሉ  ይጠብቃት።

አሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ በሸይኽ ሳሊሕ አልፈውዛን ፈትዋ ልቦች ይረካሉ ይሉ ነበር።

አሸይኽ ሳሊሕ አልፈውዛን ሀገረ ስዑዲያ ከተመሰረተች በኋላ ከሸይኻቸው ኢብኑ ባዝ ቀጥለው ሁለተኛው ከአሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሃብ ረሒመሁሏህ የልጅ ልጆች ውጭ ጠቅላይ ሙፍቲ የሆኑ ዐሊም ናቸው።

ከዚህ በፊት ላለፉት ዑለማዎቻችን አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው፣ አሁን ያሉ ሰለፊ ዑለማዎቻችንንም አላህ ይጠብቃቸው። በመልካም ስራ አድሜያቸውን ያርዝመው፣ ለዑማው ጠቃሚ ያድርጋቸው።
✍✍✍✍
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወይኔ በላቸው አለ ጭራሽ 😂😂😂😂😂😂
😁4
ለክርስቲያኖች መዳን ትልቁን ሚና የተጫወተው ዲያብሎስ ወይስ እየሱስ ነው¿😂
ምን ብሎ ተጸጸተ ወገኖቼ🙈¡¿
😁7
➲እነዚህን ምን እንበላቸው እስቲ¿😁አይ ክርስትና ደግሞ በፓንትና በሱሪ መስበክ ቀረ እንዴ¡😁

🔴ነገሩ ወዲህ ነው▼▼▼▼▼▼

➥ከላይ ያለው ምስሉ የተወሰደው ጴንጤዎች በቅርቡ ይለቀቃል ካሉት የስልጥኛ መዝሙር ነው።

➻በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ ተደጋግሞ ከሚታዩ ተግባራት መካከል"ለሰበካ ያግዘናል"በሚል የሌላውን እምነት ማንነት "መስሎ የመተወን ወይም የድራማ"ተግባር አንዱ ነው።ጤናማ የራስ ቅርጽ ካለመኖር የማንነት እጦት የሚፈጠር ሳንካ በመሆኑ ጠያቂ እንዳይኖሮ አድርጎታል።

➣የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ይህ የጴንጤዎች ትወናቸው ቢሰለቻት የሀይማኖት መለያ አልባሳትና ቁሳቁሶቿን እንዳይጠቀሙ በአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በማስመዝገብ ከልክላቸዋለች።

➣የፈረደበት ጀለብያና ጥምጣም ቀርቶላቸዋል ወንዱም ሴቱም ሳይቀር እየለበሰ የትወናው አካል ያደርገዋል።ሰዎቹ ሀይማኖታዊ መለያዎች ከእምነታቸው ጋር ያለውን ተቃርኖ እንኳን በጥሞና ለማሰላሰል የሚያስቡ አይደለም።

➥ለገበያ ይመች እንጅ የቡድሀ መነኩሴዎችን ከመልበስም አይመለሱም።በቅርቡ ለበዙት የሰይጣን አምላኪዎች የሚሆን መዝሙር ሲያወጡ የተዘቀዘቀ መስቀል ሊጠቀሙ ነው? እንዲያ ካልተጠቀሙ በምን ገበያውን ሊያደሩት እንደሚችሉ እድሜ ከሰጠን ወደፊት የምናየው ይሆናል።

➥ወደዋናው ሀሳብ ስንመለስ ግን መሠል አይነት በሰው ሀይማኖት መለያዎች ሳያምኑባቸው የመዘባበት ተግባራት በጊዜ መላ ሊበጅላቸው ይገባል።

➥ይህ ግልጽ ማታለል ከመሆኑ በተጨማሪ በሰው ኃይማኖት መለያና አስተምህሮ ላይ መቀለድም ነው።ይህንን ነውር ከነሱ ውጭ ማንም ሊያደርገው አይደፍርም።

➣ሀይማኖትን ተጠቅሞ መነገድ የተለመደ ቢሆንም በዚህ ደረጃ ሌላውን ሳይቀር እየተነኮሱ መሸቀጫ ማድረግ ግን ነውር ነው።
ነቃ በል ህዝቤ መልዕክታችን ነው
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
😁4😭1
የኢስላማዊ አጣብቂኝ ክሶች
(Islamic Dilema)

ክስ ፩ (1)

"If the Injil (the Gospels) is the word of God, Islam contradicts it and Islam fails."

"ኢንጂል (ወንጌል) የአምላክ ቃል ከሆነ፣ እስልምና ይህንን ይቃረናልና እስልምና ይከሽፋል"

🗝 መልስ

ይህ ክስ እስልምና ስለ ቀደምት መለኮታዊ መጽሀፍ ያለውን አስተምህሮ ጠንቅቆ ካለመረዳት የሚመነጭ ነው። ከዚህ በታች በነጥብ በማድረግ ማብራሪያውን እያስቀመጥኩ ልለፍ፦

1. ቁርኣን ስለ ኢንጂል (ወንጌል) ያለው አቋም

ቁርኣን ከዚህ በፊት የወረዱ መለኮታዊ መጽሀፍትን ማለትም ተውራት (ለሙሳ የተሰጠ)፣ ዘቡር (ለዳውድ) እና ኢንጂል (ለኢየሱስ/ዒሳ የተሰጠ) መጽሐፍት በጠቅላላ እውነተኛ የአምላክ ቃል መሆናቸውን ያረጋግጣል።

➺ ማረጋገጥ (Affirmation)፦ ቁርኣን እውነተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥለት ኢንጂል በወቅቱ ለነበረውና ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ መለኮታዊ ቃል የተሰጠውን ንጹሕ፣ የመጀመሪያውን መልእክት ነው። ቁርኣን (በአል-ማኢዳህ 5:46) የኢየሱስን መልዕክት ለተቀበሉ ሰዎች ኢንጂል "መምሪያና ብርሀን" ሁኖ እንደተሰጣቸው ይገልጻል።

➺ መበረዛቸው፦ ቁርኣን የመጨረሻውና ፍጹሙ መለኮታዊ የአላህ ቃል እንደሆነ እስልምና ያስተምራል። የቀደሙት መጽሐፍቶች በጊዜ ሂደት፣ በሰው ጣልቃ ገብነት ምክንያት "ተበርዘዋል" ወይም "ተለውጠዋል" ብሎ እስልምና ያስተምራል።

2. ለቀረበው የ "አጣብቂኝ ክስ" ምላሽ

ቁርኣን ከመጀመሪያውኑም ለዒሳ የተሰጠውን ያልተበረዘ ኢንጂልን እንጅ በክርስትናው አለም አሁን የሚታመንበት አራቱን ወንጌላትን (ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ) አስመልክቶ አይናገርም። ከቶውንም እስልምና እነዚህን የግለሰብ ስም የያዙ "ወንጌላት" አያውቃቸውም።

➺ እስልምና "ኢንጂል" ሲሉ የሚያመለክተው ኢየሱስ (ዒሳ) በመጀመሪያ ከአላህ ሱ.ወ የተሰጠውን መለኮታዊ መጽሀፍ ነው። ይህ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ያሉትንና በሰው የተጻፉትን፣ ታሪኮች፣ ምሳሌዎች እና ደብዳቤዎችን ያካተቱትን "ወንጌሎች" (Gospels) የሚገልጽ አይደለም።

በአሁኑ ጊዜ ያሉት ወንጌሎች የመጀመሪያውን ኢንጂል መልዕክት ሙሉ በሙሉ የያዙ አይደሉም፤ ይልቁንም፣ የመጀመሪያው ኢንጂል ምንነት ቅሪት ሊኖር ቢችልም፣ በኋለኞቹ ትውልዶች የተጨመሩ፣ የቀነሱ ወይም የተዛቡ ብዙ ይዘቶች አሉባቸው።

ኦርጅናሉ ኢንጂል ለህዝቡ የተላለፉ መመሪያዎችንና ራዕዮችን ያካተተ ነበር። በአንጻሩ አሁን ያሉት ወንጌሎች ደግሞ በሐዋርያት ወይም በደቀመዛሙርት ከቆይታ በኃላ የተጻፉ ታሪካዊ ሰነዶችና የሕይወት ዘገባዎች ናቸው።

ሲጠቃለል

🗝 ስለዚህ "ተቃርኖ" የተባለው ገለጻ የተሳሳተና ቁርኣን የሚያስተምረውን ትምህርት የሚገልጽ አይደለም። በቁርኣንና በመለኮታዊው ኦርጅናሉ ኢንጂል መካከል ምንም ተቃርኖ የለም። ቁርኣን የማይቀበለውም ኦርጅናሉን ኢንጅል ሳይሆን በሰዎች እጅ የተበረዘውን አሁን ክርስቲያኖች የሚያምኑበትን "ወንጌል" ነው። ስለዚህ ቁርኣን ኢንጅልን የአምላክ ቃል ከማለት በተጨማሪ እንድናምንበትም ያስተምራል እንጅ ተቃርኖት እንድንክደው አያስተምርም።

ይቀጥላል

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
https://t.me/Yahyanuhe
❤1
የኢስላማዊ አጣብቂኝ ክሶች
(Islamic Dilema)

ተግዳሮት ፪ (2): "ኢንጂል የተበረዘ (Corrupted) ከሆነ፣ ቁርኣን የኢንጅልን እውነተኛነት ያረጋግጣልና ቁርኣን ይከሽፋል"

"If the Injil (the Gospels) is corrupted, Islam still fails because the Qur’an affirms its authority."

🗝 ምላሽ

ቁርኣን የኦርጅናሉ ኢንጅልን መለኮታዊነት አያስተባብልም፣በተቃራኒው መልዕክቱ ከአላህ የመጣ እንደሆነ ያረጋግጣል። ነገር ግን ከአላህ የመጣው መለኮታዊ መልዕክት በሰው እጅ ሊበረዝ አይችልም ግን አይልም።

➺ ፍጹምነትና ጥበቃ

በእስልምና አስተምህሮ መሠረት፣ አላህ ቀደም ሲል ለነበሩት መለኮታዊ መጽሐፎች እንዳይበረዙ ወይንም እንዳይለወጡ መለኮታዊ ጥበቃ አልሰጠም። ለሰው ልጆች እንደ ፈተና የጥበቃ ኃላፊነት የተሰጠው ለራሳቸው ነበር።

"..እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን፡፡ እነዚያ ትዕዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፡፡ ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉትና በርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት (ይፈርዳሉ)፡፡ ሰዎችንም አትፍሩ፡፡ ፍሩኝም፡፡ በአንቀጾቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ፡፡ አላህም ባወረደው ነገር ያልፈረደ ሰው እነዚያ ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው.." (ቁርኣን፣ አል-ማኢዳህ 5:44)

በዚህ አንቀጽ ላይ "ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉትና በርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት" የሚለው ገለጻ መጽሐፉን የመጠበቅ ኃላፊነት በሰው ላይ እንደነበር ያመለክታል።

➺ ቀደምት መለኮታዊ መጽሀፍት የአገልግሎት ጊዜያቸው በቦታና በጊዜ የተገደበ ነበር። ሙሴና ኢየሱስ የተላኩት ለእስራኤላውያን ከመሆኑ በተጨማሪ መልዕክታቸውም በዘመኑ የነበረውን ህዝብ ያማከለ ነበር። መልዕክታቸው ዘላለማዊ ካለመሆኑ ጋር "መለኮታዊ ጥበቃ ያስፈልጋቸው ነበር" ተብለው የሚሟገትላቸው አልነበሩም።

➺ የቁርኣን ልዩ ባህሪ

ቁርኣን ከወረደበት ምክንያት ውስጥ አንዱ በቀደሙት መጽሐፍት ላይ የተከሰተውን የሰው ልጅ ጣልቃ ገብነት ለመሙላትና ለማረም ነው። (በአል-ማኢዳህ 5:48) ቀዳሚ ለሆኑት መጽሐፍት ሁሉ "ሙሃይሚን" ሆኖ እንደተላከ ይገልጻል።

➺ "ሙሃይሚን" የሚለው ቃል ትርጉም ቁርኣን የቀደሙትን መጽሐፍት በውስጣቸው ያለው የአላህ ቃል የትኛው እንደሆነ እየለየና እውነቱን እያረጋገጠ የሚመጣ የመጨረሻው የአላህ ቃል (ኪዳን) ነው ማለት ነው።

ቁርኣን የኦርጆናሉን ኢንጂል መለኮታዊ መነሻና መሠረታዊ መልእክቱን ያረጋግጣል እንጂ አሁን ላይ ያለውን የተበረዘ ይዘት ከስህተት ፍጹም መሆንን አያረጋግጥም። በመሆኑም ቁርኣን ራሱ የመጣው የተዛባውን ለማረም ስለሆነ፣ ኢንጂል መዛባቱ የቁርኣንን መለኮታዊ ምንጭ አይጎዳውም፤ ይልቁንም የቁርኣንን የመላክ ምክንያት የሚያረጋግጥ ነው።

➺ የቁርኣን ፍጹምነት (Perfection)

የቁርኣን ፍጹምነት ከሚረጋገጥበት መንገድ ውስጥ አንዱ የመልእክቱ ወጥ መሆንና አለመበረዝ ተጠቃሽ ነው።

➺ የሰው ጣልቃ ገብነት፦ ቁርኣን ከወረደ በኋላ አላህ ራሱ "እኛ ቁርኣንን አወረድነው፣ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን" (አል-ሒጅር 15:9) ብሏልና ቁርኣንን ከማንኛውም መዛባት ሊጠብቀው ቃል ገብቷል። ይህ ጥበቃ የቀደሙት መጽሐፍት ያልነበራቸው ልዩ መብት ነው። የቁርኣን መልዕክት በቦታና በጊዜ የተገደበ ባለመሆኑ መልዕክቱ እስከ ትንሳኤ ቀን የሚቆይ ነው።

➺ ኢንጂልን ማረጋገጥ፦ ቁርኣን ኢንጂልን ማረጋገጡ የሚያመለክተው በእምነት ሰንሰለት (chain of revelation) ውስጥ የቀደሙት መልእክቶች ከአንድ ምንጭ የመጡ መሆናቸውን እና የእውነተኛውን እምነት የማስቀጠል ታሪካዊ ሒደት አካል መሆኑን ነው። ቁርኣን የሚናገረውን ንጹሕ መልእክት (ተውሒድ/አንድ አምላክን ማምለክ) ኢንጂልም በመጀመሪያው ኦርጅናል ይዘቱ ውስጥ አካቷል። ስለዚህ፣ ቁርኣን የኢንጂልን የአስተምህሮ መነሻ እንጂ የአሁኑን የተዛባ ይዘት ስለማያረጋግጥ፣ ቁርኣን በዚህ ረገድ የሚከሽፍበት ምንም ምክንያት የለም።

🧬 የመጀመሪያውን ክስ ምላሽ በዚህ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
https://t.me/Yahyanuhe
➲ስልጤን እንዴት ማክፈር ይቻላል የሚል የሚሽነሪዎች ሴራ በስልጤ‼️

➦የጴንጤ አክፍሮት ሀይላት የረጅም ዘመን እቅድ⚠️

➦በአሏህ ፍቃድ በዚህ ፅሁፍ ለማስታወስ እና ለማንሳት የተፈለገው የአክፍሮት ሀይላት በስልጤ ላይ የሚያደርጉትን ሩጫ አውቆ የሚገባውን ጥንቃቄ ስለማድረግ ይሆናል። በተለይም የስልጤ ተወላጆች በአጠቃላይ ይህንን የአክፍሮት ሀይላት መመከትና መመለስ ባለበት ነገር ሁሉ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ሀገሩን መጠበቅ ግድ ይላል።

➦ይሄ ሀይል ለከንቱ አላማው የሚያደርገውን ልፋት አይተን ከአሁኑ ጥንቃቄ ካልወሰድን የነገ ዕለት ጉዱና ፈተናው በየቤታችን ይከሰታል።በጎረቤት የምናየው ትርምስ ሳይፈጠር አይቀርም ከንዲህ አይነቱ ፈተና አሏህ ይጠብቀን ።

➦የክፍሮት ሀይል እቅድ በስልጤ ላይ▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼

1)ኛ ወጣት ወንዶችን እና እሴቶችን በተለያዩ ስልቶች ማበላሸት በዲናቸው ጠንካራ እንዳይሆኑ ማድረግ ።
ለዚህ ቀላል መንገድ እነሱን ማግባት ፍቅር ማስያዝ ተቻችለን አንቺም በሃይማኖትሽ እኔም በሃይማኖቴ ብሎ መጀመሪያ ማሳመን ከተጋቡ ከወለዱ በኋላ አልሰማሽም ተቀበይ ብሎ ማሳመን ።

②ኛ በብር መምጣት ስራ የሌላቸውን አቅመ ደካማዎችን ስራ ያጣ ዱሪዬውን በብር መስበክ ከዛም የአካባቢዉን ሴት እንዲያገበ ማድረግ ።

③ኛ ከተቀበሉ በኃላ እንዳይነቃባቸው መስጂድ እንዲገቡ ሶደቃ እንዲሰጡ በመልካም ነገር መተባበር  ቅኑነትን ሳይፈልጉ ለዓላማቸው ሲሉ መስራትን የምናሉ።

➦በተግባርም የሆነ ክስተት ጉዳዩ እንዲህ ነው  ፦ አንድ የማይሰግድ መጥፎ ህይወት ላይ የነበረን አካል ወስደው አሰልጥነው ወደ አከባቢው እንዲመለስና በየ ግዜው እነሱ ጋር እየሄደ ኮርስ እንዲወስድ ካደረጉት በዃላ ሰፈሩ ውስጥ መስገድ መጾም ጥሩ መስራት ማስመሰል እንጂ ሌላ ምንም አይታይበት ይሄ ልጅ እንዴት በዚህ ፍጥነት እንዲህ ሊሆን ቻለ ብለው የተወሰኑ ልጆች የስልጤ ጴንጤ መስለው አንተ ጴንጤ አይደለህም ወይ ለምን እንዲህ ትሆናልህ ሲሉት ሰው እስከማገኝ ድረስ ነው ብሎ አላቸው በዛ ምክንያት ልጆች እንዳጋለጡት ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ ።

4)ኛ የሙስሊም ልጆችን ወላጅ አልባ የሆኖትን የወደቁትን ማንሳት በሚል ስም በየ ወሩ 1,2,3,4...ወይም በየአመቱ ወደራሳቸው  በማይታወቅ ሁኔታ በማስጠጋት የረጅም ግዜ እቅድ ማሰካት ነው ።

5)ኛ ስለላ(ሰላይነት ) ነዉ ማን ምን ይፈልጋል እገሊት ምን ትፈልጋልች እገሌ ምን ይፈልጋል የት አካባቢ ልጅ ዲኑን አይማርም ቁርዓን አይቀራም የማን ልጅ መማር አይችልም እያሉ በመዶለት ከሸሪዓ አስተምህሮት የራቁ አካባቢዎችን የት የት ነው በሚል ውስጥ ገብቶ በአካባቢ ስለላ በማካሄድ የረጅም ጊዜ ልፋታቸው እንደቀጠለ ነው።
6)ኛ በትምህርት በህክምና በጤና ድርጅት በዕርዳታ በዶክተሮች  በአስተማሪ ምክንያት ወደ ህዝቡ ቅርብ መሆን እና ሳይነቃባቸው መርዛቸውን (እምነታቸውን) መርጨት ነው።
ይሄንን በተመለከተ በተለይ ከሀዲያ ጎረቤት በሆኑ የስልጤ ወረዳዎች እንደ ናሙና ብዙ መጥቀስ ይቻላል። ለምሣሌ ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ሌራ፣ዳሎቻ፣አለም ገበያ፣ምስራቅ አዘርነት ቂልጦ ጎሞሮ፣ወራቤ ከተማን ብናነሳ ብዙ ሰርተዋል በመስራትም ላይ ናቸዉ ።

7)ኛ በኢኮኖሚ፣የተማሪውን ደረጃ ዝቅ በማድረግ፣የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞችን የመጣ ፣እና የስልጤ ህዝብ የመሰልጠን እደገትን በማውረድ ስራ ላይ ዘመቻ መስራት ነው ።

8)ኛ የትምህርት ቤት አካሄድን ማበላሸት ነው። እንደ ሚታወቀው የስልጤ ህዝብ እንደ አጠቃላይ ሙስሊም ነዉ በሚለው ይታወቃል ።
9)ኛ በስራ አማካኝነት ከተለያየ ቦታ በመምጣት ከስልጤ ልጅ ጋር የመጋባት ዘመቻ ነው ።

10)ኛ በስልጤ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ የይጠብቁልኝ ጥናታዊ ዘመቻ ነው።
እንደሚታወቀው የስልጤ ተወላጆች ገጠሩን በመተው ወደ ከተማ ያበዛሉ ትንሽ የተሻለ ኑሮ ላይ ሲደርሱ ቤተሰቦቻቸዉን ወደ ከተማ ያጠቃልላሉ የገጠር ቤት ባዶ እንዳይሆን በሚል ጴንጤን አምጥተው ያስገባሉ ።

በገቡበት አካባቢ የተወሰነ ሲላመዱ ትዳር የሌላቸው አግብተው የፈቱ ባል የሞተባቸው ሴቶች ጋር ይጋባሉ ይዋለዳሉ ፈተናው ከባድ ነው ።

11)ኛ መንዙማና መዝሙርን በስልጥኛ እስላማዊ አስመስሎ ማቅረብ ነው ።

12)ኛ ቁርዓን ቀርተው የተበላሹ በሱስ በሴት የተፈተኑ ሰዎችን መሰብሰብ ነዉ ።
በዚህ ሰበብ የተለያየ ማደናገሪያ በመፍጠር ሕዝቡን የማክፈር ዘመቻ ያደርጋሉ ።

13)ኛ መጽሃፋቸውን በስልጥኛ ቋንቋ በመተርጎም አላዋቂውን ህብረተሰብ ለማሳሳት መሞከር ነው ስራ ያደረጉት ። ድክመት ያዩበት ሙስሊም ስልጤን ሲያገኙ በድብቅ መጽሓፉን ያድሉታል ።

➦ለማሳጠር ብሞከርም ፅሁፉ እረዝሟል። በትዕግስት አንብበን መፍትሄውን እንምረጥ ለሀገራችን ለህዝባችን ብሎም ለአለማችን ሙስሊም ማህበረሰብ ከልብ ዱዓ እናድርግ ።አሏህ ከዲነል እስላም ጠላቶችና ሸረኞች ይጠብቀን‼️

➦ጥቆማና ማሳሰቢያ፦ይህ የአክፍሮት ሀይላት ሴራ በስልጤ ሙስሊም ማህበረሰብ ብቻ የሚያተኩር አይደለም ሴራውና ዘመቻው በሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ በሚበዛበት አካባቢ ሁሉ ለመስራት የታሰበና የታቀደ ነው።ስለዚህ ሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ አካባቢውን ከነዚህ የአክፍሮት ሀይላት እራሱን በዕልም (በትክክለኛው እስላማዊ እውቀት) ብሎም ይህንን መከላከል በሚችለው ነገር በሙሉ ልከላከል ይገባል።

➛ለሁሉም ይዳረስ ሼር እናድርግ ባረከሏሁ ፊኩም🔥🔥
🔥1
በዚህ ቻናል የተዳሰሱ ነጥቦች

1.እስላም
2.እስልምና የተፈጥሮ ሀይማኖት ነው
3.የነቢያት ሀይማኖት ምን ነበር?
4.የነቢያት ጥሪ
5.የሙስሊሞች መጀመሪያ
6.በእኔ የሚሰራዉን አላዉቅም?
7.ገለባ ክስ
8.አሏህን በወጣት መልከ አየሁት
9.የቁርኣን አሕሩፎች
10.ቂርኣት
11.እውን በእስልምና እየሱስ እንደተሰቀለ የሚያሳይ ማስረጃ አለ?
12.የቀጠለ
13.አሏህ
14.አስ-ሶመድ
15.እኔ ጂብሪል ነኝ ብሏቸዋል??
16.እውን እስልምና ሴት ልጅን ከውሻና አህያ ጋር እኩል ያደርጋታል?
17.አዳምን በራሱ መልክ ፈጠረው?
18.ሴቶች በእስልምና ➊
19.ሴቶች በእስልምና ➋
20.ሴቶች በእስልምና ➌
21.ሴቶች በእስልምና ➍
22.እውን እያንዳንዱ ሙስሊም በጀነት 72 ወይም 100  ሚስቶች አሉት ⁉️
23.እውን ከዕባህ ሀጥያትን ያስተሰርያልን❓
24.የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ትንቢት ➊
25.የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ትንቢት ➋
26.የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ትንቢት ➌
27.የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ትንቢት ➍
28.የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ትንቢት ➎
29.ያልተወለደ አምላክ እና የተወለደ
30.አዳም ላጠፋው ጥፋት ንሰሃ ገብቶ
31.ሰይጣን በጆሮው ውሰጥ ይሸናል ?
32.እውን ነብዩ ﷺ መጠጥ ይጠጡ ነበርን?
33.ለምን ሴቶች በጀሀነም በዙ?
34.ሴት እርሻ ናት
35.ምቷቸው »
36~የአላህ ረህመት
37~የበኒ ዑረይና ሰዎች የግድያ ቅጣት
38~የሴት ልጅ ምስክርነት በእስልምና?
39~ገለባ ክስ ➋

➦በpdf የተለቀቁ መጣጥፎች👇

1.ሴቶች በክርስትና
2.የመጀመሪያ ሙሥሊም ማነው?
3.እውን ነብዩ ”ﷺ” የጀነት መሆናቸውን አያውቁምን?"
4.ሴቶች በእስልምና ጥላ ሥር
5.የአምላክ ባህሪያት" በ2ቱ እምነቶች ዘንድ
6. 72 ወይም 100  ሚስቶች በጀነት ⁉️ "
7.የቁርኣን አሕሩፎች
8.ቂርኣት
9.ገድላት እና ድርሳናት ስፈተሹ
10.እኔ ጂብሪል ነኝ ብሏቸዋል?
11.አሏህን በወጣት መልኩ አየሁት
12.የነብዩ ትንቢቶች በጥቂቱ
13.ከ500 በላይ የነቢያችንን ትንቢቶች የተሰበሰበበት መጽሐፍ
14.የነብዩ ተዓምራቶች በጥቂቱ
15.ሰይጣን በጆሮ ውስጥ ይሸናልን
16.የነብያችን አሟሟት
17.የአላህ ረህመት

👉ይቀጥላል ኢንሻ አላህ


በዚህ ቻናል ላይ በተለቀቁት ትምህርቶች ዙሪያ ጥያቄና አስታያየት ካላቹ በቦት ማስቀመጥ ትችላላቹ ➥ @IslamicRespondbot

✍Islamic Respond
https://t.me/IslamicResponds
❤1
🔥ለሰይጣን መገበርና የድግምት ሥራ በክርስትና!
መክተፊያና ክርስትና😁‼️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወይኔ በላቸው ዘመወዛገብ ዘማወዛገብ😂
ተመልከቱ እንግዲህ የክርስቲያኖችን ጉድ በዚህ ልክ ይወርዳሉ😀
😁2
Forwarded from [Christianity🎯]
🔺የሎዶቅያ መልዕክት?

ጳውሎስ ወደ ሎዶቅያ የላከው በፊት ላይ ተቀባይነት የነበረው ዛሬ ላይ ግን የተወገደ መልዕክት እንደነበረው ያውቁ ኖሯል?

ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ በላከው መልዕክቱ ላይ ወደ ሎዶቅያ የላከው መልዕክት እንዳለ ጽፏል፦

“ይህችም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበች በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምትገኘውን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።”
  — ቆላስይስ 4፥16

አንዳንድ የእንግሊዘኛ ትርጉሞች በግልጽ "የጻፍኩላቸውን መልዕክት/the letter I wrote to them" ብለው አስቀምጠውታል፦

Colossians 4:16 (NLT) "After you have read this letter, pass it on to the church at *Laodicea* so they can read it, too. And you should read the letter I wrote to them."

አውዱ ላይ "የጻፍኩላቸው" እያለ ያለው ለሎዶቅያ እንደሆነ ግልጽ ያለ ፍንትውም ያለ ጉዳይ ነው። ይህም ለሮሜ፣ ለኤፌሶን፣ ለቆሮንጦስ ሰዎች ለሌሎችም መልዕክታትን ጽፎ እንደነበረው ሁሉ ለሎዶቅያ ሰዎችም መልዕክትን ጽፎላቸው እንደነበረ ማሳያ ነው።

"Commentary Critical and Explanatory on the Whole Bible" የተባለ የባይብል ማብራሪያም "ከሎዶቅያ የምትገኘውን መልዕክት" የሚለውን የጳውሎስን ንግግር "the Epistle which I wrote to the Laodiceans" በማለት *ለሎዶቅያ(ሰዎች) የጻፍኩት መልዕክት* ማለቱ እንደሆነ አብራርቶታል።

በዚህ ብቻ አያበቃም ይህ መልዕክት በጣም ብዙ በሆኑ ከ6-15ተኛ ክፍለ ዘመን በሚገኙ የባይብል እደ-ክታባት ውስጥ የሚገኝ ነው[1]።ለአብነት ያክል በVictor አማካኝነት Capua ላይ የተዘጋጀው Codex Fuldensis(541-546 A.D) ውስጥ ይህ መልዕክት ይገኛል[2]&[5]።

በጣም የሚገርመው ነገር ኤጲፋንየስ የተባለው የ4ተኛ ክፍለ ዘመን የቤተ-ክርስቲያን አባትም ይሄንን መልዕክት የጳውሎስ መሆኑን አጽድቆታል[3]።በተጨማሪም ኤጲፋንየስ የሎዶቅያ መልዕክትን ከጳውሎስ መልዕክታት መካከል 15ተኛ አድርጎ እንደመደበው ታዋቂው የNew Testament scholar የሆነው Bart D. Ehrman ያረጋግጣል[4]።

ይህ መልዕክት በዋናነት በሁለተኛው የኒቂያ ጉባኤ(787 CE) ላይ ውድቅ ተደርጓል። ሆኖም በጉባኤ ደረጃ ውድቅ ከተደረገ ቡሃላ ለራሱ በብዙ የባይብል እደ-ክታባት ላይ ተካቷል፤ German bibles ከሉተር በፊት ተካቷል, Czech Bibles ላይ በቆላስይስ እና በ1ደኛ ተሰሎንቄ መልዕክት መካከል ከአስራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን በፊት ተካቷል[5]።

እንግዲህ ይህ መልዕክት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተቀባይነት ነበረው በተለይ በምዕራብ የተከበረ መልዕክት ነበር፤ በትርጉሞች ሳይቀር ተካቶ የነበረ ነበር። ይህ ከሆነ አሁን ማስወገድ ምን አስፈለገ?

ይህ የሚያሳየን ባይብል እጅግ ሲበዛ ተዓማኒነት የጎደለው መጽሐፍ መሆኑን ነው፤ ማንም ተነስቶ የሚጨምርበት የሚቀንስበት የሆነ መጽሐፍ መሆኑን ያሳየናል። ሲያሻቸው የጳውሎስ ጹሁፍ አድርገው ይቀበሉታል ከሌሎች የባይብል ክፍሎች ጋር አካተው ቅዱስና የፈጣሪ ቃል ከሚሏቸው ጹሁፎች መካከል ያስቀምጡታል፤ ሲያሻቸው አሽቀንጥረው ይጥሉታል ይህ የሚያሳየው የፈጣሪ መልዕክት ነው ተብሎ የሚታሰበው ባይብል ላይ በዘመናት ውስጥ ሲጨመርበት ሲቀነስበት እንደኖረ ነው። ወጥ የሆነም ባይብል እንዳልነበረ አሁንም እንደለለ አለም አቀፋዊ ሐቅ ነው። በፊት ላይ እንደ ፈጣሪ ቃል ሲነበቡ የኖሩ አሁን በጉባኤና በተወሰኑ ሰዎች አማካኝነት የተወገዱበት ባይብል በምንም ሂሳብ ተዓማኝ ሊሆን አይችልም!
📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎📎
1] Forgery and Counter Forgery Bart D. Ehrman p.798
2] The Text Of The New Testament p.108
3] The panarion of Epiphanius of salamis Book 1 p.315
4] Forgery and Counter Forgery Bart D. Ehrman p.799
5] Forgery and Counter Forgery Bart D. Ehrman p.800

https://t.me/Christianity_With_History
👍1
Forwarded from Murad|⛉
ባይብል ተጠብቋልን?

_ክፍል ሁለት_

ወደ ክርስትናው ስንመጣ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የክርስትና ቀደምት ቅዱሳን አባቶችና ሊቃውንቶች በባይብል ዙሪያ ያላቸው አቋም ከሌሎች አባቶች ጋር ከመጋጨቱ በተጨማሪ የዛሬውን ባይብል ገደል የሚከት የጋራ አቋምም ነበራቸው።

በክርስትና ታሪክ ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ ድረስ አንድ ወጥ የሆነ በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ባይብል እንደለለ ይታወቃል። ለምሳሌ ፕሮቴስታንቶች 66 ሲቀበሉ ኦርቶዶክሶች 81 ይቀበላሉ ካቶሊኮች ደግሞ 73 ይቀበላሉ። ነገር ግን ከነዚህ መጽሃፍት ውጪም የነበሩ እንደ አምላክ ቃልነት ተቀባይነት የነበራቸው መጽሐፍት ነበሩ፤ ከነዚህ መካክል ሆነው ደግሞ በጥንት አባቶች ተቀባይነት ያልነበራቸው ነበሩ።

ለምሳሌ ዛሬ ላይ ሦስቱም የክርስትና ሴክቶች በሚቀበሏቸው ባይብል ዘንድ የማይገኘውን "የሔርማስ መልዕክትን" ->ኢራንየስ(2 Century)[1] ->ቀሌሚንጦስ ዘአሌክሳንደሪያ(2-3 Century)[2] ->ጠርጡሊያኖስ(2-3 Century)[3] ልክ እንደ መለኮታዊ ራዕይ ወይም እንደ Scripture አድርገው ይቀበሉት ነበር።

/በዝርዝር ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንመልከት/

የአሌክሳንደርያው ቀለሚንጦስ ዛሬ ባይብል ላይ የለሉትን እነ Didache'ን ጨምሮ የሔርማስ'ን መልዕክት ልክ እንደ በመለኮታዊ መሪነት እንደተጻፉ ነበር የሚያያቸው፦

"በግብፅ፤ የአዲስ ኪዳን ቀኖና ታሪክ ከእስክንድርያው ቀሌምንጦስ (ከ217 ዓ.ም በኋላ ያረፈ) በፊት የነበረው ሁኔታ ግልጽ አይደለም። ቀሌምንጦስ፣ ምናልባት ከያዕቆብ፣ ከ2ኛ ጴጥሮስ እና ከ3ኛ ዮሐንስ በስተቀር፣ በኋላ ላይ የተወሰኑትን 27ቱን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ ያውቃቸው እንደነበር ይገመታል። ሆኖም ለሌሎች በርካታ መጻሕፍትም ከፍተኛ ሥልጣን (ተቀባይነት) ሰጥቶ ነበር። ከእነዚህም መካከል እንደ ዲዳኬ (Didache)፣ ሄርማስ እረኛው (Shepherd of Hermas)፣ የጴጥሮስ ስብከት (Kerygma of Peter) እና ምናልባትም 1ኛ ቀሌምንጦስን የመሳሰሉትን በመለኮታዊ መሪነት እንደተጻፉ (divinely inspired) አድርጎ ይቆጥራቸው ነበር።"
(New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.30-1)

ኢራንየስ'ም(2 Century) የእብራዊያን መልዕክትን የጳውሎስ መሆኑን አይቀበልም ነበር፤ ከአሌክሳንደርያው ቀለሚንጦስ በተመሳሳይ የሔርማስ መልዕክትንም እንደ Scripture ነበር የሚቀበለው፦

"ወደ ፊልሞን የተላከውን መልእክት አይጠቅስም፤ እንዲሁም ወደ ዕብራውያን የተላከውን መልእክት ቢያውቀውም፣ ጸሐፊው ጳውሎስ መሆኑን አይቀበልም። 'እረኛው ሔርማስ' (Shepherd of Hermas) የተሰኘውን መጽሐፍ 'መጽሐፍ እንዲህ ይላል' (Scripture says) በሚለው አገላለጽ ያስተዋውቀዋል።"
(New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.31)

Hippolytus'ም 21 የአዲስ ኪዳን መጽሐፍቶችን የሚቀበል ሲሆን ከመምህሩ ኢራንየስ በተመሳሳይ የእብራዊያን መልዕክትን የጳውሎስ እንደሆነ አይቀበልም ነበር ለእርሱ ይህ መጽሃፍ ቀኖናዊ አልነበረም፦

"የኢራንየስ ደቀ መዝሙር የሆነው የሮሙ ቅዱስ ሂፖሊተስ (በ235 ዓ.ም. ያረፈ)፣ የሁለቱን ኪዳናት ቅዱሳት መጻሕፍት 'የክርስቶስ ሁለት ጡቶች' ሲል ይጠራቸዋል፤ ይህም በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው ቃል ውስጥ ያለውን የጠበቀ የምግብ (የምገባ) ግንኙነት ያመለክታል። የእርሱ አዲስ ኪዳን ቢያንስ 21 መጻሕፍትን ያካትታል። የዕብራውያንን መልእክት የጳውሎስ እንደሆነ አድርጎ ስለማይቆጥር፣ ለእርሱ ቀኖናዊ (የመጽሐፍ ቅዱስ አካል) አይደለም። [በጽሑፎቹ ውስጥ] ፊልሞንን፣ 2ኛ ወይም 3ኛ ዮሐንስን፣ ያዕቆብን ወይም ይሁዳን አይጠቀምም።"
(New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.31)

በተጨማሪ Philip schaff'ም ጥንታዊ አባቶች "የሔርማስ መልዕክት" መለኮታዊ እንደሆነ እንደሚያምኑ ተናግሯል።
ለምሳሌ ያክል ኢራንየስ፣ የአሌክሳንደርያው ቀለሚንጦስ እንዲሁም አርጌንስ  የሔርማስ መልዕክት መለኮታዊ መሆኑን በጹሁፎቻቸው መግለጻቸውን አስፍሯል፦

"የጥንት ጸሐፊዎች መጽሐፉ በእርግጥም በመንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፈ ያምናሉ። ኢራኒየስ እንደ ቅዱስ መጽሐፍ ይጠቅሰዋል፤ የእስክንድርያው ቀሌምንጦስ ስለ መጽሐፉ ሲናገር አባባሎቹ "መለኮታዊ" እንደሆኑ ይገልጻል፤ አርጌንስም ቢሆን፣ አንዳንድ አገላለጾቹ በአንዳንዶች ዘንድ ጥርጣሬን የሚያሳዩ ተደርገው ቢታዩም፣ እርሱ ግን "በመለኮታዊ አነሳሽነት እንደተጻፈ" ያለ ጥርጥር አስተያየቱን ይሰጣል።"
(Fathers of the Second Century by Philip Schaff p.8)

የሔርማስ መልዕክት 4ተኛ ክፍለ ዘመን ላይ እንደተጻፈ የሚገመተውና እጅግ ጠቃሚ ከሚባሉ የባይብል እደ-ክታባት መካከል የሚመደበው Codex Sinaiticus ውስጥም የሚገኝ ነው።[4]

የMuratorian ቀኖናም እንደ New Catholic Encyclopedia 22/23 የአዲስ ኪዳን መጽሐፎች ብቻ ነው የያዘው(24 የሚሉም ምሁራኖች አሉ)፦

"በኢጣሊያ፤ ምናልባት ከ180 እስከ 190 ዓ.ም. ገደማ (ምናልባትም በሂፖሊተስ) የተዘጋጀው የሙራቶሪያን ፍራግመንት (Muratorian Fragment) ቀኖና፣ (ጸረ-ማርሲዮናዊ የሆኑትን የወንጌላት መቅድሞች ካልቆጠርን) የቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው የአዲስ ኪዳን ቀኖና ዝርዝር ነው። ይህም 22 (ወይም 23) የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ይዘረዝራል።"
(New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.31)

ይህ የMuratorian Canon በተመሳሳይ ማለትም ልክ እነ ኢራንየስ እነ ሂፖላይተስ የእብራዊያን መልዕክትን እንደ ጳውሎስ መልዕክት እንደማይቀበሉት ሁሉ ይህ ቀኖናም የእብራዊያንን መልዕክት ከቀኖና ገለል ያደረገ ነበር።[5]

3ተኛ ክፍለ ዘመን አካባቢም ላይ የኖረው ጠርጡሊያኖስ የእብራዊያን  መልዕክትን አይቀበልም ነበር፦

"በአፍሪካ፣ ተርቱሊያን ከ2ኛ ጴጥሮስ እንዲሁም ከ2ኛ እና 3ኛ ዮሐንስ በስተቀር ሁሉንም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ይጠቀም ነበር። ምንም እንኳን የዕብራውያን መልእክት በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በስፋት ጥቅም ላይ እንደሚውል ቢቀበልም፣ የጻፈው በርናባስ ነው በማለት ከቅዱሳት መጻሕፍት (ከቀኖና) ያስወጣዋል።"
(New Catholic Encyclopedia Vol 3 P.32)

ታዲያ ይህ ሁሉ የቤተ-ክርስቲያን አባት እንደ አምላክ ቃል የተቀበለውን መጽሐፍ አሁን ማስወገድ ያስወገዱትን ደግሞ መቀበል የጤና ነው? ስጀምር "የዛሬውን ባይብል ገደል የሚከት የጋራ አቋምም ነበራቸው" ያልኩት ለዚህ ነው!

የቤተ-ክርስቲያን ታላላቅ አባቶች፣ ሊቃውንቶች በዚህ መልኩ አሁን ካለው ባይብል ጋር ፈጽሞ የራቀ አቋም ነበራቸው የሚገርመው ልዩነታቸው ግዝፈቱ *በመጽሃፍት* ደረጃ ነበር የሚለያዩት። ከአሁኑ የባይብል ቀኖናዎች ጋርም እርስ በራሳቸውም ሲጋጩ ነው የኖሩት። ለዘመናት ምንም ወጥ ያልሆነ በገዛ ቅዱሳን አባቶቹና ሊቃውንቶቹ ዘንድ ውድቀትን መለያየትን ያስተናገደ መጽሐፍ እንደ ባይብል ማን አለ? ማንም! 

1] Irenaeus Against Haer; 4.20.2
2] Clement of Alexandria Stromata; 1.17.29
3] Tertullian De Orat; 16
4] Fathers of the Second Century by Philip Schaff p.9
5] The text of New testament p.49

https://t.me/Murad11145
❤2
https://t.me/amuresponds


አሰላም አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱ ያጀማአ

ንፅፅር መማርና ማወቅ የሚፈልጉ እናም በእስልምና ላይ ለሚነሱ ሹብሀዎች መልሶች ለማግኘት ወይ ለመጠየቅ የሚፈልግ ሰዎች ይሄን ቻናል ተቀላቀሉ በቅርቡም አሪፍ ፕሮግራም የምንጀምር ይሆናል ተቀላቀሉ

ሼርም እያደረጋች የሂዳያ ሰበብ ሁኑ

ሙስሊምም ክርስቲያኑም ኢቲስቱም መቀላቀል ይችላል አላማው እውነታውን መማር ነው
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንደዚህ አይነት ውርደት በማንም አይድረስ😁
😁6