ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
The Epic of Gilgamesh (/ˈɡɪlɡəmɛʃ/) is an epic poem from ancient Mesopotamia that is often regarded as the earliest surviving great work of literature. The literary history of Gilgamesh begins with five Sumerian poems about Bilgamesh (Sumerian for "Gilgamesh"), king of Uruk, dating from the Third Dynasty of Ur (c. 2100 BC).
For more information Go to ....
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Epic_of_Gilgamesh


👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫💫
Fun fact:
The average number of books each person read over the course of a year was 12
Oct 7 2016


👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫ከታሪክ ማህደር💫
​​ክፍል አንድ
👉የንጉሥ ኃይለ መለኮት አባት ሣህለ ሥላሴ ይባላሉ። የሚኒሊክ አባት የሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሲሆኑ እናታቸው እመት እጅግአየሁ አዲያሞ ትባላለች።
👉የአፄ ሚኒሊክ የመጀመሪያ ሚስት የቴዎድሮስ ልጅ አልጣሽ ነበረች።
👉ዘውዲቱ ከሚኒሊክ እና ከአብቺው አብራክ ተወለደች።
👉የዳግማዊ ሚኒሊክ የንግሥና ማእረግ
"ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ።"
👉ኢያሱ ዐልጋ ወራሽ ከሆነ በኋላ "አቤቶ" የሚለው የሸዋ መሳፍንት የማዕረግ ስም አገኘ። የፈረስ ሰሙም አባጤና ተባለ።
የእያሱ ማዕረግ መግለጫ
" ኢያሱ ወልዱ ለዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ " ወይም "አቤቶ ኢያሱ ወ.ሚ" የሚል ነበር።
👉የቶራ መስክ ጦርነት ጥቅምት 7 ቀን 1909 ዓ.ም ተደረገ። 11000 የሚሆነው የአዲስ መንግሥት ሰራዊት በዚያን ጊዜ 30000 ነበር በተባለው የንጉሥ ሚካኤል ጦር ተደመሰሰ።
👉በሰገሌ ግንባር ሸዋ 120000 ወሎ 80000 ወታደሮችን አሰልፈው እንደ ነበር ተዘግቧል። በጦርነቱም በሁለቱም ወገኖች 15000 ሰዎች ሲሞቱ የቆሰሉትም 20000 እንደሆኑ ተነግሯል። ይህም ከአደዋ ጦርነት ጋር ሲነፃፀር እጥፍ ይሆናል ማለትም በአደዋ ጦርነት የሞቱት 7560 ሲሆኑ የቆሰሉት ደግሞ 10000 ይደርሳሉ።
👉ቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ሚካኤል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ።
👉ልጅ እያሱ በመጀመሪያ ኩላሽ ላይ መታሰራቸው ቀርቶ ሸዋ ቡልጋ አፋፍ ኮረማሽ ተራራ ላይ ታሰሩ።
📖📖📔ከ "አቤቶ እያሱ" መጽሐፍ በጥቂቱ የተቃረመ


👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫ከታሪክ ማህደር💫
ክፍል ሁለት
በሚኒሊክ ጊዜ በጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም በተደረገው ሹምሽር የመጀመሪያ ምርጫ ለማግኘት የታደሉትም ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው።
1. አፈንጉስ ነሲቡ መስቀሎ .... የፍርድ ሚኒስትር
2. ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ .... የጦር ሚኒስትር
3. ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደ አረጋይ .... የጽሕፈት ሚኒሰትር
4. ሊቀ መኳስ ከተማ .... ያገር ግዛት ሚኒሰትር
5. በጅሮንድ ሙሉጌታ ይገዙ .... የገንዘብ ሚኒስትር
6. ነጋድራስ ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ሚካኤል .... የንግድና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር
7. ከንቲባ ወልደ ፃድቅ ጎሹ .... የእርሻ ሚኒስትር
8. ቀኝአዝማች መኮንን ተወንድበላይ .... የሥራ ሚኒስትር
9. አዛዥ መታፈሪያ መልከ ፄዲቅ .... የግቢ ሚኒስትር
10. ልጅ በየነ ይመር .... የፖስታ ቴሌግራፍ እና ቴሌፎን ሹም
11. መላከ ፀሐይ ኤስድሮስ .... የትምህርት ሚኒሰትር
📖📖📔ከ "አቤቶ እያሱ" መጽሐፍ በጥቂቱ የተቃረመ


👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫ከታሪክ ማህደር💫
ክፍል ሦስት
1. ቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ሚካኤል .... ጠቅላይ ሚኒስትር እና የንግድ ሚኒሰትር
2. ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ .... የጦር ሚኒስትር
3. አፈ ንጉሥ ጥላሁን ሀብቴ .... የፍርድ ሚኒስትር
4. ደጅ አዝማች አብርሀ አርአያ .... የአገር ግዛት ሚኒስትር
5. በጅሮንድ ይገዙ በሀብቴ .... የገንዘብ ሚኒስትር
6. ፀሐፌ ትዕዛዝ አፈወርቅ ወልደ ማርያም .... የጽሕፈት ሚኒስትር
7. ቀኝአዝማች በየነ ይመር .... የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር
8. አዛዥ ግዛው .... የሥራ ሚኒስትር
9. መልአከ ፀሐይ ኤስድሮስ እስጢፋኖስ .... የትምህርት ሚኒስትር እና ሊቀ ካህናት
10. ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ .... ፖስታ ሚኒስትር ነበሩ
📖📖📔ከ "አቤቶ እያሱ" መጽሐፍ በጥቂቱ የተቃረመ


👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫ከታሪክ ማህደር💫
​​​​ክፍል አራት
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ የአቤቶ ታማኝ አገልጋይ እና በዐጤ ሚኒሊክ መልካም ፈቃድ በ1900 ዓ.ም ወደ ጀርመን ሔደው የተሽከርካሪ እደ ጥበባዊ ዕውቀት ( automotive skill ) ቀስመዋል። እንዲሁም በቆይታቸው "ሂስ ማስተርስ ቮይስ" ከሚባል ኩባንያ ጋር በመዋዋል 17 ዲስኮችን በዘለሰኛና መዲና በማስቀረፅ 17ሺህ የጀርመን ማርክ የተከፈላቸው የመጀመሪያው ዘመናዊ ኢትዮጵያዊ የኪነት ሰው ናቸው።
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ የመጀመሪያው ሹፌር መካኒክ ፣ የመጀመሪያው ዲስክ ያስቀረፀ ኢትዮጵያዊ ሠዓሊና የቅርፃ ቅርፅ ሥራ ባለሞያ ሲሆኑ ከዚህም ሁሉ በላይ አንቱ ባሰኟቸው በሠምና ወርቅ ቅኔዎቻቸው ይታወቃሉ።
የአፍሪካ ዋንጫ እንዲጀመር ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረጉት ይድነቃቸው ተሰማ የነጋድራሱ ልጅ ነበሩ።
ጥቅምት 3 ቀን 1957 ዓ.ም በ87 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።😔😔😔😔
📖📖📔ከ "አቤቶ እያሱ" መጽሐፍ በጥቂቱ የተቃረመ


👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫