ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
🤰👩‍👦መልካም የእናቶች ቀን👩‍👦🤰

እማምዬ የፍቅር ጥግ፣ የእናትነት አልፋና ኦሜጋዬ። እናንተ "ሴት እናት ናት! ሴት እህት ናት! " የምትሉ 'በደፈናው ኃይማኖተኛ ሁሉ መነኩሴ ነው' እያላችሁ ነውና ይቅር ይበላችሁ፤ ሴትነት እናትነት አይደለም። "ሴት ከውስጧ የወጣ ገዳም ውስጥ ስትመንን እናት ትሆናለች" ሴት.... "ልጅ" የሚባል መስቀል ተሸክማ የሕይወትን ቀራንዮ ስትወጣ 'እናት' ትባላለች፤ ሴት ልጅ የራሷን ዘመን ይቅርብኝ ብላ የልጆቿ የዘመን መስቀል ላይ በፍቅር ስትቸነከር ወደ እናትነት ከፍታ ታርጋለች።

ዶክተር አሸብር እና ሌሎችም፡ ከአሌክስ አብርሃም , ገጽ 52

እናመሰግናለን

#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
መልክአ እናት

ሰላም ለኪ እናታችን ባለሽበት እንዳለሽ
ከዘመኑ ሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ።

ሰላም ለአይኖችሽ
ከጭስ ጋራ ለሚሟገቱ
ከእንቅልፍ ጋር ለተፋቱ
ተቀበዝባዥ ፍጡር ሆኜ ኑሮየን ከምገፋ
ምነው እንባሽን ባረገኝ ካ'ይኖችሽ ስር እንዳልጠፋ

ሰላም ለከንፈሮችሽ
ትናንት ለማውቃቸው
ዛሬ ለምናፍቃቸው
ውዳሴ ክብር ምርቃት
ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት ሞልቶ በተረፈበት ቀዬ
ምነው ያንችን እርግማን ይናፍቃል ጆሮዬ
ከሌሎች ውዳሴና ክብር እልፍ ጊዜ የተሻለ
ለካ በእርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ።

ሰላም ለጣቶችሽ
ለሰዎች የቀረቡ ፣ከራስሽ ግን የራቁ
መስጠት መለገስን እንጂ መቀበልን ለማያውቁ
ሰላም ለኪ!
ባለሽበት እንዳለሽ።

( በእውቀቱ ስዩም፡ ኗሪ አልባ ጎጆዎች እና ሌሎችም የግጥም ስብስብ, ገፅ 32)
መልካም የእናቶች ቀን❤️🙏
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@C_h_aa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
እናት
-----
በአሐቲ ግብሩ፣እግዜር ተሳሳተ
ለልጆች አድልቶ፣ለ'እናት ሰሰተ
በዝቶ ካልጠቀመ !
መናኛ ከሚያበጅ ፣ እየደጋገመ
ከሚባክን ጭቃ…
ልጆችን ቀንሶ ፣ እናት በደገመ
እንደ ሮሐ ውቅር
እንደ ደብረ ኤረር
እንደ ዙፋንህ አምድ፣አንተን ተሸካሚ
ዘላለም 'እማ' ቶድቅ
ባደረ'ካት እሷን ፣ ..እንደ ኪሩብ ቋሚ
.
« ሚኪ እንዳለ »
እናመሠግናለን
#share #participate #comment

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🦅🖊 ስነ_ግጥም 🖌🦅

ሲጎል እያንኳኳ ግብር የጠየቀ፤
ማን ሊኖር እንደሆድ መብቱን ያስጠበቀ?
አሻፈረኝ ቢሉት ጦርነት አውጆ፤
አካላትን ማርኮ እሚያውል ከጎጆ።
በቀን ሶስት አራቴ እያንደረደረ፤
ንጉሥ ድሀ ሳይል ሁሉን ያስገበረ።
ጀግናስ ማለት እሱ ማንንም ማይፈራ፤
በመኖሩ ብቻ
ግብር የሚያስከፍል ከሰራም ካልሰራ ።

ምንጭ:- አለሚቱ ዳመና ፤ተስፋ አብ ዳካ ፤ 2004 ፤ ገጽ 93

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

📣 Quote :- Don't let yourself be controlled by three things:
🤦‍♂people🤦‍♀,
💸money💰, or
🔙past experiences.


🌈 The largest cave in the world, Hanson Doong, is in vietnam. It's over 200 meters high and has it's own climate⛅️, jungles🏞, rivers, and clouds☁️ inside.

🌡. በ1643 terriceli የተባለው ኢጣሊያዊ ባሮሜትርን (Barometer) ፈጥሮ ነበር።

🌊 በ1849 እ.ኤ.አ 6 ሜትር ቁመት ያለው በረዶ በስኮትላንድ ከሰማይ ወርዶ ነበር።😳🤷‍♂

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
💫🌪 ጥቆማ 🌪💫

" እኔና ቹ "
ደራሲ ፍስሐ
ድርሰቱ በእሱና በቻይናዊቷ ፍቅረኛው መካከል በነበረው ግንኙነት አብረው ስላሳለፏቸውና ስለተጨዋወቷቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በመመርኮዝ ብዙ አገራዊም ሆነ ማህበረሰባዊ ችግሮችን እያሳዘነም፤ እያዝናናም፤ እያስገረመም ለማሳየት ይሞክራል። ቢያነቡት ብዙ ጥቅም እንደሚያገኙበት እኔ ምስክር ነኝ።
እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

.......ኢትዮጵያ 11.5 በመቶ እድገት ባስመዘገበች ቁጥር አንድ ምግብ ላይ 11.50 ጨምሮ ያድራል። ገቢው ግን ከማደጓ በፊት የነበረው ገቢ ነው። ምንም አይነት የኢኮኖሚ ሳይንስ ውስጥ መግባት ሳያስፈልግ የእያንዳንዱ አገር እድገት ከነዋሪው ህዝብ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መገናኘት ካልቻለ እንዴትም ሆኖ እድገት መባል እንደማይችል መከራከር ያስችላል። እኔ በግሌ "ኢትዮጵያ ልታድግ ነው" ሲባል ፍርሀት ይወረኛል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ባደገች ቁጥር መብላት እያቃተኝ እንደምሔድ አውቀዋለኋ! ......
ምንጭ:- እኔና ቹ ገፅ 175
ደራሲ ፍሰሀ
እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

.........ኢትዮጵያ ውስጥ በየቢሮው ዛሬ ከምሳ በፊት ምን ሲሰራ ዋለ ብትይኝ፤ የምሰጥሽ መልስ ማናጀሮች የኮምፒውተር ጌም ሲጫወቱ፣ ፀሐፊዎች ተሰብስበው ተራ የመንደር ወሬ እያወሩ፣ የበላይ አለቃቸው ሊያሽኮረምማቸው መፈለጉን ሲተርኩ፣ ሌላው የቢሮ ሰራተኛ በቢሮ ስልክ ከወዳጅ ዘመዱ ጋር ረጅምና እርባና ቢስ ወሬ ሲያወራ፣ የቀረው እንደኔና እንደአንቺ ሲሟገት፣ ሌሎቹ በስብሰባ ሰበብ እሽግ ውሀ ሲጎነጩ... ወዘተ ነው። ስልክ እያወራ ወይም ቢሮውን ዘግቶ የእኔ አይነት የኮምፒውተር ጌም ሲጫወት የነበረ ማናጀር በጌሙ በጣም ከመመሰጡ የተነሳ ባለጉዳይ መምጣቱ በፀሐፊው በኩል ሲነገረው "ስብሰባ ላይ ነው" በያቸው ብሎ ሲመልስ ነው የምሳ ሰዓት የሚደርስለት። ከሰዓትም እንደዚያው። ወይኔ ቹ የኢትዮጵያን ቢሮክራሲ ተዟዙረሽ የማየት እድል ቢገጥምሽ ከመገረም አልፈሽ ጨርቅ ወደመጣል ታመሪያለሽ። እንዲያውም በአጭሩ ይችን አገር ያደቀቃት ሌላው ችግር ስብሰባ ነው። ስብሰባና ጭብጨባ የዚች አገር አንኳር ችግሮች ናቸው። ታምኛለሽ .... በየመንግስት መስሪያ ቤቱ ቢያንስ በሳምንት አራት ቀናት የሙሉ ቀን ስብሰባ አለ። ከስድስቱ ቀናት ወይም ከአምስት ቀን ተኩል ውስጥ አራት ቀናት በስብሰባ ያልቃል! ከስብሰባ ይልቅ ግምገማ ቢባል ይሻላል። በዚህ ምክንያት ብቻ በየዘርፉ ያሉ ባለጉዳዮች ለአንዲት ፊርማ ልክ እንደ ኢሚግሬሽን ሦስት ወር ይጉላላል! ለአንዲት ፊርማ! ለምን?.... ፈራሚው ስብሰባ ላይ ነዋ! በዚህም ላይ በእያንዳንዷ ስብሰባ ለተሰብሳቢው በመስሪያ ቤቱ በጀት እሽግ ውሀ ይቀርብለታል። ለ30 ደቂቃ ስብሰባም ቢሆን የ30ሺ ብር ውሀ ሊቀርብ ይችላል። ያውም ላይጠጡት ከፍተው ተጎንጭተው ትተውት ለሚወጡት ውሀ! ደንብ ነውና ይቅርብኝ የሚል የለም። ስለዚህ ሳይጠማቸው ይጠጡና አስተርፈውት ይወጣሉ። ከዚህ ቢሮ ወተሽ ጥቂት መቶ ኪሎሜትር ስትጓዥ አንዲት ዳቦ አጥተው በረሀብ የሚሞቱ ልጆች ታገኛለሽ። በስብሰባው ላይ ግን ስለ ረሀብ አይነሳም። እድገት ነው የሚተነተነው። ኢትዮጵያውያን ዜጎች ምንም አይነት ጉዳይ ይኑራቸው ያለወረፋ ሊፈፅሙት የሚችሉት አንዳችም ጉዳይ የለም። ቴሌ ወረፋ፣ ፍርድ ቤት ወረፋ፣ ሆስፒታል ወረፋ፣ መሬት አስተዳደር ወረፋ፣ መንገድ ትራንስፖርት ወረፋ፣ መዘጋጃ ቤት ወረፋ፣ ፖስታ ቤት ወረፋ፣ መብራት ሀይል ወረፋ፣ ውሀ ልማት ወረፋ በቃ ሁሉም ቦታ ወረፋ! ለምን?....ስብሰባ!....። ከዚያስ? ጭብጨባ!.... ከዚያስ? የባለጉዳይ መጨናነቅ። ከዚያስ? ወረፋ የሰለቻቸውን ሰዎች ለማበርከት መጣር። ከዚያስ? ባለጉዳዩን ለጉቦ ማመቻቸት። ከዚያስ? በጎን እያስጨረሱ መዝረፍ! ይህ ነው ትክክለኛው አሰራር።
ገፅ 178-179 እኔና ቹ

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ!

🌿🌿🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿 🌿 🌿🌿
🌿🌿🌿 🌿🌿🌿
🌿 🌿
🌿 🌿🌿🌿🌿
🌿🌿 🌿 🌿
🕌 ሙባረክ 🕌

በዓሉ የሰላም የፍቅር ያድርግልን! መጪው ግዜ ከገባንበት ችግር ተላቀን ደማቅ ደማቅ በዓሎችን እንደድሮው ተሰባስበን የምናከብርበት ያድርግልን!
ሰላም ፍቅር ለሁላችሁ ተመኘሁ!

🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌
@Readers_To_Know
🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

........" 'ዓለማችን ውስጥ ካሉ ሰባት ቢሊዮን ህዝቦች ውስጥ ሞትን የማያውቅ የለም። ስለ ሞት የማያውቅ ሰው የለም። ሞት መኖሩን ሁሉም ያውቃሉ። በትክክል ሞት መኖሩን የተረዱት ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው ብዬ አምናለሁ። ሞት መኖሩን ማወቅ ብቻውን ማወቅ አይባልም። ሞት መኖሩን አውቃለሁ፤ ስለዚህ እንዴት መኖርና እንዴት መሞት ነው ያለብኝ? ብሎ ራሱን የጠየቀና ምላሹንም ያገኘ፣ ምላሹን አግኝቶም በተግባር ሞት ከመኖሩ ጋር በተገናዘበ መልኩ ህይወቱን የሚመራ ብቻ ነው ሞት ስለመኖሩ ያወቀ ሰው የሚባለው። ይህን የተረዳ ሰው ምንግዜም ለህሊናው ተገዢ ሆኖ ይኖራል። አለአግባብ ለመበልፀግ ሲል የሚሮጠውን ሩጫ ያቆማል፤ ለገዘፈ ሀብት ብሎ በግፍ የሰው ነፍስ ከማጥፋት ይቆጠባል። ሞትን ማስቀረት ከማይችል ከባዕድ አምልኮ ራሱን ያገላል። በዚህም ከመጥፎ ተግባር ይቆጠባል። አሟሟቱን አሳምሮ ኑሮውን በአግባቡ ይመራል። ወራሽ ሳይኖረው በዘጠና ዓመቱ ሲዘርፍ በኖረው ገንዘብ ረጅም ህንፃ መስራቱን ያቆማል። ሊሰራ የሚችለው በሀቅ ገንዘቡን ብቻ ይሆናል። ሞት መኖሩን የተረዳ ባለስልጣን በይው አገር መሪ ህዝቦቹን እያስራበ በውጪ አገር ባንኮች ቢሊዮን ዶላሮችን ማስቀመጡን ይተዋል። ስለዚህ በኔ ፍልስፍና የሰው ልጅ የመጨረሻው የጥበብ ጣሪያው ላይ ደረሰ የሚባለው ሞት መኖሩን ሲያውቅና ሲረዳ ነው ባይ ነኝ። ታውቂያለሽ እኔ በእያንዳንዷ የህይወት ጉዞዬ ላይም ሆነ እለት ተእለት የምፈፅመውን ማናቸውንም ተግባር ከመጨረሻዋ ህይወቴ ጋር አገናኛታለሁ። እኔ ለመሞት እያጣጣርኩ በህመም ይሁን በእድሜ ማብቃት ምክንያት አልጋ ላይ ተኝቼ ማሰብ የምፈልገው ያለፈ የህይወት ጉዞዬን ነው። ያንን አስቤ ምንም አይነት የሚፀፅት መጥፎ ስራ አለመስራቴን ከተረዳሁ በቃ! ፈገግ እንዳልኩ እሞታለሁ ማለት ነው። በዚያን ጊዜ ሞትን መፍራት አይታሰብም። ከሞት በኋላ ስላለው ነገር መጨነቅም አይኖርም። አየሽ ለህሊና ተገዢ መሆን የፈለኩትም ሆነ የሆንኩት ለጥቅሜ ስል ነው። ይህችን ጥቅም ማጣት አልፈልግም። ይህንን በመረዳቴ ነው ራሴን እንደ እድለኛ የቆጠርኩት።'

'ፍፁም ሆነህ ግን መሞት አትችልም።'

'አልችልም። የአቅሜን ያክል ነው የምጠነቀቀው። ከአቅም በላይ ሆኖ ለፈፀምኩት ተግባር ልፀፀት አይገባኝም ይቅርታ ልጠይቅ ብቻ ነው የምችለው።'' ......"

ምንጭ:- እኔና ቹ ገፅ 165
ደራሲ ፍሰሀ
እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂
🥀ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰብ አባላት እንደምን አላችሁ! የቤት ውስጥ ቆይታ እንዴት ይዞአችኋል? መፅሐፍትን እያነበባችሁ ግዜያችሁን የምታሳልፉ እንዳለችሁ ተስፋ እናደርጋለን። እናም ካነበባችሁት በጥቂቱ ማካፈል ለምትፈልጉ 👉 @R_e_a_d_e_rs ላኩልን።

🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠
🦠አንገብጋቢ ካልሆነ ከቤት አንውጣ
🦠ርቀታችንን እንጠብቅ
🦠እጃችንን እንታጠብ
🦠የእኛ ጥንቃቄ ለወገኖቻችን መሆኑን
🦠እናስብ።
🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠🦠

እናመሰግናለን
የቤተሰባችን ቁጥር እንዲጨምር #share ማድረግ እንዳይረሳ

@Readers_To_Know
📓📓📓📓📓📓📓📓
🍂6710 ላይ፦

A - 1 Birr 💵
B - 10 Birr 💷
C - 50 Birr 💴
D - 100 Birr 💶
በመላክ ❤️ለልብ ህሙማን💔 ወገኖቻችን መድረስ እንችላለን!

🧞‍♂ ሁሌም ድጋፋችሁ አይለያቸው! 🧞‍♂

@Readers_To_Know
📓📓📓📓📓📓📓📓
😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣

...አንድ ሰውዬ ሁልጊዜ ወደ ቡና ቤት ጎራ ሲል አንድ አይነት መጠጥ በሶስት የተለያዩ ብርጭቆዎች በማዘዝ ፊት ለፊቱ ደርድሮ በየተራ ከሶስቱም እየተጎነጨ ነው የሚጠጣው። ታድያ ይህ ከሰው ለየት ያለ ባሕሪው የሚያስገርመው የመጠጥ ቤቱ አስተናጋጅ አንድ ቀን
" ይቅርታ ወንድሜ! ... ሁልጊዜ አንድ አይነት መጠጥ በሶስት ብርጭቆ እያዘዝከኝ ሁሉንም የምትጠጣው ግን አንተው ነህ፤ ከዚህ ሁሉ አንዱን ጠጥተህ ስትጨርስ ሌላውን ባመጣልህ አይሻልም?" ሲል ይጠይቀዋል።
ሰውየውም "የለም! የለም! አየህ! ይህ ትልቅ ምክንያት አለው፤ አንዱ ብርጭቆ የኔ ድርሻ ሲሆን ሁለቱ ግን ለስራ ፊልድ የሔዱ በጣም የምወዳቸው ጓደኞቼ ድርሻ ነው። ስለዚህ እነሱን ለማስታወስ ስል ነው በሶስት ብርጭቆ አዝዤ የምጠጣው" ሲል ይመልስለታል።
ታድያ አንድ ቀን ሰውየው አለወትሮው ሁለት ብርጭቆ መጠጥ ብቻ ቢያዘው፤ አስተናጋጁ ግራ በመጋባት "ውይ!! ዛሬ ምነው ሁለት ብቻ አዘዝከኝ?! አንዱ ጓደኛህ ሞተ እንዴ?" ሲል ይጠይቀዋል።....

ሰውየውም " የለም! የለም!፦ ሁለቱም ኧረ ደህና ናቸው!! እኔ መጠጥ ስላቆምኩ፤ የራሴን ድርሻ ቀንሼ ነው" ብሎት እርፍ 😂😂😂😂
ምንጭ፦ እስኪ ዛሬ እንኳን እንሳቅ በቅዱስ-ሀብት በላቸው

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

እንኳን ለሰኔ 1 ሰኞ አደረሳችሁ 😂

🦋. Quote :- A soft nature of a person does not mean weakness. Remember, nothing is softer than water, But it's force can break the strongest rock.

🌙. በመጀመሪያ ጨረቃ ላይ የወጣው የሶቤት ተወላጅ ኮሎኔል ዩሪጋጋሬ ይባላል። 🌎መሬትን ለመዞር አንድ ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ፈጅቶበታል።

🔭. በ1593 ኢጣሊያዊው ጋሊሊዮ ( Galileo ) ቴሌስኮፕን ( telescope ) ፈጥሮ ነበር።

🎞. "meet the zoo" የ18 ደቂቃ ቪድዮ የመጀመሪያው የ📽Youtube video ነበር።

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​......" THIS IS LIFE.
You are not beautiful, just your age is beautiful. It doesn't matter how you look and what's your skin colour cause everything will change with age. At the end you need a holding hand, not a perfect body and beautiful face...
Everyone is beautiful in there own way. You are not fat, slim, small, ugly, black, white. You are you and that's great. Don't judge anyone with their temporary appearance.".....


@Readers_To_Know
ተጠየቅ! - በላ ልበልሀ የጥንቱን የጧቱን ላሳይሀ!

ዘመኑ ድሮ ነው፤በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ-መንግስት።
ንጉስ ችሎት ተዘጋጅቶ ፣ሸንጎ ተሰርቶ አፄው ከመኳንንቱ ጋር ተሰይመዋል።ተሟጋቾቹ በአንድ ሰፊ መሬት የ"ይገባኛል" ክስ ለረጅም ጊዜ ሲከራከሩ ኖረው በመጨረሻም ንጉስ ችሎት የቀረቡ ሁለት ተዋቂ አርበኞች ናቸው።በተለያየ የጦር ሜዳ የፈፀሙት ጀብድ መሬቱን እንደሚያሰጣቸው በማመን ጀግንነታቸውን ለመዘርዘር አሰፍስፈዋል።

በመጀመርያ አንከስ የሚለው ግዙፍ አርበኛ ተነሳና እየተንጎራደደ" ንጉስ ሆይ!እግዜር ያሳይዎ፤መላዕኩ ያመልክቶ! እኔ አሽከሮ ደረቴን ለጦር እግሬን ለጠጠር እየሰጠሁ በብዙ ጦር ሜዳወች ለቁጥር የበዛ ጀብዱ ፈፅሚያለሁ።ጌታየ ጃነሆይ እዚህ ያላችሁ መኳንንትም ለዚህ ምስክር ናችሁ። ሌላው ሌላው ይቅርና አንዴ ከጠላት ጋር ስታኮስ በ17ጥይት እግሬን ተመትቼ መቁሰሌ አይዘነጋም።ስለዚህ መሬቱ የሚገባው ለኔ እንጅ ለሱ አይደለም።" አለና ሱሪውን ሰብሰብ አርጎ ጠባሳውን አሳየ።
ይሄኔ ሁለተኛው ባለጉዳይ ሲበዛ አፈ ጮሌና ብልህ ነበርና ወደ መጀመርያው ተናጋሪ በፌዝ እያየ"አይ የኛ አርበኛ!በ17ጥይት እግርህን መመታት ሙያ መሰለህ?
ለምን አንዱ ሲመታህ ዞር አትልም ነበር! እንደ ግድግዳ ተገትረህ ኢላማ ሲማርብህ ቢውል ግድ አለኝ እንዴ!" ብሎ ሲወርፈው የተሰበሰበው ታደሚ አንዴ በሳቅ አውካካ። እጅግ ከመሳቃቸው የተነሳ እንባቸው የሚወርደው እምዬ ምኒልክ እንደምንም ወደ መጀመርያው ተናጋሪ ዞረው" በል ለአንተ ሌላ መሬት እንሰጥሀለን ልጄ!ይሄኛው ለሱ ይገባል።"ብለው አሰናበቱት።

#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@C_h_aa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​🎥📻 ከታሪክማህደር 🎙🎞

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
💡 የአና ማስታወሻ 💡

ይህን ግለ ታሪክ የፃፈችው አና ትባላለች - ሙሉ ስሟ አና ፍራንክ። አሁን በሕይወት የለችም። በዚች ዓለም ላይ በሥጋ የኖረችው ለ15 ዓመታት ከዘጠኝ ወራት ብቻ ነው። በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1929 እስከ 1945 ዓ.ም። በመንፈስ ግን አሁንም አለች፣ ወደፊትም ትኖራለች።
1943 ዓ.ም ላይ የናዚ ወታደሮች አምስተርዳም ውስጥ አገር ሰላም ብለው ይኖሩ የነበሩ አይሁዶችን ከየቤታቸው እየለቀሙ ወደ ኦሽዊትና ወደሌሎች የግድያ ጣቢያዎች ማጋዝ ሲጀምሩ የአና ፍራንክ ቤተሰቦች ከግድያው ለማምለጥ ቀደም ብለው አዘጋጅተው ወደነበረው አንድ ሚስጥራዊ የመደበቂያ ሥፍራ ያመራሉ። ይህ ምስጢራዊ ቦታ የአና አባት አቶ ፍራንክ የአስመጪና ላኪነት ቢዝነሱን ያካሒድበት በነበረ ሕንፃ ጣሪያ ላይ ይገኛል። የአና ቤተሰቦች በቁጥር አራት ነበሩ፤ ማለትም ራሷ አና ፍራንክ፣ አባቷ አቶ ፍራንክ፣ እናቷ ኤዲት ፍራንክ እና ታላቅ እህቷ ማርጎት ፍራንክ።
አና ፍራንክ የምትታወቀው በፃፈችው ግለ-ታሪክ ሲሆን በዚሁ መጽሐፍ እንደገለፀችው " የሔዋን ሕልም " እና " የኬዲ ሕይወት "የተሰኙ ልቦለዶችን ፅፋ ጨርሳ ነበር። በግለ ታሪኳም የአፃፃፍ ብቃቷን አሳይታለች፤ በዚህም የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ሰው የሚለውን ማዕረግ ለመስጠት ከቀረቡ እጮዎች ውስጥ አንዷ ነበረች። እነዚህም አልበርት አነስታይን፣ ሲግመንድ ፍሮይድ፣ ቻርለስ ዳርዊን፣ ሉዊ ፓስተር እና አና ፍራንክ።
እናንተም ይህን መፅሐፍ እንድታነቡት እንጋብዛለን። እኛም በመጪው ጊዜ በአምስት ምዕራፎች በአጭሩ እናስቃኛችኋለን። ለጓደኞቻችሁ ማካፈልን አትርሱ ብቻችንን መብላት ባህላችን አደለምና!!!

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

💡 የአና ማስታወሻ 💡

......~~~~~~~~~.......
🥀 ክፍል አንድ 🥀
......~~~~~~~~~.......

.......ወጣም ወረደ ኪቲ አሁን አንድ ነገር ገብቶኛል። ሰዎችን በሚገባ የምታውቂያቸው ደህና አድርገሽ የተጋጨሻቸውና የተጣላሻቸው ጊዜ ነው። ያኔ ብቻ ነው ትክክለኛ ባሕሪያቸው እንደ ማሾ ፏ ብሎ የሚታይሽ።.....
ገፅ 40
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
........አንድ ሰው ጥሩና ትክክል ነው ብሎ ላመነበት ዓላማ ሁሉ ተገቢውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆን መቻል አለበት።..........
ገፅ 50-51
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
........ግን ቁንጫን ታህል ደቃቅ ነገር ሰውን የሚያህል ግዙፍ ፍጡር እንግዲህ እንደ እብድ ልታወራጨው ከተቻላት በእርግጥም ተፈጥሮ ኮሚክ ናት! .........
ገፅ 66-67
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
.........ታዲያ ይሄን ሁሉ እያመነዠኩ ራስን ላለማስጨነቅ ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነው። አዎ ኪቲዬ መፍትሔው አንድ ነው። ማንበብ። ቢጥምሽም ባይጥምሽም ያገኘሽውን ሁሉ ማንበብ። በበኩሌ ቢያዋጣኝም ባያዋጣኝም እያደረሱ ያለሁት ይህንኑ ነው።...........
ገፅ 72
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
..........ሞትን ተደብቆ የመኖርን ችግር ላላየው ሰው መግለፅ በጣም አስቸጋሪ ነው በየዕለቱ የሚያጋጥሙሽ ሁኔታዎች ፈፅሞ ለማመን የሚከብዱ ናቸው። የሁኔታው አሳዛኝነት የደረሰበት ደረጃ ማንም ሰው በውስጡ ሊኖረው ከሚችለው የማዘን አቅም በላይ ነው።..........
ገፅ 76
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
............የዕድሜ ልክ ምኞቴን ደግሞ አንቺም ታውቂያለሽ ኪቲዬ "አንገቷን ቀና አድርጋ ዓለምን በሙሉ ዓይኗ ማየት የምትችል የምትሔድበትን የምታውቅና አረማመዷም እርግጠኝነት የሚታይበት ለነጎድጓድም ሆነ ለመብረቅ የማትደነግጥ " ብቻ ምን ልበልሽ "ይህ ቀራት የማትባል ምሉዕ ሴት መሆን ነው የምፈልገው!" .............
ገፅ 96/118/
............~~~~~~~~...............

~~~~ይቀጥላል~~~~~

የአና ማስታወሻ /አዶኒስ እንደተረጎመው/ ከሚለው መፅሐፍ በጥቂቱ ያስተምራል እንዲሁም የፀሐፊዋን ድንቅ ችሎታ ያሳያል ተብሎ በድጋሚ የቀረበ። ቆይታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን!!!

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

💡 የአና ማስታወሻ 💡

......~~~~~~~~~.......
🥀 ክፍል ሁለት 🥀
......~~~~~~~~~.......

..........ለምን ይሆን ሰዎች ስንባል አንዳችን በሌላችን ላይ ያለን እምነት እንዲህ የሳሳው? ያለ አንዳች ምክንያት ይህ ሊሆን እንደማይችል አውቃለሁ ያም ሆኖ አንዳንዴ ምን እንደማስብ ታውቂያለሽ ኪቲ መቼም መቼም ቢሆን በሰዎች ላይ (የራሴ በምትያቸው የቅርብ ሰዎች እንኳን) እምነት ሊኖርሽ እንደማይችል ስታውቂ በጣም የሚያስፈራና የሚጨንቅ ነገር አለው። .........
ገፅ 96-97

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

...........ስለ እውነት ነው የምልሽ ኪቲዬ ብኖርም ብሞትም እምብዛም ግድ የማይሰጠኝ ደረጃ ላይ ደርሻለሁ። ምን የሚያስጨንቀኝ ነገር አለ? ዓለም እንደው አና ጎደለች ብላ ጉዞዋን አታቆም ነገር። መሆን ያለበት ነገር ተወደደም ተጠላም የግድ መሆኑ አይቀርም ይልቅ ይህን ለማገድ መሞከሩ ነው ከንቱ ድካም።..............
ገፅ 103

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

...........ሀብትህ፣ ንብረትህ ቢጠፋብህ መልሰህ ስለማግኘትህ እርግጠኛ መሆን አትችልም እንደጠፋም ሊቀር የሚችል ነገር ነው። ደስታህ ግን ጠፍቶ ሊቀር የሚችል ነገር አይደለም። ጊዜያዊ በሆነ ከፈን ሊጋረድ ብቻ ነው የሚችለው። እናም በህይወት እስካለህ ድረስ ያንን ከፈን ልትገልጠው ዕድሉ አለህ። ያለምንም መሸማቀቅና ፍርሀት የሰማዩን መንበር በሙሉ ዐይንህ ማየት እስከቻልክ ድረስ ውስጥህ ሙሉ በሙሉ ንፁህ እስከሆነ ድረስ!..............
ገፅ 114

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

~~~~ይቀጥላል~~~~

የአና ማስታወሻ /አዶኒስ እንደተረጎመው/ ከሚለው መፅሐፍ በጥቂቱ ያስተምራል እንዲሁም የፀሐፊዋን ድንቅ ችሎታ ያሳያል ተብሎ በድጋሚ የቀረበ። ቆይታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን!!!

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚