ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
💫 ቅምሻ 💫
....~~~~......
ክፍል ሁለት
..........ለምን ይሆን ሰዎች ስንባል አንዳችን በሌላችን ላይ ያለን እምነት እንዲህ የሳሳው? ያለ አንዳች ምክንያት ይህ ሊሆን እንደማይችል አውቃለሁ ያም ሆኖ አንዳንዴ ምን እንደማስብ ታውቂያለሽ ኪቲ መቼም መቼም ቢሆን በሰዎች ላይ (የራሴ በምትያቸው የቅርብ ሰዎች እንኳን) እምነት ሊኖርሽ እንደማይችል ስታውቂ በጣም የሚያስፈራና የሚጨንቅ ነገር አለው። .........
ገፅ 96-97
...........ስለ እውነት ነው የምልሽ ኪቲዬ ብኖርም ብሞትም እምብዛም ግድ የማይሰጠኝ ደረጃ ላይ ደርሻለሁ። ምን የሚያስጨንቀኝ ነገር አለ? ዓለም እንደው አና ጎደለች ብላ ጉዞዋን አታቆም ነገር። መሆን ያለበት ነገር ተወደደም ተጠላም የግድ መሆኑ አይቀርም ይልቅ ይህን ለማገድ መሞከሩ ነው ከንቱ ድካም።..............
ገፅ 103
...........ሀብትህ፣ ንብረትህ ቢጠፋብህ መልሰህ ስለማግኘትህ እርግጠኛ መሆን አትችልም እንደጠፋም ሊቀር የሚችል ነገር ነው። ደስታህ ግን ጠፍቶ ሊቀር የሚችል ነገር አይደለም። ጊዜያዊ በሆነ ከፈን ሊጋረድ ብቻ ነው የሚችለው። እናም በህይወት እስካለህ ድረስ ያንን ከፈን ልትገልጠው ዕድሉ አለህ። ያለምንም መሸማቀቅና ፍርሀት የሰማዩን መንበር በሙሉ ዐይንህ ማየት እስከቻልክ ድረስ ውስጥህ ሙሉ በሙሉ ንፁህ እስከሆነ ድረስ!..............
ገፅ 114
.....................................................................
~~~~ይቀጥላል~~~~

የአና ማስታወሻ /አዶኒስ እንደተረጎመው/ ከሚለው መፅሐፍ በጥቂቱ ያስተምራል እንዲሁም የፀሐፊዋን ድንቅ ችሎታ ያሳያል ተብሎ የቀረበ። ቆይታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን!!!
#share #participate #comment ማድረግ አይርሱ። ሰናይ ውሎ!

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ከዚም ከዛም 💫

1. እኛ ሀገር ጭንቅላትን ወደ ላይ ወደ ላይ ማነቃነቅ እሺ ማለት ሲሆን ጭንቅላትን ወደ ጎን ወደ ጎን ማነቃነቅ ደግሞ እንቢ ማለት ነው። በአልባንያ ሀገር ግን የዚህ ተቃራኒ ነው።😂😂😂

2. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አርክቴክት ምንትዋብ አዱኛ ይባላሉ።👏

3. ኮልጌት በስፓኒሽ ሒድ እራስህን ስቀል ማለት ነው አሉ 😜

4. ጉንዳን ለሰው እንዲደርስ ቢባል አንድ ሰው አንድ ሚልዮን ጉንዳኖች ያገኛል። ምን አለ ብር ቢሆኑ ኖሮ 😜😜😜

5. በአይስላንድ ቲፕ መስጠት እንደ ስድብ ይቆጠራል አሉ።

ማካፈልን እንዳይረሱ 👍
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ለፈገግታ 💫

የአሞራና የእባብ ንግግር
'''''''''''''''''''''''''''
`

'''''''''''''''''''''''''''
እባብ:- " እርካብህ ደመና ኮርቻህ አየር
ፈረስህ ነፋስ ነው መጣፊያህ ጠፈር
አዳራሽህ አየር እልፍኝህ የረር
መልክህ የመላክ ጥበብህ የእግዜር
አንተ የሰማይ ነዋሪ እኔ የመሬት
አገኝህ ይመስል ከንቱ ብታክት
ፍቅር ስደተኛው ያለ አይደርስበት
አንተን አስወደደኝ ካላጣሁት ፍጥረት
አሞራው አሞራው አየር ዋናተኛ
ና ውረድ ከዚህ ዛፍ ላይ አጠገቤ ተኛ። "
አሞራ:- " ታሪክሽን ለማያቅ በሩቅ ለሚያይሽ
በተዋበው ግጥምሽ ጣፋጩ ዜማሽ
እንደማር ወለላ ሲቀዳ ካፍሽ
ይመስለው ይሆናል ፍቅር የያዘሽ
እኔ ግን አውቃለሁ ታሪክሽን በውል
አልጋሽ መቃብር ነው መተኛሽም ሲኦል
ውዳሴሽ መርገም ነው ፍቅርሽ ነበልባል
ስለዚህ ይቅርብሽ እኔን ማታለል
አታጭም ፈልጊ ሌላ በኔ ፋንታ
በከንቱ ውዳሴ ልቡን የሚፈታ። "
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ቅምሻ 💫

ክፍል ሶስት

............ አዎ ማንም ሰው "አፍሽን ዝጊ!"ብሎ ለጊዜው ዝም ሊያሰኝሽ ይችል ይሆናል-ግን ያሻውን ያህል እየተነሳ ቢፈርጥ የራስሽ የሆነ አመለካከት እንዳይኖርሽ ሊያደርግሽ ጨረሶ አይችልም።...............እና ማንንም ቢሆን ገና ለገና ትንሽ ልጅ ነው ብሎ የመሰለውን ሀሳብ ከመግለፅ ለማገድ መሞከር የስህተቶች ሁሉ ስህተት ይመስለኛል።..............
ገፅ 117
............. አሁን እያሰብኩ ያለሁት አለምን እየወረራት ስላለው ክፉ የጥፋት ደዌ ሳይሆን ደዌው ገና ስላልደረሰበት ውብ ጎኗ ነው።.................. የእኔ ምክር ደግሞ ይህ ነው። "ሂጂ ውጪ! ወደ ሰፋፊዎቹ መስኮች ውጪና በማይጠገበው የተፈጥሮ ውበት፣ እገሌ ከእገሌ ሳይል ለፍጡራን ሁሉ እኩል በሚፈነጥቀው ዕፁብ ድንቅ የፀሐይ ብርሀን ነፍስሽን አስደስች! -ሂጂ ውጪ! ርቆሽ የነበረውን ደስታሽን እንደገና ማግኘት ከፈለግሽ ወደ ሌላ ሳይሆን ወደራስሽ ውስጥና ወደ እግዚአብሔር ተመልከቺ! አዎ-ወደ ውስጥሽ አጮልቂ ወደ እግዚአብሔርም አንጋጪ! ከውስጥሽም ሆነ ከዙሪያሽ ስለራቁት ሳይሆን በውስጥሽም ሆነ በዙሪያሽ ስለቀሩት ውብ ነገሮች አስቢ! ይህን ማድረግ ከቻልሽ ርቆሽ የነበረው ደስታም ዳግም ሊቀርብሽ የግድ ነው!"..................በዚህ ላይ - አንድ የማያነጋግር ሐቅ አለ - ለራሱ ደስተኛ የሆነ ሁሉ ሌሎችንም ደስተኛ ያደርጋል። እንዲሁም ሰብዓዊ ወኔውና መንፈሳዊ የእምነት ጽናቱ ያልራቀው ሁሉ መቼም ቢሆን ምንም ዓይነት ምፅዓት መሀል ከስሞ አይቀርም። ..............
ገፅ 130-131
.............................................................................
~~~~ይቀጥላል~~~~

የአና ማስታወሻ /አዶኒስ እንደተረጎመው/ ከሚለው መፅሐፍ በጥቂቱ ያስተምራል እንዲሁም የፀሐፊዋን ድንቅ ችሎታ ያሳያል ተብሎ የቀረበ። ቆይታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን!!!
#share #participate #comment ማድረግ አይርሱ።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
ውድ የዚቻናል አባላት 6710 ላይ A ብላችሁ በመላክ የልብ ሕክምና ማእከልን በቀላሉ መርዳት ትችላላችሁ። 6710 ላይ A ብለው ከላኩ አንድ ብር ብቻ ከሒሳቦ ላይ ወደ ማእከሉ ገቢ ይሆናል። ላልሰሙት ማካፈልን አትርሱ
እናመሰግናለን!!!!

@Readers_To_Know
💫 ቅምሻ 💫

ክፍል አራት
.............በስጋ ከሞትኩ በኋላ እንኳን በመንፈስ መኖር እፈልጋለሁ -ስሜ አብሮኝ እንዲቀበር አልፈልግም! ስለዚህም ለዚህ ተሰጥኦ ያደለኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ራሴን በራሴ ማሳደግ እንድችል - ስለማንኛውም ነገር ጥሩ አድርጌ መፃፍ እንድችል - በውስጤ ያለውን ሁሉ ያለ ምንም ችግር መግለፅ እንድችል አድርጎ የፈጠረኝ አምላኬን ከልብ አመሰግነዋለሁ። ............
ገፅ 199
.............ለምንድነው በአንድ በኩል ይበልጥ የማውደም አቅማቸው በየእለቱ እየተራቀቀ የሚሄድ የጦር አውሮፕላኖች እና ቦንቦች ያለ ማቋረጥ በገፍ የሚመረቱትና በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ የወደሙ ከተሞችን በአስቸኳይ መልሶ ለመገንባት የሚያስችሉ ተገጣጣሚ የሕንፃ አካላት ጎን ለጎን የሚመረቱት? መጀመሪያ ማውደም መልሶ ደግሞ መገንባት ምን የሚሉት ጨዋታ ነው? " ..............
ገፅ 238
..............ሕይወትን ሁላችንም እንኖራታለን። ግን ለምን እንዴትና የት እንደምንኖራት አናውቅም። ሁላችንም የምንኖረው ከዛሬ ነገ አንድ ቀን ደስተኛ እንሆን ይሆናል በሚል ተስፋ ነው- ይህም ነው የሁላችንንም ሕይወት የተለያየ የመሆኑን ያህል ተመሳሳይ የሚያደርገው።........ስንፍና፣ ግድየለሽነት፣ በዋልፈሰስነት፣ ጨዋታ ወዘተ ...ላይ ላዩን ሲታዩ ይስቡሻል ያምሩሻል- ሥራ ግን የማታ ማታ ይከፍልሻል- እርካታና ደስታንም ይሰጥሻል። ሥራ የማይወዱ ሰዎች ጨርሶ አይገቡኝም!.....................
ገፅ 239-240
.....................................................................
~~~~ይቀጥላል ~~~~
የአና ማስታወሻ /አዶኒስ እንደተረጎመው/ ከሚለው መፅሐፍ በጥቂቱ ያስተምራል እንዲሁም የፀሐፊዋን ድንቅ ችሎታ ያሳያል ተብሎ የቀረበ። ቆይታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን!!!
#share #participate #comment ማድረግ አይርሱ። እናመሰግናለን!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
​​💫 ቅምሻ 💫

ክፍል አምስት
..............ሀይማኖት ያላቸው ሰዎች በእርግጥም ደስ ሊላቸው ይገባል። ምክንያቱም ከምድራዊው በላይ ባሉት ሰማያዊ ነገሮች ማመን መቻል የሁሉም ሰው ተሰጥኦ አይደለም። ለዚህም መታደል ያስፈልጋል። ሌላውን ተይውና ከሞት በኋላ አለ የሚባለውን ፍርድና ቅጣት እንኳን እኮ የግድ ልትፈሪው አይገባሽም።እነኚህ ጽድቅና ኩነኔ፣ ገነትና ገሀነም፣ ምናምን ምናምን የሚባሉ ነገሮች ሁሉ ለብዙ ሰዎች በቀላሉ የማይዋጡ እና የማይመስሉ ናቸው። ያም ሆኖ ሀይማኖት ግን ዓይነቱ ምንም ይሁን ምን - አንድን ሰው በቀጥተኛው መንገድ እንዲጓዝ የሚረዳና ውስጣዊ ሰላምን የሚሰጥ በጣም ጥሩ ነገር ነው። ለእኔ እንደሚታየኝ ዋናው ነገር በጥሬው ሲባል እንደምሰማው "እግዚአብሔርን መፍራት" አይደለም ዋናው ነገር ሰው የመሆንን ታላቅ ክብርና ንፁህ ሕሊናን ጠብቆ መቆየት መቻል ነው። እያንዳንዱ ሰው በእያንዳንዱ ምሽት መኝታው ላይ ጋደም እንዳለ ወደ እንቅልፉ ዓለም ከመግባቱ በፊት ቀኑን ሙሉ ስላሳለፋቸው ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ እያስታወሰ የትኞቹ ጥሩዎች የትኞቹ ደግሞ መጥፎዎች እንደሆኑ መመዘን ቢችል ዋነኛ ጨዋና ጥሩ ሰው መሆን በቻለ ነበር።አዎ ያን ጊዜ ሳታውቂው በእያንዳንዱ አዲስ ቀን መጀመሪያ ላይ ራስሽን የምታስተካክይበትንና የምታሻሽይበት መንገድ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ትጀምሪያለሽ - ያለጥርጥርም በጊዜ ሂደት ማመን የሚያዳግት ያህል ብቃትን ለመጎናፀፍ ትችያለሽ። ማንም ሰው ይህን ማድረግ ይችላል-ምንም ወጪ የሚያስወጣ ነገር አይደለም - ግን ለሕይወት ምን ያህል እንደሚረዳ በቃላት መግለፅ አይቻልም። ...................
ገፅ 240
..............ያም ሆኖ አሁንም እንደያዝኳቸው ነው ያለሁት፤ እንደያዝኳቸው እንደምቆይም እርግጠኛ ነኝ። ምክንያቱም የሆነው ሁሉ እንዳለ ሆኖ አሁንም ቢሆን ሰዎች ከሥረ መሠረታቸው ጥሩዎች ናቸው ብዬ አምናለሁ።...................
ገፅ 251-252///(264)
.......................................................................
~~~~አና እናመሰግናለን!~~~~

የአና ማስታወሻ /አዶኒስ እንደተረጎመው/ ከሚለው መፅሐፍ በጥቂቱ ያስተምራል እንዲሁም የፀሐፊዋን ድንቅ ችሎታ ያሳያል ተብሎ የቀረበ። ከእኛጋር ስለነበራቹ እናመሰግናለን፤ ያመለጧቹን ክፍሎች ወደላይ በመሔድ መመልከት ትችላላችሁ።
#share #participate #comment ማድረግ አይርሱ። እናመሰግናለን!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​💫 ከታሪክ ማህደር 💫
...................................................
አና ትባላለች - ሙሉ ስሟ አና ፍራንክ። አሁን በሕይወት የለችም። በዚች ዓለም ላይ በሥጋ የኖረችው ለ15 ዓመታት ከዘጠኝ ወራት ብቻ ነው። በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1929 እስከ 1945 ዓ.ም። በመንፈስ ግን አሁንም አለች፣ ወደፊትም ትኖራለች።
1943 ዓ.ም ላይ የናዚ ወታደሮች አምስተርዳም ውስጥ አገር ሰላም ብለው ይኖሩ የነበሩ አይሁዶችን ከየቤታቸው እየለቀሙ ወደ ኦሽዊትና ወደሌሎች የግድያ ጣቢያዎች ማጋዝ ሲጀምሩ የአና ፍራንክ ቤተሰቦች ከግድያው ለማምለጥ ቀደም ብለው አዘጋጅተው ወደነበረው አንድ ሚስጥራዊ የመደበቂያ ሥፍራ ያመራሉ። ይህ ምስጢራዊ ቦታ የአና አባት አቶ ፍራንክ የአስመጪና ላኪነት ቢዝነሱን ያካሒድበት በነበረ ሕንፃ ጣሪያ ላይ ይገኛል። የአና ቤተሰቦች በቁጥር አራት ነበሩ፤ ማለትም ራሷ አና ፍራንክ፣ አባቷ አቶ ፍራንክ፣ እናቷ ኤዲት ፍራንክ እና ታላቅ እህቷ ማርጎት ፍራንክ።
አና ፍራንክ የምትታወቀው በፃፈችው ግለ-ታሪክ ሲሆን በዚሁ መጽሐፍ እንደገለፀችው " የሔዋን ሕልም " እና " የኬዲ ሕይወት "የተሰኙ ልቦለዶችን ፅፋ ጨርሳ ነበር። በግለ ታሪኳም የአፃፃፍ ብቃቷን አሳይታለች፤ በዚህም የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ሰው የሚለውን ማዕረግ ለመስጠት ከቀረቡ እጮዎች ውስጥ አንዷ ነበረች። እነዚህም አልበርት አነስታይን፣ ሲግመንድ ፍሮይድ፣ ቻርለስ ዳርዊን፣ ሉዊ ፓስተር እና አና ፍራንክ።
እናንተም ይህን መፅሐፍ እንድታነቡት እንጋብዛለን። በአምስቱ ምዕራፍ እንደቅምሻ ያየናቸው እንዳስተማሩዋቹም ተስፋ እናረጋለን። ለጓደኞቻችሁ ማካፈልን አትርሱ ብቻችንን መብላት ባህላችን አደለምና!!!
......................................................................
~~~እናመሰግናለን~~~

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
💫 ከዚም ከዛም 💫

1. የአንድ መሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት ሀይሉ 175 k.m ወይም ከአ.አ እስከ አሰላ ያለውን ርቀት ይሸፍናል።

2. በቻይና ቲቤት ግዛት ውስጥ ምላስን ጎልጉሎ የማውጣት ሒደት ከጨዋ ቤተሰብ እንደተወለድን ያሳያል አሉ።😜

3. በአውስትራሊያ ክንፍ ያላቸው ቀበሮዎች ይገኛሉ። የእነዚህ ቀበሮዎች ስጋ ለጀርባ አጥንትና ለመገጣጠሚያ ህመሞች ፈውስ ይሆናል።

4. ዶሮ እንቁላል ስትጥል በ10ኛው ቀን የምትጥለው እንቁላል ከሌሎቹ በመጠን ያደገ ነው።
#share
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
💫💫💫💫💫💫💫💫
​​ለመላው የእስልምን እምነት ተከታዮች መልካም በዓል ይሁንላችሁ!
ኢድሙባረክ!
🌓 ከግጥም ማህደር 🌗

ፉከራ
""""'''""
ፈሪ ጨነቀው ተርበደበደ
ጥይት ዘነመ እሳት ወረደ
ውረድ እንውረድ ተባባሉና
አስደበደቡት አፋፍ ቆሙና።
የፈሪ እናት ታስታውቃለች
አፋፍ ላይ ሆና ተው ሽሽ ትላለች
የጎበዝ እናት ታስታውቃለች
እመሀል ገብታ በለው ትላለች።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
🌘🌓🌔🌓🌑🌕🌖🌗
💫 ከግጥም መሀደር 💫

የወንድሙን ደም ላልመለሰ ሰው

የዕገሊት ወዳጅ ጭራሽም ልብ የለው
የወንድሙ ሬሳ ወድቆ የከረመው
ልብማ ቢኖረው ደሙን ይመልሳል
በግንባሩ ደፍቶ አንጀቱን ያርሳል።
ጠመንጃ መተኮስ እሱም ያውቅበታል
ወሬ አይደበቅም ደመኛም አውቆታል
በሩ ላይ ተጋድሞ ያላግጥበታል።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
🌕🌖🌗🌘🌑🌒🌓🌔
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💫 ከዚም ከዛም 💫

1. በአለም ውስጥ በስልክ ደውለው የማያውቁና ተደውሎላቸውም የማያውቁ ሠዎች በ2012 50% ብቻ ይሆኑ ነበር።

2. ህፃናት ወይም የአንድ አራት አመት ልጅ በቀን 400 ጊዜ ወላጆቹን ይጠይቃል ተብሎ ይገመታል።

3. ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።

4. የሰው ልጅ የድመትን 1/6(አንድ ስድስተኛ) ያያል።

5. የአሳ ነባሪ ጭራ ላይ ያለው መዋኛ የአንድ መለስተኛ አውሮኘላን ክንፎችን ያክላል።

👇👇👇👇👇👇👇👇
@Readers_To_Know
🌕🌓🌖🌒🌗🌓🌖🌑
​​👳‍♂ ለፈገግታ 👳‍♂
አንድ የውጭ ዜጋ በሚኖርበት ሀገር አንድ ኢትዮጵያዊ ሊቅ አገኘ አሉ። ኢትዮጵያ ለጉብኝት ሔዶ የግዕዝ ዜማዎችን ከመውደዱ የተነሳ በመቅረፀ ድምፁ እንደቀዳ ነግሮ ላሰማዎት አላቸው። ለካስ ይህ ሰው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግዕዝ ያውቅ መስሎታል አንዱን ጩልሌ ጠይቆት ኖሯል። ታድያ የተቀዳው ሲሰማ "ችቦ አይሞላም ወገቧ ችቦ አይሞላም ወገቧ ማር እሸት ነው ቀለቧ" የሚል ሙዚቃ ሆኖ ያገኙታል። የለም አታሎሀል- እንዳይሉት ኢትዮጵያውያን ያታልላሉ ሊል ነው። ዝም እንዳይሉት ልክ አይደለም።
" ይሀውልክ የኔ ልጅ ይህ የድሮ ነው አሁን አንጠቀምበትም፤ ይህን አጥፋና አዲሱን ልበልልህ።" ብለው አስቀየሩት አሉ።
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
#share #participate #comment

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🔥 ቅምሻ 🔥 ከእናንተው

#በዓለ_ደብረ_ታቦር_እና_ቡሄ
ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን በሰላም አደረሰን!

ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ‹ቡሄ› በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ‹መላጣ፣ ገላጣ› ማለት ነው፡፡ በአገራችን ክረምቱ፣ ጭጋጉ፣ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለ ኾነ በዓሉ ‹ቡሄ› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓለ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት፤ ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበ  ዕለት ስለ ኾነ ‹የብርሃን› ወይም ‹የቡሄ› በዓል ይባላል፡፡

ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፤ ወደ መፀው የሚገባበት፤ ወገግታ የሚታይበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚሸጋገርበት ወቅት በመኾኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንዲሉ፡፡ በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የቡሄ ዕለት ማታ ምእመናን ችቦ ያበራሉ፡፡ ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው፡፡ ሕፃናቱ ይህ በዓል ከመድረሱ በፊት ቀደም ብለው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮኹ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለዚህ በዓል የሚኾን ዳቦ ለመጋገር ስንዴያቸውን ሲያጥቡ፣ ሲፈትጉ ይሰነብታሉ፡፡ በበዓሉ ዋዜማ (ነሐሴ ፲፪ ቀን) ሕፃናት በየቤቱ እየዞሩ ‹‹ቡሄ ና በሉ፤ ቡሄ በሉ፡፡ ቡሄ መጣ፤ ያ መላጣ፤ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ …›› እያሉ ይጫወታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሡ ይሰጧቸዋል፡፡ ሕፃናቱ ‹ቡሄ› የሚሉትም ዳቦውን ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት እረኞች ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል፡፡ ‹ቡሄ› ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና በበዓሉ ችቦ የሚበራውም ከዚህ ታሪክ በመነሣት ነው፡፡ ለክርስትና ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ ለዘመድ አዝማድ ዅሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል፡፡ ልጆችም ዳቧቸውን እየገመጡ ጅራፍ ሲገርፉ ይውላሉ፡፡ የጅራፉ መጮኽ የድምፀ መለኮት ምሳሌ ሲኾን፣ ጅራፉ ሲጮኽ ማስደንገጡም ነቢያትና ሐዋርያት በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡

መምህረ ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ በደብረ ታቦር ምሥጢር መግለጡን በማስታዎስ የአብነት ተማሪዎች ከመምህራቸው ጋር በመኾን በዓለ ደብረ ታቦርን (ቡሄን) ያከብራሉ፤ ስሙን ይጠራሉ፡፡ የአብነት ተማሪዎች ‹‹ስለ ደብረ ታቦር›› እያሉ እኽል ከምእመናን በመለመንና ገንዘብ በማዋጣት ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምእመናን በመጋበዝና እርስበርስ በመገባበዝ፣ እንደዚሁም ቅኔ በማበርከት በዓለ ደብረ ታቦርን በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህም እስከ አሁን ድረስ በአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሠራበት ነባር ትውፊት ነው፡፡

ነገር ግን በአንድ አካባቢዎች በተለይ በከተማ ዙሪያ በዓለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) ሃይማኖታዊ ትውፊቱን የለቀቀ ይመስላል፡፡ ለዚህም ልጆች የሚጫወቱበት መዝሙር ግጥሙና ዜማው ዓለማዊ መልእክት የሚበዛበት መኾኑ፤ በወቅቱ ችቦ ከማብራት ይልቅ ርችት መተኮሱና በየመጠጥ ቤቱ እየሰከሩ መጮኹ፤ ወዘተ. የበዓሉን መንፈሳዊ ትውፊት ከሚያደበዝዙ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም በዚህ በዓል ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ የሚሽቀዳደሙ ነገር ግን የበዓሉን ታሪካዊ አመጣጥ የማያዉቁ ልጆችም ጥቂቶች አይደሉም፡፡

ስለዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው የበዓለ ደብረ ታቦርን መንፈሳዊነት፣ የመዝሙሮቹን ያሬዳዊነትና አከባበሩን ከቤተ ክርስቲያን መምህራን በመጠየቅ ማስተማር፤ ልጆችም ከወላጆች ወይም ከመምህራን በመጠየቅ የበዓሉን አከባበር መረዳትና የዚህን በዓል መንፈሳዊ ትውፊት ሳይበረዝ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባቸዋል፡፡ ‹‹ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና፤ የቡሄው ብርሃን ለእኛ በራልን …›› የሚለውንና ይህን የሚመስሉ መንፈሳውያን መዝሙራትን እየዘመሩ በየቤቱ በመዘዋወር የሚያገኙትን ዳቦና ገንዘብ ለነዳያንና ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ ልጆችንም ማበረታታትና አርአያነታቸውን መከተል ይኖርብናል፡፡

ምንጭ፡-

መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ መ/ር አፈወርቅ ተክሌ፤ ፳፻፭ ዓ.ም፣ ገጽ ፫፻፲፭-፫፻፲፯፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ፤ ፳፻፯ ዓ.ም፣ ገጽ ፻፲፩፡፡

መልካም በዓል ይኹንልን!
ማካፈልን እንዳይረሱ!

ለአስተያየት :-
@R_e_a_d_e_rs

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
🦅💫 ከግጥም ማህደር 💫🦅

ጠጅም አላገኘን ከተለየናቸው፤
አውራው ከተያዘ ማሩን እባካችሁ።
ለሚኒልክ ተዝካር እንዲቆይላት፤
እባክህ ማር ብላ ለመነች ንግሥት።
ንቡ እንዲበታተን አውራውን ይዛችሁ፤
ኮዳውን ተውሀ ማሩን እባካችሁ።
ወይ ለኛ አትሆነን ወይም ለራስህ፤
ልትፈጀን ነው ወይ ጤና አሳጥተህ?
ድንገት ሳላስበው በልቼ ጠጥቼ፤
ልሞትላችሁ ነው ተፍቼ ተፍቼ።
የበላሁት ጮማ ሆዴን አመመው፤
የጠጣሁትም ጠጅ ሆዴን አመመው፤
እንደምን አድርጌ ተፍቼ ላውጣው!!
ቢጠሉት ይሆናል ወይም ቢወዱት፤
ካልጋ ሥር አግብተው የሚጠብቁት።
እሱ ደልቶት ኖረ ብለው እንዳይወቅሱ፤
ካልጋ ሥር ይሻላል ብሎ ተኛ እያሱ።
/ከነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ቅኔዎች በጥቂቱ
#share #comment #participate

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌓 ቅምሻ 🌗

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተቃዋሚያቸው በአምባሳደር
ብርሃኑ ድንቄ ዓይን፣
Sisay Tefera Mekonnen
.
በግል ጥላቻ ሳንታወር ያለ አንዳች አድልዎ አጼ ኃይለ
ሥላሴን ለማስታወስ ጊዜ ካገኘን፣ አጼውን ብዙ ገጽ
ያላቸው አስደናቂ ሰው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
ኮንሰርቫቲቭ ናቸው ስንል ሊበራል የሆኑ ስራዎችን
ሲሰሩ እናገኛቸዋለን፣ ንቅዝ ናቸው ስንል ፍትህ ሲሰጡ
እናያቸዋለን፣ ጨካኝ ናቸው ስንል የርህራሄ ስራ
ከመስራት አያቋርጡም፣ በቀለኛ ናቸው ስንል ምህረት
ሲያደርጉ እናገኛቸዋለን፡፡ ይህ ፓራዶክስ ሊታመን
የማይችል ግን እውነተኛ ነገር ነው፡፡
.
አጼ ኃይለ ሥላሴ በሚያስደንቅ ሁኔታ የውስጡንና
የውጭውን ፖለቲካ እንደ ፉትቦል ተጫውተውታል፡፡
በውስጥና በውጭ የፖለቲካ ጨዋታ ኃይለ ሥላሴን
ያሸነፉ ተቃዋሚ ቡድኖች እነማናቸው ብሎ
የሚጠይቀኝ ቢኖር፣ እርጅና እና ከሳቸው እድሜ በኋላ
ወደፊት በአገሪቱ የሚሆነውን አርቆ የማስተዋል
ጉድለት ብዬ እመልስለታለሁ፡፡ በዘመናዊው አለም
ከ120-135 አመት እድሜ ያላቸው ሰዎች በህይወት
እንደሚኖሩ አልፎ አልፎ ብሰማም፣ እንደ ኃይለ ሥላሴ
ግን በ80 አመት አድሜው የንጉሠ ነገሥትነት ፍጹም
ስልጣን ይዞ በቀጥታ እያዘዘ የሚገዛ ንጉሥ ስለመኖሩ
አላውቅም፡፡
.
ኃይለ ሥላሴ በመጨረሻ ይታገሉ የነበሩት ከተፈጥሮ
ህግ ጋር ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ኃይለ ሥላሴ
ያለአንዳች ድካም በቀን 20 ሰአት የሰሩበት ጊዜ
ነበር፣ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመከታተልም በፍጹም
አይሰለቹም ነበር፡፡ እርጅና ከተጫናቸው በኋላ ግን
መርሳት፣ ማመንታት፣ መወላወል ጀመሩ፡፡
የመንግሥታቸው አባላትም በእግራቸው መቆም
የማይችሉ ንቅዞች ነበሩ፡፡ ኃይለ ሥላሴ እራሳቸውን
ከዙፋናቸው ገለበጡ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡
.
ኃይለ ሥላሴ ከዙፋናቸው እንደወረዱ የወታደራዊው
መንግሥት አለቃ ሆኖ የተሾመው ጄነራል አማን
አንዶም ‘Our Revolution’ እያለ ሲናገር በአሜሪካን
ቴሌቪዥን ሰምቼው ተገርሜያለሁ፡፡ ጄኔራል አማንን
በቅርብ አውቀዋለሁ፣ በዋሽንግተን የሚሊቴሪ አታሼ
ሆኖ ከኔ ጋር አንድ አመት ሰርቷል፡፡ ጤንነቱ ታውኮ
የህክምና ገንዘብ ሲቸግረው ለጃንሆይ አመልክቼለት
ሁለት ጊዜ በእርዳታ ገንዘብ ልከውለታል፣ እሱም
ምስጋና አቅርቧል፡፡
..
በኢትዮጵያ ያለው አስተዳደር እንዲሻሻል የሚጠይቅ
ግልጽ ደብዳቤ ለንጉሡ በጻፍኩ ጊዜም ጉዳዩን
ለጄኔራል አማን አስቀድሜ አማክሬው ነበር፡፡ የሰጠኝ
መልስ በዛሬው ጊዜ ለኢትዮጵያ ከኃይለ ሥላሴ
የሚሻል መሪ ማግኘት አይቻልም፣ ህዝቡ ወራዳ ነው፣
ብዙ ሊሻሻሉ የሚገቡ ነገሮች ቢኖሩም ሁከት
እንዳይነሳ መጠንቀቅ ያስፈልጋል የሚል ነበር፡፡
.
የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት በመቃወም በአሜሪካ
ያለውን የኢትዮጵያ ኤምባሴ ለቅቄ እንደወጣሁም፣
ጄኔራል አማን እኔን በመውቀስና ንጉሡን በማወደስ
ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ከ9 አመት በኋላ ንጉሡ አርጅተው መንግሰታቸውን
መምራት አቅቷቸው ከስልጣን ሲወድቁ ግን ጄኔራል
አማን ‘Our Revolution’ እያለ መናገር ጀመረ…
.
አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ፣ ቄሳርና አብዮት

#share #comment #participate
@Let_us_read_bot

📗📒📕📘📗📒📕👇
@Readers_To_Know
📚📚📚📚📚📚📚📚