ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

________________
ካለፈው ክፍል የቀጠለ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

🎬2.2
ከብዙ ሺ ዓመት በፊት የነበረው በእንግሊዝ የሚገኘው የሥነ ፈለክ መቀመሪያ የነበረው “ስቶንሄንጅ” በመባል የሚታወቁት ድንጋዮችና እና ውጫዊው የአውብሬይ 56 ክበባዊ መዋቅር ጂኦሜትሪ በትክክል የሠኔ 14/ 2012 ዓ.ም. ግርዶሹ የሚሠራውን መስመር ጥንቱ የመሥራቱ ነገር ለአጥኚዎች አስገራሚ ሆኗል፡፡

🎬2.3.
የኦርዮንን ኮከብ የሚመስለው የጊዛ ታላቁ ፒራሚድ ቀመርም የሠኔ 14/ 2012
ዓ.ም. የግርዶሽ መስመር መሥራቱ ለአጥኚዎቹ አስደማሚ ነገር ከመሆኑ ባለፈ sacred geometry የመሥራቱ ነገር በአጥኚዎች ዘንድ አጀብ አስብሎታል፡፡

🎬2.4
የጥንት ቻይናውያን ዕውቀት የነበሩት ከሒሳብ ቀመር ውስጥ የባይናሪ ማቲማቲክስ ተጠቃሽ ነው፡፡ እነዚህ ሱፐር ኪውቢትስ በቅርቡ ሲሆን የተመረመሩት በኳንተም ኮምፒውተር ተካተዋል፡፡ በቻይናውያን ጥንታዊ የባይናሪ ቀመር ላይም የሠኔ 14ቱን ግርዶሽ ጠቋሚ ነገር ማግኘታቸው ለሳይንቲስቶቹ አስገራሚ ሆኗቸው ይህንን ብለዋል፡-
This indicates that the ancient Chinese not only knew about binary mathematics but that the primary number pattern within the binary system that points directly to the astronomical event on the 21 June 2020. ይህ የሚያመለክተው ጥንታውያን ቻይናውያን ያወቁት ስለ ባይናሪ ሒሳብ ብቻ ሳይሆን በባይናሪ ዘዴ ውስጥ ያሉት ፕራይመሪ ቊጥሮች ወደ ሠኔ 14ቱ 2012 ዓ.ም. የሥነፈለክ ክስተትን በቀጥታ ይጠቁማሉ፡፡ በማለት እየጻፉ ነው፡፡

°°°°° ይቀጥላል °°°°°

🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
#Caution
በዕለቱ ያለ eclipse viewer ፀሐይን በዐይን ለመመልከት መሞከር የዐይን ብርሃንን (አይናችን ሊፈስ ይችላል) አሳጥቶ ስለሚያሳውር ጥንቃቄ ያድርጉ። መነጽሩም🕶 ቢሆን የISO certification የማያሟላና ተመሳስሎ የተሠራ ከሆነ የአልትራ ቫዮሌት ጨረርን ስለማይቋቋም ከመጠቀም ይቆጠቡ። እንዲሁም የፀሐይ መነፅር ፣ ፍሎፒ ዲስክ ፣ የፎቶ ፊልም ፣የራጅ ፊልም እና የመሳሰሉት ቁሶች መጠቀም በዓይን ላይ ጉዳት ያደርሳል።

እናመሠግናለን
#share #participate For any #comment 👇

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°

📗📒📕
https://t.me/Readers_To_Know/468
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓
________________
ካለፈው ክፍል የቀጠለ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

🎬🎬3ኛ)
ሌላው ይኽ የሠኔ 14ቱ የፀሓይ ግርዶሽ በ4 ድብዝዝ የጨረቃ ግርዶሽ (ፕኑምብራል ሉናር ኤክሊፕስ) የተከበበ መሆኑ ለተመራማሪዎች ክስተቱ አስገራሚ ሆኗል፡፡ እነዚህም በታላላቅ ጨረቃ (super moon) የታጀቡ የጨረቃ ግርዶሾች ቀድመው ጥር 1 (January 10) ፤ ግንቦት 28 (June 5) በመቀጠል ሠኔ 28 (July 5) እና ኅዳር 21 (November
30) ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ድንቅ አድርጎታል።

🎬3.1
98 ፐርሰንት ፀሓይ ጨልማ እሳታማ ቀለበት ሠርታ አስደናቂ ቅርጽዋን በምትታይበት በላሊበላ ሰማይ ላይ ንጉሥ ላሊበላ የሠራውን “ፈለገ ዮርዳኖስ” በመባል የሚታወቀውን ቦታ የግርዶሹ መስመር አቋርጦ መሄዱ አስደናቂ ሆኗል፡፡ ይህንንም የናሳ ጉጉል ማፕ ላይ
ተመልከቱ፡፡ በተለይ ደግሞ ጠዋት ላይ ሁለቱ ፕላኔቶች ዐጣርድ (ሜርኩሪ) እና ዝሁራ (ቬነስ) በምሥራቅ ከፀሓይ ጐን ዐብረው ተሰልፈው በላሊበላ ሰማይ መታየታቸው ጥሩ አመስጣሪ ቢያገኝ መተንተን እንደሚችል ባውቅም ነገር ግን የላሊበላው ራሱን ችሎ
አንድ ትልቅ ጽሑፍ ሊወጣው እንደሚችል በመገመት ጽሑፌን እዚ ላይ እቋጫለሁ፡፡
ይህን ክስተት በዘመናችን በማየታችን እድለኛ እንደምንሆን ይሰማኛልና ክስተቱን በፍርሃት ሳይሆን ተፈጥሮን በማድነቅና በመደሰት እናሳልፈው እላለሁ፡፡ በተረፈ ስለመጪዎቹ ግርዶሾች አንድሮሜዳ መጽሐፋችን ላይ ስለተጠቀሱ እያነበባችሁ ዕውቀትን
ቅሠሙ በጥበብም ተራቀቁ።

መ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

°°°°° ተፈፀመ °°°°°

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
ካነበብነው📖📜📰🗞 pinned «የፀሐይ ግርዶሽ እና ጥንቃቄ! የፀሐይ ግርዶሽን በዓይን በቀጥታ መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን ላይ ያደርሳል። ግርዶሹን ለመመልከት ፦ 1. ደረጃውን የጠበቀ የግርዶሽ መነፅር መጠቀም 2. ፒን ሆል ካሜራ ወይም በአነስተኛ ቀዳዳ ወደ ድፍን ካርቶን የሚገባውን ብርሃን የሚስለውን ስእል ጀርባ ለፀሐይ በማዞር መመልከት 3. ጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባውን የፀሐይ ብርሃን መሬት ወይም ግድግዳ ላይ የሚሰራውን…»
ጥያቄ

Youtube ላይ የተለቀቀው የመጀመሪያው ቪድዮ ምን የሚባል ርዕስ ነበረው? የቪዲዮው ርዝመትስ ምን ያህል ነበር?
መልሶን @Feed_it_bot ላይ ይላኩልን።

@Readers_To_Know
​​ሰላም!
ነገ እሑድ ሰኔ 14 ከጠዋቱ 12:45 ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:33 ድረስ ከቶጎ ተነስቶ እስከ ፓስፊክ ውቅያኖስ ድረስ የፀሐይ ግርዶሽ ይታያል።
በኢትዮጵያ 3:19 ላይ ግርዶሹ ያበቃል ተብሎ ሲጠበቅ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይም ለ2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ እንደሚቆይ ቅድመ ትንበያዎች አሉ።
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
የተነገሩ የጥንቃቄ መንገዶች እንዳይረሱ!

ጥያቄ ለናንተ
. ላሊበላ ውስጥ የሚገኙ አብያተክርስቲያናት ስንት ናቸው?
. መጠሪያ ስማቸውን ካወቃችሁ?
. ላሊበላ ከዋና ከተማችን ከአዲስአበባ በስንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች?

መልሳችሁን @Feed_it_bot ላኩልን!
@Readers_To_Know
እስካሁን ባለን መረጃ የነገው ተፈጥሮአዊ ክንውን በቀጥታ በEBC እንዲሁም በአምሐራ ቴሌቪዥን እንደሚተላለፍ ነው።
@Readers_To_Know
የዛሬው ተፈጥሮአዊ ክስተት በEBC ዜና እንዲሁም በትግራይ ቴሌቪዥን በመተላለፍ ላይ ይገኛል።
@Readers_To_Know
🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂
🥀ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰብ አባላት እንደምን አላችሁ! የቤት ውስጥ ቆይታ እንዴት ይዞአችኋል? መፅሐፍትን እያነበባችሁ ግዜያችሁን የምታሳልፉ እንዳለችሁ ተስፋ እናደርጋለን። እናም ካነበባችሁት በጥቂቱ ማካፈል ለምትፈልጉ 👉 @Feed_it_bot ላይ ላኩልን!

እናመሰግናለን

@Readers_To_Know
📓📓📓📓📓📓📓📓
😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣

አባትና የደረሰች ሴት ልጁ እየተጨዋወቱ ሳለ ልጅ በመሀል " አባዬ! ትናንትና ከኔ ጋር ያየኸው ልጅ እኮ እጮኛዬ ነው፤ ደስ አይልም? " ብላ አባቷን ትጠይቀዋለች።
አባት፦ " ጥሩ ነው፤ ጨዋ ሰው ይመስላል... ለመሆኑ ደህና ገንዘብ አለው? "
ልጅ፦ " በጣም ይገርማል!! ... እንዲያው ወንዶች ስትባሉ በቃ ባህሪያችሁ አንድ ነው ማለት ነው?!! ...እርሱም ሁልጊዜ ስላንተ የሚጠይቀኝ አባትሽ ምን ያህል ገንዘብ አለው እያለ ነው!!"😂😂😂😂
ምንጭ፦ እስኪ ዛሬ እንኳን እንሳቅ በቅዱስ-ሀብት በላቸው

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
እንደምን አላችሁ!❤️

"አሁን እያሰብኩ ያለሁት ዓለምን እየወረራት ስላለው ክፉ የጥፋት ደዌ ሳይሆን ደዌው ገና ስላልደረሰባት ውብ ጎኗ ነው።"
ገፅ 130 🥀አና ፍራንክ🥀

@Readers_To_Know
ካነበብነው📖📜📰🗞
​​ሰላም! ነገ እሑድ ሰኔ 14 ከጠዋቱ 12:45 ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:33 ድረስ ከቶጎ ተነስቶ እስከ ፓስፊክ ውቅያኖስ ድረስ የፀሐይ ግርዶሽ ይታያል። በኢትዮጵያ 3:19 ላይ ግርዶሹ ያበቃል ተብሎ ሲጠበቅ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይም ለ2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ እንደሚቆይ ቅድመ ትንበያዎች አሉ። 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 የተነገሩ የጥንቃቄ መንገዶች እንዳይረሱ! ጥያቄ ለናንተ . ላሊበላ ውስጥ የሚገኙ አብያተክርስቲያናት…
🥀 መልስ 🥀
_____________
የላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ላሊበላ ከአዲስ አበባ በግምት 600 ኪ.ሜ ላይ ትገኛለች። ዩኔስኮም እዚህ የሚገኙ 11 ቤተክርስቲያናትን መዝግቧል። እነሱንም ቀጥለን እናያለን፦
በስተ-ሰሜን
° ቤተ መድሃኔዓለም
° ቤተ ማርያም
° ቤተ ጎሎጎታ ሚካኤል (የንጉስ ላሊበላ መቃብር
የሚገኝበት)
° ቤተ መስቀል
° ቤተ ደናግል
በስተ-ምዕራብ
° ቤተ ጊዮርጊስ (የመስቀል ቅርፅ ይዞ ከላይ
የሚታየን)
በስተ-ምስራቅ
° ቤተ አማኑኤል
° ቤተ ቅዱስ መርቆርዮስ
° ቤተ አባ ሊባኖስ
° ቤተ ገብርኤል ወሩፋኤል
° ቤተልሔም

ስለተሳተፋችሁ እናመሰግናለን
ሀሳብ አስተያየት እንዱሁም ያላችሁን ለማጋራት @Feed_it_bot

@Readers_To_Know
🦅🖊 ስነግጥም 🖌🦅

የስልጣኔ ምንጭ፣ የሰው ዘር መገኛ፣ የታሪክ
ከበርቴ መሆናችን ታውቆ ባለም ከተወራ ፤

እኛ ምንተዳችን "ጭራ ናችሁ" ሲሉን ከድሆችም ጎራ ፤

ምናባቱ ዛሬ ምናባቱ ነገ ኮርቶ መኖር ካለ በትናንት አሻራ ።

ምንጭ:- ሙሉነህ መንግሥቱ፣ ጉራማይሌ

ከእናንተው ከተላከልን!
እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🦅🖊 ስነግጥም 🖌🦅

አይቀርም
""""""¤¤¤¤""""""

አዳም ነውና አባይ ሴትን ተከትሎ ፤
ሊደርስባት ሲከንፍ በፍቅር ነሁልሎ ።
ሱዳኒት ግብፂትም እየሸነገለች ከፊት ከፊት
ቀድማ ፤
ኪሱን ስታራግፍ በፍቅር ሲጠማ ፤
ላቡን አንጠፍጥፎ በረሀ ሲለማ ።
ጉልበቱ ሲሟጠጥ በጣር እያማጠ ፤
ፊቱን አዞረና ለናቱ እጁን ሰጠ ።

ምንጭ:- አለሚቱ ዳመና፣ 2004

እናመሠግናለን
Don't forget to
#share our channel

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አንድ 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት የዳግማዊ አጼ ምኒልክ መቶኛ የሙት ዓመት በዚህ በያዝነው ዓመት (በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር) እየተከበረ ባለበት
ወቅት ሙሉ ጊዜውን በመስጠት ንጉሱ የሰሩትን ታላቅ ስራ ሁሉ በማጣጣል እና ጥላሸት በመቀባት ዘመቻ ላይ በመጠመድ ታሪክ የማጠልሸት ድራማውን በመተወን ላይ ይገኛል፡፡ የታሪክ ማጠልሸት ዘመቻው በዋናነት እየተከናወነ ያለው ለገዥው አካል ቅርበት ባላቸው ታማኝ ሎሌዎች፣ የጥቅም ተጋሪዎች እና የእራሳቸው ስብዕና በሌላቸው አሻንጉሊቶች አማካይነት ነው፡፡ ገዥው አካል ሲያስነጥሰው መሃረብ ይዘው በሚቀርቡ አጎብዳጆቹ አማካይነት የጥላቻ መርዛማ ቃላትን፣ የሚቆጠቁጡ ባዶ ዲስኮሮችን እና እርባናየለሽ ምዕናባዊ ስዕል በአዕምሮው ላይ እየፈጠረ አጼ ምኒልክ የግዛት ማስፋፋት ጥማታቸውን ለማርካት ሲሉ በዜጎች ላይ የጭካኔ ተግባራትን እንደፈጸሙ በማስመሰል ለምንም የማይጠቅሙ እርባናየለሽ እና ተራ አሉባልታዎችን በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡

የገዥው አካል ድንጉላ አገልጋዮች በማናቸውም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በመሰማራት ታሪካዊ ቅጥፈቶችን፣ አሳሳች ዘገባዎችን፣ የሀሰት ታሪክ ፈጠራዎችን፣ ሆን ተብሎ በሀሰት ላይ የተመሰረቱ መረጃዎችን እና ነጭ ውሸቶችን እንደ በቀቀን እየደጋገሙ በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡ የዕኩይ ዓላማው አራማጆች በታላቁ የኢትዮጵያ መሪ ላይ ግነታዊ ኩምክና በመስራት፣ በማዋረድ እና እውነተኛውን ስብዕናቸውን ጥላሸት በመቀባት የስሜት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ውስጥ በመዘፈቅ ጌቶቻቸውን ለማስደሰት በታለመ ዕኩይ ምግባር ላይ ተጠምደው ይገኛሉ። የታላቁ መሪ ነብስ ከስጋቸው ከተለየች ከአንድ መቶ ዓመታት የጊዜ ቆይታ በኋላ የተቀበረን ጉዳይ በማንሳት ታላቁን መሪ ሰይጣናዊ ስብዕና እንደነበራቸው ለማስመሰል በማሰብ የዕኩይ ምግባር ጎተራዎቹ የቻሉትን ያህል ጥረት ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት ከተለዩ ሁለት ዓመታት እንኳን ሳይሞላቸው የዕኩይ ምግባራት ቋቶቹ የኢትዮጵያ አዳኝ መልዓክ ሊያደርጓቸው ይፈልጋሉ፡፡
በአሁኑ ጊዜ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ በተከፈተው ......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል ሁለት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

በአሁኑ ጊዜ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ በተከፈተው የገፍ ወይም የኃይል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ወይም ደግሞ የአጼ ምኒልክን የሙት መንፈስ ደጋግመው በማንሳት ፍጹም ጥላቻ እና የጥላቻ አመለካከት እንዲንሰራፋ በገዥው አካል ስልታዊ እና የተቀነባበረ ዘመቻ የማካሄድ አመክንዮ ለማንም ቢሆን ሊደንቅ አይገባም። ሀቁ አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ የኸውም የምኒልክን ስም ጥላሸት በመቀባት (ሰይጣናዊ ስብዕና በመስጠት) በሚሽከረከር ጉዳይ ላይ ብቻ የሚቆም ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገር ግን በቅርቡ በህይወት የተለዩትን የገዥውን አካል የአለቆች ሁሉ አለቃ (Capo di tutti capi) አቶ መለስ ዜናዊን በመላዕክነት ቀብቶ ለማቅረብ የታቀደ ዕኩይ ምግባር ነው፡፡

ዳግማዊ ምኒልክን ጥላሸት የሚቀቡ ሙትመንፈሶች፣
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ እየተካሄደ ያለው ከፍተኛ ጥላሸት የመቀባት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ያነጣጠረው የኢትዮጵያን ታሪክ በመፋቅ በአቶ መለስ ዜናዊ የመላዕክነት የህይወት ታሪክ (የመላዕክነት ትረካ) በመተካት የታላቋን ሀገር ትክክለኛ ታሪክ እንደገና ለመጻፍ፣ አዛብቶ ለመጻፍ፣ ገልብጦ ለመጻፍ፣ አወዛግቦ ለመጻፍ፣ በመቀባባት የሚያምር አስመስሎ ለማቅረብ እና እውነተኛውን ታሪክ ለማስወገድ በመደረግ ላይ ያለ ከንቱ ሙከራ ነው፡፡ የአጼ ምኒልክን ታሪክ በመሰረዝ የዘመናችን የ”አፍሪካ ታላቁ መሪ” በማለት የመለስ ዜናዊን ታሪክ ለመጻፍ ይፈልጋሉ፡፡ በሀሰት እምነት ላይ በመመስረት መለስ “አዲሱ የአፍሪካ መሪ ዝርያ“፣ መለስ “የዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስት ቀያሽ”፣ መለስ “በዓለም አቀፋዊ የሙቀት እና የአየር ጸባይ ለውጥ የአፍሪካ ጠበቃ”፣ መለስ “ከጂ-8 እና ጂ-20 መሪዎች ጋር በመሆን ክርናቸውን የሚያሳዩ አፍሪካዊ መሪ”፣ መለስ “የቻይና-አፍሪካ የትብብር መድረክ የቤጂንግ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጉባኤ ሊቀመንበር”፣ መለስ የሶማሌ ጅሃዲስቶች እና አሸባሪዎች አስወጋጅ”… ተብለው ከእውነተኛ ስብዕናቸው ውጭ በሆነ መልኩ እንዲመለክባቸው ይፍልጋሉ፡፡
የታላቁን መሪ የዳግማዊ ምኒልክን ስብዕና ጥላሸት በመቀባት .......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል ሶስት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

የታላቁን መሪ የዳግማዊ ምኒልክን ስብዕና ጥላሸት በመቀባት አቶ መለስን ቅብዓ መልዓክ (የተቀባ መልዓክ) ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ ለመሆኑ አጼ ምኒልክን ጥላሸት የሚቀቧቸው ለምንድን ነው? ምክንያቱም አጼ ምኒልክ በአመራር ጥበባቸው እና በትግላቸው ግጭትን በመፍጠር ሲናቆሩ ከነበሩት ባላባቶች፣ ለስልጣን ብቻ ከሚቋምጡ ከተለያዩ አካባቢያዊ ንጉሶች፣ ከተለያዩ ልዕልቶች የቅምጥል የአገዛዝ ስርዓት፣ እና ከጎጣዊ ምስለኔዎች የተበታተነ አገዛዝ በማላቀቅ ዘመናዊቷን የአፍሪካ ብሄር ታላቋን ኢትዮጵያን በመመስረታቸው ብቻ ነው፡፡ የዕኩይ ምግባር አራማጆች አጼ ምኒልክን ጥላሸት ይቀቧቸዋል፣ ምክንያቱም ምኒልክ ታላቆቹን የአውሮፓ ኢምፔሪያሊስት ኃያላን በጦር ሜዳ ውሎ በማሸነፍ አንጸባራቂ ድል በመቀዳጀት የኢትዮጵያን ዘለቄታዊ ነጻነት ያጎናጸፉ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ያስከበሩ ጀግና መሪ በመሆናቸው ነው፡፡ ጥላሸት ይቀቧቸዋል ምክንያቱም ምኒልክ እውነተኛ የአፍሪካ መሪ በመሆናቸው ነው፡፡ የአጼ ምኒልክን ስም በማጥፋት እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ያበረከቱትን የውርስ ትሩፋታቸውን በማንቋሸሽ ለአቶ መለስ ክብር ለመስጠት እና ከእርሳቸው የሚገኘውን ውርስ ብጹዕ/ቅዱስ ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡

ገዥው አካል የአጼ ምኒልክን ታሪክ በእራሱ ታሪክ ለመተካት ይፈልጋል፡፡ አጼ ምኒልክ የባቡር ሀዲድ በመዘርጋት የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ነበሩ፡፡ ይህንን አንጸባራቂ ታሪክ በመለወጥ አቶ መለስ ረዥም፣ ቆንጆ እና ቀላል የባቡር ሀዲድ ሲስተም በኢትዮጵያ ለማምጣት የመጀመሪያው መሪ ነበሩ በማለት የታሪክ ባለቤትነት ሽሚያን ለማጎናጸፍ ይፈልጋሉ፡፡ አጼ ምኒልክ የስልክ እና የቴሌግራፍ አገልግሎትን በአፍሪካ አህጉር በማስተዋወቅ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ነበሩ። እ.ኤ.አ በ1889 አሌክሳንደር ግራህም ቤል “የድምጽ መነጋገሪያ መሳሪያ” የፓተንት ዕውቅና ካገኙበት 13 ዓመታት በኋላ እና በአጼ ምኒልክ ቤተመንግስት የመጀመሪያው የስልክ መስመር በተዘረጋበት ጊዜ በቴክኖሎጂው ሁኔታ ጭንቀት ውስጥ ገብተው የነበሩት የቤተክህነት ሰዎች ይህ የሰይጣን ስራ ነው በማለት ንጉሱ እንዲያስወግዱት በጠየቋቸው ጊዜ አጼምኒልክ ለቴክኖሎጂው ጠቀሜታ ካላቸው ጽኑ እምነት አኳያ ሳያስወግዱት ቀርተዋል፡፡
በአስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አጼ ምኒልክ አዲስ አበባን .....

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አራት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

በአስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አጼ ምኒልክ አዲስ አበባን በምስራቅ ኢትዮጵያ ከምትገኘው የሀረር ከተማ ጋር የሚያገናኝ የስልክ መስመር በመዘርጋት መርቀው ከፈቱ፡፡ ያንን አንጸባራቂ ታሪክ ወደ ጎን በማለት የአሁኖቹ ገዥዎች በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመገናኛ ቴክኖሎጂ ሲስተምን በኢትዮጵያ ያመጡ አቶ መለስ ዜናዊ እንደሆኑ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ እውነታው ግን በተገላቢጦሽ በአፍሪካ የስልክ እና የቴሌግራፍ መስመር በመዘርጋት ግንባርቀደም የነበረችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከአፍሪካ በመጥፎ የተንቀሳቃሽ ስልክ እና የኢንተርኔት አግልግሎት አጠቃቀም ሳቢያ በመጨረሻው እረድፍ ላይ ትገኛለች፡፡ ባለፈው ሳምንት የዎል ስትሪት መጽሄት/Wall Street Journal እንደዘገበው በኢትዮጵያ ውስጥ አርሶ አደሮች የተንቀሳቃሽ ስልኮች ቢይዙም “ችግሩ የግንኙነት መስመር ለማግኘት ብዙ ማይሎችን (ኪሎሜትሮችን)መጓዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡“ በማለት የችግሩን አሳሳቢነት አመላክቷል፡፡ ኢትዮጵያ በመጥፎ የኢንተርኔት አገልግሎት አጠቃቀም ከአፍሪካ ከመጨረሻዎቹ ሀገሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

የዘመኑ ገዥዎቻችን አጼ ምኒልክ የሴቶችን ጡት ቆርጠው የሚጥሉ ጨካኝ ንጉስ እንደሆኑ አድርገው ታሪክን አዛብተው ለመጻፍ ይፈልጋሉ፡፡ ጨካኝነት ከተነሳ ዘንድ ከአቶ መለስ ዜናዊ የበለጠ ጨካኝ እና አረመኔ ይኖራልን? አቶ መለስ እራሳቸው እ.ኤ.አ በ2005 በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ መጭበርበር ምክንያት ተቃውሟቸውን ለመግለጽ በወጡ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ለአነጣጥሮ ተኳሽ ጦራቸው ትዕዛዝ በመስጠት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ አድርገዋል፡፡ ይህንን እልቂት አስመልክቶ በእራሳቸው በአቶ መለስ ልዩ ትዕዛዝ ጉዳዩን እንዲያጣራ የተሰየመው የአጣሪ ኮሚሽን ምርመራውን አካሂዶ ባቀረበው ዘገባ መሰረት በአቶ መለስ ቀጥታ ትዕዛዝ እና ቁጥጥር አማካይነት የፖሊስ እና የደህንነት ኃይሎች በዕቅድ ተይዞ እና ሆን ተብሎ ታስቦበት 193 ሰላማዊ ሰዎች እንዲገደሉ እና ሌሎች 763 ሰዎች ደግሞ ከባድ ቁስለኛ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ እ.ኤ.አ በ2004 አቶ መለስ እራሳቸው ለታጣቂዎቻቸው ትዕዛዝ በመስጠት በምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ 400 ሰላማዊ ዜጎች እንዲያልቁ አድርገዋል፡፡
ኦጋዴን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተካሄደውን የአየር ድብደባ እና መንደሮችን በማቃጠል የጥቃት ሰለባ ያደረገው ወንጀል የተፈጸመው በአቶ መለስ ስልጣን ልዩ ትዕዛዝ ነበር፡፡ በአቶ መለስ ትዕዛዝ በኦጋዴን ታጣቂ ኃይሎች ሴቶችን አስገድደው ደፍረዋል፣ መንደሮችን አቃጥለዋል፣ ህዝቡን በሽብር ቆፍን ውስጥ ለመሸበብ ሲባል “የመቀጣጫ ግድያዎችን” ማለትም በህዝብ ፊት በአደባባይ በስቅላት እንዲሁም ጭንቅላትን ቆርጦ የመጣል ወንጀሎች እንዲፈጸሙ ተደርጓል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሂዩማን ራይትስ ዎች ተሟጋች ዳይሬክተር /United Nations Advocacy Director for Human Rights Watch ስቴቭ/ ክራውሻው በኦጋዴን አካባቢ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል “ትንሿ ዳርፉር” በማለት አመሳስለው ገልጸውታል፡፡
ገዥዎቻችን አጼ ምኒልክን የኦሮሞ ህዝቦች ጠላት እንደሆኑ.......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አምስት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ገዥዎቻችን አጼ ምኒልክን የኦሮሞ ህዝቦች ጠላት እንደሆኑ አድርገው ታሪክን በመበረዝ የታሪክ ድሪቶ አቀነባብረው እንደገና የጎደፈ ታሪክ ለመጻፍ ይታትራሉ፡፡ አቶ መለስ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ እሳቸው እና የዕኩይ ምግባር አጋሮቻቸው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እስከ አሁን ድረስ ያልተነገረውን እና ለመናገር የሚዘገንነውን በሰው ልጆች ላይ የፈጸሙትን ወንጀል ወደ ፍትህ አደባባይ በማቅረብ እንዲታይ ለማድረግ ከበቂ በላይ መረጃዎች አሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 ፍሪደም ሀውስ/Freedom House/ የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ባቀረበው ዘገባ መሰረት አቶ መለስ እና አገዛዛቸው በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሰፊ የሆነ የአድልኦ እና የጭቆና መረብ በመዘርጋት ተግባራት ላይ ተጠምደው ቆይተዋል፡፡ አቶ መለስ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን እንቅስቃሴ በመገደብ ብዛት ያላቸው ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የሚጠረጠሩ የድርጅቱን አባላት እና መሪዎችን ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስር በማዋል በማጎሪያ እስርቤት አስገብተው ሲያሰቃዩ ቆይተዋል፣ አሁንም በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2001 የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስልጣናቸውን ሲለቁ እንደተናገሩት “ወደ 25,000 የሚሆኑ የኦሮሞ ህዝቦች ከኦሮሞ ህዝቦች ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር በተያያዘ የገዥው አካል ክስ ምክንያት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች እና በአዲስ አበባ ከተማ እስር ቤቶች ታስረው በመማቀቅ ላይ ነበሩ፡፡” በማለት ይፋ አድርገዋል፡፡ የመለስ የትግል ጓድ እና የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ በሚያስገርም ሁኔታ እንደተመለከቱት “ቃሊቲ እስር ቤት ኦሮምኛ ይናገራል፣ በዚሁ ግቢ በአንድ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን በሚይዝ ካምፕ ውስጥ 99 በመቶ የሚሆኑት እስረኞች ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ አብዛኞቹ እስረኞች ደግሞ የታሰሩበት ምክንያት ምን እንደሆነ አያውቁም፣ ሆኖም ግን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተጠርጣሪ በመባል ዓመታትን በእስር ቤት በማስቆጠር ላይ ይገኛሉ፡፡“ በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2006 ጂሃዲስቶች (አሸባሪዎች) የሶማሌን አገር ወረዋታል እና የሶማሌ መንግስት ጣልቃ ገብቸ ጂሃዲስቶችን እንዳስወጣለት“ጋብዞኛል” በሚል ተንኮልን.........

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀