የነቃ ትውልድ Tube
15.4K subscribers
106 photos
13 videos
3 files
389 links
" ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤..." 1ጴጥ 4፣11።

የዚህ ቻናል ዓለማ ትውልዱ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ጠንካራና ከዚህ ዓለም ክፋት እርቆ በቅድስና እግዚአብሔርን በሚያከብር
ሕይወት እንዲኖር ማድረግ ነው።

ለጥያቄ እና አስተያየት 👉 @CHRISTIAN_NEGN1 ተጠቀሙና አድርሱኝ!
Download Telegram
✔️ወደ አብ ለመድረስ ብቸኛ መንገድ ኢየሱስ ነው🤷‍♂
5
ሰላሜ ሆነሃል ኢየሱስ !
6🙏1
በህሊውናህ ውስጥ ሰውረን ኢየሱስ !
2
የእኛ አፈላለግ ከእርሱ አንጻር ስታይ ምንም አይደንቅም🙏
ለጌታ ያለንም ፍቅር የሚወራው ነገር ምን አለው ፍጹሙ የእርሱ ባለበት🙏
በአፈላለጉ ይበልጥ እንደነቅ
ፍቅሩም ያስደምመን🙏
😍5
📌"በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥
በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤..."

ዘኍልቍ 23:23።
🙏7
"በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ ..." መዝ ዳዊ 23፣4።
👍2😍1
“If any of you lacks wisdom, let him ask of God…” — James 1:5 ❤️
"ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።"

ያዕቆብ
1፣5።
🙏8
በሕይወት ውስጥ ዋናው ጉዳይ ብዙ ነገር መሰብሰብ እና ዝነኛ መሆን አይደለም ኢየሱስን ማግኘት ነው።
9👍3
⭐️ሊቀ ካህኔ ኢየሱሴ፣ ጠበቃዬ ኢየሱሴ!
🙏1
እግዚአብሔር እኔን ፈጥሮኛል ብዬ ማመን ከቻልኩ፣ የተበላሸው ክፍሌንም እንዴት ማስተካከል ይችላል ብዬ አላምንም። እራሱ አይደል የፈጠረው። ስበላሽ እንደወደደ አድርጎ ይሰራዋል።

ከዛሬ ጀምሮ የሚመጣው አመት ዳግም የመሰራት አመት ይሁንልን።
😍3
🎊እግዚአብሔር ሆይ በሕይወት ኖሮ ተኝቶ መንቃት መቻል፣ መጸለይ መቻል፣ ቃልህን ማጥናት መቻል፣ ህብረት ማድረግ መቻል፣ መማር መቻል፣ መሥራት መቻል እድል ነው።

ተመስገን🙏
🙏82🎉1
ኢየሱስ ስለ እኛ በቀራንዮ የሰራሄው ስራ ትዝ ይለናል። እናመሰግንሃለን።
🙏5❤‍🔥1
👌 እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘላለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።

ኤርምያስ 10:10
🙏2👍1
‼️ፈተና!

በሕይወት ስንኖር ሰው ነንና ለሰው የሚደርስ ፈተና ይደርስብናል። በዚህ ዓለም እስካለን ከዚህ ልናመልጥ አንችልም። ነገር ግን አንድ ጌታ አለን። አይዞአችሁ የሚለን። ድካማችን የሚገባው። በአብ ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ ዘወትር የሚማልድ።

ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ስለሆነ አንተክዝ። በእርሱ እንታመን። ኢየሱስ ይመጣል።
🙏3😍1
We should check our motives that intiate to do what we do.

It matters above the things done.

Including Prayer !
👍1😍1
🔹በእግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ ራሳችንን ሆነን እንቅረብ። አናስመስል።

Never !
🙏1😍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢየሱስ የነገስታት ንጉሥ
2🔥2💯2
#ምክር_ለወጣት_አገልጋዮች

ስሙኝ የአባቴ ብሩካን እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ትልቅ ስራ ልሰራ ፕሮግራም በያዘው ልክ አጋንንትም ከዚህ ፕሮግራም ለማውጣት ዕቅድ ይይዛል ስለዚህ የምታደርጉትን እያንዳንዱን ነገር እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ነገር ላይ አንተ አለህበት ወይ ማለቱ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው።

ዛሬ ላወራ የፈለኩት ለወደፊት የትዳር ሕይወታችሁ የምትመርጡትን ሰው እንድትላዩ ነው።
የማትጸልይ፣ ለእግዚአብሔር ቃል ጊዜ የሌላት፣ መንፈሳዊ ነገር ቀሎ የሚታይበት፣ ቤተክርስቲያን የማትሄድ፣ ለአገልጋዮች ክብር የሌላት፣ ከመንፈሳዊ ነገሮች ይልቅ ለዓለማዊ ነገር ጊዜ የምትሰጥ ማለትም ለመዝናናት፣ ለመዞር፣ ድራማ ለማየት፣ በቃ በየቀኑ Enjoy እናድርግ የምትል።
ወንድሜ በጭራሽ እንደዚህች አይነት ሴት የሕይወት አጋር አታድርግ። ዛሬ ላይ በአገልግሎት ትልቅ ስራ እየሰሩ ካሉት አገልጋዮች ጀርባ ጠንካራ የጸሎት ሴት ከኃላ እንዳለች አትርሳ።
በአንተም ሕይወት ነገ ላይ ለአገልግሎትህ ውድቀትም ሆነ ስኬት የሚስትህ ድርሻ የአንበሳውን ቦታ እንደሚይዝ አትርሳ። ከትዳሯ በላይ ለእግዚአብሔር ስራ ስፍራ የሚትሰጥ ሴት የሕይወትህ አጋርህ ትሁን።
የአንተ እጮኛህ አገልጋይ መሆንህን መቀበል አለባት ።
ሲቀጥል የአገልጋይ ሚስት መሆን ቀላል አይደለም ። እንደ ሌሎች ሚስቶች ብቻም አይደለም ።
የአገልጋይ ሚስት ለመሆን መስዋዕትነት ለመክፈል ፈቃደኛ መሆንን ይጠይቃል።

ዛሬ ላይ የት ይደርሳሉ የተባሉ አገልጋዮች በስህተት ከማይሆን ሰው ጋር አንድ ላይ ሆኖ የማይወጡት ቁልቁለት ላይ ወድቀዋል ውስጣቸው ላይ የነበረው ለዓለም መድሀኒት የሚሆን ራዕይቸው መና ሆኖል። እግዚአብሔር ከያዘላቸው ትልቅ ፕሮግራም መስመር ወጥቶ ብዙ ስቃይ እያዩ ነው። ስለዚህ ወንድሜ ከማን ጋ ነው ግንኙነት ውስጥ ያለከው? ከማን ጋርስ  ነው ግንኙነት ለመጀመር እያሰብክ ያለከው?

ልብ በል የነገ ሚስትህ ለማቆምም ለመውደቅም ምክንያት ትሆናለች።

በአጠቃላይ የትዳር አጋርህን ቃሉ
ዘፍጥረት 2:18 "ረዳት " ነው የሚለው።
✔️ በአገልግሎት ረዳት
✔️በስራ ረዳት
✔️በቤተክርስቲያን ረዳት
✔️በጥሪ ረዳት
✔️በራዕይ ረዳት
✔️በፀሎት ረዳት
✔️በአምልኮ ረዳት
✔️በስብከት ረዳት
✔️በህይወት ረዳት
✔️በፆም ፀሎት ረዳት
✔️በገንዘብ ረዳት
✔️በሀሳብ ረዳት ነው የሚያስፈልገው ።
እግዚአብሔር አምላክ እውነተኛ "ረዳት "ይስጣችሁ!!!

እህቶች ይሄ ምክር ለእናንተም ይሆናል።

“ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት።”
  — ምሳሌ 12፥4

.      #እወዳችኋለሁ
ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ


እኔን ለማገኘት @abit9 @abit9


sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
4👍1🎉1🙏1😍1
.              #ተረጋጉ

#ይህ_መልዕክቴ_ያለ_ጊዜ_ወደ_ፍቅር_ግንኙነት_ለመግባት_ለሚሮጡ_ወጣቶች_ይድረስልኝ

አንድ ወጣት ልጅ ነበር፡፡ በትምህርቱ ጎበዝ ነው፤ መልኩም ያማረ ነው:: ቤተሰቡ «ይህ ልጅ የት ይደርሳል?» ብለዉ በጉጉት ይጠብቁት ነበር። የአካባቢው ሰዎችም ጭምር «ይህ ዘራችንን በመልካም ነገር ያስጠራል» በማለት ተስፋ ያደርጉ ነበር፡፡ እርሱም በመጀመሪያ ትኩረቱ በትምህርቱ ላይ ብቻ ነበር፡ በአካባቢው ያሉ ቆንጆ ሴቶች ግን እርሱን ለማጥመድ ይፈልጉ ነበር:: በተለይ ዋርሳው የሆኑ ሴቶች በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እርሱን ለማጥመድ ይፈልጉታል፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በአንዷ እጅ ወደቀ፡፡ በእርሷም ፍቅር ተነደፈ:: ከዚያ በኋላ ደግሞ ሌሎች ሴቶችን አዳረስ:: የስምንተኛ ክፍል ጨርሶ ወደ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሄድ አልፈለገም:: የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እርሱ ከሚኖርበት ሩቅ ስለነበር ከቤት ተመላልሶ መማር አይችልም:: ስለዚህ ወደ ሌላ ከተማ መሄድ ነበረበት፡፡ እነዚያ ሴቶች እያንዳንዳቸው «እኔን ትተህ እንዴት ትሄዳለህ? ካላንተ መኖር አልችልም» ብሎ ልቡን ሰረቁት፡፡ እርሱም የእነርሱን ሐሳብ ስምቶ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ሠፈር ተመለሰ፡፡ እንደ እርሱ ጎበዝ ያልነበሩ ልጆች ትምህርታቸውን ቀጠሉ፡፡ አንዳንዶች ኮሌጅ የመግባት ዕድል አገኙ፡፡ እርሱ ግን እርሻ ማረሰ ጀመረ:: ዕድሜው ሃያዎቹ አጋማሽ ሲሆን ትዳር መሠረተ:: ልጆችን ወለደ፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩ ልጆች ተምረው መምህራን ሆነው እርሱ ይማርበት ወደ ነበረበት ትምህርት ቤት ተመድበው መጡ፡፡ ሰውየውም ይህን ሲያይ በሕይወቱ አንድ ትልቅ ስህተት እንደሠራ ተገነዘበ፡፡ አሁን ለመማር ያለው ዕድሉ ዝግ ሆኖበታል፡፡ ሚስቱንና ልጆቹን ለማን ትቶ ትምህርት ቤት ገብቶ ይማር! አሁን ያለፈውን ነገር ማሰብ እንጂ ማድረግ አይችልም::

አያችሁ አይደል ያለ ጊዜ ወደ ፍቅር ግንኙነት መግባት በጣም ብዙ ችግሮች አሉ ለዚህም የባለታሪኩ ልጅ ሕይወት ከበቂ በላይ ምስክር ነው። መግባት በጣም ቀላል ነው ነገር ግን በእሱ ምክንያት ከሚመጣው መዘዝ ማውጣት ደሞ ስቃይ ነው።  ስለዚህ እባካችሁ ተረጋጉ ሁሉም ነገር በጊዜው መድረሱ አይቀርም።
በተለይ በትምህርት ገበታ ላይ ያላችሁ ወጣቶች የእናንተ ትኩረት ትምህርትና መንፈሳዊ ሕይወታችሁ ላይ ብቻ ይሁን። ዕድል ከገኘችሁም ስራ በመስራት ላይ አድርጉት። ከዚያ ውጪ ቶሎ ብላችሁ ወደ ፍቅር ሕይወት አትግቡ። እናንተ ያላችሁበት የብቸኝነት ጊዜ ለነገ ሕይወታችሁ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን የምታዘጋጁበት ጊዜ ነው። ይሄንን ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር ከየትኛውም ሕብረት እና ግንኙነት ይልቅ ከእርሱ ጋር ብቻ እንድታሳልፉ ይፈልጋል።
የብቸኝነት ጊዜያችሁን በደብ ተጠቀሙበት እናንተ ዕድለኞች ናችሁ።

.           #ጨረስኩ

👤ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👤

🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ

inbox me 👉 @abit9 


https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
3🥰2😍2👏1
ቸኮለብኝ ልቤ ሊያገኝህ
ይድነቃቸዉ ተካ
ማርከን ዜማ @Markengeta
Yidnekachew Teka - ቸኮለብኝ

ሌላ ነገር ታገስ ብትለኝ
ጠብቃለሁ እስኪሆንልኝ
ግን አባቴ ለክብርህ ነገር
በህልውናህ ውሎ ለማደር

አዝ:- ቸኮለብኝ ልቤ ሊያገኝህ
እንዴት ብዬ ኢየሱስ ልያዝህ
ናፍቆቴ ነህ የሁሌ አምሮቴ
አንተን ማየት ክብርህ ጉጉቴ (፪x)

ኢየሱስ ዓይኔ በርቶ አንዴ ልይህ
ኢየሱስ ውስጤ ራበኝ እስከምነካህ
ኢየሱስ እኔ አልችልም መኖር ካለዚያ
ኢየሱስ በሌለበት ክብርህ ህልውናህ (፪x)

አዝ:- ቸኮለብኝ ልቤ ሊያገኝህ
እንዴት ብዬ ኢየሱስ ልያዝህ
ናፍቆቴ ነህ የሁሌ አምሮቴ
አንተን ማየት ክብርህ ጉጉቴ (፪x)

አንተን ማየት ክብርህ ጉጉቴ
አባትዬ ፊትህ ጉጉቴ
ኢየሱሴ ክብርህ ጉጉቴ
አባትዬ ክብርህ ኢየሱሴ

ኢየሱሴ የነካው ሰው
ኢየሱስን በዓይኑ ያየ ሰው
ኢየሱሴ የገባው ሰው
ኢየሱስን በዓይኑ ያየ ሰው
ለሌላ ነገር መኖር አይችልም (፪x)
ለፈለገው ነገር መኖር አይችልም
ለፈለገው ነገር መኖር አይችልም (፪x)

የመቅደስን ደጅ የሚጠኑ
ብዙ ናቸው አንተን የሚሹ
አምላክህን አሳየኝ ሚሉኝ
ክብሩ የታል እስኪ አሳውቀን

ወዴት ልበል የት ጋር ነህ ውዴ
በእኔ ዘመን ይረፍ ትውልዴ
ከእኔ ውጪ የትም አልጠቁም
በእኔ ላይ ና እስኪያይህ ሁሉም (፪x)

ኢየሱስ ዐይኔ በርቶ አንዴ ልይህ
ኢየሱስ ውስጤ ራበኝ እስከምነካህ
ኢየሱስ እኔ አልችልም መኖር ካለዚያ
ኢየሱስ በሌለበት ክብርህ ህልውናህ (፪x)

የጭንቅ ነው ስጠራህ ውዴ
የውስጤን ምጥ ቃላት ሰብስቤ
ቢነግርልኝ የልቤን ጩኸት
የጥማቴን የርሃቤን ልክ



ክብሩን የተራቤ/ተሃድሶ የሚፈልግ ይስማ😭😭😭



https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
https://t.me/ReformationNeeded
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
🔥41🙏1