ካነበብነው📖📜📰🗞
647 subscribers
20 photos
1 file
63 links
በዚህ መድረክ
#ቅምሻ
#ጥቆማ
#ከታሪክ_ማህደር
#ስነ_ግጥም
#ከዚም_ከዛም እና
#ለፈገግታ ይተላለፋሉ። እናንተም እዚህ ቻናል ላይ ካነበባቹት መፅሐፍ 📖 ፣ጋዜጣ 📰 ፣ መጽሔት 🗞፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ወቅታዊም ሆነ ዘመን ተሻጋሪ የድሮ ስራዎችን ማካፈል ለምትፈልጉ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
🌿 @Feed_it_bot ይጠቀሙ።
Download Telegram
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ ስድስት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ምንጊዜም የተሻለ መንገድ አለ፡፡ የጥላቻ ትችት ከማቅረባችን በፊት እውነተኛውን ነገር ለማወቅ የበለጠ ጽናት ሊኖረን ይገባል፡፡ ስለዳግማዊ አጼ ምኒልክ፣ ስለ አጼ ኃይለስላሴ፣ ስለ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እውነኛውን ነገር ማቅረብ ይኖርብናል፡፡ እነርሱን መጥላት ሳይሆን ከስህተቶቻቸው እንማር፣ እኛ በህይወት ያለነው የእነርሱን ስህተት መድገም የለብንም፡፡ ጥላሸት በመቀባት ላይ ላለመሰማራት ከእነርሱ ስህተት እንማር፣ ነገር ግን የእርቅን መንገድ በመፈለግ የእነርሱን ስህተቶች እናርም፡፡ ከኢትዮጵያ ወጣቱ ትውልድ ጋር ህብረት በመፍጠር ማንም ወንድ ወይም ሴት በማንነቱ/ቷ፣ በዘሩ/ሯ ሳይሆን ሰው በመሆኑ/ኗ፣ አፍሪካዊ/ት እና ኢትዮጵያዊ/ት በመሆናቸው ብቻ በመመልከት አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ ማንም ወንድ ወይም ሴት ባለው/ላት ስልጣን በመመካት ባልታጠቁ ዜጎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጦር እልቂት ሊያዝዝ/ልታዝዝ የማይችሉበት እና ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብም ሊወገድ የሚችልበት ነጻ ህሊናን በመፍጠር አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ በእያንዳንዱ/ዷ ግለሰብ የጎሳ፣ የእምነት ወይም የቋንቋ ልዩነት ሳንፈጥር በአንድነት በመሆን የእያንዳንዱ/ዷ ዜጋ መብት እና ክብር የሚጠበቅበትን ህብረተሰብ ለመፍጠር እንነሳ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው የወደፊቱን ብሩህ ዘመን ለመፍጠር የምንችለው፡፡ ለብዙ ጊዜ በመቆየት በጊዜ ደመና ተሸፍኖ የደበዘዘውን ነገር ቆፍሮ በማውጣት እና ጥላሸት በመቀባት አይደለም ፍቅር የነገሰበትን የወደፊቱን ትውልድ መገንባት የምንችለው፡፡

በጥላቻ ንግግር አንዘን ወይም ደግሞ አንቆጣ፡፡ ምንም ዓይነት እርባና የለውም፡፡ ይልቁንም ጥላሸት የመቀባት ዘመቻውን በሰከነ መልክ እናጋልጥ፡፡ መላዕክ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ስህተት እና ውሸት መሆኑን እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት ለመቀበት እና ለመበረዝ የሚደረገውን መዋተት እናጋልጥ፡፡ ከጥላቻ አራማጆች ጋር በማበር እራሳችንን ወደ ጭቃ እና የሚያጣብቅ ቆሻሻ ውስጥ አንጣል፡፡ እንዲህ የሚሉትን የጆርጅ በርናርድ ሻውን ምክሮችን በፍጹም መርሳት የለብንም፣ “ከብዙ ጊዜ በፊት ከአሳማ ጋር ማጥ ዉስጥ ላለመታገል ትምህርት አግኝቻለሁ፣ ለመታገል ከሞከርክ ቆሻሻ ትሆናለህ፣ አሳማው ግን ማጡን የነብሱን ያህል ይወደዋል፡፡“ ጥላቻን ሙያ አርገው ከሚኖሩ ሰዎች ጋር የጥላቻ ቃላትን መለዋወጥ ከአሳማ ጋር በጭቃ ማጥ ውስጥ የነጻ ትግል ውድድርን እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
ጥላቻን ወደ ፍቅር መለወጥ......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ ሰባት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ጥላቻን ወደ ፍቅር መለወጥ

በጥላቻ መንፈስ የተሞሉት ወገኖች ይጥሉ እና ይዋሹ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ የምናደርገው አንዳች ነገር የለም፡፡ በእራሳችን የሀይል ንፍቀ ክበብ ውስጥ ያለን ልዩ ችሎታ እራሳችንን ከጥላቻ ወደ ፍቅር ከመቀየር ላይ ነው፡፡ በእርግጥም አሉታዊ ኃይሎችን ወደ አዎንታዊ ኃይሎች የመቀየር ችሎታ አለን፡፡ ከጥላቻ ወደ ፍቅር ለመቀየር እንችላለን፣ ይህን የምናደርገው ግን ነገሩ ቀላል ስለሆነ አይደለም ይልቁንም የበለጠ ከባድ ስለሆነ እንጅ፡፡ ፍቅር በግለሰብ ደረጃም ይሁን፣ በሌሎችም ይሁን፣ በማህበረሰቡ ወይም በአጠቃላይ በህዝቡ ላይ ይሁን ለተግባራዊነቱ ታላቅ ስራ መስራትን ይጠይቃል፡፡ ከማህተመ ጋንዲ እና “እውነተኛው ኃይል” Satyagraha ከሚሉት አቀራረባቸው እስቲ ትምህርት እንቅሰም፡፡ ጋንዲ እንዲህ በማለት ገለጻ አድርገዋል፣ “እውነት/satya ፍቅርን በማጎናጸፍ የመንፈስ ጽናትን ይወልዳል፣ እናም ከኃይል ጋር ተመሳሳይ በመሆን ያገለግላል፡፡“ ዓላማው በጥላቻ የተሞላው/ችው እንዳያስገድድ/እንዳታስገድድ በማድረግ ሀሳባቸውን ለማስለውጥ ነው፡፡ በተግባራዊነት ሁኔታው ስንመለከተው ዓላማው በጥላቻ የተሞላውን/ችውን ጥላቻ ማራመድ የእራሱን/ሷን ልብ፣ አዕምሮ እና ነብሳቸውን የሚጎዳቸው መሆኑን በማሳመን እንዲቀየሩ ለማድረግ ነው፡፡ ከማንኛውም ጉዳትን ከሚያመጡ ነገሮች ሁሉ የሚጠብቁን እራስን፣ ማህበረሰቡን እና አገርን መውደድ ነው፡፡ በጥላቻ ከተሞሉት ወገኖች ፍቅር የተሞሉ ወገኖችን ለማፍራት እውነተኛውን ኃይል/ Satyagraha በተግባር እናውል፡፡
ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የምንማራቸው .......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ ስምንት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የምንማራቸው በርካታ ቁምነገሮች አሉ፣ እንዲህም በማለት ያስተምሩናል፣ “ጨለማን ጨለማ አያስወግደውም፣ ብርሃን ብቻ ነው ያንን ማድረግ የሚችለው፡፡ ጥላቻን ጥላቻ ሊያስወግደው አይችልም፣ ፍቅር ብቻ ነው ያንን ማድረግ የሚችል፡፡“ ብለዋል፡፡ እንዲህ በማለትም አስተምረዋል፣ “ይቅርታ የማድረግ ችሎታችንን ማሳደግና ማጠናከር ይኖርብናል፡፡ ይቅርታ የማያደርግ የማታደርግ ሰው ለማፍቀር ኃይል የለውም/የላትም፡፡ በመጥፎነታችንም ላይ ጥሩ ነገሮችም አሉ፡፡ በመጥፎ ነገሮቻችን ላይም ጥሩ ነገሮች አሉ፡፡ ይህንን ሁኔታ ባወቅን ጊዜ ጠላቶቻችንን ከመጥላት በመጠኑም ቢሆን እንታቀባለን፡፡“ ይቅርታ አድራጊነት እና እርቅ ብቸኞች የጥላቻ ፈውስ እና መድኃኒቶች ናቸው፡፡ ከዘመናችን ታላቅ ቀልድ አዋቂ ከቻርለስ ቻፕሊን እንኳ ትምህርት መቅሰም ይኖርብናል፡፡ እንዲህም ይለናል፣ “የሰው ልጅ ጥላቻ ያልፋል፣ እና አምባገነኖችም ይሞታሉ፣ እናም ከህዝቦች የነጠቁት ስልጣን ተመልሶ በህዝቡ እጅ ይገባል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጅ ሟች እስከሆነ ድረስ ነጻነት ከናካቴው ሊጠፋ አይችልም፡፡“ ነጻነት በጥላቻ ከተሞሉት የሰው ዘሮች ሁሉ የበለጠ እድሜ አለው፡፡ በጎሳ ማንነት መፈረጅን እርግፍ አድርገን እንተው እና ሰው በመሆናችን ብቻ በኢትዮጵያዊነታችን እና በአፍሪካዊነታችን እንኩራ፡፡
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉ የማስተላለፈው መልዕክት፣......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል አስራ ዘጠኝ 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉ የማስተላለፈው መልዕክት፣

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ሆነው ጥላቻን ለሚያራግቡት አጭር መልዕክት አለኝ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የምትቆሰቁሱት የዘር እና የጎሳ ጥላቻ ፍላጻ በአንድ ወቅት ተመልሶ እራሳችሁ ላይ ይሰካል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአጼ ምኒልክን ክብር እና ዝና ለማንቋሸሽ በታለመ ዕኩይ ምግባር ጡት ቆራጭ አረመኔ ነበሩ በማለት በመሳለቅ እና በማፌዝ ላይ ትገኛላችሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አጼ ምኒልክን እንዲጠሉ የሚሰበክላቸው ሰዎች ነገ ደግሞ አቶ መለስን እንዲጠሉ የማይሰበክበት ምክንያት አይኖርም፡፡ የእናንተ ታላቁ ባለራዕይ መሪ አቶ መለስ በኦጋዴን፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ቦታዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ በፈጸሟቸው የጅምላ እልቂቶች ሳቢያ በድንጋይ እና በእብነበረድ በተቀረጹ ሃውልቶች ላይ ሆነው ሁለተኛው ሮዶልፍ ግራዛኒ በመባል የሚታወሱበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡ ዛሬ ጓደኞች ብላችሁ የያዛችኋቸው ሰዎች ነገ ቀንደኛ ጠላቶቻችሁ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ዛሬ የእናንተ ጠላቶች አድርጋችሁ ጥላሸት የምትቀቧቸው ሰዎች ነገ ጽዋው ሞልቶ እጣ ፈንታችሁ ደርሶ የዘራችሁትን የምታጭዱበት ጊዜ ሲመጣዐየእናንተ ጓደኞች ሆነው ይቀርባሉ፡፡
ዳግማዊ አጼ ምኒልክ መልዓክ ወይም ጭራቅ አልነበሩም፡፡ ሰይጣን ወይም ደግሞ እግዚአብሄርም አልነበሩም፡፡ የተቀሩት የአፍሪካ አገሮች በኃአውሮፓ ኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ሲቆራረሱ፣ መጫወቻ ሲሆኑ፣ ሲነሱ ሲጣሉ፣ ሲበጠሱ ሲቀጠሉ፣ ሲሸጡ እና ሲለወጡ እንዲሁም ሲጋዙ በነበረበት ጊዜ አጼ ምኒልክ ደግሞ ኢትዮጵያን ሲያጠናክሩ እና ሲያዘምኑ የነበሩ የተከበሩ አፍሪካዊ ንጉስ ነበሩ፡፡ ዳግማዊ አጼ ምኒሊክ በአንድ መለኪያ ብች ይገምገሙ፣ በእውነት! የታሪክ ሰዎች እውነታውን መናገር አለባቸው፣ እና ሁሉንም እውነታዎች፣ ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን ስለምኒልክ ያለውንዐእውነታ ብቻ፡፡ ለአጼ ምኒልክ 100ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ ሲባል እ.ኤ.አ በ1909 በኒዮርክ ታይምስ ባሮን ዲ ጃርልስበርግ የተባለ የቤልጄም አሳሽ ለዳግማዊ አጼ ምኒልክ ምስክርነት ለጋዜጣው ቃል በመስጠት የተዘገበውን በከፊል ምስከርነት እውነታ መረጃ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡፡ ይህ ታሪካዊ የምስክርነት መረጃ ዳግማዊ አጼ ምኒልክን ከሰሯቸው ስራዎች አንጻር በትክክለኛው የታሪክ ሚዛን ላይ በማስቀመጥ እንዲገመገሙ ያስችላል የሚል ጽኑ እምነት አለ፡፡
ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የዘውድ ስልጣኑን ለመቆናጠጥ......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል ሃያ 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የዘውድ ስልጣኑን ለመቆናጠጥ ትግል ማድረግ ከጀመሩበት ከ20 ዓመታት በኋላ አቢሲኒያን ከከፊል የኋላቀርነት አገዛዝ በማውጣት ወደ አውሮፓውያን የንጉሳዊ ህገመንግስት የአገዛዝ ስርዓት ምሳሌነት አሸጋግረዋታል… እራሳቸውን ነጻ እና በእራስ የሚተማመኑ አድርገው የሚቆጥሩት ዘ እምነገደ የይሁዳ አንበሳ ስዩመ እግዚአብሔር የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ የኢጣሊያንን የቅኝ ግዛትነት ፍላጎት አምባ ጋሪማ ላይ ጦርነት ገጥመው በአሸናፊነት እንዳንኮታኮቱት… አጼ ምኒልክ ከአጼ ዮሀንስ ህልፈተ ህይወት በኋላ እ.ኤ.አ ኖቬምበር 4 1889 የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሆነው ሲሰየሙ የአቢሲኒያን መንግስት ከመሰረቱት የአካባቢያዊ መንግስታት በሙሉ ቅቡልነት አልነበራቸውም፡፡ ከብዙ ድካም እና ትግል በኋላ ነው እነዚህን የአካባቢ ገዥዎች እና ንጉስነታቸውን አንቀበልም ያሉትን አማጺ ገዥዎች በማሳመን እና በኃይል በማንበርከክ በመጨረሻ ስኬታማ ለመሆን የበቁት… ከዚያ በኋላ የአጼ ምኒልክ ዋና ዓላማ የነበረው የአውሮፓን ስልጣኔ ወደ አገራቸው ማስገባት ነበር፡፡ ንጉሱ የፊውዳሉን ህግ በማፈራረስ በእርግጥም በግዛታቸው እስከ አሁንም ድረስ ጨርሶ እንዳልጠፋ እና ባሮችን ነጻ በማውጣት የባሪያ ንግድን በማጥፋት በግዛታቸው በሙሉ ከክፍያ ነጻ የሆነ የትምህርት ስርዓትን ዘርግተዋል፡፡ በዚህም መሰረት እንደማንኛውም የአውሮፓ ሀገር ሁሉ በቀጣዮቹ ትውልዶች ትምህርት በመላ የአቢሲኒያ ግዛት ውስጥ የሚስፋፋ ይሆናል፡፡ ምኒልክ በመላ አፍሪካ በስልጣን ላይ ካሉ መሪዎች ሁሉ ልዩ ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡ እንደ የዲፕሎማሲ ሰው፣ እንደ ገንዘብ ኃላፊ፣ እንደ ወታደር ከሌሎች ወንድማዊ ንጉሶች የቅርበ መረጃዎችን በመውሰድ በእራሳቸው አካሄድ እንደሚመስላቸው የሚተረጉሙ ንጉስ ናቸው፡፡ እንደ ወታደር እና እንደ የዲፕሎማሲ ሰው የኢጣሊያኖችን በአቢሲኒያ መሸነፍ ለንጉሱ እንደ መልካም አጋጣሚ ምን ያህል ጠቃሚ የሆኑ ንጉስ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ በቅርብ ዓመታት ደግሞ የገንዘብ ብልህ ጥንቁቅ አያያዝ ምኒልክን ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለገንዘብ እንደ ወጣትም፣ የዙፋን ስልጣናቸውን ከመያዛቸው እና በዙፋኑ ላይ ከተቀመጡም በኋላ በፓሪስ የስቶክ ገበያ ትንበያን Paris Bourse ላይ ተሳትፎ ማድረጋቸው መልካም ተፈጥሯዊ ችሎታ ያላቸው መሆኑን ያመላክታል፡፡ እነዚህ ጠቃሚ ትንበያዎች የነበሩ ሲሆን ምኒልክ የዙፋን ስልጣኑን ከያዙ በኋላ ለመቋረጥ ችለዋል…
የገንዘብ አሰራር ስርዓታቸውን በማስፋት እስከ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ድረስ......

~~~ ይቀጥላል ~~~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 የመጨረሻው ክፍል 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

የገንዘብ አሰራር ስርዓታቸውን በማስፋት እስከ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ድረስ በማስፋት በአሜሪካ የባቡር ሀዲድ ካምፓኒዎች ላይ ትልቅ የድርሻ ባለቤት ለመሆን በቅተዋል፡፡ ከአሜሪካ የሴኪዩሪቲ ሰርቲፊኬቶች እና ከፈረንሳይ እና ከቤልጄም ባለሀብቶች ጋር ከ25 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ መዋዕለ ንዋይ በስራ ላይ እንዲውል አድርገው ነበር፡፡
በጣም የሚያስገርመው የአቢሲኒያው ደብዛዛ ንጉስ በሁሉም ነገሮች ላይ ያላቸው ሁለገብ እውቀት ነው፡፡ በጣም ምጡቅ የቋንቋ ችሎታ የነበራቸው ሲሆኑ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛ እና ጣሊያንኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ለመንግስታዊ ስራቸው ሙሉ ጊዜ ሰጥተው የሚሰሩ ሲሆን በአውሮፓ የሚዘጋጁ ጽሁፎችንም የመከታተል ዕድል ስላላቸው እና በትኩረት ስለሚከታተሉ አዲስ መጽሀፍ በወጣ ቁጥር ስለደራሲው ሲጠየቅ አዲስ አይሆኑም፡፡ ባዲሳባ ቤተመንግስት በሰዎቻቸው በሚታወቁበት መጽሀፍትን በማሰባሰብ ስራቸው እውቅና እንዲሰጣቸው ሲባል በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ በተገኙበት ዕለት በቤተ መጻህፍታቸው ከ20 ሺህ ያላነሱ ጥራዞች መገኘታቸው ልዩ ኩራት እንዲሰማቸው አድርጓል፡፡ የምኒልክ መጻህፍትን የማሰባሰብ የትርፍ ጊዜ ስራ በጥንት የአፍሪካ እና የኢስያ ስልጣኔዎች ዘመንም የሚደረግ ነበር፡፡

በአጼ ምኒልክ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ከሚያደርጉት ወገኖች ጋር የማቀርበው መደራደርያ ፣

በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ስለማሰራጨት ጉዳይ የማቀርበው መደራደርያ አለኝ ፡

በአጼ ምኒልክ ስብዕና ላይ የምታደርጓቸውን ውሸቶችና ቅጥፈቶች የምታቆሙ ከሆነ እኔም ስለአቶ መለስ የምናገራቸውን እውነቶች መናገር አቆማለሁ!

°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°

~~~~ || ተፈፀመ || ~~~~

°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
መልካም ዕለተ ሰንበት!
🧞‍♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞‍♂

እራሴን እንዴት ልውደድ?
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ሴቶች በወንድ አንቀፅ የተፃፈውን በሴት አንቀፅ ለውጣችሁ አንብቡት !

💡🥀1. ሁልጊዜም ከእንቅልፍህ ስትነሳ መልካም ነገሮችን ስለራስህ አስብ። ተፈጥሮህን አድንቅ እራስህን በመስታወት እያየህ ስለተሰጠህ ነገር ሁሌም አመስግን። በህይወትህ ያለህን ችግር ሳይሆን የተቸረህን ነገር አንድ ሁለት እያልክ ቁጠራቸው። ያለፈውን ነገር እረስተህ ስለሚመጣው ብሩህ ነገር አስብ።

💡🥀2. እራስህን ከሌሎች ሰዎች ስኬት ጋር አታወዳድር። አንተ የራስህ የሆነ የህይወት መንገድ አለህ ሌላውም እንደዛው።

💡🥀3. ከዚህ በፊት ያላረካቸውን መንፈስህን የሚያድሱ ነገሮችን አድርግ። የእግር ጉዞ አድርግ፣ ለራስህ ስጦታ ግዛ፣ የምትኖርበትን አካባቢ ቃኘው፣ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ተሳተፍ በዛውም ሰዎችን እንዴት መርዳት እንዳለብህ ትማራለህ፣ ተፈጥሮን አድንቅ ጉዞዎችን አድርግ እነዚህ ቦታዎች ስትሔድም በፎቶ ምስል አስቀራቸው፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን ለመለማመድ ሞክር፣ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ለመለማመድና ለመማር ሞክር፣ ሙዜሞችን ጎብኝ የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን አድንቅ፣ ከዚህ በፊት ያላነበብካቸውን መፃህፍት አንብብ፣ መንፈስህን የሚያድሱ ሙዚቃዎችንም አድምጥ ወዘተ....።

💡🥀4. ሁሉንም ሰው ማስደሰት እንደማትችል መቀበል አለብህ። ሁልጊዜም የሚፈርዱብህ ስላንተ ጥሩ ስሜት የማይሰማቸው እንዲሁም ያለፍክበትን መንገድ እንኳን ያላወቁ ሰዎች ያጋጥሙሃልና።

💡🥀5. ለቤተሰቦችህና ለጓደኞችህ ጊዜ ስጥ። ሁልጊዜም አብረውህ የሚዘልቁት እነሱ ናቸውና። አጠገብህ ስላሉ ደስተኛ ሁን እንደምትወዳቸውም ንገራቸው።
@Readers_To_Know
💡🥀6. ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ዘወትር አድርግ። ይሄም ጭንቀትን ለመከላከል ይረዳሀል።

💡🥀7. በዚህ አለም ማንም ፍፁም የለምና ጉድለትህን ውደደው። ሁላችንም በፈጣሪያችን የተፈጠርን ውብ ፍጥረቶች ነን። ሁሉም ሰው ያጠፋልና ላጠፋሀቸው ጥፋቶችም ለራስህ ይቅርታን አትንፈገው።
@Readers_To_Know
💡🥀8. የአኗኗር ዘይቤህን ቀይር። አለባበስህን አስተካክል፣ የራስህ የሆነ ስታይል ይኑርህ፣ ፀጉርህን ተቆረጥ ተንከባከብ እራስህን አትጣል ፅዳትህን ጠብቅ፤ የምትኖርበትን ቦታ ፅዳት ጠብቅ እራስህን ለማነቃቃት አስፈላጊ ነው። ወጣ ብለህ ብዙ ሰዎችን የምትተዋወቅበትን መንገድ ፍጠር፤ ከነሱጋም ደስ የሚል ጊዜ አሳልፍ። ብዙ ከማውራት ብዙ ማዳመጥ ይበልጣልና አዳማጭ ሁን።

💡🥀9. ደስተኛ ለመሆን ሁሌም ሳቅ ከፊትህ ገጽታ አይለይ ሌሎች ሰዎችንም ደስተኛ ታደርጋቸዋለህ።

💡🥀10. ስላንተ ጥሩ ስሜት የማይሰማቸውንና ሁልጊዜም የሚያጣጥሉህን ላንተ ደንታ የሌላቸውን ሰዎች ከህይወትህ አስወጣ። ባንፃሩ ላንተ ጥሩ ስሜት ካላቸው ጋር አዘውትር።
@Readers_To_Know
💡🥀11. ብቻህን የተወሰነ ጊዜ አሳልፍ። ብቻ መሆን ያን ያህል ችግር እንደሌለው ተረድተህ አንዳንድ ቦታዎች ላይ እራስህን እንደ ግል ጓደኛ አድርገህ ብቻህን መንቀሳቀስን አዳብር።

💡🥀12. ለሌሎች ሰዎች ስሜት መጠንቀቅና መንከባከብ ጥሩ ስሜትን ይሰጥሀልና አዳብረው። ሰዎች ላይ አትፍረድ በተቻለህ መጠን ሰዎችን ላለማስቀየም መጣር እንዳለብህ አትርሳ። ለሌሎች መልካም ነገርን አድርግ መልካምነትህን አይተው እንዲጎዱህ ግን አትፍቀድላቸው። እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እርዳታህን አትንፈጋቸው መልሰው እንዲያደርጉልህ ግን ምላሽ ከማንም አትጠብቅ።

💡🥀13. ልብህን ጠብቀው።

💡🥀14. ስልክህ ላይ የምታጠፋውን ጊዜ ቀንስ። የስልክ አጠቃቀምክን አስተካክል።
@Readers_To_Know
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
" እራሱን የሚወድ ለሌላው ይተርፋል "
"We Have Two Lives, And The Second Begins When We Realize We Only Have One."
🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🦋የትናንቷ ፀሐይ አቃጠለችኝ ተብሎ የዛሬዋን ፀሐይ አልሞቅም አይባልም።🦋

@Readers_To_Know
🦋"መቼ እና የት መለያየታችን ስለማናቅ ደና እደሩ እንኳን ስንባባል ነገ መልሰን ያንን ሰው ላናይም እንደምንችል እያሰብን ፍቅር፣ ይቅርታ ሁልጊዜ ከኛ ጋር ይሁን!!!"🦋

@Readers_To_Know
እንኳን ለደብረ-ታቦር ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
@Readers_To_Know
😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣

ልጆች ለእግዚአብሔር ከጻፏቸው ደብዳቤዎች
°°°°°°°°°°°×××××××××××°°°°°°°°°°°°

የተወደድከው እግዚአብሔር ሆይ!! ጉንጭህን ስሞ በሰላሳ ብር አሳልፎ የሸጠህ ይሁዳ ምን አይነት ደደብ ሰው ቢሆን ነው? እንኳን አንተ የኛ ጌታ አይደለህም፤ እኛ ቤት ያለችው ሰራተኛችን እንኳን በወር ደሞዟ ሰማንያ ብር ነው።

የተወደድከው እግዚአብሔር ስሜ ጨቡዴ ነው፡ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ በስሜ ሁልጊዜ ያሾፉብኛል። ስለዚህ እኔ ስምን መልአክ ነው የሚያወጣው ሲባል ስለሰማሁ የኔን ስም ያወጣውን መልአክ አደራ ቅጣልኝ። ጨቡዴ ነኝ

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አባዬ ሁልጊዜ አሞኛል እያለ አልጋው ላይ ተኝቶ ያቃስታል፤ ታድያ አንዳንዴ ወደ ውጭ ወጣ ሲል መንገድ ላይ ያገኙት ጓደኞቹ "ደህና ነህ ወይ? " ብለው ሲጠይቁት ግን "እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ " ይላል አይገርምህም? እነሱንስ እሺ ይሸውድ! አንተን ግን እንዴት ይዋሽሀል?

ምንጭ፦ እስኪ ዛሬ እንኳን እንሳቅ በቅዱስ-ሀብት በላቸው

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🧞‍♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞‍♂

🦈. ሻርክ ከ 1k.m ላይ የፈሰሰን ደም ማሽተት ይችላል።🐳 አንድ ሻርክ ትልቅ ለመባል ከ20-25 አመት ይፈጅበታል። ይህም የሚያሳየን ዘገምተኛ የእድገት ደረጃ እንዳለው ነው። ሻርክ 856 ጥርስ ሲኖረው አንዱ ከተሰበረ በሌላ ይተካል፤ እንዲሁም የ10 አመት ሻርክ 2400 ጥርሶችን ነቅሎ ይተካል። ሻርክ በሁለት መንገዶች ይራባል። በውልደትና በእንቁላል🥚መራባት ይችላል።

👼. በአለም በ1 ሰከንድ 4 ልጆች ይወለዳሉ ተብሎ ይገመታል።

🏅. በአፍሪካ ውስጥ የመጀመሪያው የኖቤል ፕራይዝ ተሸላሚ አልበርት ሉቱሊ ይባላል።

💆‍♂💆‍♀. አባባል:- ትንሽ ቆሎ ይዘህ ካሻሮ ተጠጋ።

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
​​🦅🖊 ስነግጥም 🖌🦅
______
___
የሕፃኗ ብሶት😢😥
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በጣም የምቀርበው በጣም የምወደው፤
ከጎረቤት አለ ሁሌም 'ማልለየው።
ሕፃን ስለሆንኩኝ ጣፋጭ እወዳለሁ፤
ሁሌም ጎረቤቴን አስቸግረዋለሁ።
እሱም እየሳቀ ብስኩት ከረሜላ፤
ጣፋጭ ነገሮችን ሰቶኝ እንድበላ።
"ነይ ግቢ" አለኝ ገርበብ አረገና፤
"እሺ" አልኩኝ እኔም ደስ አለኝና።
ከረሜላዬንም ቆረጣጠምኩና፤
መጫወት ጀመርኩኝ በንፁሕ ልቦና።
"ነይ እስኪ ሚጢዬ" ደግሞ ለስለስ ብሎ፤
ወደ መኝታ ቤት ይዞኝ ዘው ብሎ።
ካ'ልጋው ተቀምጦ ትንሽ አወጋና፤
ፈገግ ብሎ አየኝ ምኑ ገባኝና።
አልጋው ላይ ወጣና "ነይ እስኪ እንተኛ" ፤
ምኑ ባለጌ ነው አልኩኝ ነውረኛ።
ተረት ላውራሽ አይዞሽ አትፍሪ እያለ፤
እየጎተተ አስጠጋኝ እያታለለ።
ስላላማረኝ ኮስተርተር አልኩኝ፤
ከ'ጁ ልወጣ ብዙ ታገልኩኝ።
በየትኛው አቅሜ ልርታው ተፋልሜ፤
ጭምድምድ ሲያረገኝ ወደኩኝ ታምሜ።
ያ! የሚያስቀኝ ልጅ ደጉ ጎረቤቴ፤
ለካስ ጨካኝ ነው አልኩኝ ከአንጀቴ።
አበባዬ ረግፎ ቅስሜ ተሰባብሮ፤
ለእማዬ ነገርኳት የሆዴንን እሮሮ።
ኋላ የጠበቀኝ ዱላና ቁጣነው፤
እኔ ምን አውቃለሁ ያጠፋው እሱ ነው።
ወላጆች አድምጡን ጆሮአችሁን ስጡን፤
እናንተ ጠብቁን በግልጽ አወያዩን።
ፍርድ ቤትም ይከላከለን፤
ዋስ እየሰጠ አያስጠቃን።
እግዜር በጥበቡ ይጠብቀን እንጂ፤
እኛ ሕፃናት ነን በቶሎ ተጎጂ።
ምንጭ፦ ከየ ሕፃናት ድምፅ ቅፅ 7 ቁጥር 2 የተወሰደ ሕዳር-29-2003

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🧞‍♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞‍♂

🧠. የአልበርት አንስታይን ጭንቅላት ህዋስ ለእያንዳንዳችን ይድረስ ከተባለ 107 አንድ ሰው ይደርሰዋል አሉ። እና እኛ ምን አገባን 😂😂😂

🐈. ድመቶች ለ16 ሠዓታት ይተኛሉ።

🧠. ምነው ዛሬ አንጎል አንጎል አላቹ አትበሉንና የአንጎል ህዋሳት አንዱ ጥምረት ብቻ ቢዘረጋ 1,000 k.m ይሆናል።

🕯. አባባል:- የደንቆሮ ድንቁርና ብልህ ለመሆን ሲሞክር ይገለፃል።

🤷‍♂🤷‍♀. የሰው ሁለቱ የፊቶቹ ጎኖች አይመሳሰሉም። አይኖቹም👀 በፍፁም አይመሳሰሉም። አስገራሚው ነገር ደግሞ የቀኝ ጆሮዋችን👂 ከግራ ጆሮዋችን ወደላይ ተቀምጦ ይገኛል።

እናመሠግናለን

@DExtra_l @Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°° °°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🎥📻 ከታሪክ_ማህደር 🎙🎞

በመጀመሪያ ከሰብታህ ጀምሮ እስከ ጲኦሪ አንደኛ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ፳፭፻፵፭(2545) እስከ ፲፱፻፹፭(1985) ዓመት ከነገደ ካም በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፳፪(22) ናቸው፤ ዘመኑም ፭፻፷(560) ይሆናል። ከክርስቶስ ልደት በፊት ነገደ ዮቅጣን መንገሥ ከጀመሩበት ፲፱፻፹፭(1985) ዓመት ጀምሮ ቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ነገሡበት እስከ ፱፻፹፪(982) ዓመት አግዓዝያን ከተባሉ ከነገደ ዮቅጣን በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፶፪(52) ናቸው። ዘመኑም ፩(1) ሺህ ፫(3) ዓመት ይሆናል።
ከክርስቶስ ልደት በፊት ቀዳማዊ ምኒልክ ከነገሡበት ከ፱፻፹፪(982) ዓመት ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ተወለደበት እስከ ፩(1) ዓመተ ምሕረት እስከ ባዚን በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፷፯(67) ናቸው። ዘመኑም ፱፻፹፪(982) ይሆናል። ነገር ግን ባዚን ከክርስቶስም ልደት በኋላ ፱(9) ዓመት ነግስዋልና ይህ ሲጨመር ፱፻፺፩(991) ይሆናል። ከባዚን ጀምሮ የቀዳማዊ ምኒልክ መንግሥት ወደ ነገደ ዛጔ እስከ ፈለሰበት እስከ ድልናዖድ ድረስ ከ፩(1) እስከ ፱፻፲፪(912) ዓመተ ምሕረት በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፺፬(94) ናቸው። ነገር ግን ባዚን ሁለት ጊዜ ያልተቆጠረ እንደ ሆነ ፺፫(93) ይሆናል። ዘመኑም ፱፻፲፪ (፱፻፳)➾912(920) ዓመት ይሆናል። ክርስትና በኢትዮጵያ የገባው በነዚሁ ዓመታት ውስጥ ከ፪፻፺፰(298) እስከ ፫፻፳፬(324) ዓ.ም. በ አብርሃ ና አጽብሓ ዘመን ነው።
ከድልናዖድ በኋላ ከመራ ተክለ ሃይማኖት (ስመ መንግሥታቸው ዛጔ) ጀምሮ እስከ ይትባረክ በኢትዮጵያ ነገሡ የዛጔ ወገኖች ፲፩(11) ነገሥታት ናቸው። ዘመኑም ፫፻፴፫(333) ዓመት ይሆናል። የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይል ወደ ዛጔ ዘር ካለፈ በኋላ በ፫፻፴፫(333) ዓመት እንደ ገና
ወደ ቀዳማዊው ምኒልክ ዘር ወደ ይኩኖ አምላክ ከተመለሰበት ከ፲፪፻፵፭ (፲፪፻፶፫)➾1245(1253) ዓ.ም. ጀምሮ የጎንደር መንግሥት እስከሚባለው ሠርፀ ድንግል እስከ ነገሡበት እስከ ፲፭፻፶፫(1553) ዓ.ም. በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፳፮(26) ናቸው፤ ዘመኑም ፫፻፩(301) ዓመት ይሆናል።
ሠርፀ ድንግል ከነገሠበት ከ፲፭፻፶፫(1553) እስከ ፲፯፻፸፯(1777) ዓ.ም.
የጎንደር መንግሥት መጨረሻ እስከ ተክለ ጊዮርጊስ ፤ በጎንደር ቤተ መንግሥት ሆነው ኢትዮጵያን የገዙ ነገሥታት ፲፰(18) ናቸው። ዘመኑም ፪፻፹፬(284) ዓመት ይሆናል።
የጎንደር መንግሥት የሚባለው ከተጨረሰበት ከ፲፯፻፸፯(1777) ዓ.ም. ጀምሮ ዓፄ ቴዎድሮስ እስከ ነገሡበት እስከ ፲፰፻፵፭(1845) የገዙ መሳፍንት ፲፱(19) ናቸው። በነዚህም
መሳፍንት ዘመን ሙሉ ሥልጣን ሳያገኙ ለስሙ ብቻ ዘውድ እየጫኑ በጎንደር ቤተ መንግሥት ይቀመጡ የነበሩ ትውልዳቸው ከቀዳማዊ ምኒልክ ወገን የሆኑ
ነገሥታት ፲፬(14) ናቸው። ዘመነ መሳፍንት ካለፈ በኋላ ከ፲፰፻፵፭(1845) እስከ ፲፰፻፹፩(1881) በኃይልና በጉልበት የነገሡ የኢትዮጵያ ነገሥታት ፫(3) ናቸው። ዘመኑም ፴፮(36) ዓመት ይሆናል። የሸዋ መንግሥት ባላባቶች ፲፭(15) ናቸው። የግዛታቸውም ዘመን ፪፻፸(270) ዓመት ይሆናል።

እናመሠግናለን

@Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°°°°°
✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
💫🌪 ጥቆማ 🌪💫

በአንድ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህሯ ተማሪወቿን አንድ Assignment መስጠት
ፈለገች..!! ተማሪወቿን ድንች ይዘዉ እንዲመጡ አዘዘች፡፡
ድንቾቹ ላይም የሚጠሏቸዉን ሰወች ስም እንዲፅፉ አዘዘቻቸዉ..
የሚያመጡት የድንች ብዛትም በሚጠሏቸዉ ሰወች ብዛት
ልክ እንዲሆን አለች፡፡ በሁለተኛዉ ቀን አንዳንዶቹ 3፡ ሌሎች 5 ቀሪወቹ ደግሞ 8 ድንቾቹን የሚጠሏቸዉን ሰወች ስም ፅፈዉ አመጡ..መምሯ ደግሞ <<ከዛሬ
ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እኒህን ድንቾች በሻንጣችሁ ይዛችሁ ትዞራላችሁ...ሽንት ቤት ስትሄዱ እንኳ መተዉ
አትችሉም!>> ብላ አዘዘች
.
ቀኑ እየጨመረ ሲሄድ ድንቹ በመበላሸቱ ሽታዉ ይረብሻቸዉ ስለጀመረ ተማሪዎቹ ቅሬታ ማቅረብ ጀመሩ..በተለይም 8 የያዙት ከሽታው በተጨማሪ ክብደቱ
እንደበዛባቸው መናገር ጀመሩ፡፡
.
ከሳምንት በኋላ የአሳይመንቱ ገደብ ስላበቃ ተማሪወች ድንቹን አዉጥተዉ እንዲጥሉ ተፈቀደላቸዉ::
ከዛም መምህሯ<<እህ እንዴት ነበር?>> ብላ ጠየቀቻቸዉ...ሁሉም ማጉረምረም ጀመሩ ..."አረረረ ከክብደቱ ሽታዉ...አረ በጣም ነዉ የሚያስጠላዉ"...አሉ
.
.
መምህሯ<<አያችሁ በልባችሁ የምትሸከሙት ጥላቻም እንዲሁ ነዉ...ጥላቻ ልብን ይመርዛል.. በምትሄዱበት ሁሉም እየተከተለ ይረብሻችኋል...ለአንድ ሳምንት የተበላሸ
ድንችን ሽታ መቋቋም አልቻላችሁም..አስቡት ደሞ በጥላቻ የተመረዘን ልብ እድሜ ልካችሁን ይዛችሁ ስትኖሩ!!>> አለቻቸዉ
.
.
ጥላቻን ከዉስጣችሁ አዉጡት..ና ከእዳ የፀዳችሁ ሁኑ!! እዉነተኛ ፍቅር እንከን አልባን ሰዉ ማፍቀር ሳይሆን ንፁህ
ያልሆነን ሰዉ በንፁህነት መዉደድ ነዉና!!!

❤️❤️አዲሱን ዓመት ጥላቻን አስወግደን በፍቅርና በይቅርታ እንቀበለው❤️❤️

🌼፳፻፲፫🌼

እናመሠግናለን

@Feed_it_bot
°°°°°°°°°°°°°°°°°

✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
📆 ጷግሜን 📆

Re~Post

የጳጒሜን 5፤ 6 እና 7 አመጣጧ
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

📚 ጳጒሜን የተባለችው 13ኛዋ ወር በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ስትባል ሊቃውንት ተረፍ ይሏታል፡፡ የ5 ቀናትን የጳጉሜንን አመጣጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጠንቅቀው ቀምረው በባሕረ ሐሳብ ብራናቸው ላይ ጽፈውልናል፡፡

📚 ይኸውም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ያሉት 12ቱ ወራት ያላቸው ዕለታት በአጠቃላይ 360 ናቸው፡፡ በቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጥልቅ ትንተና 1 ዕለት የሚባለው 24 ሰዓት ከ52 ካልዒት ከ31 ሳልሲት ነው፡፡

📚 1 ካልዒት ማለት 24 ሰከንድ ሲኾን 52 ካልዒት ማለት 1248 ሰከንድ ነው፤ 31 ሣልሲት ማለት 12.4 ሰከንድ (ቅጽበት) ይኾናል፡፡ በመኾኑም በአንድ ቀን ውስጥ 1 ደቂቃ ከ0.4 ሰከንድ ትርፍ መኖሩን ያስረዳል፡፡

📚 በመኾኑም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ባሉት 360 ቀናት ያሉትን 52 ካልዒት ወይም 1248 ሰከንድ እንዲኽ እናባዛቸዋለን፤ 52 ካልዒት X 360 ዕለታት= 18720 ካልዒት ወይም (449, 280 ሰከንድ) ይኾናል፤ ወደ ደቂቃ ስንለውጠው 7488 ደቂቃ ወይም 5 ዕለት ይኾናልና የጳጒሜን አመጣጥ ይቺ ናት፡፡

☞☞ የጳጉሜን 5 ምስጢር

📚 አራቱ የዓመት ወቅቶች ማለትም መፀው፣ ሐጋይ፣ ጸደይና ክረምት 91, 91 ቀናት የሚኾኑት ከጳጒሜን 1 አንድ ዕለት እየተሰጣቸው ሲኾን በአጠቃላይ 364 ዕለታት ወይም 52 ሳምንት ኾኖ አንዲት ዕለት ትተርፋለች፤ ይቺም ጳጒሜን 5 ስትኾን በኢትዮጵያ ቀደምት የዘመን ቀመር ሊቃውንት “ዕለተ ምርያ፣ አዕዋዲት” ትባላለች፡፡

📚 ዕለተ ምርያ ማለት ዕለተ መድኀኒት ማለት ነው፤ ምክንያቱም ጳጒሜን 5 የመድኀኒታችን ክርስቶስ ልደትን የምናውቅባት ስለኾነች ነው፤ ይኸውም ጳጒሜን 5 በዋለችበት ዕለት የክርስቶስ ልደት ዕለት በተመሳሳይ መልኩ ይውላል፡፡

📚 ለምሳሌ የዚኽ ዘመን ጳጉሜን 5 ዕለት ሐሙስ ናት፤ በተመሳሳይ መልኩ የ2013 የጌታችን የልደት በዓል ታኅሣሥ 29 ሐሙስ ላይ ይውላል፡፡ በዚህ ምክንያት ዕለተ ምርያ የሚል ሥያሜ ሊሰጣት ችሏል፡፡

📚 በተጨማሪም ጳጒሜን 5 የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የዐዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደኾነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ በመኾኑ ዕለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ መዋሉ በእጅጉ ይደንቃል።

☞☞ ጳጉሜን 6 እና አመጣጧ

📚 የ6ተኛዋ ጳጒሜን አመጣጥን ስናይ፡- በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ስሌት 1 ዓመት የምንለው 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው፡፡ ይህን የየዓመቱን 6 ሰዓት ስንቈጥር የኹለት ዓመት 12 ሰዓት፤ የሦስት ዓመት 18 ሰዓት፤ የአራተኛው ዓመት 24 ሰዓት ወይም አንድ ዕለት ሲሆን ይኸውም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መጀመሪያ ሲኾን ይኸውም በቀደምት የአቡሻክር ሊቃውንት “መጠነ ራብዒት፣ ሠግረ ዮሐንስ” ትባላለች። ዘመነ ዮሐንስ ተራምዶ የሚያልፍባት ለማለት ነው፡፡

📚 እኛ ጳጒሜን 6 ስናደርግ ምዕራባውያኑ ግን የጳጒሜን ወራትን በማጥፋታቸው ኹሌ ለእነርሱ 28 የኾነችው የካቲትን በአራት ዓመት አንዴ 29 ያደርጋሉ፤ Leap Year ብለው ይጠሯታል።

☞☞ ጳጒሜን 7 እና አመጣጧ

📚 የኢትዮጵያን ቀደምት ሊቃውንትን በእጅጉ እንድናደንቅ ከሚያደርገን አንዱ የጳጒሜን 7ትን ስሌት ጠንቅቀው አስልተው በብራና የአቡሻክር መጽሐፍ ላይ ጽፈውልን ስሌቱን አስልተው ማለፋቸው ሲኾን፤ የስሌቱም መጠሪያ “ዕሪና መዓልት ዕሪና ሌሊት” በመባል ይታወቃል፡፡

📚 ይኸውም 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ የኾነው የፀሓይ ዐውደ ዓመት የ6 ካልዒት ወይም የ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ጥርቅም ወይም ከላይ ያየናት የአንዷ ዕለት 0.4 ሰከንድ ጥርቅም ነው፡፡

📚 ስናሰላውም የ5 ዓመቱ 30 ካልዒት፤ የ10ሩ ዓመት 60 ካልዒት (1 ኬክሮስ ወይም 24 ደቂቃ) ይሆናል፡፡ የ100 ዓመት (10 ኬክሮስ) ወይም 240 ደቂቃ (4 ሰዓት) ይኾናል፡፡ የ200 ዓመት 20፤ የ300 ዓመት 30፤ የ400 ዓመት 40 ኬክሮስ፤ የ500 ዓመት 50 ኬክሮስ፤ የ600 ዓመት 60 ኬክሮስ ሲሆን 60 ኬክሮስ ማለት 1440 ደቂቃ ወይም 24 ሰዓት ወይም 7 ተኛዪቱ ጳጉሜን ናት፡፡

📚 ሆኖም ግን የአቡሻሕርና የባሕረ ሐሳብ መምህራን ጳጕሜን 7 የተገኘችው ከጥቃቅን መስፈርት ወገን ከሆነችው ከካልዒት በመሆኑ ሒሳቧ ብቻ ታስባ ድቁቅ ደቃይቅ ተብላ ብቻ እንድትተው በማዘዝ ዕለቷ ግን በኅሊና ብቻ እንድትታሰብ እንጂ ተቆጥራ እንዳትከበር አዘዋል፡፡ በመሆኑም በማሰብ ብቻ እንጂ በዕለትነት ተቆጥራ አትውልም፡፡

📚 በአቡሻሕሩ ስሌት መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ 12 ዕሪና መዓልት 12 ዕሪና ሌሊት (ጳጉሜን 7) ተመላልሶ በ1700 ዓ.ም. ወይም በ7800 ዓመተ ዓለም ኾኖ 13ኛው ከተጀመረ 311 ሆኖ በዘመነ ሉቃስ ይኸው ሊፈጸም በ2011 ዓ.ም ካሰላነው 289 ዓመት ይቀራል ወይም በ2300 ዓ.ም. ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡

📚 ይህ በሚሆን ጊዜ ዐቀድ የሚባል ኮከብ አለ፤ ሰሌዳው በፀሓይ ልክ፤ ባሕርዩ ጽሉም ነው፤ ርሱ በ600 ዓመት መጥቶ ፀሓይን ይጋርዳታል፤ ያን ጊዜ ሌሊቱና መዓልቱ ጨለማ ኹኖ ይውላል ያድራል፤ ይኸውም የመከራ ፊት አውራሪ አጫሪ ነው፤ ይኸውም በዐጤ ኢያሱ ወይም ፀሓይ ሰገድ በተባለ በዐጤ ዮስጦስ ጊዜ ተደርጓል ብለው መዝገብውልናል፡፡ ይህን ስናይ የቀደምት ኢትዮጵያውያንን ዕውቀት ሁሌም እንድናደንቅ ያደርገናል፤ መልካም የጳጉሜን 13ኛ ወራት ይሁንልን፡፡
ይቆየን!
🌼
ለመጪው ዘመን ከቁጥር ሳንጎድል በሰላም በፍቅር ያድርሰን!

እናመሠግናለን
#Coททεcт WiтhUs 👣 @Feed_it_bot

┈┈┈••✦✦••┈┈┈
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣

እንደምን አላችሁልኝ! የአመት በዓል ሽር ጉዱ እንዴት አርጎአችኋል? ወንዶች ስራውን ሁሉ እናንተ ላይ ጥለው ሴቶች ፈታ እያሉ እንደሆነ ቅሬታ እያቀረባችሁልኝ ነው😜😂
ተዉ እንጂ ሴቶች ባይሆን በግ ማረዱን እንኳን አግዙአቸው እንጂ! ሴትነቱስ ለመቼ ነው!
በዓሉን በጾም ለምናሳልፍ ደግሞ ቅዳሜ እንገናኝ ተባብለናል ..... የሆነ ሰው ምን አለኝ መሰላችሁ "ነገ በቃ ጾም ስለሆነ ለምን ተኝተን ሲነጋ ቅዳሜ ተነስተን አናከብርም አለኝ" አብሮን የነበረው ጓደኛዬም ምን ቢለው ጥሩ ነው "እንዴ ሌሎቹ ሲበሉ ማን ሊያይልህ ነው" አላለውም፤ ለነገሩ ልክ ነው ትን ቢላቸውስ 😂 ... ለማንኛውም 😂🎩 ለፈገግታ 🎩🤣 ነበር መልካም አመት በዓል ተመኝቻለሁ! በአዲሱ አመት ከቻናላችን ጋር ጥሩ ጊዜ እናሳልፋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ!

🌼 መልካም በዓል 🌼
@Readers_To_Know
🗓 የዘመን አቆጣጠር በኢትዮጵያ 🗓

Re~Post

ዘመን የሚለካው የጸሐይንና ጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት አድርጎ ዕለት፣ ወር እና ዓመት በሚል መስፈሪያ ተጠራቅሞ ነው::
ዕለት ፦ አንድ ዕለት ማለት አንድ የብርሃን እና አንድ የጨለማ ክፍለ ጊዜ ያለው ሲሆን ጸሐይ አንድ ግዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ
የያዘ ነው:: በሌላ አባባል ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ ያምትሽከረከርበት ጊዜ ነው::
ወር ፦ አንድ ወር ማለት ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ ሙሉ ሆና እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው:: ይህም ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዞራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 29.5 ዕለታት ማለት ነው::
ዓመት፦ አንድ ዓመት ማለት መሬት በጸሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ሲሆን 365 ዕለታት ከሩብ ያህል ነው::
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርም እነዚህን መስፈሪያዎች በመጠቀም 30 ዕለታት ያሉዋቸው 12 ወራት (መስከረም፣ ጥቅምት፣ ህዳር፣ ታህሳስ፣ ጥር፣ የካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዚያ፣ ግንቦት፣ ሰኔ፣ ሐምሌ እን ነሐሴ) እና 5 (በየ4 ዓመታት ደግሞ 6) ዕለታት ያሏት 13ኛ ወር (ጷግሜን) ዑደት ይጠቀማል:: ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የ13 ወር ባለቤት የምትባለው::
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሃይማኖታዊ ይዘት ሲኖረው መነሻ የሚያደርገውም የክርስቶስን ልደት ነው:: ዘመናቱም በሐዋርያት ተሰይመው በአራት መደባት ይዞራሉ፤ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ(ጷግሜን 6 ዕለታት የሚሆንበት) እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው:: አዲስ ዘመን የሚጀምረውም መስከረም 1 ነው::
ምንጭ – መስከረም 2004 አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌻፳፻፲፫🌻
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ
ማቴዎስ በሰላም አደረሳችሁ
አደረሰን!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እናመሠግናለን
#Coททεcт WiтhUs 👣 @Feed_it_bot

┈┈┈••✦✦••┈┈┈
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀
🧞‍♂👣 ከዚምከዛም 👣🧞‍♂

🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼
ብዙ ጊዜ ከዘመነ እገሌ ወደ ዘመነ እገሌ በሰላም አደረሳችሁ ሲባል ሰምታችሁ ይሆናል። ይሕ በአራቱ ወንጌላት የሚሰየመው ዘመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተጀመረና በስፋት የሚነገር ነው። የዘመኑ ስያሜ የትኛው ወንጌላዊ እንደሆነ የምናውቅበት ቀላል ቀመርን ይዤላችሁ መጥቻለሁ። የዘንድሮው ማለትም የ2013 ዘመን ለየቱ ወንጌላዊ እንደተሰጠ በምሳሌ መልክ አቅርቤላችኋለው፤ ለሌላው ዘመንም ቀመሩ እንደዛው አመቱን በመቀየር ብቻ አስልቶ ማወቅ ይቻላል።
🦋
ዓመተ-ዓለም =
ዓመተ-ኩነኔ(ፍዳ) + ዓመተ-ምህረት

ዓመተ-ዓለም = 5500 + 2013
ዓመተ-ዓለም= 7513
👣
ዓመተ-ዓለም ÷ 4 = መጠነ-ራብዒት
7513 ÷ 4 = 1878
4

35
32
31
28

33
32
1 ◅◄ ቀሪ
ቀሪው '0' ወይም '4' ከሆነ ዘመነ-ዮሐንስ
ቀሪው '1' ከሆነ ዘመነ-ማቴዎስ
ቀሪው '2' ከሆነ ዘመነ-ማርቆስ
ቀሪው '3' ከሆነ ዘመነ-ሉቃስ
በዚህም መሠረት በ2013 ዘመነ ማቴዎስ ይባላል ማለት ነው።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
አመት በዓሉ ወይም መስከረም አንድ መቼ ቀን እንደሚውል ወይም መባቻው ምን ዕለት እንደሆነ አስቀድማችሁ ለማወቅም የሚከተለውን ቀመር ተመልከቱ።
🦋 መባቻ = ዓመተ-ዓለም + መጠነ-ራብዒት ÷ 7
= 7513 +1878 ÷ 7
= 9391 ÷ 7
= 1341 ቀሪ '4'
ቀሪው '0' ከሆነ ሰኞ
ቀሪው '1' ከሆነ ማግስተ-ሰኞ
ቀሪው '2' ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው '3' ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው '4' ከሆነ አርብ
ቀሪው '5' ከሆነ ቅዳሜ በመግደፍ
ቀሪው '6' ከሆነ እሑድ መባቻ ይሆናል።
👣
በዚህም መሠረት 2013 መስከረም አንድ አርብ ቀን ይውላል።

እስቲ እናንተ ደግሞ የ2016 ዓ.ምን ዘመኑን እና መባቻውን አስልታችሁ በ
@Feed_it_bot ላኩልኝ። ቀድሞ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ላሳየኝ ሽልማት🎁🎉 አዘጋጅቻለሁ!

እናመሠግናለን
#Coททεcт WiтhUs 👣 @Feed_it_bot

┈┈┈••✦✦••┈┈┈
@Readers_To_Know
❀꧁✤┈┈┈••✦✦••┈┈┈✤꧂❀