💫 ከታሪክ ማህደር 💫
...................................................
አና ትባላለች - ሙሉ ስሟ አና ፍራንክ። አሁን በሕይወት የለችም። በዚች ዓለም ላይ በሥጋ የኖረችው ለ15 ዓመታት ከዘጠኝ ወራት ብቻ ነው። በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1929 እስከ 1945 ዓ.ም። በመንፈስ ግን አሁንም አለች፣ ወደፊትም ትኖራለች።
1943 ዓ.ም ላይ የናዚ ወታደሮች አምስተርዳም ውስጥ አገር ሰላም ብለው ይኖሩ የነበሩ አይሁዶችን ከየቤታቸው እየለቀሙ ወደ ኦሽዊትና ወደሌሎች የግድያ ጣቢያዎች ማጋዝ ሲጀምሩ የአና ፍራንክ ቤተሰቦች ከግድያው ለማምለጥ ቀደም ብለው አዘጋጅተው ወደነበረው አንድ ሚስጥራዊ የመደበቂያ ሥፍራ ያመራሉ። ይህ ምስጢራዊ ቦታ የአና አባት አቶ ፍራንክ የአስመጪና ላኪነት ቢዝነሱን ያካሒድበት በነበረ ሕንፃ ጣሪያ ላይ ይገኛል። የአና ቤተሰቦች በቁጥር አራት ነበሩ፤ ማለትም ራሷ አና ፍራንክ፣ አባቷ አቶ ፍራንክ፣ እናቷ ኤዲት ፍራንክ እና ታላቅ እህቷ ማርጎት ፍራንክ።
አና ፍራንክ የምትታወቀው በፃፈችው ግለ-ታሪክ ሲሆን በዚሁ መጽሐፍ እንደገለፀችው " የሔዋን ሕልም " እና " የኬዲ ሕይወት "የተሰኙ ልቦለዶችን ፅፋ ጨርሳ ነበር። በግለ ታሪኳም የአፃፃፍ ብቃቷን አሳይታለች፤ በዚህም የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ሰው የሚለውን ማዕረግ ለመስጠት ከቀረቡ እጮዎች ውስጥ አንዷ ነበረች። እነዚህም አልበርት አነስታይን፣ ሲግመንድ ፍሮይድ፣ ቻርለስ ዳርዊን፣ ሉዊ ፓስተር እና አና ፍራንክ።
እናንተም ይህን መፅሐፍ እንድታነቡት እንጋብዛለን። በአምስቱ ምዕራፍ እንደቅምሻ ያየናቸው እንዳስተማሩዋቹም ተስፋ እናረጋለን። ለጓደኞቻችሁ ማካፈልን አትርሱ ብቻችንን መብላት ባህላችን አደለምና!!!
......................................................................
~~~እናመሰግናለን~~~
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫

💫 ከዚም ከዛም 💫
1. የአንድ መሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት ሀይሉ 175 k.m ወይም ከአ.አ እስከ አሰላ ያለውን ርቀት ይሸፍናል።
2. በቻይና ቲቤት ግዛት ውስጥ ምላስን ጎልጉሎ የማውጣት ሒደት ከጨዋ ቤተሰብ እንደተወለድን ያሳያል አሉ።😜
3. በአውስትራሊያ ክንፍ ያላቸው ቀበሮዎች ይገኛሉ። የእነዚህ ቀበሮዎች ስጋ ለጀርባ አጥንትና ለመገጣጠሚያ ህመሞች ፈውስ ይሆናል።
4. ዶሮ እንቁላል ስትጥል በ10ኛው ቀን የምትጥለው እንቁላል ከሌሎቹ በመጠን ያደገ ነው።
#share

🌓 ከግጥም ማህደር 🌗
ፉከራ
""""'''""
ፈሪ ጨነቀው ተርበደበደ
ጥይት ዘነመ እሳት ወረደ
ውረድ እንውረድ ተባባሉና
አስደበደቡት አፋፍ ቆሙና።
የፈሪ እናት ታስታውቃለች
አፋፍ ላይ ሆና ተው ሽሽ ትላለች
የጎበዝ እናት ታስታውቃለች
እመሀል ገብታ በለው ትላለች።
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
🌘🌓🌔🌓🌑🌕🌖🌗
ፉከራ
""""'''""
ፈሪ ጨነቀው ተርበደበደ
ጥይት ዘነመ እሳት ወረደ
ውረድ እንውረድ ተባባሉና
አስደበደቡት አፋፍ ቆሙና።
የፈሪ እናት ታስታውቃለች
አፋፍ ላይ ሆና ተው ሽሽ ትላለች
የጎበዝ እናት ታስታውቃለች
እመሀል ገብታ በለው ትላለች።
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
🌘🌓🌔🌓🌑🌕🌖🌗
💫 ከግጥም መሀደር 💫
የወንድሙን ደም ላልመለሰ ሰው
የዕገሊት ወዳጅ ጭራሽም ልብ የለው
የወንድሙ ሬሳ ወድቆ የከረመው
ልብማ ቢኖረው ደሙን ይመልሳል
በግንባሩ ደፍቶ አንጀቱን ያርሳል።
ጠመንጃ መተኮስ እሱም ያውቅበታል
ወሬ አይደበቅም ደመኛም አውቆታል
በሩ ላይ ተጋድሞ ያላግጥበታል።
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
🌕🌖🌗🌘🌑🌒🌓🌔
የወንድሙን ደም ላልመለሰ ሰው
የዕገሊት ወዳጅ ጭራሽም ልብ የለው
የወንድሙ ሬሳ ወድቆ የከረመው
ልብማ ቢኖረው ደሙን ይመልሳል
በግንባሩ ደፍቶ አንጀቱን ያርሳል።
ጠመንጃ መተኮስ እሱም ያውቅበታል
ወሬ አይደበቅም ደመኛም አውቆታል
በሩ ላይ ተጋድሞ ያላግጥበታል።
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
🌕🌖🌗🌘🌑🌒🌓🌔
💫 ከዚም ከዛም 💫
1. በአለም ውስጥ በስልክ ደውለው የማያውቁና ተደውሎላቸውም የማያውቁ ሠዎች በ2012 50% ብቻ ይሆኑ ነበር።
2. ህፃናት ወይም የአንድ አራት አመት ልጅ በቀን 400 ጊዜ ወላጆቹን ይጠይቃል ተብሎ ይገመታል።
3. ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።
4. የሰው ልጅ የድመትን 1/6(አንድ ስድስተኛ) ያያል።
5. የአሳ ነባሪ ጭራ ላይ ያለው መዋኛ የአንድ መለስተኛ አውሮኘላን ክንፎችን ያክላል።
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
🌕🌓🌖🌒🌗🌓🌖🌑

👳♂ ለፈገግታ 👳♂
አንድ የውጭ ዜጋ በሚኖርበት ሀገር አንድ ኢትዮጵያዊ ሊቅ አገኘ አሉ። ኢትዮጵያ ለጉብኝት ሔዶ የግዕዝ ዜማዎችን ከመውደዱ የተነሳ በመቅረፀ ድምፁ እንደቀዳ ነግሮ ላሰማዎት አላቸው። ለካስ ይህ ሰው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግዕዝ ያውቅ መስሎታል አንዱን ጩልሌ ጠይቆት ኖሯል። ታድያ የተቀዳው ሲሰማ "ችቦ አይሞላም ወገቧ ችቦ አይሞላም ወገቧ ማር እሸት ነው ቀለቧ" የሚል ሙዚቃ ሆኖ ያገኙታል። የለም አታሎሀል- እንዳይሉት ኢትዮጵያውያን ያታልላሉ ሊል ነው። ዝም እንዳይሉት ልክ አይደለም።
" ይሀውልክ የኔ ልጅ ይህ የድሮ ነው አሁን አንጠቀምበትም፤ ይህን አጥፋና አዲሱን ልበልልህ።" ብለው አስቀየሩት አሉ።
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
#share #participate #comment
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚

🔥 ቅምሻ 🔥 ከእናንተው
#በዓለ_ደብረ_ታቦር_እና_ቡሄ
ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን በሰላም አደረሰን!
ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ‹ቡሄ› በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ‹መላጣ፣ ገላጣ› ማለት ነው፡፡ በአገራችን ክረምቱ፣ ጭጋጉ፣ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለ ኾነ በዓሉ ‹ቡሄ› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓለ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት፤ ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበ ዕለት ስለ ኾነ ‹የብርሃን› ወይም ‹የቡሄ› በዓል ይባላል፡፡
ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፤ ወደ መፀው የሚገባበት፤ ወገግታ የሚታይበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚሸጋገርበት ወቅት በመኾኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንዲሉ፡፡ በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የቡሄ ዕለት ማታ ምእመናን ችቦ ያበራሉ፡፡ ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው፡፡ ሕፃናቱ ይህ በዓል ከመድረሱ በፊት ቀደም ብለው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮኹ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለዚህ በዓል የሚኾን ዳቦ ለመጋገር ስንዴያቸውን ሲያጥቡ፣ ሲፈትጉ ይሰነብታሉ፡፡ በበዓሉ ዋዜማ (ነሐሴ ፲፪ ቀን) ሕፃናት በየቤቱ እየዞሩ ‹‹ቡሄ ና በሉ፤ ቡሄ በሉ፡፡ ቡሄ መጣ፤ ያ መላጣ፤ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ …›› እያሉ ይጫወታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሡ ይሰጧቸዋል፡፡ ሕፃናቱ ‹ቡሄ› የሚሉትም ዳቦውን ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት እረኞች ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል፡፡ ‹ቡሄ› ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና በበዓሉ ችቦ የሚበራውም ከዚህ ታሪክ በመነሣት ነው፡፡ ለክርስትና ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ ለዘመድ አዝማድ ዅሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል፡፡ ልጆችም ዳቧቸውን እየገመጡ ጅራፍ ሲገርፉ ይውላሉ፡፡ የጅራፉ መጮኽ የድምፀ መለኮት ምሳሌ ሲኾን፣ ጅራፉ ሲጮኽ ማስደንገጡም ነቢያትና ሐዋርያት በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡
መምህረ ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ በደብረ ታቦር ምሥጢር መግለጡን በማስታዎስ የአብነት ተማሪዎች ከመምህራቸው ጋር በመኾን በዓለ ደብረ ታቦርን (ቡሄን) ያከብራሉ፤ ስሙን ይጠራሉ፡፡ የአብነት ተማሪዎች ‹‹ስለ ደብረ ታቦር›› እያሉ እኽል ከምእመናን በመለመንና ገንዘብ በማዋጣት ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምእመናን በመጋበዝና እርስበርስ በመገባበዝ፣ እንደዚሁም ቅኔ በማበርከት በዓለ ደብረ ታቦርን በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህም እስከ አሁን ድረስ በአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሠራበት ነባር ትውፊት ነው፡፡
ነገር ግን በአንድ አካባቢዎች በተለይ በከተማ ዙሪያ በዓለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) ሃይማኖታዊ ትውፊቱን የለቀቀ ይመስላል፡፡ ለዚህም ልጆች የሚጫወቱበት መዝሙር ግጥሙና ዜማው ዓለማዊ መልእክት የሚበዛበት መኾኑ፤ በወቅቱ ችቦ ከማብራት ይልቅ ርችት መተኮሱና በየመጠጥ ቤቱ እየሰከሩ መጮኹ፤ ወዘተ. የበዓሉን መንፈሳዊ ትውፊት ከሚያደበዝዙ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም በዚህ በዓል ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ የሚሽቀዳደሙ ነገር ግን የበዓሉን ታሪካዊ አመጣጥ የማያዉቁ ልጆችም ጥቂቶች አይደሉም፡፡
ስለዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው የበዓለ ደብረ ታቦርን መንፈሳዊነት፣ የመዝሙሮቹን ያሬዳዊነትና አከባበሩን ከቤተ ክርስቲያን መምህራን በመጠየቅ ማስተማር፤ ልጆችም ከወላጆች ወይም ከመምህራን በመጠየቅ የበዓሉን አከባበር መረዳትና የዚህን በዓል መንፈሳዊ ትውፊት ሳይበረዝ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባቸዋል፡፡ ‹‹ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና፤ የቡሄው ብርሃን ለእኛ በራልን …›› የሚለውንና ይህን የሚመስሉ መንፈሳውያን መዝሙራትን እየዘመሩ በየቤቱ በመዘዋወር የሚያገኙትን ዳቦና ገንዘብ ለነዳያንና ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ ልጆችንም ማበረታታትና አርአያነታቸውን መከተል ይኖርብናል፡፡
ምንጭ፡-
መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ መ/ር አፈወርቅ ተክሌ፤ ፳፻፭ ዓ.ም፣ ገጽ ፫፻፲፭-፫፻፲፯፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ፤ ፳፻፯ ዓ.ም፣ ገጽ ፻፲፩፡፡
መልካም በዓል ይኹንልን!
ማካፈልን እንዳይረሱ!
ለአስተያየት :-
@R_e_a_d_e_rs

🦅💫 ከግጥም ማህደር 💫🦅
ጠጅም አላገኘን ከተለየናቸው፤
አውራው ከተያዘ ማሩን እባካችሁ።
ለሚኒልክ ተዝካር እንዲቆይላት፤
እባክህ ማር ብላ ለመነች ንግሥት።
ንቡ እንዲበታተን አውራውን ይዛችሁ፤
ኮዳውን ተውሀ ማሩን እባካችሁ።
ወይ ለኛ አትሆነን ወይም ለራስህ፤
ልትፈጀን ነው ወይ ጤና አሳጥተህ?
ድንገት ሳላስበው በልቼ ጠጥቼ፤
ልሞትላችሁ ነው ተፍቼ ተፍቼ።
የበላሁት ጮማ ሆዴን አመመው፤
የጠጣሁትም ጠጅ ሆዴን አመመው፤
እንደምን አድርጌ ተፍቼ ላውጣው!!
ቢጠሉት ይሆናል ወይም ቢወዱት፤
ካልጋ ሥር አግብተው የሚጠብቁት።
እሱ ደልቶት ኖረ ብለው እንዳይወቅሱ፤
ካልጋ ሥር ይሻላል ብሎ ተኛ እያሱ።
/ከነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ቅኔዎች በጥቂቱ
#share #comment #participate
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ጠጅም አላገኘን ከተለየናቸው፤
አውራው ከተያዘ ማሩን እባካችሁ።
ለሚኒልክ ተዝካር እንዲቆይላት፤
እባክህ ማር ብላ ለመነች ንግሥት።
ንቡ እንዲበታተን አውራውን ይዛችሁ፤
ኮዳውን ተውሀ ማሩን እባካችሁ።
ወይ ለኛ አትሆነን ወይም ለራስህ፤
ልትፈጀን ነው ወይ ጤና አሳጥተህ?
ድንገት ሳላስበው በልቼ ጠጥቼ፤
ልሞትላችሁ ነው ተፍቼ ተፍቼ።
የበላሁት ጮማ ሆዴን አመመው፤
የጠጣሁትም ጠጅ ሆዴን አመመው፤
እንደምን አድርጌ ተፍቼ ላውጣው!!
ቢጠሉት ይሆናል ወይም ቢወዱት፤
ካልጋ ሥር አግብተው የሚጠብቁት።
እሱ ደልቶት ኖረ ብለው እንዳይወቅሱ፤
ካልጋ ሥር ይሻላል ብሎ ተኛ እያሱ።
/ከነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ቅኔዎች በጥቂቱ
#share #comment #participate
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🌓 ቅምሻ 🌗
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተቃዋሚያቸው በአምባሳደር
ብርሃኑ ድንቄ ዓይን፣
Sisay Tefera Mekonnen
.
በግል ጥላቻ ሳንታወር ያለ አንዳች አድልዎ አጼ ኃይለ
ሥላሴን ለማስታወስ ጊዜ ካገኘን፣ አጼውን ብዙ ገጽ
ያላቸው አስደናቂ ሰው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
ኮንሰርቫቲቭ ናቸው ስንል ሊበራል የሆኑ ስራዎችን
ሲሰሩ እናገኛቸዋለን፣ ንቅዝ ናቸው ስንል ፍትህ ሲሰጡ
እናያቸዋለን፣ ጨካኝ ናቸው ስንል የርህራሄ ስራ
ከመስራት አያቋርጡም፣ በቀለኛ ናቸው ስንል ምህረት
ሲያደርጉ እናገኛቸዋለን፡፡ ይህ ፓራዶክስ ሊታመን
የማይችል ግን እውነተኛ ነገር ነው፡፡
.
አጼ ኃይለ ሥላሴ በሚያስደንቅ ሁኔታ የውስጡንና
የውጭውን ፖለቲካ እንደ ፉትቦል ተጫውተውታል፡፡
በውስጥና በውጭ የፖለቲካ ጨዋታ ኃይለ ሥላሴን
ያሸነፉ ተቃዋሚ ቡድኖች እነማናቸው ብሎ
የሚጠይቀኝ ቢኖር፣ እርጅና እና ከሳቸው እድሜ በኋላ
ወደፊት በአገሪቱ የሚሆነውን አርቆ የማስተዋል
ጉድለት ብዬ እመልስለታለሁ፡፡ በዘመናዊው አለም
ከ120-135 አመት እድሜ ያላቸው ሰዎች በህይወት
እንደሚኖሩ አልፎ አልፎ ብሰማም፣ እንደ ኃይለ ሥላሴ
ግን በ80 አመት አድሜው የንጉሠ ነገሥትነት ፍጹም
ስልጣን ይዞ በቀጥታ እያዘዘ የሚገዛ ንጉሥ ስለመኖሩ
አላውቅም፡፡
.
ኃይለ ሥላሴ በመጨረሻ ይታገሉ የነበሩት ከተፈጥሮ
ህግ ጋር ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ኃይለ ሥላሴ
ያለአንዳች ድካም በቀን 20 ሰአት የሰሩበት ጊዜ
ነበር፣ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመከታተልም በፍጹም
አይሰለቹም ነበር፡፡ እርጅና ከተጫናቸው በኋላ ግን
መርሳት፣ ማመንታት፣ መወላወል ጀመሩ፡፡
የመንግሥታቸው አባላትም በእግራቸው መቆም
የማይችሉ ንቅዞች ነበሩ፡፡ ኃይለ ሥላሴ እራሳቸውን
ከዙፋናቸው ገለበጡ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡
.
ኃይለ ሥላሴ ከዙፋናቸው እንደወረዱ የወታደራዊው
መንግሥት አለቃ ሆኖ የተሾመው ጄነራል አማን
አንዶም ‘Our Revolution’ እያለ ሲናገር በአሜሪካን
ቴሌቪዥን ሰምቼው ተገርሜያለሁ፡፡ ጄኔራል አማንን
በቅርብ አውቀዋለሁ፣ በዋሽንግተን የሚሊቴሪ አታሼ
ሆኖ ከኔ ጋር አንድ አመት ሰርቷል፡፡ ጤንነቱ ታውኮ
የህክምና ገንዘብ ሲቸግረው ለጃንሆይ አመልክቼለት
ሁለት ጊዜ በእርዳታ ገንዘብ ልከውለታል፣ እሱም
ምስጋና አቅርቧል፡፡
..
በኢትዮጵያ ያለው አስተዳደር እንዲሻሻል የሚጠይቅ
ግልጽ ደብዳቤ ለንጉሡ በጻፍኩ ጊዜም ጉዳዩን
ለጄኔራል አማን አስቀድሜ አማክሬው ነበር፡፡ የሰጠኝ
መልስ በዛሬው ጊዜ ለኢትዮጵያ ከኃይለ ሥላሴ
የሚሻል መሪ ማግኘት አይቻልም፣ ህዝቡ ወራዳ ነው፣
ብዙ ሊሻሻሉ የሚገቡ ነገሮች ቢኖሩም ሁከት
እንዳይነሳ መጠንቀቅ ያስፈልጋል የሚል ነበር፡፡
.
የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት በመቃወም በአሜሪካ
ያለውን የኢትዮጵያ ኤምባሴ ለቅቄ እንደወጣሁም፣
ጄኔራል አማን እኔን በመውቀስና ንጉሡን በማወደስ
ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ከ9 አመት በኋላ ንጉሡ አርጅተው መንግሰታቸውን
መምራት አቅቷቸው ከስልጣን ሲወድቁ ግን ጄኔራል
አማን ‘Our Revolution’ እያለ መናገር ጀመረ…
.
አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ፣ ቄሳርና አብዮት
#share #comment #participate
@Let_us_read_bot
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተቃዋሚያቸው በአምባሳደር
ብርሃኑ ድንቄ ዓይን፣
Sisay Tefera Mekonnen
.
በግል ጥላቻ ሳንታወር ያለ አንዳች አድልዎ አጼ ኃይለ
ሥላሴን ለማስታወስ ጊዜ ካገኘን፣ አጼውን ብዙ ገጽ
ያላቸው አስደናቂ ሰው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
ኮንሰርቫቲቭ ናቸው ስንል ሊበራል የሆኑ ስራዎችን
ሲሰሩ እናገኛቸዋለን፣ ንቅዝ ናቸው ስንል ፍትህ ሲሰጡ
እናያቸዋለን፣ ጨካኝ ናቸው ስንል የርህራሄ ስራ
ከመስራት አያቋርጡም፣ በቀለኛ ናቸው ስንል ምህረት
ሲያደርጉ እናገኛቸዋለን፡፡ ይህ ፓራዶክስ ሊታመን
የማይችል ግን እውነተኛ ነገር ነው፡፡
.
አጼ ኃይለ ሥላሴ በሚያስደንቅ ሁኔታ የውስጡንና
የውጭውን ፖለቲካ እንደ ፉትቦል ተጫውተውታል፡፡
በውስጥና በውጭ የፖለቲካ ጨዋታ ኃይለ ሥላሴን
ያሸነፉ ተቃዋሚ ቡድኖች እነማናቸው ብሎ
የሚጠይቀኝ ቢኖር፣ እርጅና እና ከሳቸው እድሜ በኋላ
ወደፊት በአገሪቱ የሚሆነውን አርቆ የማስተዋል
ጉድለት ብዬ እመልስለታለሁ፡፡ በዘመናዊው አለም
ከ120-135 አመት እድሜ ያላቸው ሰዎች በህይወት
እንደሚኖሩ አልፎ አልፎ ብሰማም፣ እንደ ኃይለ ሥላሴ
ግን በ80 አመት አድሜው የንጉሠ ነገሥትነት ፍጹም
ስልጣን ይዞ በቀጥታ እያዘዘ የሚገዛ ንጉሥ ስለመኖሩ
አላውቅም፡፡
.
ኃይለ ሥላሴ በመጨረሻ ይታገሉ የነበሩት ከተፈጥሮ
ህግ ጋር ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ኃይለ ሥላሴ
ያለአንዳች ድካም በቀን 20 ሰአት የሰሩበት ጊዜ
ነበር፣ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመከታተልም በፍጹም
አይሰለቹም ነበር፡፡ እርጅና ከተጫናቸው በኋላ ግን
መርሳት፣ ማመንታት፣ መወላወል ጀመሩ፡፡
የመንግሥታቸው አባላትም በእግራቸው መቆም
የማይችሉ ንቅዞች ነበሩ፡፡ ኃይለ ሥላሴ እራሳቸውን
ከዙፋናቸው ገለበጡ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡
.
ኃይለ ሥላሴ ከዙፋናቸው እንደወረዱ የወታደራዊው
መንግሥት አለቃ ሆኖ የተሾመው ጄነራል አማን
አንዶም ‘Our Revolution’ እያለ ሲናገር በአሜሪካን
ቴሌቪዥን ሰምቼው ተገርሜያለሁ፡፡ ጄኔራል አማንን
በቅርብ አውቀዋለሁ፣ በዋሽንግተን የሚሊቴሪ አታሼ
ሆኖ ከኔ ጋር አንድ አመት ሰርቷል፡፡ ጤንነቱ ታውኮ
የህክምና ገንዘብ ሲቸግረው ለጃንሆይ አመልክቼለት
ሁለት ጊዜ በእርዳታ ገንዘብ ልከውለታል፣ እሱም
ምስጋና አቅርቧል፡፡
..
በኢትዮጵያ ያለው አስተዳደር እንዲሻሻል የሚጠይቅ
ግልጽ ደብዳቤ ለንጉሡ በጻፍኩ ጊዜም ጉዳዩን
ለጄኔራል አማን አስቀድሜ አማክሬው ነበር፡፡ የሰጠኝ
መልስ በዛሬው ጊዜ ለኢትዮጵያ ከኃይለ ሥላሴ
የሚሻል መሪ ማግኘት አይቻልም፣ ህዝቡ ወራዳ ነው፣
ብዙ ሊሻሻሉ የሚገቡ ነገሮች ቢኖሩም ሁከት
እንዳይነሳ መጠንቀቅ ያስፈልጋል የሚል ነበር፡፡
.
የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት በመቃወም በአሜሪካ
ያለውን የኢትዮጵያ ኤምባሴ ለቅቄ እንደወጣሁም፣
ጄኔራል አማን እኔን በመውቀስና ንጉሡን በማወደስ
ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ከ9 አመት በኋላ ንጉሡ አርጅተው መንግሰታቸውን
መምራት አቅቷቸው ከስልጣን ሲወድቁ ግን ጄኔራል
አማን ‘Our Revolution’ እያለ መናገር ጀመረ…
.
አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ፣ ቄሳርና አብዮት
#share #comment #participate
@Let_us_read_bot
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
“የብዕር አሟሟት ሌላ”
ከጸጋዬ ገብረ መድኅን
.
(1959 ዓ.ም)
የቃለ – ልሣን ቅመሙ
የባለቅኔ ቀለሙ
ነጠበ እንጂ ፈሰሰ አንበል፣ ቢዘነበል እንኳ ደሙ
ሰከነ እንጂ ከሰለ አንበል፣ ቢከሰከስ እንኳን ዐፅሙ፤
የቃል እሳት ነበልባሉ
አልባከነምና ውሉ
የዘር – ንድፉ የፊደሉ
ቢሞት እንኳን ሞተ አትበሉ።
እስካልተዳፈነ ፍሙ
እስካልተሰበረ ቅስሙ
እስካልተቀበረ ስሙ
የደራሲ ዐፅመ – ወዙ
የብዕር ቀስተ – መቅረዙ
ሕዋሳቱ እስካልቀዘዙ፤
አልፏልና ከሥጋ – ሞት
በቃሉ ሚጠት ስልባቦት
በፊደሉ አድማሰ – ፍኖት
በኅብረ ቀለሙ ማኅቶት
በሥነ – ግጥሙ ምትሃት
በግሱ ንጥረ – ልሳናት
በነባቢቱ ነፍስ እሳት፤
ይነዝራልና ደም – ሥሩ፣ አይሞትምና ፀዳሉ
ቢሞት እንኳ ሞተ አትበሉ …
የብዕር አሟሟት ሌላ
ሲፈስ የብሌኑ ኬላ
የፊደል መቅረዝ አሟሟት
ከውስጥ ነው እንደ ጋን መብራት
በቁም ነው እንደ ቁም ፍትሐት
የሚያጨልም የነፍስ እሳት፤
እንጂ ብዕር ሞተ አትበሉ፣ እሳቱን ሳያስለመልም
ነበልባሉን ሳያከስም
ውጋጋኑን ሳያጨልም።
ቃለ – ምንጩን ካልመሰነ፣ ስለቱን ካልጐለደፈ
መቅረዙን ካልተዳፈነ፣ ከፊደሉ ካልነጠፈ
ዐፅመ – ወዙን ካልደረቀ፣ ጧፉን ቀልጦ ካልሰፈፈ
ጡጦ እንደጠፋበት አራስ፣ ቁም ተዝካሩን ካልለፈፈ
ብዕሩ ቀርቶ ምላሱ፣ በሃሜት ካልተንጠፈጠፈ፤
የቃለ – እሳት ነበልባሉ
የድምፀ ብርሃን ፀዳሉ
የኅብረ ቀለማት ኃይሉ
አልባከነምና ውሉ
የዘር – ንድፉ የፊደሉ
ቢሞት እንኳን ሞተ አትበሉ።
#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ከጸጋዬ ገብረ መድኅን
.
(1959 ዓ.ም)
የቃለ – ልሣን ቅመሙ
የባለቅኔ ቀለሙ
ነጠበ እንጂ ፈሰሰ አንበል፣ ቢዘነበል እንኳ ደሙ
ሰከነ እንጂ ከሰለ አንበል፣ ቢከሰከስ እንኳን ዐፅሙ፤
የቃል እሳት ነበልባሉ
አልባከነምና ውሉ
የዘር – ንድፉ የፊደሉ
ቢሞት እንኳን ሞተ አትበሉ።
እስካልተዳፈነ ፍሙ
እስካልተሰበረ ቅስሙ
እስካልተቀበረ ስሙ
የደራሲ ዐፅመ – ወዙ
የብዕር ቀስተ – መቅረዙ
ሕዋሳቱ እስካልቀዘዙ፤
አልፏልና ከሥጋ – ሞት
በቃሉ ሚጠት ስልባቦት
በፊደሉ አድማሰ – ፍኖት
በኅብረ ቀለሙ ማኅቶት
በሥነ – ግጥሙ ምትሃት
በግሱ ንጥረ – ልሳናት
በነባቢቱ ነፍስ እሳት፤
ይነዝራልና ደም – ሥሩ፣ አይሞትምና ፀዳሉ
ቢሞት እንኳ ሞተ አትበሉ …
የብዕር አሟሟት ሌላ
ሲፈስ የብሌኑ ኬላ
የፊደል መቅረዝ አሟሟት
ከውስጥ ነው እንደ ጋን መብራት
በቁም ነው እንደ ቁም ፍትሐት
የሚያጨልም የነፍስ እሳት፤
እንጂ ብዕር ሞተ አትበሉ፣ እሳቱን ሳያስለመልም
ነበልባሉን ሳያከስም
ውጋጋኑን ሳያጨልም።
ቃለ – ምንጩን ካልመሰነ፣ ስለቱን ካልጐለደፈ
መቅረዙን ካልተዳፈነ፣ ከፊደሉ ካልነጠፈ
ዐፅመ – ወዙን ካልደረቀ፣ ጧፉን ቀልጦ ካልሰፈፈ
ጡጦ እንደጠፋበት አራስ፣ ቁም ተዝካሩን ካልለፈፈ
ብዕሩ ቀርቶ ምላሱ፣ በሃሜት ካልተንጠፈጠፈ፤
የቃለ – እሳት ነበልባሉ
የድምፀ ብርሃን ፀዳሉ
የኅብረ ቀለማት ኃይሉ
አልባከነምና ውሉ
የዘር – ንድፉ የፊደሉ
ቢሞት እንኳን ሞተ አትበሉ።
#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
ካነበብነው📖📜📰🗞 pinned «ውድ የዚቻናል አባላት 6710 ላይ A ብላችሁ በመላክ የልብ ሕክምና ማእከልን በቀላሉ መርዳት ትችላላችሁ። 6710 ላይ A ብለው ከላኩ አንድ ብር ብቻ ከሒሳቦ ላይ ወደ ማእከሉ ገቢ ይሆናል። ላልሰሙት ማካፈልን አትርሱ እናመሰግናለን!!!! @Readers_To_Know»
“ያጼ በካፋ በግ”
.
.
አፄ በካፋ አንድ የሚወዱት ለማዳ በግ ነበራቸው።
ሲቀላውጥ ይውልና አዳሩ ከእልፍኛቸው ነው
የሚያድር። የመወደዱ ብዛት አዋጅ ወጣለት። “ያጼ
በካፋ በግ በገባበት ቤት ሳይጋበዝ የቀረ እንደሆነ
አይቀጡ ቅጣት እቀጣለሁ” ተባለ።
እንደ አቀማጠሉት ታውቆት ቅልውጡ ባሰበት።
በቅልውጡ የተነሳ ሰው አጥብቆ ተመረረ። ቅልውጡ
ቀርቶ ከደጅ የሚሰጣውን ያወድማል።
እንዲህ እያስለቀሰ ሲኖር አንድ ቀን ሲፈርድበት
ከአንድ ደብተራ ቤት ዘው አለ። ደብተራው “እንኳ
የመጣህልኝ” ብሎ ሲያበቃ ደጁን ዘግቶ እንክት አርጎ
አረደው። ሥጋውን ዘልዝሎ ኸጓዳው ሰቀለ። የበጉ
አመል የትም ሲቀላውጥ ውሎ አዳሩ ከንጉሡ እልፍኝ
ነበር። ሲጠፋ ጊዜ በያለበት ፈልጉ ተባለ።
ወደ ተንኮለኛ ደብተራ እንመለስ።
የበጉን ደበሎ ብራና ፋቀው። ቀጥሎ ብራናውን
በትንንሽ ቆራርጦ በቍራጮቹ፣
“የንጉሡን በግ እኔ ነኝ አርጄ የበላሁት። ጮማ ነበር።
መጣፈጡም ግሩም ነው። መታረዱም ይገባዋል።
መክለፍለፍ አብዝቶ ድሀ አስለቅሷልና”
ብሎ ጽፎ ቁራጮቹን ወስዶ በስውር ሰው እንዳያየው
አርጎ ካደባባይ በተናቸው።
መቸም በከተማው የንጉሥ ባለሟል ጠፍቷል ተብሎ
በያለበት ፍለጋ ተይዟል። ሁለት ወይ ሦስት ሰዎች
ቁራጮች አይተው አንስተው አንብበው ለንጉሡ
አደረሱ።
በተነበበ ጊዜ ንጉሡ እጅግ አጥብቀው ተቆጡ፡
“እንዴት አባቱ ያለ ደፋር ነው! ተማረዱ ጽፎ አደባባይ
ብራናውን መበተኑ። ቆይ ሳትያዝ የቀረህ እንደሆነ”
አሉና በምስጢር አርገው፤
“ስስ ወርቅ አምጡና መዝኑ። ተተመዘነ በኋላ
ወስዳችሁ ከግቢው አደባባይ ዠምራችሁ እስከ
አውራው ጐዳና በትኑት። ቀጥላችሁ የታመነ የታመነ
ዘበኛ ተተነሰነሰው ወርቅ እልፍ ብለው ቆባ ብለው
አጐንብሶ የሚያነሳውን ሰው ይያዙ” ብለው አዘዙ።
መቼም ሌባና አጥፊ እንቅልፍ የለው የሚወራውን
የሚሆነውን ሁሉ ተጠንቅቆ እህ ይላል። በብልሃቱ
ብዛት የበጋቸው ሌባ የወርቅ ወጥመድ መጠመዱን
አወቀ።
“ቆይ እዚህማ ብልሃት አለኝ” ይልና ቶሎ መጫምያ
አሰፍቶ ታቹን ምድር የሚረግጠውን ወገን በሰም
መረገው። ቀጥሎ መጫምያውን አጥልቆ ጥምጥሙን
አሳምሮ ጠምጥሞ መቋምያውን ይዞ አንጓቦ ወርቅ
በተዘራበት መንገድ አረጋገጡን ወደ ምድር ጫን
እያደረገ እየረገጠ ወርቁ ከሰሙ ውስጥ እንዲጠልቅ
ነው ብልሃቱ።
እንደዚህ እየሆነ እየተንደላቀቀ ሁለት ሦስት ጊዜ
ተመላለሰ። ከቤቱ እየገባ የተለጠፈውን ወርቅ እያነሳ
እያስቀመጠ አንድም ሰው ሳያውቅበት ማታ በሆነ ጊዜ
“እስኪ ወርቁን አንሱትና መዝኑት” ተባለ። ቢመዝኑት
ቅምጥል ብሎ ጐደለ። ለንጉሡ ይኼንን ቢያሰሙ
የባሰውን ተናደዱ።
ዘበኞቹም “እኛ ኩስትር ብለን ነው የጠበቅነ ዳሩ ግን
አንድም ሰው አጐንብሶ ሲያነሳ አላየነ” አሉ።
ንጉሡ ቢቸግራቸው “ጠንቋዮች ጥሩ” ብለው
አስመጡ። “እንደዚህ ያለ ሥራ የሚሰራ የት ነው
የተቀመጠው?“ ብለው ጠየቋቸው። ከገሌ አፈር ላይ
ነው ብለው አሉ።
ወታደር ሂዱ ያዙ ተብሎ ታዞ ይሄዳል ግን ማንም
አያገኙ። ስለምን ደብቴ እጅግ ብልህ ነውና
የሚያረጉትን ሁላ አውቆታል። ለዚህ ብልሃት ተአራት
አምስት አገር አፈር አስመጥቶ ከቤቱ ውስጥ
አስቀምጦ ከዝያ ላይ ይቀመጥበታል። ያገሩን አፈር
እያለዋወጠ ማለት ወታደር ታዞ ሲሄድ ጠንቋዮቹ
በመሯቸው ስፍራ ሰውየውን ያጡታል።
የተቀመጠበትን አፈር ትቶ ከሌላ አፈር ላይ
ይቀመጣል። ወታደሩም በከንቱ ማሰኑ ጠንቋዮቹም
ተነቀፉ።
ንጉሡም የባሰውን ተናደዱ። ከዚህ ወዲህ ቆይ ሌላ
ብልሃት አለኝ ብለው ሚስጢርዎን በሆድዎ ከተው
ድግስ ደገሱ። አለቆች፣ ካህናት፣ ተማሪ፣ ደብተራ
የተባለ ሁሉ ትምህርት የጠቀሰ ሁሉ ግብር እንዲበላ
አዘዙ። በዚህ ማኽል የታመኑ የታመኑ ሰዎች
በምስጢር አርገው መርጠው አሰናዱ።
“ድግሱ በደረሰ ጊዜ እነዚህን የተመረጡትን ሰዎች
ካህናቱ ሁሉ ገብተው ሲበሉ ሲጠጡ መጠጡን በገፍ
አርጋችሁ ስፍራውን ተከፋፍላችሁ ይዛችሁ ኮስተር
ብላችሁ ጠብቁ። በመጠጥ ብዛት የተነሳ ያ ተንኮለኛ
ለባልንጀራው ሳይለፈልፍ አይቀርምና በሰማችሁ ጊዜ
ለምለም ዦሮውን በስለት ቀንጥቦ ምልክት እንዲሆን
ነው” ብለው አዘዙ። “ካህናቱ ጠዋት ሲወጡ ከዦሮው
ምልክት ያለበት እንዲያዝ” አሉ።
እውን እንዳሉትም በመጠጥ ብዛት የተነሳ ደብቴ
ተቸነፈና ለባልንጀራው ተበጉ መታረድ ጀምሮ እስከ
ወርቁ እስከ ጠንቋዮቹ ድረስ የሆነውን ሁሉ
ዘከዘከለት። ይህን ሁሉ ሲዘከዝክ በዠርባው በኩል
የቆመው ሰላይ ወደነሱ ዦሮውን ጣል አርጎ ኑሮ አንዱ
ሳያመልጠው ሁሉን ሰምቷል። በስካር ብዛት የተነሳ
ሁሉም ተረፍርፎ እንቅልፍ ወስዷቸው ያ የሰማው
ሰላይ ይህን ጊዜ ነው ብሎ ለምለም ዦሮውን
ቀነጠበ።
ደብቴ ብዙ እንቅልፍ ተተኛ በኋላ ዦሮው ቆጠቆጠው።
በጁ ቢዳብስ ዦሮው ተቀንጥባ “አሁን ገና ተያዝሁ”
ይልና አያሌ ተማሪዎችና ደብተሮች ከተረፈረፉት
ለምለም ዦሮዋቸውን ቀነጠበ። እንዳይነጋ የለም ነጋ።
መቼም ያ ሰላይ የደብቴን ዦሮ የቀነጠበ ለሽልማቱ
ሲል የምስራችን አድርሷል። ንጉሡም ደስ ብሏቸው
“ምንየ በነጋ” ብለው ቸኩለዋል።
ሲነጋ “በሉ እንግዴህ ካህናቱንና ተማሪውን ሁሉ
አስወጡ። ያ ለምለም ዦሮውን የተቆረጠውን ያዙና
አምጡ” ብለው አዘዙ። ካህናት በወጣ አያሌ ለምለም
ዦሮዋቸው ተቆርጦ ይህንን ነገር ለንጉሡ ባስታወቁ
ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተናደዱ። ቀጥለውም የምስራች
ቀናኝ ብሎ ያለኝን ይጠራ አሉ።
በመጣ ጊዜ “በል አንተ አብደሃልን? ይህን ሁሉ
ያዛውንት ጆሮ ቁረጥልኝ ብየኻለሁን” አሉት።
“እኔስ ንጉሥ ሆይ ያንድ ተማሪ ለምለም ዦሮውን ብቻ
ነው የቆረጥሁት” አለ።
ንጉሡም “እንግድያውስ ይህ ሸረኛ ደብተራ ሲነቃ
የሰራውን ሥራ ዦሮው አስታውሶት ተነስቶ የነዚህን
ሁሉ ተማሪ ዦሮ መንድቧል” አሉ።
ተዚህ ወዲህ በደብቴ ብልሃት ተገርመው እንደዚህ
ያለ ብልህ ተመቅጣት ይልቅስ ሸልሞ መሾም
ይበልጣል ለመንግሥት ይጠቅማል ብለው አውጥተው
አውርደው አስበው፣
“ነጋሪት ይውጣ አዋጅ ንገሩ የንጉሥን በግ የበላ
ደብተራ ምሬአለሁ። ከቶም ሸልሜ እሾመዋለሁ።
ላልከዳ ምያለሁ። ይምጣ አይስጋ ብላችሁ አስታውቁ”
ብለው አዘዙ።
አዋጁም ተነገረ።
ደብቴ ይኼንን አዋጅ በሰማ ጊዜ አጥብቆ ደስ ብሎት
ጌጡን አጋጊጦ ሲደለቅ ወደ አደባባይ ብቅ ብሎ
ላጋፋሪ ለንጉሡ መምጣቱን እንዲያስታውቅለት
ለመነ። አስታወቀ ተጠርቶ ገባ።
“ስማ ተጀምሮ እስከ ድግሱ ድረስ እንደምን አደረግህ”
ብለው በመልካም ዓይን አይተውት ጠየቁት።
እርሱም ተጀምሮ እስኪጨርስ ያደረገውን ሁሉ
አፈሰሰ።
ንጉሡም ቃሉን ሁሉ ሰምተው ተገረሙ። ወድያውም
ሾሙት።
.
[ምንጭ] – Major J. Eadie. 1924. “An
Amharic Reader”. pp. 7-11.
#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
.
.
አፄ በካፋ አንድ የሚወዱት ለማዳ በግ ነበራቸው።
ሲቀላውጥ ይውልና አዳሩ ከእልፍኛቸው ነው
የሚያድር። የመወደዱ ብዛት አዋጅ ወጣለት። “ያጼ
በካፋ በግ በገባበት ቤት ሳይጋበዝ የቀረ እንደሆነ
አይቀጡ ቅጣት እቀጣለሁ” ተባለ።
እንደ አቀማጠሉት ታውቆት ቅልውጡ ባሰበት።
በቅልውጡ የተነሳ ሰው አጥብቆ ተመረረ። ቅልውጡ
ቀርቶ ከደጅ የሚሰጣውን ያወድማል።
እንዲህ እያስለቀሰ ሲኖር አንድ ቀን ሲፈርድበት
ከአንድ ደብተራ ቤት ዘው አለ። ደብተራው “እንኳ
የመጣህልኝ” ብሎ ሲያበቃ ደጁን ዘግቶ እንክት አርጎ
አረደው። ሥጋውን ዘልዝሎ ኸጓዳው ሰቀለ። የበጉ
አመል የትም ሲቀላውጥ ውሎ አዳሩ ከንጉሡ እልፍኝ
ነበር። ሲጠፋ ጊዜ በያለበት ፈልጉ ተባለ።
ወደ ተንኮለኛ ደብተራ እንመለስ።
የበጉን ደበሎ ብራና ፋቀው። ቀጥሎ ብራናውን
በትንንሽ ቆራርጦ በቍራጮቹ፣
“የንጉሡን በግ እኔ ነኝ አርጄ የበላሁት። ጮማ ነበር።
መጣፈጡም ግሩም ነው። መታረዱም ይገባዋል።
መክለፍለፍ አብዝቶ ድሀ አስለቅሷልና”
ብሎ ጽፎ ቁራጮቹን ወስዶ በስውር ሰው እንዳያየው
አርጎ ካደባባይ በተናቸው።
መቸም በከተማው የንጉሥ ባለሟል ጠፍቷል ተብሎ
በያለበት ፍለጋ ተይዟል። ሁለት ወይ ሦስት ሰዎች
ቁራጮች አይተው አንስተው አንብበው ለንጉሡ
አደረሱ።
በተነበበ ጊዜ ንጉሡ እጅግ አጥብቀው ተቆጡ፡
“እንዴት አባቱ ያለ ደፋር ነው! ተማረዱ ጽፎ አደባባይ
ብራናውን መበተኑ። ቆይ ሳትያዝ የቀረህ እንደሆነ”
አሉና በምስጢር አርገው፤
“ስስ ወርቅ አምጡና መዝኑ። ተተመዘነ በኋላ
ወስዳችሁ ከግቢው አደባባይ ዠምራችሁ እስከ
አውራው ጐዳና በትኑት። ቀጥላችሁ የታመነ የታመነ
ዘበኛ ተተነሰነሰው ወርቅ እልፍ ብለው ቆባ ብለው
አጐንብሶ የሚያነሳውን ሰው ይያዙ” ብለው አዘዙ።
መቼም ሌባና አጥፊ እንቅልፍ የለው የሚወራውን
የሚሆነውን ሁሉ ተጠንቅቆ እህ ይላል። በብልሃቱ
ብዛት የበጋቸው ሌባ የወርቅ ወጥመድ መጠመዱን
አወቀ።
“ቆይ እዚህማ ብልሃት አለኝ” ይልና ቶሎ መጫምያ
አሰፍቶ ታቹን ምድር የሚረግጠውን ወገን በሰም
መረገው። ቀጥሎ መጫምያውን አጥልቆ ጥምጥሙን
አሳምሮ ጠምጥሞ መቋምያውን ይዞ አንጓቦ ወርቅ
በተዘራበት መንገድ አረጋገጡን ወደ ምድር ጫን
እያደረገ እየረገጠ ወርቁ ከሰሙ ውስጥ እንዲጠልቅ
ነው ብልሃቱ።
እንደዚህ እየሆነ እየተንደላቀቀ ሁለት ሦስት ጊዜ
ተመላለሰ። ከቤቱ እየገባ የተለጠፈውን ወርቅ እያነሳ
እያስቀመጠ አንድም ሰው ሳያውቅበት ማታ በሆነ ጊዜ
“እስኪ ወርቁን አንሱትና መዝኑት” ተባለ። ቢመዝኑት
ቅምጥል ብሎ ጐደለ። ለንጉሡ ይኼንን ቢያሰሙ
የባሰውን ተናደዱ።
ዘበኞቹም “እኛ ኩስትር ብለን ነው የጠበቅነ ዳሩ ግን
አንድም ሰው አጐንብሶ ሲያነሳ አላየነ” አሉ።
ንጉሡ ቢቸግራቸው “ጠንቋዮች ጥሩ” ብለው
አስመጡ። “እንደዚህ ያለ ሥራ የሚሰራ የት ነው
የተቀመጠው?“ ብለው ጠየቋቸው። ከገሌ አፈር ላይ
ነው ብለው አሉ።
ወታደር ሂዱ ያዙ ተብሎ ታዞ ይሄዳል ግን ማንም
አያገኙ። ስለምን ደብቴ እጅግ ብልህ ነውና
የሚያረጉትን ሁላ አውቆታል። ለዚህ ብልሃት ተአራት
አምስት አገር አፈር አስመጥቶ ከቤቱ ውስጥ
አስቀምጦ ከዝያ ላይ ይቀመጥበታል። ያገሩን አፈር
እያለዋወጠ ማለት ወታደር ታዞ ሲሄድ ጠንቋዮቹ
በመሯቸው ስፍራ ሰውየውን ያጡታል።
የተቀመጠበትን አፈር ትቶ ከሌላ አፈር ላይ
ይቀመጣል። ወታደሩም በከንቱ ማሰኑ ጠንቋዮቹም
ተነቀፉ።
ንጉሡም የባሰውን ተናደዱ። ከዚህ ወዲህ ቆይ ሌላ
ብልሃት አለኝ ብለው ሚስጢርዎን በሆድዎ ከተው
ድግስ ደገሱ። አለቆች፣ ካህናት፣ ተማሪ፣ ደብተራ
የተባለ ሁሉ ትምህርት የጠቀሰ ሁሉ ግብር እንዲበላ
አዘዙ። በዚህ ማኽል የታመኑ የታመኑ ሰዎች
በምስጢር አርገው መርጠው አሰናዱ።
“ድግሱ በደረሰ ጊዜ እነዚህን የተመረጡትን ሰዎች
ካህናቱ ሁሉ ገብተው ሲበሉ ሲጠጡ መጠጡን በገፍ
አርጋችሁ ስፍራውን ተከፋፍላችሁ ይዛችሁ ኮስተር
ብላችሁ ጠብቁ። በመጠጥ ብዛት የተነሳ ያ ተንኮለኛ
ለባልንጀራው ሳይለፈልፍ አይቀርምና በሰማችሁ ጊዜ
ለምለም ዦሮውን በስለት ቀንጥቦ ምልክት እንዲሆን
ነው” ብለው አዘዙ። “ካህናቱ ጠዋት ሲወጡ ከዦሮው
ምልክት ያለበት እንዲያዝ” አሉ።
እውን እንዳሉትም በመጠጥ ብዛት የተነሳ ደብቴ
ተቸነፈና ለባልንጀራው ተበጉ መታረድ ጀምሮ እስከ
ወርቁ እስከ ጠንቋዮቹ ድረስ የሆነውን ሁሉ
ዘከዘከለት። ይህን ሁሉ ሲዘከዝክ በዠርባው በኩል
የቆመው ሰላይ ወደነሱ ዦሮውን ጣል አርጎ ኑሮ አንዱ
ሳያመልጠው ሁሉን ሰምቷል። በስካር ብዛት የተነሳ
ሁሉም ተረፍርፎ እንቅልፍ ወስዷቸው ያ የሰማው
ሰላይ ይህን ጊዜ ነው ብሎ ለምለም ዦሮውን
ቀነጠበ።
ደብቴ ብዙ እንቅልፍ ተተኛ በኋላ ዦሮው ቆጠቆጠው።
በጁ ቢዳብስ ዦሮው ተቀንጥባ “አሁን ገና ተያዝሁ”
ይልና አያሌ ተማሪዎችና ደብተሮች ከተረፈረፉት
ለምለም ዦሮዋቸውን ቀነጠበ። እንዳይነጋ የለም ነጋ።
መቼም ያ ሰላይ የደብቴን ዦሮ የቀነጠበ ለሽልማቱ
ሲል የምስራችን አድርሷል። ንጉሡም ደስ ብሏቸው
“ምንየ በነጋ” ብለው ቸኩለዋል።
ሲነጋ “በሉ እንግዴህ ካህናቱንና ተማሪውን ሁሉ
አስወጡ። ያ ለምለም ዦሮውን የተቆረጠውን ያዙና
አምጡ” ብለው አዘዙ። ካህናት በወጣ አያሌ ለምለም
ዦሮዋቸው ተቆርጦ ይህንን ነገር ለንጉሡ ባስታወቁ
ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተናደዱ። ቀጥለውም የምስራች
ቀናኝ ብሎ ያለኝን ይጠራ አሉ።
በመጣ ጊዜ “በል አንተ አብደሃልን? ይህን ሁሉ
ያዛውንት ጆሮ ቁረጥልኝ ብየኻለሁን” አሉት።
“እኔስ ንጉሥ ሆይ ያንድ ተማሪ ለምለም ዦሮውን ብቻ
ነው የቆረጥሁት” አለ።
ንጉሡም “እንግድያውስ ይህ ሸረኛ ደብተራ ሲነቃ
የሰራውን ሥራ ዦሮው አስታውሶት ተነስቶ የነዚህን
ሁሉ ተማሪ ዦሮ መንድቧል” አሉ።
ተዚህ ወዲህ በደብቴ ብልሃት ተገርመው እንደዚህ
ያለ ብልህ ተመቅጣት ይልቅስ ሸልሞ መሾም
ይበልጣል ለመንግሥት ይጠቅማል ብለው አውጥተው
አውርደው አስበው፣
“ነጋሪት ይውጣ አዋጅ ንገሩ የንጉሥን በግ የበላ
ደብተራ ምሬአለሁ። ከቶም ሸልሜ እሾመዋለሁ።
ላልከዳ ምያለሁ። ይምጣ አይስጋ ብላችሁ አስታውቁ”
ብለው አዘዙ።
አዋጁም ተነገረ።
ደብቴ ይኼንን አዋጅ በሰማ ጊዜ አጥብቆ ደስ ብሎት
ጌጡን አጋጊጦ ሲደለቅ ወደ አደባባይ ብቅ ብሎ
ላጋፋሪ ለንጉሡ መምጣቱን እንዲያስታውቅለት
ለመነ። አስታወቀ ተጠርቶ ገባ።
“ስማ ተጀምሮ እስከ ድግሱ ድረስ እንደምን አደረግህ”
ብለው በመልካም ዓይን አይተውት ጠየቁት።
እርሱም ተጀምሮ እስኪጨርስ ያደረገውን ሁሉ
አፈሰሰ።
ንጉሡም ቃሉን ሁሉ ሰምተው ተገረሙ። ወድያውም
ሾሙት።
.
[ምንጭ] – Major J. Eadie. 1924. “An
Amharic Reader”. pp. 7-11.
#share #comment #participate
@R_e_a_d_e_rs
@Let_us_read_bot
📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
👣🧞♂ከዚም ከዛም🧞♂👣
1. የአለማችን ጥንታዊ ከተማ ደማስቀስ ትባላለች፤ መገኛዋም በሶሪያ ምድር ነው።
2. Titanic መርከብ 🛳⚓️ 3547 ሠዎችን መያዝ ትችል ነበር። ወደላይ ርዝመቷም 269 m ነበር።
3. የአለም እግርኳስ⚽️ ዋንጫ🏆 በኡራጋይ🇺🇾 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1930 ዓ.ም ተጀመረ።
4. የኮንሶ ዋና ከተማ ካራይቲን ሲሆን ከካራይቲን በ17 k.m "New work" በአፈር ቁልል የተሠሩ ሠማይ ጠቀስ ፎቆች የሚገኙበት ቦታ ነው።
5. አባባል:- ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቆመን ማውረድ አቃተን!🤷♀🤷♂

🔑 ቅምሻ 🔑
🦅 ክፍል አንድ 🦅
....... የሰሎሜ አባት ያለምክንያት የሚባክን ገንዘብና ጊዜ ያበሳጫቸዋል። ገንዘብ የጊዜ ምንዛሪ ነው፤ ጊዜም ያልተመነዘረ ገንዘብ ነው የሚል ፍልስፍና አላቸው። ህይወት ረቂቅ ምስጢር ናት፤ አምላክ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህችን ምስጢራዊት ሕይወት ዕድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት አደለን። ይህቺም ከረጢት በውስጧ ዕድል በተሰኙ ፈርጦች ተሞልታለች። ከረጢቷን እንዳትሰረቅና ያለግዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጪ እንዳትሆን ፤ ኀላፊነቱን ፈጣሪ ለኛው ነው የሰጠን። በከረጢቷ ውስጥ ያሉትም ፈርጦች አንድ በአንድ ፣ አንዳንዴም ከአንድ በላይ ባንዴ እያብለጨለጩ ከባለ ከረጢቱ እጅ ላይ ይወድቃሉ። ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜው ያልተጠቀምንባቸው የዕድል ፈርጦች ከጊዜ ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈውን ይነጉዳሉ። ስኬት በትጋትና በሥራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደለም ይላሉ። ድኽነትም የባከኑ ዕድሎችና ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው እንጂ ያርባ ቀን እድል ነው ብለው አያምኑም።.............
ገፅ 42
~~~ይቀጥላል ~~~
"የተቆለፈበት ቁልፍ 🗝"
ከሚለው መጽሐፍ በጥቂቱ የተቃረመ።
ደራሲ :- ዶክተር ምህረት ደበበ
#share #comment #participate
አስተያየቶ ለኛ ያስፈልጋልና ቅር ያላቹን እንዲሁም ይቀጥል የምትሉትን አጋሩን። በተጨማሪም ስለ ቻናሉ አስተያየት ካላችሁ 👇

Forwarded from Quality Button [SCAM]
Behager lij is a home for incredible Ethiopian graphic designs and Branding. We excel at making creative and unique designs. check out works here and witness for yourself.
Contact 0922582607 or @naoliman
Contact 0922582607 or @naoliman