ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

ዓለማችን የሰለጠነች እንዳይመስላችሁ። የመጀመሪያው ዋሻ ቆፍሮ ይኖር የነበረው ሰው ከሥልጣኔ ቁንጮ ላይ እንደደረሰ ተሰምቶ ይሆናል። እሳትን የፈጠረውም እንደዛው። አሁን የተፈጠሩትን ውስብስብ መሣሪያዎች ስናይ ከሥልጣኔ ጫፍ የደረስን ሊመስላችሁ ይችላል። ነገርግን ዓለም ማብረቅረቅ ጀመረች እንጂ ገና አልሰለጠነችም። ... የሰው ልጅ የአዕምሮውን የመፍጠር እና የማሰብ ችሎታ ገና ምንም አልነካውም ማለት ይቻላል። የዛሬ መቶ ዓመት ከመቃብራችሁ ብትነቁ ይህን ታረጋግጣላችሁ። የሰው ልጅ የአእምሮ ህዋስ በብዙ ሚሊዮን እጥፍ ሊበለፀግ ይችላል።
ራማቶሓራ, ይስማዕከ ወርቁ፡ ገፅ 69

#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@zhangidaa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🧞‍♂👣 ከዚም_ከዛም 👣🧞‍♂

መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን ዕድል እንድትጠቀም ያደርግሃል፤ መሄድ ግን የማታውቀውንም ዕድል እንድትሞክር ያረዳሃል። ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ፣ ቆይቶም ትበሰብሳለህ። ስትሄድ ግን መጀመሪያ ትደክማለህ፣ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ። ባለቀ ትናንት አትታሰር፣ በተበላ ዛሬ አትወሰን፣ ይልቅ ወደማይታየው ነገ ሂድ። ነገ ወዳንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ። አንድ ቦታ ላይ የግድ እንድንቆም ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ሥር ይሰጠን ነበር። የመሄዳችን ዋናው ምክንያቱ የምንቆምበት ምክንያት አለመኖሩ ነው።


#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@zhangidaa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓 እኒህ የኢራቅ ኩርዶች የሚናገሯቸው ድንቅ አባባሎች ናቸው!
1 ችግሮችን ለመጋፈጥ ካልፈለግህ ችግሮችን እያነገሥካቸው ትሄዳለህ ይላሉ ኩርዶች፡፡ ችግርን ካታለልከው መልሶ ይይዝሃል፤ ከተጋፈጥከው ግን ጥሎህ ይሸሻል የሚል አባባልም አላቸው፡፡
2 የምትሠራው በር ምንጊዜም ልትሄድበት የምትችል መሆኑን አረጋግጥ፡፡ለአንድ ጊዜ መውጫ ብለህ በሩን ከሠራኸው ከበሩ በኋላ ወዴት እንደምትሄድ ግራ ይገባሃል፡፡በሩን ከነ መንገዱ አስበው፡፡መንገዱን ከነ መዳረሻው፤ መዳረሻውንም ከነመቆያው፤መቆያውን ከነ መክረሚያው፡፡
3 ችግርን በመፍትሔ መፍታትና ችግርን በሌላ ችግር ማለፍ ይለያያሉ፡፡ችግርን በችግር ካለፍከፈው ጊዜ እየገዛህ ነው፡፡ችግርን በመፍትሔ ካለፍከው ደግሞ ልብ እየገዛህ ነው፡፡❣️ እናመሠግናለን ❣️
#share #participate #comment

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓
ሂንዲዎች ብርሃነ-ሕሊና ለመጎናፀፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕይወቶችን መኖር ይጠይቃል ይላሉ፤ ቡድሂስቶች ደግሞ እንደ ጉተማ ቡድሃ ያለ ልዕለ-ሰብ ፍጡር እንኳን የሁሉ ነገር አናት ከሆነው የብርሃነ-ሕሊና ደረጃ ላይ ለመድረስ ከመቻሉ በፊት በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሕይወቶች ውስጥ ኖሮ ማለፍ እንዳለበት ይናገራሉ። በአጠቃላይ ሁሉም ብርሃነ-ሕሊናን መጎናጸፍ በጣም አስቸጋሪ፣ የማይቻልና ረቂቅ፡ ልዕለ-ሀይል ሰብዓዊ ፍጡራን ብቻ የሚታደሉት፡ እጅግ ልፋትን የሚጠይቅ መሆኑን አጥብቀው ያምናሉ። እኔ ግን ብርሃነ-ሕሊና (Enlightenment) በጣም ቀላል፡ እጅግ ቀላል ከሆኑ የተፈጥሮ ክስተቶች አንዱ ነው እላችኋለሁ።

ምንጭ፡ ብርሃነ-ሕሊና, ኦሾ

❣️ እናመሠግናለን ❣️
#share #participate #comment👇
@R_e_a_d_e_rs

@zhangidaa

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
😂🌍 ለፈገግታ 🌎😂

"እኔ በግሌ 'ኢትዮጵያ ልታድግ ነው' 😳 ሲባል ፍርሀት ይወረኛል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ባደገች ቁጥር መብላት እያቃተኝ እንደምሄድ አውቀዋለኋ!🤷‍♂ ኢትዮጵያ 11.5 በመቶ እድገት ባስመዘገበች ቁጥር አንድ ምግብ ላይ 11.5 ጨምሮ ያድራል። ገቢው ግን ከማደጓ በፊት የነበረው ገቢ ነው።"😂😂😂
ምንጭ፦ ይቅርባቹ 😜
እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🦅🖊 ስነ_ግጥም 🖌🦅

አባት
""""¤¤¤''''""
አባትም ያረግዛል
አባትም ያምጣል
አባትም ይወልዳል
እናት የሞተች ቀን አባት ሴት ይሆናል።
ያውም ከሴት ሴት ማህፀኑ ሰፊ ሲያፈቅር ካንጀቱ
ማለቂያ የሌለው ውቅያኖስ ነው ጡቱ
የአባትነት ፍቅር ልኩንም ላወቀው
እናት የሞተች ቀን አባትም እናት ነው።
~~~~~~~"""""""""""~~~~~~~

እናመሠግናለን
ለአስተያየት፣ እናንተ የፃፋቹት ነገር እንዲሁም እንዲፖሰትሎት የሚፈልጉት ነገር ካለ👉 @R_e_a_d_e_rs ምንጭ የተጠበቀ ነው።


📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
Forwarded from Quality ButtonSCAM
"ማንበብ አስተውሎትን፣ ጥበብን እና ትዕግስትን ታጎናፅፋለች"
Quality Button
"ማንበብ አስተውሎትን፣ ጥበብን እና ትዕግስትን ታጎናፅፋለች"
ይሄን ለወዳጅ ዘመዶችዎ share በማድረግ የቻናላችን ቤተሰብ አድርጓቸው
እናመሠግናለን
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

ኃይማኖት ያለ ዕውቀት አሸባሪ ያደርግሃል። ሥልጣን ያለ ዕውቀት አምባገነን ያደርግሃል። ነፃነት ያለ ዕውቀት ሥርዓት አልበኛ እና ሀኬተኛ ያደርጋል። ዕውቀት አልባነት የስህተቶች ሁሉ ስር ናት። ማርከሻው መድሀኒት ትምህርት ነው። በብራዚል እስር ቤት ውስጥ አንድ እስረኛ አንድ መፅሐፍ አንብቦ መጨረሱን ሪፖርት ባደረገ ቁጥር ከእስር ጊዜው ውስጥ አንድ ሳምንት ይቀነስለታል። የትምህርት ምንጩም መጽሐፍ ነው። ዓላማውም ዕውቀት እና ጥበብን መጎንጨት ነው።
ምንጭ፦ ዶ/ር ኬኬ

እናመሠግናለን
ለአስተያየት፣ እናንተ የፃፋቹት ነገር እንዲሁም እንዲፖሰትሎት የሚፈልጉት ነገር ካለ👉 @R_e_a_d_e_rs 👉 @zhangidaa ምንጭ የተጠበቀ ነው።

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🐎🐎📽 ክፍል አንድ 🎞🐎🐎

የአውሮፓ ሀገራት አፍሪካን በተቀራመቱበት ዘመን ኢጣሊያም ኢትዮጲያን በቅኝ ግዛቷ ለማድረግ መንገድ የሚከፍትላትን የውጫሌ ውል ከአፄ ምኒልክ ጋር ውጫሌ ከተማ ላይ በተወካይዋ አንቶሌኒ መሰረት ተዋዋለች፡፡ ከተደረገው ውል አንቀፅ 17 ግን የአማርኛ እና የኢጣልያንኛ ትርጓሜው የተለያየ ነው፡፡ በአማርኛ የተፃፈው ‹‹ ግርማዊ የኢትዮጲያ ንጉሠ ነገሥት ከአውሮፓ መንግስታት ጋር ግንኙነት ለማድረግ ወይም
ለመነጋገር ሲፈልጉ በግርማዊ የኢጣሊያ ንጉሥ አማካይነት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡›› የሚል ሲሆን የኢጣሊያንኛው ትርጉም ግን እንዲህ የሚል ነበር….‹‹ ግርማዊ የኢትዮጲያ ንጉሠ ነገሥት ከአውሮፓ መንግስታት ጋር ግንኙነት ለማድረግ ወይም ለመነጋር ሲፈልጉ በግርማዊ የኢጣሊያ ንጉሥ አማካይነት ያደርጋሉ፡፡›› የዚህ ፍቺው ኢትዮጲያ በኢጣሊያ ሞግዚት አስተዳደር ስር መሆኗን የሚገልፅ ነው፡፡ ይህንንም
የኢጣሊያ መንግስት ለአውሮፓ መንግስታት በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ይህም በታወቀ ግዜ አንቀፅ 17 ይቅር በሚል አፄ ምኒልክ ከባለሟሎቻቸው ጋር ወሰኑ
በዚህም ሌላ ውል ተፈረመ፡፡ ኮንት አንቶሌኒ ‹ይቅር› የሚለውን ቃል የተረዳው እንዳለ ይቀመጥ አይለወጥ በሚል ነበርና አለመሆኑን ሲረዳ ምኒልክ እልፍኝ ገብቶ ደነፋ፡፡
የኢጣሊያ መንግስት ይህን እንደውርደት ይቆጥራል፡፡ ክብሩን ለማስጠበቅ ጦርነት ያደርጋል፡፡ ክብሩን በጉልበት ያስጠብቃል ብሎ ፎከረ፡፡
~~~ ክፍል ሁለት ይቀጥላል ~~~

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🐎🐎📽 ክፍል ሁለት 🎞🐎🐎

እቴጌ ጣይቱ እንዲህ አሉት… ‹‹የዛሬ ሳምንት አድርገው፡፡ እኔ ሴት ነኝ፡፡ ጦርነት አልወድም፤ ነገር ግን ሀገሬን እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ! እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር
አስጥቶ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ለአፈሩ ክብር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ! ሂድ! የኢትዮጲያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው፡፡ ሂድ ባሻህ ግዜ ተመለስ ተሰናድተን እንጠብቅሃለን፡፡ ያንተን
ወንድነትና የጣይቱን ሴትነትም ያን ግዜ እናየዋለን ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ፡፡››
በዚህም የኢትዮጲያና የኢጣሊያ ወዳጅነት ጥያቄው፡ የጦርነቱ አይቀሬነትም ተረጋገጠ።
የኢጣሊያ መንግስት በተወካዩ አማካይነት ኢትዮጲያ ላይ ጦርነት ሲያውጁ አፄ ምኒልክ የኢጣሊያ በጦር መሳሪያም ሆነ በስልጣኔ ከፍ ማለቱ ሳያሸብራቸው ‹‹ቴዎድሮስ በመቅደላ ዮሐንስ በመተማ የሞቱላትን ሀገር እኔም ደሜን አፍስሼ ነፃነቷን አስጠብቃለሁ፡፡ እሞትላታለሁ›› ብለው አዋጅ አወጁ…
‹‹….የሀገሬ ሰው ከአሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም፤ አንተም አላስቀየምሀኝም፡፡ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ዕርዳኝ፤ ጉልበት የሌለህ ለልጅህ ለሚስትህ ለሃይማኖትህ ስትል በሐዘን ዕርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ፤ አልተውህም፡፡
ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም..ዘመቻዬ በጥቅምት ነው እና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ፡፡››
አዋጁን ተከትሎ ህዝብ ከዳር አስከ ዳር ተመመ፡፡ እቴጌይቱ እንዳሉት ደረቱን ለጥይት እግሩን ለጠጠር ሰጥቶ ሀገሩን ከጠላት ሊታደግ የኢትዮጲያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ነቅሎ ተነሳ፡፡
~~~ ክፍል ሶስት ይቀጥላል ~~~

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🐎🐎📽 ክፍል ሶስት 🎞🐎🐎

የሩቁንም ሀገር የጎጃሙንም፣ የደንቢያውንም፣ የቋራውንም፣ የበጌምድሩንም ከጨጨሆ በላይ ያለውን አገር ሁሉ አሸንጌ ድረስ ክተት ብለው አዘዙ፡፡ የሰሜንና የወልቃይት ጠገዴንም ሰው መቀሌ ድረስ ክተት ብለው አዘዙ፡፡ ከዚህ በኋላ ራስ መኮንን የሐረርጌን ጦር ይዘው በመስከረም እኩሌታ አዲስ አበባ ገቡ፡፡ ከጊቤ በታች ያለው አገር ጦር የወለጋው ሹም ፊታውራሪ ተክሌ ጦራቸውን ይዘው ገቡ፡፡ አፄ ምኒልክ አዋጃቸውን በመስከረም ወር ካስነገሩ በኋላ ለአገር ጥበቃ አጎታቸውን ራስ ዳርጌ ሣህለ ሥላሴን ሾመው እርሳቸው በጥቅምት 2 ቀን 1888 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ተነስተው በጊዳ በኩል አድርገው ጥቅምት 18 ቀን ወረይሉ ከተማ ገቡ፡፡ ከዚያም ራስ ሚካኤልን፣ ራስ ወሌን፣ ራስ መኮንንን፣ ራስ መንገሻ አቲከምን፣ ራስ አሉላን፣ ዋግሹም ጓንጉልን፣ ደጃች ወልዴን፣ ፊታውራሪ ገበየሁን፣ ፊታውራሪ ተክሌን፣ ሊቀ መኳስ አድነውን፣ ቀኛዝማች ታፈሰን ‹‹ቀድማችሁ ወደ አላጌ ዝመቱ የሚቀላችሁ ከሆነ ወጉት፡፡ የሚከብዳችሁ ከሆነ ላኩብኝ ›› ብለው አስቀድመው መላካቸውን ይነገራል፡፡
ምን አልባትም ይህ አዋጅ ታውጆ የኢትዮጲያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ተሞ አድዋ ላይ ጣሊያንን ድባቅ ባይመታ ኖሮ የኛ ዕጣ እንደሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራት በባርነት ቀንበር ወድቀን በኛ ማንነት ላይ የኢጣሊያ ማንነት ተለጥፎብን እንቀር ነበር፡፡ ለዛም አይደል
‹‹ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፡ ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ግዜ ሐበሻ›› የተባለው፡፡
~~~ ክፍል አራት ይቀጥላል ~~~

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🐎🐎📽 ክፍል አራት 🎞🐎🐎

የአድዋ ጦርነት የተጀመረው የካቲት 23 ቀን 1988 ዓ.ም ከማለዳው 11 ሰዓት ከ 32 ደቂቃ ላይ ነበር፡፡ የጄኔራል አልቤርቶኔ ክፍለ ጦር በፊታውራሪ ገበየሁ፣ በዋግሹም ጓንጉል፣ በራስ ሚካኤል እና በራስ መንገሻ ጦር ላይ በሰነዘረው ጥቃት ተከፈተ፡፡ የንጉሰ ነገስቱ ሠራዊት የመሐል ጦር አዛዥ ፊታውራሪ ገበየሁ በዚህ ከጣሊያኖች ጋር በተደረገው ጦርነት የተመሰከረለት ጀግና ነበር፡፡ ጎራዴውን መዞ በዋናው የትግል አውድማ ላይ ተወርውሮ ገባ፡፡ በዚህም ጊዜ በጠመንጃ ጥይት ተመትቶ ህይወቱ አለፈ፡፡ በገበየሁ መሞት ተሸብሮ የነበረው የኢትዮጵያ ወታደር ወድያው መልሶ ተረጋጋ፡፡ በታላቅ ቆራራጥነት አልቤርቶኔን እንደገና ገጠመው፡፡ በ4 ሰዓት አከባቢ ላይ አልቤርቶኔ ከመኮንኖቹ አብዛኞቹን አጥቷል፡፡ በጦርነቱ እንደተሸነፈ ግልፅ ነበር፡፡ የኢጣሊያ ወታደሮች በድንጋጤ ተውጠው ፈረጠጡ፡፡ ከፊሉ ተማረከ፡ የቀረውም ወደ ሌሎቹ
ክፍላተ ጦር በመሸሽ ራሱን አተረፈ፡፡ በዚህ ጊዜ ያልተነካው ክፍል የሚይዘውን አጥቶ ይተራመስ ገባ፡፡ በዚህ ሰዓት ቀጥታ በአጼ ምኒሊክ የሚታዘዘው ጦር ከውጊያው ገባ፡፡ በጦርነቱ ወቅት አጼ ምንሊክ በትክክል ወዴት እንደሚገኙ ጣልያኖች አያውቁም ነበር፡፡ ሁልጊዜ ሳይለዩት አብረውት ከሚገኙት ሁለት ሊቀመኳሶች አንዱ በአለባበሱ ንጉሱን መስሎ በስፍራው ይገኛል፡፡ ከሊቀመኳስ ተግባሮች ውስጥ አንዱ የጠላትን ትኩረት ወደ እሱ በመሳብ ንጉሰ ነገስቱን መጠበቅ ነው፡፡ በጦርነቱ ስፍራ አጼምኒሊክ እንደ አንድ ተራ ወታደር ለብሶ በጦርነቱ መሃከል ተገኝቶ ያዋጋም ይዋጋም ነበር፡፡
ቀኑን ሙሉ ውጊያ ሆኖ ከምሽቱ ዐስራ ሁለት ሰዓት ላይ ድሉ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹የኢትዮጲያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹 መሆኑ ታወቀ፡፡

~~~ ክፍል አምስት ይቀጥላል ~~~

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🐎🐎📽 ክፍል አምስት 🎞🐎🐎

በአድዋው ጦርነት እቴጌ ጣይቱ ብጡል የኢትዮጵያን ጦር በሞራል በማነቃቃትና በማበረታት እንዲሁም ሠራዊቱን እግር በእግር እየተከተሉ በፉከራ ያበረታቱ ነበር፡፡
እቴጌ ጣይቱ ጥቁር ጥላ አስይዘው ዓይነ ርግባቸውን ገልጠው በእግር እየተራመዱ በንጉሠ ነገሥቱ ልጅ ወ/ሮ ዘውዲቱና በደንገጡሮቻቸው ታጅበው ከወታደሩ ጎን
ተሰልፈው ነበር፡፡ የኋላው ወታደር ሲያመነታ ‹ በርታ ምን ሆነሃል ድሉ የእኛ ነውና በለው› ብለው ይናገራሉ፡፡ ወንድ ሴት ሲያበረታው መሸሽ አይሆንለትምና ሁሉም በወኔና በጀግንነት ወደፊት ገፋ፡፡ እቴጌይቱም በዚህ ቀን የሴትነት ባሕሪያቸውን ትተው እንደ ወንድ ወታደሮቻቸውን በቀኝና በግራ አሰልፈው ወደ ጦርነቱ ገቡ፡፡ መድፈኞቻቸውንም በቀኛቸው በኩል ጠምደው እየተኮሱ በመካከል የሚዋጋውን የጠላት ጦር ይቆሉት ጀመር፡፡

በየካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም መላው የኢትዮጲያ ህዝብ በአፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ አጋፋሪነት በባዶ እግሩ አድዋ ዘምቶ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ድል አደረገ፡፡ይህም ኢትዮጲያን አንድ የማድረጉን ዘመቻ ቋጨው፡፡ ወደ ማዕከላዊ መንግስት ለመጠቃለል እምቢተኛ የነበሩት ገዦች ለሀገራቸው ክብር ከሚቃወሟቸው አፄ ምኒልክ ጎን ተሰልፈው ጠላትን ድባቅ መቱት፡፡ ይህም ያ ትውልድ በተሻለ መልኩ በጎሳና በሃይማኖት ሳይለያይ ስለ ሀገር ፍቅር ስለ ክብርና ስለ ነፃነት ስለ መብት ያወቀና የተረዳ መሆኑን አስረግጦ ያስረዳናል፡፡

እናመሠግናለን
#share #participate #comment
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

➛ ጣይቱ :- ምን አውቀህ ነው ታድያ
አንቶኔሊን ተክተህ፣ የአገርህ
የኢጣሊያ ተወካይ ሆነህ እንደዚህ
ያለ ክብር የሚነካ ደብዳቤ
ይዘህልን የመጣሀው?
➛ ሳሊምቢኒ :- እቴጌ በታም ይክርታ እኔ
የመሰለው፣ ውቻሌ ውል አስራ
ሰባተኛው ክፍል ልክ እንደ
ኢታሊያኖ ኳንኳ፣ "የኢትዮጵያ
ንጉሠ ነገሥት፣ የውጭ ጉዳይ
ነገር ሁሉ በኢታሊያ በኩል
ሊአረጉት እሺ ብሏል" ብሎ ናው።
➛ ጣይቱ :- ትሰማኛለህ ሳሊምቢኒ?
➛ ሳሊምቢኒ :- አቤት እቴጌ!
➛ ጣይቱ :- ለመሆኑ የሀገሬን ታሪክ
ታውቀዋለህ?
➛ ሳሊምቢኒ :- መቼም በመተኑ ........
➛ ጣይቱ :- ከንግሥተ ሳባ አንስተህ
እስከ ትናንቱ አጼ ዮሐንስ
ድረስ በሀገሩ ክብርና ነፃነት
ለድርድር የሚቀመጥ የአበሻ
መሪ ሰምተህ ታውቃለህ?
➛ ሳሊምቢኒ :- አልሰምቶም እቴጌ!
➛ ጣይቱ :- ታድያ! የድሮዎቹን እንኳን
ቢረሳ! የትናንቶቹ አጼ
ቴዎድሮስና አጼ ዮሐንስ ለእፍኝ
አፈራቸው የነበራቸውን ስስት
ዘንግቶ ለኢትዮጵያዊ ክብራቸው
የከፈሉትን የሕይወት ዋጋ
ከሚዛኑ ደፍቶ ዛሬ "እባካችሁ
ሀገሬን በእናንተ ስር አድርጉልኝ!"
ብሎ የሚለምን ፤ ምኒልክ
የእነማን ልጅ ይመስልሀል!
ትውልድስ ምን ይለናል! (ንዴታቸውን መቆጣጠር እየተሳናቸው ብድግ ይላሉ።) ትሰማኛለህ ሳሊምቢኒ ........
➛ ሳሊምቢኒ :- (ሁሉም ይነሳሉ) አቤት እቴጌ!
➛ ጣይቱ :- (በንዴት እየተንጎራደዱ) እኔ
ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም፤
ነገር ግን ሀገሬ እንደዚህ
ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ
ከምትሸከም ጦርነትን
እመርጣለሁ!

➾ ምንጭ :- ጌትነት እንየው ፣ እቴጌ ጣይቱ ፣ ገፅ 34-35

እናመሰግናለን
#አካፍሉ #ተሳተፉ #ለአስተያየት👇
@R_e_a_d_e_rs
@zhangidaa
@infho

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🏹🗯 አድዋ 🗯🏹

እንኳን ለ124ተኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
🇮🇹
🏹
🇪🇹
@Readers_To_Know
👆 ከመርሐፅዮን ጌታቸው ስራዎች

እናመሰግናለን

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@Readers_To_Know