This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
(40) ማለት ይህ ነው።
6666 🥹😭😭😭😭
6666 🥹😭😭😭😭
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለጌታችን እና መድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በአል በሰላም አደረሰን። የትንሣኤው ብርሃን ከሰማይ እንደሚወርድ ያውቃሉ?
የትንሣኤው ብርሃን
እንኳን "ለብርሃነ ትንሣኤው" በሰላም አደረሳችሁ የተለመደ የትንሣኤ ሰላምታ ነው። በዚህ ሰላምታ ውስጥ "ብርሃነ ትንሣኤ" የሚለው ስለ የትኛው ብርሃን ይናገራል?
ይህ የትንሣኤ ብርሃን አባባል ብቻ አይደለም። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተቀበረበት መቃብር ላይ የተሰራ ቤተ ክርስቲያን አለ። ስሙም Church of Sepulchre ይባላል።
ይህ ቤተ ክርስቲያን በስድስት አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ባለቤትነት ያለ ነው። እነርሱም ( የግሪክ ኦርቶዶክስ ፣ የሮም ካቶሊክ ፣ የአርመን ኦርቶዶክስ ፣ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ፣ የሶርያ ኦርቶዶክስ እና የእኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ናቸው።)
በዚህ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ የኦርቶዶክሳውያን ትንሣኤ በዓል ዋዜማ ሰው ሳይለኩሰው በክርስቶስ መቃብር ላይ የሚበራ ተአምራዊ ብርሃን አለ።
ይህ ብርሃን ያበራል ግን አያቃጥልም። ይህንን የትንሣኤ ብርሃን ለማየት አባቶቻችን ትንሣኤ በየሩሳሌም ያከብሩ ነበር። ዛሬም የጉዞ ወኪሎች የትንሣኤ ኢየሩሳሌም ጉዞ ያዘጋጃሉ።
የትላንቱን የትንሣኤ ብርሃን CNN በቪድዮው ላይ በሚታየው መልኩ ከቦታው ዘግቦታል። እንደዛሬ እንዲህ በቪድዮ ማየት ከመቻላችን በፊት የትንሣኤ ብርሃን በተአምረ ማርያም ተጽፎ ሰማነው አነበብነው እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ በየዓመቱ ስለመታየቱ አይናገርም።
እግዚአብሔር ፈቅዶ ይኼንን በኢየሩሳሌም ተገኝተን ለማየት ያብቃን።
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።

❤2