🧞♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞♂
እራሴን እንዴት ልውደድ?
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ሴቶች በወንድ አንቀፅ የተፃፈውን በሴት አንቀፅ ለውጣችሁ አንብቡት !
💡🥀1. ሁልጊዜም ከእንቅልፍህ ስትነሳ መልካም ነገሮችን ስለራስህ አስብ። ተፈጥሮህን አድንቅ እራስህን በመስታወት እያየህ ስለተሰጠህ ነገር ሁሌም አመስግን። በህይወትህ ያለህን ችግር ሳይሆን የተቸረህን ነገር አንድ ሁለት እያልክ ቁጠራቸው። ያለፈውን ነገር እረስተህ ስለሚመጣው ብሩህ ነገር አስብ።
💡🥀2. እራስህን ከሌሎች ሰዎች ስኬት ጋር አታወዳድር። አንተ የራስህ የሆነ የህይወት መንገድ አለህ ሌላውም እንደዛው።
💡🥀3. ከዚህ በፊት ያላረካቸውን መንፈስህን የሚያድሱ ነገሮችን አድርግ። የእግር ጉዞ አድርግ፣ ለራስህ ስጦታ ግዛ፣ የምትኖርበትን አካባቢ ቃኘው፣ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ተሳተፍ በዛውም ሰዎችን እንዴት መርዳት እንዳለብህ ትማራለህ፣ ተፈጥሮን አድንቅ ጉዞዎችን አድርግ እነዚህ ቦታዎች ስትሔድም በፎቶ ምስል አስቀራቸው፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን ለመለማመድ ሞክር፣ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ለመለማመድና ለመማር ሞክር፣ ሙዜሞችን ጎብኝ የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን አድንቅ፣ ከዚህ በፊት ያላነበብካቸውን መፃህፍት አንብብ፣ መንፈስህን የሚያድሱ ሙዚቃዎችንም አድምጥ ወዘተ....።
💡🥀4. ሁሉንም ሰው ማስደሰት እንደማትችል መቀበል አለብህ። ሁልጊዜም የሚፈርዱብህ ስላንተ ጥሩ ስሜት የማይሰማቸው እንዲሁም ያለፍክበትን መንገድ እንኳን ያላወቁ ሰዎች ያጋጥሙሃልና።
💡🥀5. ለቤተሰቦችህና ለጓደኞችህ ጊዜ ስጥ። ሁልጊዜም አብረውህ የሚዘልቁት እነሱ ናቸውና። አጠገብህ ስላሉ ደስተኛ ሁን እንደምትወዳቸውም ንገራቸው።
@Readers_To_Know
💡🥀6. ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ዘወትር አድርግ። ይሄም ጭንቀትን ለመከላከል ይረዳሀል።
💡🥀7. በዚህ አለም ማንም ፍፁም የለምና ጉድለትህን ውደደው። ሁላችንም በፈጣሪያችን የተፈጠርን ውብ ፍጥረቶች ነን። ሁሉም ሰው ያጠፋልና ላጠፋሀቸው ጥፋቶችም ለራስህ ይቅርታን አትንፈገው።
@Readers_To_Know
💡🥀8. የአኗኗር ዘይቤህን ቀይር። አለባበስህን አስተካክል፣ የራስህ የሆነ ስታይል ይኑርህ፣ ፀጉርህን ተቆረጥ ተንከባከብ እራስህን አትጣል ፅዳትህን ጠብቅ፤ የምትኖርበትን ቦታ ፅዳት ጠብቅ እራስህን ለማነቃቃት አስፈላጊ ነው። ወጣ ብለህ ብዙ ሰዎችን የምትተዋወቅበትን መንገድ ፍጠር፤ ከነሱጋም ደስ የሚል ጊዜ አሳልፍ። ብዙ ከማውራት ብዙ ማዳመጥ ይበልጣልና አዳማጭ ሁን።
💡🥀9. ደስተኛ ለመሆን ሁሌም ሳቅ ከፊትህ ገጽታ አይለይ ሌሎች ሰዎችንም ደስተኛ ታደርጋቸዋለህ።
💡🥀10. ስላንተ ጥሩ ስሜት የማይሰማቸውንና ሁልጊዜም የሚያጣጥሉህን ላንተ ደንታ የሌላቸውን ሰዎች ከህይወትህ አስወጣ። ባንፃሩ ላንተ ጥሩ ስሜት ካላቸው ጋር አዘውትር።
@Readers_To_Know
💡🥀11. ብቻህን የተወሰነ ጊዜ አሳልፍ። ብቻ መሆን ያን ያህል ችግር እንደሌለው ተረድተህ አንዳንድ ቦታዎች ላይ እራስህን እንደ ግል ጓደኛ አድርገህ ብቻህን መንቀሳቀስን አዳብር።
💡🥀12. ለሌሎች ሰዎች ስሜት መጠንቀቅና መንከባከብ ጥሩ ስሜትን ይሰጥሀልና አዳብረው። ሰዎች ላይ አትፍረድ በተቻለህ መጠን ሰዎችን ላለማስቀየም መጣር እንዳለብህ አትርሳ። ለሌሎች መልካም ነገርን አድርግ መልካምነትህን አይተው እንዲጎዱህ ግን አትፍቀድላቸው። እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እርዳታህን አትንፈጋቸው መልሰው እንዲያደርጉልህ ግን ምላሽ ከማንም አትጠብቅ።
💡🥀13. ልብህን ጠብቀው።
💡🥀14. ስልክህ ላይ የምታጠፋውን ጊዜ ቀንስ። የስልክ አጠቃቀምክን አስተካክል።
@Readers_To_Know
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
" እራሱን የሚወድ ለሌላው ይተርፋል "
"We Have Two Lives, And The Second Begins When We Realize We Only Have One."
🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃
❣ እናመሠግናለን ❣
@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°
✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀

🦋"መቼ እና የት መለያየታችን ስለማናቅ ደና እደሩ እንኳን ስንባባል ነገ መልሰን ያንን ሰው ላናይም እንደምንችል እያሰብን ፍቅር፣ ይቅርታ ሁልጊዜ ከኛ ጋር ይሁን!!!"🦋
@Readers_To_Know
@Readers_To_Know
😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣
ልጆች ለእግዚአብሔር ከጻፏቸው ደብዳቤዎች
°°°°°°°°°°°×××××××××××°°°°°°°°°°°°
የተወደድከው እግዚአብሔር ሆይ!! ጉንጭህን ስሞ በሰላሳ ብር አሳልፎ የሸጠህ ይሁዳ ምን አይነት ደደብ ሰው ቢሆን ነው? እንኳን አንተ የኛ ጌታ አይደለህም፤ እኛ ቤት ያለችው ሰራተኛችን እንኳን በወር ደሞዟ ሰማንያ ብር ነው።
የተወደድከው እግዚአብሔር ስሜ ጨቡዴ ነው፡ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ በስሜ ሁልጊዜ ያሾፉብኛል። ስለዚህ እኔ ስምን መልአክ ነው የሚያወጣው ሲባል ስለሰማሁ የኔን ስም ያወጣውን መልአክ አደራ ቅጣልኝ። ጨቡዴ ነኝ
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አባዬ ሁልጊዜ አሞኛል እያለ አልጋው ላይ ተኝቶ ያቃስታል፤ ታድያ አንዳንዴ ወደ ውጭ ወጣ ሲል መንገድ ላይ ያገኙት ጓደኞቹ "ደህና ነህ ወይ? " ብለው ሲጠይቁት ግን "እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ " ይላል አይገርምህም? እነሱንስ እሺ ይሸውድ! አንተን ግን እንዴት ይዋሽሀል?
ምንጭ፦ እስኪ ዛሬ እንኳን እንሳቅ በቅዱስ-ሀብት በላቸው
❣ እናመሠግናለን ❣
@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°
✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
ልጆች ለእግዚአብሔር ከጻፏቸው ደብዳቤዎች
°°°°°°°°°°°×××××××××××°°°°°°°°°°°°
የተወደድከው እግዚአብሔር ሆይ!! ጉንጭህን ስሞ በሰላሳ ብር አሳልፎ የሸጠህ ይሁዳ ምን አይነት ደደብ ሰው ቢሆን ነው? እንኳን አንተ የኛ ጌታ አይደለህም፤ እኛ ቤት ያለችው ሰራተኛችን እንኳን በወር ደሞዟ ሰማንያ ብር ነው።
የተወደድከው እግዚአብሔር ስሜ ጨቡዴ ነው፡ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ በስሜ ሁልጊዜ ያሾፉብኛል። ስለዚህ እኔ ስምን መልአክ ነው የሚያወጣው ሲባል ስለሰማሁ የኔን ስም ያወጣውን መልአክ አደራ ቅጣልኝ። ጨቡዴ ነኝ
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አባዬ ሁልጊዜ አሞኛል እያለ አልጋው ላይ ተኝቶ ያቃስታል፤ ታድያ አንዳንዴ ወደ ውጭ ወጣ ሲል መንገድ ላይ ያገኙት ጓደኞቹ "ደህና ነህ ወይ? " ብለው ሲጠይቁት ግን "እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ " ይላል አይገርምህም? እነሱንስ እሺ ይሸውድ! አንተን ግን እንዴት ይዋሽሀል?
ምንጭ፦ እስኪ ዛሬ እንኳን እንሳቅ በቅዱስ-ሀብት በላቸው
❣ እናመሠግናለን ❣
@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°
✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🧞♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞♂
🦈. ሻርክ ከ 1k.m ላይ የፈሰሰን ደም ማሽተት ይችላል።🐳 አንድ ሻርክ ትልቅ ለመባል ከ20-25 አመት ይፈጅበታል። ይህም የሚያሳየን ዘገምተኛ የእድገት ደረጃ እንዳለው ነው። ሻርክ 856 ጥርስ ሲኖረው አንዱ ከተሰበረ በሌላ ይተካል፤ እንዲሁም የ10 አመት ሻርክ 2400 ጥርሶችን ነቅሎ ይተካል። ሻርክ በሁለት መንገዶች ይራባል። በውልደትና በእንቁላል🥚መራባት ይችላል።
👼. በአለም በ1 ሰከንድ 4 ልጆች ይወለዳሉ ተብሎ ይገመታል።
🏅. በአፍሪካ ውስጥ የመጀመሪያው የኖቤል ፕራይዝ ተሸላሚ አልበርት ሉቱሊ ይባላል።
💆♂💆♀. አባባል:- ትንሽ ቆሎ ይዘህ ካሻሮ ተጠጋ።

🦅🖊 ስነግጥም 🖌🦅
_________
የሕፃኗ ብሶት😢😥
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በጣም የምቀርበው በጣም የምወደው፤
ከጎረቤት አለ ሁሌም 'ማልለየው።
ሕፃን ስለሆንኩኝ ጣፋጭ እወዳለሁ፤
ሁሌም ጎረቤቴን አስቸግረዋለሁ።
እሱም እየሳቀ ብስኩት ከረሜላ፤
ጣፋጭ ነገሮችን ሰቶኝ እንድበላ።
"ነይ ግቢ" አለኝ ገርበብ አረገና፤
"እሺ" አልኩኝ እኔም ደስ አለኝና።
ከረሜላዬንም ቆረጣጠምኩና፤
መጫወት ጀመርኩኝ በንፁሕ ልቦና።
"ነይ እስኪ ሚጢዬ" ደግሞ ለስለስ ብሎ፤
ወደ መኝታ ቤት ይዞኝ ዘው ብሎ።
ካ'ልጋው ተቀምጦ ትንሽ አወጋና፤
ፈገግ ብሎ አየኝ ምኑ ገባኝና።
አልጋው ላይ ወጣና "ነይ እስኪ እንተኛ" ፤
ምኑ ባለጌ ነው አልኩኝ ነውረኛ።
ተረት ላውራሽ አይዞሽ አትፍሪ እያለ፤
እየጎተተ አስጠጋኝ እያታለለ።
ስላላማረኝ ኮስተርተር አልኩኝ፤
ከ'ጁ ልወጣ ብዙ ታገልኩኝ።
በየትኛው አቅሜ ልርታው ተፋልሜ፤
ጭምድምድ ሲያረገኝ ወደኩኝ ታምሜ።
ያ! የሚያስቀኝ ልጅ ደጉ ጎረቤቴ፤
ለካስ ጨካኝ ነው አልኩኝ ከአንጀቴ።
አበባዬ ረግፎ ቅስሜ ተሰባብሮ፤
ለእማዬ ነገርኳት የሆዴንን እሮሮ።
ኋላ የጠበቀኝ ዱላና ቁጣነው፤
እኔ ምን አውቃለሁ ያጠፋው እሱ ነው።
ወላጆች አድምጡን ጆሮአችሁን ስጡን፤
እናንተ ጠብቁን በግልጽ አወያዩን።
ፍርድ ቤትም ይከላከለን፤
ዋስ እየሰጠ አያስጠቃን።
እግዜር በጥበቡ ይጠብቀን እንጂ፤
እኛ ሕፃናት ነን በቶሎ ተጎጂ።
ምንጭ፦ ከየ ሕፃናት ድምፅ ቅፅ 7 ቁጥር 2 የተወሰደ ሕዳር-29-2003

🧠. የአልበርት አንስታይን ጭንቅላት ህዋስ ለእያንዳንዳችን ይድረስ ከተባለ 107 አንድ ሰው ይደርሰዋል አሉ። እና እኛ ምን አገባን 😂😂😂
🐈. ድመቶች ለ16 ሠዓታት ይተኛሉ።
🧠. ምነው ዛሬ አንጎል አንጎል አላቹ አትበሉንና የአንጎል ህዋሳት አንዱ ጥምረት ብቻ ቢዘረጋ 1,000 k.m ይሆናል።
🕯. አባባል:- የደንቆሮ ድንቁርና ብልህ ለመሆን ሲሞክር ይገለፃል።
🤷♂🤷♀. የሰው ሁለቱ የፊቶቹ ጎኖች አይመሳሰሉም። አይኖቹም👀 በፍፁም አይመሳሰሉም። አስገራሚው ነገር ደግሞ የቀኝ ጆሮዋችን👂 ከግራ ጆሮዋችን ወደላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ካነበብነው📖📜📰🗞 via @like
🎥📻 ከታሪክ_ማህደር 🎙🎞
በመጀመሪያ ከሰብታህ ጀምሮ እስከ ጲኦሪ አንደኛ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ፳፭፻፵፭(2545) እስከ ፲፱፻፹፭(1985) ዓመት ከነገደ ካም በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፳፪(22) ናቸው፤ ዘመኑም ፭፻፷(560) ይሆናል። ከክርስቶስ ልደት በፊት ነገደ ዮቅጣን መንገሥ ከጀመሩበት ፲፱፻፹፭(1985) ዓመት ጀምሮ ቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ነገሡበት እስከ ፱፻፹፪(982) ዓመት አግዓዝያን ከተባሉ ከነገደ ዮቅጣን በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፶፪(52) ናቸው። ዘመኑም ፩(1) ሺህ ፫(3) ዓመት ይሆናል።
ከክርስቶስ ልደት በፊት ቀዳማዊ ምኒልክ ከነገሡበት ከ፱፻፹፪(982) ዓመት ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ተወለደበት እስከ ፩(1) ዓመተ ምሕረት እስከ ባዚን በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፷፯(67) ናቸው። ዘመኑም ፱፻፹፪(982) ይሆናል። ነገር ግን ባዚን ከክርስቶስም ልደት በኋላ ፱(9) ዓመት ነግስዋልና ይህ ሲጨመር ፱፻፺፩(991) ይሆናል። ከባዚን ጀምሮ የቀዳማዊ ምኒልክ መንግሥት ወደ ነገደ ዛጔ እስከ ፈለሰበት እስከ ድልናዖድ ድረስ ከ፩(1) እስከ ፱፻፲፪(912) ዓመተ ምሕረት በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፺፬(94) ናቸው። ነገር ግን ባዚን ሁለት ጊዜ ያልተቆጠረ እንደ ሆነ ፺፫(93) ይሆናል። ዘመኑም ፱፻፲፪ (፱፻፳)➾912(920) ዓመት ይሆናል። ክርስትና በኢትዮጵያ የገባው በነዚሁ ዓመታት ውስጥ ከ፪፻፺፰(298) እስከ ፫፻፳፬(324) ዓ.ም. በ አብርሃ ና አጽብሓ ዘመን ነው።
ከድልናዖድ በኋላ ከመራ ተክለ ሃይማኖት (ስመ መንግሥታቸው ዛጔ) ጀምሮ እስከ ይትባረክ በኢትዮጵያ ነገሡ የዛጔ ወገኖች ፲፩(11) ነገሥታት ናቸው። ዘመኑም ፫፻፴፫(333) ዓመት ይሆናል። የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይል ወደ ዛጔ ዘር ካለፈ በኋላ በ፫፻፴፫(333) ዓመት እንደ ገና
ወደ ቀዳማዊው ምኒልክ ዘር ወደ ይኩኖ አምላክ ከተመለሰበት ከ፲፪፻፵፭ (፲፪፻፶፫)➾1245(1253) ዓ.ም. ጀምሮ የጎንደር መንግሥት እስከሚባለው ሠርፀ ድንግል እስከ ነገሡበት እስከ ፲፭፻፶፫(1553) ዓ.ም. በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፳፮(26) ናቸው፤ ዘመኑም ፫፻፩(301) ዓመት ይሆናል።
ሠርፀ ድንግል ከነገሠበት ከ፲፭፻፶፫(1553) እስከ ፲፯፻፸፯(1777) ዓ.ም.
የጎንደር መንግሥት መጨረሻ እስከ ተክለ ጊዮርጊስ ፤ በጎንደር ቤተ መንግሥት ሆነው ኢትዮጵያን የገዙ ነገሥታት ፲፰(18) ናቸው። ዘመኑም ፪፻፹፬(284) ዓመት ይሆናል።
የጎንደር መንግሥት የሚባለው ከተጨረሰበት ከ፲፯፻፸፯(1777) ዓ.ም. ጀምሮ ዓፄ ቴዎድሮስ እስከ ነገሡበት እስከ ፲፰፻፵፭(1845) የገዙ መሳፍንት ፲፱(19) ናቸው። በነዚህም
መሳፍንት ዘመን ሙሉ ሥልጣን ሳያገኙ ለስሙ ብቻ ዘውድ እየጫኑ በጎንደር ቤተ መንግሥት ይቀመጡ የነበሩ ትውልዳቸው ከቀዳማዊ ምኒልክ ወገን የሆኑ
ነገሥታት ፲፬(14) ናቸው። ዘመነ መሳፍንት ካለፈ በኋላ ከ፲፰፻፵፭(1845) እስከ ፲፰፻፹፩(1881) በኃይልና በጉልበት የነገሡ የኢትዮጵያ ነገሥታት ፫(3) ናቸው። ዘመኑም ፴፮(36) ዓመት ይሆናል። የሸዋ መንግሥት ባላባቶች ፲፭(15) ናቸው። የግዛታቸውም ዘመን ፪፻፸(270) ዓመት ይሆናል።
❣ እናመሠግናለን ❣
@Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°°°°°

💫🌪 ጥቆማ 🌪💫
በአንድ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህሯ ተማሪወቿን አንድ Assignment መስጠት
ፈለገች..!! ተማሪወቿን ድንች ይዘዉ እንዲመጡ አዘዘች፡፡
ድንቾቹ ላይም የሚጠሏቸዉን ሰወች ስም እንዲፅፉ አዘዘቻቸዉ..
የሚያመጡት የድንች ብዛትም በሚጠሏቸዉ ሰወች ብዛት
ልክ እንዲሆን አለች፡፡ በሁለተኛዉ ቀን አንዳንዶቹ 3፡ ሌሎች 5 ቀሪወቹ ደግሞ 8 ድንቾቹን የሚጠሏቸዉን ሰወች ስም ፅፈዉ አመጡ..መምሯ ደግሞ <<ከዛሬ
ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እኒህን ድንቾች በሻንጣችሁ ይዛችሁ ትዞራላችሁ...ሽንት ቤት ስትሄዱ እንኳ መተዉ
አትችሉም!>> ብላ አዘዘች
.
ቀኑ እየጨመረ ሲሄድ ድንቹ በመበላሸቱ ሽታዉ ይረብሻቸዉ ስለጀመረ ተማሪዎቹ ቅሬታ ማቅረብ ጀመሩ..በተለይም 8 የያዙት ከሽታው በተጨማሪ ክብደቱ
እንደበዛባቸው መናገር ጀመሩ፡፡
.
ከሳምንት በኋላ የአሳይመንቱ ገደብ ስላበቃ ተማሪወች ድንቹን አዉጥተዉ እንዲጥሉ ተፈቀደላቸዉ::
ከዛም መምህሯ<<እህ እንዴት ነበር?>> ብላ ጠየቀቻቸዉ...ሁሉም ማጉረምረም ጀመሩ ..."አረረረ ከክብደቱ ሽታዉ...አረ በጣም ነዉ የሚያስጠላዉ"...አሉ
.
.
መምህሯ<<አያችሁ በልባችሁ የምትሸከሙት ጥላቻም እንዲሁ ነዉ...ጥላቻ ልብን ይመርዛል.. በምትሄዱበት ሁሉም እየተከተለ ይረብሻችኋል...ለአንድ ሳምንት የተበላሸ
ድንችን ሽታ መቋቋም አልቻላችሁም..አስቡት ደሞ በጥላቻ የተመረዘን ልብ እድሜ ልካችሁን ይዛችሁ ስትኖሩ!!>> አለቻቸዉ
.
.
ጥላቻን ከዉስጣችሁ አዉጡት..ና ከእዳ የፀዳችሁ ሁኑ!! እዉነተኛ ፍቅር እንከን አልባን ሰዉ ማፍቀር ሳይሆን ንፁህ
ያልሆነን ሰዉ በንፁህነት መዉደድ ነዉና!!!
❤️❤️አዲሱን ዓመት ጥላቻን አስወግደን በፍቅርና በይቅርታ እንቀበለው❤️❤️
🌼፳፻፲፫🌼
❣ እናመሠግናለን ❣
@Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°°°°°°

📆 ጷግሜን 📆
Re~Post
የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ
✍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
📚 ጳጒሜን የተባለችው 13ኛዋ ወር በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ስትባል ሊቃውንት ተረፍ ይሏታል፡፡ የ5 ቀናትን የጳጉሜንን አመጣጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጠንቅቀው ቀምረው በባሕረ ሐሳብ ብራናቸው ላይ ጽፈውልናል፡፡
📚 ይኸውም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ያሉት 12ቱ ወራት ያላቸው ዕለታት በአጠቃላይ 360 ናቸው፡፡ በቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጥልቅ ትንተና 1 ዕለት የሚባለው 24 ሰዓት ከ52 ካልዒት ከ31 ሳልሲት ነው፡፡
📚 1 ካልዒት ማለት 24 ሰከንድ ሲኾን 52 ካልዒት ማለት 1248 ሰከንድ ነው፤ 31 ሣልሲት ማለት 12.4 ሰከንድ (ቅጽበት) ይኾናል፡፡ በመኾኑም በአንድ ቀን ውስጥ 1 ደቂቃ ከ0.4 ሰከንድ ትርፍ መኖሩን ያስረዳል፡፡
📚 በመኾኑም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ባሉት 360 ቀናት ያሉትን 52 ካልዒት ወይም 1248 ሰከንድ እንዲኽ እናባዛቸዋለን፤ 52 ካልዒት X 360 ዕለታት= 18720 ካልዒት ወይም (449, 280 ሰከንድ) ይኾናል፤ ወደ ደቂቃ ስንለውጠው 7488 ደቂቃ ወይም 5 ዕለት ይኾናልና የጳጒሜን አመጣጥ ይቺ ናት፡፡
☞☞ የጳጉሜን 5 ምስጢር
📚 አራቱ የዓመት ወቅቶች ማለትም መፀው፣ ሐጋይ፣ ጸደይና ክረምት 91, 91 ቀናት የሚኾኑት ከጳጒሜን 1 አንድ ዕለት እየተሰጣቸው ሲኾን በአጠቃላይ 364 ዕለታት ወይም 52 ሳምንት ኾኖ አንዲት ዕለት ትተርፋለች፤ ይቺም ጳጒሜን 5 ስትኾን በኢትዮጵያ ቀደምት የዘመን ቀመር ሊቃውንት “ዕለተ ምርያ፣ አዕዋዲት” ትባላለች፡፡
📚 ዕለተ ምርያ ማለት ዕለተ መድኀኒት ማለት ነው፤ ምክንያቱም ጳጒሜን 5 የመድኀኒታችን ክርስቶስ ልደትን የምናውቅባት ስለኾነች ነው፤ ይኸውም ጳጒሜን 5 በዋለችበት ዕለት የክርስቶስ ልደት ዕለት በተመሳሳይ መልኩ ይውላል፡፡
📚 ለምሳሌ የዚኽ ዘመን ጳጉሜን 5 ዕለት ሐሙስ ናት፤ በተመሳሳይ መልኩ የ2013 የጌታችን የልደት በዓል ታኅሣሥ 29 ሐሙስ ላይ ይውላል፡፡ በዚህ ምክንያት ዕለተ ምርያ የሚል ሥያሜ ሊሰጣት ችሏል፡፡
📚 በተጨማሪም ጳጒሜን 5 የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የዐዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደኾነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ በመኾኑ ዕለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ መዋሉ በእጅጉ ይደንቃል።
☞☞ ጳጉሜን 6 እና አመጣጧ
📚 የ6ተኛዋ ጳጒሜን አመጣጥን ስናይ፡- በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ስሌት 1 ዓመት የምንለው 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው፡፡ ይህን የየዓመቱን 6 ሰዓት ስንቈጥር የኹለት ዓመት 12 ሰዓት፤ የሦስት ዓመት 18 ሰዓት፤ የአራተኛው ዓመት 24 ሰዓት ወይም አንድ ዕለት ሲሆን ይኸውም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መጀመሪያ ሲኾን ይኸውም በቀደምት የአቡሻክር ሊቃውንት “መጠነ ራብዒት፣ ሠግረ ዮሐንስ” ትባላለች። ዘመነ ዮሐንስ ተራምዶ የሚያልፍባት ለማለት ነው፡፡
📚 እኛ ጳጒሜን 6 ስናደርግ ምዕራባውያኑ ግን የጳጒሜን ወራትን በማጥፋታቸው ኹሌ ለእነርሱ 28 የኾነችው የካቲትን በአራት ዓመት አንዴ 29 ያደርጋሉ፤ Leap Year ብለው ይጠሯታል።
☞☞ ጳጒሜን 7 እና አመጣጧ
📚 የኢትዮጵያን ቀደምት ሊቃውንትን በእጅጉ እንድናደንቅ ከሚያደርገን አንዱ የጳጒሜን 7ትን ስሌት ጠንቅቀው አስልተው በብራና የአቡሻክር መጽሐፍ ላይ ጽፈውልን ስሌቱን አስልተው ማለፋቸው ሲኾን፤ የስሌቱም መጠሪያ “ዕሪና መዓልት ዕሪና ሌሊት” በመባል ይታወቃል፡፡
📚 ይኸውም 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ የኾነው የፀሓይ ዐውደ ዓመት የ6 ካልዒት ወይም የ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ጥርቅም ወይም ከላይ ያየናት የአንዷ ዕለት 0.4 ሰከንድ ጥርቅም ነው፡፡
📚 ስናሰላውም የ5 ዓመቱ 30 ካልዒት፤ የ10ሩ ዓመት 60 ካልዒት (1 ኬክሮስ ወይም 24 ደቂቃ) ይሆናል፡፡ የ100 ዓመት (10 ኬክሮስ) ወይም 240 ደቂቃ (4 ሰዓት) ይኾናል፡፡ የ200 ዓመት 20፤ የ300 ዓመት 30፤ የ400 ዓመት 40 ኬክሮስ፤ የ500 ዓመት 50 ኬክሮስ፤ የ600 ዓመት 60 ኬክሮስ ሲሆን 60 ኬክሮስ ማለት 1440 ደቂቃ ወይም 24 ሰዓት ወይም 7 ተኛዪቱ ጳጉሜን ናት፡፡
📚 ሆኖም ግን የአቡሻሕርና የባሕረ ሐሳብ መምህራን ጳጕሜን 7 የተገኘችው ከጥቃቅን መስፈርት ወገን ከሆነችው ከካልዒት በመሆኑ ሒሳቧ ብቻ ታስባ ድቁቅ ደቃይቅ ተብላ ብቻ እንድትተው በማዘዝ ዕለቷ ግን በኅሊና ብቻ እንድትታሰብ እንጂ ተቆጥራ እንዳትከበር አዘዋል፡፡ በመሆኑም በማሰብ ብቻ እንጂ በዕለትነት ተቆጥራ አትውልም፡፡
📚 በአቡሻሕሩ ስሌት መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ 12 ዕሪና መዓልት 12 ዕሪና ሌሊት (ጳጉሜን 7) ተመላልሶ በ1700 ዓ.ም. ወይም በ7800 ዓመተ ዓለም ኾኖ 13ኛው ከተጀመረ 311 ሆኖ በዘመነ ሉቃስ ይኸው ሊፈጸም በ2011 ዓ.ም ካሰላነው 289 ዓመት ይቀራል ወይም በ2300 ዓ.ም. ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡
📚 ይህ በሚሆን ጊዜ ዐቀድ የሚባል ኮከብ አለ፤ ሰሌዳው በፀሓይ ልክ፤ ባሕርዩ ጽሉም ነው፤ ርሱ በ600 ዓመት መጥቶ ፀሓይን ይጋርዳታል፤ ያን ጊዜ ሌሊቱና መዓልቱ ጨለማ ኹኖ ይውላል ያድራል፤ ይኸውም የመከራ ፊት አውራሪ አጫሪ ነው፤ ይኸውም በዐጤ ኢያሱ ወይም ፀሓይ ሰገድ በተባለ በዐጤ ዮስጦስ ጊዜ ተደርጓል ብለው መዝገብውልናል፡፡ ይህን ስናይ የቀደምት ኢትዮጵያውያንን ዕውቀት ሁሌም እንድናደንቅ ያደርገናል፤ መልካም የጳጉሜን 13ኛ ወራት ይሁንልን፡፡
ይቆየን!
🌼
ለመጪው ዘመን ከቁጥር ሳንጎድል በሰላም በፍቅር ያድርሰን!
❣ እናመሠግናለን ❣
#Coททεcт WiтhUs 👣 @Feed_it_bot
┈┈┈••✦✦••┈┈┈

እንደምን አላችሁልኝ! የአመት በዓል ሽር ጉዱ እንዴት አርጎአችኋል? ወንዶች ስራውን ሁሉ እናንተ ላይ ጥለው ሴቶች ፈታ እያሉ እንደሆነ ቅሬታ እያቀረባችሁልኝ ነው😜😂
ተዉ እንጂ ሴቶች ባይሆን በግ ማረዱን እንኳን አግዙአቸው እንጂ! ሴትነቱስ ለመቼ ነው!
በዓሉን በጾም ለምናሳልፍ ደግሞ ቅዳሜ እንገናኝ ተባብለናል ..... የሆነ ሰው ምን አለኝ መሰላችሁ "ነገ በቃ ጾም ስለሆነ ለምን ተኝተን ሲነጋ ቅዳሜ ተነስተን አናከብርም አለኝ" አብሮን የነበረው ጓደኛዬም ምን ቢለው ጥሩ ነው "እንዴ ሌሎቹ ሲበሉ ማን ሊያይልህ ነው" አላለውም፤ ለነገሩ ልክ ነው ትን ቢላቸውስ 😂 ... ለማንኛውም 😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣 ነበር መልካም አመት በዓል ተመኝቻለሁ! በአዲሱ አመት ከቻናላችን ጋር ጥሩ ጊዜ እናሳልፋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ!
🌼 መልካም በዓል 🌼

🗓 የዘመን አቆጣጠር በኢትዮጵያ 🗓
Re~Post
ዘመን የሚለካው የጸሐይንና ጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት አድርጎ ዕለት፣ ወር እና ዓመት በሚል መስፈሪያ ተጠራቅሞ ነው::
ዕለት ፦ አንድ ዕለት ማለት አንድ የብርሃን እና አንድ የጨለማ ክፍለ ጊዜ ያለው ሲሆን ጸሐይ አንድ ግዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ
የያዘ ነው:: በሌላ አባባል ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ ያምትሽከረከርበት ጊዜ ነው::
ወር ፦ አንድ ወር ማለት ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ ሙሉ ሆና እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው:: ይህም ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዞራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 29.5 ዕለታት ማለት ነው::
ዓመት፦ አንድ ዓመት ማለት መሬት በጸሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 365 ዕለታት ከሩብ ያህል ነው::
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርም እነዚህን መስፈሪያዎች በመጠቀም 30 ዕለታት ያሉዋቸው 12 ወራት (መስከረም፣ ጥቅምት፣ ህዳር፣ ታህሳስ፣ ጥር፣ የካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዚያ፣ ግንቦት፣ ሰኔ፣ ሐምሌ እን ነሐሴ) እና 5 (በየ4 ዓመታት ደግሞ 6) ዕለታት ያሏት 13ኛ ወር (ጷግሜን) ዑደት ይጠቀማል:: ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የ13 ወር ባለቤት የምትባለው::
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሃይማኖታዊ ይዘት ሲኖረው መነሻ የሚያደርገውም የክርስቶስን ልደት ነው:: ዘመናቱም በሐዋርያት ተሰይመው በአራት መደባት ይዞራሉ፤ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ(ጷግሜን 6 ዕለታት የሚሆንበት) እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው:: አዲስ ዘመን የሚጀምረውም መስከረም 1 ነው::
ምንጭ – መስከረም 2004 አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌻፳፻፲፫🌻
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ
ማቴዎስ በሰላም አደረሳችሁ
አደረሰን!

🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼
ብዙ ጊዜ ከዘመነ እገሌ ወደ ዘመነ እገሌ በሰላም አደረሳችሁ ሲባል ሰምታችሁ ይሆናል። ይሕ በአራቱ ወንጌላት የሚሰየመው ዘመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተጀመረና በስፋት የሚነገር ነው። የዘመኑ ስያሜ የትኛው ወንጌላዊ እንደሆነ የምናውቅበት ቀላል ቀመርን ይዤላችሁ መጥቻለሁ። የዘንድሮው ማለትም የ2013 ዘመን ለየቱ ወንጌላዊ እንደተሰጠ በምሳሌ መልክ አቅርቤላችኋለው፤ ለሌላው ዘመንም ቀመሩ እንደዛው አመቱን በመቀየር ብቻ አስልቶ ማወቅ ይቻላል።
🦋
ዓመተ-ዓለም =
ዓመተ-ኩነኔ(ፍዳ) + ዓመተ-ምህረት
ዓመተ-ዓለም = 5500 + 2013
ዓመተ-ዓለም= 7513
👣
ዓመተ-ዓለም ÷ 4 = መጠነ-ራብዒት
7513 ÷ 4 = 1878
4
35
32
31
28
33
32
1 ◅◄ ቀሪ
ቀሪው '0' ወይም '4' ከሆነ ዘመነ-ዮሐንስ
ቀሪው '1' ከሆነ ዘመነ-ማቴዎስ
ቀሪው '2' ከሆነ ዘመነ-ማርቆስ
ቀሪው '3' ከሆነ ዘመነ-ሉቃስ
☄በዚህም መሠረት በ2013 ዘመነ ማቴዎስ ይባላል ማለት ነው።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
አመት በዓሉ ወይም መስከረም አንድ መቼ ቀን እንደሚውል ወይም መባቻው ምን ዕለት እንደሆነ አስቀድማችሁ ለማወቅም የሚከተለውን ቀመር ተመልከቱ።
🦋 መባቻ = ዓመተ-ዓለም + መጠነ-ራብዒት ÷ 7
= 7513 +1878 ÷ 7
= 9391 ÷ 7
= 1341 ቀሪ '4'
ቀሪው '0' ከሆነ ሰኞ
ቀሪው '1' ከሆነ ማግስተ-ሰኞ
ቀሪው '2' ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው '3' ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው '4' ከሆነ አርብ
ቀሪው '5' ከሆነ ቅዳሜ በመግደፍ
ቀሪው '6' ከሆነ እሑድ መባቻ ይሆናል።
👣
በዚህም መሠረት 2013 መስከረም አንድ አርብ ቀን ይውላል።
እስቲ እናንተ ደግሞ የ2016 ዓ.ምን ዘመኑን እና መባቻውን አስልታችሁ በ @Feed_it_bot ላኩልኝ። ቀድሞ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ላሳየኝ ሽልማት🎁🎉 አዘጋጅቻለሁ!

🎥📻 ከታሪክማህደር 🎙🎞
#መስከረም_2 ቀን 1967 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሬዲዮ የንጉሠ ነገሥቱን
ከሥልጣን መውረድና በጊዚያዊ ወታደራዊ መንግሥት መተካት የታወጀበት ቀን ነው።
የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት እንዴት ሊወድቅ ቻለ የርሳቸውስ ጥፋት ምን ነበረ
ሁላችን እንደምናውቀው አገራችን ኢትዮጵያ 83 በላይ የሚሆን ጐሣና ቋንቋ የአላት አገር
ናት። እነዚህ ሁሉ ጐሣዎች ዓለምን ይቅርና በተቀመጡባት በአንዲቱ በናታቸው አገር ውስጥ
የተጠራቀሙት እርስ በራሳቸው አይተዋወቁም ነበር ። የአንድነትንና የፍቅርን ድልድይ
ሠርተው የተራራቁትን አቃርበው የተጣሉትን አስማምተው ከትምሕርት እርቆ ይኖር የነበረውን
ሕዝባቸውን አስተምረው ኢትዮጵያን ቀርቶ ከዓለም ጋር እንዲተዋወቅ የአደረጉት ቀዳማዊ አፄ
ኃይለሥላሴ ናቸው።
በእርግጥ ኢትዮጵያ በመንግሥትነት ደረጃ ከታወቀችበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለሥላሴ
ድረስ ብዙ ነገሥታት አልፈዋል። እነዚህም የአለፉት ነገሥታት አፄ ኃይለሥላሴ ለኢትዮጵያ
የሠሩትን ለመሥራት ያልተመኙበት ያላሰቡበት ያልጀመሩበት ጊዜ የለም። ነገር ግን እነዚያ
ሲመኙትና ሲአስቡት የነበረው የሥልጣኔ ጮራ እንደ ደመና ሲጓዝ ቆይቶ በአፄ ኃይለሥላሴ
ዘመነ መንግሥት ሊደርስ ቻለ። ተራርቆ የነበረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲገናኝና
እንዲተዋወቅ የአደረጉ እንዲሰለጥን ትምሕርት ቤት የከፈቱ ጤናው እንዲበቅ ሆስፒታል
ያቋቋመ እንዳይበደል ሕገ መንግሥት የመሠረቱ ምክር ቤት እንዲከፈት የአደረጉ 1600
ዘመን በግብጽውያኖች እጅ የነበረውን መንፈሳዊ ሥልጣን ከግብጽዎች እጅ አስለቅቀው
በኢትዮጵያ እጅ እንዲሆን የአደረጉ፣ ከወገናችን ጳጳስና ሊቀ ጳጳስ ፓትረያርክም መርጠን
ለመሾም ሥልጣን እንድናገኝ የአደረጉ።
ከፊደል ጀምሮ እስከ ዩኒቬርሲቲ የአለውን ዕውቀት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያገኝ የአደረጉ።
በጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሮጌውን የድንቁርና ገላ አውጥቶ ጥሎ አዲሱን የዕውቀት
ገላ እንዲለብስ የአደረጉት አፄ ኃይለሥላሴ ናቸው።
የኤርትራ ባሕራችን ከነወደሱ በተወሰደ በ1145 ዓመት
የአሰብ ወደብ በተወሰደ በ84 ዓመት
በጐስ ሀብሀብና መንሳ በተወሰደ በ81 ዓመት
ጊንዳ በተወሰደ በ80 ዓመት ኤርትራ በተወሰደች በ66 ዓመት ጋንቤላ ከነባሕሩ እንግሊዞች
በወሰዱት በ58 ዓመት እንዲመለስ የአደረጉ የአየርና የባሕር ኃይል እንዲቋቋም የአደረጉ በነ
አፄ ካሌብ ጊዜ የቀረ የንግድና የጦር መርከቦቻችን በቀይ ባሕራችን ላይ እንዲዘዋወሩና
ከዓለም ጋር እንዲ ገናኙ የአደረጉ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል
እንድትሆን የአደረጉ አፄ ኃይለሥላሴ ናቸው ። የኤርትራ ባሕራችን የአዶሊስና የምጽዋ
ወደቦቻችን በአረቦች የተነጠቅነው በ800 ዓ.ም በአፄ ውድም አስፈሬ ዘመነ መንግሥት
ነው።በተጨማሪ አቶ ተክለ ጻድቅ መኩርያ በ1951 ዓ.ም የጻፉትን የኢትዮጵያ ታሪክ 1ኛ
መጽሐፍ ገጽ 379 , 380 እና ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ኤርትራን በተረከቡ ጊዜ መስከረም
24 ቀን 1945 ዓ ም የአደረጉት ንግግር ፍሬ ከናፍር 2ኛ መጽሐፍ ገጽ 690 ተመልከቱ።
ይህ ሁሉ ሥራ በሚሠራበት ጊዜ የነበረውን ችግር የማያውቀው ሁሉም ነገር በተሎ
እንዲሠራለት የሚፈልገው የአሁኑ ችኩል ትውልድ የሚመኘውን ያህል አትራመድ እንጅ
ኢትዮጵያ ማናቸውንም የሥልጣኔ ጮራ ሁሉ ለማየትና ለመቅመስ የቻለችው በቀዳማዊ አፄ
ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ነው ።
አፄ ኃይለሥላሴ ኢትዮጵያ ከነበረችበት የጨለማ ኑሮ ተረክበው አቅማቸው በሚፈቅድላቸው
መጠን ጨለማውን እየአስለቀቁ ብርሃን እየተኩ በመጓዝ ላይ ሳሉ እርሳቸው አስተምረው
ያሳደጉአቸው ልጆቻቸው ሲደርሱ የተፈጥሮ ሕግ ነውና እርሳቸው ደግሞ እየአረጁ መጡ።
አሁን የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት እንዴት ሊወድቅቻለ ወደሚለው ነጥብ እገባለሁ።
የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት ለመውደቅ የቻለው በርሳቸው ላይም ይኸን የመስለ እጅግ
የሚያሳዝን በደል ሊፈጸም የበቃው ምክንያቱ ብዙ መሆኑ ቢታወቅም እንዱና ዋናው ግን
የራሳቸው ጥፋት ነው ይኸውም በቃኝን አለማወቃቸው ነው። በኢትዮጵያ ዘመነ መንግሥቱን
በሰላም ያሳለፈ ንጉሠ ነገሥት አለመኖሩ ሲታወቅም እንደ አፄ ኃይለሥላሴ ፈተና የበረከተበት
የለም ።ስለሆነም በየጊዜው የደረሰባቸውን ፈተና ሁሉ በትእግሥትና በጥበብ መቀስ
እየቆረጡ አልፈው ኢትዮጵያን ለረጅም ዘመናት ሊመሯት ችለዋል። በዚህም ረጅም
የአስተዳደር ዘመናቸው በዓለም ላይ ከፍያለ ተዋቂነትን ክብርና ሞገስን ከመጐናጸፋቸውም
በላይ አገራቸውንም ኢትዮጵያን በይበልጥ በዓለም እንድትታወቅና እንድትከበር
አድርገዋታል።
ኢትዮጵያ መንግሥትነትን ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለሥላሴ ድረስ 269
ነገሥታቶች መንገሣቸው ቢታወቅም እንደርሳቸው ዓለምን ዙሮ የጐበኘ በዓለም የታወቀና
የተከበረ ብዙ ደስታና ክብር ያዬ የለም።
ኢትዮጵያ በመንግሥትነት ደረጃ ከታወቀችበት ጊዜ ጀምሮ ከአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ
መንግሥት በፊት አንድ የውጭ አገር መሪ ኢትዮጵያን እረግጧት አያውቅም ነበር። 63
መሪዎች የጐበኟት ብዙ አምባሳደሮች ቢሮ የከፈቱባት ልኬታቸው ያልታወቀ ታሪክ
ተመራማሪዎች የሥራ ተቋራጮች ጋዜጠኞች ፊልም አንሺዎችና ቱሪስቶች በብዛት የገቡባት
በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ነው ።
ዕድሜ እየገፋ ሲመጣ ትዕግሥቱና ጥበቡ ያልቅና የመቀሱም ስለት ይበርድና አንድ ቀን
ጠላቶቼ ከአጠመዱት ወጥመድ ገብቸ ከመዋረድ እንደ ተወደድኩና እንደተከበርኩ ሥራውን
በፈቃዴ መልቀቅ አለብኝ ብለው የሚተካውን መንግሥት በሰላም አደራጅተው መልቀቅ
ሲገባቸው ያነን ዕድሜ ይዘው አስተምረው ያሳደጉአቸው ልጆቻቸው እስኪነሱባቸው ድረስ
መጠበቅ አልነበረባቸውም።
ጃንሆይ ማድረግ የነበረባቸው ዘውድ ለኢትዮጵያ ታላቅ ክብርና ቅርስ ስለሆነ ዘውድ
በኢትዮጵያ እንዳይጠፋ ለእንግሊዝ መንግሥት ዘውድ በተሰጠው ክብርና ማዕረግ ልክ
እንዲሰጠው አድርገው ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሕዝብ አስመርጠው በዘውዱ እጅ የነበረውን
ሥልጣን ሕዝብ ለመረጠው ጠቅላይ ሚኒስትር አስረክበው እርሳቸው እንደተወደዱና
እንደተከበሩ ዘውዳቸውን ይዘው ከማናቸውም ሥልጣን እርቀው መቀመጥ ነበረባቸው ።
ይኸንም ማድረግ የነበረባቸው ሲሆን ቀደም አለዚያም የ80ኛው ዓመት የልደት በዓላቸው
ከመድረሱ በፊት በዚያው ዘመን ጥቅምት 23 ቀን የዘውድ በዓላቸው በሚከበርበት ቀን
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመረጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ማስረከብ ነበረባቸው። የዚህ ዓይነቱ
ሥርዓት አሁን በአልኩበት ጊዜ ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ እንዲያ ሁነው በተከበሩበት ዓለም ላይ
በነዚያ ተኩላዎች እጅ ይኸን የመሰለ ውርደት አይደርስባቸውም ነበር ።
እንዲሁም ደርግ ሻብያ ወያኔ በከፈቱት ጦርነት ያንድ እናት ልጆች ገላጋይ አጥተው ያ ሁሉ
ሕዝብም አያልቅም ነበር። ሦስቱ የአንድናት ልጆች በከፈቱት ጦርነት በሦስቱ የጦር ግንባር
በጥይት በርሀብ በበሺታ በቀይ ሺብር በእሥር ቤት በስደት የአለቀው ሕዝብ በደንብ ቢቆጠር
ከ8-10 ሚሊዮን ይሆናል።
ምንጭ:-የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ታሪክ,በበሪሁን ከበደ

https://t.me/Readers_To_Know/528
👆👆👆🌼 መልስ 🌼
🦋ዓመተዓለም=
ዓመተ ኩነኔ(ፍዳ)+ዓመተምህረት
ዓመተዓለም =5500+2016
ዓመተዓለም=7516
ዓመተዓለም፥4=መጠነ ራብዒት
7516፥4=1879
4
35
32
31
28
36
36
0 ቀሪ
ቀሪው"0" ስለሆነ ዘመነ ዮሀንስ
መባቻ=ዓመተዓለም+መጠነራብዒት፥7
መባቻ=7516+1879፥7
መባቻ=9395፥7
መባቻ=1342 ቀሪ 1 ይመጣል~
ስለዚህ ቀሪው 1 ነው መባቻው ማግስተ ሰኞ ነው🦋
ከተሳተፉት ይህን መልእክት የላከልን የቻናላችን ቤተሰብ መልሱን አግኝቶታል ስለተሳትፎአችሁ እናመሠግናለን!
🌼🌻 መልካም አዲስ ዓመት 🌻🌼
🌼🌻 ፳፻፲፫ 🌻🌼

🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻
🌼 ድመቶች🐈 በማሰብ ደረጃ ከቺምፓንዚ እና ከዝንጀሮ 🦍 ቀጥሎ ይመደባሉ።
🌼 ሰው አይኑን👀 ሳይጨፍን ማዛጋት አይችልም።
🌼 ምስጥ ያለምግብ አንድ አመት መቆየት ትችላለች። ቅማል አምስት አመት ትቆያለች አሉ። የሰው ልጅ ግን ያው ሰባት ቀኖች ብቻ ይበቁታል።
🌼 ሕብለ ሰረሰር 19 c.m ርዝመት አለው።
🌼 አባባል:- ሳይራመድ በታሪክ ምንጣ፤
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ።
❣ እናመሠግናለን ❣
#Coททεcт WiтhUs 👣 @Feed_it_bot
┈┈┈••✦✦••┈┈┈
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼🌻
🌼 ድመቶች🐈 በማሰብ ደረጃ ከቺምፓንዚ እና ከዝንጀሮ 🦍 ቀጥሎ ይመደባሉ።
🌼 ሰው አይኑን👀 ሳይጨፍን ማዛጋት አይችልም።
🌼 ምስጥ ያለምግብ አንድ አመት መቆየት ትችላለች። ቅማል አምስት አመት ትቆያለች አሉ። የሰው ልጅ ግን ያው ሰባት ቀኖች ብቻ ይበቁታል።
🌼 ሕብለ ሰረሰር 19 c.m ርዝመት አለው።
🌼 አባባል:- ሳይራመድ በታሪክ ምንጣ፤
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ።
❣ እናመሠግናለን ❣
#Coททεcт WiтhUs 👣 @Feed_it_bot
┈┈┈••✦✦••┈┈┈
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓
ከእመጓ መጽሐፍ የተቀነጨበ .....
(ዶ/ር ዓለማዮሁ) ፦ ".....ፍላጎታችሁ ትምህርት መሥጠት ከሆነ ታድያ ይህን ያክል ምሥጢራዊ ማድረግ ለምን አስፈለገ? ሁሉን ነገር ትውልዱ ቢያውቀው ምን አለ? ታሪኩን ምሥጢር፥ መድኃኒቱን ምስጢር፥ቅርሱን ሁሉ ምሥጢር ማድረግ ምን ይጠቅማል?! እኛስ የክርስቶስ ፍቅር የለንምን? የቃል ኪዳኑ በረከት አይገባንምን???"
አባ አክሊሉ (ኬሚካል ኢንጂነር የነበሩ) ፦ "በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተውታላችሁ:: ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፥ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፥ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፥ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ::
ምኞታችሁ ልክ የለውም፥ አምሮታችሁ ብዙ ነው:: የአማራችሁን ስታገኙ ወድያው ይሰላቻችኋል:: ተው የተባላችሁትን ትሽራላችሁ፥ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፥ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ:: ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደ ፊት ቤተ መቅደሱን በመስታዎት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ:: ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ፥ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም:: ሁሉ አላችሁ :ግን ባዷችሁን ናችሁ:: ሃይማኖት እንጅ እምነት የላችሁም!
'መድኃኒት ነው ያልከው?!' መቀመሚያውን ነግሬህ ማርከሻውን ሳልገልጥልህ መጀመርያውን ብቻ ሞጭልፈህ ትተኸኝ ትሄዳለህ:: ጥበብን "ሀ ግእዝ" ብየ ላስተምርህ ብሞክር፥ መንደር ውስጥ በቃረምካት ዕውቀት ተመክተህ በመሰልቸት "ሆ ሳብዕ" ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ::
የግል ታሪካችሁ ቢታይ ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተለከፈከፈ የተማሪ ኮፋዳ ውስጥ ያለ እህል ይመስላል:: ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ፥ ሰርታችሁ ሀብት ስታፈሩ፥ ከላይ የሆናችሁበትን ሀገር ለቃችሁ፥ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ:: ትቀጥላላችሁ፥ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ:: ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወድያው ትጸጸታላችሁ:: በጽኑ ታማችኋል!
ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ:: ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ፤እናም ወደኋላ ስለታሪካችሁና ስለ ቅርሳችሁ ባሰብችሁ ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማችኋል::
ስለሆነም ከኋላ ታሪካችሁና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ:: የአሸናፊነትንና የተሸናፊነትን ትርጉም በአንድ ላይ የያዙ ሃውልቶችን ታቆማላችሁ:: ለግልጽነትና ለነጻነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ ዕርቃን ወደ መሆን ወረዳችሁ::
ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ:: በዚህ ዓለም ጥድፊያ ታማችኋል:: ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፤ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ፤ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ አገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ:: በቁማችሁ የናቃችሁትን የሀገራችሁን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትናፍቃላችሁ::
ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ:: ግብዝነታችሁ መጠን የለውም:: ሁለት ሀገር እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ፤ አንዱን በደም ሌላኛውን በመታወቅያ ታስባላችሁ:: ከአንዱም ግን በአግባቡ አትኖርም:: ዘመናችሁም በምልልስና በመዋተት ያልቃል::ምን እንደምትፈልጉ አታውቁም እናም ፍለጋችሁ አያልቅም!!
በዚህ የተነሳ ምሥጢር ለመካፈል ቅርስ ለመረከብ የሚያስችል ሰብእና አልገነባችሁም:: እኛ የመገናኛውን ድልድይ ስላልሠራንና ከእናንተ ስለራቅን ሳይሆን ስለማታዩት ወይም ማየት ስለማትፈልጉ አለበለዚያም እንደ ልቦወለድ ገጸ ባሕርይ የራሳችሁን ያሸበረቀ አስረካቢ ፈጥራችሁ እውኑን ሳይሆን ምናባችሁን መረከብ ፈልጋችሁ ስለምታጡት ነው:: እኛ ደግሞ እናንተን ታዩን ዘንድ አላሸበረቅንም፤ማሸብረቅም አንፈልግም:: በዚህ ምክንያት ለእናንተ ምሥጢር ለመንገር ፥ቅርስ ለማውረስ እጅግ ከባድ ሆኗል:: እኛ አባቶቻችንን እናምናለን:: በእነርሱም ደስ ይለናል:: የነገሩንን ተቀብለን ቃል ኪዳናቸውን ጠብቀን እንኖራለን::
"ጽላተ ሙሴ አክሱም ጽዮን እንዳለች ሲነግሩን መጋረጃ ገልጠን፥ ሳጥን ከፍተን እንይ እላልንም፤ጌታ የተሰቀለበት የግማደ መስቀሉ ክፋይ ግሼን ማርያም አለ ሲሉን ቆፍረን አውጥተን እንመልከት አላልንም፤ ቅዱሱ ጽዋ መንዝ ውስጥ አለ ሲሉንም ዋሻ እናስስ አላልንም::" አባቶቻችንን እምነን፤ ሀገራችን የበረከት ምድር መሆኗን ተረድተን፤ የጌታችንን የጸጋ ስጦታ ተቀብለን በእምነት እንኖራለን::ምንም የለንም፤ሁሉ ግን የኛ ነው:: ደሆች ብንባልም ባለጸጎችም ነን:: የተራቆትን ብንመስልም የጸጋ ልብስ አለን:: ሐዘንተኞች ብንመስልም ደስተኞች ነን:: ስለ ሀገራችን መባረክ፥ ቅድስት ሀገር መሆን፥ቅዱስ ቅርስ በእጃችን እንዳለ ዓለም እንዲያረጋግጥልን አንፈልግም:: የሌለንን አለን፥ያልተሰጠንን ተቀብለን ብለን የምንኮፈስ ግብዞችም አደለንምና:: የሌለን ነገር ለመጠበቅና ለመታመን ስንል ሥጋችንን እየጎሰምን በገዳም ለመኖር የምንወስን ጅሎችም አይደለንምና!!! "
ከእመጓ መጽሐፈ ገጽ 161-164 የተወሰደ