ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
በግርዶሹ ዙሪያ የተሰጡ ማሳሰቢያዎች
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የፀሐይ ግርዶሽ እና ጥንቃቄ!

የፀሐይ ግርዶሽን በዓይን በቀጥታ መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን ላይ ያደርሳል። ግርዶሹን ለመመልከት ፦

1. ደረጃውን የጠበቀ የግርዶሽ መነፅር መጠቀም

2. ፒን ሆል ካሜራ ወይም በአነስተኛ ቀዳዳ ወደ ድፍን ካርቶን የሚገባውን ብርሃን የሚስለውን ስእል ጀርባ ለፀሐይ በማዞር መመልከት

3. ጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባውን የፀሐይ ብርሃን መሬት ወይም ግድግዳ ላይ የሚሰራውን ስእል መመልከት

4. በዛፎች ቅጠል አልፎ መሬት ላይ የሚያርፈውን የፀሐይ ስእል መመልከት

5. ለቴሌስኮፕም ሆነ ባይነኩላር የፀሐይ ብርሃን መጣኝ ደረጃውን የጠበቀ ፊልተር ግጥሞ መመልከት

6. ግርዶሹን የሚያሳዩ የቀጥታ ስርጭቶችን መመልከት

የፀሐይ መነፅር ፣ ፍሎፒ ዲስክ ፣ የፎቶ ፊልም ፣የራጅ ፊልም እና የመሳሰሉት ቁሶች መጠቀም በዓይን ላይ ጉዳት ያደርሳል - #ESSS

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°

https://t.me/Readers_To_Know/458
ማስጠንቀቂያ

#የአይን_ብሌናችንን_እንዳናጣ_ጥንቃቄ

የሰኔ 14/2012 ዓ.ም የፀሐይ ግርዶሽን በተመለከተ የቀረበ መረጃ፡፡

🌑የ2012 ዓ.ም ግርዶሽ የሚታየው፡-

- ሰኔ እሁድ 14/2012 ዓ.ም ነው፣
- በግርዶሹ 6፡00 ሰዓት የሚፈጅ ጨለማ ይታያል፡፡
- በመላ ኢትዮጵያ ይታያል፡፡
- በተለይ ወለጋ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ አላማጣ፣ ኢንጂባራ 98% ጨለማ ሆኖ ይታያል፡፡
- የዓለምን አሰራር የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካን፣ የከፍተኛ የተፈጥሮ ኃይል ሊገኝ ይችላል ብለው ሳንቲስቶች ሀሳባቸውን እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡

- ከምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ድረስ ግርዶሹ ይታያል፡፡
- ፀሐይ 98% ትሸፈናለች፡፡

🌑የሚታይበት እና የሚያበቃበት፡-

- ከማዕከላዊ አፍሪካ ከኮንጎ ይነሳል፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ የመን፣ ፓኪስታን፣ ታይዋን፣ ንድና ቻይናን አቋርጦ ፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ ያበቃል፡፡


🌑ሙሉ ግርዶሹ የሚታይበት ወቅት

- ከሌሊቱ ሰኔ 14/2012 ዓ.መ
- 11፡00 ሰዓት ይጀምራል፣
- ከጠዋቱ 12፡45 እስከ ቀኑ 6፡33


‼️ማስጠንቀቂያ፡-

- በዓይን ለማየት አይቻልም ዐይን ያሳውራል፣
- በሱቅ ውስጥ የሚሸጥ መነጽር መጠቀም አይገባም፡፡
- ለፀሐይ ግርዶሽ ተብሎ የተዘጋጀ መነጽር አለ፡፡
- መነጽሩ አገር ውሰጥ አይገኝም፡፡
-ለፀሀይ ግርዶሽ የሚሆን መነፀር አለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ጥንቃቄ ያድርጉ
- ሲጨልም ማየት እንችላለን ነገር ግን ያለመነጽር ለማየት አንሞክር፣በጣም ጥንቃቄ ሊታከልበት ይገባል
- ዐይናችን ሊፈስ ይችላል፣


አብዛኛው ኢትዮጽያዊ መረጃው ስሌለው እና የፀሀይ ግርዶሽ የሚታይበት ቀን ስለደረሰ ቢያንስ ለ ሚወዷቸው 10ሰወች ሼር በማድረግ መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ የበኩልውን ይወጡ

🎖ዶ/ር ሊያ ታደሰ

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°

https://t.me/Readers_To_Know/458
አሁን ደግሞ ባለፎ የጀመርነውን የመ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰን ገለፃ እንቀጥላለን።
ሙሉውን ያለመታከት እንድታነቡት እጋብዛለሁኝ!
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓
________________
ካለፈው ክፍል የቀጠለ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
🎬🎬2ኛ)
ይህ የ2012 ዓ.ም. ግርዶሽ ከብዙ ሺሕ ዓመታት በፊት በጥንት ሥልጡን ሕዝቦች ይህ ክስተት መጠቆሙ ለእኔ አስደንቆኛል፡፡

🎬2.1
ይኸውም በማያ ሕዝቦች ይኸውም ከክርስቶስ ልደት በፊት 2000 ዘመን ቀደም ብለው የነበሩት ሥልጡን የማያ ሕዝቦች ልዩ የዘመን መቀመሪያና ትንቢታት ነበሯቸው፡፡ ይልቁኑ የነርሱ የዘመን ቀመር ማብቂያው 2012 ዓ.ም. ላይ ነበርና በፈረንጆቹ 2012 ዓ.ም. ላይ ከፍተኛ ፍርሃት የነበረበት ናሳም ይህን ይዞ በተደጋጋሚ መግለጫ የሚሰጥበት እንደ ነበር ብዙዎቻችሁ ታውቃላችኊ፡፡
2012 የሚል አስፈሪ ፊልም ተሠርቶ እንደነበር ትውስታችን ነው፡፡ ከብዙ ሺ ዓመት በፊት ማያዎች ከተናገሩት ውስጥ በ2012 ላይ መሬት፣ ጨረቃ፣ ፀሓይ፣ የፍኖተ ሐሊብ ማዕከል (ሚልክዌይ ሴንተር) አንድ መስመር ይሠራሉ (galactic alignment sun and milk way) ብለው ነበር፡፡ ያን መስመር ከሠሩ ዓለም ከሶላር ሲስተም ጋር የተያያዘች በመሆኗ ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ከፍተኛ ለውጥ ልታስተናግድ ትችላለች፤ የሰዎች አስተሳሰብ፣ ኢኮኖሚ ወዘተርፈ በማይገመት ፍጥነት ሊለወጥና ወደ ሌላ የዘመን ለውጥ መሄጃ ነው የሚል ነበር፡፡
ሆኖም ግን በሚገርም መልኩ በኢትዮጵያው የዘመን ቀመር ሠኔ 14/ 2012 ዓ.ም. (June 21, 2020) ያለው የፀሓይ ግርዶሽ ላይ ግን በሚገርም መልኩ ፀሓይ፣ ጨረቃ፣ መሬት አንድ መስመር በትክክል መሥራታቸው ብቻ ሳያበቃ በግንኙነት መስመራቸው ላይ ሰመር ሶልስቲስ ተጨምሮበታል፡፡
ይህ ሠኔ 14 ፀሐይ በሰማያዊው ሉል ላይ ወደ ሰሜን አቅጣጫ መጓዟን የምታቆምበት ዕለት ሲሆን “ሰመር ሶልስቲስ” (Summer Solstice) ይባላል፡፡ ይህ ዕለት በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ በጋ የሚጀምርበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በየዓመቱ ሠኔ 14 ላይ በሰመር ሶልስቲስ
ወቅት ፀሐይ ከአርክቲክ ወሰን በስተሰሜን ያለው ክልል ላይ 24 ሰዓት ሙሉ የማትጠልቅ ሲሆን አንታርቲክ መስመር ጀምሮ በስተደቡብ አቅጣጫ ደግሞ 24 ሰዓት ሙሉ ጨለማ የሚሆንበት አስገራሚ ዕለት ነው፡፡ ይህ የፀሓይ፣ የጨረቃ፣ የመሬት፣ የሰመር ሶልስቲስ ግንኙነት በዚህ ሳያበቃ “ከስካይ ክሮስ” ጋር መገጣጠሙ አስደማሚ ነው ይላሉ የዘርፉ ሳይንቲስቶች፡፡
ይህንን ይዘው ሳይንቲስቶቹ፦“The June 21st , 2020 summer solstice eclipse, will be the most amazing alignment in human history. This astronomical event that will no longer take place elsewhere ’ (የሠኔ 14/2012 ዓ.ም. የሰመር ሶልስቲስ ግርዶሽ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ እጅግ አስገራሚው የግንኙነት መስመር ይሆናል፤ ይህ የሥነ ፈለክ ሁኔታ በየትም ቦታ ያልተከናወነ ነው)
ብለዋል፡፡ ታዲያ ይኼ መገጣጠም በምድራችን ላይ ይዞት የሚመጣ ያልታሰበ ዐዲስ ለውጥ ይኖር ይሆን? የሚለው ጥያቄ መልስ ያልተገኘለት ነውና ከክስተቱ በኋላ የምናየው ይሆናል ሲሉ ግማሾቹ ሳይንቲስቶች ግማሾቹ ግን በትክክል ምድራችን ላይ ለውጥ ይኖራል ብለው ብዙ ጥናታዊ ጽሑፎችን አቅርበዋል።

°°°°° ይቀጥላል °°°°°

🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
#Caution
በዕለቱ ያለ eclipse viewer ፀሐይን በዐይን ለመመልከት መሞከር የዐይን ብርሃንን (አይናችን ሊፈስ ይችላል) አሳጥቶ ስለሚያሳውር ጥንቃቄ ያድርጉ። መነጽሩም🕶 ቢሆን የISO certification የማያሟላና ተመሳስሎ የተሠራ ከሆነ የአልትራ ቫዮሌት ጨረርን ስለማይቋቋም ከመጠቀም ይቆጠቡ። እንዲሁም የፀሐይ መነፅር ፣ ፍሎፒ ዲስክ ፣ የፎቶ ፊልም ፣የራጅ ፊልም እና የመሳሰሉት ቁሶች መጠቀም በዓይን ላይ ጉዳት ያደርሳል። ማንበባችሁን #React በማድረግ አሳውቁን!

እናመሠግናለን
#share #participate #comment

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°

📗📔📕
https://t.me/Readers_To_Know/460
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

________________
ካለፈው ክፍል የቀጠለ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

🎬2.2
ከብዙ ሺ ዓመት በፊት የነበረው በእንግሊዝ የሚገኘው የሥነ ፈለክ መቀመሪያ የነበረው “ስቶንሄንጅ” በመባል የሚታወቁት ድንጋዮችና እና ውጫዊው የአውብሬይ 56 ክበባዊ መዋቅር ጂኦሜትሪ በትክክል የሠኔ 14/ 2012 ዓ.ም. ግርዶሹ የሚሠራውን መስመር ጥንቱ የመሥራቱ ነገር ለአጥኚዎች አስገራሚ ሆኗል፡፡

🎬2.3.
የኦርዮንን ኮከብ የሚመስለው የጊዛ ታላቁ ፒራሚድ ቀመርም የሠኔ 14/ 2012
ዓ.ም. የግርዶሽ መስመር መሥራቱ ለአጥኚዎቹ አስደማሚ ነገር ከመሆኑ ባለፈ sacred geometry የመሥራቱ ነገር በአጥኚዎች ዘንድ አጀብ አስብሎታል፡፡

🎬2.4
የጥንት ቻይናውያን ዕውቀት የነበሩት ከሒሳብ ቀመር ውስጥ የባይናሪ ማቲማቲክስ ተጠቃሽ ነው፡፡ እነዚህ ሱፐር ኪውቢትስ በቅርቡ ሲሆን የተመረመሩት በኳንተም ኮምፒውተር ተካተዋል፡፡ በቻይናውያን ጥንታዊ የባይናሪ ቀመር ላይም የሠኔ 14ቱን ግርዶሽ ጠቋሚ ነገር ማግኘታቸው ለሳይንቲስቶቹ አስገራሚ ሆኗቸው ይህንን ብለዋል፡-
This indicates that the ancient Chinese not only knew about binary mathematics but that the primary number pattern within the binary system that points directly to the astronomical event on the 21 June 2020. ይህ የሚያመለክተው ጥንታውያን ቻይናውያን ያወቁት ስለ ባይናሪ ሒሳብ ብቻ ሳይሆን በባይናሪ ዘዴ ውስጥ ያሉት ፕራይመሪ ቊጥሮች ወደ ሠኔ 14ቱ 2012 ዓ.ም. የሥነፈለክ ክስተትን በቀጥታ ይጠቁማሉ፡፡ በማለት እየጻፉ ነው፡፡

°°°°° ይቀጥላል °°°°°

🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
#Caution
በዕለቱ ያለ eclipse viewer ፀሐይን በዐይን ለመመልከት መሞከር የዐይን ብርሃንን (አይናችን ሊፈስ ይችላል) አሳጥቶ ስለሚያሳውር ጥንቃቄ ያድርጉ። መነጽሩም🕶 ቢሆን የISO certification የማያሟላና ተመሳስሎ የተሠራ ከሆነ የአልትራ ቫዮሌት ጨረርን ስለማይቋቋም ከመጠቀም ይቆጠቡ። እንዲሁም የፀሐይ መነፅር ፣ ፍሎፒ ዲስክ ፣ የፎቶ ፊልም ፣የራጅ ፊልም እና የመሳሰሉት ቁሶች መጠቀም በዓይን ላይ ጉዳት ያደርሳል።

እናመሠግናለን
#share #participate For any #comment 👇

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°

📗📒📕
https://t.me/Readers_To_Know/468
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓
________________
ካለፈው ክፍል የቀጠለ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

🎬🎬3ኛ)
ሌላው ይኽ የሠኔ 14ቱ የፀሓይ ግርዶሽ በ4 ድብዝዝ የጨረቃ ግርዶሽ (ፕኑምብራል ሉናር ኤክሊፕስ) የተከበበ መሆኑ ለተመራማሪዎች ክስተቱ አስገራሚ ሆኗል፡፡ እነዚህም በታላላቅ ጨረቃ (super moon) የታጀቡ የጨረቃ ግርዶሾች ቀድመው ጥር 1 (January 10) ፤ ግንቦት 28 (June 5) በመቀጠል ሠኔ 28 (July 5) እና ኅዳር 21 (November
30) ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ድንቅ አድርጎታል።

🎬3.1
98 ፐርሰንት ፀሓይ ጨልማ እሳታማ ቀለበት ሠርታ አስደናቂ ቅርጽዋን በምትታይበት በላሊበላ ሰማይ ላይ ንጉሥ ላሊበላ የሠራውን “ፈለገ ዮርዳኖስ” በመባል የሚታወቀውን ቦታ የግርዶሹ መስመር አቋርጦ መሄዱ አስደናቂ ሆኗል፡፡ ይህንንም የናሳ ጉጉል ማፕ ላይ
ተመልከቱ፡፡ በተለይ ደግሞ ጠዋት ላይ ሁለቱ ፕላኔቶች ዐጣርድ (ሜርኩሪ) እና ዝሁራ (ቬነስ) በምሥራቅ ከፀሓይ ጐን ዐብረው ተሰልፈው በላሊበላ ሰማይ መታየታቸው ጥሩ አመስጣሪ ቢያገኝ መተንተን እንደሚችል ባውቅም ነገር ግን የላሊበላው ራሱን ችሎ
አንድ ትልቅ ጽሑፍ ሊወጣው እንደሚችል በመገመት ጽሑፌን እዚ ላይ እቋጫለሁ፡፡
ይህን ክስተት በዘመናችን በማየታችን እድለኛ እንደምንሆን ይሰማኛልና ክስተቱን በፍርሃት ሳይሆን ተፈጥሮን በማድነቅና በመደሰት እናሳልፈው እላለሁ፡፡ በተረፈ ስለመጪዎቹ ግርዶሾች አንድሮሜዳ መጽሐፋችን ላይ ስለተጠቀሱ እያነበባችሁ ዕውቀትን
ቅሠሙ በጥበብም ተራቀቁ።

መ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

°°°°° ተፈፀመ °°°°°

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
ካነበብነው📖📜📰🗞 pinned «የፀሐይ ግርዶሽ እና ጥንቃቄ! የፀሐይ ግርዶሽን በዓይን በቀጥታ መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን ላይ ያደርሳል። ግርዶሹን ለመመልከት ፦ 1. ደረጃውን የጠበቀ የግርዶሽ መነፅር መጠቀም 2. ፒን ሆል ካሜራ ወይም በአነስተኛ ቀዳዳ ወደ ድፍን ካርቶን የሚገባውን ብርሃን የሚስለውን ስእል ጀርባ ለፀሐይ በማዞር መመልከት 3. ጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባውን የፀሐይ ብርሃን መሬት ወይም ግድግዳ ላይ የሚሰራውን…»
ጥያቄ

Youtube ላይ የተለቀቀው የመጀመሪያው ቪድዮ ምን የሚባል ርዕስ ነበረው? የቪዲዮው ርዝመትስ ምን ያህል ነበር?
መልሶን @Feed_it_bot ላይ ይላኩልን።

@Readers_To_Know
​​ሰላም!
ነገ እሑድ ሰኔ 14 ከጠዋቱ 12:45 ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:33 ድረስ ከቶጎ ተነስቶ እስከ ፓስፊክ ውቅያኖስ ድረስ የፀሐይ ግርዶሽ ይታያል።
በኢትዮጵያ 3:19 ላይ ግርዶሹ ያበቃል ተብሎ ሲጠበቅ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይም ለ2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ እንደሚቆይ ቅድመ ትንበያዎች አሉ።
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
የተነገሩ የጥንቃቄ መንገዶች እንዳይረሱ!

ጥያቄ ለናንተ
. ላሊበላ ውስጥ የሚገኙ አብያተክርስቲያናት ስንት ናቸው?
. መጠሪያ ስማቸውን ካወቃችሁ?
. ላሊበላ ከዋና ከተማችን ከአዲስአበባ በስንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች?

መልሳችሁን @Feed_it_bot ላኩልን!
@Readers_To_Know
እስካሁን ባለን መረጃ የነገው ተፈጥሮአዊ ክንውን በቀጥታ በEBC እንዲሁም በአምሐራ ቴሌቪዥን እንደሚተላለፍ ነው።
@Readers_To_Know
የዛሬው ተፈጥሮአዊ ክስተት በEBC ዜና እንዲሁም በትግራይ ቴሌቪዥን በመተላለፍ ላይ ይገኛል።
@Readers_To_Know
🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂
🥀ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰብ አባላት እንደምን አላችሁ! የቤት ውስጥ ቆይታ እንዴት ይዞአችኋል? መፅሐፍትን እያነበባችሁ ግዜያችሁን የምታሳልፉ እንዳለችሁ ተስፋ እናደርጋለን። እናም ካነበባችሁት በጥቂቱ ማካፈል ለምትፈልጉ 👉 @Feed_it_bot ላይ ላኩልን!

እናመሰግናለን

@Readers_To_Know
📓📓📓📓📓📓📓📓
😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣

አባትና የደረሰች ሴት ልጁ እየተጨዋወቱ ሳለ ልጅ በመሀል " አባዬ! ትናንትና ከኔ ጋር ያየኸው ልጅ እኮ እጮኛዬ ነው፤ ደስ አይልም? " ብላ አባቷን ትጠይቀዋለች።
አባት፦ " ጥሩ ነው፤ ጨዋ ሰው ይመስላል... ለመሆኑ ደህና ገንዘብ አለው? "
ልጅ፦ " በጣም ይገርማል!! ... እንዲያው ወንዶች ስትባሉ በቃ ባህሪያችሁ አንድ ነው ማለት ነው?!! ...እርሱም ሁልጊዜ ስላንተ የሚጠይቀኝ አባትሽ ምን ያህል ገንዘብ አለው እያለ ነው!!"😂😂😂😂
ምንጭ፦ እስኪ ዛሬ እንኳን እንሳቅ በቅዱስ-ሀብት በላቸው

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
እንደምን አላችሁ!❤️

"አሁን እያሰብኩ ያለሁት ዓለምን እየወረራት ስላለው ክፉ የጥፋት ደዌ ሳይሆን ደዌው ገና ስላልደረሰባት ውብ ጎኗ ነው።"
ገፅ 130 🥀አና ፍራንክ🥀

@Readers_To_Know
ካነበብነው📖📜📰🗞
​​ሰላም! ነገ እሑድ ሰኔ 14 ከጠዋቱ 12:45 ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:33 ድረስ ከቶጎ ተነስቶ እስከ ፓስፊክ ውቅያኖስ ድረስ የፀሐይ ግርዶሽ ይታያል። በኢትዮጵያ 3:19 ላይ ግርዶሹ ያበቃል ተብሎ ሲጠበቅ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይም ለ2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ እንደሚቆይ ቅድመ ትንበያዎች አሉ። 🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔 የተነገሩ የጥንቃቄ መንገዶች እንዳይረሱ! ጥያቄ ለናንተ . ላሊበላ ውስጥ የሚገኙ አብያተክርስቲያናት…
🥀 መልስ 🥀
_____________
የላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ላሊበላ ከአዲስ አበባ በግምት 600 ኪ.ሜ ላይ ትገኛለች። ዩኔስኮም እዚህ የሚገኙ 11 ቤተክርስቲያናትን መዝግቧል። እነሱንም ቀጥለን እናያለን፦
በስተ-ሰሜን
° ቤተ መድሃኔዓለም
° ቤተ ማርያም
° ቤተ ጎሎጎታ ሚካኤል (የንጉስ ላሊበላ መቃብር
የሚገኝበት)
° ቤተ መስቀል
° ቤተ ደናግል
በስተ-ምዕራብ
° ቤተ ጊዮርጊስ (የመስቀል ቅርፅ ይዞ ከላይ
የሚታየን)
በስተ-ምስራቅ
° ቤተ አማኑኤል
° ቤተ ቅዱስ መርቆርዮስ
° ቤተ አባ ሊባኖስ
° ቤተ ገብርኤል ወሩፋኤል
° ቤተልሔም

ስለተሳተፋችሁ እናመሰግናለን
ሀሳብ አስተያየት እንዱሁም ያላችሁን ለማጋራት @Feed_it_bot

@Readers_To_Know
🦅🖊 ስነግጥም 🖌🦅

የስልጣኔ ምንጭ፣ የሰው ዘር መገኛ፣ የታሪክ
ከበርቴ መሆናችን ታውቆ ባለም ከተወራ ፤

እኛ ምንተዳችን "ጭራ ናችሁ" ሲሉን ከድሆችም ጎራ ፤

ምናባቱ ዛሬ ምናባቱ ነገ ኮርቶ መኖር ካለ በትናንት አሻራ ።

ምንጭ:- ሙሉነህ መንግሥቱ፣ ጉራማይሌ

ከእናንተው ከተላከልን!
እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🦅🖊 ስነግጥም 🖌🦅

አይቀርም
""""""¤¤¤¤""""""

አዳም ነውና አባይ ሴትን ተከትሎ ፤
ሊደርስባት ሲከንፍ በፍቅር ነሁልሎ ።
ሱዳኒት ግብፂትም እየሸነገለች ከፊት ከፊት
ቀድማ ፤
ኪሱን ስታራግፍ በፍቅር ሲጠማ ፤
ላቡን አንጠፍጥፎ በረሀ ሲለማ ።
ጉልበቱ ሲሟጠጥ በጣር እያማጠ ፤
ፊቱን አዞረና ለናቱ እጁን ሰጠ ።

ምንጭ:- አለሚቱ ዳመና፣ 2004

እናመሠግናለን
Don't forget to
#share our channel

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀