እግዚአብሔር የሚወደው ጾም!
...
ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 58
1 በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።
2 ነገር ግን ዕለት ዕለት ይሹኛል መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ፤ ጽድቅን እንዳደረጉ የአምላካቸውንም ፍርድ እንዳልተዉ ሕዝብ እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ።
3 ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
4 እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
5 እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
6 እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
7 እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
8 የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።
9 የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፥
10 ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።
11 እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።
12 ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ።
13 ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥
14 በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።

❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
(40) ማለት ይህ ነው።
6666 🥹😭😭😭😭
6666 🥹😭😭😭😭
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለጌታችን እና መድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በአል በሰላም አደረሰን። የትንሣኤው ብርሃን ከሰማይ እንደሚወርድ ያውቃሉ?
የትንሣኤው ብርሃን
እንኳን "ለብርሃነ ትንሣኤው" በሰላም አደረሳችሁ የተለመደ የትንሣኤ ሰላምታ ነው። በዚህ ሰላምታ ውስጥ "ብርሃነ ትንሣኤ" የሚለው ስለ የትኛው ብርሃን ይናገራል?
ይህ የትንሣኤ ብርሃን አባባል ብቻ አይደለም። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተቀበረበት መቃብር ላይ የተሰራ ቤተ ክርስቲያን አለ። ስሙም Church of Sepulchre ይባላል።
ይህ ቤተ ክርስቲያን በስድስት አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ባለቤትነት ያለ ነው። እነርሱም ( የግሪክ ኦርቶዶክስ ፣ የሮም ካቶሊክ ፣ የአርመን ኦርቶዶክስ ፣ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ፣ የሶርያ ኦርቶዶክስ እና የእኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ናቸው።)
በዚህ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ የኦርቶዶክሳውያን ትንሣኤ በዓል ዋዜማ ሰው ሳይለኩሰው በክርስቶስ መቃብር ላይ የሚበራ ተአምራዊ ብርሃን አለ።
ይህ ብርሃን ያበራል ግን አያቃጥልም። ይህንን የትንሣኤ ብርሃን ለማየት አባቶቻችን ትንሣኤ በየሩሳሌም ያከብሩ ነበር። ዛሬም የጉዞ ወኪሎች የትንሣኤ ኢየሩሳሌም ጉዞ ያዘጋጃሉ።
የትላንቱን የትንሣኤ ብርሃን CNN በቪድዮው ላይ በሚታየው መልኩ ከቦታው ዘግቦታል። እንደዛሬ እንዲህ በቪድዮ ማየት ከመቻላችን በፊት የትንሣኤ ብርሃን በተአምረ ማርያም ተጽፎ ሰማነው አነበብነው እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ በየዓመቱ ስለመታየቱ አይናገርም።
እግዚአብሔር ፈቅዶ ይኼንን በኢየሩሳሌም ተገኝተን ለማየት ያብቃን።
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።

❤2