ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
📆 ጷግሜን 📆

🦅 ክፍል ሶስት 🦅

የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

☞☞ ጳጉሜን 6 እና አመጣጧ
📚 የ6ተኛዋ ጳጒሜን አመጣጥን ስናይ፡- በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ስሌት 1 ዓመት የምንለው 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው፡፡ ይህን የየዓመቱን 6 ሰዓት ስንቈጥር የኹለት ዓመት 12 ሰዓት፤ የሦስት ዓመት 18 ሰዓት፤ የአራተኛው ዓመት 24 ሰዓት ወይም አንድ ዕለት ሲሆን ይኸውም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መጀመሪያ ሲኾን ይኸውም በቀደምት የአቡሻክር ሊቃውንት “መጠነ ራብዒት፣ ሠግረ ዮሐንስ” ትባላለች። ዘመነ ዮሐንስ ተራምዶ የሚያልፍባት ለማለት ነው፡፡

📚 እኛ ጳጒሜን 6 ስናደርግ ምዕራባውያኑ ግን የጳጒሜን ወራትን በማጥፋታቸው ኹሌ ለእነርሱ 28 የኾነችው የካቲትን በአራት ዓመት አንዴ 29 ያደርጋሉ፤ Leap Year ብለው ይጠሯታል፡፡

~~~ይቀጥላል~~~

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ካነበብነው📖📜📰🗞 pinned «ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰቦች በዚህ ጷግሜን ወር ጥያቄና መልስ አዘጋጅተንላችኋል። የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ መመለስ የቻሉትን መዝግበን ጷግሜን 6 ለሁለት ሰዎች ስጦታ አዘጋጅተናል። ጥያቄው ከተለቀቀ በኋላ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ጥያቄዎቹን መመለስ ይቻላል። ከ 4:00 በኋላ መልሱ ዋጋ የለውም። አንድ የመለሰ እንደ አንድ ሶስት የመለሰ እንደ ሶስት በጥያቄው ብዛትና በመለሰው መልስ ብዛት ነጥቡ…»
📆 ጷግሜን 📆

🦅 ክፍል አራት 🦅

የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

☞☞ ጳጒሜን 7 እና አመጣጧ
📚 የኢትዮጵያን ቀደምት ሊቃውንትን በእጅጉ እንድናደንቅ ከሚያደርገን አንዱ የጳጒሜን 7ትን ስሌት ጠንቅቀው አስልተው በብራና የአቡሻክር መጽሐፍ ላይ ጽፈውልን ስሌቱን አስልተው ማለፋቸው ሲኾን፤ የስሌቱም መጠሪያ “ዕሪና መዓልት ዕሪና ሌሊት” በመባል ይታወቃል፡፡

📚 ይኸውም 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ የኾነው የፀሓይ ዐውደ ዓመት የ6 ካልዒት ወይም የ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ጥርቅም ወይም ከላይ ያየናት የአንዷ ዕለት 0.4 ሰከንድ ጥርቅም ነው፡፡

📚 ስናሰላውም የ5 ዓመቱ 30 ካልዒት፤ የ10ሩ ዓመት 60 ካልዒት (1 ኬክሮስ ወይም 24 ደቂቃ) ይሆናል፡፡ የ100 ዓመት (10 ኬክሮስ) ወይም 240 ደቂቃ (4 ሰዓት) ይኾናል፡፡ የ200 ዓመት 20፤ የ300 ዓመት 30፤ የ400 ዓመት 40 ኬክሮስ፤ የ500 ዓመት 50 ኬክሮስ፤ የ600 ዓመት 60 ኬክሮስ ሲሆን 60 ኬክሮስ ማለት 1440 ደቂቃ ወይም 24 ሰዓት ወይም 7 ተኛዪቱ ጳጉሜን ናት፡፡

📚 ሆኖም ግን የአቡሻሕርና የባሕረ ሐሳብ መምህራን ጳጕሜን 7 የተገኘችው ከጥቃቅን መስፈርት ወገን ከሆነችው ከካልዒት በመሆኑ ሒሳቧ ብቻ ታስባ ድቁቅ ደቃይቅ ተብላ ብቻ እንድትተው በማዘዝ ዕለቷ ግን በኅሊና ብቻ እንድትታሰብ እንጂ ተቆጥራ እንዳትከበር አዘዋል፡፡ በመሆኑም በማሰብ ብቻ እንጂ በዕለትነት ተቆጥራ አትውልም፡፡

📚 በአቡሻሕሩ ስሌት መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ 12 ዕሪና መዓልት 12 ዕሪና ሌሊት (ጳጉሜን 7) ተመላልሶ በ1700 ዓ.ም. ወይም በ7800 ዓመተ ዓለም ኾኖ 13ኛው ከተጀመረ 311 ሆኖ በዘመነ ሉቃስ ይኸው ሊፈጸም በ2011 ዓ.ም ካሰላነው 289 ዓመት ይቀራል ወይም በ2300 ዓ.ም. ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡

📚 ይህ በሚሆን ጊዜ ዐቀድ የሚባል ኮከብ አለ፤ ሰሌዳው በፀሓይ ልክ፤ ባሕርዩ ጽሉም ነው፤ ርሱ በ600 ዓመት መጥቶ ፀሓይን ይጋርዳታል፤ ያን ጊዜ ሌሊቱና መዓልቱ ጨለማ ኹኖ ይውላል ያድራል፤ ይኸውም የመከራ ፊት አውራሪ አጫሪ ነው፤ ይኸውም በዐጤ ኢያሱ ወይም ፀሓይ ሰገድ በተባለ በዐጤ ዮስጦስ ጊዜ ተደርጓል ብለው መዝገብውልናል፡፡ ይህን ስናይ የቀደምት ኢትዮጵያውያንን ዕውቀት ሁሌም እንድናደንቅ ያደርገናል፤ መልካም የጳጉሜን 13ኛ ወራት ይሁንልን፡፡
🌼
ለመጪው ዘመን ከቁጥር ሳንጎድል በሰላም በፍቅር ያድርሰን!

~~~ ተፈፀመ ~~~

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ጷግሜን 6
የመጨረሻዋ የ2011 ቀንን ከተቀያየማችሁት ሰው ጋር ይቅርታ እንድትጠያየቁ፣ አሮጌውን ወደጎን እንድትጥሉ በቻናላችን ስም እንጠይቃለን!
የነገ ሰው ይበለን!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@Readers_To_Know
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
​​አሸናፊ አግኝተናል! አሸናፊው በተደረገው የጥያቄና መልስ ውድድር 15 ነጥብ አግኝቷል።
🗓 የዘመን አቆጣጠር በኢትዮጵያ 🗓

ዘመን የሚለካው የጸሐይንና ጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት አድርጎ ዕለት፣ ወር እና ዓመት በሚል መስፈሪያ ተጠራቅሞ ነው::
ዕለት ፦ አንድ ዕለት ማለት አንድ የብርሃን እና አንድ የጨለማ ክፍለ ጊዜ ያለው ሲሆን ጸሐይ አንድ ግዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ
የያዘ ነው:: በሌላ አባባል ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ ያምትሽከረከርበት ጊዜ ነው::
ወር ፦ አንድ ወር ማለት ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ ሙሉ ሆና እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው:: ይህም ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዞራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 29.5 ዕለታት ማለት ነው::
ዓመት፦ አንድ ዓመት ማለት መሬት በጸሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 365 ዕለታት ከሩብ ያህል ነው::
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርም እነዚህን መስፈሪያዎች በመጠቀም 30 ዕለታት ያሉዋቸው 12 ወራት (መስከረም፣ ጥቅምት፣ ህዳር፣ ታህሳስ፣ ጥር፣ የካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዚያ፣ ግንቦት፣ ሰኔ፣ ሐምሌ እን ነሐሴ) እና 5 (በየ4 ዓመታት ደግሞ 6) ዕለታት ያሏት 13ኛ ወር (ጷግሜን) ዑደት ይጠቀማል:: ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የ13 ወር ባለቤት የምትባለው::
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሃይማኖታዊ ይዘት ሲኖረው መነሻ የሚያደርገውም የክርስቶስን ልደት ነው:: ዘመናቱም በሐዋርያት ተሰይመው በአራት መደባት ይዞራሉ፤ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ(ጷግሜን 6 ዕለታት የሚሆንበት) እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው:: አዲስ ዘመን የሚጀምረውም መስከረም 1 ነው::
ምንጭ – መስከረም 2004 አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ 🌼
🌼ዮሐንስ በሰላም አደረሳችሁ 🌼
🌼 አደረሰን! 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😁 ለፈገግታ 😁

A: ሄሎ
B: ማን ልበል
A: ደውለሽ ማንልበል💁‍♂? ማን ብለሽ ነው የደወልሽው?
B: ሰማይ ቤት
A: ኦ! አዳም በአንቺ ምክንያት ከገነት ስለተባረረ እስቲ
ምድር ቤት አጠያይቂ
B: ኧረ ባክህ! ቆይ አንተ ማነህ?
A: ዲያቢሎስ 🧟‍♂
B: ለነገሩ ከሱ አትሻልም (ጥርቅም😳!)

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል አራት 🦅

............ ሽታ ከሌሎቹ የስሜት ህዋሳቶቻችን ይልቅ ለአእምሮአችን በተለይ ስሜታችንን ለሚቆጣጠረው ክፍል እጅግ ቅርብ ነው ። ለዚህም ነው ጠረን ከፍቅርና ከፍርሀት ስሜቶቻችን ጋር ያለው ቁርኝት ዘመናት ያልሻረው ሐቅ የሆነው ። እንኳን በሰው በእንስሳውም ዓለም ጠረን ሀይለኛ የስሜት ቆስቋሽ ነው። የሽቶ መዐዛና የጽጌረዳ ለዛ የማይገዛው ማን አለ ? ክፉ ጠረንም ቢሆን ጉልበቱ ቀላል አይደለም ። ምራቅ የሚያዝረበርብ የምግብ ሽታ ፣ ስሜት የሚኮረኩር የፍቅረኛ መዐዛና ነፍስ ያላወቀን ሕፃን የሚያስፈነድቀውን የእናት ጠረን የሚበልጥ ግን የለም።.................
ገፅ 111
........... ድኻ ድኻ የሚሆነው ገንዘብ ስለሌለው ሳይሆን ፣ ገንዘብን ከማሳደር ማውደም ስለሚቀናውም ነው። የድኻ ድኻነቱ ደስታውንና ኀዘኑን ፣ የትኛውንም ጠንካራ ስሜቱን ተቆጣጥሮ ከስሜቱ በላይ መኖር አለመቻሉም ነው ። ከለመደው የዕጦት ኑሮ ላለመውጣትም ይመስል ፣ ያገኛትን በአንድ ቀን ባለው ኃይል ከዘመድ ከጎረቤት ጋር ተባብሮ ያወድማታል ። ድሀ ብድር መውሰድና ፍቅር መስጠት አይፈራም ። ጥላቻና ሞትም ከድሃ ያን ያህል የራቁ ነገሮች ናቸው ማለት አይደለም ። ብዙ መገዳደልና መደባደብም እዚህ ይበዛል ። ድኽነት የተወሳሰበ ያስተሳሰብና የአኗኗር ውጤት ነው። የማይዳሰስ ግን በቀላሉ የማይገፋ ..... አሳዛኝ ሰዎች የሰፈሩበት የመከራ ተራራ ነው። ..............
ገፅ 119

~~~ይቀጥላል ~~~

"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ።
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
Forwarded from Quality ButtonSCAM
Horoscope and zodiac information
የሕብራተ-ክዋክብት በ12 ይከፈላል ።
የመጀመሪያዉ የzodiac ምልክት Aeris ይባላል ።ብዙዎቹ "the infant" ይሉታል። አንዳነዶች ደግሞ ጠቦቱ እና ወጠጤው በግ ሲሉ ፀበኛ አና ተዋጊ መሆኑን ለመግለፅ ይጠቀሙታል። የኤሪስ የልደት ሰንጠረዥ ከመጋቢት 12-ሚያዝያ-12 ድረስ የሚቆይ ነው ።
እነዚንና የመሳሰሉትን ለማየት👇
🧞‍♂👣 ከዚም ከዛም👣 🧞‍♂

1. ድመቶች🐈 110 ያህል የድምፅ አይነቶችን ማውጣት ይችላሉ።

2. ሰው ከ5-10 🕑 ደቂቃ ያለ ዓየር መቆየት ይችላል ተብሎ ይገመታል።

3. የሴቷ ዘር (እንቁላል🥚) የእስክሪቢቶ ጫፍ ያክላል ተብሎ ይገመታል።

4. አንጎል🧠 አንስተን ብናነጥፈው 24 m^2 የሚያክል እርዝማኔ አለው።

5. አባባል:- የትላንቷ ፀሐይ🌞 አቃጠለችኝ ተብሎ የዛሬዋን ፀሐይ አልሞቅም አይባልም።

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
😂🌍 ለፈገግታ 🌎😂

ጨርሰው ያንብቡት

“ጦር አውርድ”
ከበዕውቀቱ ሥዩም
.
… ከዘመናት ባንዱ ዘመን የሀበሻ መዲና በነበረችው አክሱም በጐረቤቶቿ በኑብያና በየመን ሰላም ነገሠ …
ይልቁንም በአክሱም ብልፅግና ሰፈነ፤ ሁሉም እንጀራና ወይን ጠገበ።
ከጥቂት ዓመታት በኋላ ከተመሰገኑት ያክሱም ሊቃውንት አንዱ ንጉሡ በተገኙበት ጉባኤ ‘ልቦናዬ ያሳየኝን ልናገር’ አሉ። ተፈቀደላቸው።
“ግርማዊ ጃንሆይ” አሉ ባማረ ድምፃቸው …
“ግርማዊ ጃንሆይ አክሱም የምትገኝበት ሁኔታ ለረጋው ሕሊናየ ሥጋት ፈጥሮብኛል፤ ይሄ ሥጋት ደግሞ ቀስ በቀስ ወደ ወገኖቼ መጋባቱ አይቀርም።”
“ምንድን ነው የሥጋትህ ምንጭ?” አሉ ንጉሡ።
ሊቁ ማብራራት ጀመሩ።
“እንደምናየው በመንግሥታችን ሰላም አለቅጥ ሰፍኗል … የባሩድ መዓዛ ከሸተተን ብዙ ዘመን ሆነን … የሽለላ
የፉከራ ዜማዎቻችን ተዘነጉ። እረኞቻችንን ስሟቸው …
በዜማዎቻቸው ውስጥ የብልግናና የፍቅር እንጂ የጉብዝናና የጀግንነት ስንኝ አይገኝም። ጋሻዎቻችን በተሰቀሉበት ድር አደራባቸው … ጦሮቻችን ዶልዱመዋል … ሀኔዎቻችን ዛጉ … ነጋሪቶቻችን ዳዋ
ዋጣቸው … ሰላም ልማዶቻችንና ትውፊታችንን አጠፋብን። ሕንፃ ያለ ጡብ ያለ ጣሪያ ሕንፃ እንደማይሆን እኛም ያለ ነውጣችን ያለ ሽለላችን ያለ ድላችን እና ያለ ሽንፈታችን እኛ አይደለንም።
“ግርማዊነትዎ እንደሚያውቁት አንበሳ ከሚዳቋ ጋር ተኝቶ ማየት ለጊዜው የሚያስደስት ትዕይንት ሊሆን
ይችላል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ይሰለቻል። የሁሉም ዓይን አንበሳው ሚዳቆዋን ሲያሳድዳት … ሰብሮም
ሲገነጣጥላት ለማየት ይናፍቃል።
“ጃንሆይ … ‘እርግቦች በሰገነቶቻችን ላይ ሰፍረዋል፤ የዘንባባ ዛፎች በጓሮአችን በቅለዋል’ ብለው የሚያዘናጉትን አይስሟቸው! … ብርቱ መንግሥት
ከርግቦች ላባ ፍላፃ ያበጃል … ከዘንባባዎች ዝንጣፊ የጦር ሶማያ ይሰራል። “ለራሳችን ብርቱዎች ነን ብለን እንጃጃላለን … ካልታገሉ ሀቅንም ማወቅ አይቻልም። ጐረቤቶቻችን ከፈገግታቸው ባሻገር ምን እያሴሩ እንደሆኑ
አናውቅም። የጐረቤቶቻችን በር ተዘግቷል … በዚህ ምክንያት በእልፍኛቸው ውስጥ ምን እየተሰራ እንደሆነ አናውቅም … የጐረቤቶቻችንን ልክ አለማወቅ በቤታችን ላይ ሥጋት እንዲያንዣብብ አድርጓል።
“ጃንሆይ! የምንኖረው ፈተና በሌለበት ዘመን ነው። ፈተና የሌለበት ዘመን የተፈጥሮን ሕግ ያዛባል። እስቲ
ጐረምሶቻችንን እይዋቸው! … እንደ ሴት ዳሌና ጡት ማብቀል ጀምረዋል … በምትኩ ፂማቸውን ካገጫቸውና ከከንፈራቸው ጠርዝ አርግፈዋል …
መዳፎቻቸው ከሐር ጨርቅ ይለሰልሳሉ … እግራቸውን ዘርግተው የባልቴት ተረት በመተርተር ጊዜያቸውን ያጠፋሉ … የደም ቀለም አያውቁም!
“አያቶቻችን ፍላፃ የወጠሩባቸው ደጋኖች የሴት ልጆቻችን የጥጥ መንደፊያ ሆኑ … ስለዚህ የምንለብሰው ሸማ በውርደት አድፏል። ይሄን እድፍ ከደም በቀር የሚያነፃው ምን አለ?”
ንጉሡ ከመኳንንቱ ጋር ይሄን አድምጠው፣ “ታዲያ ምን ይሻላል?” አሉ።
“ኑብያዎችን ለምን አንወጋም?” አሉ ሊቁ።
“ኑብያዎች ምን አደረጉን?”
“ሁለታችንን በሚለየው ድንበር ላይ ዋርካ ተክለዋል!”
“እና ቢተክሉስ?”
“ዋርካዎች እየሰፉ በመጡ ቁጥር የኛን መሬት መውሰዳቸው አይቀርም!”
“እና ምን ይሻላል?”
“እናቅምሳቸው!” አሉ ሊቁ።
“እንበላቸው!” አሉ መኳንንት።
“በሏቸው” አሉ ንጉሡ።

ሁኔታዎች ተቀያየሩ። ሴቶች ቆሎ በማመስ ጭብጦ በማሰናዳት ተጠመዱ። ወንዶች ኢላማ ልምምዱን አጣደፉት። አሮጌ ጋሻዎች
ከተሰቀሉበት ወረዱ። ደጋኖች ተወለወሉ። ፍላፃዎች ተሳሉ። የጐበዞች አረማመድ ተለወጠ። የእረኞች
የፍቅር ዘፈን አንደበታቸው ላይ ሟሟ።
የደም ቃና ያላቸው ዜማዎች መስኩን ዱሩን ጋራውን ሞሉት። የአክሱም ባንዲራ ከእንቅልፏ ተቀሰቀሰች።

ጥቂት ወራት አለፈ። ከወደ ኑብያ ግድም ደብዳቤ መጣ።
“ዛቲ ጦማር ዘተፈነወ ትኀበ ንጉሠ አክሱም …
… የየመን ሊቃውንት አንድ መረጃ ነገሩን … እናንተ አክሱሞች በኛ ላይ ሠራዊት ልታዘምቱ እንደተሰናዳችሁ ሰምተን አዝነናል። ይሁን እንጂ የጠባችን ምክንያት በድንበሮቻችን ላይ የተተከሉት
የዋርካ ዛፎች መሆናቸውን በማወቃችን ለሰላም የሚበጀውን አድርገናል። ከዛሬ ጀምሮ ዋርካዎች እንዲቆረጡ ትእዛዝ አስተላልፈናል … ይቅርታ አድርጉልን !”
የሚታይ ማህተም ደብዳቤው ከደረሳቸው በኋላ ንጉሡ ሊቁን አስጠሩ።
“ምን ይሻለናል? ኑብያዎች ሳንወጋቸው ዋርካዎችን ቆረጡ! እንግዲህ ምን ሰበብ እንፈጥራለን?” አሉ
በቅሬታ።
“ግርማዊ ሆይ!” አሉ ሊቁ “የሰማነው ዜና በእውነቱ የሚያስቆጣ ነው። እንደሚያውቁት ሠራዊት ለማደራጀት ብዙ ገንዘብ ብዙ ጉልበት ብዙ ጊዜ
ፈጅተናል። ጐበዞቻችንን ከሙያቸው አፈናቅለን አስታጥቀናቸዋል። ሴቶቻችን ቡሃቃቸውን አሟጠው ስንቅ ሰርተዋል። ይሄ ሁሉ ያለ አንዳች ተግባር ብላሽ
መሆን የለበትም ጃንሆይ!” አሉ በመማፀን ድምፅ።
“ታድያ ምን አድርግ ነው የምትለኝ?”
“የዘመቻችንን እቅድ ሰልሎ ለኑብያዎች የነገራቸው የየመን መንግሥት ነው።”
“እናስ?”
“በዚህ ምክንያት የመኖች የኛን ሉዐላዊነት ደፍረዋል።
ስለዚህ ለምን ዘመቻውን ወደ የመን አናዛውረውም?”
አማራጭ አልተገኘም። በማግስቱ አዋጅ ተነገረ፤
“ጠላታችን ወደሆነው ወደ የመን ሀገር ዝመቱ። በዚያ ሕያው የሆነውን ሁሉ ፍጁ ! … ከተሞቻቸውንም ወደ ፍርስራሽ ለውጡ ! …”.
.
ምንጭ – “በራሪቅጠሎች ”። 1996 ገጽ 76-81
#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
📜 ከታሪክ ማህደር 📜

የአየር መንገድ ሥራ ከተጀመረበት ጊዜ ሳያቋርጡ ለመንገደኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አየር መንገዶች ሥራ የጀመሩበት ዘመን (እ.ኤ.አ)
1. ኬ.ኤል.ኤም 17 ሜይ 1920
2.አቪያንካ 19 ሴፕቴምበር 1921
3.ኳንታስ 2 ኖቬምበር 1922
4.ኤሮፍሎት 15 ጁላይ 1923
5.ሲ.ኤስ.ኤ 28 ኦክቶበር 1923 በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ተቋርጦ (1939-45) እንደገና የጀመረ

6.ፊን ኤይር 20 ማርች 1924 በጦርነቱ ተቋርጦ በ1945 የጀመረ

7.ሳቢና 1 ኤፕሪል 1924

👉👉8.አቪዬሽን ወደ ኢትዮጵያ የገባው 18 ኦገስት 1929 ወይም ነሐሴ 12 1921 ዓ.ም

ምንጭ 'አቪዬሽን በኢትዮጵያ' በካፕቴን መኮንን 1995... ገጽ 21

#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል አምስት 🦅

........ ደመነፍስ እንግዲህ ከንቁ አእምሮአችን ሥር ያለው የተንጣለለው ከፊል ንቁና ድብቁ አእምሮአችን ነው የሚባለው። አንዳንዴ በደመነፍስ ኖረን በደመነፍስ መሞትም አለ። ደመነፍስ ስንል በርግጥ አንዳንዴ የሰውን እንስሳዊ የፍላጎት ግፊትንም ለመግለጽ እንጠቀምበታለን ።........ ነቅቶ የሚንከላወሰውን አእምሮአችንን በጥልቅ የማንነታችን ውቅያኖስ ውስጥ ተወሽቆ እሱ ነው አሉ የሚያሾረው የሚያሽከረክረውም ።
ደመነፍስ የነፍስ ደም ነው፤ መልኩ ግን ቀይ አይደለም ፤ የነፍስ ነገሮች በቀለም ሳይሆን በሀሳብ ደርዝ ነው የሚገልፁት። ደመ ሥጋ የሥጋ ህልውና እንደሆነ ሁሉ ደመነፍስም የነፍስን አኗኗር ይወስናል። ደመ ስጋ ለሰውነት ሁሉ የሚያስፈልገውን ምግብና ኦክሲጅን ያደርሳል ። ብሎም ካንዱ ክፍል ወደ ሌላው ጠቃሚ መልዕክተኛ ንጥረ ነገሮችንና ተወጋጅ ቆሻሻዎችን በልብ እየተገፋ ያመላልሳል ቀን ከሌት። እሱ በቆመበት ቀን ሕይወትም ትቆማለች ።ደመነፍስም በነፍስ አለም ያንኑ ሳይሠራ ይቀራል? ቀን በውን .... ሌት በህልም .... አውቀን በንቃት .... ሳናውቅ በፍዘት ....የቀዳነውን ሐሳብ አመላላሽ .... ባቡራችን .... ቧንቧችን ነው።...........
ገፅ 206

~~~ይቀጥላል~~~

"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ

#share #comment #participate


📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🦅🖊 ስነግጥም 🖌🦅

ኤድያ ጨርቅን ማመን የሚያምን ይመነው ፤
ሲነጋ ቢደምቅ ሲመሽ ወላቂ ነው ፤
ድሎቴን ለማይወድ ጠቦኝ ለሚቀረው ፤
ብሰፋው ባሰፋው ለሚተረተረው ።
ደካማ ነውና ሳውቀው መቀደዱን ፤
ዋ! በተውኩት ኖሮ ብጥስጣሽ መውደድን ።
እንደሱማ ነበር ብልጭልጭ ፍልቅልቅ ፤
ሲነጋ ጠላቂ ሲመሽ ሊወላልቅ ።
እብድ ይበሉኝ እንጂ በቃኝ የሱ ነገር ፤
ዛሬም ነገም ማጠብ መቆሸሹ ላይቀር ።

ምንጭ:- ከታገል ሰይፉ፣ ቀፎውን አትንኩት፣ አ.አ ብርሀንና ሰላም
#share #participate #comment


📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
​​🔑 ቅምሻ 🔑

🦅 ክፍል ስድስት 🦅

ስለ ኦቲዝም አጠቃላይ መረጃ ታገኙበታላችሁ ፤ትወዱታላችሁም።
ክፍል ስድስትPage 2
ክፍል ስድስትPage 3