👣🧞♂ከዚም ከዛም🧞♂👣
1. የአለማችን ጥንታዊ ከተማ ደማስቀስ ትባላለች፤ መገኛዋም በሶሪያ ምድር ነው።
2. Titanic መርከብ 🛳⚓️ 3547 ሠዎችን መያዝ ትችል ነበር። ወደላይ ርዝመቷም 269 m ነበር።
3. የአለም እግርኳስ⚽️ ዋንጫ🏆 በኡራጋይ🇺🇾 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1930 ዓ.ም ተጀመረ።
4. የኮንሶ ዋና ከተማ ካራይቲን ሲሆን ከካራይቲን በ17 k.m "New work" በአፈር ቁልል የተሠሩ ሠማይ ጠቀስ ፎቆች የሚገኙበት ቦታ ነው።
5. አባባል:- ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቆመን ማውረድ አቃተን!🤷♀🤷♂
#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚

🔑 ቅምሻ 🔑
🦅 ክፍል አንድ 🦅
....... የሰሎሜ አባት ያለምክንያት የሚባክን ገንዘብና ጊዜ ያበሳጫቸዋል። ገንዘብ የጊዜ ምንዛሪ ነው፤ ጊዜም ያልተመነዘረ ገንዘብ ነው የሚል ፍልስፍና አላቸው። ህይወት ረቂቅ ምስጢር ናት፤ አምላክ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህችን ምስጢራዊት ሕይወት ዕድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት አደለን። ይህቺም ከረጢት በውስጧ ዕድል በተሰኙ ፈርጦች ተሞልታለች። ከረጢቷን እንዳትሰረቅና ያለግዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጪ እንዳትሆን ፤ ኀላፊነቱን ፈጣሪ ለኛው ነው የሰጠን። በከረጢቷ ውስጥ ያሉትም ፈርጦች አንድ በአንድ ፣ አንዳንዴም ከአንድ በላይ ባንዴ እያብለጨለጩ ከባለ ከረጢቱ እጅ ላይ ይወድቃሉ። ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜው ያልተጠቀምንባቸው የዕድል ፈርጦች ከጊዜ ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈውን ይነጉዳሉ። ስኬት በትጋትና በሥራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደለም ይላሉ። ድኽነትም የባከኑ ዕድሎችና ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው እንጂ ያርባ ቀን እድል ነው ብለው አያምኑም።.............
ገፅ 42
~~~ይቀጥላል ~~~
"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተቃረመ።
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ
#share #comment #participate
አስተያየቶ ለኛ ያስፈልጋልና ቅር ያላቹን እንዲሁም ይቀጥል የምትሉትን አጋሩን። በተጨማሪም ስለ ቻናሉ አስተያየት ካላችሁ 👇

Forwarded from Quality Button [SCAM]
Behager lij is a home for incredible Ethiopian graphic designs and Branding. We excel at making creative and unique designs. check out works here and witness for yourself.
Contact 0922582607 or @naoliman
Contact 0922582607 or @naoliman
😂 ለፈገግታ 😂
A. አንተ እስካሁን እንዴት አላገባህም
ቆይ!
B. ምን ባክህ ሚሆን ሰው አጥቼ ነው።
እንደው እስኪ አንተ ፈልግልኝ ?
A. እኔ በምን አውቄ ፤ ምን አይነት
ትመችሀለች?
B. ያው ቤተክርስቲያን የምትወድ፣ ሰው
አክባሪ፣ ትሁት፣ሀሜት የማትወድ፣
አፍቃሪ፣ ልጃገረድ ብትሆን ደስ
ይለኛል።
A. 😳😳😳 እንዴ ወንድሜ በዚህ
መስፈርት መነኩሴ ራሱ ሚገኝ
አይመስለኝም።
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
A. አንተ እስካሁን እንዴት አላገባህም
ቆይ!
B. ምን ባክህ ሚሆን ሰው አጥቼ ነው።
እንደው እስኪ አንተ ፈልግልኝ ?
A. እኔ በምን አውቄ ፤ ምን አይነት
ትመችሀለች?
B. ያው ቤተክርስቲያን የምትወድ፣ ሰው
አክባሪ፣ ትሁት፣ሀሜት የማትወድ፣
አፍቃሪ፣ ልጃገረድ ብትሆን ደስ
ይለኛል።
A. 😳😳😳 እንዴ ወንድሜ በዚህ
መስፈርት መነኩሴ ራሱ ሚገኝ
አይመስለኝም።
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🔑 ቅምሻ 🔑
🦅 ክፍል ሁለት 🦅
.........አቶ ኦላናም " እህ ..ህ ..ህ " ብለው ጉሮሮአቸውን ጠረግ አረጉና "እንግዲህ ከየት እንጀምር ለሚለው መቼም ካለንበት ነው። ወደየት እንሂድ ለሚለው ደግሞ ወደፊትና መድረስ ወደሚገባን ነው። ይህ ግልጽ ቢሆንም ሁሌም ቀላል አይደለም። ለምሳሌ ካለንበት ለመጀመር ያለንበትን ማወቅና መቀበል ኀላፊነትንም መውሰድን ይጠይቃል። ይህም ከባዶ ኩራትና ያልሆነውን ነን ብሎ ከማሰብ መላቀቅን የግድ ይላል። በተጨማሪም አሁን ለሆነውና መሆን ላቃተን ነገር ያለፈውን ትውልድ ወይም አሁን የሚመሩንን ሰዎች ከመወንጀልና ራስን ከኃላፊነት ለማሸሽ ከሚደረግ ስውር ሽሽት ነጻ መሆንን ያጠቃልላል። ታሪክን ለመመጻደቂያና ለመደበቂያ ሳይሆን፣ እንደ አንድ የትምህርት መድረክ ለመጠቀም ጠንቅቆ ማወቅም ትልቅ ፋይዳ አለው። ወደፊት መሔድ ነው ስል ሁሌም የብዙሀኑ የጅምላ ጉዞ አንድም ባለህበት ርገጥ ነው፤ ወይም እንደ ግመል ሽንት የኋልዮሽ ስለሆነ ነው። ይህም በባህል፤ በሀይማኖትና በአኗኗር ልማድ ውስጥ ጎልቶ ይታያል። " በማለት አባቷ ነገሩን ለሰሎሜ ማስረዳታቸውን ቀጠሉ።
" በየትኛውም ሥልጣኔ ውስጥ ፈር ቀዳጅና ፋና ወጊ ተብለው ለውጥ ያመጡ ሰዎች መጀመሪያ ወንጀለኛ፣ ከዚያም አሳሳች ተብለው መፈረጃቸው የተለመደ ነው። በእርግጥም እነዚህ ጥቂት ብርቅዬ ከዋክብት ከሕብረተሰቡ በሠላሳና በአርባ አመት ቀድመው ወደፊት የሄዱ ስለሆነ ከሰው አይገጥሙም። ሰው አንድም ባለበት ስለሚረግጥ አንድም የኋልዮሽ እንሽርት ጨዋታ ላይ ስለሚባትል እነሱን ይፈራቸዋል ፤ ስለዚህም ይጠላቸዋል። ምንም እንኳ እንደ እውነት ፀርና አሳች መሲሕ ቢታዩም ፣ በሚቀጥለው ትውልድ ግን ሁሌም ብሩህ ከዋክብት ተብለው ይሞገሳሉ ፤ የመታሰቢያ ሐውልትም ይሠራላቸዋል ።" አሉ አይናቸውን ከሰሎሜ ላይ ሳይነቅሉ ።
" የሚቀጥለው ትውልድ ደግሞ በነሱ ሐውልትና ትምሕርት ዙርያ ሲርመሰመስ ፣ ሳያስበው ወደ ኋላ ተንሸራቶ በራሱ ጨለማ ውስጥ ይገባና የራሱን ዘመን ፋና ወጊዎችና እውነት ገላጮች እያሳደደ ዕድሜውን ያቃጥላል። የእኛም ሕዝብ ከዚህ የተለየ አይደለም። እኔ እንደሚመስለኝ ለእኛም አገር አቅጣጫ ጠቋሚና ፈር ቀዳጅ መሪዎች በዋናነት ያስፈልጋሉ። እነዚህ በአስተሳሰባቸው ብዙሀኑን ከእንቅልፍ ቀስቃሾች ፣ የሥልጣኔ አድማስ አመልካቾች ከወጡልን ፣ ሀብት ብቻ አይደለም ፤ ሥልጣኔም በምድራችን እንደ ኃይለኛ ጅረት እንደገና የማይፈስበት ምክንያት የለም። ስለዚህ የት እንጀምር? ካለንበት ፤ መቼ እንጀምር? አሁን ፤ ማን ይጀመር? እኔ አንቺ እኛ ..... የት ለመድረስ? ሰው የደረሰበት ደግሞም ያልደረሰበት ፤ ትልቁና ከባዱ እንዴት እንጀምር? ነው። "ብለው ትንሽ ዝም አሉ።........
ገፅ 79-80
~~~ይቀጥላል ~~~
"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተወሰደ።

🦅 ክፍል ሶስት 🦅
........... ከልጅ ጋር መሆን እንዴት ሕይወት ያድሳል። ሁሉንም ነገር እነሱ የሚያዩበት እይታ ተስፋ ያዘለና እምቅ ኀይልን የሚለቅ ነው። ደስታም ሩቅ አይሆንም ። ጉጉትና ደግነት ፣ ፍቅርና ወዳጅነት በልጆች ዓለም ሳይበረዝና ሳይለዝዝ ይኖራል ። .............
.............. ልጅ ለማወቅ የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች አዋቂዎችን ለምን ይሆን የሚያውኳቸው። በተደጋጋሚ መልስ ያጣች ልጅ ደግሞ ቀስ በቀስ ያላዋቂ አዋቂ ወደ መሆን ትቀየርና እሷም መጠየቅ ታቆማለች ።ደርሳ የራሷ ልጅ ሲኖራት እሷም ሌላ ያላዋቂ ልጅ ታፈራለች ።በዚህ መሠረት በትምህርት ቤትም ሆነ በቤት ዕውቀትን የተራቡ ልጆችኝ ተቀብለን ዕውቀት ብለን በምንሰጣቸው የተዛባ መረጃ ተብትበናቸው ያላዋቂ አዋቂዎችን እናፈራለን ። እነሱንም እንደኛ ።
ያላዋቂ አዋቂነትም ተብትቦ ማኅበረሰብ በሚኮራበት ባህል በተባለ ባቡር ሁላችንንም ፍፃሜ ወደሌለው እንጦሮጦስ ይዞን ይወርዳል ። ጥቂት ደፋርና እምቢ ባይ በጥያቄ አስጨናቂ ከዚህ ወረርሽኝ የተረፉ ነፍሶች እስኪገኙ ። ማኅበረሰብን ካላዋቂ አዋቂነቱ የሚያባንኑ ። ነገርግን ልጆች አላዋቂዎች ስለሆኑ ማን ይሰማቸዋል ? አላዋቂ የሚባለው ጠያቂ ፣ አዋቂው ደግሞ የማይጠይቅ መሆኑ አንዱ የህይወት አሳዛኝ ገጽታ ሳይሆን አይቀርም። በርግጥም ድንቅ ነው !! ጥያቄ አቁመው በቁመት ስላደጉ ብቻ አዋቂ የሚል የክብር ስም በዕድሜያቸው ብቻ ለገፉ ህፃናት እንደ ካባ ሲደረብ።..............
ገፅ 100

ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰቦች በዚህ ጷግሜን ወር ጥያቄና መልስ አዘጋጅተንላችኋል። የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ መመለስ የቻሉትን መዝግበን ጷግሜን 6 ለሁለት ሰዎች ስጦታ አዘጋጅተናል። ጥያቄው ከተለቀቀ በኋላ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ጥያቄዎቹን መመለስ ይቻላል። ከ 4:00 በኋላ መልሱ ዋጋ የለውም።
አንድ የመለሰ እንደ አንድ ሶስት የመለሰ እንደ ሶስት በጥያቄው ብዛትና በመለሰው መልስ ብዛት ነጥቡ ይያዛል።
ጥያቄውን ለመመለስ
ይህን👉 @R_e_a_d_e_rs ይጠቀሙ👍 and don't delete your answer since it helps us to count
መልካም እድል!!
መልዕክቱ ላልደረሳቸው አካፍሉ 👍
From
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
አንድ የመለሰ እንደ አንድ ሶስት የመለሰ እንደ ሶስት በጥያቄው ብዛትና በመለሰው መልስ ብዛት ነጥቡ ይያዛል።
ጥያቄውን ለመመለስ
ይህን👉 @R_e_a_d_e_rs ይጠቀሙ👍 and don't delete your answer since it helps us to count
መልካም እድል!!
መልዕክቱ ላልደረሳቸው አካፍሉ 👍
From
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🌼 ስነ-ግጥም 🌼
የሞላ ማድጋ ከጀርባ ካዘሉ ፤
ጎደሎ እንስራ ያዘሉት ተሻሉ ፤
ሙሉ ያዘሉቱ ከላይ ያፈሳሉ ፤
ጀርባቸውን ከታች ያበሰብሳሉ ፤
ጎደሎ ያዘሉ ምን ቢንገላጀጁ፣ ምን
ቢንገዋለሉ ፣
መሙላትን ይሻሉ ።
ምሉዕ ነን የሚሉ፣
እያደር ሲጎሉ፣ ይንቦጫቦጫሉ ።
ምንጭ:- የቀንድ አውጣ ኑሮ፣ 2002፣ የተሻሻለ
#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
የሞላ ማድጋ ከጀርባ ካዘሉ ፤
ጎደሎ እንስራ ያዘሉት ተሻሉ ፤
ሙሉ ያዘሉቱ ከላይ ያፈሳሉ ፤
ጀርባቸውን ከታች ያበሰብሳሉ ፤
ጎደሎ ያዘሉ ምን ቢንገላጀጁ፣ ምን
ቢንገዋለሉ ፣
መሙላትን ይሻሉ ።
ምሉዕ ነን የሚሉ፣
እያደር ሲጎሉ፣ ይንቦጫቦጫሉ ።
ምንጭ:- የቀንድ አውጣ ኑሮ፣ 2002፣ የተሻሻለ
#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ካነበብነው📖📜📰🗞 pinned «ሰላም የዚህ ቻናል ቤተሰቦች በዚህ ጷግሜን ወር ጥያቄና መልስ አዘጋጅተንላችኋል። የጠየቅናቸውን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ መመለስ የቻሉትን መዝግበን ጷግሜን 6 ለሁለት ሰዎች ስጦታ አዘጋጅተናል። ጥያቄው ከተለቀቀ በኋላ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ጥያቄዎቹን መመለስ ይቻላል። ከ 4:00 በኋላ መልሱ ዋጋ የለውም። አንድ የመለሰ እንደ አንድ ሶስት የመለሰ እንደ ሶስት በጥያቄው ብዛትና በመለሰው መልስ ብዛት ነጥቡ…»
📆 ጷግሜን 📆
🦅 ክፍል አንድ 🦅
የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ
✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
📚 ጳጒሜን የተባለችው 13ኛዋ ወር በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ስትባል ሊቃውንት ተረፍ ይሏታል፡፡ የ5 ቀናትን የጳጉሜንን አመጣጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጠንቅቀው ቀምረው በባሕረ ሐሳብ ብራናቸው ላይ ጽፈውልናል፡፡
📚 ይኸውም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ያሉት 12ቱ ወራት ያላቸው ዕለታት በአጠቃላይ 360 ናቸው፡፡ በቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጥልቅ ትንተና 1 ዕለት የሚባለው 24 ሰዓት ከ52 ካልዒት ከ31 ሳልሲት ነው፡፡
📚 1 ካልዒት ማለት 24 ሰከንድ ሲኾን 52 ካልዒት ማለት 1248 ሰከንድ ነው፤ 31 ሣልሲት ማለት 12.4 ሰከንድ (ቅጽበት) ይኾናል፡፡ በመኾኑም በአንድ ቀን ውስጥ 1 ደቂቃ ከ0.4 ሰከንድ ትርፍ መኖሩን ያስረዳል፡፡
📚 በመኾኑም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ባሉት 360 ቀናት ያሉትን 52 ካልዒት ወይም 1248 ሰከንድ እንዲኽ እናባዛቸዋለን፤ 52 ካልዒት X 360 ዕለታት= 18720 ካልዒት ወይም (449, 280 ሰከንድ) ይኾናል፤ ወደ ደቂቃ ስንለውጠው 7488 ደቂቃ ወይም 5 ዕለት ይኾናልና የጳጒሜን አመጣጥ ይቺ ናት፡፡
~~~ይቀጥላል~~~

☞☞ የጳጉሜን 5 ምስጢር
📚 አራቱ የዓመት ወቅቶች ማለትም መፀው፣ ሐጋይ፣ ጸደይና ክረምት 91, 91 ቀናት የሚኾኑት ከጳጒሜን 1 አንድ ዕለት እየተሰጣቸው ሲኾን በአጠቃላይ 364 ዕለታት ወይም 52 ሳምንት ኾኖ አንዲት ዕለት ትተርፋለች፤ ይቺም ጳጒሜን 5 ስትኾን በኢትዮጵያ ቀደምት የዘመን ቀመር ሊቃውንት “ዕለተ ምርያ፣ አዕዋዲት” ትባላለች፡፡
📚 ዕለተ ምርያ ማለት ዕለተ መድኀኒት ማለት ነው፤ ምክንያቱም ጳጒሜን 5 የመድኀኒታችን ክርስቶስ ልደትን የምናውቅባት ስለኾነች ነው፤ ይኸውም ጳጒሜን 5 በዋለችበት ዕለት የክርስቶስ ልደት ዕለት በተመሳሳይ መልኩ ይውላል፡፡
📚 ለምሳሌ የዚኽ ዘመን ጳጉሜን 5 ዕለት ማግስተ ሰኞ ናት፤ በተመሳሳይ መልኩ የ2012 የጌታችን የልደት በዓል ታኅሣሥ 29 ማግስተ ሰኞ ይውላል፡፡ በዚህ ምክንያት ዕለተ ምርያ የሚል ሥያሜ ሊሰጣት ችሏል፡፡
📚 በተጨማሪም ጳጒሜን 5 የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የዐዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደኾነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ በመኾኑ ዕለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ መዋሉ በእጅጉ ይደንቃል፡፡

☞☞ ጳጉሜን 6 እና አመጣጧ
📚 የ6ተኛዋ ጳጒሜን አመጣጥን ስናይ፡- በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ስሌት 1 ዓመት የምንለው 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው፡፡ ይህን የየዓመቱን 6 ሰዓት ስንቈጥር የኹለት ዓመት 12 ሰዓት፤ የሦስት ዓመት 18 ሰዓት፤ የአራተኛው ዓመት 24 ሰዓት ወይም አንድ ዕለት ሲሆን ይኸውም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መጀመሪያ ሲኾን ይኸውም በቀደምት የአቡሻክር ሊቃውንት “መጠነ ራብዒት፣ ሠግረ ዮሐንስ” ትባላለች። ዘመነ ዮሐንስ ተራምዶ የሚያልፍባት ለማለት ነው፡፡
📚 እኛ ጳጒሜን 6 ስናደርግ ምዕራባውያኑ ግን የጳጒሜን ወራትን በማጥፋታቸው ኹሌ ለእነርሱ 28 የኾነችው የካቲትን በአራት ዓመት አንዴ 29 ያደርጋሉ፤ Leap Year ብለው ይጠሯታል፡፡