Repentance (ንስሓ)
304 subscribers
753 photos
29 videos
27 files
24 links
(መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ)
@repentmore
Download Telegram
Forwarded from aßeselom
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በሌሎች ቦታ ለመልቀቅ ይሄንን ቪድዮ መጠቀም ትችላላችሁ።
ይህንን ያውቁ ኖሯል?
.
የመዝወር ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ

# አድራሻ: በጉራጌ ክልል በምሁር-አክሊል ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ በደቡብ ምዕራብ አቅጠጫ በወልቂጤ መስመር 212 ኪሜ ይርቃል፡፡ ቤተክርስትያኑ በምሑር ገደም አቅራቢያ/ቀደም ብሎ/ በጨቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ የሚገኝ ታላቅ የበረከት ቦታ ነው፡፡

# ታሪክ: ቤተክርስቲያኑ ለመመሥረት ግንቦት 25 ቀን 1993 ዓ.ም በሀዲያ፣ ጉራጌና ከንባታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ መልካም ፍቃድና ትዕዛዝ በቆሞስ አባ ኪዳነ ማርያም መሪነት የመሠረት ድንጋይ የተጣለ ሲሆን ከብዙ ፈተና በኋላ የካቲት 30 ቀን 1994 ታቦተ ህጉ ወደ መንበሩ ገብቷል፡፡

ቤተክርስቲያኑ በአሁኑ ጊዜ በመልአከ ብርሃን ቆሞስ አባ ኢያሱ ሰብስቤ የሚተዳደር ሲሆን በእሳቸውም መሪነት ትልቅ ህንጻ ቤተክርስቲያን ተመስርቶ ከታላላቅ ገዳማት በማይተናነስ መልኩ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

በአሁን ጊዜ በደብሩ የሚከናወኑ ተግባራት:

1. ከ125 በላይ የአብነት ተማሪዎችን ሰብስቦ ሙሉ ወጪያቸውን ችሎ የሚያስተምር ሲሆን በደብሩ አራት ጉባኤ ቤቶች ማለትም የንባብ፣ የዜማ ፣ የቅኔ ፣ የአቋቋም እና የቅዳሴ ፣ እንዲሁም የበገና ትምህርት የሚሰጥ ሲሆን ቀሪ ጉባኤ ቤቶች ደግሞ በመገንባት ላይ ናቸው፡፡

የአብነት ትምህርት ፣ የቅዳሴ ፣ የዳዊት እና የበገና ትምህርት በOnline ጉባዔ መማር ለሚፈልግ በሀገርም ሆነ በውጪ ለሚገኝ ሰው በዚህ ስልክ ደውሎ መመዝገብ ይችላል። ( +251911467735 እና +251912488194 )

2. እንደ ገዳም ሥርዓት ዘወትር የማይቋረጥ የሌሊት ምስጋና ፣ ኪዳን ፣ ቅዳሴ ፣ መሐረነ አብ ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ትምህርትና የመሳሰሉት ይደረጋሉ፡፡

3. ለካህናት ማሰልጠኛ እና አጠቃላይ አገልግሎት የሚሆን ባለ አራት ወለል/G+3/ ሕንጻ እየተገነባ ይገኛል፡፡

አባታችን አባ ኢያሱ በወር ሦስቱን ሳምንት በገዳሙ ተገኝተው ሕፃናቱን እያስተማሩ እና የክህነት አገልግሎትን እየፈጸሙ ቆይተው በመጨረሻው ሳምንት ደግሞ አዲስ አበባ በመምጣት የንስሓ ልጆቻቸውን በየቤተክርስቲያኑ እየተዟዟሩ ንስሓ ይቀበላሉ። ከንስሓ ልጆቻቸውም አስራት ገንዘብ ይሰበስባሉ። ሴቶች የንስሓ ልጆቻቸውም ጤፍ ፣ ስንዴ፣ ሽሮ ፣ በርበሬ እና አትክልቶችን ያዘጋጃሉ።
በየወሩ የመጨረሻ ቅዳሜ ከጠዋቱ 3:00-6:00 ሰዓት ድረስ በብስራተ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የነዳያን ምገባ መርሐ ግብር ይከናወናል። አባታችን እና ንስሓ ልጆቻቸው ነዳያንን ይመግባሉ፣ ነዳያን ንስሓ ይገባሉ ፣ የአባታችን ንስሓ ልጆች የሆኑ ሐኪሞችም እዚያው ብስራተ ገብርኤል ተገኝተው ለነዳያን ነፃ የህክምና አገልግሎት ይሰጣሉ። ይኼንን በቦታው ተገኝቶ መሳተፍ እና በሀሳብ ፣ በጉልበት ማገዝ ለሁሉ ኦርቶዶክሳዊ ተፈቅዷል።

በየወሩ የመጨረሻ እሁድ አራት ኪሎ በአታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 7:00-10:00 ሰዓት ድረስ አባ ኢያሱ የንስሓ ልጆቻቸውን አጠቃላይ ጉባዔ ሰብስበው ፣ አስተምረው እና ባርከው ፣ በገዳሙ ለሚያድጉት ሕፃናት የተዘጋጀውን ቀለብ ጭነው ወደ መዝወር ገብርኤል ይመለሳሉ። ይህ የማይቋረጥ አገልግሎት ዘወትር ይከናወናል። አዲስ አበባ የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን አማኞች በአታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በወሩ የመጨረሻው እሁድ ተገኝተው መሳተፍ ይችላሉ።

መዝወር ገብርኤልን ልዩ የሚደርገው በኦሪት ዘጸዓት 13፣12 ‹‹ማሕጸን የሚከፍተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ይለይ….አስቀድሞ የተወለደው ለእግዚአብሔር ይሆናል›› ተብሎ በሙሴ በተነገረው ሥርዓት መሠረት ቤተክርስቲያኑ የበኩራት ልጆችን ተቀብሎ እያስተማረ ያሳድጋል፡፡ ካሉት የአብነት ተማሪዎች ውስጥ ከ14 የሚበልጡ በኩራት ልጆች ይገኛሉ። እነዚህ ልጆች የአባታችን ንስሓ ልጆች በ3/4 ዓመት እድሜ ለቤተ ክርስቲያን የሰጧቸው የበኩር ልጆች ናቸው። ዛሬ ሰው ከገቢው ከአስር እንዱን አስራት ለማውጣት በሚቸገርበት ወቅት የአባታችን ንስሓ ልጆች የበኩር ልጆቸውን ለቤተ ክርስቲያን እየሰጡ ነው። ይህንን ተአምር በዚህ ዘመን ማየት አይደለም መስማት መታደል ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረበት ሰው በቀር ይህንን ማን ሊያደርገው ይችላል?

መዝወር ገብርኤል አገልግሎቱ እየሰፋ ነው። የካህናት ማሰልጠኛ እና አጠቃላይ አገልግሎት መስጫ G+3 ሕንፃ በመገንባት ላይ ይገኛል። ይኼንንም አገልግሎት ለማገዝ ለአጠቃላይ ኦርቶዶክሳዊያን ጥሪ ያስተላልፋል።

# አባታችን አባ ኢያሱን አግኝቶ ምክር ለመጠየቅ ፣ በሀሳብ ለማገዝ እንዲሁም በርቱ ለማለት በስልካቸው መደወል ይቻላል። (+251912488194)

# መዝወር ገብርኤል የግልም ሆነ የጋራ ጉዞ ለማድረግ አድራሻው:
- ከመርካቶ አውቶብስ ተራ "ጅማ-ወለኔ" በሚለው አውቶብስ ቀጥታ ጉዞ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ መውረድ ይቻላል።
- በግል ጉዞ ለማድረግ በወልቂጤ በኩል ወደ ምሑር ኢየሱስ በሚወስደው መንገድ መሄድ ይቻላል። በቱሉ ቦሎ በኩልም አዲስ አቋራጭ መንገድ አለው። በGPS እየተመሩ ለመሄድም አድራሻው ይህ ነው። ( https://maps.app.goo.gl/CLXkf7bFkxrBRLkE8 )

# አጠቃላይ አገልግሎቶችን በገንዘብ ማገዝ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው በሚከተሉት የንግድ ባንክ አካውንቶች መጠቀም ይቻላል።

- 1000225277269 መዝወር ደ/ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን።
- 1000238217079 አባ ኢያሱ ሰብስቤ (mobile banking አማራጭ አለው)
- 1000003676467 አባ ኢያሱ ሰብስቤ።

የቤተ ክርስቲያኑን ታሪክ ለማንበብ (https://www.hawirethiopia.com/am/destination/42)


# በመዝወር ገብርኤል የሚከበሩ ዓመታዊ ክብረ በዓላት
1. መስከረም 2 (ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕትነትን የተቀበለበትን/ አንገቱ የተሰየፈበትን ምክንያት በማድረግ/ 2. ታህሳስ 19 (መልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል ሦስቱን ሕጻናት ማለትም አናንያ፣ አዛሪያና ሚሳኤልን ከእሳት ያዳነበትን ቀን ምክንያት በማድረግ)፡፡
3. ሰኔ 30 (የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን በዓለ ልደት ምክንያት በማድረግ)
4. ሐምሌ 19 (መልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ያደነበትን ቀን ምክንያት በማድረግ) ፡፡
5. ከነሐሴ 1-16 ደግሞ የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታን ምክንያት በማድረግ ሙሉ ጾሙ ሱባኤ ይኖራል፡፡

# በዩቲዩብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:

* አባ ኢያሱ መልካሙ እረኛ ማህበረ ቅዱሳን ( https://youtu.be/--3UWB1zQss?si=EswHSJgEK9z3sWBb )

* የአብርሃም እንግዳ ማህበረ ቅዱሳን ( https://youtu.be/ZR_40nUvxA0?si=3cFpoPq5clcYBuE- )

* መሰቀል 2018 በጉራጌ ማህበረ ቅዱሳን ( https://youtu.be/cwhE8NnATAo?si=kHQh_2XoqyZYWfdn )

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፣ ወለወላዲቱ ድንግል ፣ ወለመስቀሉ ክቡር።