የነቃ ትውልድ Tube
15.4K subscribers
106 photos
13 videos
3 files
389 links
" ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤..." 1ጴጥ 4፣11።

የዚህ ቻናል ዓለማ ትውልዱ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ጠንካራና ከዚህ ዓለም ክፋት እርቆ በቅድስና እግዚአብሔርን በሚያከብር
ሕይወት እንዲኖር ማድረግ ነው።

ለጥያቄ እና አስተያየት 👉 @CHRISTIAN_NEGN1 ተጠቀሙና አድርሱኝ!
Download Telegram
‼️ፈተና!

በሕይወት ስንኖር ሰው ነንና ለሰው የሚደርስ ፈተና ይደርስብናል። በዚህ ዓለም እስካለን ከዚህ ልናመልጥ አንችልም። ነገር ግን አንድ ጌታ አለን። አይዞአችሁ የሚለን። ድካማችን የሚገባው። በአብ ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ ዘወትር የሚማልድ።

ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ስለሆነ አንተክዝ። በእርሱ እንታመን። ኢየሱስ ይመጣል።
🙏3😍1
We should check our motives that intiate to do what we do.

It matters above the things done.

Including Prayer !
👍1😍1
🔹በእግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ ራሳችንን ሆነን እንቅረብ። አናስመስል።

Never !
🙏1😍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢየሱስ የነገስታት ንጉሥ
2🔥2💯2
#ምክር_ለወጣት_አገልጋዮች

ስሙኝ የአባቴ ብሩካን እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ትልቅ ስራ ልሰራ ፕሮግራም በያዘው ልክ አጋንንትም ከዚህ ፕሮግራም ለማውጣት ዕቅድ ይይዛል ስለዚህ የምታደርጉትን እያንዳንዱን ነገር እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ነገር ላይ አንተ አለህበት ወይ ማለቱ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው።

ዛሬ ላወራ የፈለኩት ለወደፊት የትዳር ሕይወታችሁ የምትመርጡትን ሰው እንድትላዩ ነው።
የማትጸልይ፣ ለእግዚአብሔር ቃል ጊዜ የሌላት፣ መንፈሳዊ ነገር ቀሎ የሚታይበት፣ ቤተክርስቲያን የማትሄድ፣ ለአገልጋዮች ክብር የሌላት፣ ከመንፈሳዊ ነገሮች ይልቅ ለዓለማዊ ነገር ጊዜ የምትሰጥ ማለትም ለመዝናናት፣ ለመዞር፣ ድራማ ለማየት፣ በቃ በየቀኑ Enjoy እናድርግ የምትል።
ወንድሜ በጭራሽ እንደዚህች አይነት ሴት የሕይወት አጋር አታድርግ። ዛሬ ላይ በአገልግሎት ትልቅ ስራ እየሰሩ ካሉት አገልጋዮች ጀርባ ጠንካራ የጸሎት ሴት ከኃላ እንዳለች አትርሳ።
በአንተም ሕይወት ነገ ላይ ለአገልግሎትህ ውድቀትም ሆነ ስኬት የሚስትህ ድርሻ የአንበሳውን ቦታ እንደሚይዝ አትርሳ። ከትዳሯ በላይ ለእግዚአብሔር ስራ ስፍራ የሚትሰጥ ሴት የሕይወትህ አጋርህ ትሁን።
የአንተ እጮኛህ አገልጋይ መሆንህን መቀበል አለባት ።
ሲቀጥል የአገልጋይ ሚስት መሆን ቀላል አይደለም ። እንደ ሌሎች ሚስቶች ብቻም አይደለም ።
የአገልጋይ ሚስት ለመሆን መስዋዕትነት ለመክፈል ፈቃደኛ መሆንን ይጠይቃል።

ዛሬ ላይ የት ይደርሳሉ የተባሉ አገልጋዮች በስህተት ከማይሆን ሰው ጋር አንድ ላይ ሆኖ የማይወጡት ቁልቁለት ላይ ወድቀዋል ውስጣቸው ላይ የነበረው ለዓለም መድሀኒት የሚሆን ራዕይቸው መና ሆኖል። እግዚአብሔር ከያዘላቸው ትልቅ ፕሮግራም መስመር ወጥቶ ብዙ ስቃይ እያዩ ነው። ስለዚህ ወንድሜ ከማን ጋ ነው ግንኙነት ውስጥ ያለከው? ከማን ጋርስ  ነው ግንኙነት ለመጀመር እያሰብክ ያለከው?

ልብ በል የነገ ሚስትህ ለማቆምም ለመውደቅም ምክንያት ትሆናለች።

በአጠቃላይ የትዳር አጋርህን ቃሉ
ዘፍጥረት 2:18 "ረዳት " ነው የሚለው።
✔️ በአገልግሎት ረዳት
✔️በስራ ረዳት
✔️በቤተክርስቲያን ረዳት
✔️በጥሪ ረዳት
✔️በራዕይ ረዳት
✔️በፀሎት ረዳት
✔️በአምልኮ ረዳት
✔️በስብከት ረዳት
✔️በህይወት ረዳት
✔️በፆም ፀሎት ረዳት
✔️በገንዘብ ረዳት
✔️በሀሳብ ረዳት ነው የሚያስፈልገው ።
እግዚአብሔር አምላክ እውነተኛ "ረዳት "ይስጣችሁ!!!

እህቶች ይሄ ምክር ለእናንተም ይሆናል።

“ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት።”
  — ምሳሌ 12፥4

.      #እወዳችኋለሁ
ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ


እኔን ለማገኘት @abit9 @abit9


sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
4👍1🎉1🙏1😍1
.              #ተረጋጉ

#ይህ_መልዕክቴ_ያለ_ጊዜ_ወደ_ፍቅር_ግንኙነት_ለመግባት_ለሚሮጡ_ወጣቶች_ይድረስልኝ

አንድ ወጣት ልጅ ነበር፡፡ በትምህርቱ ጎበዝ ነው፤ መልኩም ያማረ ነው:: ቤተሰቡ «ይህ ልጅ የት ይደርሳል?» ብለዉ በጉጉት ይጠብቁት ነበር። የአካባቢው ሰዎችም ጭምር «ይህ ዘራችንን በመልካም ነገር ያስጠራል» በማለት ተስፋ ያደርጉ ነበር፡፡ እርሱም በመጀመሪያ ትኩረቱ በትምህርቱ ላይ ብቻ ነበር፡ በአካባቢው ያሉ ቆንጆ ሴቶች ግን እርሱን ለማጥመድ ይፈልጉ ነበር:: በተለይ ዋርሳው የሆኑ ሴቶች በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እርሱን ለማጥመድ ይፈልጉታል፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በአንዷ እጅ ወደቀ፡፡ በእርሷም ፍቅር ተነደፈ:: ከዚያ በኋላ ደግሞ ሌሎች ሴቶችን አዳረስ:: የስምንተኛ ክፍል ጨርሶ ወደ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሄድ አልፈለገም:: የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እርሱ ከሚኖርበት ሩቅ ስለነበር ከቤት ተመላልሶ መማር አይችልም:: ስለዚህ ወደ ሌላ ከተማ መሄድ ነበረበት፡፡ እነዚያ ሴቶች እያንዳንዳቸው «እኔን ትተህ እንዴት ትሄዳለህ? ካላንተ መኖር አልችልም» ብሎ ልቡን ሰረቁት፡፡ እርሱም የእነርሱን ሐሳብ ስምቶ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ሠፈር ተመለሰ፡፡ እንደ እርሱ ጎበዝ ያልነበሩ ልጆች ትምህርታቸውን ቀጠሉ፡፡ አንዳንዶች ኮሌጅ የመግባት ዕድል አገኙ፡፡ እርሱ ግን እርሻ ማረሰ ጀመረ:: ዕድሜው ሃያዎቹ አጋማሽ ሲሆን ትዳር መሠረተ:: ልጆችን ወለደ፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩ ልጆች ተምረው መምህራን ሆነው እርሱ ይማርበት ወደ ነበረበት ትምህርት ቤት ተመድበው መጡ፡፡ ሰውየውም ይህን ሲያይ በሕይወቱ አንድ ትልቅ ስህተት እንደሠራ ተገነዘበ፡፡ አሁን ለመማር ያለው ዕድሉ ዝግ ሆኖበታል፡፡ ሚስቱንና ልጆቹን ለማን ትቶ ትምህርት ቤት ገብቶ ይማር! አሁን ያለፈውን ነገር ማሰብ እንጂ ማድረግ አይችልም::

አያችሁ አይደል ያለ ጊዜ ወደ ፍቅር ግንኙነት መግባት በጣም ብዙ ችግሮች አሉ ለዚህም የባለታሪኩ ልጅ ሕይወት ከበቂ በላይ ምስክር ነው። መግባት በጣም ቀላል ነው ነገር ግን በእሱ ምክንያት ከሚመጣው መዘዝ ማውጣት ደሞ ስቃይ ነው።  ስለዚህ እባካችሁ ተረጋጉ ሁሉም ነገር በጊዜው መድረሱ አይቀርም።
በተለይ በትምህርት ገበታ ላይ ያላችሁ ወጣቶች የእናንተ ትኩረት ትምህርትና መንፈሳዊ ሕይወታችሁ ላይ ብቻ ይሁን። ዕድል ከገኘችሁም ስራ በመስራት ላይ አድርጉት። ከዚያ ውጪ ቶሎ ብላችሁ ወደ ፍቅር ሕይወት አትግቡ። እናንተ ያላችሁበት የብቸኝነት ጊዜ ለነገ ሕይወታችሁ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን የምታዘጋጁበት ጊዜ ነው። ይሄንን ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር ከየትኛውም ሕብረት እና ግንኙነት ይልቅ ከእርሱ ጋር ብቻ እንድታሳልፉ ይፈልጋል።
የብቸኝነት ጊዜያችሁን በደብ ተጠቀሙበት እናንተ ዕድለኞች ናችሁ።

.           #ጨረስኩ

👤ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👤

🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ

inbox me 👉 @abit9 


https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
3🥰2😍2👏1
ቸኮለብኝ ልቤ ሊያገኝህ
ይድነቃቸዉ ተካ
ማርከን ዜማ @Markengeta
Yidnekachew Teka - ቸኮለብኝ

ሌላ ነገር ታገስ ብትለኝ
ጠብቃለሁ እስኪሆንልኝ
ግን አባቴ ለክብርህ ነገር
በህልውናህ ውሎ ለማደር

አዝ:- ቸኮለብኝ ልቤ ሊያገኝህ
እንዴት ብዬ ኢየሱስ ልያዝህ
ናፍቆቴ ነህ የሁሌ አምሮቴ
አንተን ማየት ክብርህ ጉጉቴ (፪x)

ኢየሱስ ዓይኔ በርቶ አንዴ ልይህ
ኢየሱስ ውስጤ ራበኝ እስከምነካህ
ኢየሱስ እኔ አልችልም መኖር ካለዚያ
ኢየሱስ በሌለበት ክብርህ ህልውናህ (፪x)

አዝ:- ቸኮለብኝ ልቤ ሊያገኝህ
እንዴት ብዬ ኢየሱስ ልያዝህ
ናፍቆቴ ነህ የሁሌ አምሮቴ
አንተን ማየት ክብርህ ጉጉቴ (፪x)

አንተን ማየት ክብርህ ጉጉቴ
አባትዬ ፊትህ ጉጉቴ
ኢየሱሴ ክብርህ ጉጉቴ
አባትዬ ክብርህ ኢየሱሴ

ኢየሱሴ የነካው ሰው
ኢየሱስን በዓይኑ ያየ ሰው
ኢየሱሴ የገባው ሰው
ኢየሱስን በዓይኑ ያየ ሰው
ለሌላ ነገር መኖር አይችልም (፪x)
ለፈለገው ነገር መኖር አይችልም
ለፈለገው ነገር መኖር አይችልም (፪x)

የመቅደስን ደጅ የሚጠኑ
ብዙ ናቸው አንተን የሚሹ
አምላክህን አሳየኝ ሚሉኝ
ክብሩ የታል እስኪ አሳውቀን

ወዴት ልበል የት ጋር ነህ ውዴ
በእኔ ዘመን ይረፍ ትውልዴ
ከእኔ ውጪ የትም አልጠቁም
በእኔ ላይ ና እስኪያይህ ሁሉም (፪x)

ኢየሱስ ዐይኔ በርቶ አንዴ ልይህ
ኢየሱስ ውስጤ ራበኝ እስከምነካህ
ኢየሱስ እኔ አልችልም መኖር ካለዚያ
ኢየሱስ በሌለበት ክብርህ ህልውናህ (፪x)

የጭንቅ ነው ስጠራህ ውዴ
የውስጤን ምጥ ቃላት ሰብስቤ
ቢነግርልኝ የልቤን ጩኸት
የጥማቴን የርሃቤን ልክ



ክብሩን የተራቤ/ተሃድሶ የሚፈልግ ይስማ😭😭😭



https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
🔥41🙏1
#የነቃ_ወጣት

የነቃ ወጣት የሚያደርገው እግዚአብሔር አድርግ ያለውን ነው። እግዚአብሔር ተዋደዱ ስላለን እርስ በእርስ መዋደድ ። በእኔ ተስፋ አድርጉ ስላለን በእርሱ ተስፋ ማድረግ። ዳግም የሚመጣውን ክርስቶስን በጉጉት መጠበቅ። ባጠቃላይ የነቃ ወጣት የመንፈስ ፍሬ ይታይበታል(ገላ 5፣22-23)። የሚረዳም መንፈስ በውስጡ አለው።

የነቃ ወጣት እግዚአብሔር ቶው ያለውን ይተዋል። ወንድሙን አይጠላም። ከዝሙት ይሸሻል። ባጠቃላይ የሥጋን ሥራ አያደርግም(ገላ 5፣19-21)።

እግዚአብሔር በታሪክ የሚቆጣው አድርግ ያለውን ባለማድረግ እና አታድርግ ያለውን በማድረግ ነው።



@ReformationNeeded
@ReformationNeeded
@ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
2👍1
እንዳልበድልህ ጠብቀኝ !
2🙏1
‎            #አግቢኝና_ጌታን_እቀበላለሁ

‎መንፈሳዊ ድርድር ወይስ የፍቅር ወጥመድ?

‎ብዙ ጊዜ አንዲት ወጣት (ወይም ወጣት) አማኝ ያልሆነን ሰው ስታፈቅር፣ ያ ሰው ግንኙነቱን ለማጽናት የሚጠቀምበት ትልቁ "ካርድ" ይህ ነው፦ "ካገባሽኝ እኔም ያንቺን ሃይማኖት እቀበላለሁ፤ አንቺ ባለሽበት እሆናለሁ" ይላል። ይህ ንግግር ለሰሚው "ነፍስን ወደ ጌታ ማምጣት" ቢመስልም፣ በውስጡ ግን ትልቅ መንፈሳዊ አደጋ አለው።

‎1. #የልብ_መለወጥ (Repentance) በሰው አይገዛም!:- ጌታን መቀበል የግል ውሳኔ እንጂ ለፍቅር ተብሎ የሚደረግ "ኮንትራት" (ውል) አይደለም።

#እውነታው፦ አንድ ሰው ጌታን መቀበል ያለበት ስለ ኃጢአቱ ተጸጽቶና የጌታን አዳኝነት አምኖ እንጂ፣ አንቺን ለማግኘት ብሎ መሆን የለበትም። (ልብ በሉ ሰው በእኛ ምክንያት ጌታን አይቀበል እያልኩ አይደለም ነገር ግን የልቡ motive ለእኛ ብሎ ነው ወይስ የምርም የክርስቶስ ፍቅር ገብቶት?)

#ምሳሌ፦ እንደ "መሸጫ ሱቅ" አስበው። አንዱን ዕቃ ለመግዛት ሌላውን በነጻ እንደማግኘት (Buy one get one free)፣ አንቺን ለማግኘት ጌታን "በነጻ" እንዲቀበል መገፋፋት የጌታን ክብር ዝቅ ማድረግ ነው።

‎2. "#ሁለት_የማይገጥሙ_ቀንበሮች"
‎መጽሐፍ ቅዱስ "ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ" (፪ኛ ቆሮ. ፮፥፲፬) ይላል።

#ችግሩ፦ እርሱ ጌታን የተቀበለው አንቺን ፈልጎ ከሆነ፣ አንቺ ላይ ያለው ስሜት ሲቀዘቅዝ ወይም በትዳር ውስጥ ግጭት ሲፈጠር፣ አብሮት የተቀበለው "ጌታ" ትርጉም ያጣበታል። ምክንያቱም መሠረቱ ክርስቶስ ሳይሆን "አንቺ" ነሽ።

#ምሳሌ፦ እንደ "ሁለት የተለያዩ ፍጥነቶች" አስበው። አንደኛው በሰማያዊ ባቡር፣ ሌላኛው በምድራዊ መኪና እየተጓዘ አብሮ ለመሄድ መሞከር መጨረሻው አደጋ ነው።

#‎3_የንግሥት_ኤልዛቤልና የአክዓብ "Mission"
‎አንዳንዶች "እኔ እለውጠዋለሁ/እለውጣታለሁ" በሚል ስሌት ይገባሉ። ነገር ግን ብዙ ጊዜ የሚሆነው ተቃራኒው ነው።

#ባህሪው፦ ትዳር ውስጥ ከገባችሁ በኋላ "አሁንማ አግብቼሻለሁ፤ የፈለግኩትን ባደርግ መብቴ ነው" የሚል መንፈስ ሊመጣ ይችላል። ያኔ አንቺን ከቤተክርስቲያንና ከጸሎት ሕይወትሽ ማራቅ ይጀምራል።

#ምሳሌ፦ እንደ "ጨውና ውኃ" አስበው። ንጹህ ውኃ ውስጥ ብዙ ጨው ብትጨምር ውኃው ጨው ይሆናል እንጂ ጨው ውኃ አይሆንም። የዓለም ተጽዕኖ በቤታችሁ ላይ ከበረታ መንፈሳዊነትሽን ሊያጠፋው ይችላል።
#ለወጣቶች_የሚሆን_የመፍትሔ_ምክር

#ቅድሚያ ለጌታ ይሁን፦ ያ ሰው በእውነት ጌታን መቀበል ከፈለገ፣ ካንቺ ጋር ግንኙነት ሳይጀምር በፊት በራሱ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ይሂድ፣ ንስሐ ይግባና ክርስቲያናዊ ሕይወቱን በተግባር ያሳይ።

#ምስክር ሁኚለት እንጂ ዋስትና አትሁኚው፦ ወንጌልን ንገሪው፣ እንዲጸልይ አበረታቺው፤ ነገር ግን "ካልተቀበልክ አላገባህም" የሚል የድርድር ፍቅር ውስጥ አትግቢ።

#ትዳር "የወንጌል ማስፋፊያ" ሜዳ አይደለም፦ ትዳር የአንድ ዓላማና የአንድ መንፈስ ሰዎች ጥምረት ነው። "ትለወጣለች" ወይም "ይለወጣል" በሚል ግምት ወደማይታወቅ ጨለማ አትዝለል።

#ማጠቃለያ:-አንድ ሰው ጌታን መቀበል ያለበት "ገነትን" ሽቶ እንጂ "አንቺን" ሽቶ መሆን የለበትም። በሰው ፍቅር ላይ የተገነባ መንፈሳዊነት ሰውየው ሲጠፋ አብሮ ይጠፋል። በአለት (በክርስቶስ) ላይ ያልተመሠረተ ቤት ደግሞ ንፋስ ሲመጣ መውደቁ አይቀሬ ነው!

ማንኛውንም ሀሳብ በኮሜንት መስጫ ላይ በነጻነት ማውራት ትችላላችሁ

‎.      #እወዳችኋለሁ
🤵ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ🤵


እኔን ለማገኘት @abit9 @abit9



@ReformationNeeded
@ReformationNeeded
@ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
4🔥1🥰1
2018 ቀላል አልነበረም

        🌻አንድ አመት🌻
         🌻12 ወራት🌻
       🌻52 ሳምንታት🌻
        🌻365 ቀናት🌻
     🌻8760 ሰዓታት🌻
   🌻525,600 ደቂቃዎች🌻
   🌻3,153,600 ሰከንዶች🌻

ድፍን አንድ ዓመት በእግዚአብሔር ምሕረት ብቻ ክብር ከዘለዓለም እስከ ለዘለዓለም ለእርሱ ብቻ ይሁን 🙏🙏


https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
🙏3🥰21
🌻🌻ቸር ስለሆነ ምህረቱም ለዘላለም ስለሆነ ዛሬን አየን። ክብር ክብር ለእርሱ ብቻ ይሁን🌻🌻

1/1/2019 ዓ ም።

መዝሙር 124፣1-8
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን፡
እስራኤል እንዲህ ይበል፦

“እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን፡
ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥
በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤

በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥
በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤
በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።

ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ።

ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች። ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።

ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ፡
በእግዚአብሔር ስም ነው።”


🌼🌼እንኳን አደረሳችሁ Family🌼🌼


@ReformationNeeded
@ReformationNeeded
@ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
1
📌ማነው በራሴ ለዛሬ ደረስኩ የሚል? የለም አይደል? ስለዚህ ላሻገረን ክብርን እንስጥ።

መልካም አድስ ዓመት። 2019 ዓ.ም።
🙏5
ሰላም ውዶች🙏

ልብ አንጠልጣይ የሆነና ብዙዎችን ያስለቀሰ ከራስ ጋር ትግል የምል ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ ወደ እናንተ መቅረብ ልጀምር ነው የዚህ ልብወለድ ዋናው መልዕክት  
አዎ ከራስ ጋር ትግል!!
1. ጓደኝነት ምን ማለት ነው?ፍቅር ምንድነው?
2. ስንት አይነት ጓደኛ አለ? ማስመሰል ምንድነው?
3.ከራሳችንን ጋር እንዴት ልንታገል እንችላለን?
4.ፀፀት እና ሌሎችም ነገሮችን የያዘ

እነዚህን ሁሉ የያዘ ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ በቅርቡ ጠብቁ

ይሄ ልብወለድ ይጀምር የምትሉ ሀሳባችሁን በኮሜንት መስጫ ላይ ጻፉ👇👇
8🙏5😍1
ከራስ ጋር ትግል ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ ተጀመረ

🤦‍♀ ከራስ ጋር ትግል🤦‍♀  
📖ተከታታይ ልብወለድ📖  
   ምዕራፍ=አንድ     
    ክፍል=1  

ሰላም ሜሮን እባላለሁ የምኖረው በውቢቷ ከተማ ሀዋሳ ነው የ11 ክፍል ተማሪ ነኝ የምኖረው ከእናቴ እና ከአባቴ ጋር እና ከታላቅ እህቴ ጋር ነው ብዙ ሰው ከእህትሽ ጋር መንታ ናቹ ይሉናል ግን የ 2 አመት ታላቄ ናት ሶሲዬ በዚህ አመት Enterance ተፈታኝ ነች የምናመልከው ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ሲሆን የሶሎ ዘማሪ እና ኳይር ነን 3 የልብ ጓደኞች አሉኝ ናሆም ቢኒያም እና ሊዲያ ሶስቱም አብሮ አደጎቼ ናቸው እነሱ ማለት ለኔ ከምናገረውና ከምገልፀው በላይ የሆኑ ሰዎች ናቸው ግን ከሊዱ ጋር ለየት ያለ ነው  የሊዱዬ እናት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በህፃንነቷ ጥላት ሄዳለች የምትኖረው ከእናቷ እህት ከአክስቷ ጋር ነው አክስቷ ደግሞ አዲስ አበባ ቤተሰብ ስላላት ብዙም ሀዋሳ አትሆንም በዛ ሰአት ሊዱ እኛ ቤት ትሆናለች ሊዱ ትክክለኛ እህቴ እንደሆነች ሲነገረኝ ነው ያደኩት ብቻ ግን እነሱ ማለት የህይወቴ አንድ ክፍል ናቸው. ዛሬ ቀኑ ቅዳሜ ነው እናም ክላስ ስለሌለ የሌለ ለጥ ብያለሁ ከዚያም "ቁርስ ይለፍሽና አንድ ፊቱን ከምሳ ጋር ትበያለሽ" የሚል ድምፅ እና ሳቅ ሰማሁና አይኔን ስገልጥ እማ እና ሶሲ ናቸው "አሁን አንቺ ሞልቶልሽ ቀድመሽ ተነሳሽና እኔ ላይ ሙድ መያዝሽ ነው" አልኳት በጣም አናዳኝ በነገራችን ላይ ቀድማኝ ተነስታ አታውቅም😁 "ከዚያም አይ ጎሎብኝ ነው" አለችኝ እየሳቀች እኔም ለእሷ እልህ ብዬ ተነሳሁ እና ቁርስ ቀርቦ ስለነበር ፊቴን ተጣጥቤ ወደ ሳሎን ሄድኩ እናም እማን ""እማዬ!!" ብዬ ሳምኳት ደስ እያለን በጥሩ ሁኔታ ቁርስ በላን እናም ቡና ጠጥተን ወደየ ስራችን ገባን ያው የቅዳሜ ስራ ትንሽ ያደክማል ግን ደስ የሚል ነገር አለው እኔ ሙሉ ቤቱን አፀዳሁ ሶሲ ልብስ አጠበች እማ ምሳ እያዘጋጀች የእናት አንጀት ሆኖባት ""ቆይ ቆይ አትችሉም" እያለች በእንስፍስፍ አንጀቷ እየሳሳችልን ሰራን እማይዬ በጣም በልጅነቷ ነው ከአባ ጋር የተጋቡት እናም እኛንም በለጋ እድሜዋ ነው የወለደችን ብዙ ሰው እናቴ ነች ስላቸው ይገረማሉ አባቴንም እንደዛው አባ ከእኛ ተለይቶ መሄድ ስለማይወድ ስብሰባ እና የተለያዩ እኛ የማንሄድባቸው ቦታዎች እስከሆኑ ድረስ እንጂ ከዚያ ውጭ አብረን ነው ምንንቀሳቀሰው ስራችንን እንደጨራረስን  ሶሲ ደከመኝ አለች እና ሶፋ ላይ ጋደም አለች እኔም በሁኔታዋ ተገርሜ "እረ ቸርች ረፍዷል" ብዬ ጮኩባት "ባክሽ ገናነው አይዙርብሽ" አለችኝ የባሰ እየተመቻቸች እኔም ተናድጄ "ምን አገባኝ ማታ በቅጣት ብዛት አንጎልሽ ሲዞር አይ የለ" ብዬ ተውኳት ወዲያውም  "ሰላም ለዚህ ቤት" የሚል ድምፅ ሰምቼ ስወጣ አባቴ ነው ""ሰላምህን ተቀብለናል"" ብዬ የያዘውን ቦርሳ ተቀበልኩት እና ገባን አብረን ተሰባስበን የምሳ ሰአት ቢያልፍም ምሳችንን በላንና አባዬ "አትሄዱም አረፈደም? አለን እና ሶሲ እያቅማማችም ቢሆን ብታረፍድ የሚከተላትን ቅጣት ስለምታውቅ እሺ ብለን ልብሳችንን ቀያይረን ወጣን  መንገድ ላይ ጓደኞቻችንን ስናገኝ ስናወራ አሁንም ስናገኝ እኔ ባላየ እያለፍኩ ሶሲ ስታናድደኝ እንዲህ እንዲህ እያልን እየተጨቃጨቅን "ዘና በይ የሀበሻ ቀጠሮ አይደል!!" አለችኝ ቀስ ብላ እያየችኝ "እስቲ ሙች በይኝ" አልኳት በጣም በንዴት ሁልጊዜ ጉዟችን እንዲህ ነው እያረፈድን እኔ እየተናደድኩ ግን አብዛኛው ጊዜ የምሄደው ከእነ ቢኒ ጋር ነው ያው አይደረስ የለ ደረስን ስንገባ ልምምድ ተጀምሯል እኛም ፀለይንና ጀመርን በጣም  አሪፍ ጊዜ ነበር ከዚያም አሰልጣኛችን አመስግና ጨረስን ልክ እንደጨረስን ሁሉም ወደኛ ዞሩ ልክ ሲያዩኝ "የለሁበትም" አልኩ ወዲያው በእኔ ሁኔታ ተገርመው ወደ ሶሲ ዞር አሉ "እቀጣለሁ" አለች እና አስኮናኞች ብለው ስቀውብን ሰላም ተባባልን በእኛ ህብረት ውስጥ  ያለው ደስ የሚል  እውነተኛ ፍቅር ነው  በጣም ደስ የሚል ህብረት😊 ሁለተኛ ግን እንዳይደገም እያሉን ወጣን እናም ወደ ቤት ጉዞ ጀመርን መንገድ ላይ ስንጨዋወት ስለ ኳይራችን ስለ ህብረታችን እየተወያየን ምን ማድረግ  እንዳለብን መች እንደምናገለግል እናም ስለቀሩት ወገኖቻችን እያሰብን እንደተለመደው ወደ ቤታቸው በመሄድ ማበረታት እንዳለብን እየተወያየን እኛ ቤት ደረስን እና እኔና ሶሲ ተሰናብተናቸው ገባን ልክ እቤት እንደደረስንም እማ እማ እያልን በጣም መጮህ ጀመርን. . . . . . .

#ይቀጥላል ......


https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
2👍1😍1
♦️ማንም ልመልሰው የማይችለውን ጥያቄ የእግዚአብሔር ቃል ይመልሳል።

ወጣት፤ ቃሉን እናጥና ፣እናሰላስል ፣እናውራ፣ እንኑሪ።
1
#እጮኝነት

እጮኛ ማለት እጩ ባል ወይም እጩ ሚስት ማለት ሲሆን ለወደፊት በትዳር  አንድ ላይ ለመኖር በሚያስቡ በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል የሚመሰረት ጤናማ ሕብረት ነው እነዚህ ሰዎች በሚኖራቸው ጊዜ እርስ በእርሳቸው የሚጠናኑበት ይበልጥ የሚግባቡበት ስለ ግንኙነታቸው የሚፅልዩበት ስለ ወደ ፊት ሕይወታቸው የሚያቅዱበት ጊዜ ነው::

#እጮኛ_የሌላችሁ_ሰዎች:-

ለወደፊት ለሚኖራችሁ የእጮኝነት ሕይወት በጌታ ጊዜ ሰጥታችሁ በደንብ ፅልዩ እሺ እግዚአብሔርን ያማከሩበት ነገር ሁሌም መጨረሻው ያማረ ነው። ሌላው ራሳችሁ ላይ ስሩ ይሄን ስል የወደፊት አጋራችሁ ቢኖረው ብላችሁ የምታስቡት ማንነት የሕይወት አቋም አለ አይደል ያንን ነገር በምትችሉት ሁሉ እናንተም ለማሟላት ጣሩ እግዚአብሔርም እኮ ለእነሱም አባት ነው መልካም የሚለውን ነገር ነው ሊያደርግላቸው የሚፈልገውና የወደፊት የሕይወት አጋራችሁ የሚገባውን አይነት ማንነት ለመያዝ ራሳችሁ ላይ ስሩ::
ለምሳሌ የሚጸልይ ሰው የምትፈልጉ ከሆነ እናንተም የጸሎት ሰው ሁኑ።
በቅድስና የሚመላለስ ከሆነ እናንተም በሁሉ ነገር ተቀደሱ።
ድንግል ከሆነ እናንተም ድንግልናችሁን ጠብቁ። ዛሬ እንደፈለጋችሁ እየሆናችሁ ነገ ምንም ያልተነካ ሰው ነው የሚፈልገው ማለት የመጨረሻ ሞኝነት ነው። ድንግል ሴት ለድንግል ወንድ ነው አለቀ።
ስለዚህ እናንተ የምትፈልጉት ነገር እንዲኖረው የምትፈልጉ ከሆነ ያንን ነገር ቀድማችሁ እናንተም ያዙ።

#እጮኛ_ያላችሁ_ሰዎች:-

ይሄ ግንኙት የእግዚአብሔር ፈቃድ ያለበት ከሆነ በመጀመርያ የምር እናንተ በማንነታቸው ከልባችሁ ውደዷቸው ታማኝ አፍቃሪ ሁኑላቸው ትዕግስተኛና ግልፅ ሁኑላቸው በምትችሉት ሁሉ ከጎናቸው ሁኑላቸው የይቅርታ ልብ ይኑራችሁ ላላችሁበት ግንኙነት ለመልካም ነገር የምትደክሙ ሁኑ ግንኙነታችሁን ከማንም ጣልቃ ገብነት ጠብቁት ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ነገር ካልመጠ በቀር። ጥፋታችሁን እመኑ አንዳንዴም ዝቅ ብላችሁ አሳልፉ እሱ ካልደወለ አልደውልም ቴክስት ካልመለሰች አልመልስም አይባልም እሺ በዚህ ግንኙነት ውስጥ መቻቻል አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው ። እሺ ለሚወዱት ለሚያፈቅሩት ሰው showing up everyday is bare minimum ሌላው ውሸት አለመከባበር የማን አለብኝ ስሜት የግልፅኝነት ችግር አይኑርባችሁ በመጨረሻም በአፅዎት የምነግራችሁ ነገር ነው።

#የእጮኝነት_ሕይወትን_ያቋረጣችሁ:-

ይሄ ሀሳብ እንደእኔ እጮኝነቱን ለቆማችሁ ሰዎች ነው በመጀመርያ ይህ ግንኙነት ትዳር ስላልሆነ በአንድም በሌላም ምክንያት ሊፈርስ እንደሚችል ማወቅ ይኖርባቹሃል በቃ ይፈጠራል። ሌላው በአንድ ጊዜ ከዛ ግንኙነት ውስጥ ውልቅ ብላችሁ ለመውጣት አትጣደፉ ፀልዩበት ባላግባባችሁ ጉዳይ ላይ ከአጋራችሁ ጋር በግልፅ ተነጋግራችሁ መፍትሄ ፈልጉበት ግንኙነቱን ለመታደግ መሄድ የምትችሉትን ርቅት ሁሉ ሂዱ በዚህ ውስጥ ምንም ለውጥ ከሌለ ቆም ብላችሁ ስላችሁበት ሁኔታ አስቡ ማቆም ካለባችሁም አቁሙ እኔም በመጀመሪያ ያደረኩት ይሄንን ነበር ነገር ግን ጌታ አቁም ስል ጊዜ መውሰድ አልፈለኩም። እንደሚባለው ቀላል ባይሆንም ግን ለውስጥ ሰላም ሲባል አንዳንድ ስንብቶች አስፈላጊ ናቸው።  እኔም የእናንተ ወንድማችሁ ፍሬ 2017 ላይ ወደዚህ የፍቅር ሕይወት ውስጥ ገብቼ ነበር ነገር ግን ግንኙነቱ የእግዚአብሔር ሀሳብ የሌለበትና እኔን ሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሔር ፕሮግራም ልያወጣኝ እንደሆነ አይቼ ምንም እንኳ ነገሩ ቢከብድም ከዚህ ግንኙነቱ ሙሉ በሙሉ ወጥቻለሁ። በዚህ ዙሪያ ወደፊት በትምህርት እመጣለሁ ለሌሎችም ትምህርት ስለሚሆን። ስለዚህ በእጮኝነት ላይ የእግዚአብሔር ሀሳብ ከሌለ ከዚያ ግንኙነት ለማውጣት ጊዜ አትውሰዱ።

🧔ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ🧔

.     #እወዳችኋለሁ

  እኔን ለማገኘት  👉 
@abit9                      


https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
8🥰4👍1🙏1
በዚህ ዘመን ዝም ብለን ካግበሰበስን አዕምሮአችንን ልያበላሹ የሚችሉ እዚህም እዚያም የሚናገኛቸው ነገሮች:-

- የማህበራዊ ሚዲያ ንግግሮች በተለይ አነቃቂ፣ ገምብ እየተባሉ የሚቀርቡ። ( ምንጫቸው ይጣራ )

- የተለያዩ መጽሐፍቶች ( please check the source)

- ሌላው ወሎአችን check ይደረግ


መፊትሔው:-

መጽሐፍ ቅዱስ
ፀሎት
ምንጩ የተጣራ video ብቻ ማየት
ውሎ ማስተካከል...ወዘተ

Please ያገኘነውን ሁሉ አናግበስብስ። ወንድማዊ ምክሬ ነው።
3🙏2
🤦‍♀ ከራስ ጋር ትግል🤦‍♀  
📖ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📖  
   ምዕራፍ=አንድ   
    ክፍል=2


ከዛ ወዬ ወዬ ውሾች እያለች ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደተገናኘ ሰው እቅፍ አደረገችን እናም ""ዛሬ ምነው ቆያችሁ? ቡና እያፈላሁ ነው አቦል ላይ ደረሳችሁ" አለችን ሶሲም" ነገ ፕሮግራም አለን ስለሱ ስንመካከር ነበር ለዛ ነው የቆየነው" አለቻት እማም "ውይ እንደሱስ ከሆነ እሺ" አለቻት እናም እኛ ልብሳችንን ለመቀያየር ገባን እማም  ""ቆይ መክሰስ ላቅርብ"" ብላን ወደ ጓድያ ገባች እኛ ልብሳችንን ቀይረን ሳሎን ልክ እንደ እንግዳ ቁጭ አልን አባ ነፍሱንም አያውቅም ነበር ዜና እያየ እንደገባን ራሱ አላየም እኛም ጉዱን ለማየት ብለን ዝም አልነው በመሀከላችን ፀጥታ ሰፈነ ሶሲ ወደኔ ጠጋ አለች እና "ተጫወች እንደ ቤትሽ እይው" አለችኝ እንኳን እንዲህ ብለሽኝ ብዬ "ሰበር ዜና!! የአቶ ሰለሞን ቤት ውስጥ ሁለት ቁመታቸው ክርክም ያለ ቀልቀል የሚሉ ልጆች በአጠቃላይ ፀጉረ ልውጦች ከሰአቱ 12:09 ሲገቡ ታይተዋል ዘገባውን ያቀረብኩት እኔ ሜሮን ሰለሞን ነኝ ለተጨማሪ መረጃ ሶስና ሰለሞን ከሀዋሳ!" አልኩና ቆፍጠን ብዬ ቁጭ አልኩ ሶሲም ጎሮሮዋን ጠራርጋ  ልትቀጥል ስትል አባቴ በጣም ሳቀና "እኔ ነኝ ምቀጥለው" አለ ሶሲም ""እንዴ እስካሁን ዘግተኸን?? አይቻልም" አለችው እና ከሶሲ ጋር የሌለ ጭቅጭቅ ውስጥ ገቡ እኔም በመሀል ወሬያቸው እያሳቀኝ እያለ እማ መክሰስ አቀረበች ሶሲም "ውይ እማ ልቦጭቅሽ ስል ምነው መክሰሱን ከየት ሀገር ቢመጣ ነው እንዲህ የቆየው?" ብላ ሳቀች እማም "ማን አየብሽ 'ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ' አሉ ላቅርብ ባልኩ?!" አለችን እኔ በጣም ስለራበኝ  "እረ እንብላ እርቦኛል" አልኳቸው የተራበው ሆዴን እያሻሸሁ እና አመስግነን በልተን ቡናም ጠጣን እማ እና አባቴ ቁጭ አሉ እና እኔና ሶሲ ቆመን ዘመርን አባቴ ቃል አካፍሎን ሶሲ ፀልያ በሉ ግቡ እና አጥኑ ተብለን በተመስጦ ማጥናት ጀመርን በመሀል ቢኒ ደወለ "ወዬ ቢኒ አልኩት አንቺ አዝግ አለሽልኛ" ("አለሁልህ የኔ more አዝግ") አልኩት "ነገ እንገናኛለን አ" ሲል ስልኬ Laud ላይ ስለነበር ሶሲ በአይኗ የሆነ አስታየት ነገር አይታኝ አፏን ይዛ ሳቀች በሁኔታዋ ተገርሜ  አዎ ደውሉልኝ ለነ ሊዱም ነግሬያቸዋለሁ" አልኩት ሶሲ ይህን ጊዜ ብቻዋን "እኔ ደግሞ ወሬ አገኘሁ ብዬ ልበላ" አለች ከዛ ከቢኒ ጋር ቻው ተባብለን ወደ ጥናቴ ተመለስኩ አጥንቼም እንደጨረስኩ ትንሽ text chat አድርጌ ተኛሁ ኮሽ ሳይልብኝ የሰላም እንቅልፍ ተኝቼ  በእንቅልፍ አለም በሰመመን እንደሆንኩ ልክ የሆነ ቅዝቃዜ ይሰማኝ ነበር አይኔን እንደጨፈንኩ በቀስታ አልጋውን ስነካ በጣም ይቀዘቅዛል ምን እንደሆነ ለማወቅ ብን ብዬ ስነሳ. . . . . . . . . . .

#ይቀጥላል

@abit9
🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹
https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
4🥰1🙏1
🟩 አምላካችን:-

"እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤..." ።

1ኛ ጢሞቴዎስ 6:16
3